Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
NOW

በ FM 97.1 እንግዶች ነን አድምጡን🙏

@etconp
👍21🙏5👌2
Live stream finished (31 minutes)
Forwarded from Ethio Construction Engineering (जॉर्डनो ג׳ורדנו ጆርዳኖ جوردانو จอร์แดโน่ JORDANO Ιορδάνοςஜார்டானோ)
Let’s discuss about MESOB tower

ምስሉ ላይ የተቀመጡ ጥያቄዎችን እንወያይበት በ discussion group @cotmp

እንደኔ እንደኔ ግን ይህ ህንፃ design stage’ኡን እንደጨረሰ contract ለሀገር ውስጥ ኮንትራክተሮች በ JOINT-VENTURE መስጠት እና quality የውጭ ሀገር consultantኦች ቁጥጥር ቢያረጉ

፩. የሀገር በቀል ኮንትራክተሮች ልምድ ይካብታል

፪. ኮንትራክተሮቻችን በ አለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ በመሆን ነገ የውጭ ምንዛሪ ያስገኙልናል

፫. የውጭ ምንዛሬ እናተርፍበታለን

ይህን በተመለከተ መንግስት አስፈላጊውን equipment እንዲያሟሉ ለሀገር በቀል ተቋራጮች ከማመቻቸት በተጨማሪ ብድር ቢመቻች ባይ ነኝ በግሌ።

JORDANO’s point of view

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Youtube YouTube:- https://youtu.be/qIpy-LMQ8QE

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=
👍20❤3👌2
ጥያቄ፦ የሥራ ማስጀመሪያ ክፍያ (advance
payment) ከእያንዳንዲ የሥራ ተቋራጩ
ክፍያ (Interim Payment) ላይ የሚቀነስ ሲሆን ጠቃላላ ክፍያው ተቀንሶ መጠናቀቅ ያለበት የፕሮጀክቱ ዋጋ ስንት ፐርሰንት እስኪደርስ ድረስ ነው? @ETCONp 😇
Anonymous Quiz
15%
50%
15%
65%
50%
90%
20%
100%
👍18❤4
Ethio Construction Engineering
👉ሰላም ጤና ይስጥልን!

🚧ቅድመ ክፍያ

🌟የሥራ ማስጀመሪያ ቅድመ ክፍያ (Advance payment) አሠሪው የጊዜው ለተቋራጩ ከሚከፍለው ክፍያ (Interim payment) ላይ እየተቀነሰ  ለባለቤቱ የሚመለስ ሲሆን በ'FIDIC Article 14.2(b)  መሰረት የፕሮጀክቱ ባለቤት የሥራ ማስጀመሪያ ብሎ ለተቋራጩ የለቀቀለት ቅድመ ክፍያ ሙሉ ለሙሉ ተቀንሶ መጠናቀቅ ያለበት ለፕሮጀክቱ ግንባታ የተያዘው ዋጋ ቢበዛ ዘጠና በመቶ  (90%) ሥራ ላይ አስከሚውል ድረስ ነው።

🖱ያ ማለት የፕሮጀክቱ በጀት 90% ከማለፉ በፊት ቅድመ ክፍያ የተለቀቀው ገንዘብ ከእያንዳንዱ ለተቋራጩ መከፈል ካለበት ክፍያዎች ላይ ተቀንሶ መጠናቀቅ አለበት።

☄ስለምትከታተሉን እናመሰግናለን🙏

🫵ለ YOUTUBE ቻናላችን አዲስ ከሆኑ SUBSCRIBE በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ እንዲሁም ለወዳጅዎ ያጋሩ🙏👇

https://www.youtube.com/@ETHIOCONp

@etconp
🙏20👍7❤3🏆1
የእግረኛ ድልድይ ጉዳት

አራት ኪሎ የሚገኘው የእግረኞች መሸጋገሪያ ድልድይ ጉዳት ደረሰበት


አራት ኪሎ ዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠገብ የሚገኘው የእግረኞች መሸጋገሪያ ድልድይ ጉዳት ደርሶበታል፡፡

አደጋውን ተከትሎም ከአምሥት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ እና ከአራት ኪሎ ወደ አምሥት ኪሎ ያለው መስመር ዝግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ተሽከርካሪዎችም አደባባይ ሳይደርሱ ተለዋጭ መንገድ እንዲጠቀሙ እየተደረገ ነው፡፡

ጉዳት የደረሰበትን ድልድይ ለማንሳት ጥረት እየተደረገ ሲሆን÷ ለጊዜውም የትራፊክ እንቅስቃሴው በተለዋጭ መንገድ እየተከናወነ ነው፡፡

የጉዳቱ ምክንያት እስካሁን ባይገለጽም አሁን ላይ ጥገና እየተደረገለት ይገኛል ተብሏል፡፡

Via Ethio Fm

@etconp
👍4❤3
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
👍3
👉የዛሬው ክፍል፦ ምክር ነው

🌟የኮንስትራክሽን ሠራተኛ (አርክቴክት፣ መሐንዲስ፣ ሙያተኛ) በሙሉ ሁለተኛ ፈጣሪ ነው፣ የከበረ ሙያ፣ የጥበብ ቁንጮ ነው። በተሰማራንበት ፕሮጀክት ሁሉ የሚያስከብር ንግግር፣ የሚያሳምን ሀሳብ፣ ምክንያታዊ የሆነ መልስ መስጠት አለብን።

⏺ምንም ነገር ከመሥራታችን በፊት ማሰብ፣ መለካት፣ ደጋግሞ ለራስ ማዳመጥ፣ ትክክለኛ መሆናችንን በማስረጃ ማመን፣ ... እነዚህን ካለፍን በኋላ ለሌሎች ማስተላለፍ ወይም በሥራው ላይ የተግባር ውሳኔ ማስተላለፍ አለብን።

▶️የግንባታ ሠራተኛ የሚያስተውል፣ የተረጋጋ፣ የሚያውቅ፣ የሚያሳምን፣ የማይጮህ፣ የሚለካ ደርባባ መሆን ይገባዋል።

🫵ስለኮንስትራክሽን ሕግ እና አንዳንድ የሥራ ሂደቶች ጠቃሚ መረጃዎች በ Youtube ገፃችን ማድረስ እንጀምራለን

☄ስለምትከታተሉን እናመሰግናለን🙏

🫵ለ YOUTUBE ቻናላችን አዲስ ከሆኑ SUBSCRIBE በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ እንዲሁም ለወዳጅዎ ያጋሩ🙏👇

https://www.youtube.com/@ETHIOCONp

@etconp
👍36❤7👌3💯3🙏2
👉Open Vacancy

🚧Company: Kabana Trading PLC

⏺Position: Site Engineer

📍Place of work: Project (Addis Ababa)

🖱Job Type: Permanent

🌟Requirement: BSc Degree in Civil Engineering, COTM or in a related field with relevant work experience

▶️Relevant Experience: 5 year & above specially on Building construction

⏺Quantity Required: 2

⚡️Deadline: March 08, 2024 (11:00 Local Time)

🫵How to Apply: Interested applicants should bring their application letter along with a non- returnable CVs and Copies of credentials documents in person to Kabana Trading PLC Head office around 22 Adey Ababa Stadium behind Foziya Building, Yoki Building 3rd Floor Office No. 304., Tel No. +251 11 822 82 29.

☄ስለምትከታተሉን እናመሰግናለን🙏

🫶የ ስራ እና ጨረታዎች በ ትኩሱ እንዲደርስዎ ይህ ቴግራም ቻናላችን ይቀላቀሉን

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBot መልእክት ኣሰቀምጡልን😍

https://t.me/ETCONpWORK
👍10
The symbol for shear stress is_____
Anonymous Quiz
32%
Δ delta
37%
Tau
2%
Kilogram
29%
gamma γ
👍9🙏4👌1🕊1
የታላቁ የህዳሴ ግድብ 95 በመቶ ተጠናቋል

የታላቁ የህዳሴ ግድብ በመላው ኢትዮጵያውያን ተሳትፎና በመንግስት ቁርጠኝነት 95 በመቶ መድረሱንና ወደ ማገባደጃው መቃረቡ ተገለፀ፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበርያ ፕሮጀክት ፅ/ቤት የግድቡ የግንባታ መሰረተ ድንጋይ የተቀመጠበትን 13ኛ አመት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ፅሕፈት ቤቱ በመግለጫው የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ 95 በመቶ መድረሱን ጠቁመው 13ኛ አመቱን ታሳቢ ያደረገ መርሀ ግብር በተለያዩ ሁነቶች ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጿል፡፡

በዚህም በ”ህብረት ችለናል” በሚል መሪ ቃል በቦንድ ሽያጭ፣ በንቅናቄ፣ በፓናል ውይይቶች ባሉ ዝግጅቶች ነው ይከበራል የተባለው፡፡ እስካሁን ለተደረገው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ላደረጉ አካላት የእውቅናና የምስጋና መርሀ ግብርም ይካሄዳል ተብሏል፡፡

በሁነቱ ለህብረተሰቡ በቂ መረጃዎችን በመስጠት ከዚህ ቀደም የነበሩ መነቃቃት ለመፍጠር መታቀዱ ተገልጿል።

በዚህ ሁነት ከ200 እስከ 300 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን በተያዘው አመት ከ2ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዷል።

የግድቡ ግንባታ በጋራ ከሰራን ማሳካት እንችላለን የሚለውን ማሳየት የቻለ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ይህ አንድነት በሌሎች መስኮችም እንዲደገም ተጠይቋል።

Via አዲስ ዋልታ

@etconp
👍13❤3😁1
Which type of Bridge is shown in this figure?


1️⃣.Arch bridge 🌁
2️⃣. Cantilever bridge 🌁
3️⃣. Truss bridge 🌉
4️⃣.Beam bridge 🌁

@etconp





Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Instagram :- https://instagram.com/etconp?igshid=MzRlODBiNWFlZA==

Telegram:- https://t.me/ETCONp

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

Twitter :- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
👍16❤1🏆1
CONSTRUCTION 🏗️ INDUSTRY IN ETHIOPIA 🇪🇹

የካቲት 24 / 2016 ዓም በ FM 97.1 ከ EVA show ጋር የነበረኝ ውይይት

የ ግንባታ ሴክተሩ ሁለተኛው ኢኮኖሚ ነው በ ኢትዮጵያ ከ ግብርና በመቀጠል፤ በ GDP ከተመለከትን አንደኛውን ድርሻ ይይዛል የ ምጣኔ ሀብታችን 60% ነው።

ይሁንና አሁን ላይ አብዛኛው ፕሮጀክት ለ ውጭ ሀገር ተቋራጮች ኮንትራት እየተሰጠ ይገኛል፤ ይህ የውጭ ሀገር ምንዛሪ እጥረት ይዳርገናል ይባስ ብሎ በምህንድስናው ብዙ ምሩቅ ያፈራችው ሀገራችንን የስራ አጥ ቁጥር ይጨምራል ይሄም ሚሆነው የሀገር ቤት ባለሞያዎችን ከውጭ ሀገር የመጡ ተቋራጮች በ አመርቂ ሁኔታ ስለማይቀጥሩ ነው።

ለዚህ ምን መፍትሄ አላችሁ????

ተሳተፉ

ሰሞኑን በ facebookገፃችን live በመግባት እንወያያለን
👏16👍6❤5
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
👍2❤1👌1
👉ስለ Athematic Error

🚧በጨረታ ግምገማ ሂደት አንድ ተቋራጭ ባስገባው ጨረታ ሰነድ ላይ የሞላው እያንዳንዱ የሥራ ልኬት (quantities) በተቀመጠላቸውነጠላ ዋጋ (Unit price/rate) እየተባዙ በገምጋሚ ኮሚቴው የሚረጋገጡበት ሂደት Athematic checking ይባላል። የዚህ ሂደት ዋናው ዓላማ አሸናፊው ተቋራጭ ያስገባቸው ነጠላ ዋጋዎች እና ብዜቶች ትክክል መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሲሆን ስህተቶች (Errors) ሊገኝበት ይችላል።

🌟እንደ መነሻ ኬዝ ከላይ የተጠየቀውን ምሳሌ እናንሳ፦ አንድ ተቋራጭ የጨረታ ሰነዱ ሲከፈት ጠቅላላ ድምር 50,000,000 ብር ያስገባ ሲሆን ሁለተኛ የወጣው ተጫራች 50,050,000 ብር አስገብቷል።

ሃምሳ ሚሊዮን (50,000,000 ብር ) ያስገባው ተጫራች ዝቅተኛ ዋጋ (List Price) መሰረት አድርጎ Athematic checking ላይ ችግር ካልተገኘበት አሸናፊ እንደሆነ ይገለጻል።

ተቋራጩ በ'Athematic checking ሂደት ውስጥ ለ112 ኪዩቢክ ሜትር አርማታ በአንድ ኪዩቢክ ሜትር ልኬትነጠላ ዋጋ በ8,000 ብር ሂሳብ ጠቅላላ የአርማታ ዋጋ 896,000 ብር  አስገብቷል ነገር ግን ወረቀቱ ላይ የመዘገበው ነጠላ ዋጋ 8000 (ስምንት ሺህ) ሳይሆን አንድ ዜሮ ጨምሮ 80000 (ሰማንያ ሺህ) ነው። 'Athematic checking የ112 ኪዩቢክ ሜትር አርማታ ዋጋ ከ896,000 ብር ወደ 8,960,000 ብር ከፍ ያለ ሲሆን ከስምንት ሚልዮን ብር በላይ ልዩነት አመጣ።

ነገር ግን ይህ ተጫራች ሁለተኛ የወጣውን ተጫራች በሃምሳ ሺህ (50,000) ብር ልዩነት አሸንፎ ነበር። በዚህ ሂደት ሊታዩ የሚገባቸው የሕግ አግባቦች፦

⏺የኢትዮጵያ የመንግስት ግዢ ባለሥልጣን የነበረው (Public Procurement Agency - PPA) ለተለያዩ የግዢ ሁኔታዎች መመሪያ ያጸደቀ ሲሆን ለኮንስትራክሽን ሥራዎች በሚያገለግለው መመሪያ Instructions to Bidders (ITB) አንቀጽ 33.1. (a) ላይ "በአንድ ልኬት ላይ የተቀመጠ ነጠላ ዋጋ እና በሥራ መጠንና ነጠላ ዋጋ ብዜት በሚገኘው አጠቃላይ ዋጋ መካከል ልዩነት ከተፈጠረ በሕዝብ (በፕሮጀክት ባለቤቱ ወይም ተቀካዩ) አካል አስተያየት ግልጽ ካልሆነ በቀር የነጠላ ዋጋ (unite price) እንደገዢ ተቆጥሮ በብዜት የተገኘው አጠቃላይ ዋጋ (sub total) ይስተካከላል ወይም ይታረማል።

ነገር ግን የሕዝብ አካሉ (አሠሪው ወይም ሕጋዊ ተቀካይ ባለሙያዎቹ) የነጠላ ዋጋ ሲጻፍ የአስርዮሽ ነጥብ የተሳሳተ አቀማመጥ (misplacement of the decimal point) እንዳለ ካሰበ ወይም ካመነበት፣ በዚህ ሁኔታ የተጠቀሰው የብዜቱ አጠቃላይ ዋጋ (total price) ገዢ ሆኖ ለአንድ ሥራ ልኬት የተቀመጠው ነጠላ ዋጋ (unit price) ይስተካከላል ወይም ይታረማል
" የሚል ግልጽ ሀሳብ አስቀምጧል።

በመሆኑም ተቋራጩ ያስገባው ዋጋ የአስርዮሽ ነጥብ የተሳሳተ አቀማመጥ (misplacement of the decimal point) ኖሮበት ብዜቱ ግን በአግባቡ ከተቀመጠ እና የጨረታ ኮሚቴው ስህተት መሆኑን ካለው ነበራዊ የግንባታ ሥራዎች ነጠላ ዋጋ አንጻር ተቀራራቢ የሚሆነው የአሥርዮሽ ማስተካከያ ሲሆን እንደሆነ ካረጋገጠ ነጠላ ዋጋውን ትቶ ብዜቱን እንዲይዝና ነጠላ ዋጋው እንዲስተካከል ማድረግ አለበት።

▶️ከላይ በተጠቀሰው አንቀጽ መሰረት፦

🖱[1ኛ]፦  በሀገራችን የትኛውም ቦታ የአንድ ኪዩቢክ ሜትር አርማታ ሙሌት ዋጋ ከ6,000 እስከ 15,000 ብር ስለሆነ 8,000 ብር ተቀባይነት ይኖረዋል እንጂ "ተቋራጩ ለአንድ ኪዩቢክ ሜትር ዋጋ ሰማንያ ሺህ (80,000 ብር) አስገብቷል ብሎ መጣል ሙያዊ እምነት ያልታከለበት ወይም አውቆ እንደመካድ የሚቆጠር ነው።

🖱[2ኛ]፦ ተጫራቹ ለ112 ኪዩቢክ ሜትር ያስገባው ብዜት ዋጋ 896,000 ብር መሆኑ የአንድ ኪዩቢክ ሜትር አርማታ ሙሌት ስምንት ሺህ (8000) ብር መሆኑ ስለሚጠቁም ለሙያው ቅርብ የሆነ ወይም ምክንያታዊ የሆነ ውሳኔ እንዲወሰን መደረግ ይኖርበታል ማለት ነው።

☄በዚሁ አንቀጽ ሥር ንዑስ አንቀጽ (b) ላይ "በእያንዳንዱ የሥራ ክፍሎች ሥር ያለው ንዑስ ድምሮች እና ጠቅላላ ድምር መካከል የመጨመር ወይም የመቀነስ ልዩነት ከተስተዋለ በእያንዳንዱ ሥራዎች ሥር ያለው ንዑስ ድምር ገዢ ይሆንና ጠቅላላ ድምሩ ይስተካከላል።

⏺በንዑስ አንቀጽ (c) ደግሞ በፊደል የተጻፈው እና በአሐዝ የተቀመጠው ልዩነት ካለው በፊደል የተቀመጠው ዋጋ ገዢ ይሆናል። ነገር ግን ይህ በፊደል የተቀመጠው ዋጋ ከ'Athematic Error ጋር የሚገናኝ ከሆነ በአሐዝ የተቀመጠው ዋጋ ገዢ ይሆናል በማለት አስቀምጧል።

🫵ስለሚከታተሉን እናመስግናለን🙏

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBot መልእክት ኣሰቀምጡልን😍

🫶የኮንስትራክሽን ስራ እና ጨረታዎች በ ትኩሱ እንዲደርስዎ ይህ ቴግራም ቻናላችን ይቀላቀሉን👇

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍33🙏6❤1
🌟ውድ ቤተሰቦቻችን የ Ms Project ቲቶርያል ለ ጀማሪዎች የሚሆን እየሰራን ቆይተናል ዛሬ ከ ትላንት የቀጠሉ ክፍል 6 እና 7 በ YouTube ገፃችን ለቀነዋል

🖱ለ ቀጣይ ተለቅ ያለ ፕሮጀክት ለ Advanced የሚሆን በ ኣዲሱ ሶፍትዌር እንደምንሰራ ቃል እንገባለን❤️

👉Amharic Ms Project Tuetorial Part 6 & 7 is Uploaded

🫵ለ YOUTUBE ቻናላችን አዲስ ከሆኑ SUBSCRIBE በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ እንዲሁም ለወዳጅዎ ያጋሩ🙏👇

https://www.youtube.com/@ETHIOCONp

https://youtu.be/6QFU3DyRYzQ
🙏8👍4❤1
ነጻ የስልጠናና የስራ እድል ለሴቶች

አቡቀለምሲስ የሪል እስቴት ማሰልጠኛ ተቋም።


እንኳን ለ March 8 አደረሳችሁ እያለ እንደተለመደው አለምዓቀፍ የሴቶች ቀን ማርች ኤይትን በማስመልከት ተቋማችን አቡቀለምሲስ የሪል እስቴት ማሰልጠኛ ተቋም ለአምስት ወጣት ሴቶች ነጻ የስልጠናና የስራ ዕድልን አመቻችቷል።

ስልጠናው በሪል እስቴት ሽያጭ ሙያ ሲሆን ሁለት ወራትን ይወስዳል።

ስልጠናው ቅዳሜ ከሰዓትና እሁድ ጠዋት የሚካሄድ ሲሆን መጋቢት 7 2016ዓም የሚጀመረው 25ኛው ዙር ሰልጠና አካል ይሆናሉ።

የስልጠና ቦታ ወሰን ሰፈር ብሬክስ ህንጻ አራተኛ ፎቅ።

በስልክ ቁጥሮቻችን

0951040404
0993232323

በመደወል ተመዝገቡ

@etconp
👍10🙏2❤1
👉በአዲስ አበባ የኬብል ካር ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ!

🌟ኦቪድ ግሩፕ የትራንስፖርት ችግርን መፍታት የሚያስችል የኬብል ካር (በገመድ ላይ ተንጠልጣይ የህዝብ ትራንስፖርት) ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ ታደሰ ገልጸዋል።

🚧ኦቪድ ግሩፕ በቴክኖሎጂ የታገዙ ዘመናዊ ቤቶችን ከመገንባት ባሻገር የትራንስፖርት ችግርን ለመፍታት በአዲስ አበባ የኬብል ካር ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ የፕሮጀክት ጥናት ማጠናቀቁን ዋና ሥራ አስፈፃሚው አስታውቀዋል።

🖱የባቡር እና የመኪና መሰረተ ልማቶችን ማፍረስ ሳያስፈልግ በገመድ ላይ ተንጠልጣይ የህዝብ ትራንስፖርት ወይም ኬብል ካር ቴክኖሎጂን በአዲስ አበባ ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል።

✨በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ የኢትዮጵያን ገጽታ የሚያጎሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው፤ ኦቪድ ግሩፕም በግንባታው ዘርፍ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ዘመናዊ ከተማ ለመገንባት በመንግስት የሚደረገውን ጥረት የበለጠ የሚደግፍ መሆኑን አረጋግጠዋል።

☄ኦቪድ ሀገራዊ ልማትን ከማገዝ ባለፈ በግንባታው ዘርፍ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እና በአጭር ጊዜ የማጠናቀቅ ስራውን እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ተዘግቧል።

Via ኢዜአ

@etconp
👍18👏3❤1
👉ሴት ነዳፊዎቻችን

🌟እንኳን ለዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን አደረሰን❤️

🖱ረ/ፕሮፌሰር ዶክተር ቃል ኪዳን አስናቀ ገጸምድር ነዳፊ

☄ዶክተር ቃል ኪዳን አስናቀ በአዲስአበባ ተወልደው ያደጉ ሲሆን የመጀመርያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በናዝሬት ትምህርትቤት ተከታትለዋል።

የመጀመሪያ ዲግሪአቸውን በኪነህንጻ በ1993 ዓም ያገኙ ሲሆን በ2002 ዓም ደግሞ ሁለተኛ ዲግሪአቸውን በአካባቢ እቅድና በገጸምድር ንድፍ ሰርተዋል። በመቀጠልም በ2014 ዓም የመጨረሻውን የፒኤችዲ ዲግሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተቀብለዋል።

ዶ/ር ቃል ኪዳን የመጨረሻውን ዲግሪ የያዙ የመጀመሪያዋ ኢትዮዽያዊ የገጸምድር ነዳፊ ሲሆኑ በኢትዮዽያና ከኢትዮዽያ ውጪ በአያሌ የገጸ ምድር ንድፍ እና ስራ ቁጥጥር ስራ ላይ የተሳተፉ ነዳፊ ሲሆኑ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር ናቸው።

ከነደፏቸው ስራዎች መካከልም በሀርጌሳ ሶማሊላንድ የሚገኘውን የጊድ ደብሌ እጽዋት ማዕከል ማስተር ፕላን እና ዝርዝር ንድፍ፣ በቤት አርክቴክቶች ስር የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ካምፓስ ገጸምድር ንድፍ እና ግንባታ ቁጥጥር፣ በ ኤስቢ አማካሪዎች ስር የመቀሌ ቤተመንግስት ማስተር ፕላን፣ ገጸምድር ንድፍ እና ግንባታ ቁጥጥር፣ ከ"ዚያስ" አርክቴክቸርና ኢንጂነሪንግ ጋር ላጋር አንድ እና ሁለት ህንጻዎች ገጸምድር ንድፍ፣ ከባሮክ ነዳፊዎች ጋር የአዲስ አበባ ቦሌ አለምአቀፍ የገጸምድር ማስተር ፕላን እና ንድፍ ይጠቀሳሉ።

በተጨማሪም የአያሌ ዩኒቨርስቲ ግቢዎችን ገጸ ምድር የነደፉ ታዋቂ ነዳፊ ሲሆኑ ብዙ የምርምር  ወረቀቶችን አሳትመዋል።

ዶክተር ቃልኪዳን በራሳቸው ከነደፉት የገጸ ምድር ንድፍ በተጨማሪ አበይት የገጸምድር ንድፍ ስራዎች በሚኖሩበት ወቅት  በተለያዩ ባለድርሻ አካላት እየተጋበዙ  እየተጋበዙ የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ።

@etconp
❤17👍17👏3🥰1🏆1