በጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በሕገወጥ መንገድ እየተወረሩ መሆናቸው ተገለጸ
ይህንን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ቢሮ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ሽፈራው ናቸው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ታኅሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. የቀረበ ሲሆን፣ ሪፖርቱን ለመታደም ከመጡ ተቋማት ከቀረቡ አቤቱታዎች መካከል የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት ክፍት የሆኑ ቦታዎች ሕገወጥ ወረራን ይመለከታል፡፡
ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በግለሰቦች እየተወረሩ መሆኑን፣ በታችኛው ዕርከን የሚገኙ አመራሮች የግብር ደረሰኝ እየሰጧቸው ያላግባብ ቦታዎቹ እየተሰጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የቤቶች ልማት ቢሮ በዚህ ጉዳይ ሁለትና ሦስት ቦታዎች ላይ ችግር እንዳጋጠመው በመግለጽ፣ ለአረንጓዴ ልማት የሚውሉ ቦታዎች ላይ የባለቤትነት ጥያቄዎች መበራከታቸውን ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል፡፡
ቦታዎቹን በሕገወጥ መንገድ ወስደው በክረምት ወቅት ጤፍ የሚዘሩ ግለሰቦች መኖራቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ የፍትሕ ቢሮው በጉዳዩ ላይ በቂ ትኩረት ማድረግ አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ በበኩላቸው፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት ተብለው የተተው ቦታዎችን ከሕገወጦች መከላከል እንደሚገባ በመግለጽ፣ ቦታዎቹን በባለቤትነት እንዲያስተዳድሩት የተሰጣቸው ተቋማት ተገቢውን ማስረጃ በመያዝ ሕገወጥ ወረራውን መከላከል እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡
ለአረንጓዴ ልማት ከተተው ቦታዎች መካከል አንዱ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፍትሕ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ፈይሳ፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በሕገወጦች እንዳይያዙ የሚያስተዳድራቸው ተቋም ኃላፊነት እንደተሰጠው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሊኖረው ይገባል፡፡
በጋራ መኖሪያ ቤቶችና በማኅበር ቤቶች አካባቢ ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በሕገወጦች ተወረዋል የሚሉ ክሶች እንደሚቀርቡ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
እነዚህን ቦታዎች አንዳንድ ጊዜ የሚያስተዳድሩ አካላት ማስረጃ እንደሌላቸውና በዚህም ሳቢያ የሚመጡ ችግሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡
ለአብነትም በአያት አካባቢ 10,000 ካሬ ሜትር ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በግለሰቦች መያዛቸውን አክለዋል፡፡
ለእነዚህ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት ለአረንጓዴ ልማት ክፍት የተደረጉ ቦታዎችን የሚያስተዳድረው አካል ይዞታው በሥሩ እንደሚገኝ የሚገልጽ ማስረጃ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፣ ማስረጃው በሌለበት ግን ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አንዳንድ ጊዜ እውነታው ሌላ ሆኖ በቂ ማስረጃ ባለመኖሩ፣ ፍርድ ቤቶች በተቃራኒው የሚፈርዱበት ሁኔታ አለ ብለዋል፡፡
Via Ethiopian Reporter
@etconp

👍9👌1
➡️የመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራልን የማደስ ስራ በ18 ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ውል መታሰሩ ተገለጸ።
▶️የእድሳት ስራው በ172 ሚሊየን ብር እንደሚከናወንም ተገልጿል።
▶️ከ1936 ጀምሮ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው የመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከ80 ዓመታት በላይ ማገልገሉ ነው የተገለፀው።
▶️የእድሳት ስራው በሁለት ተከፍሎ እንደሚሠራ የተገለፀ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር የህንፃ ቤተክርስቲያኑ የእድሳት ስራ እንደሚከናወን እና ይህም በ172 ሚሊየን ብር ለመስራት ከስምምነት ላይ ተደርሷል።
▶️ሁለተኛው ዙር የእድሳት ስራ ጊቢውን እና አጠቃላይ የጊቢውን መልክዓምድር የማሳመር እና ውበቱን እንደጠበቀ እንዲቆይ የማድረግ ስራ መሆኑ ተገልጿል።
▶️በ3 ወር ውስጥ ጥናት በማካሄድ የካቴድራሉን የእድሳት ስራ ለመስራት ቢጀመርም የጥናት ስራው ብቻውን ወደ 2 አመት አከባቢ ፈጅቷል ነው የተባለው።
▶️በተቻለ አቅም የእድሳት ስራውን ባጠረ ጊዜ በጥንቃቄ ለማከናወን ሲባል የጥናት ጊዜው መርዘሙ ነው የተገለፀው።
▶️የሁለተኛውን ዙር የእድሳት ስራ ለመጀመርም ሰፊ ጥናት እየተደረገ መሆኑ እና የሚያስፈልገው የበጀት መጠንም እየተሰላ መሆኑ ተገልጿል።
▶️ይህ ቤተክርስቲያን በቅዱስ ሲኖዶሱ የሚመራ ቢሆንም ግን እንደ ሌሎች ገዳማትና አድባራት ሁሉ በህዝብ ርዳታ እና ልገሳ የእድሳት ስራው እየተከናወነ መሆኑን የገለፁት የካቴድራሉ አስተዳዳሪ ሊቀ ስልጣናት ቆሞስ አባ ሲራክ አድማሱ ናቸው።
▶️ቅዱስ ሲኖዶሱ እስካሁን 10 ሚሊየን ብር ገቢ ማድረጉን ገልፀው የመላው የእምነቱ ተከታይ ርብርብ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።
Via Ethio Fm

👍13🎃1
ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ለ105 የጎጆ ሮስካ የአገር ውስጥ ተመዝጋቢዎች ዕጣ አወጣ!
ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ትሬዲንግ ኃ/የተ የግል ማኅበር የመኖሪያ ቤት ግንባታ ለማከናወን አቅማቸው አናሳ ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ያዘጋጀውን፤ የጎጆ ሮስካ የቤት ዕቁብ የአገር ውስጥ ሞዴል ዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ግራንድ ኤልያና ሆቴል አከናውኗል።
በዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓቱ ላይ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች፣ የጎጆ ብሪጅ ሀውስ የቦርድ አባላት፣ የዳሽን ባንክ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም በርካታ የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ደንበኞች ተገኝተዋል።
በዕጣውም ኹለት ሳይቶች ማለትም በብሄረ ፅጌ አካባቢ እንዲሁም በአያት ሜቄዶንያ አካባቢ ባሉ ሳይቶች ሲሆኑ፤ በአጠቃላይ በሚገነቡ 118 ቤቶች ውስጥ በብሔረ ፅጌ አካባቢ 42 መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም 63 ቤቶች በድምሩ 105 ቤቶች ዕጣ ይፋ ተደርጓል።
Via አዲስ ማለዳ

👍8
🚧የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን /contract signing date/
➡️የኮንስትራክሽን ውል ስምምነት /contract agreement በአሰሪ/ client እና በተቋራጭ/contractor መካከል የሚፈረምበት ቀን የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
➡️እዚህ ላይ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020 ድንጋጌ እና አንድ ውል ተቋቋመ ሊባል የሚችለው መቸ ነው? የሚለው ማለትም የውል አቀራረብ/offer እና አቀባበል/acceptance በሚመለከት በፍትሀብሄር ህጉ 1681 እና ተከታዮቹ የተደነገገው እና የውል ፎርም ጉዳይ ከግምት ውስጥ መግባት ጭምር አለበት፡፡
➡️የግል የኮንስትራክሽን ውል ጉዳዮችን በሚመለከተው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020(1) ላይ አሰሪና ተቋራጭ ስለሚሰራው ስራ እና ስለዋጋው ካልተስማሙ በስተቀር የተቋራጭነት ውል አለ እንደማይባል ተደንግጓል፡፡
➡️ሌላው ከአስተዳደር መስሪያ ቤት ጋር የሚደረጉ ውሎችን በሚመለከት ስለውሎች በጠቅላላው የተደነገገው ጭምር ተፈጸሚነት እንዳለው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3131(1) ይደነግጋል፡፡
➡️የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በጽሁፍ መደረግ እንዳለባቸው በፍትሀብሄር ህግ ስለውሎች በጠቅላላው በሚደነግገው ክፍል በአንቀጽ 1724 ላይ ተደንግጓል፡፡
➡️የውልን ጉዳይ ስለሚመለከት ማስረጃ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2005(1) ላይ እንደተደነገገው ደግሞ የጽሁፍ ሰነድ በላዩ ላይ የተጻፈውን ቀን በሚመለከት በተፈራራሚዎች መካከል ሙሉ እምነት የሚጣልበት ማስረጃ ነው ይላል፡፡
▶️እንግዲህ ውል የተደረገበት ቀን በአሰሪና ተቋራጭ መካከል የውል ግንኙነት መቋቋሙን ለማረጋገጥ ይጠቅማል፡፡
▶️ውል ደግሞ ከተቋቋመበት ቀን ጀምሮ በተዋዋዮች መካከል እንደህግ እንደሚቆጠር የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731(1) ይደነግጋል፡፡
➡️ሆኖም ግን ውሉ የተደረገበት ቀን የውሉ የግንባታ ስራ መጀመሪያ ቀን ተደርጐ ሊወሰድ አይገባም፡፡

👍15
🚧ከተማችን አዲስ አበባን ስማርት ሲቲ (Smart City) በማድረግ በኩል አይነተኛ ሚና ያለው ዘመናዊ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ ነው።
➡️መሰረታዊ የትራንስፖርት እንቅስቃሴን በማሳለጥ ፣ የትራፊክ ፍሰት ስርዓቱን በማዘመን ፣ በመንገድ ደህንነት ፣በወንጀል እንቅስቃሴ፣ በእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ፣የአምቡላንስ አገልግሎቱን ለማቀላጠፍና ለማዘመን አገልግሎቱን ከአንድ ማእከል መስጠት የሚያስችል ፣ ከመሬት ወለል በታች የተገነባ ባለአራት ወለል (G-4 ) እጅግ ዘመናዊና የዘመኑን የእድገት ደረጃ የዋጀ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ሂደት ላይ ነው፡፡
➡️ፕሮጀክቱ ለግንባታው ወደ አንድ ቢሊዬን ብር እንዲሁም ለቴክኖሎጂ ገጠማ ደግሞ ወደ1 ቢሊዬን ወጪ የሚደረግበት ሲሆን የተጀመረውን አዲስ አበባን በሁሉም መስክ ስማርት ሲቲ (Smart City) በማድረግ በኩል አይነተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡
ምንጭ አአኮቢ

👍13🤩2🤣1
የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል ተመረቀ!
በአዲስ አበባ የተገነባው የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቆ ተመረቀ።
ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኙት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግና የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋቂ ማኅማት ማዕከሉን መርቀውታል።
የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል በቻይና መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ ላለፉት ሁለት ዓመታት ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ማዕከሉ በ40 ሺሕ ስኩዌር ሜትር ላይ ያረፈና የተቋሙን ሥራ ለማሣለጥ የሚያስችሉ ዘመናዊ ቁሳቁስ መሟላቱ ተጠቁሟል።
ጎን ለጎንም የድንገተኛ ክፍል፣ የመረጃ ክፍል፣ ላብራቶሪ፣ የሥልጠና እና የመሰብሰቢያ አዳራሽና ሌሎች መሠረታዊ ክፍሎችን የያዘ ነው ተብሏል።
ማዕከሉ የአህጉሪቱን የበሽታ መከላከል ሥራ በተለይም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ የጤና ሥርዓት ለመዘርጋት የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ታምኖበታል።
የማዕከሉ ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ ማለትም አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችሉ የማጠቃለያ ሥራዎች እየተካሄደ ሲሆን በቅርቡ ተጠናቆ ማዕከሉ ወደ ሥራ ይገባል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።
የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል የተገነባው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2018 የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በገቡት ቃል መሠረት ነው።

👍10
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሲሚንቶ ግብይትን ለመመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ መመሪያ ይፋ አደረገ!
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሲሚንቶ ግብይትን ለመመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ መመሪያ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።
ሚኒስቴሩ አዲስ መመሪያ ይፋ ያደረገው የሲሚንቶ ገበያው በአቅርቦትና ፍላጎት መካከል ያለውን አለመጣጣም እና ህገወጥነት ለማስተካከል፣በአሁኑ ወቅት ሥራ ላይ ያለው የሲሚንቶ የሥርጭት ሥርዓት አፈፃፀሙ በርካታ ክፍተቶች ያለበት በመሆኑ እና ከህብረተሰቡና በዘርፉ ስራ ላይ ካሉ ተዋንያኖች በተገኘው ግብዓት መነሻ በማድረግ መሆኑን አስታውቋል።
በመሆኑም ሚኒስቴሩ የሲሚንቶ ግብይትን ለመመቆጣጠር ካለፈው ዓመት ጀምሮ ስራ ላይ አውሎት የነበረውን የአሠራር መመሪያ ቁጥር 908/2014 በማሻሻል መመሪያ ቁጥር 940/2015 ስራ ላይ እንዲውል ይፋ ማደረጉን አስታውቋል።
መመሪያው ሲሚንቶን ከማምረት እስከ ማከፋፈል እና ይህን የሚያስፈፅሙ የመንግስት አካላት ሊከተሏቸው ስለሚገቡ የአሰራር ስርዓቶችን ያያዙ 13 አንቀፆችን ማካተቱን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
አዲሱ መመሪያ ከፈለጉ በ @etconpbot ፃፉልን

👍8🤯1👌1🤣1
🚧24 ሰአት የሚሰራበት አስገራሚ ፕሮጀክት።
🏠የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን በተቋራጭነት የሚያከናውነው የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ዋና ቢሮ ግንባታ።
💫ሜክሲኮ፣አዲስ አበባ

👍7❤4💔1
💫ትላንት ረቡዕ የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ እና በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ተመርቋል።
➡️ስለ ማዕከሉ ምን ይታወቃል ?
🚧ማዕከሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሌ ጋርመንት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሊዝ ነፃ ባቀረበው በ90 ሺሕ ሜትር ስኩዌር መሬት ስፋት ያለው መሬት ላይ የተገነባ ነው።
🚧የህንፃው ግንባታ ብቻ በ40 ሺሕ ሜትር ስኩዌር ላይ ያረፈ ነው፡፡
🚧የቻይና መንግሥት 80 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት የግንባታውን ሙሉ ወጪ ሸፍኗል።
🚧የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ 25 ወራትን ፈጅቷል።
🚧ማዕከሉ የድንገተኛ አደጋ ኦፕሬሽን፣ የመረጃ፣ የላብራቶሪ፣ የስልጠና ፣ የኮንፈረንስ ማዕከል ፣ ቢሮዎች እና አፓርትመንቶች አሉት።
🚧የማዕከሉ ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ (አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችሉ የማጠቃለያ ሥራዎች) እየተካሄደ ነው።
🚧ማዕከሉ በቅርቡ ሙሉ ስራው ተጠናቆ ወደ ሥራ ይገባል።
🚧በግንባታው ላይ ቻይናውያንና ኢትዮጵያውያን የህንፃ ባለሞያዎች እየተሳተፉበት ነው።
Via ENA

👍7