Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.28K photos
359 videos
1.99K files
3.34K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
Chongqing, China 🇨🇳
Highway
Amazing
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)
👉ዛሬ ደሞ ትንሽ ስለ ግድብ እንንገራቹ @COTMp
.
▶ግድብ (Dam) ማለት ግዙፍ አካል ሲሆን የውንዝን ሸለቆ ላይ ተገንብቶ የውሃን ተፋሰስ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሚገታ ነው።
*ይህ መግታት (blockage) በውሃ ተፋሰስ ላይ መታቆርን (reservoir) ይፍጥራል ይህም ወሃውን ለተፈለገው አገልግሎት እንዲውል ቀላል ያደርገዋል።
ይህ አጋጅ ገዝፈ አካል ወይም ግድብ ከተለያዩ ቁሶች ይሰራል ፦ ኮንክሪት፣ የድንጋይና አፈር
መደምደም (compaction) ወዘተ...
.
➡ግድብ በዋነኛነት ለነዚህ አገልግሎቶች ይገነባል፦👇
.
1- ጎርፍን ለመቆጣጠር (for flood control)
.
2- ለውሃ አቅርቦት እና የመስኖ ስራ (for water supply and
irrigation)
.
3- የኤሌትሪክ ሃይልን ለማመንጨት (for electric power generation)
.
4- የአንድን ወንዝ ፍሰት ለመመጠን እና ለመቆጣጠር - (for regulation or balancing of a river flow)
.
⚡ አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)
👉 ከ ታሪክ ማህደር በ Building Codes ዙርያ @COTMp
.
Building Codes - የሚገነቡ ህንፃዎች ማሟላት የሚገባቸውን
እስታንዳርዶች የያዘ የህጎች ስብስብ ነው፡፡ ህንፃዎች የግንባታ
ፍቃድን ለማግኘት Building Code መከተል አለባቸው፡፡
የእስታንዳርዶቹ አስፈላጊነትም - ሴፍቲ ፤ ጤና እና ጠቅላላ
የህንፃውን ደህንነት ( Structural , Mechanical , Sanitary , Fire resistance. Earth quake, Flood , Water Supply, Light, Ventilation, ወዘተ ) ለማረጋገጥ ነው ……. ኣለማችን ላይ EBCS,Eurocode , IS, BS, ወዘተ የምንላቸው የህንጻ ኮዶች ኣሉ፡፡ የኛ ደሞ EBCS(Ethioian building code of standards) ይባለል።
.
.
ከላይ የምትመለከቱት ህንፃ በሃገረ ሩሲያ - ሙሉ ለሙሉ
ከእንጨት ተገንበቶ የነበረ ረጅም ህንፃ ሲሆን Fire resistance
standard ባለሟሟላቱ የአካባቢው ባለስልጣናት አፍርሰውታል፡፡
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)
👉ስለ TRUSS ... @COTMp
.
*Truss የምንለው Axial Load (compressive & tensile force) ብቻ የሚሸከሙ መዋቅሮች ናቸው፡፡
የትረስ ሜምበሮች የሚገናኙት በፒን ኮኔክሽን ማለትም (በአብዛኛው በብየዳና በብሎን ) ነው የሚገናኙት፡፡
*ሁለት አይነት ትረሶች አሉ Plain (2D) and Space truss (3D
ለምሳሌ የቴሌ ታወሮች )፡፡ *ትረሶችን ለህንፃና ለድልድዮች
ተመራጭ የሆኑበት ምክንያት ጠንካራና ክብደታቸው ቀላል ስለሆነ ነው፡፡ እናም ዛሬ ስለትረስ ልናወራ የቻልንበት ዋነኛ ምክንያት ብዙ ሳይቶች ላይ የግንባታ ግድፈት ስለምናይ አንዳንድ ነገር ለመጠቆም ያህል ነው::
ምንድነው ነገሩ ትረሶች ሲፈጠሩ Axial Load ብቻ እንዲሸከሙ ነው ሺርና ሞመንት መሸከም አይችሉም - Axial ፎርስም የሚሸከሙት የሚመጣውን ሎድ ቀጥታ መገናኛቸው ወይም joint ላይ ሲጫንባቸው ብቻ ነው:: ይህም ከጆይቱ ነው ወደ ሜምበሮች ሄዶ ከዛ ነው ወደ ኮለን ወይም ቢም የሚሄደው - ሳይት ላይ ግን ፐርሊኑን መሃል ሜምበሮቹ ላይ ሲበይዱት ይታያል - joint ላይ ነው መበየድ ወይም መታሰር ያለበት - ሳይት ላይ የሚደረገው ከሳይንስ ውጪ ነው ሃይለኛ ንፋስ ወይም ዝናብ ያለባቸው አካባቢዎች ይህ ነገር አሳሳቢ እና ኣደጋም ሊያደርስ ይችላል፡፡
Share Share Share
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)
👉ስለ Road structure components @COTMp
.
*Super Elevation = የመንገድ Curve ላይ መኪናን ከመንገዱ
ውጪ የሚጎትትን Centrifugal Force ለመቋቋም የአስፓልቱ
ከርቭ ዙሪያውን ከፍ ተደርጎ ይሰራል - ለሹፌሩም ምቾትን ይሰጣል እንዲሁም በሚታጠፍበት ግዜ ኣደጋን ይቀንሳል፡፡
.
*Pavement Crown = ለፍሳሽ ተብሎ የአስፓልቱ መሃል ከዳርኞቹ ይልቅ ከፍ ተደርጎ ይሰራል የሚሰራ ኮምፐነንት ነው። ሌሎችም components ከላይ በ ፒክቸሩ እንደምታዩት ዲፋይን ተደርገዋል
.
ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
Flat slab with drop panel
▶️ለ ውድ የ ቻናላችን ቤተሰቦች😍
፡
👉እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለ ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ።🙏
.
⚡ቻናላችን Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ። እናመሰግናለን!
👉ውድ የቻናላችን ተከታታዮች
፡
▶️ዛሬ እናንተን አሳታፊ እና ተሸላሚ የሚያደርግ ጥያቄ ይዘን ቀርበናል
፡
▶️ይህ ከላይ የምትመለከቱት የየትኛው የአዲስ አበባ ህንፃ (Interior) ነው?
፡
▶️ትክክለኛ መልስ በፍጥነት ለመለሱ 3 ሰዎች የ25 👌 50 👌 ፡እና 👌 የ 100 ሜጋ ባይት የገና ስጦታ ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡
፡
▶️ @Philemona7 በሚለው ሊንክ በመጫን መልሱን inbox ያድርጉልን፡፡ ▶️ መልሱን ስትልኩ አብራችሁ ስም እና ስልክ ቁጥር ላኩልን፡፡
Ethio Construction Engineering
👉ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ፡ ▶️ዛሬ እናንተን አሳታፊ እና ተሸላሚ የሚያደርግ ጥያቄ ይዘን ቀርበናል ፡ ▶️ይህ ከላይ የምትመለከቱት የየትኛው የአዲስ አበባ ህንፃ (Interior) ነው? ፡ ▶️ትክክለኛ መልስ በፍጥነት ለመለሱ 3 ሰዎች የ25 👌 50 👌 ፡እና 👌 የ 100 ሜጋ ባይት የገና ስጦታ ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡ ፡ ▶️ @Philemona7 በሚለው ሊንክ በመጫን መልሱን inbox ያድርጉልን፡፡ ▶️…
👉የተሸላሚዎች ስም ዝርዝር 👇 ስልክ ቁጥራቹ ላኩልን
1. @Abuderdae
2. @ATLAS2025
3. TOYB
.
👏👏👏👏👏
▶️በጣም ብዙ ሰው ትክክለኛው መልስ ኣግኝትቶታል ነገር ግን ፈጥነው የመለሱት 3ቱ ናቸው፡፡ ለሁላችሁም የተሳተፋቹ ከልብ እናመሰግናለን፡፡🙏
.
🇪🇹 የጥያቄው መልስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት የተገነባው በ1965 ዐ.ም የሚገኘው ከብሔራዊ ትያትር ፊት ለፊት 🇪🇹
፡
▶️መልካም በዓል❤️
▶️እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ፡፡😍
.
⚡አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።እንወዳችዋለን፡፡❤️
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)
👉 የአፈርን የመሸከም አቅም (BEARING CAPACITY) እንዴት እንጨምር?? ላላችሁን...
.
* ሶስት አይነት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከያ ቴክኒኮች አሉ - mechanical, chemical & other stabilization techniques
.
A) ሜካኒካል ውስጥ :-
.
1. Compaction - አፈሩን ስንጠቀጥቀው density/ unit
weight ይጨምራል ያ ማለት ደግሞ አፈርን የመሸከም አቅም ጨመረ ማለት ነው::
.
2. Excavation and Replacement – expansive soil ከሆነ ወይም ሌላ አስቸጋሪ አፈር ከሆነ ይህን መጠቀም እንችላለን
.
3. Mixing of Different Soils - ሳይታችን ላይ ያለው አፈር
coarse ወይም fine ብቻ ከሆነ ወይም ደግሞ አፈሩ አንድ አይነት
ብቻ ፀባይ ካለው ከተለያዩ አፈሮች ጋር በመደባለቅ የተሻለ የአፈር
ፀባይ ማግኘት እንችላለን
.
B) ኬሚካል :-
.
1. Lime stabilization - ይህንን የምንጠቀመው በአብዛኛው
ለexpansive soil ነው፡፡ አፈሩን ከ Lime ጋር በመደባለቅ
plasticity መቀነስ እንችላለን፡፡ የlime መጠኑ ከሚያስፈልገው
በላይ ከበዛ ግን B.C. ይቀንሳል፡፡
.
2. Cement stabilization - ሲሚንቶን ከአፈር ጋር በመደባለቅ
የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት መንገድ ነው፡፡ concrete
pavement ስር መጠቀም እንችላለን በአብዛኛው ለአየር
መንገዶች ፤ ለአውራ ጎዳናዎች ፤ ግድቦችን ከሽርሸራ ለመከላከል
ወ.ዘ.ተ. መጠቀም እንችላለን፡፡
.
3. Asphalt stabilization - አስፓልትን ከአፈር ጋር በመደባለቅ
የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት ዘዴ ነው በተለይም ለcohesive
አፈሮች፡፡ አፈሩን water proof በማድረግና ውሃማነትን በመቀነስ
B. Cን መጨመር እንችላለን፡፡ በአብዛኛው ይህንን ድብልቅ
ለመንገዶች እንደ base course መጠቀም እንችላለን፡፡
.
.
C) ሌሎች የአፈርን ባህሪ ማስተካከያ መንገዶች:-
.
1. Drainage - ፓይፖችን አፈር ውስጥ በመቅበር ወይም
ጉድጓዶችን በመጠቀም ground water የምንቆጣጠርበት ነው
.
2. Precompression - ግንባታ ከመጀመራችን በፊት አፈሩ ላይ
ሎድ በመጫን ኮምፓክት የምናደርግበት ዘዴ ነው
.
3. Dynamic Stabilization
.
ሀ) Blasting - ቦምብ ወደውስጥ በመቅበር በፍንዳታው አፈሩ ይጠቀጠቃል::
.
ለ) Compaction Piles - ፓይሎችን ወደውስጥ በማስገባት
አፈሩ ወደ ጎን እንዲሸሽና እንዲጠቀጠቅ ማድረግ ይቻላል፡፡
ፓይሉን ስናስወጣውም በተቦረቦረው ጉድጓድ ውስጥ የተሻለ አፈር በማስገባት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከል እንችላለን፡፡
.
4. Injection And Grouting - አፈሩን በሲሚንቶ ወይም
በተለያዩ chemical ውህዶች በpressure በመምታት ground
water ና settlement መቆጣጠር እንችላለን፡፡
.
የተሻለውን ዘዴ ለመምረጥ የአፈሩንና የአካባቢውን ሁኔታ ፤
ኢኮኖሚ ፤ ሴፍቲና የመሳሰሉትን ነገሮች ማጤን አለብን፡፡
.
👉FOR MORE UPDATED AMHARIC CONSTRUCTION INFO JOIN US HERE 👇
http://t.me/COTMp
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)
👉 ከ ታሪክ ማህደር በ Building Codes ዙርያ @COTMp
.
Building Codes - የሚገነቡ ህንፃዎች ማሟላት የሚገባቸውን
እስታንዳርዶች የያዘ የህጎች ስብስብ ነው፡፡ ህንፃዎች የግንባታ
ፍቃድን ለማግኘት Building Code መከተል አለባቸው፡፡
የእስታንዳርዶቹ አስፈላጊነትም - ሴፍቲ ፤ ጤና እና ጠቅላላ
የህንፃውን ደህንነት ( Structural , Mechanical , Sanitary , Fire resistance. Earth quake, Flood , Water Supply, Light, Ventilation, ወዘተ ) ለማረጋገጥ ነው ……. ኣለማችን ላይ EBCS,Eurocode , IS, BS, ወዘተ የምንላቸው የህንጻ ኮዶች ኣሉ፡፡ የኛ ደሞ EBCS(Ethioian building code of standards) ይባለል።
.
.
ከላይ የምትመለከቱት ህንፃ በሃገረ ሩሲያ - ሙሉ ለሙሉ
ከእንጨት ተገንበቶ የነበረ ረጅም ህንፃ ሲሆን Fire resistance
standard ባለሟሟላቱ የአካባቢው ባለስልጣናት አፍርሰውታል፡፡
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)
👉የቻይናው Three Gorges Dam አስገራሚ ቁጥሮች @COTMp
.
* የግድቡን መሰረት ለመስራት 80,000 ድማሚት ሲጠቀሙ ይህ
ማለት ከ20 የሂሮሺማ የኒውክሌር ጥቃቶች ጋር እኩል ነው፡፡
.
* የግድቡ Reservoir ርዝመት 660ኪ.ሜ ነው - ይህም ማለት
ከአ.አ ማይጨው እንደማለት ነው፡፡
.
*18200 MW ያመነጫል ይህም 7965mw ከሚያመነጨው
የጃፓኑ Kashiwazaki-Kariwa የዓለማችን ትልቁ የኒውክሌር
ማብሊያ 230 ፐርሰትን ይበልጣል፡፡ ከህዳሴ ግድብ ደሞ 300 ፐርሰት/ 3 እጥፍ ይበልጣል፡፡
.
*ግንባታው 30 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ኮንክሪት ፈጅቷል - ይህም
ማለት 30 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ኮንክሪት ተጠቅመን 1 ሜትር
ዲያሜትር ያለው ድፍን ኮንክሪት pipe ብንሰራ ዓለምን አንድ ዙር
መዞር ይችላል፡፡
.
*463,000 ቶን ብረት የተጠቀሙ ሲሆን - ይህን ያህል ቶን ብረት
ተጠቅመን 63 ኤፍል ታወሮችን መገንባት እንችላለን፡፡
.
*በአማካኝ 77.5 ሜትር width ሲኖረው ይህም ከማንኛውም
አቅጣጫ የሚመጡ የሚሳኤል ጥቃቶችን እንዲቋቋም
ያደርገዋል፡፡ በተጨማሪም ከግዝፈቱ የተነሳ የቀን እርዝመት
በማይክሮ ሰከንድ እንዲጨምር አድርጓል፡፡ ከታላቁ የቻይና ግንብ
ቀጥሎ ከስፔስ ላይ የሚታይ የቻይና ሁለተኛው የሲቪል
ኢንጂነሪንግ ውጤት ነው፡፡
.
*ግንባታው ከ630 ቢሊየን ብር በላይ ሲፈጅ በ 2012 ተጠናቆ ከ1 ዓመት ከ6 ወር በኋላ ሙሉ ወጪውን መልሷል፡፡
.
*ሀብታሟ ሀገር ሳውዲ አረቢያ ከነዳጅ ፣ ከእንፋሎት ወዘተ
55000MW ስታመነጭ ሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ በትንሹ
45000MW ከውሃ ብቻ ማመንጨት ትችላለች
* እስካሁን ባለው 4000MW አይሆንም የምናመነጨው፡፡
18200 MW የሚያመነጨው 630 ቢሊየን ብር ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የመለሰ ኢትዮጵያ 45000 MW ስታመነጭ ምን ያህል
ብር ማግኘት እንደምትችል አስቡት።
ለማንኛውም Hydraulic Engineering ይህን ያህል ተፅዕኖ መፍጠር ይችላል፡፡
▶️ውቢትዋ ደሴ ከተማ ❤️
፡
👉የናንተ ከተማም ላኩልን
፡
🙏ወብ ምሽት ተመኘን😍
፡
⚡ቻናላችን Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ። እናመሰግናለን!
Burj kahlifa
What’s the name of this test ? The name of the instrument?

Use discussion group
Dubai
ውብ ምሽት ተመኘን
Xiangjiang gate designed by RMJM, located in Huan China 🇨🇳
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Fîłmøñ Łûël)
👉 እስቲ ኣሁን ደሞ ስለ Sheet Pile Wall ትንሽ እንንገራቹ። @COTMp
.
*እነዚህን ከላይ የምታዩትን ምስል Sheet Pile ይባላሉ እነዚህ ሲስተሞች በማያያዝ አንድ ወጥ ግድግዳ/wall ለመገንባት እንጠቀምባቸዋለን፡፡
*Sheet pile ዎል እንደ Retaining wall, cofferdam እና ተመሳሳይ የ ግድግዳ ስትራክቸሮች ለመገንባት ልንጠቀምባቸው እንችላለን፡፡ *የተወሰነው አካላቸው መሬት ውስጥ የሚቀበረውም pile driving ማሺን በመጠቀም ነው፡፡ በከለር ፎቶ የሚታየው Larson/ U Type ይባላል::
✌ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
t.me/COTMp
👆👆👆👆👆