Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
Laguna Garzon Bridge 🌉

ይህ የምትመለከቱት ድልድይ ያልተለመደ ክብ ቅርጽ አለው። የዚህ ድልድይ መገኛ Garson Uruguay 🇺🇾 ነው። የዚህን ድልድይ ንድፍ ያዘጋጀው እውቁ አርክቴክት Rafael vinoly ነው። ይህ ድልድይ በክብ ቅርፅ የተቀየሰው አሽከርካሪዎች ፍጥታቸውን እንዲቀንሱ ነው። ይህም ድልድይ የእግረኛ እና የብስክሌት መንቀሳቀሻ አው። ይህም ድልድይ ለአገልግሎት ከዋለ ቡሀላ በቀን እስከ 1000 መኪና እያስተናገደ ይገኛል።

This circular shaped bridge 🌉 is designed in circular shape to force divers to slow down. It accommodates up to 1000 vehicles a day after it starters giving service .

Garzon, Uruguay 🇺🇾
Is it cost efficient? Let’s discuss about it

#bridge

@etconp
👉Combined ➕ stepped Footing.
.
⚡️Why we use it?
.
🚧Put your Answer @COTMP
👉የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ እና በኮንስትራክሽን ውል የስራ መጀመሪያ ቀን/Commencement date/
፡
✉️PART - ONE @ETCONp
.
▶️በኮንስትራክሽን ውል ውስጥ የስራ መጀመሪያ ቀን እና ውል የተደረገበት ቀን
የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡
ይሄውም የሆነበት ውሉ በተደረገበት እለት የግንባታ
ስራ ይጀመራል ተብሎ ስለማይታሰብ ነው፡፡
፡
▶️በኮንስትራክሽን ውል የስራ መጀመሪያ ቀን/Commencement date/
-በመርህ ደረጃ የውል የግንባታ ስራ ማከናወኛ የጊዜ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው ከኮመንስመንት ዴት ጀምሮ ነው፡፡ስለዚህ የውሉ የግንባታ ጊዜ ተብሎ የሚጠቀሰውን ቀን ውሉ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ መቁጠር ስህተት ነው፡፡
*ምክንያቱም የኮንስትራክሽን ውል በአሰሪና ተቋራጭ መካከል ከተፈረመ በኋላ የግንባታው ተጨባጭ ስራ በተለያየ ምክንያት ሊዘገይ ይችላል፡፡ለምሳሌ ግንባታው የሚከናወንበት ቦታ የይገባኛል ጭቅጭቅ ቢነሳበት ጭቅጭቁ እስኪፈታ ድረስ አሰሪው የግንባታውን ሳይት ለተቋራጩ ማስረከብ ያልቻለ እንደሆነ ግንባታው ችግሩ እስከሚፈታ ድረስ ሳይጀመር መቆየቱ የማይቀር
ይሆናል፡፡
*ለተቋራጩ የሳይት ርክክብ/site handover/ ካልተፈጸመለት ስራ መጀመር አይችልም፡፡
*ስለዚህ ተቋራጩ ሳይት ሳይረከብ የግንባታውን ጊዜ መቁጠር ተገቢነት የለውም፡፡
*እንደዚሁም ተቋራጩ የግንባታ ቁሳቁስ እና የሰው ሀይል ሞቢላይዝ እስከሚያደርግበት ምክንያታዊ ጊዜ ድረስ የስራ መጀመሪያ ቀን ሊጀምርበት አይገባም፡፡
-በዚህ ረገድ በተግባር አልፎ አልፎ ስህተት ሲሰራ ይስተዋላል፡፡ይሄውም አሰሪዎች አንዳንዴ የግንባታውን ጊዜ ውሉ ከተደረገበት ቀን ጀምረው በመቁጠር እና ተቋራጩን በቂ ምክንያት ካለህ የጊዜ ማራዘሚያ/Time extension/ ጠይቅ የሚሉበት ሁኔታና አጋጣሚ አለ፡፡ይሄ ተገቢ አሰራር አይደለም፡፡
-በዚህ ረገድ በሀገራችን እና በአለም ሀገራት እየተሰራባቸው ያሉ የዳበሩ
የፊዲክ ጀኔራል ኮንዲሽኖች እና በሀገራችን ተጣጥመው የተቀረጹ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ምን ይዘት አላቸው የሚለውን እና የፍትሀብሄር ህግ ድንጋጌዎችን ደግሞ ቀጥለን እንዳስሳለን፡፡
▶️FIDIC RED BOOK 1999
-በፊዲክ ሬድ ቡክ 1999 ቨርሽን ክሎስ 8.1 ላይ ኢንጅኒየሩ ለተቋራጩ ስራ እንዲጀምር ማስታወቅ እንዳለበት እና ከ7 ቀን ያላነሰ ጊዜ መስጠት እንደሚገባው ይጠቅሳል፡፡
*እንደዚሁም በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት በልዩ ሁኔታ ካልተቀመጠ በስተቀር የስራ መጀመሪያው ቀን/ Commencement date/ ተቋራጩ በጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ42 ቀናት ውስጥ መሆን እንዳለበት ተቀምጧል፡፡
*በተጨማሪም ተቋራጩ ከስራ መጀመሪያ ቀን በኋላ ወዲያውኑ እና ያለመዘግየት የግንባታ ስራ መጀመር እንዳለበት ይገልጻል፡፡
-ተቋራጩ/contractor/ ከስራ መጀመሪያ ቀን በኋላ ይቅርታ ሊያሰጥ የሚችል
ምክንያት ሳይኖረው ያለመዘግየት የግንባታ ስራ መጀመር እንዳለበት በክሎስ ላይ የተቀመጠውን ግዴታውን ያልተወጣ እንደሆነ ደግሞ አሰሪው/client/
ውሉን ለማቋረጥ እንደሚችል ክሎስ 15.2(c) ላይ ተቀምጧል
▶️FIDIC 1987
-በኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ፎር ወርክስ ኦፍ ሲቪል ኢንጅነረንግ ኮንስትራክሽን ፊዲክ 1987 ቨርሽን ክሎስ 41.1 ላይ ስለ ኮመንስመንት ዴት/የስራ መጀመሪያ ቀን ተቀምጧል፡፡
*ይዘቱም መሀንዲሱ የስራ መጀመሪያውን ቀን በጨረታ ሰነዱ አፔንዴክስ ላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለተቋራጩ ማስታወቅ እንዳለበት የሚገልጽ ነው፡፡
*ተቋራጩም የስራ መጀመሪያው ቀን በመሀንዲሱ ከተገለጸለት በኋላ ያለመዘግየት እና በተቻለ ፍጥነት የግንባታ ስራውን መጀመር እንዳለበት ይገልጻል፡፡
*የግንባታ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ መቆጠር የሚጀምረውም ከኮመንስመንት ዴት ጀምሮ ስለመሆኑ ክሎስ 43.1 ላይ ተቀምጧል፡፡
-እንግዲህ ተቋራጩ በቂ ምክንያት ሳይኖረው በክሎስ 41.1 ላይ በተመለከተው አግባብ የግንባታ ስራውን ሳይጀምር የቀረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ለማቋረጥ እና ተቋራጩን ከሳይት ለማስወጣት መብት/expel right/ እንዳለው ክሎስ 63.1 ያስቀምጣል፡፡
▶️MoWUD 1994
-ይህ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በ1994 ስራ ላይ አውሎት የነበረው የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/MoWUD 1994 በተለይ ከፊዲክ/FIDIC 1987 ቨርሽን የተወሰደ ሲሆን ስለኮመንስመንት ዴት በሁለቱም ጀኔራል ኮንዲሽኖች ላይ ተመሳሳይ ይዘት ባለው ሁኔታ ያስቀምጣሉ፡፡
ስለዚህ ማብራሪያውን መድገም አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም፡፡
▶️PPA 2011
-በፒፒኤ 2011 ቨርሽን ክሎስ 71 ላይ የስራ መጀመሪያ ቀን በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ላይ ሊቀመጥ እንደሚችል ወይም ደግሞ በአስተዳደራዊ መንገድ በኢንጅኒየሩ በሚሰጥ ትእዛዝ ሊታወቅ እንደሚችል ይጠቅሳል፡፡
-እንዲሁም በሌላ ሁኔታ በውሉ ላይ ካልተገለጸ በስተቀር ለተቋራጩ የጨረታ አሸናፊነቱ ከተገለጸ ቀን ጀምሮ ታስቦ ከ120 ቀናት ለማለፍ አይችልም፡፡
▶️የፍትሀብሄር ህግ
-የስራ ማከናወኛ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2610 - 2637) በሚመለከት በውሉ ላይ የጊዜ ጉዳይ በግልጽ ያልተጠቀሰ እንደሆነ ተቋራጩ ወዲያውኑ ስራ መጀመር እንደሚኖርበት በአንቀጽ 2619 ላይ ተደንግጓል፡፡የግንባታ ጊዜ በተገለጸባቸው ውሎች ደግሞ ስራ ተቋራጩ ስራውን ወዲያው ያልጀመረ እንደሆነ እና በጊዜ ገደቡ የግንባታ ስራውን ለመፈጸም የማይችል መሆኑ የታወቀ እንደሆነ አሰሪው ለተቋራጩ ስራውን የሚጀምርበትን ጊዜ ሊወስንለት እንደሚችል በአንቀጽ 2618 ላይ ተቀምጧል፡፡
*ሌላው እነዚህ ደንቦች ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ስራ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3019-3040) በሚመለከተው የግል የስራ ተቋራጭነት ውል ላይ ጭምር ተፈጻሚነት እንደሚኖራቸው ከአንቀጽ 3019(2) ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል፡፡
-የአስተዳደር መስሪያ ቤት የኮንስትራክሽን ውል ማለትም የመንግስት ስራዎች መቋረጥ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3244 እና ተከታዮቹ) በሚመለከት
እያንዳንዱ ተዋዋይ ወገን ግዴታዎቹን በውሉ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ መፈጸም ይኖርበታል፡፡
*በውሉ ላይ ግልጽ የጊዜ ስምምነት የሌለ እንደሆነ ደግሞ ግዴታው በአእምሮ ግምት በቂ በሆነ ጊዜ መፈጸም እንደሚኖርበት በአንቀጽ 3174 ላይ ተቀምጧል፡፡
*ይህ ድንጋጌ ስለአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በጠቅላላው የተደነገገ ሲሆን የመንግስት ስራዎች መቋረጥ ውልን በሚመለከተው ልዩ ክፍል ላይም በግልጽ ስለስራ ጊዜ ተደንግጓል፡፡
-ይሄውም በኮንስትራክሽን ውሉ ላይ የግንባታ ስራዎቹ በሙሉ የሚከናወኑበት ጠቅላላው ጊዜ ብቻ ተጠቅሶ እንደሆነ አሰሪው መስሪያ ቤት/client/ የግንባታ ስራው የሚጀመርበትን ጊዜ/ Commencement date/ ዘርዝሮ ለተቋራጩ ማስታወቅ እንዳለበት በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3253(2) ላይ ተደንግጓል፡፡
.
በ ጉባዔ አሰፋ
፡
🏗ይቀጥላል... #ConstructionLaw
.
http://t.me/COTMp
ALDER HEADQUARTER
ይህ የምትመለከቱት ህንፃ በመካከለኛው ምስራቅ የመጀመሪያው ክብ ህንፃ ( elevation wise)ነዉ።
መገኛው መካከለኛው ምስራቅ ነው።

👉🏿የህንፃው ሁኔታ ፡ - የተጠናቀቀ
👉🏿የህንፃው አገልግሎት ፡ - የንግድ እና የቢሮ
👉🏿 የተጠናቀቀው ፡ - 2010 GC

ርዝመት

👉🏾የጣርያው ጫፍ ፡ - 110ሜትር

የቴክኒካዊ ዝርዝር

👉🏾ህንፃው ያረፈበት ቦታ :- 61,900 ሜትር እስኩዌር

ንድፍ እና ተቋራጭ

👉🏿አርክቴክት ፡ - MZ Architect
👉🏿 ተቋራጭ ፡ - ALDAR Laing O’Rourke
👉🏿ባለቤት ፡ - Aldar Properties

The project delivery system was DBB

👉🏿የህንፃው ይህን ቅርፅ እንዲይዝ ያደረገው through use of diagrid , diagonal grid of steel structure.

የዚህን ህንፃ presentation በPDF ነገ ይዘንላችሁ ምንቀርብ ይሆናል።

Abu Dhabi UAE 🇦🇪

Source:- Wikipedia

Dubai UAE 🇦🇪

ውብ ምሽት ተመኘን

我們希望有一個美麗的夜晚

‎كنا نتمنى أمسية جميلة

हमने एक खूबसूरत शाम की कामना की

We wished a beautiful evening

Мы пожелали прекрасного вечера

@ETCONp
Ethio Construction Engineering
👉የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ እና በኮንስትራክሽን ውል የስራ መጀመሪያ ቀን/Commencement date/ ፡ ✉️PART - ONE @ETCONp . ▶️በኮንስትራክሽን ውል ውስጥ የስራ መጀመሪያ ቀን እና ውል የተደረገበት ቀን የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ይሄውም የሆነበት ውሉ በተደረገበት እለት የግንባታ ስራ ይጀመራል ተብሎ ስለማይታሰብ ነው፡፡ ፡ ▶️በኮንስትራክሽን…
👆👉 ከ ትላንት የቀጠለ...
፡
🏗የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ PART TWO @ETCONp
.
-የኮንስትራክሽን ውል ስምምነት/contract agreement በአሰሪ/client እና
በተቋራጭ/contractor መካከል የሚፈረምበት ቀን የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
-እዚህ ላይ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020 ድንጋጌ እና አንድ ውል ተቋቋመ
ሊባል የሚችለው መቸ ነው? የሚለው ማለትም የውል አቀራረብ/offer እና አቀባበል/acceptance በሚመለከት በፍትሀብሄር ህጉ 1681 እና ተከታዮቹ የተደነገገው እና የውል ፎርም ጉዳይ ከግምት ውስጥ መግባት ጭምር አለበት፡፡
-የግል የኮንስትራክሽን ውል ጉዳዮችን በሚመለከተው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020(1) ላይ አሰሪና ተቋራጭ ስለሚሰራው ስራ እና ስለዋጋው ካልተስማሙ በስተቀር የተቋራጭነት ውል አለ እንደማይባል ተደንግጓል፡፡
-ሌላው ከአስተዳደር መስሪያ ቤት ጋር የሚደረጉ ውሎችን በሚመለከት
ስለውሎች በጠቅላላው የተደነገገው ጭምር ተፈጸሚነት እንዳለው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3131(1) ይደነግጋል፡፡
*የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በጽሁፍ መደረግ እንዳለባቸው በፍትሀብሄር ህግ ስለውሎች በጠቅላላው በሚደነግገው ክፍል በአንቀጽ 1724 ላይ ተደንግጓል፡፡
-የውልን ጉዳይ ስለሚመለከት ማስረጃ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2005(1)
ላይ እንደተደነገገው ደግሞ የጽሁፍ ሰነድ በላዩ ላይ የተጻፈውን ቀን በሚመለከት በተፈራራሚዎች መካከል ሙሉ እምነት የሚጣልበት ማስረጃ ነው ይላል፡፡
-እንግዲህ ውል የተደረገበት ቀን በአሰሪና ተቋራጭ መካከል የውል ግንኙነት መቋቋሙን ለማረጋገጥ ይጠቅማል፡፡ውል ደግሞ ከተቋቋመበት ቀን ጀምሮ በተዋዋዮች መካከል እንደህግ እንደሚቆጠር የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ
1731(1) ይደነግጋል፡፡ሆኖም ግን ውሉ የተደረገበት ቀን የውሉ የግንባታ ስራ መጀመሪያ ቀን ተደርጐ ሊወሰድ አይገባም፡፡
---------///---------///----------
▶️በአጠቃላይ የስራ መጀመሪያ ቀን እና ውል የተፈረመበት ቀን ከውል አተገባበር ጠቀሜታ አንጻር የተለያየ ፋይዳ ያላቸው ናቸው፡፡የውሉን የስራ ጊዜ በተለይ ውሉ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ መቁጠር ተገቢነት የለውም፡፡
*ኮመንስመንት ዴት የውሉን የግንባታ ማከናወኛ ጊዜ ለመቁጠር እንደመነሻ ተደርጐ ሊወሰድ ይገባል፡፡
*የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ/completion date/ ትክክለኛ ቀን ተሰልቶ መታወቅ ያለበት ከኮመንስመንት ዴት ጀምሮ ቀኑ ተቆጥሮ መሆን አለበት፡፡
*የውሉን ጊዜ ለማስላት ውሉ ከተፈረመበት ቀን የተጀመረ እንደሆነ ግን የግንባታ ማጠናቀቂያ ቀን የማሳጠር ውጤት ስለሚኖረው እና ይሄውም ተቋራጩን አላግባብ የመዘግየት ቅጣት/ሊኩዴትድ ዳሜጅ/ እንዲጀመርበት ስለሚያደርግ እና ወደ አለመግባባት ስለሚያመራ ውሉ የተደረገበትን ቀን እና ኮመንስመንት ዴት ልዩነት በሚገባ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
:
© በ ጉባዔ አሰፋ
፡
#ConstructionLaw
.
http://t.me/COTMp
survying.rar
66.7 MB
Surveying file

Content
1. introduction to surveying
2. Unit of measurement
3. Leveling
4. Measurement of Angle
5. Traverse and traverse computation
6. Area computation
7. Topographic surveying
8. Volumes of earth work
9. GPS presentation

And advanced book ( engineering surveying)

ፋይሉ 67.8MB ስለሆነ WiFi ቢጠቀሙ ይመረጣል።

ፋይሉ compress ተደርጓል ስለዚህ winRAR ያስፈልጎታል።

በውስጡ 12 PDF ፋይሎች አሉት።
#survying

@etconp
👉Types of Construction Contracts and Their Comparison @ETCONP
.
✍There are different types of construction contracts and their comparison is presented in this article.
*A construction contract is an agreement between two or more parties to execute the construction works as per certain terms and conditions.
:
*A construction contracts contains general and special conditions of agreement, details of construction project work, their specifications, time limits, payments and penalties for delivery delays etc. and ensures every party’s rights and obligations.
.
*A construction contract document is a valid document can be enforced under certain authority or law.
:
Types of Construction Contract Documents
.
*At early stages for any construction project, owner with his engineer or consultant prepares necessary documents for tender process which will be included in the contract.
*These documents are called contract documents.
:
👉Following are the types of documents in a construction contract:
.
*General conditions
*Special conditions
*Drawings and specifications
*B.O.Q (bill of quantity)
*Letter of acceptance
*Contractor bid
*Conditions of Construction Contract
.
☝️Conditions of contract are terms which rule the relationships between the owner and the contractor, define each party’s rights and obligations, specify method of payment and determine actions required when existing any disputes between the owner and the contractor.
.
👏Following are the conditions of contract for construction projects:
.
*General conditions of contract
*Special conditions of contract
*General conditions of contract
.
*
They are standard terms that suit the majority of projects, they include:
.
*Definition of the project
*Contract components
*Rights and responsibilities for the owner and the contractor
*Project schedule
*Payment method
*Warranty and delay penalty
.
***Special conditions of contract:-
*They are the modifications required to suit the uniqueness of the project, make the contract flexible for the nature of the project and achieve project objectives.
.
#ConstructionContract
.
http://t.me/COTMp
Ethio Construction Engineering
ALDER HEADQUARTER ይህ የምትመለከቱት ህንፃ በመካከለኛው ምስራቅ የመጀመሪያው ክብ ህንፃ ( elevation wise)ነዉ። መገኛው መካከለኛው ምስራቅ ነው። 👉🏿የህንፃው ሁኔታ ፡ - የተጠናቀቀ 👉🏿የህንፃው አገልግሎት ፡ - የንግድ እና የቢሮ 👉🏿 የተጠናቀቀው ፡ - 2010 GC ርዝመት 👉🏾የጣርያው ጫፍ ፡ - 110ሜትር …
aldarheadquartersbuilding-presentation @etconp.pdf
950.3 KB
Aldar headquarters building presentation

የዚህ ህንፃ presentation በpdf ይዘንላችሁ መተናል።

Content

👉🏿Introduction
👉🏿 concept
👉🏿concept of the building
👉🏿architecture
👉🏿the circular shape in architecture
👉🏿Geometry of the facade
👉🏿 facade curvature
👉🏿original design variation
👉🏿space
👉🏿the construction process
👉🏿structure
👉🏿material

@etconp
Archicad manual @ETCONP.pdf
20.2 MB
ACHICAD MANUAL

Contents

👉🏿
Introduction
👉🏿concepts and tools
👉🏿 project and office setup
👉🏿creating a virtual building
👉🏿visualization
👉🏿 project information
👉🏿Document Layout
👉🏿 project management and coordination

#archicad #virtual #3D

@etconp
#AlertEpidemics

Standard conditions of contracts about epidemics

▶️ Standard condition of contract for construction of civil work projects December, 1994
▶️ fidic part II standard condition of contract 1987


Clause 34 sub-clause(6). Epidemics
In the event of any outbreak of illness of an epidemic nature, the Contractor shall comply with and carry out such regulations, orders and requirements as may be made by the Government, or the local medical or sanitary authorities for the purpose of dealing with and overcoming the same.

@etconp
ጥያቄ

Which admixture causes early setting and Hardening of concrete ?

1. Workability admixture
2. Accelerators
3. Retarders
4. Air entraining admixture

#admixture #concrete #quiz

@etconp
ጥያቄ

What type of excavator is this ?

1. Drag line
2. Face shovel
3. 360 degree excavator
4. Backhoe loader

#equipment #excavator

@etconp
surveying advanced @etconp.pdf
3.1 MB
Surveying

Content
1. Error in measurement
2. Distance in measurement
3. Leveling
4. Theodolite and traverse surveying
5. Adjustment of survey observation
6. Triangulation and trilateration
7. Curve range
8. Area and volume
9. Point location and setting out

#surveying

@etconp
LAS LAJAS SANCTUARY

ይህ የምትመለከቱት መቅደስ ስሙ Las Lajas ይባላል።
መገኛውም ኮሎምቢያ ሲሆን ለሀገሪቱ የቱሪስት መስዕብ የሚኖረውም ድርሻ የላቀ ነው።
ይህ ቤተመቅደስ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ነው።

በተለምዶ “በሸለቆ ውስጥ የእግዚአብሔር ተዓምር “ ወይም "miracle of GOD in the abyss.” በመባል ይታወቃል።

አሁን ያለው ቤተክርስቲያን የተገነባው በ 1916 እና በ 1949 መካከል ባለው የጎቲክ style መነቃቂያ ጊዜ ነው።

This sanctuary is one of the most fascinating religious structures in all of Colombia .

The present church ⛪️ was built in Gothic revival between 1916 and 1949.

Nariño, Colombia 🇨🇴

Source:- Wikipedia

ውብ ምሽት ተመኘን

我們希望有一個美麗的夜晚

‎كنا نتمنى أمسية جميلة

हमने एक खूबसूरत शाम की कामना की

We wished a beautiful evening

Мы пожелали прекрасного вечера

Waarii gaarii sifan haawaa

@ETCONp
➡Hydraulics and water supply Lecture @COTMp
.
👉ለዛሬ ደሞ የ ላየኛው የምድር ውሃ (surface water) ለማጣራት የምንጠቀማቸው ዘዴዎች ኣዘጋጅተናል 👇
.
⓵ስክሪኒንግ (screening) - ይህ የመጀመረርያው የማጣራት
ደረጃ ሲሆን በዚህ የማጣራት ዘዴ ውስጥ በውሃው ላይ የሚንሳፈፉ ግዙፍ አካላትን ለምሳሌ የዛፍ ጉቶ ፣ግንድ፣ ቅጠል እና ልዩ ልዩ የፕላስቲክ ተንሳፋፊ ቁሳቁሶች ወደ ዋናው የማጣሪያ ገንዳ እና ስርዓት
እንዳይገቡ ያግዳል ።
.
⓶ማርጋት (Coagulation )፦ በዚህ የማጣራት ደረጃ ላይ
ለአይን እይታ ያነሱ ጥቃቅን
አካላትን (Particle size 10^-7cm የሚሆኑ) በማርጋት እና
የኬሚካል ቻርጃቸውን ኒውትራላይዝ የሚያረግ ኬሚካል በመጨመር እርስ በእርሳቸው
እንዲሳሳቡ ማድረግ ነው ።
ለዚህ የአልሙኒየም ፖሊመሮች (Alum) እና አይረን (Fe+3)
አገልግሎት ላይ ይውላሉ።
እንደ የቁልቋል ተክል ያሉ የተፈጥሮ አርጊዎች (coagulants) መጠቀምም ይቻላል
.
⓷ጉግለት (Flocculation)፦ ይህ እርከን ፤ ማርጋት
(coagulation ) ወቅት የረጉ ጥቃቅን አካላትን እርስ በእርሳቸው ቦንድ እስኪፈጥሩ እና እርስ በእርሳቸው ተጣብቀው እስኪጓግሉ ውሃው በተለያየ ፍጥነት የሚማሰልበት ነው።
ይህ ዘዴ ሜካኒካል ወይም ማኑዋል በሆነ መልኩ ይተገበራል።
.
⓸መዝቀጥ/ማዝቀጥ (sedimentation) ፦ በፍሎኩሌሽን ወቅት የጓጎለው ጥቃቅን አካላት በዚህን የማጣራት ደረጃ እንዲዘቅጡ ይደረጋል ። ይህ ዘዴ የሚተገበረው የሚጣራው የውሃን ፍጥነት በመቀነስ ግራቪቲን ተጠቅሞ እንዲዘቅጥ ማድረግ ነው።
በግራቪቲ ለማዝቀጥ የሚከብዱ እጅግ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን በፍሎኩሌሽን ወቅት ስንጠቀማቸው የነበሩ ኬሚካሎችን በመጠቀም እንዲዘቅጡ ይደረጋል።
.
⓹ ማጥራት (filtration ) ፦ በዚህ የማጥራት ደረጃ ከማዝቀጥ
ደረጃ ያለፉ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን እጅግ ጥቃቅን ቀዳዳዎች ባሉት አካል (medium ) እንዲያልፍ በማድረግ የድፍረስነቱን መጠን እጅግ መቀነስ ነው።
.
⓺ማከም (Disinfection) ፦ ከላይ በተጠቀሱ የማጣሪያ ሂደቶች የተጣራው ውሃ
(በዋነኛነት ከተለያዩ ህይወት ከሌላቸው ጥቃቅን ቆሻሻዎች)
ለህብረተሰቡ ለአገልግሎት
ከመድረሱ በፊት በዚህ ሂደት (ዲስኢንፌክሽን) ማለፍ አለበት ።
ምክንያቱም ውሃው ለአገልግሎት የሚቀርበው ከተለያዩ በአይን ከማይታዩ በሽታ አምጪ ተህዋስያን ነፃ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው ። ዲስኢንፌክሽን ውሃውን በማፍላት ፣ ሚካኒካል
በሆነ መልኩ ፣ ለጨረር በማጋለጥ (radiation ) እንደሁም በኬሚካል ሊከናወን ይችላል።
በሃገራችን በዋነኛነት
ሃሎጅኖችን (ብሮሚን ክሎሪን እና አይኦዲን ) በመጠቀም
ኬሚካል በመጠቀም ውሃን እናክማለን ።
፟
➡ከዚህ ሁሉ የማጣራት ሂደት በኋላ የተጣራው ውሃ ይጠራቀምና
ለተጠቃሚዎች ይዳረሳል።
.
▶ስለ surface waterን የማጣራት ሂደቶች ጥቂት የሆነ ገለፃን እንዳደረግንላችሁ ተስፋ
እናደርጋለን ። ርእሱ ሰፊ እንደመሆኑ ዳግመኛ በጥልቀት ለመዳሰስ ቃል እንገባለን✌
.
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
t.me/COTMp
👆👆👆👆👆
⚡ አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።
🛑 በጣም ጠቃሚ መረጃ
.
👌ኮሮና ለመከላከል በቻይና ሰዎች የሰጧቸው ዋና ዋና ጠቃሚ ምክሮች:-
.
#1. ሁለት አይነት ጫማ ይኑርዎት። አንዱ ከቤት ውጪ የሚጠቀሙበት ሲሆን ሌላኛው ቤት ውስጥ የሚጠቀሙበት ይሆናል። ከቤት ውጪ የሚጠቀሙበትን በፍጹም ወደ ቤት ውስጥ አያስገቡ። ቤት ውስጥ የሚጠቀሙበትን በፍጹም ወደ ውጪ አያውጡ።

#2. አንድ የተለየ ጠረጴዛ ይኑርዎት። ከውጪ የሚገዟቸውን እቃዎች ለማኖር የሚያገለግል አንድ የተለየ ጠረጴዛ ይኑርዎት። ከውጪ የሚገዟቸውን እቃዎች በሙሉ ለምሳሌ እንደ መድሐኒት: መጠጦች: አትክልቶች እና ሌሎችንም ሳይነኩ ለ24 ሰዓት በጠረጴዛው እንዲቆዩ ያድርጉ።

#3. በተቻለ መጠን የገንዘብ ኖቶችንም ሆነ ሳንቲሞችን አይስጡ: አይቀበሉ። የገንዘብ ኖቶችንም ሆነ ሳንቲሞችን ወደ ወደ ቤት የሚያመጡ ከሆነ ለዚህ ጉዳይ ለይተው ባስቀመጡት ጠረጴዛ ላይ ለ24 ሰዓት አቆይተው ይጠቀሙ።

#4. ሁሉንም አይነት አትክልቶች ማለትም ቀይ ሽንኩርት: ነጭ ሽንኩርት: ድንች እና ሌሎችንም በፈላ ውሃ ሙልጭ አድርገው ይጠቡ። በፈላ ውሃ ሊታጠቡ የማይችሉ አትክልቶችን አይግዙ።

#5. ከቤት ከወጡ በተቻለ መጠን የእጅ ስልክዎን ይዘው አይሂዱ። ይዘው ከወጡ ደግሞ ወደ ቤት ሲመልሱ በአልኮል ያጽዱ።

#6. ከቤት ከወጡ በተቻለ መጠን የቤት ቁልፎችን ይዘው አይውጡ። ይዘው ከወጡ ደግሞ ወደ ቤት ሲመልሱ በአልኮል ያጽዱ።

#7. ከቤት ወጥተው ሲመልሱ እጅዎንና ፊትዎን በሳሙና ይታጠቡ። ቤት እንደተመለሱ የለበሱትን ልብስ አውልቀው እንዲታጠብ ያድርጉ።

#8. ሴት እህቶቻችን ከቤት ስትወጡ ጸጉራችሁ በአግባቡ መጠቅለሉን አረጋግጡ:: ጸጉራችሁን በእጃችሁ አትነካኩ:: ፊታችሁን ጸጉር በነካ እጃችሁ አትንኩ።

#9. አትክልት ለመግዛት ሲሄዱ የእጅ ጓንት ያድርጉ። ወይም አትክልቶችን ሲያነሱ የፕላስቲክ ከረጢቶችን በሁለቱም እጅዎት ማጥለቅዎትን እርግጠኛ ይሁኑ። ወደ ቤት ሲመልሱ የእጅ ጓንትዎን ማጠብዎን አይዘንጉ። በፕላስቲክ ከረጢቶች ተጠቅመው ከሆነ ወደ ቤት ሲመልሱ ወይም ወዲያውን ከተጠቀሙ በኋላ ያስወግዱ።

#10. ሁልጊዜ ከቤት ከመውጣትዎ በፊት ራስዎን እና የሚያመጧቸውን ነገሮች ደህንነት እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ ያቅዱና በቂ ዝግጅት ያድርጉ።

#11. በጣም የግድ ካልሆነ በስተቀር ምግብ ወይም መድሐኒት ለመግዛት ባይሰለፉ ይመረጣል። መሰለፉ ደግሞ የግድ ከሆነ እስከ ሁለት ሜትር ርቀትዎን ይጠብቁ።

#12. ከውሾች እና ድመቶች ጋር ያለዎትን ንክኪ ያስወግዱ።

#13. በተቻለ መጠን አረጋውያን ወደ ውጪ ባይወጡ ይመክራል። ቤት ውስጥ ያሉ ወይም በአካባቢው ያሉ ሰዎች ለአረጋውያን የሚፈልጉትን ነገር ገዝተው ቢያመጡላቸው ይመክራል።

#14. ሁልጊዜ ከቤትዎ ከመውጣትዎ በፊት ከላይ የተጠቀሱትን መልዕክቶች በመመልከት አቅደው ተግባራዊ ያድርጉ።

ምንጭ ፡ ድረ ገጽ
Design-of-column-Excel-Sheet @etconp.xlsx
35.7 KB
Design of column sample

#sample #design #column #RC

እኛ ለናንተ ስናጋራ እናንተም ለጓደኞቻችው በማጋራት አጋርነታችሁን አሳዩን።


@etconp
design example of six sorey building @etconp.pdf
898.4 KB
Seismic Design of 6 story building

#sesmicdesign

እኛ ለናንተ ስናጋራ እናንተም ለጓደኞቻችው በማጋራት አጋርነታችሁን አሳዩን።

@etconp