Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
🏷በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚስተዋለውን ችግር ለመፍታት ከሙያ ማኅበራት ጋር ተቀራርቦ መሥራት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ።
 
📌የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የስነ ምግባር ደንብና ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ከሙያ ማኅበራት ጋር እየመከረ ነው።

📍የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጅነር ሀብታሙ ሴኤታ እንዳሉት የወጪ ሀገራት በኮንስትራክሽን ኢንዳስትሪው ዘርፍ ውጤታማ የኾኑት ከሙያ ማኅበራት ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠራቸው ነው።

💫ኢትዮጵያም ዘርፉን ለማሳደግ የሙያ ማኅበራትን ተሳትፎ ማሳደግ ይገባታል ነው ያሉት።

▶️በኢትዮጵያ ለኮንስትራክሽን ዘርፉ ማነቆ ያሏቸውን ችግሮች ያሏቸውን ጉዳዮችም ኢንጅነር ሀብታሙ አንስተዋል:-

🚧ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው የሚወጡ የምህንድስና ተመራቂዎች በተግባር የተፈተነ ክህሎት አለመኖር

🚧ከ 60 እስከ 70 በመቶ የሚኾኑ ኮንትራክተሮች የዉጪ ሀገራት መኾናቸው

🚧የኮንትራክተሮች የግንባታ መዘግየት፣ የግንባታ ጥራት ማነስ፣ ግንባራ ጀምሮ አለመጨረስ

🚧በርካታ የግንባታ ግብዓቶች ከውጪ የሚገቡ መኾናቸው

🚧በዩኒቨርሲቲዎች እና ሌላ ምርምር ተቋማት የሚሠሩ ጥናቶች በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሚስተዋለውን ችግር በተጨባጭ የማያሳዩ እና በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የማይተገበሩ መኾኑ

🚧ፕሮጀክቶችን የመምራትና የመከታተል አቅም ዝቅተኛ መኾን

🚧ለኢንዱስትሪው ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ መኾን
ስለኾነም ከላይ የተጠቀሱት መሠረታዊ ችግሮችን ለመፍታት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የሚመራበት ፖሊሲ እየተዘጋጀ እንደኾነም ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል።

Via በለጠ ታረቀኝ

@etconp
👍9
THE QUESTION WAS ….

The second question

#2. Suppose Engineers decided to install pile in a given area where they couldn’t get bed rock what kinda pile is it gonna be ?

Reference:- https://t.me/ETCONp/6117

Attach your mobile phone number with your answer

The first person who got it right will be rewarded

Youtube:- https://youtu.be/qIpy-LMQ8QE

Telegram:- https://t.me/ETCONp

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=


Link :- https://www.facebook.com/100064135238834/posts/pfbid02ZD1kHj7doY9GSp7NbrxUMEWSzBZKw5m6yw3rC9quEmXJNoP9vYPZbQ5Miy1KtvBUl/?mibextid=cr9u03

The second person who got the answer right is TEMESGEN BEKELE

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
👍11
🏷በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ዙሪያ የሚስተዋሉ የሥነ-ምግባር ክፍተቶችን ለማስተካከል የባለድርሻ አካላት ሚና እጅግ የላቀ ነው ተባለ

🚧ይህ የተባለው በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በኢትዮጵያ ከሚገኙ በተለያዩ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዘርፎች ለተሰማሩ የሙያ ማህበራት አዲስ በተዘጋጀው ረቂቅ የሥነ-ምግባር ደንብ ዙሪያ በሚኒስቴር መ/ቤቱ አዳራሽ ጥር 8 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

🚧ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር፣ ሚኒስትር ዴኤታ ወንድሙ ሴታ (ኢንጂነር) እንደተናገሩት በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የተሠማሩ የተለያዩ የሙያ ማህበራት በመልካም ሥነ-ምግባር ታንጸው መጓዝ ከቻሉ ለሀገሩቱ የኢኮኖሚ ዕድገትና ለዜጎች የሥራ እድልን በመፍጠር ረገድ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

🚧ሚኒስትር ዴኤታው አክለው እንደተናገሩት የሀገሪቱ ትልቁ በጀት የሚመደብለትና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚጠይቀውን የኮንስትራክሽን ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ የዓለም ተሞክሮና ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ተጠቅመን በሥነ-ምግባር የታነጹ የሙያ ማህበራትን በማቋቋም መንግስትና ባለድርሻ አካላት በአብሮነት መንፈስ ተቀራርበው ሊሠሩ ይገባል ሲሉ ለመድረኩ ተሳታፊዎች አስገንዝበዋል፡፡

🚧ለውይይት በቀረበው የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሥነ-ምግባር ረቂቅ ደንብ በመመርኮዝ ተሳታፊዎች በርካታ አስተያየቶችን አቅርበዋል፡፡

🚧ካቀረቧቸው አስተያየቶች መካከል፡- በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የተሠማራን አካላት ያለብንን የፋይናንስና የቴክኖሎጂ ችግር፣ በሁሉም ክልሎች እኩል የመሳተፍ ዕድል ያለማግኘት፣ የጨረታ አካሄዶች ግልጽነት የጎደላቸው መሆን፣ መንግስት ለፌዴራልና ለክልሎች የብቃት ማረጋገጫ ትኩረት አለመስጠቱና አሠራሩ አድሎ የበዛበት መሆኑ፣ በአዲስ አበባ ተወልደው ላደጉ የዘርፉ ባለሙያዎች በክልሎች ሄደው ለመስራት እድሉን ማግኘት አለመቻላቸውና በአዲስ አበባ እኩል ተወዳዳሪ መሆን ያለመቻል ችግሮች ስላሉብን እነዚህን እና መሰል ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሙያ ማህበሩን አጠናክሮ በማስቀጠሉ ሂደት ላይ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ቀጣይነት ያለው እገዛ ሊደርግልን ይገባል ሲሉ ተሳታፊዎቹ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

Via ሞገስ ዓሊ

@etconp
👍8🙏1
🏷በመዲናዋ በ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ የለሚ ፓርክ ግንባታ በይፋ ተጀመረ

🚧የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የለሚ ፓርክ ግንባታን በይፋ አስጀምረዋል።
 
🚧ፓርኩ 14 ሺህ 400 ሔክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን÷1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጭ ይደረግበታል ተብሏል።
 
🚧የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የፓርኩን ግንባታ ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት÷በመዲናዋ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ሰርቶ ከተማዋን ውብ ለማድረግ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ወሳኝ ነው።
 
🚧የፓርኩ ግንባታም በመንግስት እና በግል ባለሃብቶች የሚሸፈን ነው ብለዋል።
 
🚧ህብረተሰቡ የሚገነባው ፓርክ በእቅዱ መሰረት እንዲከናወን አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@etconp
🤔5👍3🥰1👏1🤣1
🏷BENEFITS OF STRUCTURAL HEALTH MONITORING:

🚧1- New infrastructure such as major bridges are now commonly designed with built-in structural health monitoring systems to ease long term maintenance and to validate design assumptions.

🚧2- Older infrastructure can see their lifespan extended with state-of-the art SHM systems.

🚧3- Structural health monitoring can be used for real-time alarms should a major issue like a landslide or a sinkhole damages an existing infrastructure.

🚧4- Tall structures such as wind turbines, cellular towers and skyscrapers can be closely monitored with the proper instruments.

@etconp
👍6
🏷በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ስራ አፈጻጸም።

🚧በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት በግንባታ ፈቃድ፣ ክትትልና ቁጥጥር በተሰሩ ስራዎች የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

🚧ባለስልጣኑ በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡

🚧በህንጻ መጠቀሚያ፣ ውጭ ማስታወቂያ እና ሌሎች መሰል ዘርፎች የሚስተዋለውን ህገወጥነት ለመከላከል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ተብሏል፡፡

🚧የውጭ ማስታወቂያ ፈቃድ አገልግሎትን ለማሻሻል በ15 ሺህ 093 ሕገ ወጥ ማስታወቂያዎች  ላይ እርምጃ ለመውሰድ ታቅዶ በ70 ሺህ 964 ላይ ተፈጻሚ ተደርጓል፡፡

🚧ባለስልጣኑ በስድስት ወራት ከተለያዩ አገልግሎቶች 73 ሚሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዶ 71 ሚሊዮን ብር ሰብስቧል፡፡

🚧በመጀመሪያው ስድስት ወራት ለ18 ሺህ ተገልጋዮች  የፕላን  ስምምነት  እንዲሰጥ ዕቅድ ተይዞ ለ15 ሺህ 300፣ እንዲሁም ለ8 ሺህ 650 አዲስ እና አዝ ቢዊልት የግንባታ ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ ለ7 ሺህ 439 ተገልጋዮች ተሰጥቷል፡፡ በነዚህ አገልግሎቶች 86 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡

🚧በተያያዘ በመንፈቅ ዓመቱ ለ1 ሺህ 650  ግንባታዎች ማሻሻያና ማራዘሚያ ፈቃድ ለመስጠት በዕቅድ የተያዘ ሲሆን ለ1 ሺህ 316 ተገልጋዮች አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡

🚧እንዲሁም የእድሳት እና ጊዜያዊ የግንባታ ፈቃድ መስጠትን በተመለከተ ለ14 ሺህ 55 ታቅዶ የዕቅዱን 80 በመቶ ወይም ለ11 ሺህ 495 ተገልጋዮች ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡

🚧የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ስራ በመስራት ጥራትና ደህንነትን ለማሻሻል በስድስት ወራት ለ6 ሺህ 200 የግልና የመንግስት ግንባታዎች የግንባታ እርከን የማሳወቅ ስራ ለመስራት ታቅዶ 5 ሺህ ለሚሆኑት ተደራሽ ተደርጓል፡፡

🚧በተጨማሪም 9 ሺህ 608 በሚደርሱ አዲስና ነባር ግንባታዎች የክትትል እና ቁጥጥር ለመስራት ታቅዶ 9 ሺህ 853 ግንባታዎች ላይ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ከዕቅድ በላይ በማሳካት አበረታች ውጤት ተመዝግቧል፡፡ በዚህም የህንጻ መጠቀሚያ ፈቃድ የወሰዱ ህንጻዎች አጠቃቀምን በመከታተል የማስተካከያ እርምጃ ተወስዷል፡፡

🚧በሌላ በኩል 4 ሺህ 740 ሙሉ ለሙሉ ለተጠናቀቁ ሕንፃዎች የመጠቀሚያ ፈቃድ ለመስጠት የታቀደ ሲሆን 3 ሺህ 887 እንዲሁም ለ780 በከፊል ለተጠናቀቁ ሕንፃዎች የመጠቀሚያ ፈቃድ ለመስጠት በማቀድ ለ757 ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡

🚧ባለስልጣኑ በመንፈቁ 3 ሺህ 446 በሚሆኑ በማዕከል ደረጃ ለተሰጡ የውጭ ማስታወቂያ ፈቃዶች ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ በማቀድ 3 ሺህ 412 ላይ ክትትልና ቁጥጥር አድርጓል፡፡

🚧የመሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማትን ፕሮጀክቶች ለማቀናጀት 189 ፕሮጀክቶች የተቀናጀ የመሠረተ ልማት ግንባታ ፈቃድ ለመስጠት የታቀደ ሲሆን የዕቅዱን 91 በመቶ ወይም በ173 ፕሮጀክቶች ላይ ተደራሽ ተደርጓል፡፡

🚧በተያያዘ 322 አዲስና ነባር የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ክትትል  ለማድረግ ታቅዶ 266 ማሳካት ተችሏል፡፡

🚧ብቁና ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለመፍጠር ለ3 ሺህ 110 የሥራ ተቋራጩች፣ ለአማካሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ መሳሪያ አከራዮችና ግብዓት አምራቾች የተደረገ ምዝገባ ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ ለ2 ሺህ 362 መስጠት ተችሏል፡፡

Via አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን

@etconp
👍6🍌1
Quiz number three ( give away quiz) will be posted today on our Facebook page at 9pm(3 local time)

The first person who get the answer right will be rewarded 100 birr mobile card

ዛሬ ከምሽቱ 3 ሰዐት ላይ 3ተኛ የ 100 ብር ኮርድ ሚያሸልም ጥያቄ ፌስቡክ ገፃችን ላይ ይለቀቃል

Yesterday’s winter was TEMESGEN BEKELE

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
👍8
THE QUESTION WAS ….

The third question

#3. Mention at list 4 types of mat foundation and elaborate them

Note:- you can only answer in English

If you can’t manage to answer it within 24hours it’s timeout the question will be canceled

Attach your mobile phone number with your answer

The first person who got it right will be rewarded

Youtube:- https://youtu.be/qIpy-LMQ8QE

Telegram:- https://t.me/ETCONp

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

The person who got the answer right first is BIRUK TEREFE ( second time)

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
👍9
🏷በአዲስ አበባ ከመስቀል አደባባይ ቀጥሎ ትልቁ  የህዝብ አደባባይ ሊገነባ ነው።

🚧በ ትላንትናው እለት 14 ሺህ 400 ሔክታር መሬት ላይ ያርፋል የተባለውና በ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚገነባው የለሚ ፖርክ ግንባታ በይፋ ተጀምሯል።

🚧ከመስቀል አደባባይ ተጨማሪ በመዲናዋ ትልቁ የህዝብ አደባባይ ይሆናል የተባለው ይኸው ፕሮጀክት ወጪው በመንግስት እና በግል ባለሀብቶች የሚሸፈን ነውም ተብሏል።

🚧በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ላይ የተገኙት የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፕሮጀክቱ በ18 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ሥራ እንደሚጀምር አስታውቀዋል።

🚧የፓርኩ ግንባታ መጀመር ለ 1 ሺህ 100 ሰወዎች የስራ እድል የሚፈጥር ሲሆን ከነዚህ ውስጥም ለ 400ዎቹ ቋሚ የስራ እድል እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

🚧ፖርኩ የመኪና ማቆምያ፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ ጂምናዝየሞችን፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ የህዝብ መሰባሰቢያ ስፍራ (public space)፣ የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ፣ የሰርግና ሌሎች አገልግሎቶች የሚውል መናፈሻ፣ ሱፐርማርኬት፣ የቢሮ አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎች፣ መጽሀፍት የማንበቢያ ስፍራና የመሳሰሉት ይኖሩታል፡፡

@etconp
👍5🤮3❤2👏2🥱1
📌የህንጻ ግንባታ የአካል ጉዳት ያለባቸውን ሰዎች ተገልጋይነት ታሳቢ ማድረግ ይኖርበታል

🇪🇹️በኢትዮጵያ የህንጻ አዋጅ አንቀጽ 36 ላይ "ማንኛውም የህዝብ መገልገያ ህንጻ ውስጥ በተሸከርካሪ ወንበር ለመንቀሳቀስ የሚገደዱትን እና መራመድ የሚችሉ ሆኖ ደረጃ መውጣት የሚሳናቸውን ጨምሮ የአካል ጉዳት ላለባቸው ሰዎች የሚመች መዳረሻ መዘጋጀት አለበት" በሚል በግልጽ ተደንግጓል፡፡

▶️ድንጋጌው በአስገዳጅ/obligatory/ ሁኔታ የተቀመጠ ነው፡፡

▶️በተጨማሪም በህንጻ ግንባታ ወቅት የሚሰሩ መጸዳጃ ቤቶች የአካል ጉዳት ላለባቸው ሰዎች የሚመቹ እና ሊደርሱባቸው የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል እነዚሁ መጸዳጃ ቤቶችም በበቂ መጠን/ቁጥር መኖር ይገባቸዋል፡፡

▶️ሌላው ከመሬት ወለል በላይ/above the ground floor/ ከ20(ሀያ) ሜትር
በላይ ከፍታ የሚኖራቸው የህንጻ ግንባታዎች ልዩ ግዴታ አለባቸው፡፡

▶️ይሄውም ህንጻው አሳንሰር ወይንም ተመሳሳይ አገልግሎት ሊኖረው እንደሚገባ እና አሳንሰሩም ያለማቋረጥ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባው የህንጻ አዋጁ አንቀጽ 33(4) እና(5) ይደነግጋል፡፡

▶️ስለዚህ አሳንሰር ከግራውንድ ፍሎር ጀምሮ ወደላይ ከሀያ ሜትር በላይ ከፍታ ላላቸው ህንጻዎች የቅንጦት ሳይሆን በህግ የተቀመጠ ግዴታ ነው ማለት ነው፡፡

▶️ይህን የህንጻ ግንባታ ህግ መጣስ ደግሞ ከህንጻ አዋጁ አንቀጽ 47 ጀምሮ በተደነገገው አግባብ የወንጀል ተጠያቂነትን ያስከትላል፡፡

▶️ስለሆነም የህንጻ አዋጁ በሚያስቀምጠው አግባብ የህንጻ ግንባታዎችን እንዲከናወኑ ማድረግ ከተጠያቂነት የሚያድን ከመሆኑም ባሻገር የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች በህግ የተሰጣቸውን መብት እንዲገለገሉ ምቹ ሁኔታ መፍጠርም መሆኑን ለመጠቆም እንወዳለሁ፡፡

Via ጉባኤ አሰፋ

@etconp
👍6
There will be giveaway quiz which will be posted only on our Facebook page at 9pm(3local time)

be alarmed

The prize is 100 birr mobile card

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
👍1
እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ::
❤8👍2
THE QUESTION WAS

The fourth question

You can workout on a paper and attach the picture on the comment secession

Editing is strictly FORBIDDEN whoever edit it’s answer will be disqualified

#4. What is the active earth pressure for a soil of height 3 meter unit weight of 20kN/M3 and angle of internal friction 30°

Note:- you can only answer in English

If you can’t manage to answer it within 24hours it’s timeout the question will be canceled

Attach your mobile phone number with your answer

The first person who got it right will be rewarded

Youtube:- https://youtu.be/qIpy-LMQ8QE

Telegram:- https://t.me/ETCONp

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=
👍4
Answer

Active earth pressure is when the backfill pushes the retaining wall away from the backfill , Ka( coefficient of active earth pressure) = (1-sinφ)/(1+ sinφ)
የተሞላው backfill ሲገፋው retaining wallኡን Active earth pressure እንላለን
እግሩ ላይ (at the base) = Ka x unit weight of the soil x height = የምናገኘው KN/m² (at the base)
ሶስት መዐዘን ስለሆነ የ triangle area = ½ x B x H
ከፍታችን 3 ሜትር ነው ስለዚህ የሶስት መዐዘኑን area ስናገኝ KN/m unit ይሆናል ምስሉ ላይ ሰርቼላችኋለው effective depth(z) ⅓ from the base ነው የ triangle so ⅓ x H = 1m in our case ስለዚህ pa acts 1m above the base of the retaining wall

እንደዚህ የሰራ አለ?????? መልስ ብቻ ያስቀመጠ አለ without showing the steps

@etconp

Telegram:- https://t.me/ETCONp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Youtube:- https://youtu.be/qIpy-LMQ8QE

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=
👍11
🏷አዲስአበባ ቸርችል ጎዳና  አካባቢ የተገነባው መልካ ኢንተርናሽናል ሆቴል የፊታችን ቅዳሜ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም በይፋ እንደሚመረቅ ተገለፀ።

🚧አቶ መልካ ንዳ፤ የሆቴሉ ባለቤት  ፣ አቶ አንተነህ አየለ፤ የሆቴሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ አቶ አክሱም መልካ፤ ማኔጂንግ ዳይሬክተር በሰጡት መግለጫ ሆቴሉ በ2 ሺ 480 ካሬ ሜትር በሆነ ቦታ ላይ የከተመው መልካ ሆቴል ለግንባታው 700 ሚልየን ብር እንደወጣበት አስረድተዋል።

🚧መልካ ሆቴል ባለአራት ኮከብ ሆቴል ደረጃን ያሟላል ተብሎ የሚገመት ሲሆን ተጨማሪ ግንባታዎችን በማከናወን በቅርቡ የባለአምስት ኮከብ ደረጃን እንደሚያሟላ ተነግሯል።

🚧መልካ ሆቴል 115 ደረጃቸውን የጠበቁ የመኝታ ክፍሎች፣ 2  የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ 2 ትላልቅ ሬስቶራንቶች፣  2 ባሮች፣ 2 የተሟላ ዕቃዎች ያሏቸው የማብሰያ ክፍሎች፣ አንድ ደረጃውን የጠበቀ ጅምናዝየም፣ሳውና እና ማሳጅ፣ ናይት ክለብ፣ 150 መኪኖችን የሚያስተናግድ ፓርኪንግ   እና የመሳሰሉትን ያሟላ ነው።

🚧መልካ ሆቴል ጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም የአዲስአበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጨምሮ ዲኘሎማቶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣  በተገኙበት በይፋ እንደሚመረቅ ተነግሯል።

Via ድሬቲዩብ ሪፖርተር

@etconp
👍9🤮1🎃1
🏷ኮንስትራክሽን በ ታሪክ የኋሊት

🚧ሜክሲኮ አደባባይ የሚገኘው በኖርዌያዊው ነዳፊ ድርጅት በኖርኮንሳልት የተነደፈው የንግድ ምክርቤት ህንጻ።

🚧ህንጻው እኤአ 1961 በ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ግንባታው የተጀመረ ሲሆን ግንባታው ሊጠናቀቅ ሲቀርብ ቀኃስ ከዋናው ህንጻ ነዳፊ ከሚስተር አስከላንድ ጋር በ1964 እኤአ ሲጎበኙት ይታያል።

🚧ኖር ኮንሳልት ከንግድ ሚኒስቴር ህንጻ ውጪ እንደ ልዑል መኮንን ሆስፒታል(ኋላ ላይ ጥቁር አንበሳ የተባለው) ን የመሳሰሉ ታላላቅ ህንጻዎችን የነደፈ ታዋቂ ድርጅት ነው።

Via ዘርይሁን ጉልቴ በኩል

@etconp
👍11