Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
Ethio Construction Engineering
The difference between Diagrid structural system and Exoskeletal structural system - Diagrid structural system is diagonally arranged whereas Exoskeletal structural systems are not not expected to be diagonal - if you see in the picture that I compiled…
Wall system (የግድግዳ ግንባታ ስርዓት)

- ግድግዳ ከተለያዩ የግንባታ እቃዎች ሊሰራ ይችላል ለመዘርዘር ያህል ከ ጣውላ(timber board or plywood ) ፣ ከ ብሎኬት፣ ከባለፌሮ አርማታ (RC)፣ ከ ቆርቆሮ( EGA sheet) በሀገራችን ደግሞ በጭቃም ይሰራል ( wood and mud- sticking the mud on the wood) በ እስያ ደግሞ በቀርከሃ መስራት የተለመደ ነው።

የግድግዳ ጥቅም ከውጭ ከባቢ የ አየር ሁኔታ እኛ መቆጣጠር ማንችለውን በማስቀረት የምንፈልገውን እና የምንቆጣጠረውን የዐየር ሁኔታ ይፈጥርልናል በተጨማሪም privacy እንድናገኝ ያስችለናል።

Note ላይ ከ አገልግሎቻቸው አንፃር ለሁለት wall system ተከፍሏል አንብቡት።

በቀጣይ አንዳንድ ዝርዝሮችን ይዤላችሁ መጣለው….. stay tuned

@etconp

Facebook :- https://www.facebook.com/etconp/

Youtube:- https://youtu.be/qIpy-LMQ8QE
👍11
A pile foundation may consist of a group of piles, joined by pile cap at the top and typically spaced at 2 to 4 timers the pile diameter.
There are two modes of failure for pile group, namely individual pile failure and block failure.
During design, the distribution of axial load among the piles is assumed uniform.
However, center piles are expected to carry greater loads than perimeter piles in sand. The reverse is true for pile group in clay.
Block failure on the other hand, is more likely to occur in fine-grained soil rather than coarse-grained soil. It may be induced when the pile spacing is less than 2 to 3 times the pile diameter.
https://t.me/ETCONp
👍10❤1
Ethio Construction Engineering
Wall system (የግድግዳ ግንባታ ስርዓት) - ግድግዳ ከተለያዩ የግንባታ እቃዎች ሊሰራ ይችላል ለመዘርዘር ያህል ከ ጣውላ(timber board or plywood ) ፣ ከ ብሎኬት፣ ከባለፌሮ አርማታ (RC)፣ ከ ቆርቆሮ( EGA sheet) በሀገራችን ደግሞ በጭቃም ይሰራል ( wood and mud- sticking the mud on the wood) በ እስያ ደግሞ በቀርከሃ መስራት የተለመደ ነው። የግድግዳ…
Further on wall system

በሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ባህላዊ የቤት አገነባብ ዘቤዎች አሉ ሰሜን ብትሄዱ የሰሜን የቤት አገነባብ (ባህላዊ) የደቡብ ወይም ከምስራቁ ኢትዮጵያ ቤት አገነባብ ዘቤ እጅግ ይለያል የተለያየበት ዋነኛ ምክንያት አቅራቢያ ባለው የግንባታ እቃ እና የ አየር ንብረት ነው። ለምሳሌ ወደ ሰሜን ብትሄዱ G+1 በ አለታማ ድንጋይ ከ ጭቃ(እንደ mortar) በማገናኘት ከ አንድ ወለል በላይ ይሰራሉ ሶሌታቸውን (slab) በወፍራም መሮ እንጨት በመረብረብ ጭቃ በመመረግ slab ይሰራሉ ወደ ደቡብ ብትሄዱ እጅግ የሚያምሩ በጎጆ ቤቶች በገጠሩት የደቡብ ክልል የተለመደ ነው። ወደ ምስራቅ ብትሄዱ ደግሞ tent (ድንኳን ቤቶች) ከ አየር ንብረቱ ጋር ተያይዞ የተለመደ ነው። በተለይ በ አፋር የመሬት መንቀጥቀጥ እሳተ ጎመራው (ኤርታሌ) አቅራቢያ መሆኑን ተያይዞ frequently occur ያረጋል earthquake ይሄን counter ለማድረግ ቀለል ያለ material ይጠቀማሉ።

ዛሬ እስኪ ስለ ጭቃ ቤት አሰራር እናውራ በሀገራችን በክልል ከተሞች በሰፊው የሚጠቀሙትን አልፎ አልፎ መዲናችን ላይም የሚስተዋሉትን የጭቃ ቤቶች እናውራ

- መጀመሪያ ከተቀየሰ በኋላ ከ 30-50 ሳንቲ ይቆፈራል ከ 15 ሳንቲ diameter በየ 10- 20 ሳንቲም ርቀት ከዛን እንጨቶቹ ጉድጓድ ላይ ይተከላሉ ከዛም ቱንቢ ይጣልና ቀጥ ማለቱ ከታወቀ ከዛም በ ግንብ ይታጠራሉ ከዛም በ እንጨት ይረበረባሉ ከዛም ጭቃ ከ ጭድ(rough surface እንዲኖረው እና ለ ልስን እንዲመች) ጋር የተለወሰ ይመረጋል ካንቹ ለ ግድግዳ ከምንጠቀመው እንጨት ጋር የተያያዘ ነው ከዛ finishing ስራ።

To be continued..

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
👍10👏3
Ethio Construction Engineering
ስላም ቤተሰቦች ለዛሬ አንድ ጥየቄ እንጠይቃቸሁ # ከ ላይ photo ላይ አምትመለከቱት አሰራር ምን ተብሎ ይጠራል? What is its purpose? https://t.me/ETCONp
Methods of Retrofitting Building.

The following are the most usual method of retrofitting a building.

1.Retrofitting of the Structural Components
~ Jacketing
2.Retrofitting of the Structural System
~ Beam Addition Method
~ Seismic Wall Addition Method
~ Seismic Isolation Method
3.Retrofitting of Foundation
~ Plie Addition Methods
~ Ground Improvement Techniques
4.Retrofitting of Historic Structures
~ Post-Tensioning
~ Epoxy
Next we will see Advantage and disadvantage of Retrofitting....
https://t.me/ETCONp
👍7👌4
Ethio Construction Engineering
Further on wall system በሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ባህላዊ የቤት አገነባብ ዘቤዎች አሉ ሰሜን ብትሄዱ የሰሜን የቤት አገነባብ (ባህላዊ) የደቡብ ወይም ከምስራቁ ኢትዮጵያ ቤት አገነባብ ዘቤ እጅግ ይለያል የተለያየበት ዋነኛ ምክንያት አቅራቢያ ባለው የግንባታ እቃ እና የ አየር ንብረት ነው። ለምሳሌ ወደ ሰሜን ብትሄዱ G+1 በ አለታማ ድንጋይ ከ ጭቃ(እንደ mortar) በማገናኘት ከ አንድ…
Further on wall system

ባለ ብሎኬት ግድግዳ

Further on wall system

ባለ ብሎኬት ግድግዳ

- ብሎኬት በመደርደር የምትሰራው የ
ግድግዳ አይነት ነው
- ባሀገራችን በ 3 size ገበያ ላይ አለ

* ባለ 10
* ባለ 15
* ባለ 20

-በቀን ቢበዛ እስከ 5 ኮርስ ቢደረደር ይመከራል mortarኡን እንዳይጫነው እና ጥንካሬ እንዳያሳጣው።

- ውሀ በጣም መጠጣት አለበት ጥንካሬ እንዲያገኝ

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Youtube:- https://youtu.be/qIpy-LMQ8QE
👍18
የቦሌ ሚካኤል አደባባይ ተሻጋሪ ድልድይ ግምባታ

ይህ የማሳለጫ ድልድይ 600 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን በከተማዋ በግንባታ ላይ ከሚገኙት ትላልቅ የማሳለጫ ድልድዮች በርዝመቱ ቀዳሚውን ቦታ ይይዛል፡፡ የዚህ ማሳለጫ ድልድይ የግራ መስመር ቀደም ሲል ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት መደረጉም ይታወሳል፡፡

በአሁኑ ወቅት በቀኝ በኩል ያለውንም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል፡፡

ግንባታው ሲጠናቀቅ ቦሌ ሚካኤል አደባባይ ላይ እየተፈጠረ የሚገኘውን የትራፊክ መጨናነቅ ችግር በእጅጉ የሚፈታ ይሆናል፡፡

ምንጭ AACRA

@etconp
👍8
ለግለሰቦች የተሸጡ መኖሪያ ቤቶችን አስይዞ 800 ሚሊየን ብር ከባንክ የተበደረው ሪል ስቴት አልሚ ተቋም አቤቱታ ቀረበበት።

ወጂዝ ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከ2010 ጀምሮ ቤት የሚፈልጉ ግለሰቦችን በ20 ወራት ውስጥ ቤት ሰርቶ እንደሚያስረክብ በመግለፅ በተያዘው ጊዜ ውስጥ ገንዘቡን ከፍለው እንዲጨርሱ አድርጓል።

ግለሰቦቹ ገንዘቡን በተባለው ጊዜ እንዲሁም ቀደም ብለው ከፍለው ቢጨርሱም ቤቱን መረከብ እንዳልቻሉ ይገልፃሉ።

የ2010 ተመዝጋቢዎች በሳይት "ሲ" እና "ዲ" ተከፍሎ ቤታቸው እየተገነባ እንደሆነ ቢነገራቸውም፣ በሳይት "ሲ" ያለው የግንባታ ደረጃ ከ35 በመቶ እንደማይበልጥ እና የሳይቲ "ዲ" ግንባታ ደግሞ ወደ 50 በመቶ እንደደረሰ ተናግረዋል።

በውላቸው መሠረት በ 2 ዓመት ጊዜ ቤታቸውን እንደሚረከቡ የተገለፀላቸው የቤት ባለቤቶች፣ 5 ዓመት መጠበቃቸውን እና ቤቱን ማግኘት አለመቻላቸውን በቅሬታ አንስተዋል።

ቤቱን ለግለሰቦቹ ከማስረከብ ይልቅ ያላለቀውን የቤት ግንባታ በማስያዝ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ከአዋሽ ባንክ 800 ሚሊየን ብር መበደሩን ለማወቅ ተችሏል።

ግለሰቦቹ ቤታቸውን ማግኘት ባይችሉ እንኳን የከፈሉት ገንዘብ እንዲመለስላቸው ቢጠይቁም፣ ለቤቱ ከከፈሉት ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ተጨማሪ ሌላ 4 ሚሊየን ብር በ3 ቀናት ውስጥ እንዲከፍሉ እና ድርጅቱ በ12 ወራት ውስጥ ቤቱን አጠናቆ እንደሚያስረክባቸው በመግለፅ ይህ ካልሆነ ግን ድርጅቱ ጉዳዩን ወደሚፈታው የህግ አካል ለመሄድ እንደሚገደድ መግለጹን ተናግረዋል።

እኛው ተበድለን እያለ እንደበደለ ሰው ተቆጥረን ይህ መሆኑ ትክክል አይደለም የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ የሚመለከተው አካል መፍትሔ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል፡፡

አሁንም ቢሆን የምንፈልገው የከፈልንበትን ቤታችንን ነው ሲሉ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የቤት አልሚውን ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

Via EthioFM

@etconp
👍16
Ethio Construction Engineering
Further on wall system ባለ ብሎኬት ግድግዳ Further on wall system ባለ ብሎኬት ግድግዳ - ብሎኬት በመደርደር የምትሰራው የ ግድግዳ አይነት ነው - ባሀገራችን በ 3 size ገበያ ላይ አለ * ባለ 10 * ባለ 15 * ባለ 20 -በቀን ቢበዛ እስከ 5 ኮርስ ቢደረደር ይመከራል mortarኡን እንዳይጫነው እና ጥንካሬ እንዳያሳጣው። - ውሀ በጣም መጠጣት…
Northern Ethiopia cultural housing style

- ከጥንት ከ አክሱማውያን ዘመን ጀምሮ ሲወርድ ሲዋራረድ የነበረ የቤት አሰራር ዘይቤ ነው።

- ድንጋይ በ ጭቃ በማጣበቅ ከ አንድ በላይ ወለል(multistory) በመስራት ከሌሎች ባህላዊ የቤት አሰራሮች ይለያል።

- ባህላዊው አሰራር ጣራው ሚለብሰው
በ ሳር ነው።

ይሄን አይነቱን ቤት ለመስራት ቅደም ተከተሎች

፩. ከ 50 እስከ 120ሳንቲ ስፋት ያለው
እስከ 1.50 ሜትር ጥልቀት ያለው
ጉድጓድ መቆፈር መሰረት ለመጣል

፪. ጠንከር ያለ ባልጩታማ ድንጋይ
መደርደር በጭቃ በማጣበቅ

፫. ልክ መሰረት ጥላችሁ የመጀመሪያውን ወለል (ground floor) ስትጨርሱ የመጀመሪያው ወለል አናቱን በወፋፍራም እንጨት ትረበርቡታላችሁ ለ ሶሌታ (slab) መስሪያ ከ ዛም ጭቃ ይመረጋል ወለሉ።

፬. ጣራ ስራ የተለመደውን አሰራር መተግበር ይቻላል።

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Youtube:- https://youtu.be/qIpy-LMQ8QE
👍12
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Philemona7) via @like
👉የአዲስ አበባ አዳዲስ ገፅታዎች!
.
🙏ውብ ምሽት ተመኘን🙏
.
✋Addis Ababa Ethiopia ❤️

@etconp
❤5👍1
👉ከመገናኛ ወደ ቦሌ በሚወስደው መስመር ላይ የሚገኘው የኢምፔሪያል ተሸጋጋሪ ድልድይ የቀኝ ክፍል ከዛሬ ጥዋት ጀምሮ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል።

የአዲስ አበባ መገዶች ባለስልጣን ፤ የተሸጋጋሪ ድልድዩን የግራ ክፍልና ሌሎች የመንገድ ግንባታውን ቀሪ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሠራ እንደሚገኝ አሳውቋል።

Via AARA

@etconp
👍8🤡1🎃1
👉ኮንስትራክሽን ክሌም
          **    *
🏷የኮንስትራክሽን ክሌም ለመስራት የውሉ የክፍያ መንገድ ላምፕ ሰም ወይስ አድሜዠርመንት የሚለውን መለየት ግድ ነው።

➡️የውሉ አይነትም ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(DBB) ወይም ዲዛይን ቢዩልድ(DB) ስለመሆኑ  መለየት ይገባል።

➡️DBB እና DB የተለያየ ጀኔራል ኮንዲሽን ይጠቀማሉ።ለምሳሌ FIDIC 2017 Red Book ለDBB እና Yellow Book ለDB መጠቀም ይቻላል።

➡️የክፍያ መንገዱ ላምፕ ሰም ወይም አድሜዠርመንት መሆኑ ግን የጀኔራል ኮንዲሽን እንድትቀይር አያስገድድም።
ለምሳሌ ፒፒኤ 2011 ቨርሽን ለሁለቱም የክፍያ መንገዶች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

➡️ስፔሻል ኮንዲሽን ላይ የተለወጠ የጀኔራል ኮንዲሽን ክሎስ ያለ እንደሆነ ማረጋገጥም ቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት።

➡️ከዚህ በኋላ ለክሌሙ አግባብነት ያለውን የውል ድንጋጌ፣የህግ ድንጋጌ እና የጀኔራልና ስፔሻል ኮንዲሽን ድንጋጌ መለየትና መስፈርቱን የሚያሟላ ክሌም ማዘጋጀት ይቻላል።

➡️ከዚያም ክሌሙ ለአማካሪ፣ለዲስፒውት ሪቪው ቦርድ፣ለአርቢትሬሽን ወይስ ለፍርድ ቤት መቅረብ እንደሚገባው ለመለየት ጀኔራል ኮንዲሽኑን እና በዋናነት ስፔሻል ኮንዲሽኑን ማየት ይገባል። አመሰግናለሁ

Via ጉባዔ አሰፋ

@etconp
👍18👌3❤1
👉በነገራችን ላይ የመወያያ ግሩፓችን @COTMp በቀን ብዙ ጥያቄዎች ይስተናገዱበታል።

🚧ከ 7900 በላይ ቋሚ አባላት አለው።

🚧ብዙዎቻችን እንደ ቤተሰብ ሆነንበታል ምክንያቱም ሁሉም ጥያቄዎ ለመመለስ በደስታ የሚጠብቅበት ግሩፕ ነው።

🔖ጥያቄ? ካለዎት፣ ሌሎችን ማገዝ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉን።👇

https://t.me/COTMp
👍6
👉የአገር ውስጥ ጦርነት እና የኮንስትራክሽን እቃወች የዋጋ ንረት ከኮንስትራክሽን ውሎች አንጻር ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት (Force Majeure) ሊባል ይችላል?

➡️የሀገር ውሰጥ ጦርነት በባህሪው ግጭት በለባቸው አካባቢወች የኮንስትራክሽን ስራወችን የማስቆም እና የተጀመሩ ግንባታወችን እስከመውደም እና የግንባታ ቁሳቁስ መጥፋትን ሊያስከትል እንደሚችል ይታመናል፡፡

➡️የአገር ውስጥ ጦርነት ባለበት አገር ውስጥ ሆኖ በቀጥታ ግጭት የሚካሄድበት ቦታ ባይሆን እንኳ በጦርነቱ ምክንያት በኮንስትራክሽን ስራወች ላይ የተለያ ጫና መፈጠሩ አይቀርም፡፡   

➡️በዚህም ምክንያት የውል ህግ፣የግዥ ህግ፣ፊዲክ እና አገራችን ለኮንስትራክሽን ውሎች የምትጠቀምባቸው ጀኔራል ኮንዲሽኖች የሀገር ወስጥ ጦረነትን በተመለከተ ድንጋጌወችን አካተው ይገኛሉ፡፡ይህን የህግና የውል ሁኔታ በአግባቡ ተገንዝቦ መፍትሄ መስጠት ውልን ከሚያስተዳድሩ አካላት የሚጠበቅ በመሆኑ እና በጉዳዩ ላይ ለበለጠና ለዳበረ ውይይት መነሻ ግንዛቤ መፍጠር ደግሞ ከዘርፉ ባለሙያወች የሚጠበቅ በመሆኑ ይህ ጸሁፍ ተዘጋጅቷል፡፡
                       
👉በውል ህግ በተለይ በፍትሐብሄር ህግ ስለውሎች በጠቅላላው በሚደነግገው ክፍል በአንቀጽ 1791(1) ላይ ከተዋዋይ ወገኖች አንደኛው እንደውሉ ያልፈጸመ እንደሆነ ጥፋት ባያደርግ እንኳ ለሌላኛው ተዋዋይ ወገን የጉዳት ኪሳራ የመክፈል ሀላፊነት እንዳለበት ይደነግጋል፡፡
➡️በዚሁ አንቀጽ 1791(2) ላይ ደግሞ እንደውሉ ያልፈጸመው ወገን ግዴታውን ያልፈጸመበትን በቂ ምክንያት ማቅረብ የቻለ እንደሆነ እና ይሄውም ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት መሆኑ የተረጋገጠለት እንደሆነ የውሉ አለመፈጸም ከሚያመጣው ሀላፊነት ሊድን እንደሚችል ያስገነዝባል፡፡ 
🏷ስለዚህ ከአቅም በላይ የሆነ ሀይል(Force majeure) ሲባል ምን ማለት ነው?የሀገር ውስጥ ጦርነትስ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ተደርጐ ሊወሰድ ይችላል ወይ የሚለውን ማየት አስፈላጊ ነው፡፡
                      
➡️ከአቅም በላይ የሆነ ሀይል ተከስቷል የሚባለው ተቋራጩ ሊያስበው የማይችል እና ግዴታውን ከመወጣት ፍጹም በሆነ ሁኔታ የሚከለክለው ነገረ ሲከሰት ስለመሆኑ የፌዴራል ፕሮክዩርመንት ዳይሬክቲቭ አንቀጽ 49 ያስቀምጣል፡፡
➡️በዚሁ በፌዴራል ፕሮክዩርመንት ዳይሬክቲቭ ላይ አለማቀፍ ወይም የሀገር ውስጥ ጦርነት ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ተደርገው እንደሚቆጠሩ በግልጽ ያስቀምጣል፡፡
➡️ፊዲክ ሬድ ቡክ 1999 ቨርሽን ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ለሚለው በክሎስ 19 ላይ ትርጉም አስቀምጦለታል፡፡በዚህም ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ልዩ ሁኔታ ሲሆን ከተዋዋዮች ቁጥጥር ውጭ የሆነ፣ተዋዋዮች ውል ውል ከመግባታቸው በፊት ሊያውቁትና ሊያስቡት የማይችሉት፣ከተከሰተ ተዋዋዮች ሊያስወግዱት የማይችሉት እና ክስተቱ በአንደኛው ወገን ችግር ያልመጣ መሆን ይገባዋል፡፡

➡️ይሄው ፊዲክ ሬድ ቡክ ጦርነት፣የሀገር ውስጥ ጦርነት እና ሽብር ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ተደርገው እንደሚወሰዱ ዘርዝሮ አስቀምጧል፡፡

➡️በተጨማሪም ፒፒኤ 2011 ክሎስ 18 ላይ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያትን በሚመለከት አስቀምጧል፡፡በዚህም ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ማለት ከተቋራጩ ቁጥጥር ውጭ የሆነ እና የውል ግዴታውን ለመወጣት የማያስችለው ፍጹማዊ ሁኔታ ነው፡፡
➡️ፒፒኤ 2011 የሀገር ውስጥ ጦርነትን ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት አድርጐ ያስቀምጠዋል፡፡
                
➡️ስለዚህ የሀገር ውስጥ ጦርነት ከኮንስትረክሸን ውሎች ጋር በተየያያዘ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ተደርጐ ይወሰዳል ከተባለ ሂደቱና ውጤቱ ምን ይመስላል የሚለውን ማየት አስፈላጊ ነው፡፡

➡️ሂደቱን በተመለከተ ጀኔራል ኮንዲሽኖችም ሆነ የህትሀብሄር ህጉ በተለይ የውል ግዴታየን ለመፈጸም የማያስችል ከአቅም በላይ የሆነ ሀይል ገጥሞኛል የሚለው ተዋዋይ ወገን
*ሁኔታውን ለሌላኛው ተዋዋይ ወገን ማሳወቅ ወይም ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፣
* ሁኔታውን ተቋቁሞ የውል ግዴታውን ለመወጣት ጥረት ማድረግ ይኖርበታል
*⃣ከአቅም በላይ የሆነው ሁኔታ የሚያስከትለውን ጉዳት መጠን በሚችለው መቀነስ ይጠበቅበታል፡፡ 
*ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት መከሰቱ ከተረጋገጠ ተዋዋዩ ወገን ግዴታውን አልፈጸመም በሚል ለሌላኛው ተዋዋይ ወገን ኪሳራ ለመክፈል የሚገደድበት አግባብ አይኖርም፡፡እንደውም ተቋራጩ እንደውሉ ሁነኔታ በገጠመው ከአቅም በላይ የሆነ መክንያት የደረሰበትን ተጨማሪ ወጭ እንደ ሰራተኛ ዲሞቢላይዜሽን ያሉ ወጭወችን ከአሰሪው ላይ ለመጠየቅ የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል፡፡በተጨማሪም ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ ለመስጠት በቂ ምክንያት ይሆናል፡፡እንደውሉ ልዩ ሁኔታ ውል ለማቋረጥም ምክንያት ተደርጐ ሊወሰድ ይችላል፡፡
          
➡️ሌላው የኮንስትራክሽን እቃወች የዋጋ ጭማሪ/መናር በተለይ ተዋዋዮች በውላቸው ላይ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ተደርጐ እንደሚቆጠር በግልጽ ካልጠቀሱ በስተቀር ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ተደርጐ እንደማይቆጠር የፌዴራል ፕሮክዩርመንት ዳይሬክቲቭ አንቀጽ 49 ይደነግጋል፡፡ፒፒኤ 2011 ደግሞ የዋጋ መናር ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ተደርጐ አይወሰድም በሚል ያስቀምጣ

➡በመሰረቱ የግንባታ እቃወች ዋጋ ንረት ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ተደርጐ የማይወሰድበት መነሻው በኮንስትራክሽን ውሎች የዋጋ ንረት ማካካሻ መኖሩን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ ምክንያታዊ ግምት አለ፡፡ነገር ግን በአንዳንድ ክልሎች የኮንስትራክሽን እቃወች ዋጋ ንረት ማካካሻ የማይተገበርበት ሁኔታ በመኖሩ ተቋራጮችን ለከፍተኛ ኪሳራ ይዳርጋል፡፡

🏷ስለዚህ ተቋራጮችም ሆነ አሰሪዎች በሀገራችን በቅርብ ጊዜያት የተከሰቱት የሀገር ውስጥ ጦርነትና የኮንስትራክሽን እቃወች የዋጋ ንረት የሚኖራቸውን የውልና የህግ ውጤት በመረዳት የተጀመሩ የመሰረተልማት ግንባታወች እንዲጠናቀቁ ለማስቻል በሚያመች መንገድ ህጋዊና ሚዛናዊ የውል አስተዳደር ስራወችን በብስለት መፈጸም አስፈላጊ መሆኑን ለመጠቆም እወዳለሁ፡፡

Via Gubaie Assefa

@etconp
👍16👏2😱1👌1🕊1
👉የግንባታ ስራና ሰራተኛ ነገር

➡️በሀገራችን የግንባታ ግብዓቶች መወደድ እንዳለ የታወቀ ነው ምክንያቶቹንም እንረዳለን።
*⃣የግንባታ ሰራተኞች ክፍያ መወደድ ግን ከኑሮ ውድነት ጋር አያይዘን በመጠኑ ብንረዳም ሙሉ ለሙሉ ለመቀበል ግን ከባድ ነው።

➡️ሰባ በመቶ አካባቢ ወጣት ይዘን ፣ ከሰላሳ በመቶ በላይ ሾል አጥ የሰው ሃይል ኖሮን ለአናጢ በቀን 800 እንደውም አንዳንድ ቦታ እስከ 1000 ብር ግንበኛ ለሳኝ  የብረት ሰራተኛን አይተን ቀጥረን ለቀን ሰራተኛ  300 ብር ድረስ ገበያው ላይ እንደሚከፈል እናያለን ።

➡️ይሄንን ችግር እና የግንባታ ዘርፍ ለብዙ ወጣቶች የስራ እድል ሊፈጥር መቻሉን አይቼአለሁ።
*⃣እንዲሁም በቅርቡ በካናዳ የግንባታ እና ሪል እስቴት ዘርፍ ላይ በተካሄደ የግንባታ ሰራተኞችን በተመለከተ የቀረበ ጥናታዊ ጽሁፍ ሲቀርብ በቦታው ነበርኩኝ።
*⃣በቀጣይ 5 ዓመታት ውስጥ ከ750ሺህ በላይ የግንባታ ሰራተኞች ጡረታ እንደሚወጡ እና ካለባቸው የቤት እጥረት አንጻር ላሰቡት ግንባታ ከ2.5ሚሊየን በላይ የሚሆኑ የግንባታ ሰራተኞችን ወደ ሀገራቸው ለማስገባት እቅዱ እንዳላቸው ስለሰማሁ እድሉን የሀገራችን ወጣቶች ቢጠቀሙበት ብዬ አስቤ ነበር።

➡️አስቤም አልተቀመጥኩም ነበር። ከጥቂት ዓመታት በፊት አስበው የነበረ የግንባታ ሰራተኞች በተለይም አናጢ፣ ስካፎልደሮች፣ ግንበኞች የሚያሰለጥን ተቋም የመክፈት እቅዴን ቆስቁሼው ፈቃድ የሚሰጠው አካል ዘንድ ቀርቤ አስረድቼ ነበር ።
*⃣ምን ያደርጋል! ታዲያ የመስፈርታቸው ጋጋታ  ሾለ ስራው የማያውቅ ባለሙያ እንዳዘጋጀው በግልጽ ቢያሳይም በእነሱ መስፈርት እንዴት መስራት እንደሚቻል አጥንተን አቀረብን ...ግን ሊረዱት አልቻሉም እኛም ልንረዳቸው አልቻልንም።
*ለክፍል ውስጥ ስልጠና በቂ ቦታ አዘጋጅተን፣ ግንባታ ሾል ላይ በመሰማራታችን በቂ የግንባታ  መሳሪያዎች እንዳሉን ነግረን በብዛት የተጠየቅነው ስካፎልዲንግ በየአይነቱ ከነ መገጣጠሚያዎቹ እንዳሉን አስረድተን፣ ሰልጣኞች ተግባራዊ ልምምድ የሚሰሩባቸው  በተለያዩ ደረጃዎች ላይ የሚገኙ ጅምር ህንጻዎች ከበቂ መለማመጃ ሜዳዎች ጋር....ሌላም ብናቀርብም ....የክፍል ውስጥ ስልጠና የምትሰጡበት ቦታ እና የመስክ ስልጠና የምትሰጡበት አንድ ጊቢ ውስጥ መሆን አለበት ካልሆነም ከሶስት መቶ ሜትር ርቀት በላይ መሆን የለበትም በሚል ሳይሳካ ቀረ...

➡️እኛ አዳዲስ ፈቃደኛ የሆኑ ወጣቶችን በየሳይቱ እየተለማመዱ እንዲሰሩ በማድረግ ለስራዎቻችን ለወጣቶቻችንም ለዘርፉም ሳይት ላይ የሰለጠኑ  organic carpenters, scaffolders እንዲወጡ እናበረታታለን ውጤቱም አርኪ ነው።

➡️ነገር ግን ምዕራብ ሀገራት በርካታ የተፍታቱ እጅና እግሮች ያላቸው ጥቂት ደግሞ በቋንቋቸው ሊግባቧቸው የሚችሉ በርካታ የግንባታ ሰራተኞችን እየፈለጉ.... *⃣ሀገራችንም ብዙ እየፈለገች ገንቢዎችም አብዝተው እየከፈሉ በቂ የሆነ የሰለጠኑ ወጣቶችን በማፍራትና በኤምባሲዎቻችን ውጤታማ የውጭ ግንኙነት በማድረግ ቢያንስ መቶ ሺህ ወጣቶችን መላክ ቢቻል ለሀገር የሚጠቅም ነገርን ዝም ብሎ ማለፍ አቅቶኝ ጻፍኩት።

➡️አንዳንዴ ምናለ መንግስት አንድ ዩንቨርስቲ ቢሰጠኝና ወጣቱን ስራ በስራ ባደረግኩት ብዬም እመኛለሁ። በእርግጠኝነት በዚህ ወቅት ከዩንቨርሲቲዎቻችን ከወጡት ምሩቃን ይልቅ ባለ እጆቹ ተፈላጊዎች ናቸው ።

🏷የምትችሉ አቅምና ብቃቱ ያላችሁ ብታሳኩት ደስ ይለኛል ሀሳቤንም በነጻ ለማካፈል ዝግጁ መሆኔን እገልጻለሁ።

Via Desalegne Kebede

@etconp
👍33👌4🏆3
👉በስልጠና የዳበረ እውቀት ለስራ ውጤታማነት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡

➡️በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች እውቀትና ክህሎታቸውን በተለያዩ ስልጠናዎች ሲያዳብሩና ሲያሻሽሉ በዘርፉ አመርቂ ውጤት ማምጣት ይቻላል፡፡

➡️ይህን የተረዳው የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስትቲዩት ጋር በመተባበር ለተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ባለሙያዎች ስልጠናዎችን በመስጠት የፈፃሚዎችን የመፈፀም አቅም እንዲሻሻል እያረገ ይገኛል፡፡

➡️ቢሮው የያዝነውን ሳምንት ጨምሮ ለተከታታይ 12 ቀናት ከቢሮውና ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ የኮንትራት አስተዳደር ፣ የፕሮጀክት ኦዲት ፣ የምህንድስና ግዥ ፣ የላብራቶሪ  እንዲሁም የዲዛይንና ዋጋ ተከላ ባለሙያዎች በ FIDIC, tender and bid procedure, construction manual, , PPA contract administration, claim and dispute resolution, ዙሪያ የሚያተኩር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

➡️በስልጠናው ከ110 በላይ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን ከኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት እና ከስራ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የተውጣጡ ሰራኞችም ተሳታፊ ሁነዋል፡፡

➡️ስልጠናው የስራ ተነሳሽነትን የሚፈጥር፣ አነቃቂ እንዲሁም ጉድለቶችን በመለየት የማሻሻያ እርምጃዎችን መውሰድ የሚያስችል እንደሆነ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡

*የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ታህሳስ 25/2015 ዓ.ም

@etconp
👍12🙏2
👉የአርማታ ብረት ላይ የሚታዩ ችግሮች /ILLNESS IN REINFORCEMENT CONCRETE/

➡️1. á‹áŒˆá‰ľ/Corrosion in reinforcement bar/

When the rebar is exposed to outer environment other than concrete it will rust /corrode As you guys know know reinforcement counters tension as a result of corrosion the tension member fails it’s causes tension failure

*⃣የፌሮ መዛግ - ፎሮ ከ አርማታ እቅፍ በወጣ ጊዜ ዝገት ያስከትላል ለምሳሌ አፈር ላይ ረዥም ጊዜ ከተኛ ይዝጋል ወይም ደግሞ ለረዥም ግዜ coloride ያለበት ወይም ጨዋማ ውሀ ከነካው ይሄም tension failure /ውጥረትን መቋቋም የማይችል ባለፌሮ አርማታ መዋቅር(RC structure)  ይሆናል።

➡️2.  Carbonation of concrete
 
Is the chemical reaction between carbon dioxide in the air and calcium hydroxide and hydrated calcium silicate in the concrete to give mainly carbonates. This slowly changes the PH of concrete.

*⃣Carbonation - አርማታችን  በከባቢያችን(አየር)  ካሉ “ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ” ፣ “ካልሲየም ሀይድሮ ኦክሳይድ” እና “ሀይድሬትድ ካልሲየም ሲልኬት” ጋር በመዋሀድ ወደ ካርቦኔት ይቀይረዋል ይኼም PH value alter እንዲያረግ ያረጋል፡፡

➡️3. Sanding

Unreasonable sand grading, high mud content too fine soil and sand will also cause the ground sand, affecting the early hydration of cement and concrete condensation. construction vibration is too large: this will aggravate the concrete surface bleeding, thereby reducing the surface strength of concrete. 

*⃣አርማታችን - ከተፈለገው በላይ ነጭ የመሆን(“አመዳም”) የመሆን ነገር ይሄም የሚሆነው   አርማታ በሚቦካበት ጊዜ ያልተፈለጉ ብናኞች ሲዋሀዱ ነው፤ በ አርማታ ውህደት ጊዜ በውሀ እና በሲሚንቶ መሀል ያለው ውህደት temperature ከፍ እንዲል ያደርጋል ይሄም hydration ይባላል ወይም ደግሞ (concrete maturity) ብዙ ብናኞች በገቡ ጊዜ  አርማታችን ቶሎ ይረጋል ከወትሮ ቀደም ብሎ ይሄም የ አርማታው ጥንካሬ (compressive strength) ላይ በ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡

➡️4.  Cracks in concrete

the deformation of concrete it might be due to ratio or quality of Material

*⃣የ አርማታ መሰንጠቅ - ይሄም የሚሆነው አርማታ ስናቦካ የምንፈልገውን compressive strength(fck) ለማግኘት በratio ነው ወይም በመስፈር በዚን ጊዜ የ አሰፋፈር ችግር ካለ in the long run ስንጥቃት ይኖራል ሌላው ደግሞ የ ግብዓት ጥራት ለምሳሌ ደለላማ አሸዋ ከተጠቀምን ስንጥቃት ይበዛዋል ፡፡

➡️5. Concrete segregation

one of the defects of concrete it’s the separation of cement paste and aggregates of concrete from each other during handling and placement.

Via zion

@etconp
👍19❤1
🌏ከ300 ሜትር በላይ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ያሏቸው ከተሞች

🌟የተባበሩት አረብ ኤምሬትሷ ዱባይ ደረጃውን በሰፊ ልዩነት ትመራለች።

🌘 ውብ ምሽት ተመኘን

@etconp
🏆5👍3
👉የትራንስፖርት ሙዚየም ሊገነባ ነው !

➡️የትራንፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የኢትዮጵያን የትራንስፖርት ታሪክ፣ ወቅታዊና የመጪውን ዘመን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የሚያስቃኝ ሙዚየም ለመገንባት የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

➡️የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በተገኙበት የሙዚየሙ ግንባታ የዲዛይን ትውውቅ ተከናውኗል፡፡

➡️ለመገንት የታቀደው ግዙፍ የትራንስፖርት ሙዚየም ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ጥቅም ላይ ያዋለቻቸውን የየብስ ትራንስፖርት አማራጮችን የሚያስቃኝ መሆኑን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

➡️ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ዘመናት የተጠቀሟቸው ታሪካዊ ተሸከርካሪዎች፣ የጭነት መኪናዎች፣ ባቡሮች፣ አውቶቡሶችና የአየር ትራንስፖርት እንዲሁም የውሃ ትራንስፖርትና ልዩ ልዩ የትራንስፖርት አማራጮችና ቁሳቁሶችን አካቶ የሚይዝ ሙዚየም መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

➡️በተጨማሪም ሙዝየሙ ዓለም የደረሰበትን የትራንስፖርት የዕድገት ደረጃ የሚያስቃኝና የኢትዮጵያን የወደፊት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ መሻቶቿን የሚያመላክት ሙዚየም እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

➡️የሙዚየም ግንባታው እውን መሆን ዜጎች የሀገራቸውን የትራንስፖርት ታሪካዊ ዳራ እንዲያውቁ ከማገዙ ባሻገር በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መስክ ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ አካላት ማጣቀሻ ሊሆኑ የሚችሉ ሰነዶች የሚቀርቡበት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

➡️ለሀገር ውስጥና ለውጪ ሀገር ጎብኚዎች ተጨማሪ የጉብኝት አማራጭ በመሆን የሚያገለግል እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

➡️ሙዚየሙ በአዲስ አበባ አፍሪካ ህብረት አካባቢ የሚገነባ ሲሆን ግንባታው በቅርቡ እንደሚጀመርም ተገልጿል፡፡

@etconp
👍6
👉የጨረታ ማስከበሪያ/bid bond/
            ----------------        
➡️የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና አይነት ነው፡፡

*⃣አንድ ለግንባታ ጉዳይ ጨረታ ተሳታፊ የሚሆን ተጫራች ተቋራጭ የሚያቀርበውና ተጫራቹ እንደፈለገ ጨረታውን አቋርጦ እንዳይቀር ለማድረግ እና ምናልባት ተቋራጩ በጨረታው ቢያሸንፍ ውል እንዲገባ ማስገደጃና ዋስትና እንዲሆን ጨረታውን ባወጣው አካል የሚያዝ ዋስትና ነው፡፡

➡️ይህንኑ በሚደግፍ ሁኔታ በፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001ዓ.ም አንቀጽ 40 ላይ ተደንግጓል፡፡

*⃣የዚህ ድንጋጌ ይዘትም ተጫራቹ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት በኋላ ውሉን ለመፈረም ፈቃደኛ ካልሆነ ወይም እንዲያቀርብ የተጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ካላቀረበ ወይም የጨረታ ማስከበሪያው ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ተጫራቹ ራሱን ከውድድሩ ያገለለ እንደሆነ የጨረታ ማስከበሪያው ጨረታውን ባወጣው የመንግስት መስሪያ ቤት የሚወረስ ስለመሆኑ የሚገልጽ ነው፡፡

➡️ጨረታ የሚያወጡ መስሪያ ቤቶችም በሚያዘጋጁት የጨረታ ሰነድ ላይ ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ አብረው ማቅረብ እንዳለባቸው ሊገለጽ ይገባል፡፡የጨረታ ማስከበሪያው መጠንም ጤነኛ ባልሆነ እና ቅንነት በጎደለው ሁኔታ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስቡትን ተጫራቾች ወደጨረታው እንዳይገቡ ከወዲሁ ለማስቀረት የሚያስችል መሆን ይኖርበታል፡፡

➡️ለአሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በምን ሁኔታ መገለጽ አለበት?በህጉ አግባብ ያለመገለጽ ውጤቱስ?(Announcing the successful bidder)

➡️ለአሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ መገለጽ ያለበት እና ሊደርሰው የሚገባ በጽሁፍ በደብዳቤ መልክ ነው፡

*⃣የደብዳቤውም ይዘት የመንግስት መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የተቀበለው ስለመሆኑ፣የአሸነፈበትን ዋጋ፣አሸናፊው ተጫራች ማቅረብ ያበትን የውል ማስከበሪያ መጠን(Amount of performance security) የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡(Federal public procurement directive:አንቀጽ 16.24 እና አዋጅ ቁጥር 649/2001ዓ.ም አንቀጽ 46) ስለዚህ በህጉ አግባብ አሸናፊነቱ ያልተገለጸለትን አሸናፊ ተጫራች ውል አልተዋዋለም በማለት የጨረታ ማስከበሪያ መውረስ የሚቻል አይሆንም ማለት ነው፡፡
    
Via ጉባኤ አሰፋ(የ ኮንስትራክሽን ህግ አማካሪ) 09-75-576924

@etconp
👍17