Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉የአዲስ አበባ የከርሰ ምድር ውሃ እየተሟጠጠ መሆኑን ጥናት አመለከተ

🌟የአዲስ አበባ የከርሰ ምድር ውሃ እየተሟጠጠና በመዲናይቱ የውሃ አቅርቦት አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰ በዚህ ሳምንት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ላይ የምህንድስና ባለሙያዎች ያቀረቡት ጥናት ማመልከቱን ሪፖርተር ዘግቧል።

🚧መዲናይቱ በአሁኑ ወቅት በቀን 1.2 ሚሊዮን ኪውቢክ ሜትር የውሃ ፍላጎት እንዳላት ሲገለፅ ነገር ግን የውሃ አቅርቦቱ 40 በመቶ የሚሆነውን ፍላጎት ብቻ እየሸፈነ ስለመሆኑ ተመላክቷል። የከተማዋ የውሃ ፍላጎት ከአቅርቦት በላይ መሆኑ የውሃ ጥራት እንዲኖር አድርጓልም ተብሏል።

⏺ቁጥጥር ያልተደረገበት የከርሰ ምድር ውሃ አጠቃቀም እንደሚስተዋል ጥናቱ ሲጠቁም የውሃ ማጠራቀሚያ ታንኮች ላይ ጥገኛ መሆን ችግሩን እያባባሰው እንደሆነ ተጠቁሟል። ይህንን ለመቅረፍ የዝናብ ውሃን ለማከማቸት የሚረዱ ማጠራቀሚያዎችን መገንባት እንደሚገባና መንግስትም የውሃ ቁፋሮ እና የከርሰ ምድር ውሃ አጠቃቀምን የተመለከቱ ጠንካራ ህጎች ማውጣት እንዳለበት ባለሙያዎቹ አሳስበዋል።

@etconp
👍8❤1
የሰሞኑ የአዲስ አበባ መልሶ ማልማት ስራ ‘’ቅይጥ የመሬት አጠቃቀምን’’ የሚከተል ነው ተባለ።

መጋቢት 20፣2016

ቅይጥ የመሬት አጠቃቀም፤ ለመኖሪያ፣ የንግድ ስራ እና ለአገልግሎት የሚውሉ ህንፃዎች አንድ ቦታ ላይ እንዲገነቡ የሚያደርግ መሆኑን ሠምተናል።

ይህም ቀደም ሲል የነበረውን የመሬት አጠቃቀም የቀየረ ነው ሲል፤ ከ18 ኪሎ ሜትር የሚበልጠውን የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ያጠናው ድርጅት ነግሮናል።

ቀደም ሲል የሚታወቀው የመሬት አጠቃቀም የመኖሪያ አካባቢ፣ የንግድ ቦታዎች፣ የኢንቨስትመንት ስፍራዎች በሚል የሚከፋፈል እንደነበር ‘’ኮምፓስ ኤፒድ ኮንሰልተንሲ’’ የተሰኘው የዚሁ አማካሪ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ጎሣዬ በቀለ አስታውሰዋል።

በቅይጥ የመሬት አጠቃቀም፤ አንድን ህንጻ በተለያየ ደረጃ በመከፋፈል ለመኖሪያም ለንግድም ማዋል እንደሚቻል የሚያነሱት ኢንጂነር ጎሣዬ፤ እንዲህ አይነቱ የመሬት አጠቃቀም የአንድ አካባቢ የንግድ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድግ ተናግረዋል።

በመልሶ ልማቱ የመኖሪያ ህንጻዎችም ሆኑ የንግድ ተቋማት ከመንገዶች ገባ እንዲሉ ትኩረት ተሰጥቷል ተብሏል።

ኮምፓስ ኤፒድ ኮንሰልተንሲ* የአዲስ አበባን የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት  አስመልክቶ ባካሄደው ጥናት ላይ፤ ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ ሞያተኞች እንዳሳተፈ ሠምተናል።

ንጋቱ ረጋሣ

Via Sheger FM

@etconp
👍9
Compression members always tend to buckle in the direction of the
Anonymous Quiz
30%
Axis of load
54%
Perpendicular to the axis of load
9%
Minimum cross section
7%
Least radius of gyration
👍7❤1🙏1
ETCONp Example On Column Interaction Chart.pdf
2.9 MB
👉Example:- Draw the interaction diagram for column cross section

400 mm Length
400 mm width

Considered 100mm is Concrete Cover

Use:C-25/30, S - 460

🖱Show at least a minimum of 6 points in the interaction diagram.

i. Pure axial compression
ii.Balanced Failure
iii. Zero tension (Onset of cracking)
iv. Pure flexure
V. A point b/n balanced failure and pure flexure
Vi. A point b/n pure axial compression and zero tension

🫵The Full Answer Is On the PDF

@etconp
👍16🙏5❤3
👉በአዲስ አበባ የሚከናወነው 'የልማት ኮሪዶር' የሚነካቸውን ወይም የሚያካትታቸውን ስፍራዎች በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎች ደርሰውኛል

🌟ይህንን በተመለከተ በመንግስት የተዘጋጀ አንድ ባለ 318 ገፅ ዝርዝር የማስተር ፕላን ዶክመንትን ዛሬ የተመለከትኩ ሲሆን ይህ በምስል 1 ላይ የምትመለከቱት ፕሮጀክቱ የሚያካትታቸውን ቦታዎች ነው።

- በዚህም መሰረት ከፒያሳ ጀምሮ ወደ ብሄራዊ፣ ሜክሲኮ አደባባይ፣ ሳርቤት፣ ጎተራ አድርጎ ወሎ ሰፈር ይደርሳል።

- ፕሮጀክቱ አምስት ክፍለ ከተሞችን (አራዳ፣ ልደታ፣ ቂርቆስ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ቦሌ) የሚያካትት ሲሆን በአጠቃላይ 10.4 ኪ/ሜ ርዝመት ይኖረዋል፣ የፕሮጀክቱ ቦታ ስፋትም 460 ሄክታር ይደርሳል።

- ፕሮጀክቱን ለመፈፀም ተሞክሮዎች ከኩሪቲባ (ብራዚል)፣ ከቦጎታ (ኮሎምቢያ) እና ከካናሪ ዋርፍ (እንግሊዝ) ተወስደዋል።

- በፕሮጀክቱ መስመር ላይ ታሪካዊ ህንፃዎች ተብለው የተቀመጡት የአ/አ ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት ህንፃ፣ የድሮው ፖስታ ቤት፣ ባንኮ ዲሮማ፣ ሴጣን ቤት ቲያትር፣ እንደ ሊሴ ገ/ማርያም ያሉ ትምህርት ቤቶች፣ ፖስታ ቤት፣ ኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ እና ክቡ የንግድ ባንክ ህንፃዎች ናቸው። እነዚህ በፕሮጀክቱ ሊነኩ የማይችሉ እንደሆነ ያሳያል።

- በመጨረሻም፣ 'የዲፕሎማቶች ሰፈር' የሚባል ፕሮጀክት የታሰበ ሲሆን ዲፕሎማቶች ብቻ የሚኖሩባቸው ኤምባሲዎች፣ ቆንስላዎች እና ተያያዥ አገልግሎት መስጫዎች ይገነባሉ (ምስል 2 ይመልከቱ)

Via Elias Meseret

@etconp
👍14❤3
Q. 1 the plane is called principal plane if the value of normal stresses
Anonymous Quiz
23%
Minimum
40%
Max.
30%
Max. OR min.
7%
None
🙏10👍5🕊3
Q. 2
a plane where normal stress either maximum or minimum, then the shear stress is
Anonymous Quiz
10%
Maxi.
10%
Min.
23%
Max. Or min.
57%
Zero
👍8
👍12❤5
👉አራዳ የከተማ የስህበት ማዕከል እንድትሆን ታላቅ አስተዋፅኦ ያለውና ቀድሞ አራዳ ገበያ በመባል ከሚጠራው የከተማው ነባር የገበያ ማዕከል አቅራቢያ የሚገኘው የመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አራዳ ጊዮርጊስ) ቤተ-ክርስቲያን ምስረታው ከአዲስ አበባ እድሜ ያልተናነሰና (ካልበለጠ) የግነቱ ታሪክም በእጅጉ ከአድዋ ድል ጋር ተያይዞ የሚነገርለት በአዲስ አበባ ከሚገኙ ቤተ-ክርስቲያኖች መካከል አንዱና ዋነኛው ነው።

🚧ቤተ-ክርስቲያኑ በመጀመሪያ ክብ የጎጆ ቅርፅ የነበረዉ ሲሆን አሁን የሚታየው የቤተ-ክርስቲያኑ ገፅታ በግሪካዊው ህንጻ ነዳፊ ኦርፋኒደስ ተነድፎ ከጣልያን በምርኮ በተገኘውና የመጀመሪያውና ታሪካዊዉ የአቢሲኒያ ባንክን በገነባው ህንጻ ገንቢ (Engineer) ሰባስቲያኖ ሙሴ ካስታኛ (Sebastiano Monsieur Kastagna- ሙሴ ቀስተኛ) መሪነት ፤ በግሪክና አርመን የግንባታ ሠራተኞች ተሳታፊነት በ1900 ዓ.ም ዳግም ታንጿል።

🌟የህንጻ ግንባታው በባለሙያዎች ስምንት ክባዊ ቅርጽ (Octagon plan) የንድፍ መሰረትነት ተዋቅሮ ከአዲስ አበባ በተለይም ከቀበናና ከኮተቤ አካባቢዎች ተመርጠዉ በመጡና በመልክ በመልክ ተጠርበዉ በታነጹ ውብ ድንጋዮች ተገንብቶ በፈረንሳይ በተሠራ ያማረ የጣሪያ ጉልላት (dome) የተከደነ ታሪካዊ ቤተ-ክርስቲያን (Cathedral) ነው።

🖱አራዳን ከጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ነጥሎ ማሠብ በማይቻልበት ደረጃ ቤተ-ክርስቲያኑ አሁንም በማዕከለ አራዳነት እያገለገለ ይገኛል።

📸ምስል ምንጭ: በሰርጌ ደውል ፣ በፋሲል ጊዮርጊስና ዴኒስ ጄራርድ በአዲስ አበባ ዙሪያ የተፃፉ የከተማ ታሪክ መፅሀፍት እና ናትናኤል ፍሬው

Via NArc Home Architecture

@etconp
👍13😢2
🫵እራሳችሁ መሞከር የምትችሉት የአውሮፓ ነፃ የስኮላርሺፕ የትምህርት እድሎች 2024

🌟1. Swedish Institute Scholarship for Global Professionals 2025 (Fully Funded)

https://lnkd.in/d-ghTsNG

🌟2. Romanian Government Scholarship 2025 (Fully Funded)

https://buff.ly/3NUDqrg

🌟3. French Government Eiffel Excellence Scholarship 2024 (Fully Funded)

https://buff.ly/3CAXAAS

🌟4. Hungary Government Stipendium Hungaricum Scholarships 2024 (Fully Funded)

https://buff.ly/3EKnYtX

🌟5. Uppsala University Scholarships In Sweden 2024 (Funded)

https://buff.ly/3Xg5DeM

🌟6. University of Oulu Scholarship In Finland 2024 (Funded)

https://buff.ly/3QICKWd

🌟7. Ernst Mach Austria Scholarship in Europe (Fully Funded)

https://buff.ly/3Jg3wUl

🌟8. Utrecht University Excellence Scholarship in Netherlands (Fully Funded)

https://buff.ly/3VVJEsu

🌟9. University of Pecs Stipendium Hungaricum Scholarship 2024 (Fully Funded)

https://buff.ly/3TzsvHb

🌟10. University of Pavia Scholarship in Italy 2024 (Fully Funded)

https://buff.ly/3Nr194A

@etconp
👍12🕊3🙏2👌2❤1
ከ ETCONp PPA በ አማርኛ.pdf
1.5 MB
👉PPA በ አማርኛ

🌟ለግንባታ ስራዎች እና ጨረታ ሰነድ ግዥ ዝርዝር መመሪያ ወይም ደንብ የተካተተበት ፋይል

📽ለ YOUTUBE ቻናላችን አዲስ ከሆኑ SUBSCRIBE በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ እንዲሁም ለወዳጅዎ ያጋሩ👇

https://www.youtube.com/@ETHIOCONp

@etconp
🙏11👍5❤1
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ

፦ፕሌት 1mm-30mm any size ቆርጠን በስተን ጣጣዉን ጨርሰን እናስረክቦታለን

፦jbolt 12mm-32mm በፈለጉት ቁመት ጥርስ አዉጥተን አጥፈን እንሰጦታለን

፦ankerbolt

፦stafa(ስታፋ ባለ 6 እና ባለ 8)በየትኛዉም size የተዘጋጀ አለን

፦ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን

አድራሻችን
ቁ.1  አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
ቁ.2 ተክለሐይማኖት
ቁ.3 መርካቶ
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ

0904040477
0911016833
0994941706

ይደዉሉልን ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም ቢሆኑ ካሉበት እንልክልዎታለን።
🏆4👍2❤1😢1
👉የአሸዋ ደለል መጠን (Silt Content)

✨በአርማታ (concrete)፣ ልስን (plastering)፣ ወለል ጭረሳ (floor screed) እና የአሸዋ ግርፍ (rendering) ሥራዎች በብዛት የምንጠቀምባቸው ሦስት የግንባታ ግብአቶች ሲሚንቶ፣ አሸዋ እና ጠጠር (Cement, Sand/Fine aggregate & Coarse Aggregate) ናቸው።

🚧ሲሚንቶ ዋናው ዓላማው የግንባታ ግብአቶች እስር በእርሳቸው ያላቸውን የመጣበቅ/የመጣመር ሂደት ማጠናከር (As binding agent) ሲሆን የአሸዋ ድርሻ የውስጥ ለውስጥ (air voids) መሙላትና ማእከላዊ የሆነ ማጣበቅና ጥንካሬ መስጠትን ማገዝ ነው።

📌የጠጠር ዋናው ድርሻ ደግሞ የኮንክሬት ክፍሎችን ጥንካሬ መስጠት ነው። 

🖱አሸዋ (Fine aggregate) ማእከላዊ ወሳኝ ግብአት ተብሎም ይታወቃል። በትላልቅ አውሮፓውያን እና በሩቅ ምስራቅ ሀገራት በተለይ በህንድ እና በቻይና ልዩ ትኩረት የሚሰጠው እና እንደሲሚንቶ የአሸዋ ማጣሪያ ፋብሪካ ጭምር የተገነባለት ግብአት (material) ነው። ይህ ሆኖ ሳለ የአሽዋ መሰረታዊ የቤተሙከራ  ማረጋገጫ ምዘናዎች ውስጥ ቀላሉ ነገር ግን ልዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የደለል ይዘቱ (silt content) ነው። /ደለል ማለት በጣም የላመ ወይም የደቀቀ ዱቂታማ የአፈር አይነት ነው/። አሸዋ በተቻለ መጠን ምንም የደለል ይዘት አንዳይኖረው ይመከራል። ደለላማ የአፈር መጠን በአሸዋ ውስጥ በብዛት ካለበት አሸዋው ጥቅም ላይ ሲውል የአርማታ ባህርይን ወደ ጭቃማ ጸባይ ይቀይራል ማለት ነው። ደለላማ የአፈር ክፍል አሸዋው ማንኛውንም የቤተሙከራ መስፈርት (laboratory tests) በብቃት እንዳያልፍ ያደርገዋል። አርማታ ጥንካሬ እንዳይኖረው እና ልስን በቀላሉ እንዲፈራርስ የሚያደግ ነው።

🌟ደቃቅ አፈር/ደለል (silt content) የሚባለው እንደ ፕሮጀክቱ አይነት ልዩ ሀሳቦች የሚነሱበት ቢሆንም በ'ASTM, AASHTO, IS እና በሌሎች መመሪያዎች ላይ እንደተጠቆመው በብዛት ከ75 micro-millimeter sieve በታች የሚወርደውን ክፍል ነው።

🚧በመሆኑም አሸዋ በውስጡ ከስድስት በመቶ (6%) በላይ ደለላማ አፈር (silt content) እንዲኖረው አይፈቀድም። በግንባታ ቤተሙከራዊ የግብአት መስፈርቶች (Experimental criterion) መሰረት አሸዋ ከ6% በላይ ደቃቅ አፈር አንዳለበት ከታወቀ ሁለት አይነት ርምጃ ይወሰዳል።

▶️አንደኛው:- አሸዋውን በአሸዋ ወንፊት መንፋት (sieving) ሲሆን (ሁለተኛው) አሸዋውን አስወግዶ (rejection) ሌላ መስፈርቱን የሚያሟላ አሸዋ መጠቀም ነው።

⏺በብዙ የሀገራችን የግንባታ ቦታዎች ላይ አሸዋ በቁም ወይም በአግዳሚ ወንፊት ሲነፋ የሚስተዋለው ይህንን የደለል ለመቀነስ እና ከአሸዋ ቅርጽ መጠን በላይ (Above determined sieve size of sand) የሆነ ጠጠራማ ክፍልን (aggregated particles) ለመለየት ነው።

@etconp
👍14❤10👌1
❤4👍4
What do you say about the plumber 🧑‍🔧 ?


Comment below ⬇️ 👇🏻 @cotmp

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://www.youtube.com/@ETHIOCONp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

X formerly (Twitter):- https://x.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
😁4👍1👌1
👉የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እውነታዎች

🚧የዋናው ግድብ ከፍታ 145 ሜትር ሲሆን፤ ርዝመቱ 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ነው

🚧የዋናው ግድብ ውፍረት የግድቡ ግርጌ ላይ 130 ሜትር ሲሆን፤ የግድቡ ጫፍ ወይም የላይኛው ክፍል ደግሞ 11 ሜትር ነው

🚧ግድቡ የሚይዘው የውኃ መጠን 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

🚧ግድቡ የሚሸፍነው የቦታ ስፋት ደግሞ 1 ሺህ 680 ስኩዌር ኪሎ ሜትር 

⚡️የግድቡ የኃይል ማመንጫ ዩኒቶች 16 ናቸው

⚡️እያንዳንዱ ዩኒት የሚያመነጨው የኃይል መጠን ከ375 እስከ 400 ሜጋዋት ነው

⚡️6ሺህ 450 ሜጋዋት ኃይል ማምረት ይችላል

🌟ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ 2ሺህ ሜጋዋት ያህሉን ለጎረቤት ሀገራት መሸጥ ይቻላል

🌟በዓመት እስከ 580 ሚሊዮን ዶላር ማግኘት ይቻላል

🌟የግድቡ ውኃ የሚተኛበት መሬት ርዝመት 246 ኪሎ ሜትር ነው

Via ኢዜአ

@etconp
❤16👍8