👉 INTERCON Construction Chemicals
● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Wall Putty, Prime Coat
● Concrete Repair Mortar
● Floor hardener, Epoxy
● Grout, Self-level mortar
● Quartz paint, Contextra
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers
● Geotextiles and other construction chemicals and materials
☎️ Tel: 0961955555
🔹 Address 1: Signal road, around
Dinberwa Hospital
🔹 Addres 2: Wellosefer, Infront of
Dani Plaza

❤2
👉የለሚ - ጀማ ወንዝ የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ በ5.1 ቢሊየን ብር ሊገነባ ነው
🚧በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ደጋማ ቦታዎች ተነስቶ ጉዞውን ወደ ታላቁ ዓባይ የሚያደርገው የጀማ ወንዝ፣ ከተራ የውሃ ፍሰት ባለፈ የሺህ ዓመታት ታሪክ፣ የተፈጥሮ ውበት እና የብዙሃን ህይወት የተሳሰረበት ታላቅ ፀጋ ነው፤
💫ይህ ወንዝ በታሪካዊቷ ሸዋ ምድር ውስጥ እንደ ደም ስር ተዘርግቶ መርሐቤቴን፣ እንሳሮን፣ ባሶና ወረናን፣ መንዝን፣ ጣርማበርን እና ሞረትና ጅሩን ጨምሮ በርካታ ወረዳዎችን በማስተሳሰር ይታወቃል፤
⏺የጀማ ውበት የሚገለጠው በተለዋዋጭ ባህሪው ነው። በክረምት ወራት ወንዙ የኃይል እና የቁጣ ተምሳሌት ይመስላል፤ እንደ ገደል ናዳ እየተወረወረ፣ ለም አፈሩን እየገመሰ እና ድንጋዮችን እየናደ በቀይ አፈር ተለብሶ ይጓዛል።
⏺የወንዙ ታሪክም እንደ ውበቱ ጥልቅ ነው። በ14ኛው ክፍለ ዘመን በተጻፈው የጋድለ ተክለሃይማኖት ድርሳን ውስጥ መጠቀሱ የወንዙን ጥንታዊነት ሲያረጋግጥ፣ እንደ ፔድሮ ፓዜ ያሉ የመጀመሪያዎቹ አውሮፓውያን ሚስዮናውያን የወንዙን ግርማ አይተው መደመማቸው በታሪክ ተመዝግቧል።
⏺ዛሬ ግን ጀማ የወሬ እና የታሪክ ብቻ ሳይሆን የልማትም ተምሳሌት እየሆነ ነው። በአሁኑ ወቅት ከለሚ - ጀማ ወንዝ የሚዘረጋው የ5.1 ቢሊየን ብር የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ ግንባታ፣ ለዘመናት በትራንስፖርት እጥረት ተገልሎ የቆየውን ይህን ለም ምድር ከገበያ ማዕከላት ጋር የሚያስተሳስር ወሳኝ ድልድይ ነው። መንገዱ የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርቶችንም ሆነ የአካባቢውን የግብርና ውጤቶች ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለማድረስ ትልቅ አቅም ይፈጥራል።
⏺ባጠቃላይ ጀማ ወንዝ ያለፈውን ታሪክ፣ የአሁኑን ተፈጥሯዊ ውበት እና የወደፊቱን የኢኮኖሚ ተስፋ አቅፎ የያዘ የኢትዮጵያ ሀብት ነው። ይህን ወንዝ ተሻግሮ የሚገነባው ዘመናዊ መንገድም፣ የጀማን ውበት ለዓለም ከማሳየት ባለፈ ለአካባቢው ህዝብ የብልጽግና በር እንደሚከፍት ጥርጥር የለውም።
@etconp

15,782 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የጀማ ተፋሰስ፣ ከመሬት በታች ካለው የጁራክቲክ የድንጋይ ንጣፍ እስከ ላይኛው የእሳተ ገሞራ ዓለት ድረስ ያለውን የተፈጥሮ ምስጢር ለብሶ ይፈሳል።
⏺የጀማ ውበት የሚገለጠው በተለዋዋጭ ባህሪው ነው። በክረምት ወራት ወንዙ የኃይል እና የቁጣ ተምሳሌት ይመስላል፤ እንደ ገደል ናዳ እየተወረወረ፣ ለም አፈሩን እየገመሰ እና ድንጋዮችን እየናደ በቀይ አፈር ተለብሶ ይጓዛል።
በዚህ ወቅት ጀማ ግርማ ሞገሱ ያስፈራል፤ ድምጹም ያጓራል። ሆኖም ክረምቱ አልፎ መስከረም ሲጠባ ጀማ ራሱን ይለውጣል። ያ የቆሸሸ የሚመስለው ወንዝ ወደ ወተት ነጭነት፣ ቆይቶም ወደ ኩል መሳይ ጥራት ተቀይሮ በአካባቢው ተራራዎች መካከል እንደ ውብ ጌጥ ያበራል። ይህ ተለዋዋጭ ባህሪው ጀማን ሁልጊዜም አዲስ፣ ሁልጊዜም ማራኪ ያደርገዋል።
⏺የወንዙ ታሪክም እንደ ውበቱ ጥልቅ ነው። በ14ኛው ክፍለ ዘመን በተጻፈው የጋድለ ተክለሃይማኖት ድርሳን ውስጥ መጠቀሱ የወንዙን ጥንታዊነት ሲያረጋግጥ፣ እንደ ፔድሮ ፓዜ ያሉ የመጀመሪያዎቹ አውሮፓውያን ሚስዮናውያን የወንዙን ግርማ አይተው መደመማቸው በታሪክ ተመዝግቧል።
⏺ዛሬ ግን ጀማ የወሬ እና የታሪክ ብቻ ሳይሆን የልማትም ተምሳሌት እየሆነ ነው። በአሁኑ ወቅት ከለሚ - ጀማ ወንዝ የሚዘረጋው የ5.1 ቢሊየን ብር የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ ግንባታ፣ ለዘመናት በትራንስፖርት እጥረት ተገልሎ የቆየውን ይህን ለም ምድር ከገበያ ማዕከላት ጋር የሚያስተሳስር ወሳኝ ድልድይ ነው። መንገዱ የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርቶችንም ሆነ የአካባቢውን የግብርና ውጤቶች ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለማድረስ ትልቅ አቅም ይፈጥራል።
⏺ባጠቃላይ ጀማ ወንዝ ያለፈውን ታሪክ፣ የአሁኑን ተፈጥሯዊ ውበት እና የወደፊቱን የኢኮኖሚ ተስፋ አቅፎ የያዘ የኢትዮጵያ ሀብት ነው። ይህን ወንዝ ተሻግሮ የሚገነባው ዘመናዊ መንገድም፣ የጀማን ውበት ለዓለም ከማሳየት ባለፈ ለአካባቢው ህዝብ የብልጽግና በር እንደሚከፍት ጥርጥር የለውም።
የፕሮጀክቱ ዋና ዋና መረጃዎች
• ጠቅላላ በጀት፦ 5.1 ቢሊየን ብር።
• የመንገዱ ርዝመት፦ 20 ኪሎ ሜትር።
• የግንባታው ዓይነት፦ ሲሚንቶ ኮንክሪት (Cement Concrete)።
• የሥራ ተቋራጭ፦ ህብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን።
• የግንባታ ጊዜ፦ 1 ዓመት።
• የመንገዱ ስፋት፦ በገጠር ከ8-10 ሜትር፣ በከተማ 15 ሜትር።
@etconp
❤11
✈️ Runway Markings – Key Points
- Runway Centerline:
- Dashed white line along the middle of the runway
- Guides aircraft during takeoff and landing
- Threshold Markings:
- Series of white longitudinal stripes
- Indicates the beginning of the usable runway for landing
- Touchdown Zone:
- Markings located just beyond the threshold
- Helps pilots aim for a safe landing area
- Aiming Point Markings:
- Two thick white rectangles further down the runway
- Visual target for pilots during approach
- Edge Markings:
- Solid white lines along both sides of the runway
- Define the lateral limits of the runway surface
- Blast Pad:
- Yellow-marked area at the end of the runway
- Not used for takeoff or landing; absorbs jet blast
- Runway Designation ("13 R"):
- Indicates magnetic heading (130°)
- “R” means it’s the right runway in a parallel configuration.

❤6👍3
👉The primary purpose of the arches in bridge construction is to support the bridge deck and its loads by efficiently transferring weight to the supports at either end, known as abutments.
🏷Here is how the arch achieves this:
📌Load Transfer: Unlike beam bridges that push loads straight down, an arch transfers the vertical weight of the bridge and its loads both outward and downward to the abutments.
📌 Compression: The arch shape is a curved structure that converts vertical pressure into horizontal thrust, which is then resisted by the strong abutments on either side.
📌 Stability and Strength: This design allows arch bridges to span greater distances than simple beam bridges while using less material and providing significant strength and durability.
📌 Versatility: Depending on the design, the arch can be above or below the roadway.
In a deck arch bridge (like the one pictured, the area between the deck and arch is called the spandrel.

❤8
#ADVERTISEMENT
Ab Con General Waterproofing Works
የውሃ አቅርቦትዎን በከፍተኛ ደረጃ ለመጨመር በፋይበርግላስ የውሃ ማጠራቀሚያ ሴፕቲክ ታንክ ስርዓታት ይጠቀሙ !!!
◇ በፋይበርግላስ የተሰራ የውሃ ሴፕቲክ ታንክ በጉድጓድ ዉስጥ ከሚመጣ የሽንት ቤት ፍሳሾች ሙሉ ለሙሉ የተከለለ ስለሚሆን ለዉሀ ብክለት አስተማማኝ ነዉ ።
◇በፋይበርግላስ የተሰራ የውሃ ሴፕቲክ ታንክ መበስበስ እና መሰነጣጠቅ የሚባል ነገር ፈፅሞ አይታሰብም።
◇በፋይበርግላስ የተሰራ የውሃ ሴፕቲክ ታንክ ለማፅዳት በቀላሉ የሚመች ሲሆን ፣ በዉሀ ዉስጥ በፍጥነት ለሚራባዉ አልጌ ደግሞ ፈፅሞ የማይመች ነዉ ።
◇በፋይበርግላስ የተሰራ የውሃ ሴፕቲክ ታንክ ከመሬት በታች በጉድጎድ ዉስጥ ስለሚሰራ ቦታ ቆጣቢ ነዉ።
◇ለመዋኛ ገንዳ
◇ ለመኖሪያ ቤቶች ፣፤ሪል እስቴቶች ፤ድርጅቶች ፤ሆስፒታሎች፥ ሆቴሎች ፥ ኤምባሲዎች፥የእርሻ ቦታዎች ፥ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወዘተ የኛ ተጠቃሚዎች ናቸዉ።
🤳0913967277
0968966602

❤3👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉አሁናዊ ኪነህንጻ
💫ዘምዘም ባንክ
🚧ነዳፊ: እስክንድር አርክቴክትስ
⏺ዘምዘም ባንክ ብሄራዊ ባንክ አጠገብ በተረከበው ቦታ የሚያስገነባው የዋና መስሪያቤት ንድፍ ስራ ተጠናቋል።
🔰በ 4135 ሜ.ካ ላይ ያረፈው ባለ 31 ፎቅ ክፍታ ያለው ህንጻ ሲሆን 1 ታችኛው ወለል ፣ 5 ምድር ቤት ፣ ሙዚየም ፣ የመስገጃ ቦታ ፣ የስብሰባ አዳራሽ ፣ ቢሮዎች ፣ ቦርድ ሩም ፣ ሬስቶራንት ፣ 324 መኪኖችን ማቆም የሚችል ፓርኪንግ እና የዘምዘም ባንክ ቅርንጫፍ መክፈቻ ቢሮ ያካትታል ፡፡
Via ዘምዘም ባንክ

❤13
👉ፕሮጀክቶችን የሚያጓትቱ ኮንትራክተሮች በሕግ ተጠያቂ ሊሆኑ ነው
🚧በሐገር አቀፍ ደረጃ 170 ፕሮጅክቶች ግንባታ ላይ ናቸው ተብሏል
💫የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ በቸልተኝነት ምክንያት እንዳይጠናቀቁ በሚያደርጉ ኮንትራክተሮች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።
የአስተዳደሩ የኮሙኒኬሽን ቡድን መሪ ዶክተር አስራት አሳሌ ለአሐዱ ሬዲዮ እንደተናገሩት፣ ሥራቸውን በአግባቡ በማያከናውኑ አካላት ላይ ኮንትራታቸውን ከማቋረጥ ባለፈ ሕጋዊ ሂደትን በመከተል ተጠያቂ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ወደ 170 የሚጠጉ የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ መሆናቸውን የገለጹት ዶክተር አስራት፣ ከእነዚህ መካከል ዘጠኝ የሚሆኑት መጠናቀቃቸውን አረጋግጠዋል።
ከተጠናቀቁት ፕሮጀክቶች መካከልም ሶዶ፣ ነገሌ ቦረና፣ ጅግጅና እና ድሬዳዋ፣ ጊቤ ወንዝ አካባቢ የተገነቡት ይገኙበታል። የቱሉ ቦሎ-ኬላ መንገድ ደግሞ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል ብለዋል።
ዶክተር አስራት በንግግራቸው የመንገድ ፕሮጀክቶች መጓተት ከኮንትራክተሮች አቅም ውስንነት በተጨማሪ፣ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክልሎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንባታው በተያዘለት ጊዜ እንዳያልቅ ምክንያት መሆናቸውን አብራርተዋል።
የመንገድ ሥራ ጥራትን በተመለከተ አስተዳደሩ የራሱ የሆነ የክትትል ክፍል እንዳለውና በየቦታው ተመድበው ሁኔታውን የሚከታተሉ መሐንዲሶች መኖራቸው ተገልጿል።
የአስተዳደሩ አመራሮችም በየወቅቱ በቦታው ድረስ በመውረድ የመስክ ምልከታ እንደሚያደርጉ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም የጥራት ደረጃውን ለመጠበቅና የግንባታ ፍጥነቱን ለማፋጠን የሚረዳ መሆኑ ተጠቁሟል።
Via Ahadu Radio

❤13👍4
👉 INTERCON Construction Chemicals
● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Wall Putty, Prime Coat
● Concrete Repair Mortar
● Floor hardener, Epoxy
● Grout, Self-level mortar
● Quartz paint, Contextra
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers
● Geotextiles and other construction chemicals and materials
☎️ Tel: 0961955555
🔹 Address 1: Signal road, around
Dinberwa Hospital
🔹 Addres 2: Wellosefer, Infront of
Dani Plaza
● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Wall Putty, Prime Coat
● Concrete Repair Mortar
● Floor hardener, Epoxy
● Grout, Self-level mortar
● Quartz paint, Contextra
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers
● Geotextiles and other construction chemicals and materials
☎️ Tel: 0961955555
🔹 Address 1: Signal road, around
Dinberwa Hospital
🔹 Addres 2: Wellosefer, Infront of
Dani Plaza
❤6🙏1
👉ማሳሰቢያ ለደረጃ አንድ የኮንስትራክሽን እና የአማካሪ ድርጅቶች በሙሉ
መንግስት የሀገራዊ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው እንዲዘምን፣ ብሎም ውጤታማ፣ ዘላቂ እና ተወዳዳሪ ዘርፍ እንዲሆን የሚያስችሉ የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በቅርቡም በሀገር አቀፍ ደረጃ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ኢንሽየቲቭ ፍኖተ ካርታን ይፋ አድርጎ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡
በዚህም የዘርፉን ማነቆዎች በመለየትና በመፍታት ለሀገራዊ ዘላቂ ልማት የላቀ ሚና የሚጫወት፣ ለዘርፉ ተዋናዮች ምቹ እና ተወዳዳሪ የሆነ የኮንስትራክሽን ዘርፍ እውን እንዲሆን በሚደረገው ርብርብ መላው የዘርፉን ቤተሰቦች ተደማሪ ተሳትፎ ወሳኝ ያደርገዋል፡፡
ከዚህ አንጻር የዘርፉን ሀገራዊ ዓላማ ለማሳካት ከሚያስችሉ ጉዳዮች መካከል የአገራችን ደረጃ-1 የግንባታ ኩባንያዎችን እና ደረጃ አንድ አማካሪ ደርጅቶችን ያላቸዉን አቅም መግምገም እንዲቻል የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በቁጥር 02/መ34/0289/18 በቀን 18/05/2018 የመጠየቂያ ቅጽ በማያያዝ በደብዳቤ ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም እስካሁን ምላሽ በመስጠት ረገድ ሙያዊ እና ስነምግባራዊ ሃላፊነታቸውን የተወጡት ጥቂቶች ናቸው፡፡
በመሆኑም ይህ መረጃ ከተለቀቀበት ጥር 27/2018 አንስቶ እስከ የካቲት 10/2018 ዓ.ም ድረስ የመጠየቂያ ቅጹን በመሙላት አዋሬ አደባባይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን መስሪያ ቤት ስምንተኛ ፎቅ ላይ ለግንባታ ቁጥጥር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ቢሮ እንድታቀርቡ በድጋሚ እየጠየቅን ይህ ሳይሆን ቢቀር ለሚፈጠሩ የአሰራር ክፍተቶች ኃላፊነቱና ተጠያቂነቱ በሂደቱ ያልተሳተፋችሁ ድርጅቶች ላይ እንደሚሆን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን

❤4👍3
ADVERTISMENT
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)
🔅 የተለያዩ [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።
♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።
☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1
አድራሻ፦ ቁ 1.መርካቶ
ቁ.2 አየር ጤና ኪዳነ ምህረት
ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።

👉ኢንሰቲትዩቱ ዘርፉ በቴክኖሎጂ ማስደገፍ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
▶️ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ተወዳዳሪ እንድሆኑ ለማስቻል የዘርፉን ቴክኖሎጂዎች በተሻለ መልኩ በመምረጥ፣ በመገምግምና በማሸጋገር እንድሁም ቴክኖሎጂውን በተሻለ መልኩ በማሰራጨት በኢንዱስትሪው ጥቅም ላይ እንድውሉ እና ይህኑ የሚደግፍ መመሪያዎችና አሰራር ሥርዓቶችን ለመቅጽ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ከRising Hongfa ኃላፊነቱ የተወሰነ አ.ማ ጋር ተፈራርሟል፡፡
📝📓በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት በኢንስቲትዩቱ የአቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ቅድስት ማሞ ሲሆኑ፣ ባደረጉት ንግግርም ኢንስቲትዩቱ የዘርፉን ተዋናዮች አቅም ከመገንባት፣ ችግር ፈችና ለፖሊሲ ግብዓትነት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ጥናትና ምርምሮችን ከማድረግ በተጨማሪ ለዘርፉ ተወዳዳሪነትና ውጤታማነት ፋይዳ ያላቸውን ቴክኖሎጂዎችን በመለዬትና ውጤታማነታቸውን በማረጋገጥ በኢንዱስትሪው ጥቅም ላይ እንድውሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ሲሰራ መቆየቱን ተናግሯል፡፡
✴️ ይህም የመግባቢያ ሰነድ ይህንኑ በተሻለና በተቀናጀ መልኩ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ኢንዱስትሪው በማሸጋገር ዘርፋ በማህበረ-ኢኮኖሚ ዕድገት መጫወት የሚገባውን ሚና እንድጫወት አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡
✴️ አክስዮን ማህበሩን በመወከል ንግግር ያደረጉት አቶ አመንቴ ዳድ ሲሆኑ፣ በንግግራቸውም አክስዮን ማኅበሩ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የአክስዮን ድርሻነት የተቋቋመ መሆኑን በማስገንዘብ፣ የተቋቋመበት ዓላማም ኢንዱስትሪው የሚጠቀማቸውን ከፍተኛ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ለኢንዱስተሪው የማስተዋወቅና የማሸጋገር እንድሁም በዘርፉ ጥቅም ላይ እንድውሉ ዓላማ አድርጎ የሚሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ከኢንስቲትዩቱ ጋር የተደረገው የመግባቢያ ስምምነት ፊርማ ቴክኖሎጂዎችን በተደራጀና ቀጣነት ባለው መልኩ እንድሸጋገሩ ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
✴️ በዚህ መግባቢያ ሰነድ ላይ እንደተገለጸው ኢንስቲትዩቱ ቴክኖሎጂዎችን ከመምረጥ ቴክኖሎጂዎቹን፣ ከማሸጋገርናማሰራጨት በስልጠና ዎርክሾፖችን በማዘጋጀት፣ የኢንዱስትሪው ተዋናዮች የግንዛቤ የማስጨበጥ እና በመሳሰሉት ረገድ ተቋማዊና ቴክንካዊ ድጋፍ የማድርግ እንድሁም Rising Hongfa ኃላፊነቱ የተወሰነ አ.ማ በበኩሉ የቴክኖሎጂ ማሸጋገሩንና ማሰራጨቱን በገንዘብና በቴክንክ የመደገፍ፣ በኢንዱስትሪው ቴክኖሎጂዎቹን የማላመድ፣ የክትትልና የመቆጣጠር እና የመሳሰሉት ኃላፊነቶች ተጥሎበታል፡፡
✴️ በአጠቃላይ ሁለቱም ተቋማት ለኢንዱስትሪው ተወዳዳሪነትና ውጤታማነት የበኩላቸውን ሚና በጋራ ለመወጣት የተቀናጁ መሆናቸውን በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡

❤9
“በ57 ሕጋዊ ሰውነት ባላቸው ማህበራት ተደራጅተው፣ የሚጠበቅባቸውን 25 በመቶ ቅድመ ቁጠባ (ወደ 4 ቢሊዮን ብር ገደማ) ለቆጠቡ 6,194 መምህራን፤ ወቅታዊ አማካይ ዋጋው 24 ቢሊዮን ብር የሚገመት ከሊዝ ነፃ 40 ሄክታር መሬት በማቅረብ፣ 5 ቢሊዮን ብር የካሳ ክፍያ በመፈፀም እና የ25/75 የፋይናንስ አማራጭን በማመቻቸት፣ የመኖሪያ ቤት ግንባታን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረናል።”
Via ከንቲባ አዳነች አቤቤ
@etconp
Via ከንቲባ አዳነች አቤቤ
@etconp
❤5
የከተማ ቦታ ህግ final-land-lease-regulation.pdf
550.5 KB
የከተማ ቦታን በሊዝ ለማስተዳደር እንዲያስችል የተዘጋጀ ረቂቅ
ሞዴል ደንብ ቁጥር------/2004 (እንደተሻሻለው)
https://t.me/ETCONpWORK
@etconp
ሞዴል ደንብ ቁጥር------/2004 (እንደተሻሻለው)
https://t.me/ETCONpWORK
@etconp
❤2
❤4👏1