Ethio Construction Engineering
32.4K subscribers
6.23K photos
359 videos
1.99K files
3.2K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉ምርጥ 120 ካሬ ላይ የሚያርፍ የመኖርያ ቤት ሙሉ ዲዛይን የምትፈልጉ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱ👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a62fd7b49a15_etconp
👏5😭2❤1
🏗 የሲቪል ኢንጂነሪንግ ቋሚ እና አስፈላጊ ምህፃረ-ቃላት (Top 50 Civil Engineering Abbreviations)

​ለግንባታ፣ ለዲዛይን እና ለኢንጂነሪንግ ባለሙያዎች እንዲሁም ተማሪዎች በስራ ሰዓት በቀላሉ ሊያገኟቸው የሚገቡ 50 ዋና ዋና የሲቪል ኢንጂነሪንግ አህጽሮተ ቃላት (Abbreviations) ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፦

​🔹 የቁሳቁስ እና የኮንክሪት ዝግጅት

(Materials & Concrete)
​RCC – Reinforced Cement Concrete
​PCC – Plain Cement Concrete
​OPC – Ordinary Portland Cement
​PPC – Portland Pozzolana

Cement
​PSC – Portland Slag Cement
​AAC – Autoclaved Aerated

Concrete
​TMT – Thermo-Mechanically

Treated Steel
​CM – Cement Mortar
​BM – Bench Mark
​TBM – Temporary Bench Mark

​🔹 የንባብ፣ ስራ አስኪያጅ እና የዕቅድ ቃላት (Planning & Management)

​BOQ – Bill of Quantities
​BBS – Bar Bending Schedule
​QA – Quality Assurance
​QC – Quality Control
​DPR – Detailed Project Report
​GFC – Good for Construction
​RFI – Request for Information
​RFQ – Request for Quotation
​RFP – Request for Proposal
​CPM – Critical Path Method
​PERT – Program Evaluation and Review Technique
​EPC – Engineering, Procurement & Construction
​PMC – Project Management Consultant

​🔹 የመሬት፣ የደረጃ እና የመንገድ ስራዎች (Site, Levels & Roads)

​DPC – Damp Proof Course
​FFL – Finished Floor Level
​NGL – Natural Ground Level
​GL – Ground Level
​RL – Reduced Level
​C/C – Centre to Centre
​C/C Road – Cement Concrete Road
​SBC – Safe Bearing Capacity
​WMM – Wet Mix Macadam
​DBM – Dense Bituminous Macadam
​BC – Bituminous Concrete
​DLC – Dry Lean Concrete

​🔹 መዋቅሮች፣ ንፅህና እና የፍሳሽ ስራዎች (Structures, MEP & Utilities)

​MEP – Mechanical, Electrical & Plumbing
​HVAC – Heating, Ventilation & Air Conditioning
​SWD – Storm Water Drain
​STP – Sewage Treatment Plant
​ETP – Effluent Treatment Plant
​UGWT – Underground Water Tank
​OHWT – Overhead Water Tank
​FOB – Foot Over Bridge
​ROB – Road Over Bridge
​RUB – Road Under Bridge

​🔹 የዲዛይን እና የደረጃ መመሪያዎች (Design, Codes & Standards)

​IS – Indian Standard
​IRC – Indian Roads Congress
​NBC – National Building Code
​CAD – Computer-Aided Design
​BIM – Building Information Modeling

​🌐 ለተጨማሪ መረጃ እና ሌሎች የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዜናዎች የ YouTube ገፃችን ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp
❤19👏2🔥1
👉ድምፃችን ተሰምቷል🙏

የታሪካዊውን ክቡ የንግድ ባንክ የፊት ገፅታን በእጅጉ የሚጎዳው ግንባታን ተከትሎ ያሰማነው ጩኸት ተሰምቶ በአሁኑ ሰዓት ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተነስቷል።

ይህን መልዕክት እያስተላለፍኩ ያለሁት በአሁኑ ደቂቃ እዚያው ሕንፃው አጠገብ ሆኜ ነው።

የተቃውሞ ድምፃችንን ማሰማታችንን ተከትሎ ከጎናችን የቆማችሁትን፣ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፣ ልጥፎችን ሪአክት በማድረግ፣ በኮመንትና ሼር በማድረግ የተባበራችሁትን በሙሉ ከልብ እናመሠግናለን።

የሕዝብን ቅሬታ ተከትሎ ለግንባታው መፍረስ ግንባር ቀደም ሚናውን የተጫወተው በኢ/ር ሕይወት ሳሙኤል ዋና ዳይርክተር የሚመራው የአዲስ አበባ ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ስለመሆኑ መረጃው ደርሶናል፣ ከልብ እናመሠግናለን!

እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ከግንባታ ፈቃድ ቁጥጥር ባለሥልጣን ጋር በመሆን ድምፃችን በመስማቱ ምሥጋናችን የላቀ ነው!።

ምንጭ ጌታሁን ሔራሞ

@etconp
👍17❤7👏6
👉የ Isolated Footing ዲዛይን ለማረግ የሚረዳ እንዲሁም ስራቹ  የሚያቀልላቹ ምርጥ Excel ፋይል ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ አውርደው ይጠቀሙ👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a5f6b3b1c816_etconp
❤3👏3
Engineering Formula.pdf
1.1 MB
👉በጣም ጠቃሚ ኢንጅነሪንግ ቀመሮች

​🌐 ለተጨማሪ መረጃ እና ሌሎች የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዜናዎች የ YouTube ገፃችን ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp
👏6❤2
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ

Rent Control and Administration Proclamation

በአዲስ አበባ ከተማ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረው የመኖሪያ ቤት አከራይ ተከራይ ውል እድሳት ጋር ተያይዞ በመነሳት ላይ ያለው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ፤

ይህ አዋጅ ተፈፃሚ የሚሆነው ተጠሪነታቸው ለክልል በሆኑ ከተሞች፣ በአዲስ አበባ እና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ላይ በሚፈፀም የመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ ሲሆን ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ አዋጁ በሌሎች ከተሞች ላይ ተፈፃሚ ሊሆን ስለሚችልበት ሁኔታ ክልሎች ነባራዊ ሁኔታውን እያዩ እንደሚወስኑ አዋጁ ያስቀምጣል።

በተጨማሪም አዋጁ ተፈፃሚ ከሚሆንበት ሁኔታ ውጪ ተፈፃሚ የማይሆንበት ሁኔታ ተመለከቷል።

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል የኪራይ ዘመኑ ሳይጠናቀቅ በአከራዩና ተከራዩ ስምምነት፣ ተከራይ ቤቱን መልቀቅ ሲፈልግ የሁለት ወር የቅድሚያ ማስታወቂያ በመስጠት ወይም የቤት ባለቤትነት በሕጋዊ መንገድ ለሌላ ሰው ሲተላለፍ የ6 ወር ማስጠንቀቂያ በመስጠት ሊቋረጥ ይችላል።

እነኚህ ውሉ በማስጠንቀቂያ የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች ሲሆኑ ውሉ ያለማስጠንቀቂያ የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች ደግሞ በአንቀጽ 16 ስር ተዘርዝረው ይገኛሉ።

@etconp
❤2
የኢትዮጵያን የሪል እስቴት ገበያ ለአለም አቀፍ ኢንቨስተሮች የሚያስተዋውቅ አዲስ ስምምነት ተፈረመ!

የኢትዮጵያ ሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር (EREDA) እና ዶክሳ ቢዝነስ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ. በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍን በሀገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ለማጠናከር የሚያስችሉ ሁለት ስትራቴጂካዊ የመግባቢያ ሰነዶችን በዛሬዉ እለት  ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱ የሪል እስቴት ዘርፉን ትብብር ለማሳደግ፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስፋፋት እንዲሁም የዲያስፖራውን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጻል፡፡

በስምምነቱ መሠረት በሀገር ውስጥ የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበርን ተቋማዊ አቅም ማጠናከር፣ የአባልነት መስፋፋትን መደገፍ፣ በመንግስት እና በግል ዘርፍ መካከል ያለውን ትብብር ማሳደግ እና የዕውቀት ልውውጥ መድረኮችን በጋራ ማዘጋጀት ዋና ዋና ትኩረቶች ሲሆኑ  በዚህም ዶክሳ ቢዝነስ ትሬዲንግ ለተመረጡ መርሃግብሮች የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር (EREDA) ተመራጭ የኢቨንት አስተባባሪ አጋር ሆኖ እንደሚሰራም ነዉ የተገለፀዉ።

በሌላ በኩል ስምምነቱ የዲያስፖራ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት እና የውጭ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ ያለመ ሲሆን፣ የመጀመሪያዎቹ አለም አቀፍ የሪል እስቴትና ኢንቨስትመንት ትስስር ፕሮግራሞች በሪያድ (ሳውዲ አረቢያ)፣ በጆሃንስበርግ (ደቡብ አፍሪካ) እና በእስራኤል እንደሚካሄዱ ተጠቅሷል፡፡

ሁለቱ ተቋማት ቀደም ሲል እንደ "Addis Africa Real Estate Expo 2026" ያሉ ትልልቅ መድረኮችን በጋራ ማዘጋጀታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በቀጣይም የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች በግልጽነት እና በተጠያቂነት መመሪያዎች የሚመሩ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ዶክሳ ቢዝነስ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ. በቢዝነስ ልማት፣ በስትራቴጂካዊ ግንኙነት፣ በኢቨንት ማስተባበር፣ በማርኬቲንግ ኮሙኒኬሽን እና በባለድርሻ አካላት ትስስር ላይ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን፣ ቢዝነሶችን፣ ባለሀብቶችን፣ መንግስታዊ ተቋማትን እና ማህበረሰቡን የሚያገናኙ ዘላቂና ፈጠራ ያላቸው መድረኮችን በመፍጠር ለኢኮኖሚያዊና ለኢንዱስትሪ ልማት አስተዋፅኦ ያደርጋል::

Via Fast Mereja

@etconp
❤7👍4🔥2
የሳምንቱ ዓለም አቀፍ ኮንስትራክሽን ዳሰሳ

በዚህ ሳምንት በአለም አቀፍ የኮንስትራክሽን, የሕንፃ ዲዛይን እና የኢንጂነሪንግ ዘርፍ የተከናወኑ ዋና ዋና እና አዳዲስ መረጃዎችን እንደሚከተለው አሰናድተናል፡-

​1. አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች እና አረንጓዴ ኮንስትራክሽን

​የካርቦን ልቀት ቅነሳ በሲሚንቶ ኢንዱስትሪ: የአለም ትልልቅ የኮንስትራክሽን ግብዓት አምራቾች የካርቦን ልቀትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ አዳዲስ የስነ-ምህዳር ተስማሚ (Eco-friendly) የሲሚንቶ አማራጮችን በስፋት ወደ ገበያ እያስገቡ ይገኛሉ።

​ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በቦታ ቁጥጥር: አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የያዙ ድሮኖች እና ካሜራዎች የፕሮጀክቶችን ሂደት በሰዓት ሰዓት እየተቆጣጠሩ፣ ሊፈጠሩ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ በመተንበይ የደህንነት ደረጃውን ከፍተኛ ስፍራ እያደረሱት ይገኛሉ።

​2. ታላላቅ ዓለም አቀፍ ፕሮጀክቶች
​የመዋቅር እና የዲዛይን ዕድገቶች:

በመካከለኛው ምስራቅ እና በእስያ እየተገነቡ ያሉት ግዙፍ የከተማ ልማት ፕሮጀክቶች ዘመናዊ የብረት እና የብርጭቆ ውህደት ዲዛይኖችን በመጠቀም የዓለምን ትኩረት ስበዋል።

​ዘላቂ የኢነርጂ ግንባታዎች: ህንፃዎች ራሳቸውን ከፀሐይ እና ከንፋስ ኃይል ኤሌክትሪክ ማመንጨት እንዲችሉ ተደርገው የሚገነቡባቸው ፕሮጀክቶች በዚህ ሳምንት ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆረዋል።

​💡 ጠቃሚ ምክር: በኮንስትራክሽን ዘርፍ ስኬታማ ለመሆን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና የቁሳቁስ ጥራትን መቀበል ወሳኝ ነው።

​🔗 ተጨማሪ መረጃዎችን እና የዘርፉን ትኩስ ዜናዎች ለማግኘት ሌላኛው የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ!

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤5🔥1👏1
2. To convert the units of M.K.S. to units of S.I., a factor 9.80665 is used for
Anonymous Quiz
28%
A. mass
26%
B. force
9%
C. work energy
5%
D. power
31%
E. all the above
🥰4👍3❤2
3. In a mortar, the binding material is
Anonymous Quiz
90%
A. cement
5%
B. sand
2%
C. Aggregate
3%
D. cinder.
👍5❤2🎉1
5. The initial setting time of lime-pozzolana, is
Anonymous Quiz
67%
A. 30 minutes
16%
B. 60 minutes
6%
C. 90 minutes
11%
D. 120 minutes.
🎉5🔥2❤1
👉ደረጃ (Stair Case) ስትራክቸራል ዲዛይኑ በቀላሉ ለመስራት ከታች ባለው ሊንክ ማውረድ ይችላሉ👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a664a8fafe65_etconp
👌3😭2
#ADVERTISEMENT

🏗 Still preparing Bill of Quantities (BOQ) manually?
የስራ ዝርዝር ለማዘጋጀት ምን ያህል ጊዜ ይወስድቦታል?

AddisBOQ prepares your BOQ and cost estimate in minutes.
✔ BOQ & cost estimation for Ethiopian rates, for multiple cities
✔ Rebar wastage optimizer (የብረት ብክነት መቆጣጠሪያ)
✔ Daily site log for project records
📱 Website & Android app
👉 AddisBOQ.com
✈️ Join our Telegram channel: @AddisBOQ
❤7👍3🔥1
👉የወቅቱ የዝናብ እጥረት በድንገት ሳይታሰብ ሊከሰት ከሚችል የጎርፍ አደጋ ወይም ውድመት ለመከላከል እንደግልም ሆነ እንደ መንግስት አፅንኦት ሊሰጠው የሚገባ ተግባር የጎርፍ መቆጣጠሪያ (Flood Control) አቅዶ መስራት ተገቢ ነው ፅሁፌን ከወደዳቹት ሼር አድርጉት።

⭐️የጎርፍ መቆጣጠሪያ (Flood Control) ምንድን ነው?

✅ የጎርፍ መቆጣጠሪያ ማለት ጎርፍ በሰዎች ሕይወት፣ በንብረት፣ በመሠረተ ልማቶች፣ በግብርናና በአካባቢ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚደረጉ የምህንድስና (Structural) እና የአስተዳደር (Non-Structural) እርምጃዎችን በእቅድ፣ በዲዛይን፣ በግንባታ፣ በአስተዳደርና በጥገና በተቀናጀ ሁኔታ መተግበር ነው።

👉 የጎርፍ መቆጣጠሪያ ዋና ዓላማው ጎርፍን ፈጽሞ ማጥፋት ሳይሆን የጎርፍ አደጋን ተቀባይነት ባለው ደረጃ መቀነስና የሰው ሕይወትን፣ ንብረትን እና ተፈጥሯዊ ሀብቶችን መጠበቅ ነው።

ጎርፍ ማለት ወንዞች፣ ሸለቆዎች፣ ሐይቆች፣ የዝናብ ማስወገጃ ስርዓቶች ወይም የውኃ ማከማቻዎች አቅማቸውን ሲያልፍ ውኃው ወደ መሬት በመውጣት የሚፈጠር የተፈጥሮ ክስተት ነው።

✅ የጎርፍ መቆጣጠሪያ ዓላማዎች
▢ የሰው ሕይወትን መጠበቅና ጉዳትን መቀነስ።
▢ ቤቶችን፣ መንገዶችን፣ ድልድዮችን፣ ፋብሪካዎችንና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን መጠበቅ።
▢ የእርሻ መሬቶችንና እንስሳትን ከጎርፍ መከላከል።
▢ በጎርፍ የሚደርስ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ መቀነስ።
▢ የመጓጓዣና የመገናኛ አገልግሎቶችን ማስቀጠል።
▢ የውኃ አቅርቦትና የፍሳሽ ስርዓቶችን መጠበቅ።
▢ የአፈር መሸርሸርን እና የደለል ክምችትን መቀነስ።
▢ የተፈጥሮ ሥነ-ምህዳሮችን መጠበቅ።
▢ ከየአየር ንብረት ለውጥ የሚመጡ አደጋዎችን መቋቋም።
▢ የውኃና የመሬት ሀብትን በዘላቂነት ማስተዳደር።

✅ የጎርፍ መንስኤዎች
▢ ከፍተኛና ረጅም ጊዜ የሚዘንብ ዝናብ።
ወንዞች የመሸከም አቅማቸውን ሲያልፉ።
▢ ፈጣን ጎርፍ (Flash Flood)።
▢ የግድብ ወይም የግርጌ መከላከያ መፍረስ።
▢ ደካማ የከተማ የዝናብ ውኃ ማስወገጃ ስርዓት።
▢ የባህር ማዕበልና ከፍተኛ ማዕበል (Storm Surge)።
▢ ፈጣን የበረዶ መቅለጥ።
▢ የአየር ንብረት ለውጥ።

✅የጎርፍ ዓይነቶች
1. የወንዝ ጎርፍ (River Flood)
ወንዞች ከዳርቻቸው በላይ ሲፈስሱ የሚከሰት ጎርፍ።

2. ፈጣን ጎርፍ (Flash Flood)
በአጭር ጊዜ ከባድ ዝናብ በመዝነብ የሚፈጠር፣ በጣም አደገኛ የሆነ ጎርፍ።

3. የከተማ ጎርፍ (Urban Flood)
የዝናብ ውኃ ማስወገጃ ስርዓት በቂ ካልሆነ ወይም ከተዘጋ የሚፈጠር ጎርፍ።

4. የባህር ዳርቻ ጎርፍ (Coastal Flood)
በማዕበል፣ በከፍተኛ ማዕበል ወይም በባህር ውኃ ከፍ መሆን የሚከሰት።

5. የመሬት ውስጥ ውኃ ጎርፍ (Groundwater Flood)
የመሬት ውስጥ ውኃ ከፍ ብሎ ወደ መሬት ገጽ ሲወጣ የሚፈጠር።

✅ የጎርፍ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች
1. የምህንድስና (Structural) መፍትሔዎች
▢ ግድቦችና የውኃ ማከማቻዎች (Dams and Reservoirs)
▢ የወንዝ ግርጌ መከላከያዎች (Levees and Embankments)
▢ የጎርፍ መከላከያ ግድግዳዎች (Floodwalls)
▢ የውኃ ማስቀየሪያ ቻናሎች (Diversion Channels)
▢ የጎርፍ ማቆያ ገንዳዎች (Retention and Detention Basins)
▢ የወንዝ ቻናል ማሻሻያ (Channel Improvement)
▢ የዝናብ ውኃ ማስወገጃ ስርዓቶች (Stormwater Drainage)
▢ ቼክ ዳሞች (Check Dams)
▢ የወንዝ አቅጣጫ መቆጣጠሪያ ሥራዎች (River Training Works)

2. የአስተዳደር (Non-Structural) መፍትሔዎች
▢ የጎርፍ ትንበያ (Flood Forecasting)
▢ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት (Early Warning System)
▢ የጎርፍ ሜዳ አጠቃቀም እቅድ (Floodplain Zoning)
▢ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ (Land Use Planning)
▢ የተፋሰስ አስተዳደር (Watershed Management)
▢ የሕዝብ ግንዛቤ ማሳደግ
▢ የጎርፍ መድን (Flood Insurance)
▢ የጎርፍ አደጋ ግምገማ

✅ የጎርፍ ቁጥጥር ሲታቀድ የሚገመገሙ ነገሮች፦
▢ የዝናብ መጠንና ጥንካሬ
▢ የወንዝ ፍሰት
▢ የተፋሰሱ ባህሪ
▢ የአፈር ዓይነት
▢ የመሬት አጠቃቀም
▢ የመሬት ቁልቁለት
▢ የቀድሞ የጎርፍ መረጃዎች
▢ ለአደጋ የተጋለጠ ሕዝብ
▢ የመሠረተ ልማት ተጋላጭነት
▢ በሃይድሮሎጂ የሚታዩ መርሆዎች
▢ የዝናብ–ፍሰት ግንኙነት
▢ ከፍተኛ ፍሰት (Peak Discharge)
▢ የመሰብሰቢያ ጊዜ (Time of Concentration)
▢ ውኃ ሰርጎ መግባት (Infiltration)
ትነትና የእፅዋት ልቀት (Evapotranspiration)
▢ የመሠረታዊ ፍሰት (Base Flow)
የማከማቻ አቅም
▢ የፍሰት መስመር (Hydrograph) ትንተና
▢ የዲዛይን ዝናብ ትንተና

✅ የእፅዋት ሚና
▶ ውኃ ወደ አፈር እንዲሰርግ ያግዛሉ።
▶ የውኃ ፍሰትን ፍጥነት ይቀንሳሉ።
▶ አፈርን ከመሸርሸር ይጠብቃሉ።
▶ የመሬት ውስጥ ውኃ ማጠራቀምን ያሳድጋሉ።
▶ የተፋሰስ ጤናን ያሻሽላሉ።

✅ በከተሞች ውስጥ የጎርፍ ቁጥጥር
ዘላቂ የዝናብ ውኃ አስተዳደር (SuDS)
▶ ውኃ የሚያስርጉ ንጣፎች
▶ የዝናብ ውኃ መሰብሰብ
▶ አረንጓዴ ጣሪያዎች
▶ የማቆያ ገንዳዎች
▶ የመስረጊያ ቦዮች

✅ መደበኛ የፍሳሽ መስመሮች ጥገና
በኢትዮጵያ የጎርፍ ቁጥጥር
በኢትዮጵያ የጎርፍ ቁጥጥር በተለይ በወቅታዊ ዝናብ፣ በተራራማ ተፋሰሶች፣ በመሬት መራቆት እና በፈጣን የከተማ መስፋፋት ምክንያት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። የሚተገበሩ ዋና ዋና እርምጃዎች የወንዝ ግርጌ መከላከያዎች ግንባታ፣ ግድቦች፣ የተፋሰስ ማሻሻያ፣ የአፈርና ውኃ ጥበቃ፣ ደን ልማት፣ የከተማ የዝናብ ውኃ ማስወገጃ ስርዓቶችና የማህበረሰብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ናቸው።

✅ የጎርፍ ቁጥጥር ጥቅሞች
▢ የሰው ሕይወትን ያድናል።
▢ የንብረት ጉዳትን ይቀንሳል።
▢ የግብርና ምርትን ይጠብቃል።
▢ የአፈር መሸርሸርን ይቀንሳል።
▢ መንገዶችንና ድልድዮችን ይጠብቃል።
▢ ዘላቂ ልማትን ያግዛል።
▢ ከየአየር ንብረት ለውጥ ጋር የመላመድ አቅምን ያጠናክራል።

ተግዳሮቶች
▶ ከፍተኛ የግንባታና የጥገና ወጪ።
▶ የአየር ንብረት ለውጥ።
▶ የደለል ክምችት በግድቦች ውስጥ።
▶ በጎርፍ ሜዳዎች ላይ ያልተቆጣጠረ ሰፈራ።
▶ ደካማ የዝናብ ውኃ ማስወገጃ ጥገና።
▶ የአካባቢ ሥነ-ምህዳር ተፅዕኖዎች።

✅ ማጠቃለያ
▶ የጎርፍ መቆጣጠሪያ የውኃ ሀብት ምህንድስናና የአደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፍ ውስጥ እጅግ ወሳኝ ዘርፍ ነው። ዘላቂና ውጤታማ የጎርፍ አስተዳደር የምህንድስና መፍትሔዎችን (እንደ ግድቦች፣ የወንዝ ግርጌ መከላከያዎች፣ የዝናብ ውኃ ማስወገጃ ስርዓቶችና የጎርፍ ማቆያ ገንዳዎች) ከአስተዳደራዊ መፍትሔዎች (እንደ የጎርፍ ትንበያ፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት፣ የተፋሰስ አስተዳደር፣ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድና የሕዝብ ግንዛቤ ማሳደግ) ጋር በማቀናጀት ሲተገበር ሕይወትን፣ ንብረትን፣ ግብርናን፣ መሠረተ ልማቶችንና ተፈጥሯዊ ሥነ-ምህዳሮችን ከጎርፍ አደጋ በተሻለ ሁኔታ መጠበቅ ይቻላል።

Via Mekamu

@etconp
❤4👏1
🏗️ የQuantity Surveying ሙያን በቤትዎ ኦንላይን ይማሩ!

ይህ ኮርስ ለሲቪል እና ኮንስትራክሽን ኢንጂነሮች፣ አርክቴክቶች፣ ተማሪዎች፣ ተቋራጮች እና በ Quantity Surveying መስክ ሙያቸውን ለማሳደግ ለሚፈልጉ ሁሉ ተዘጋጅቷል።

📢በዚህ ኮርስ የሚማሩት

✅ Quantity Surveying መሠረታዊ መርሆች
✅ Drawing ንባብ (Reading Construction Drawings)
✅ Quantity Takeoff በሙሉ
✅ Bill of Quantities (BOQ) አዘገጃጀት
✅ Material Quantity Calculation
✅ Cost Estimation እና Cost Control
✅ Rate Analysis
✅ Measurement Standards
✅ የተግባር ምሳሌዎች (Real Project Examples)
✅ ፕሮፌሽናል የQS የስራ ሂደት

🎥 ኮርሱ በቀላል አማርኛ በቪዲዮ እና ዶክመንት ፋይሎች የተዘጋጀ ሲሆን በፈለጉት ጊዜ በስልክ ወይም በኮምፒውተር መማር ይችላሉ።

💰 የኮርሱ ዋጋ: 1,999 ብር ብቻ!

🚀 ዛሬውኑ ይመዝገቡ እና የ Quantity Surveying ክህሎትዎን ወደ ሌላ ደረጃ ያሳድጉ!

⭐️ኮርሱ ለመጀመር👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a5e233a9c5e0_etconp
❤8👏5
👉Main abbreviation in civil engineering

1. BBS= Bar Bending Schedule

2. F.O.S= Factor of Safety

3. RCC = Reinforced Cement Concrete

4. PCC = plain cement concrete

5. NDT = Non destructive test

6. DL = Dead load

7. LL = live load

8. UDL = uniformly distributed load

9. FEM = finite element method

10. CAD = computer aided design

🙋 Question 💬

1️⃣. What’s EBCS

2️⃣. what’s BIM stands for

3️⃣. what’s FCR

4️⃣. What’s W/C ratio

5️⃣. What’s FM ?

6️⃣. What’s TMT ?

7️⃣. What’s Fck

8️⃣. What’s HYSD

@etconp
❤12👍1
👉Why Do Roads Develop Potholes?

Potholes form when water enters cracks, weakens the pavement layers, and repeated traffic breaks the damaged surface.

Poor drainage, heavy loads, and aging asphalt accelerate the process.

🔖SUBSCRIBE OUR YOUTUBE👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp
❤10
👉በሃያ አንደኛዉ ክፍለ ዘመን ብቁና አትራፊ ኮንትራክተር መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?

በሃያ አንደኛዉ ክፍለ ዘመን ብቁና አትራፊ ኮንትራክተር መሆን ማለት ከቀድሞው አሰራር ወጥቶ በቴክኖሎጂ፣ በጥራት እና በዘመናዊ  አስተዳደር መመራት ማለት ነው።
​በአሁኑ ሰዓት የኮንስትራክሽን ገበያው እጅግ ተወዳዳሪ እና ፈጣን ለውጥ የሚታይበት ነው። ትናንት የነበረ አሰራር ዛሬ ለኪሳራ ሊዳርግ ይችላል። ታዲያ በዘመኑ አሸናፊ እና ትርፋማ ሆኖ ለመቀጠል ልብ ሊባሉ የሚገቡ ሶስት ዋና ዋና ምሰሶዎች አሉ።

​1. የጥራት እና የጊዜ አጠባበቅ (Quality and Timeliness)
• ​ምን ማለት ነው? ፕሮጀክትን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ፣ በታቀደው ጥራት እና በጀት ማጠናቀቅ ማለት ነው።
• ​ለምን ያስፈልጋል? በኮንስትራክሽን ቢዝነስ ውስጥ ትልቁ የማስታወቂያ መሣሪያህ "የሰራኸው ስም" ነው። ፕሮጀክት በሰዓቱ ሲጠናቀቅ የደንበኛ እምነት ይገነባል፤ ቅጣት እና ተጨማሪ ወጪም ይቀራል።
• ​እንዴት ተግባራዊ ይሆናል? ጥብቅ የሥራ መርሃ ግብር (Work Schedule) በማውጣት፣ በየዕለቱ የሥራ አፈጻጸም በመከታተል እና ጥራቱን የጠበቀ ቁሳቁስ ብቻ በመጠቀም።
• ​ተጨማሪ  ሃሳብ፦ የዘመኑ ኮንትራክተር የጊዜ መዘግየትን አስቀድሞ ለመከላከል እንደ MS Project ወይም Primavera ያሉ የዲጂታል ፕላኒንግ ሶፍትዌሮችን መጠቀም አለበት።

በሃያ አንደኛዉ ክፍለ ዘመን ብቁና አትራፊ ኮንትራክተር መሆን ማለት ከቀድሞው አሰራር ወጥቶ በቴክኖሎጂ፣ በጥራት እና በዘመናዊ  አስተዳደር መመራት ማለት ነው።
​በአሁኑ ሰዓት የኮንስትራክሽን ገበያው እጅግ ተወዳዳሪ እና ፈጣን ለውጥ የሚታይበት ነው። ትናንት የነበረ አሰራር ዛሬ ለኪሳራ ሊዳርግ ይችላል። ታዲያ በዘመኑ አሸናፊ እና ትርፋማ ሆኖ ለመቀጠል ልብ ሊባሉ የሚገቡ ሶስት ዋና ዋና ምሰሶዎች አሉ።

​2. የግብዓት እና የዋጋ አስተዳደር (Cost & Material Management)
• ​ምን ማለት ነው? የግንባታ ግብዓቶችን (ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ወዘተ) ዋጋ መዋዠቅ እየተከታተሉ፣ ወጪን በጥበብ መቆጣጠር እና ማባከንን መቀነስ ማለት ነው።
• ​ለምን ያስፈልጋል? የቁሳቁስ ብክነት እና የዋጋ ግምት ስህተት የብዙ ኮንትራክተሮችን ትርፍ ይበላል። ፋይናንስን በትክክል መያዝ የድርጅቱን ህልውና ያረጋግጣል።
• ​እንዴት ተግባራዊ ይሆናል? ግዢዎችን በጅምላ እና የዋጋ ማስተካከያዎችን አጢኖ በመፈጸም፣ እንዲሁም በግንባታ ቦታ ላይ ያሉ ቁሳቁሶች እንዳይበላሹ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ።
• ​ተጨማሪ  ሃሳብ፦ በግንባታ ቦታ ላይ የሚወጣውን እያንዳንዱን ሳንቲም የሚመዘግብ ዲጂታል የሂሳብ አያያዝ (Digital Accounting System) መጠቀም ለውጤታማነት ቁልፍ ነው።

በሃያ አንደኛዉ ክፍለ ዘመን ብቁና አትራፊ ኮንትራክተር መሆን ማለት ከቀድሞው አሰራር ወጥቶ በቴክኖሎጂ፣ በጥራት እና በዘመናዊ  አስተዳደር መመራት ማለት ነው።
​በአሁኑ ሰዓት የኮንስትራክሽን ገበያው እጅግ ተወዳዳሪ እና ፈጣን ለውጥ የሚታይበት ነው። ትናንት የነበረ አሰራር ዛሬ ለኪሳራ ሊዳርግ ይችላል። ታዲያ በዘመኑ አሸናፊ እና ትርፋማ ሆኖ ለመቀጠል ልብ ሊባሉ የሚገቡ ሶስት ዋና ዋና ምሰሶዎች አሉ።
​
​3. ዲጂታል እይታ እና ማስታወቂያ (Digital Presence)
• ​ምን ማለት ነው? ድርጅትህን እና የሰራሃቸውን ስራዎች በዲጂታል ዓለም (በሶሻል ሚዲያ እና በድረ-ገጽ) ማስተዋወቅ ማለት ነው።
• ​ለምን ያስፈልጋል? ዘመኑ የዲጂታል ነው። ደንበኞችህ አሁን ላይ አገልግሎት የሚፈልጉት በራፍ ላይ ቆመው ሳይሆን ስልካቸውን ገልጠው ነው።
• ​እንዴት ተግባራዊ ይሆናል? የድርጅትህን የሥራ ከባቢ፣ የተጠናቀቁ ሕንፃዎችን እና የሴፍቲ አሰራሮችን ቪዲዮ እና ፎቶ በማንሳት በፌስቡክ፣ ቲክቶክ እና ቴሌግራም ማካፈል፤ ደንበኞች በቀላሉ ሊያገኙህ የሚችሉበትን መንገድ መዘርጋት።
• ​ተጨማሪ ሃሳብ፦ በድሮው ጊዜ የነበረውን "በቃል የሚደረግ ንግድ" (Word of mouth) አሁን ከዲጂታል ማርኬቲንግ ጋር በማቀናጀት ሰፊ ተደራሽነትን መፍጠር።

​ማጠቃለያ መልእክት፦

​"ሃያ አንደኛውን ክፍለ ዘመን የሚመጥን ኮንትራክተር ለመሆን ጡንቻ ብቻ ሳይሆን አዕምሮ፣ ቴክኖሎጂ እና ዘመናዊ አሰራር ያስፈልጋል። አሸናፊው ነገ የሚገነባው በዛሬው ብልህ እቅድ ነው።"

Via National Magazine

@etconp
👍16❤7