Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
🏷የአቃቂ ዞናል ስታዲየም የካፍ ስታንዳርድን እንዲያሟላ አድርጎ ለመስራት የሚያስችል የዲዛይን ክለሳ ተደረገ፡፡

🚧የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በባለቤትነት እያስገነባው የሚገኘው የአቃቂ ዞናል ስታዲየም የካፍ ስታንዳርድን በሚያሟላ መልኩ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ያስችላል የተባለለት የተከለሰ ዲዛይን በዛሬው ዕለት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአማካሪ ድርጅቱ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

🚧በኔማድ የኪነ ህንጻ መሀንዲሶች ኃ/የተ/የግ.ማህበር የተዘጋጀው ይህ ዲዛይን ስታዲየሙ ዕውን በሚሆንበት ጊዜ  የካፍ መስፈርቶችን እንዲያሟላ ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን ሲጠናቀቅም በከተማችን ብቻም ሳይሆን በሀገር-ዓቀፍ ደረጃ በብቸኝነቱና በደረጃው ላቅ ያለ ስታዲየም ሆኖ ለስፖርት ማሕበረሰቡ  አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

🚧ከ25,000 በላይ የተመልካቾች እንዲሁም 140 ቪ.አይ.ፒ መቀመጫዎችን የመያዝ ዓቅም ያለው ይህ ስታዲየም ከዋናው የእግርኳስ መጫወቻ ሜዳ በተጨማሪ ሁለት የማሟሟቂያ ሜዳዎች እንዲሁም ሌላ የታዳጊዎች መጫወቻ  ሜዳ፣የመሮጫ ትራክ፣የአትሌቲክስ ስፖርት ማከናወኛ ስፍራ፣የቤት ውስጥ ውድድር የሚከናወንበት ቦታዎችን የሚያካትት ሲሆን ከነዚህም በተጨማሪ  መሰብሰቢያ አዳራሽ፣የመልበሻ ክፍሎች፣ካፍቴሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች እንደሚሟሉለት ዲዛይኑ በቀረበበት ወቅት መመልከት ተችሏል፡፡

@etconp
👍11🤣1
🏷አርባ ምንጭ ከተማ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት በአፍሪካ ከሚገኙ ምርጥ 10 ከተሞች አንዷ ትሆናለች ተባለ

🚧በአርባ ምንጭ ከተማ በቀጣይ ሶስት ወራት የአረንጓዴ አካባቢዎችን ጨምሮ የመዝናኛ ስፍራዎች እና በዋና ዋና አስፋልት መንገድ በግራና ቀኝ  የማልማት ስራ ተግባራዊ  ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

🚧ከእዚህ በተጨማሪ ከተማዋ ያላትን ተፈጥሯዊ ፀጋ ጥቅም ላይ በማዋል የቱሪስት መስህብ ማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች ከሀገር ውስጥ እና ከውጪ አልሚዎች ጋር በመተባበር እየተሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ማርቆስ ማቲዎስ ለብስራት ሬድ ተናግረዋል፡፡

🚧ይህንኑ እውን ለማድረግ ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡን ያስታወቁት ከንቲባው ከተማዋን ጨምሮ በዙሪያዋ ያሉ የቱሪስት መዳረሻዎችን መጠቀም የሚያስችል ስራ እንደተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

🚧በእዚህም ሂደት የአርባ ምንጭ ከተማን ውበት እና ፈጣን እድገት የሚያመላክቱ የመሰረተ ልማት ስራዎች ግንባታ በማፋጠን ከተማዋን በ2025 በአፍሪካ ከሚገኙ 10 ዋና ዋና ከተሞች አንዷ ለማድረግ ታቅዷል ሲሉ ከንቲባው በተጨማሪነት አንስተዋል፡፡

🚧መንግስትን ጨምሮ መዋለ ነዋያቸውን ፈሰስ በማድረግ ወደ እንቅስቃሴ የገቡ ባለሀብቶች ጋር በመቀናጀት ከተቀመጠው ጊዜ በቀደመ መልኩ እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ አመላክተዋል፡፡

Via ናትናኤል ሀብታሙ

@etconp
❤8👍6👏1
🏷የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር እያስገነባቸው ያሉ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀቶችን በቅርበት ለመከታተል የሚያስችለውን አዲስ አደረጃጀት በመፍጠር ወደ ስራ እንደገባ የሚታወስ ነው፡፡

🚧በአዲሱ የአደረጃጀት የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤቶቹ የመንገድ ፕሮጀክቶች በሚገኙባቸው አካባቢዎች የተቋቋሙ በመሆናቸው፤ ኘሮጀክቶቹን በቅርበት ለመከታተልና ለመደገፍ አስቻይ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡

🚧በዚህም ረገድ ከተቋቋሙት የኘሮጀክት ጽ/ቤቶች መካከልም የፍጥነት እና ልዩ ፕሮጀክቶች ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ስር የአዳማ አዋሽ ፣ የሞጆ-ሐዋሳ እና የኮይሻ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ጽ/ቤቶች ይገኛሉ፡፡

🌟የሞጆ-ሐዋሳ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ፅ/ቤት በአጠቃላይ 17,850,833,680.64 በሚሆን የገንዘብ መጠን 6 የመንገድ ፕሮጀክቶችን (በዲዛይንና በጨረታ ሂደት ላይ ያሉትን ሳያካትት) እያስተዳደረ ይገኛል፡፡

🌟በሌላ በኩል የአዳማ-አዋሽ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ፅ/ቤት በአጠቃላይ 6,688,456,565.74  በሚሆን የገንዘብ መጠን 1 (በዲዛይንና በጨረታ ሂደት ላይ ያሉትን ሳያካትት) የመንገድ ኘሮጀክት እያስተዳደረ ይገኛል፡፡

💫በዚህም መሰረት  የሞጆ-ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ፅ/ቤት እና የአዳማ-አዋሽ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ፅ/ቤት  ያካተቷቸውን ፕሮጀክቶች መረጃ  እናስተዋውቃለን፡፡

💫ከታች የተጠቀሱትን ፕሮጀክቶች አስመልክቶ የአካባቢው ህብረተሰብ እና የመስተዳድር አካላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስተያየትና ጥያቄዎችን ለማቅረብ በአዳማ-አዋሽ እንዲሁም በሞጆ-ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ አካባቢ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ጽ/ቤት ማምራት እንደምትችሉ እየገለጽን ፣ እነዚህ ጽ/ቤቶች የታለመላቸውን ግብ እንዲመቱ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ያሳስባል፡፡

🌟የአዳማ ኪ.ሜ60 የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክ አካባቢ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ጽ/ቤት መገኛ 📍አድራሻ፡- አዳማ ከተማ  ሞኤንኮ ፊትለፊት

🌟የሞጆ-ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ጽ/ቤት መገኛ
📍አድራሻ፡- ሻሸመኔ ከተማ  ሲሲሲሲ ካምኘ ውስጥ

@etconp
👍8
@ETCONp 2015 2nd Quarter Rate .Pdf.pdf
24.3 MB
🏷በ2015 ዓ.ም ሁለተኛ ሩብ ዓመት ተግባራዊ የሚደረግ የግንባታ ሥራዎች ይፋዊ ቀጥተኛ ዋጋ ተመን (2nd Quarter Construction Works of Direct Cost)

🔑በተለይ የዋጋ ተመን (BOQ - Priced bill of Quantities) ለምታወጡ የዲዛይን አማካሪዎች እና የፕሮጀክት መሐንዲሶች ይጠማችኋል።

💫በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የምትገኙ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችም እንደመነሻ ሀሳብ ይጠቅማችኋል።

📍የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ

@etconp
👍8🙏6
🎉📚 BIG NEWS! My new book is finally here! "Get Your Dream Job" is a practical guide that will help you achieve your professional goals. I'll be sharing tried and tested tips and strategies to help you find the right path towards your dream job! 💡

I'll be guiding you step by step through the preparation process, from CV writing to the interview, so you can be confident and ready for any kind of job opportunity. 📈

If you're looking for inspiration and motivation for your career, don't miss this chance! 💪 Take control of your future and order the book now! 📚

💥 Don't miss the opportunity to change your work life forever! 💥 Order now! Available on all Kindle marketplaces.

https://www.amazon.com/dp/B0BTK9B699

@etconp
👍6😱1
የታሕሳስ ወር ዜና መፅሄት.pdf
4.6 MB
🏷የታሕሳስ ወር ዜና መፅሄት

📍የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥር 25/2015 ዓ/ም

@etconp
👍5
🏷በሶማሌ ክልሏ ጎዴ ከተማ መነሻነት ስያሜውን ያገኘውና በየካ አባዶ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ በሚገኘው ጎዴ ትምህርት ቤት ውስጥ በ490 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚገነባው SB+G+4 የመማሪያ ሕንፃ ግንባታን ለማጠናቀቅ በምሽት ፈረቃ ጭምር ስራዎችን እየተሰሩ የሚገኝ ሲሆን አሁን ላይ የሁለተኛ ወለል ኮለን ሙሌት መከናወኑ ተመላክቷል፡፡

📍የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥር 25/2015 ዓ/ም

@etconp
👍4
🏷በመንገድ የመሠረተ ልማት ማስተር ፕላን ዝግጅት እና በፕሮጀክት ቅንጅት አፈጻጸም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ።

🚧በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በሀገራዊ የመሰረተ ልማት ቅንጅት መሪ ስራ አስፈጻሚ አዘጋጅነት  የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን የሚያከናውኑ ተቋማት የሚናበቡበትን እና የሚደጋገፉበትን ስርዓት ለመፍጠር የጋራ እቅድ መነሻ በማድረግ በግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ከአስፈጻሚ ተቋማት ጋር በመሆን ክትትልና ድጋፍ ተደርጎባቸው የተለያዩ ችግሮች እና ፕሮጀክቱ በሚያልፍባቸው አካባቢ ባሉ አመራሮችና የፕሮጀክት ባለቤት እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ በመስራታቸው የመጣውን ለውጥና መሰራት የሚገባቸውን ስራዎች ለመገምገም  በሐዋሳ ከተማ ጥር 25 ቀን 2015 ዓ/ም የጋራ መድረክ ተካሄዷል፡፡

🚧መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የመሰረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ኢንጂነር  ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት ሀገራችን በሚቀጥሉት  አመታት ካደጉት ሀገራት መካከል እንድትመደብ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ይታወቃል።

🚧ይህንንም እቅድ ለማሳካት የመሠረተ-ልማት ዝርጋታ እና ተደራሽነት በዋናነት የሚጠቀስ በመሆኑ በዘርፉ የሚስተዋሉ የመሰረተ ልማት ብክነት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲሁም በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ባለመሰራቱ የሚከሰቱ የአሰራር ችግሮችን መቅረፍ አለብን፡፡

🚧አያይዘውም የሚገነቡ መሰረተ ልማቶች አንዱ አንዱን የሚጎዳ  ሳይሆን በመደጋገፍ በዘርፉ ለሚከሰቱ ችግሮች የሚመለከታቸውን  አካላት ተጠያቂ በማድረግ ለስራው ትኩረት በመስጠት ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ለለውጥ ልንሰራ ይጋባል ብለዋል፡፡

🚧በውይይት መድረኩ የደቡብና ማዕከላዊ ሪጅን የፕሮጀክት ማኔጅመንት ቢሮ የመንገድ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ሪፖርት፣  በሪጅኑ  የሚገነቡ የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ በተካሄዱት የመስክ ምልከታዎች እና በመሰረተ ልማት ማስተር ፕላን ዝግጅት ላይ ሰፋ ያለ ገለጻ ተደርጓል፡፡

🚧ከወሰን ማስከበር ፣ ከግመታ ሰነዶች ጋር እና በመቀናጀትና ተናቦ  ከመስራት ጋር  ለሚፈጠሩት ችግሮች የሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት ሃላፊነቱን በመውሰድ መስራት ይኖርባቸዋል ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎቹ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደሚያደርገው  ክትትልና ድጋፍ ክልሎችም በስራቸው የሚገኙ የመሰረተ ልማት ተቋማት ላይ ተመሳሳይ ሥራ  ልሠሩ  ይገባል ብለዋል፡፡

🌟በማጠቃለያው በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የሀገራዊ የመሰረተ ልማት ቅንጅት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ቴዎድሮስ ተገኜ እንደተናገሩት ይህ መድረክ ከዚህ በኋላ ተነጋግረን ብቻ የምናልፈው ሳይሆን  የዘርፉ የስራ ሃላፊዎች ከማህበረሰቡና  ከባለድርሻ አካላት ጋር  ተቀራርበው በመሥራት የመሠረተ ልማት የቅንጅት ችግሮችን የሚፈቱበት ልሆን ይገባል ብለዋል፡፡
 

@etconp
👍6
2022_English-Yearbook-compressed.pdf
22.3 MB
💫በአፍሪካ የስነቤት ገንዘብ አቅርቦት የ2022 መጽሀፍ።

🌟ሴንተር ፎር አፎርደብል ሀውሲንግ ፋይናንስ ፎር አፍሪካ በተባለው ድርጅት የተዘጋጀውን የ 2022 አመታዊ የስነቤት ገንዘብ አቅርቦት ላይ የሚያተኩረውን እጅግ ጠቃሚ መጽሀፍ አውርደው እንዲያነቡ እንጋብዛለን፡፡

👌መጽሀፉ አሁናዊ ሲሆን በአገራችን ኢትዮጵያ ላይ እጅግ ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አካቷል፡፡

💫2022 Year book on Housing Finance in Africa

🌟Please find the 2022 Year book on Housing Finance in Africa by the Centre for Affordable Housing Finance in Africa (CAHF)
Via CAHF

@etconp
👍6
🏷ቢሮው ጥር 23/2015 በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ስራዎችን በዕጣ ማከፋፈሉን ተከትሎ የማሕበራቱ ስም እንዲሁም የተመደቡበት ፕሮጀክት አድራሻ፡፡

📍ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

💫ጥር 26/2015

@etconp
👍6
🏷ከመሬት መንሸራተት ጋራ ተያይዘው የሚከሰቱ ችግሮች ላይ እና በቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫ ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ፅሁፍ በማቅረብ ዉይይት ተካሄደ፡፡

🚧የመሬት መንሸራተትን ለመቅረፍ በዲዛይን ወቅት ቅድመ ጂኦ ቴክኒካል ጥናት በጥልቀት መከናወን እንዳለበት በቀረበዉ ጥናት ላይ ተመላክቷል፡፡

🚧ይህ የተገለጸው ከመሬት መንሸራተት ጋራ ተያይዞ የሚከሰቱ የመንገድ የመሰረተ ልማት ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል የባለሙያዎች ጥናትና ምክክር መድረክ (Workshop) ቃሊቲ በሚገኘው የኢመአ መንገድ ምርምር ማዕከል በተካሄደበት ወቅት ነው።

🚧በውይይት መድረኩ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የቃሊቲ መንገድ ምርምር ስራተኞች እና ሀላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ምሁራን፣ የሲቪል መሐንዲሶች ማህበር ተወካይ፣የኢመአ የመንገድ ዲዛይን ክፍል ሰራተኞች እና አማካሪ መሃንዲሶች ተሳትፈውበታል።

🚧ጥናቱ የተዘጋጀው በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ  ሲሆን በጥናቱ የተገኙ ግኝቶች ለተሳታፊዎች ቀርበዋል።

🚧በመላው አገሪቱ ከተገነቡት እና በግንባታ ሂደት ላይ በሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ የመሬት መንሸራተት እንደሚከሰት በጥናቱ ላይ ተመልክቷል።
ለጥናቱ መነሻነት ከአዲስ አበባ ባህርዳር በሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኘው የአባይ ሸለቆ፣ ከደብረብርሃን -አጣዬ- ደሴ እና ዋቻ-ማጂ የመንገድ መስመሮች እንደ ማሳያነት ተወስደዋል።

🚧በዕለቱ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር የቀረበው ወርክሾፕ ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን ከአሁን በኃላ ተከታታይ ወርክሾፖች ከተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋራ በመናበብ እንደሚዘጋጅ ተጠቁሟል።

🚧በመሬት መንሸራተት ምክንያት የተበላሹትን መንገዶች ለመጠገን በአመት መንግስት ብዙ ገንዘብ እንደሚያወጣ በጥናቱ ላይ ተመላክቷል።

🚧ይህንን እና መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ ኢመአ በመንገድ ምርምር ማዕከል ውስጥ በርካታ የጥናት እና ምርምር ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

@etconp
👍11
🏷ADMIXTURES

▶️Admixtures are the special ingredients added during concrete mixing to enhance the properties and performance of fresh concrete.
▶️Various types of admixtures are available in the market which is used in construction work.

🚧FUNCTION OF ADMIXTURES:

1. To accelerate or retard the setting time of fresh concrete.
2. To improve the workability or flowability of concrete.
3. To increase the strength and durability of concrete.
4. To reduce the heat of hydration.
5. To reduce the segregation and bleeding.
6. To decrease the permeability.
7. To achieve other desired properties.

🚧TYPES OF ADMIXTURES:

🌟1. ACCELERATING ADMIXTURES:

⏺This admixture is added in concrete or mortar for increasing the rate of hydration of hydraulic cement and for shortening the setting time Calcium chloride (CaCl2) is the most widely used accelerating admixture.

🌟2. RETARDING ADMIXTURES:

⏺Retarding admixtures delay the initial rate of hydration of cement and extend the setting time of cement paste. This admixture can be used in high
temperature and where the concrete has to be transported to a long distance. It is also suitable for using in grouting oil wells.

🌟3. AIR-ENTRAINING ADMIXTURES:

⏺Air entraining admixtures help to produce a certain amount of air bubbles in the concrete mixture. The main goal of this admixture is to increase the
resistance against freeze-thaw degradation and cohesion. It also improves the workability of fresh concrete without changing the setting or the rate of
hardening.

🌟4. WATER REDUCING ADMIXTURES:

⏺As the name suggest, water reducers are added to a concrete mixture, mortar or grout to increase the flowability without increasing the water content.

🚧Advantages Of Water Reducing Admixtures:

1. The rate of concrete placement is faster.
2. Strength, durability, density etc. are significantly
improved.
3. Segregation, permeability, and cracking are
reduced.

🚧SPECIAL ADMIXTURES:

1. Superplasticizing admixtures.
2. Corrosion-inhibiting admixtures.
3. Grouting admixtures.
4. Coloring admixtures etc.

@etconp
👍13🤯1
🏷ዕለቱን በ ኮንስትራክሽን ታሪክ

📍ማዘጋጃ ቤት ህንጻ አዲስ አበባ

🌟የ ዛሬ 58 ዓመት ጥር 27 ቀን 1957 ዓ.ም የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ተመርቆ ተከፈተ።

🌟መሀል አራዳ ላይ የሚገኘው የማዘጋጃ ቤት ህንፃ በ 8 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ህንፃ ነበር።

🌟ህንፃውን ዲዛይን ያደረገው አርክቴክት አርትሮ ሜዜዲሚ የሚባል ጣሊያናዊ ሲሆን ኢንጅነር መኮንን ሙላቱ የተባሉ ኢትዮጵያዊ የቁጥጥር ስራውን በመስራት ለአዲስ አበባ ከተማ ታላቅ ውለታ ውለዋል።

🌟ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ጥቅምት 23 ቀን 1942 ዓ.ም የሕንፃ ግንባታውን ለማስጀመር የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጡ ሲሆን (ህንፃው ዲዛይን ሲደረግ 600 መቶ ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲኖሩትና የመኪና ማቆሚያና መናፈሻ ቦታ ጨምሮ በ75 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ላይ እንዲያርፍ ነው) ተመርቆ የተከፈተው ግንባታው ከተጀመረ ከ 15 ዓመት በኋላ ጥር 27 ቀን 1957 ዓ.ም ከቀኑ አምስት ሰዓት ላይ ነበር።

🌟ወደ ሕንፃው ሲገባ በሚታየው ሰሌዳ ላይ የሚከተለው ጽሁፍ ሰፍቶ ይታያል፦

💫«ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለመናገሻው ከተማ ለአዲስ አበባ ሕዝባቸው፣ ለማኅበራዊ ኑሮው፣ ለኤኮኖሜውና ለባህሉ ዕድገት አማካይ የአገልግሎት ቤት ይሆን ዘንድ ፈቅደው ያሠሩትን ይህን ሕንፃ፣ በሠላሳ አራተኛው ዘመነ መንግሥታቸው መርቀው ከፈቱ።

Via ጀማል አብዱልአዚዝ

@etconp
👍16❤1
🏷ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል ባለሙያ

🌟የፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል ባለሙያ (መሐንዲስ) የሙያ ፍቃድ ለማውጣት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በመመሪያ ቁጥር 648/2013 ዓ.ም ባወጣው መመሪያ መሠረት አመልካቹ ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ በኮንስትራክሽን ዘርፍ በዲግሪ እና ከዚያ በላይ በሆነ ደረጃ የተመረቀ መሆን ያለበት ሲሆን ለዲግሪ ሰባት (7) ዓመት፣ ለማስተርስ አምስት (5) ዓመት ላመለከተበት ዘርፍ አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ ውስጥ ቢያንስ ሁለት ዓመቱ እንደ አግባቡ በዚዛይን ወይም በዲዛይን ክለሳ ወይም በኮንስትራክሽን (ግንባታ) ወይም በአስተዳደር (ማኔጅመንት) ሥራዎች ላይ የተሳተፈ መሆን ይኖርበታል።

🌟ባለሙያው ከላይ የተዘረዘሩት ሥራዎች በቁጥር ሁለት (2) ሥራዎችን በራሱ እና እንደ አግባቡ በተቆጣጣሪነት የተሰሩ ለፕሮፌሽናል ብቃት ማረጋገጫ ካቀረቡት በተጨማሪ አንድ (1) ሥራ ማቅረብ ይኖርባቸዋል" ይላል።

🌟ፕራክቲሲንግ ባለሙያ" ተብሎ የሚሰጥባቸው መስኮችም፦

⏺ፕራክቲሲንግ አርክቴክት (Architect)
⏺ፕራክቲሲንግ ስትራክቸራል (structural) መሐንዲስ
⏺ፕራክቲሲንግ ሳኒታሪ (Sanitary) መሐንዲስ
⏺ፕራክቲሲንግ ኤሌክትሪካል (Electrical) መሐንዲስ
⏺ፕራክቲሲንግ መካኒካል (Mechanical) መሐንዲስ
⏺ፕራክቲሲንግ ሰርቨየር (Surveyor)
⏺ፕራክቲሲንግ የመንገድ (Highway) መሐንዲስ
⏺ፕራክቲሲንግ ፔቭመንት (Pavement) መሐንዲስ
⏺ፕራክቲሲንግ ሎኬሽን (Location) መሐንዲስ
⏺ፕራክቲሲንግ የድልድይ (Bridge) መሐንዲስ
⏺ፕራክቲሲንግ ጂኦቴክኒካል (Geotechnical) መሐንዲስ
⏺ፕራክቲሲንግ ማቴሪያል (Material) መሐንዲስ
⏺ፕራክቲሲንግ የመሬት ገጽታ ማስዋብ (Landscape) መሐንዲስ
⏺ፕራክቲሲንግ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት (CoTM)
⏺ፕራክቲሲንግ የከተማ ፕላን (Urban planner) ባለሙያ
⏺ፕራክቲሲንግ ኢንቫይሮንታል መሐንዲስ (Environmentalist)

@etconp
👍24💔1
Ethio Construction Engineering
Floor system (ስርዓተ-ወለል) ተንጠልጣይ ወለል(suspended slab) መዋቅራዊ የህንፃ አካል ሲሆን የተደለደለ እና ለጥ ያለ ወይም ለ ramp ተዳፋት( sloppy) ቦታ ይሰጠናል። የግብዓት አንፃር ፩. በፌሮ እና በ አርማታ የሚሰራ ፪. በጣውላ ሚሰራ ፫. በ ብረት ብቻ ሚሰራ ፬. ተገጣጣሚ ከድጋፍ አንፃር ፩. በመሬት የሚደገፍ ፪. ተንጠልጣይ - በ አርማታ…
Solid slabs

በሁለት ይከፈላሉ one way እና two way

ቃሉ የመጣው reference የተወሰደው x and y direction ነው። ድጋፍ የሆነው beam ከ X - direction ጋር ትይዩ ይሆናል ወይ ደግሞ ከ Y- direction ጋር ስለዚህ በምስሉ ላይ ምትመለከቱት ጥንድ በ አንድ አቅጣጫ የቢም ድጋፍ ያለው one way slab ሲባል በ X እና በ Y ጥንድ ትይዩ ድጋፍ ያለው two way slab ይባላል load distribution ምስሉ ላይ ተመልከቱ።

ቀጣይ flat slabን እንዳስሳለን

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Youtube:- https://youtube.com/@Etconp432

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=
👍9🥰1
🏷የግንባታ ፍቃድ አጠያየቅ እና የወሰንተኛ ጉዳይ

🚧የማሻሻያ፣ የመጠቀሚያ ፈቃድ፣ ጊዜያዊ ግንባታ ወይም የማፍረስ ሥራ ለማከናወን የሚቀርብ የግንባታ ፈቃድ ጥያቄ ሲኖር በተናጠል በተዘጋጀላቸው (ማለትም ለአዲስ ለማስፋፊያ ወይም ለማሻሻያ ግንባታ ቅፅ፣ ለግንባታ እድሳት ፈቃድ ቅፅ፣ ለግንባታ ማፍረስ ፈቃድ ቅጽ፣ ለአገልግልት ለውጥ ቅጽ፣ ለጊዜያዊ ግንባታ ቅጽ) በመሙላት የግለሰብ ከሆነ በአመልካቹ ተፈርሞ፣ በመንግስታዊ፣ በሕዝባዊ እና የመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተያዘ ወይም የሚተዳደር ከሆነ በኃላፊው ተፊርሞ እና የድርጅቱ ማህተም አርፎበት ጥያቄው መቅረብ ይኖርበታል።

🚧ማንኛውም የግንባታ ፈቃድ ጠያቂ ስለወሰንተኞቹ ትክክለኛ መረጃ በወሰንተኛ ግንባታ መግለጫ ቅጽ ላይ ወሰንተኛውን በማስሞላትና በማስፈረም ማቅረብ አለበት፣ ቅፁን ለመሙላት ፈቃደኛ በማይሆን ወሰንተኛ የከተማ አስተዳደሩ ቅፁን የማስሞላት ሃላፊነት አለበት። ወሰን ላይ የሚገነባ የምግብ ማብሰያና መሰል አገልግሎት ሰጪ ክፍሎች ግድግዳ የእሳት ቃጠሎን በተሻለ ሁኔታ መከላከል በሚችል ድፍን የግድግዳ ቁሳቁስ መገንባት አለበት እንዲሁም ጭስ እና እንፋልት ወደወሰነተኛ መውጣት የለበትም።

🚧በተለያዩ አካባቢዎች የሚገነቡ አንድ ዓይነት ስታንዳርድ ፕላኖች ያላቸው ግንባታዎች የየራሳቸው የግንባታ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል።

🚧ከዚህም በተጨማሪ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ማካተት ይኖርበታል፣ ወለልና በላይ ያለው ማንኛውም ግንባታ (የምድር በታች ወለል ቢኖረውም ባይኖረውም) ከወሰን ሁለት ሜትርና ከዚያ በታች ተጠግቶ የሚሰራ ከሆነ በቅድሚያ የወሰን ላይ ግንባታ ቅጽ መሙላትና ስምምነት ማግኘት ይኖርበታል፣ ለፈቃድ የሚቀርበው ስትራክቸራል ዲዛይን የወሰንተኛውን ነባር ህንፃ መዋቅር ይዘት ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት፤ የሚቀርበው የዲዛይን ሠነድ የወሰንተኛውን ነባር ህንፃ መጠን ለምሳሌ የኃይል ሚዛን (Load) ከግምት ያስገባበት አግባብ ማመልከት አለበት፣ በወሰንተኛ ነባር ግንባታ ደህንነት ላይ ምንም አይነት መናጋት እንዳይፈጠር በቁፋሮና በግንባታ ሂደት መወሰድ የሚኖርበትን የሚያሳይ የጥንቃቄ ንድፍ ለፍቃድ ከሚቀርበው ሰነድ ጋር መቅረብ አለበት።

🚧አየር ማስገቢያ ሳይኖረው ብርሃን ብቻ የሚያስገባ ግንባታ ወሰን ላይ ለመሥራት ለዚሁ ተብለው በተዘጋጁና አሳልፈው በማያሳዩ ውፍረታቸው ከ5 ሳ.ሜ የማያንስ የመስታወት ግርግዳ መጠቀም ይቻላል ይህም በሚቀርበው ዲዛይን ላይ በግልጽ መጠቀስ ሲኖርበት ወሰን ላይ የተሰራ ከሆነ ወሰንተኛው እንደማንኛውም ድፍን የግድግዳ አካል አስጠግቶ ሊሰራበት ስለማይከለከል የብርሃን ማስገቢያ መስፈርት ለሚጠየቅበት ተጨማሪ ወይም አማራጭ የብርሃን ምንጭ ማመልከት አለበት።

🚧 ማንኛውም ሰው ግንባታውን እስከ ወሠን አስጠግቶ ማከናወን ይችላል ሆኖም ወሠን ላይ ለመገንባት ያቀደ ሰው በአዋሳኙ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የሚያደርገውን የመከላከያ ዘዴዎች ለአጎራባቹ ማሳወቅ ይኖርበታል።

🚧ግንባታው ተጀምሮ እስኪጠናቀቀ ድረስ በአጎራባቹ አደጋና ችግር በማያስከትል ሁኔታ መከናወን አለበት።

🚧በማንኛውም ጊዜ ወሰንተኛው ግንባታውን እንዲከታተል መፍቀድ አለበት።

🚧በማንኛውም የግንባታ ወቅት ለሚፈጠር ችግር ገንቢው ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳል።

🌟በአዋጁ፣ በደንቡ እና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ባረቀቀው የሕንጻ መመሪያ (Building Directives) እና በሌሎች የማስፈጸሚያ ሰነድች ላይ የተገለፁትን መስፈርቶች ያላሟላ የግንባታ ፈቃድ ጥያቄ በግንባታ መጠየቂያ ቅጽ ላይ በተመለከተው ቦታ ያልተሟላበትን ምክንያት በመግለፅ ተመላሽ መደረግ ይኖርበታል።

@etconp
👍14👌1🍌1
🏷what is structural engineering and what structural engineer do and its responsibility ?

🚧structural engineering is a branch of civil engineering that involves the application of the laws of physics, mathematics and empirical knowledge to safely design the ‘bones’ and load bearing elements of man made structures.

🌟Responsibility

 🚧making sure that the structures we use in our daily lives, like bridges and tall buildings, are safe, stable and don’t collapse under applied loads.

🚧design the load bearing elements like beam,column ,slab,pile,pear,fondation in different shapes depends on its applied load , pressures and stresses of their environment such as gravity loads, imposed load ,wind load, earthquakes load ...

🏷መዋቅራዊ ምህንድስና ምንድን ነው?
መዋቅራዊ መሐንዲስ ምን ይሰራል እና ኃላፊነቱ?

🚧ስትራክቸራል ምህንድስና የፊዚክስ፣ የሒሳብ እና የተጨባጭ ዕውቀት ህጎችን መተግበርን የሚያካትት የሲቪል ምህንድስና ቅርንጫፍ ነው።

🌟ሀላፊነቱስ

🚧በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የምንጠቀማቸው መዋቅሮች እንደ ድልድይ እና ረጃጅም ሕንፃዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ የተረጋጉ እና በተጫኑ ሸክሞች የማይፈርሱ መሆናቸውን ማረጋገጥ።

🚧እንደ ሞገድ ፣ አምድ ፣ ንጣፍ ፣ ክምር ፣ ፒር ፣ በተለያዩ ቅርጾች ላይ ያሉ የመፍቻ አካላትን ዲዛይን ያድርጉ በተተገበረው ሸክሙ ፣ ጫናዎች እና የአካባቢያቸው ውጥረቶች እንደ የስበት ጭነት ፣ የተጫነ ጭነት ፣ የንፋስ ጭነት ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ጭነት

@etconp
👌7👍3🐳1