Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
🏷በአዲስ አበባ ከመስቀል አደባባይ ቀጥሎ ትልቁ  የህዝብ አደባባይ ሊገነባ ነው።

🚧በ ትላንትናው እለት 14 ሺህ 400 ሔክታር መሬት ላይ ያርፋል የተባለውና በ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚገነባው የለሚ ፖርክ ግንባታ በይፋ ተጀምሯል።

🚧ከመስቀል አደባባይ ተጨማሪ በመዲናዋ ትልቁ የህዝብ አደባባይ ይሆናል የተባለው ይኸው ፕሮጀክት ወጪው በመንግስት እና በግል ባለሀብቶች የሚሸፈን ነውም ተብሏል።

🚧በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ላይ የተገኙት የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፕሮጀክቱ በ18 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ሥራ እንደሚጀምር አስታውቀዋል።

🚧የፓርኩ ግንባታ መጀመር ለ 1 ሺህ 100 ሰወዎች የስራ እድል የሚፈጥር ሲሆን ከነዚህ ውስጥም ለ 400ዎቹ ቋሚ የስራ እድል እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

🚧ፖርኩ የመኪና ማቆምያ፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ ጂምናዝየሞችን፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ የህዝብ መሰባሰቢያ ስፍራ (public space)፣ የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ፣ የሰርግና ሌሎች አገልግሎቶች የሚውል መናፈሻ፣ ሱፐርማርኬት፣ የቢሮ አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎች፣ መጽሀፍት የማንበቢያ ስፍራና የመሳሰሉት ይኖሩታል፡፡

@etconp
👍5🤮3❤2👏2🥱1
📌የህንጻ ግንባታ የአካል ጉዳት ያለባቸውን ሰዎች ተገልጋይነት ታሳቢ ማድረግ ይኖርበታል

🇪🇹️በኢትዮጵያ የህንጻ አዋጅ አንቀጽ 36 ላይ "ማንኛውም የህዝብ መገልገያ ህንጻ ውስጥ በተሸከርካሪ ወንበር ለመንቀሳቀስ የሚገደዱትን እና መራመድ የሚችሉ ሆኖ ደረጃ መውጣት የሚሳናቸውን ጨምሮ የአካል ጉዳት ላለባቸው ሰዎች የሚመች መዳረሻ መዘጋጀት አለበት" በሚል በግልጽ ተደንግጓል፡፡

▶️ድንጋጌው በአስገዳጅ/obligatory/ ሁኔታ የተቀመጠ ነው፡፡

▶️በተጨማሪም በህንጻ ግንባታ ወቅት የሚሰሩ መጸዳጃ ቤቶች የአካል ጉዳት ላለባቸው ሰዎች የሚመቹ እና ሊደርሱባቸው የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል እነዚሁ መጸዳጃ ቤቶችም በበቂ መጠን/ቁጥር መኖር ይገባቸዋል፡፡

▶️ሌላው ከመሬት ወለል በላይ/above the ground floor/ ከ20(ሀያ) ሜትር
በላይ ከፍታ የሚኖራቸው የህንጻ ግንባታዎች ልዩ ግዴታ አለባቸው፡፡

▶️ይሄውም ህንጻው አሳንሰር ወይንም ተመሳሳይ አገልግሎት ሊኖረው እንደሚገባ እና አሳንሰሩም ያለማቋረጥ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባው የህንጻ አዋጁ አንቀጽ 33(4) እና(5) ይደነግጋል፡፡

▶️ስለዚህ አሳንሰር ከግራውንድ ፍሎር ጀምሮ ወደላይ ከሀያ ሜትር በላይ ከፍታ ላላቸው ህንጻዎች የቅንጦት ሳይሆን በህግ የተቀመጠ ግዴታ ነው ማለት ነው፡፡

▶️ይህን የህንጻ ግንባታ ህግ መጣስ ደግሞ ከህንጻ አዋጁ አንቀጽ 47 ጀምሮ በተደነገገው አግባብ የወንጀል ተጠያቂነትን ያስከትላል፡፡

▶️ስለሆነም የህንጻ አዋጁ በሚያስቀምጠው አግባብ የህንጻ ግንባታዎችን እንዲከናወኑ ማድረግ ከተጠያቂነት የሚያድን ከመሆኑም ባሻገር የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች በህግ የተሰጣቸውን መብት እንዲገለገሉ ምቹ ሁኔታ መፍጠርም መሆኑን ለመጠቆም እንወዳለሁ፡፡

Via ጉባኤ አሰፋ

@etconp
👍6
There will be giveaway quiz which will be posted only on our Facebook page at 9pm(3local time)

be alarmed

The prize is 100 birr mobile card

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
👍1
እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ::
❤8👍2
THE QUESTION WAS

The fourth question

You can workout on a paper and attach the picture on the comment secession

Editing is strictly FORBIDDEN whoever edit it’s answer will be disqualified

#4. What is the active earth pressure for a soil of height 3 meter unit weight of 20kN/M3 and angle of internal friction 30°

Note:- you can only answer in English

If you can’t manage to answer it within 24hours it’s timeout the question will be canceled

Attach your mobile phone number with your answer

The first person who got it right will be rewarded

Youtube:- https://youtu.be/qIpy-LMQ8QE

Telegram:- https://t.me/ETCONp

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=
👍4
Answer

Active earth pressure is when the backfill pushes the retaining wall away from the backfill , Ka( coefficient of active earth pressure) = (1-sinφ)/(1+ sinφ)
የተሞላው backfill ሲገፋው retaining wallኡን Active earth pressure እንላለን
እግሩ ላይ (at the base) = Ka x unit weight of the soil x height = የምናገኘው KN/m² (at the base)
ሶስት መዐዘን ስለሆነ የ triangle area = ½ x B x H
ከፍታችን 3 ሜትር ነው ስለዚህ የሶስት መዐዘኑን area ስናገኝ KN/m unit ይሆናል ምስሉ ላይ ሰርቼላችኋለው effective depth(z) ⅓ from the base ነው የ triangle so ⅓ x H = 1m in our case ስለዚህ pa acts 1m above the base of the retaining wall

እንደዚህ የሰራ አለ?????? መልስ ብቻ ያስቀመጠ አለ without showing the steps

@etconp

Telegram:- https://t.me/ETCONp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Youtube:- https://youtu.be/qIpy-LMQ8QE

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=
👍11
🏷አዲስአበባ ቸርችል ጎዳና  አካባቢ የተገነባው መልካ ኢንተርናሽናል ሆቴል የፊታችን ቅዳሜ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም በይፋ እንደሚመረቅ ተገለፀ።

🚧አቶ መልካ ንዳ፤ የሆቴሉ ባለቤት  ፣ አቶ አንተነህ አየለ፤ የሆቴሉ ዋና ሼል አስኪያጅ፣ አቶ አክሱም መልካ፤ ማኔጂንግ ዳይሬክተር በሰጡት መግለጫ ሆቴሉ በ2 ሺ 480 ካሬ ሜትር በሆነ ቦታ ላይ የከተመው መልካ ሆቴል ለግንባታው 700 ሚልየን ብር እንደወጣበት አስረድተዋል።

🚧መልካ ሆቴል ባለአራት ኮከብ ሆቴል ደረጃን ያሟላል ተብሎ የሚገመት ሲሆን ተጨማሪ ግንባታዎችን በማከናወን በቅርቡ የባለአምስት ኮከብ ደረጃን እንደሚያሟላ ተነግሯል።

🚧መልካ ሆቴል 115 ደረጃቸውን የጠበቁ የመኝታ ክፍሎች፣ 2  የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ 2 ትላልቅ ሬስቶራንቶች፣  2 ባሮች፣ 2 የተሟላ ዕቃዎች ያሏቸው የማብሰያ ክፍሎች፣ አንድ ደረጃውን የጠበቀ ጅምናዝየም፣ሳውና እና ማሳጅ፣ ናይት ክለብ፣ 150 መኪኖችን የሚያስተናግድ ፓርኪንግ   እና የመሳሰሉትን ያሟላ ነው።

🚧መልካ ሆቴል ጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም የአዲስአበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሎ አዳነች አቤቤ ጨምሮ ዲኘሎማቶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣  በተገኙበት በይፋ እንደሚመረቅ ተነግሯል።

Via ድሬቲዩብ ሪፖርተር

@etconp
👍9🤮1🎃1
🏷ኮንስትራክሽን በ ታሪክ የኋሊት

🚧ሜክሲኮ አደባባይ የሚገኘው በኖርዌያዊው ነዳፊ ድርጅት በኖርኮንሳልት የተነደፈው የንግድ ምክርቤት ህንጻ።

🚧ህንጻው እኤአ 1961 በ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ግንባታው የተጀመረ ሲሆን ግንባታው ሊጠናቀቅ ሲቀርብ ቀኃስ ከዋናው ህንጻ ነዳፊ ከሚስተር አስከላንድ ጋር በ1964 እኤአ ሲጎበኙት ይታያል።

🚧ኖር ኮንሳልት ከንግድ ሚኒስቴር ህንጻ ውጪ እንደ ልዑል መኮንን ሆስፒታል(ኋላ ላይ ጥቁር አንበሳ የተባለው) ን የመሳሰሉ ታላላቅ ህንጻዎችን የነደፈ ታዋቂ ድርጅት ነው።

Via ዘርይሁን ጉልቴ በኩል

@etconp
👍11
🏷ለባከነ የግንባታ ጊዜ ''የጊዜ የጉዳት መቀጫ'' /Liquidated damage/

➡️በኮንስትራክሽን ውል ላይ የውሉ የግንባታ ሾል ተብሎ የተቀመጠውን በዲዛይኑ እና ዝርዝር ስፔስፊኬሽኑ መሰረት በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሰርቶ ማጠናቀቅ የተቋራጩ ሀላፊነት ነው፡፡             

➡️ተቋራጩ የውሉን የግናባታ ስራ በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በወቅቱ ሰርቶ ያላጠናቀቀ እንደሆነ ከውሉ ማጠናቀቂያ ጊዜ/completion date/ በኋላ ግንባታው እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ ለእያንዳንዱ ቀን ተቋራጩ የግንባታ መዘግየት ምክንያት ለአሰሪው የጊዜ የጉዳት መቀጫ/Liquidated damage/ የመክፈል ሀላፊነት ይኖርበታል፡፡

⏭በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሲባል ምን ማለት ነው?

▶️አንዳንድ አሰሪዎች/client/ በግንዛቤ እጥረት በውሉ ላይ የተቀመጠው ተቋራጩና አሰሪው ለግናባታው ማጠናቀቂያ የተስማሙበትን የቀን ብዛት/የጊዜ እርዝማኔ/ መቆጠር የሚጀምረው ውሉ በግራ ቀኙ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ እንደሆነ ይረዱታል፡፡ይሄ አረዳድ ስህተት ነው፡፡

⏹በኮንስትራክሽን ውል ስለ ጊዜ አቆጣጠር በተለይ

⏺የግንባታ ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ ፣
⏺ሞቢላይዜሽን ፔሬድ/mobilization period/፣
⏺የሳይት መረከቢያ ቀን/site handover/፣
⏺የስራ መጀመሪያ ቀን/commencement date/ እና
⏺የስራ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ የሚሉትን መረዳት የግንባታ የጊዜ የጉዳት መቀጫ/Liquidated damage/ የሚለውን በአግባቡ ለማወቅ ይጠቅማል፡፡

⏹በመሰረቱ በውሉ የተቀመጠው የስራ ማከናወኛ የጊዜ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው ተቋራጩ የግናባታውን ሳይት ከአሰሪው ከተረከበ በኋላ ነው፡፡ይሄውም ከሳይት ርክክብ በኋላ የስራ መጀመሪያ ቀን /commencement date/ በመሀንዲሱ የሚወሰን እና ለተቋራጩ የሚገለጽለት ይሆናል፡፡

⏹እንግዲህ  በመሀንዲሱ ከሚወሰነው የስራ መጀመሪያ ቀን ጀምሮ በውሉ ላይ የተቀመጠው ቀን ይቆጠርና የስራ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ መቼ እንደሆነ ለማወቅ ያስችላል ማለት ነው፡፡

➡️እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ነገር በኮንስትራክሽን ውሉ ላይ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከውሉ የማጠናቀቂያ ጊዜ አስቀድሞ ለማጠናቀቅ ውል ሊደረግ የሚችልበት እድልም አለ፡፡/Partial completion/ ማለት ነው፡፡የቀን አቆጣጠሩ ከላይ እንደተብራራው የሚሰላ ይሆናል፡፡

*⃣ስለሆነም የግንባታ መዘግየት ቅጣት የሚለው ጉዳይ የሚመጣው ተቋራጩ የውሉን የግንባታ ስራ በውሉ ስራ የማጠናቀቂያ ጊዜ /completion date/ ሳያጠናቅቅ የቀረ እንደሆነ ነው፡፡የገንዘብ ቅጣቱ የሚጣለው በተቋራጩ ላይ ነው፡፡

*⃣ተቋራጩ ግንባታውን ላዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን በውሉ የተቀመጠውን የጊዜ ኪሳራ መቀጫየሚከፍል ይሆናል፡፡በነገራችን ላይ እየተቀጡ መስራት ለተቋራጩ መብትም ጭምር ነው፡፡ይህ ማለት አሰሪው የውሉ ማጠናቀቂያ ጊዜ ስላለቀ ውል አቋርጣለሁ ማለት አይችልም፡፡በውሉ ላይ የተቀመጠው የመዘግየት ቅጣት ጣሪያ መጠን ከሞላ በኋላ ግን አሰሪው ውል ማቋረጥ ይችላል፡፡ውል ከተቋረጠ በኋላ የመዘግየት ቅጣት የሚባል ነገርም የለም፡፡

*⃣*⃣ሌላው ተቋራጩ ወደ መዘግየት ቅጣት እንዲገባ ከመደረጉ አስቀድሞ በአግባቡ መረጋገጥ ያለበት ነገር መሀንዲሱ ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ/Extension of Time / ፈቅዷል ወይስ አልፈቀደም የሚለው ነጥብ ነው፡፡ምክንያቱም ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ ተፈቅዶለት ከሆነ የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜውም አብሮ ስለሚራዘምና ቀኑ ስለሚቀየር ነው፡፡

▶️የሀገራችንን የህግ ማእቀፍ በዚህ ረገድ ምን ይላል? የሚለውን ለመመለስ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1887 እስከ 1895 ድረስ የተደነገጉትን መዳሰስ ይጠይቃል፡፡

*⃣በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1889 ላይ ተዋዋዮች በውላቸው ምናልባት አንደኛው ወገን እንደውሉ ግዴታውን ያልፈጸመ እንደሆነ ወይም አጓድሎ የፈጸመ እንደሆነ ወይም አዘግይቶ የፈጸመ እንደሆነ የሚከፍለውን የመቀጮ መጠን አስቀድመው በውላቸው ለመወሰን እንደሚችሉ በሚፈቅድ መልኩ ተደንግጓል፡፡

*⃣እዚህ ላይ የውል ግዴታን አዘግይቶ መፈጸም ስለሚያስከትለው ቅጣት የሚዋዋሉት በተለይ የግንባታ ጊዜ የጉዳት መቀጫ/liquidated damage/ የሚመለከት ይሆናል፡፡

▶️የመዘግየት ቅጣት ስምምነት ባለ ጊዜ አሰሪው የውሉ ስራ እንዲፈጸምና የቅጣት ገንዘቡንም ለመቀበል መብት እንደሚኖረው የፍ/ህ/ቁ 1890(2) ይደነግጋል፡፡

*⃣እንደዚሁም አሰሪው ኪሳራ ባይደርስበት እንኳ የመዘግየት ቅጣት ገንዘቡ ሊከፈለው እንደሚገባ የፍ/ህ/ቁ 1892(1) ይደነግጋል፡፡እንግዲህ ተቋራጩ ግንባታውን በወቅቱ ያላጠናቀቀው አሰሪውን ሆነ ብሎ ለመጉዳት አስቦ ጉልህ በሆነ ቸልተኝነት ወይም በከባድ ጥፋት መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ አሰሪው በውሉ ከተቀመጠው የቅጣት ገንዘብ በላይ በደረሰበት ትክክለኛ ጉዳት መጠን ልክ ከተቋራጩ ላይ ኪሳራ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 1892(2) ይደነግጋል፡፡

▶️ሌላው የመዘግየት ቅጣት መጠን በዳኞች ሊቀነስ የሚችልበት እድል ስለመኖሩ የፍ/ህ/ቁ 1893 ይደነግጋል፡፡ይሄውም ተቋራጩ ግዴታውን በከፊል የፈጸመ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡

*⃣ይህ ማለት ተቋራጩ ባከናወነው ስራ ሁሉ ቅጣት የሚጣልበት አይሆንም ማለት ነው፡፡

▶️በዚህ ረገድ በሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ አንቀጽ 47(1) ላይ ተቋራጩ ስራውን በውሉ የማጠናቀቂያ ጊዜ ካላጠናቀቀ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን የውሉን ዋጋ 1/1000 እንደሚከፍል እና ይሄውም አጠቃላይ መጠኑ ከውሉ ዋጋ ከ(10-20%)መብለጥ እንደማይችል ይደነግጋል፡፡

*⃣ሆኖም ግን በከፊል ለተከናወነው ስራ መሀንዲሱ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት በሰጠ ጊዜ የቅጣቱ መጠን የሚሰላው ባልተከናወነው ስራ መጠን ዋጋ ላይ በመመስረት ይሆናል ማለት ነው፡፡

▶️በመጨረሻም የመዘግየት ቅጣት በኛ ሀገር ከላይ እንዳየነው እንደቅጣት የሚቆጠርና በህጉ ቅጣቱ እውቅና የሚሰጠው ሲሆን በኮመን ሎው የህግ ስርአት ግን ቅጣት አይደለም፡፡

*⃣በኮመን ሎው የጊዜ የጉዳት መቀጫ በአሰሪው ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር እኩል ሆኖ መመዛዘን የሚኖርበት ሲሆን የቅጣት አይነት ተመሳሳይ ባህሪ ካለው ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡

#ConstructionLaw

@etconp
👍30🙏1
🚧Commonly used slabs construction

📌Flat Slab It stands for reinforced concrete slab. Here the concrete columns are used to provide direct support to the slab. It is also known as beam-less slab since there are no beams in the slab.

📌Conventional Slab Under this slab system, the support to the slab is provided through beams and columns. Here, the density of the slab is small but the depth of the beam is heavy. The load is transmitted to the beams and then to the columns.

📌Hollow Core_Slab Under this slab system, the slabs are precasted. These slabs are suitable when it is required to finish the construction quickly.

📌Hardy Slab Hardy slab is made of hardy bricks. Hardy bricks belong to the hollow bricks which are formed with concrete hollow bricks. The purpose of these bricks is to fill parts of the slab.

📌Waffle Slab Waffle slab alias grid slab stands for a reinforced concrete roof or floor comprising of square grids having deep sides.

*⃣This type of slab is mostly found in the entrance of hotels, malls, restaurants for stunning illustrative view as well as set up artificial lighting.

📌Dome Slab This type of slab is mostly found in temples, mosques, palaces etc. The dome slab is constructed on the conventional slab.

📌Pitch Roof Slab Pitch roof refers to an inclined slab, normally built on resorts for a natural look. With regard to conventional roofing materials, very lightweight tile-sheets are mainly applied in this type of slab.

📌Post Tension Slab This type of slab is tensioned as soon as the slab is constructed. Here, the compression is resisted by providing reinforcement.

📌Projected Slab Projected alias cantilever slab means the slab with one side fixed and the other side is free.

*⃣The type of slab is frequently used in hotels, universities, function halls, etc.

📌Miscellaneous Slab This type of slab is suitable for drawing rooms and kitchen for stockpiling house material.

@etconp
👍13
🏷ስለሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (Retention Money/Bond) እና የጥገና/የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)
             
🚧የሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (Retention Money/Bond)  የሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ የሚባለው በኮንስትራክሽን ውል አስተዳደር ወቅት ሼል ተቋራጩ ሥራውን ፈጽሞ ክፍያ በሚጠይቅበት ወቅት የፕሮጀክቱ  ባለቤት ከግንባታው አማካሪ መሀንዲስ ጋር በመሆን ስለሥራው ጥራት ደረጃ በሚል ሊይዘው የሚችለው ዋስትና ነው፡፡
የሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (retention) ዓላማ የግንባታውን ጥራት ለማስጠበቅ ሲባል ሥራ ተቋራጮች ለአሰሪዎች የሚገቡት ዋስትና ነው፡፡የግዥ መመሪያውም በአንቀጽ 28.5(ለ) ላይ በግልጽ እንደሚደነግገው በእያንዳንዱ የክፍያ ሰርተፍኬት ላይ 5(አምስት) ፐርሰንት የክፍያው ገንዘብ የሚያዝ ይሆናል፡፡

➡️በዋናነት ከተያዘው ገንዘብ ውስጥ 50(ሃምሳ) ፐርሰንት የሚሆነው ገንዘብ ሥራው እንደ ተጠናቀቀ እና ጊዚያዊ የርክክብ ምስክር ወረቀት (provisional acceptance certificate) ከተሰጠ በኋላ ለሥራ ተቋራጩ ይመለስለታል፡፡ የቀረው ገንዘብ ደግሞ እስከ አንድ አመት ድረስ ዋቢ ሆኖ ይቆያል፡፡ ነገር ግን የተቀረው የመያዣ ገንዘብን አስቀድሞ ሥራ ተቋራጩ ለአንድ አመት የሚጸና ዋስትና ማቅረብ ከቻለ የተያዘበትን ቀሪ ገንዘብ ማስለቀቅ ይችላል፡፡

➡️በተመሳሳይ መልኩም የሲቪል ሥራዎችን በተመለከተም እኤአ በ1994 ዓ.ም የወጣው የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ወጥ ውልም ስለ የዋና ገንዘብ መያዣ ዋስትና በአንቀጽ 59(5) እና 60 ላይ ተቀራራቢ ድንጋጌዎችን ያስቀምጣል፡፡

▶️የሪቴንሽን ገንዘብ (retention) የፕሮጀክቱ ግንባታ ተጠናቆ የጊዜያዊ  እና የመጨረሻ ርክክብ ከተፈጸመ በኋላ የተያዘው 5(አምስት) ፐርሰንት ገንዘብ አብዛኛውን ጊዜ ተመላሽ አይሆንም፡፡  በዚህ ሳቢያም ሼል ተቋራጮች ለሌላ ወጪ የሚዳረጉበት ሁኔታ አለ፡፡

*⃣/The law stipulates that the retention bond shall be paid to contractor after provisional acceptance or final acceptance but its applicability is denied by government side most of the time. So, dear contractors, please ask before you bankrupt/

⏹የጥገና ወይም የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)

▶️የጥገና ዋስትና የተበላሹ የግንባታ ግብዓቶችንና የሥራ አሰራር ግድፈቶችን ለመከላከል በሚል ሥራ ተቋራጩ ለፕሮጀክት ባለቤቱ የሚገባው ዋስትና ነው፡፡

*⃣በተለይም ከላይ ስለ ሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (retention) ቆይታ እንደተመለከተው ለአንድ ዓመት ጊዜ የሚያዝበት ምክንያት ከጥራት ጉድለት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመጠገን ነው፡፡

*⃣በሚለቀቅበትም ጊዜ ያለ ቅድመ ሁኔታ ዋስትና ሥራ ተቋራጩ እንዲያቀርብ የሚደረግበት ምክንያት በህንጻው ግንባታ ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ለመጠገን በሚል ነው፡፡

*⃣የጥገና እና ብልሽት አላፊነት መያዣ በዋናነት የዋና ገንዘብ መያዣ ቆይታ እንዳበቃ የሚጀምር ነው፡፡

*⃣በርግጥ ሥራ ተቋራጩ ለባለቤቱ ለተወሰኑ ዓመታት ዋቢ ይሆናል፡፡

🌟ለምሳሌ፡- በሲቪል የግንባታ ሥራዎች በተለይም በፍ/ህ/ቁ 3039 እንዲህ የሚል ይነበባል፡-“ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ካስረከበበት ጊዜ ጀምሮ ስለመልካም አሰራር፣ ስለ ሥራው እና ስለጠንካራነቱ ለ10 (አስር) አመት መድን (guarantee/ warranty) ነው፡፡ በዚህም ጊዜ ውስጥ በሥራው ጉድለት ወይም በተሰራበት መሬት ዓይነት ምክንያት በተሰራው ሥራ ላይ ለሚደርሰው መጥፋት ወይም መበላሸት አላፊ ነው፡፡”

*⃣በተመሳሳይ መልኩ የመንግስት የግንባታ ውሎችንም በተመለከተ የፍትሐብሔር ሕጉ ከአንቀጽ 3277-3282 ላይ የ10 (አስር) አመት የብልሽት መድን ጊዜ ያስቀምጣል፡፡
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በቅጽ 18 በሰ/መ/ቁ 101378  በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እና ናሰው ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ ማህበር መካከል በነበረው ክርክር የጥገና ዋስትና (maintenance bond) ሊኖር እንደሚችል ካተተ በኋላ አንድ ሼል ተቋራጭ በሠራው ህንጻ ላይ የተከሠተ እርግጠኛ የአሰራር ጉድለት በሌለበት ሁኔታ ወደፊት የሚታይና የሚከሰት የአሰራር ጉድለት ሊኖር ይችላል በሚል ምክንያት ሼል ተቋራጮች ለሰሩት ሼል የመጨረሻ ክፍያ የማግኘት መብት መከልከል አግባብነት የሌለው መሆኑን እሰገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡


#ConstructionLaw

@etconp
👍22❤3👌1
🔖ማሳሰብያ ለ ውድ ቤተሰቦቻችን

🚧ለ ሁሉም በ መንግስት እና ግል ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ማለትም የ COTM፣ CIVIL፣ ARCHITECTURE፣ HYDROLICS እና ተመሳሳይ ትምህርት ክፍል ላይ የ Telegram Group ኣድሚን ለሆናቹ በ ሙሉ ...

🏷የ ዲፓርትመንታቹ ወይም ክላሳቹ ቴሌግራም ግሩፕ ላይ ኣድሚን ለሆናቹ ብቻ ለግል ጉዳይ ልናነጋግራቹ ስለፈለግን @ETCONpADMIN ላይ እንድትፅፉልን በ ትህትና እንጠይቃለን፡፡🙏

@etconp
👍7
🏗በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በአገሪቱ የሚታየውን ችግር የመፍትሄ ሃሳብ

📌1.E-procurement: በግንባታ ጨረታ አሰራር አጫራቹ ከተጫራቾች ጋር በሰው የሚደረጉ ግንኙነቶች
በweb-based application system (E-procurement) ቢተካ፡ በዘርፉ ያሉትን ማጭበርበርና ሙስናን መቀነስ እንደሚቻል ቻይናን ጨምሮ የብዙ አገሮች ተሞክሮ ያሳያል::

➡️የኢትዮጵያ ሊስት ቢድ (least-bid) የግዥ መመሪያ በመርህ ደረጃ መሰረታዊ ችግር ሳይኖርበት ነገር ግን አፈጻጸሙ፣ በዘርፍ ባለሙያዎች ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅትና ልምድ የሚጠይቅ በመሆኑ: በስህተትና በአድሎ  የታጀበ የቢሮ ኅላፊ እና የጨረታ አዎዳዳሪ/ገምጋሚ ኮሚቴ ውሳኔ፣ ለመርማሪም ሆነ ለመንግስት ካቢኔ “quantum physics” በመሆኑ አገሪቱን ዋጋ እያስከፈላት ነው::

➡️ባለፈው የፌደራል መንግስት ያጸደቀጸ ቀው የግዥ መመሪያ የኮንትራክሽን E Procurement አንዱ አካል በመሆኑ
ቶሎ ወደ ስራ ቢገባ.

📌2.Construction work philosophy: በተለያዩ ሃገራት በተደረገ  ጥናት ግብርና ነክ  ያልሆኑ  ኢንደስትሪ (Non-Farm Related Industry) ምርታማነት (productivity) ባለፍት 40 ዓመታት (ከ1966 እኤአ ጀምሮ) በየዓመቱ የ 1.8% ጭማሪ ሲያሳይ የኮንስትራክሽን ምርታማነት 0.6% ቅናሽ አሳይቷል፣፣ ይሁን እንጅ ኮንስትራክሽን ስራዎች የተናጠል ምርታማነት እድገት ያሳዩ ሲሆን ይህም በግንባታ ማሽነሪዎች እድገት ውጤት የመጣ መሆኑን ሲያትቱ የNon-Farm Related Industry ከፍተኛ የምርታማነት ሚስጥር በ”Mechanization, Automation & Prefabrication” ምክንያት እንደሆነ ያስረዳሉ::

➡️የተለያዩ አገራት ተመራማሪዎች ለኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው መፍትሄ ያስቀመጡት: ዘርፉ ከፍተኛ የሆነ የ”collaboration and working culture” አብዮት እንደሚያስፈልገው ነው::

⏺የተውሰኑ  ጥናቶች ከማኑፋክቸሪግ ኢንደስትሪ ፍልስፍና (ካይዘን፣Lean manufacturing) በመነሳት lean-construction/Agile construction ፊሎዞፊ ለዓለም አስተዋውቀው ይህም design-built; design-built-operate/maintain; Engineering-Procurement-Construction (EPC), Integrated Project Delivery (IPD) የመሳሰሉትን የፕሮጀክት አቅርቦት (project delivery) ዘዴ እንዲፈጠሩና  የፍልስፍናው ተጠቃሚ የሆኑ ብዙ ስኬታም ድርጅቶችን ፈጥሯል::

👉🏾ለምሳሌ የቻይናው CCCC (China construction communication company), Salini Impregio (GERDP Contractor)የመሳሰሉት:: በተጨማሪም የ”reinforced concrete Prefabrication” ቴክኖሎጂም የማኑፋክቸሪንግ ፊሎዞፊ ውጤት ነው::

➡️የ Agile Construction Philosophy የአሜሪካ ፕሮጀክት ማናጅመንት ኢንስቲቲውት (PMI) በ2017 እትሙ ለዘርፍ መፍትሄ መሆኑን በመረዳት በስታንዳርድ መልኩ አዘጋጅቶታል::

*⃣ይሁን እንጅ የኛ ሃገር የዘርፉ ባለድርሻ አካላትና ሙህራን ይህን የsynergistic/collaboration ፍልስፍና በተገቢው መንገድ ወደዘርፉ ማዋሃድ ሲገባቸው እነ Ohno በጃፓን ቶዮታ (manufacturing industry) ላይ ምርታማ የሆኑበትን ካይዘን በግንባታው ዘርፍ ለውጥ ያመጣል በማለት: በስልጠናና ስብሰባ የባለሙያውን ጊዜ በመግደል ከእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ አይነት: ተግዳሮት ሲፈጥሩ ይታያል::

➡️የሚያሳዝነው የካይዘን አባት Ohno የፍልስፋናው መነሻ Henry Ford & Edward Deming [Pioneer Engineers for manufacturing production's Process-Productivity]  እና Shewhart & Deming (1939) [የcontinuous improvement cycle/PDCA ያገኙ ስታስቲሻን] እንደሆኑ ይናገራል::

📌3.የConcrete Prefabrication Plant በዞን ከተሞች መክፈት: የ”concrete prefabrication technology በ1905 በሊቨርፑል የአለክሳንደር ብሮዴ ግኝት ሲሆን ይህም በሁለተኛው አለም ጦርነት ብዙ ቤቶች በመውደማቸው፡ ሃሳቡ በስፋት ዳብሮ  የወቅቱን ከፍተኛ የሆነ የቤት ችግር የመፍቻ መንገድ ነበር፣ በተለይ በጀርመንና በፈረንሳይ::

👌የሰለጠነ ባለሙያ እጥረት ከጊዜ ወደጊዜ መጨመሩም የመስክ ግንባታን (site construction) በፋብሪካ በተመረቱ ተመሳሳይ የግንባታ አካል (precast elements) እንዲቀየር ከፍተኛ አስተዋጾ አድርጓል::

🌟ቻይና 57 ፎቅ በ2 ሳምንት ሰርታለች፣ ዘንድሮም 1000 የኮሮና ታማሚ የሚያስተናግድ  25, 000 ስኩየር ካሬ ላይ G+1, ሆስፒታል በ10 ቀን ሰርታለች:: በፋብሪካ የሚመረቱ አካሎች ከፍጥነት በተጨማሪ፣ ከአየር ጸባይ ተጽኖ ነጻ ናቸው፡ የብረት ፎርም/ሞልድ ስለሚጠቀሙ ኢኮኖሚያዊና የጥራት አድቫንቴጅ አላቸው፡ ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ ግንባታን ማዛወር ይቻላል።

🇪🇹እኛስ መቼ ይሆን?

Via Matiwos Tsegaye

📩ሀሳብዎ @COTMp ፃፉልን እንወያይበት

@etconp
👍27👏2👌2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🏷የካርል አደባባይ በትራፊክ መብራት ሊቀየር ነው

💫በአዲስ አበባ ከተማ ከብስራተ ገብርኤል ወደ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኘው የካርል አደባባይ የትራፊክ ፍሰቱን የበለጠ ለማሳለጥ ወደ ትራፊክ ሲግናል መብራት ሊቀየር ነው፡፡

🚧የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አሁን ላይ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨነናቅ ችግር ለመፍታት የካርል አደባባይን ወደ ትራፊክ መብራት ለመቀየር ዛሬ ምሽት የግንባታ ስራ ጀምሯል::

@etconp
👍14❤2🤣2👏1🤔1
🏷Different types of concrete utilized in construction works

📌Normal concrete: It is commonly used.

📌Lightweight concrete: With the
inclusion of coarse light aggregate (extended clay aggregate), the insulating properties become superior and it can reduce strength as well as weight.

📌Aerated concrete: It is a type of lightweight concrete. Irrespective of aggregate, aerated concrete comprises of bubbles, which are developed through a chemical process and further enhance the quality of the insulation.

📌Heavy concrete: Specifically, heavy aggregate (e.g. barite, iron ore, steel granulate etc.) having high dry unit weight. Mainly applied for radiation protection.

📌Ultra high performance concrete (UHPC): In this type of cement, furnace cement is utilized in place of Portland cement. It has extreme strength and good stability. It facilitates lean design, cost savings and economic usage.

📌Water impermeable concrete: It is the type of Concrete that contains a strong water-resistant capacity against water penetration. It is mainly utilized to seal some portions of the in the ground.

📌Waterproof_concrete: It has similarity with water-impermeable concrete, inclusion of barriers.

📌Self compacting concrete : In this type of concrete, plasticiser is included, no extra compacting is required, thinly pored surface and complex geometries.

📌Translucent concrete: Glass optical fibres are provided in the fine concrete. They create specific patterns, based on their density and structure, and cause the concrete to become translucent.

📌Refractory concrete: Resists temperatures ranging from 500 to 2000 °C

📌 Recycled concrete: With the help of recycled materials, the aggregate is produced (e.g. building rubble).

📌Concrete screed: It contains small aggregate size to retain thin layers. It is specifically suitable for producing floor layers.

📌Pre stressed concrete: Steel reinforcement is pre-stretched, which produces a strong compressive stress. The properties of concrete are utilized in a superior way to form more organized building parts. The stiffness resists major deflection even with large spans.

📌Textile concrete: It stands for a composite material containing low thickness and stgrong resistance capacity against compression and deflection. There are flexible forms through specific reinforcing materials.

📌Fibre concrete: Fibres are produced from plastic, glass fibre, carbon, natural fibres or similar.

📌Self cleaning concrete: The surface is prepared with photo catalytically effective metal oxides or sulphides. The characteristics like the self-cleansing, pollutant disintegrating effect is obtained by light.

Besides, the surface should be super-hydrophobe (water repellent) or super-hydrophile (water-attractive)

@etconp
👍10👌2
🏷Triple E Hotel

🌟በመዲናችን ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03፣ 22 በተለምዶ ዳውን ታውን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ500 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈው ትሪፕል-ኢ ሆቴል እና ስፓ በትላንትናው ዕለት ተመርቋል።

💫ከአራት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደወጣበት የተነገረለት ይኸው ሆቴል በ4 ዓመት ግንባታው ተጠናቆ የሙከራ ስራውን የጀመረው በሐምሌ ወር ነበር።

@etconp
👍4