Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.28K photos
359 videos
1.99K files
3.35K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉የ ዕለተ ዕሁድ ጠቃሚ ጉርሻ ከ @ETCONp
.
▶️የፕረዘንቴሽን ፍርሀትን እንዴት ማስወገድ እንችላለን?
.
✍ፕረዘንቴሽን በትምህርት ሂወታችን ውስጥ ከሚያጋጥሙን ሂደቶችና የመፈተኛ መንገዶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡
*በተለይ በከፍተኛ ትምህርት ላይ መምህራን አሳሳይንመንቶችን ፣ ፕሮጀክቶችን ፣ የምርምር ስራዎችን እና የመሳሰሉትን ተማሪዎች በክላስ ውስጥ ፕረዘንት እንዲያደርጉ ይጠይቃሉ፡፡
*ከትምህርት አለም ውጪም በተለያዮ የስራ ጉዳዮች ላይ ፕረዘንት እንድናደርግ ሊጠበቅብን ይችላል፡፡
*ታዲያ በፕረዘንቴሽን ጊዜ የብዙዎች ችግር ፍርሀት ነው፡፡ ሰው ፊት ቆሞ የመናገር ፍርሀት፡፡
*የፕረዘንቴሽን ፍርሀት የብዙ ሰዎች ችግር ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት እስከ 80 % የሚሆኑትን ሰዎች ጋር ያለ ችግር ነው፡፡ በእርግጥ ችግር ነው ተብሎም ሊነሳም አይችል ይሆናል፡፡ ምክንያቱም መምህራንን ጨምሮ የ public speaking ልምድ ያላቸው አርቲስቶች፣ ፓለቲከኞች፣ የሀይማኖት መሪዎች ሁሉ የሚጋሩት common ስሜት ስለሆነ ነው፡፡
*ይህ የፕረዘንቴሽን (public speaking) ፍርሀት ጤናማ ስሜት ነው፡፡ የሁሉም ሰው የጋራ ሰሜትና እንዲያውም የራሱ ጥቅሞችም ያሉት ስሜት ነው፡፡ ችግር የሚሆነው ፍርሀቱ በጣም ከበዛና ቅጥ ካጣ ነው፡፡
የሚከተሉት መንገዶች የፕረዘንቴሽንን ፍርሀት ለመቀነስና ውጤታማ ፕረዘንቴሽን ለማድረግ ያግዛሉ፡፡
1. የፕረዘንቴሽን ፍርሀት ጤናማና common ስሜት እንደሆነ መረዳት፡፡
Literally ሁሉም ሰው ይፈራል፡፡ ልዮነቱ፡አንዳንዶች ማኔጅ ያደርጉታል አንዳንዶች አያደርጉትም፡፡
*ይህ የፍርሀት ስሜት ሊያስደነግጠን ሳይሆን በደንብ እንድንዘጋጅ ሊያመላክተን ይገባል፡፡
*ፍርሀት ጥቅም አለው፡፡ ይሄውም ባዮሎጂካሊ በሰውነታችን ውስጥ የሆርሞንን መጠን ከፍ በማድረግ የበለጠ ኢነርጂ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡
2. ፕረዘንቴሽን ልምምድ (rehearsal )
ፕረዘንቴሽን ልምምድ ይፈልጋል፡፡ ፕረዘንት የምናደርገውን ነገር በደንብ ማወቃችንን፣ ቋንቋችንን፣ ድምፃችንን እንዲሁም ሰአት አጠቃቀማችንን የምናስተካክለው በልምምድ ኀው፡፡
*ፕረዘንት የሚያደርግ ሰው ልክ እንደ መድረክ ተዋናይ ነው፡፡ ፕረዘንቴሽንም በራሱ በተወሰነ መንገድ ትወና ነው፡፡ በመሆኑም ማንም ተዋናይ በደንብ ሳይለማመድ መድረክ ላይ እንደማይወጣ ፕረዘንት የሚያደርግ ሰውም በበቂ ሁኔታ ልምምድ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
*በምንለማመድበት ጊዜ ጓደኞቻችን ፊት ሊሇን ይችላል ወይም ብቻችንን ቆመን ሰው ፊት እንዳለን በማሰብ መለማመድ ይቻላል፡፡
" Practice makes perfect"
3. መረጋጋት፣ እራስን ማረጋጋት
4. በቂ አየር መውሰድ ፣ መተንፈስ
5. ፕረዘንት የምናደርግበትን ቦታና መምህራኑን ቀድሞ ማወቅ፡፡ ይህም ሲባል ፕረዘንት የምናደርግበት ቦታ ቀደም ብለን በመሄድ ማየትና የምንቆምበትን ቦታ ስሜቱን መረዳት ነው፡፡
6. አለባበስን ማስተካከል፡፡ ጥሩ አለባበስ በራስ መተማመንን ይጨምራል፡፡
7. ፕረዘንት የማድረግ ፍላጎትን ማዳበር፣ ይህም ሲባል ፕረዘንቴሽንን እንደ ግዴታ ሳይሆን የሰራነውን ነገር ለሰዎች እንደምናሳይበት እንደ ጥሩ አጋጣሚ መውሰድ፡፡
8. በቂ አረፍት ወስዶ መገኘት
9. ቀደም ብሎ መገኘት (አለማርፈድ)
10. ከመጀመሪያው ውጤታማ ስራ መስራት፡፡ ምክንያቱም የአንዳንዶች የፍርሀት ምንጭ በቂ ስራ ካለመስራትና ካለመዘጋጀት ነው፡፡
.
http://t.me/ETCONp
▶️TODAY BIG TIP ... @ETCONp
:
👉አብዛኛዎቻቹ በጠየቃችሁን መሰረት እንዲሁም ኣሁን ለምትሰሩት HOLSTIC PROJECT አጋዥ ይሆናሉ ብለን ያሰብናቸው የ HOLSTIC PROJECT SAMPLE እንካቹ ብለናል፡፡
፡
🅾አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።
.
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
painting 123final draft Holistic cost analysis .pdf
215.5 KB
👉FINAL DRAFT ON COST ANALYSIS
.
📚 @ETCONp
Cluster BOQ G+2.xls
185 KB
📚 @ETCONp
BOQ.pdf
69.1 KB
📚 @ETCONp
TAKE OFF.pdf
166.2 KB
📚 @ETCONp