Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
😂😂😂 ለ ፈገግታ 😂😂😂

👉ፍቅር በኮንስትራክሽንኛ

💌ከ PROJECT-A ለ PROJECT-B የተፃፈ የ ፍቅር ደብዳቤ
==================

ይድረስ Good Aesthetic view ላለሽ ውድ ፍቅረኛየ

ከምን እንደምጀምር ኣላውቅም ግን site ላይ ካየሁሽ ጀምሮ ፍቅርሽ ልቤ ውስጥ cast ሆኗል እናም ብዙ ጊዜ ኣንቺን ለማየት እዛ site ብመላለስም curing እንደ ጠማው concrete ደርቄ እስካሁን ስጠብቅሽ ኣለው፡፡

ኣንቺ ግን እንደ ኣሁኑ reinforcement bar በዛው ቀረሽ፡፡

እኔ ግን ምን ገጥሟት ይሆን በሚል defect ልቤን ልክ እንደ pile foundation በየቀኑ በሰቀቀን ይቆፍራል፡፡

ከብዙ ጊዚያት በኃላ ከብዙ tenderers በልጬ award ላደርግሽ ብሞክርም ኣንቺ ግን Flat slab ያለ Beam ይሰራ የለ እንዴ? የአብሮነታችን ትርጉም ምንድ ነው? ስትይኝ Compaction እንደበዛበት Concrete ኣይኔ Bleeding ሆነ ስራው::

በናትሽ Column ያለ Bar እንደማይቆመው ሁሉ እኔ እና ኣንቺ Mix ካልሆንም የልቤ crack መጠኑ እየሰፋ ይሄዳል::

ስለዚህ ከ Maintenance በፊት ያንቺ offer ያስፈልገኛል ኣሁንም መልስሽ እምቢ ከሆነ ግን ከ 3rd Floor Building ልክ እንደ falling out of plaster ራሴን እፈጠፍጥልሻለሁ

ኣሁን እዛው ላይ ነኝና መልስሽ በኣፋጣኝ በ Lift ላኪልኝ ወረቀቱ Wind Load እንዳይወስደው ኣደራ በ Gypsum ኣጣቢቅው::

መፅሀፉ እንኳ እንደዚህ ይል የለ "ፍቅር ግን ከሌለን Agro stone ነን" መፅሀፈ Construction 4ኛ ዓመት 1ኛሰሚስተር

✍Via መምህር መድሃንየ ሕሉፍ
ADIGRAT UNIVERSITY

መልካም ቀን❤️

@etconp
🤣56👍22❤14
ጊፍት ሪል ስቴት በ70 ሚሊዮን ብር ወጪ ለ40 አቅመ ደካሞች የጋራ መኖሪያ ቤት መገንባቱን ገለጸ

በቤት ልማት ዘርፍ ተሰማርቶ በመስራት ላይ የሚገኘው ጊፍት ሪል ስቴት፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ 40 አቅመ ደጋሞች የጋራ መኖሪያ ቤት መገንባቱን አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ለአቅመ ደካሞች ያስገነባው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በኹለት ሳምንታት ውስጥ አጠናቆ እንደሚያስረክብም ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ ገልጿል፡፡

ጊፍት ሪል ስቴት ከእህት ኩባንያዎች ጋር በመተባበር ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ እንዲሁም በተለያዩ አገራዊ ጥሪ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ አምስት ወለሎች ያሉት ሲሆን፤ እስከ 70 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በቀረበው ጥያቄ መሰረት ቤቶቹን ገንብቶ ለማጠናቀቅ ኹለት ወራት ብቻ መውሰዱ ተገልጿል፡፡

ጊፍት ሪል ስቴት በሽያጭ ከሚያቀርባቸው የተለያዩ ቤቶች ባሻገር የቤት እጥረትን ለመቅረፍ ለአቅመ ደካሞች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁሟል፡፡

Via አዲስ ማለዳ

@etconp
👍9
የጥምር 12 ኮዬ ፈጬ2 ሎት1 የመንገድ ፕሮጀክት 17.8 ኪ.ሜትር የሚሸፍን የመንገድ ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በኮዬ ፍጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ 5ፕሮጀከቶችን በተለያዩ የስራ ተቋራጮች እያስገባ ይገኛል፡፡

ከእነዚህ ፕሮጀክቶች መካካል ከ711.7 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የጥምር12 ኮዬ ፍጬ2 ሎት1 የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አንዱ ነው፡፡

የመንገዱን ግንባታ እያከናወነ የሚገኘው IFH የስራ ተቋራጭ ሲሆን ሲቪል ወርከር ኮንሰልቲግ ኢንጂነርስ ፔሊሲ ደግሞ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን እየተከታተለው ይገኛል፡፡

ይህ የመንገድ ግንባታ የአስፋልት እና የኮብል መንገድ ጨምሮ 17.8 ኪ.ሜ ርዝመትና ከ10 እስከ 20 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት አለው፡፡
አሁን ላይ የከርቭስቶን ፣ የሰቤዝ ፣ የድጋፍ ግንብ ግንባታ እና ሌሎች ተያያዥ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

ይሁን እንጂ የወሰን ማስከበር ሥራዎች በተያዘላቸው ጊዜ ባለመጠናቀቃቸው ግንባታው በታሰበው ፍጥነት እንዳይከናወን ተፅእኖ አሳድረዋል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመንገዱ ወሰን ውስጥ የሚገኙ ቀሪ የወሰን ማስከበር ስራዎችን በማጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን

@etconp
👍6🤮2
ትኩረቱን በአቃቂ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ግንባታ ሂደት ላይ ያደረገ የመስክ ምልከታ ተካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም በአቃቂ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በመገኘት የፕሮጀክቱን አፈፃፀም በመገምገም የቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

የስራ ተቋራጩ ባለድርሻዎች፣አማካሪ ድርጅቱ ፣የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ እና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በዚህ የመስክ ምልከታ ላይ ከስራ ተቋራጩ ተነስቶ የነበረው የክፍያ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ተደርጎ ጥያቄውን መፍታት ተችሏል፡፡

በመቀጠልም ፕሮጀክቱን ተዘዋውረው የተመለከቱት ቢሮ ኃላፊዋ የተጀመሩ ስራዎች በተያዘው ዕቅድ መሰረት እንዲከናወኑና ሌሎች በዚህ ሳምንት መጀመር ስለሚገባቸው ስራዎችና በዚህም መነሻነት ስለሚጠበቁ ውቴቶች አቅጣጫ እና የስራ መመሪያ አስቀምጠዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የካቲት 13/2015 ዓ/ም

@etconp
👍8🤡1
📢የምስራች ከ @ETCONpWORK

🫵  የ ETCONp ድርጅት የሆነው ETCONp WORK የኮንስትራክሽን አቅርቦት ክፍተትን ለሞሞላት ከኮንስትራክሽን አቅርቦት ጋር የተያያዙ ስራዎችን ላይ ለመስራት አቅዷል

🌟የኮንስትራክሽን ባለሞያዎች ማለትም አናጺ፣ግንበኛ፣ፌራዩ፣ፎርማን እና ተዛማጅ ስራ የሚሰሩ ምታገኙበት
🌟 ኮንትራክተሮች  እና የኮንስትራክሽን ንግድ ውስጥ የተሰማሩ ሰዎች በ ቀላሉ የሚያገኙበት
🌟የ ኮንስትራክሽን ስራ እና ጨረታ የሚለጠፍበት
🌟የኮንስትራክሽን ማሽነሪ እና ማቴርያል አከራዮችም ከፈለጉ ከታች ባለው ቻናል ይቀላቀሉን።

https://t.me/ETCONpWORK
👍4
✨✨✨ concrete pump ምታከራዩ ካላችሁ ለስራ ተፈልጎ ነው በ @etconpworks ብታናግሩን ።

@etconpwork
@etconp
👍2
Designed highrise building inspired by lalibela rock hewan church and axum obelisk #facade I did the architectural design with #autocad and #sketchup and the #structuraldesign with #etabs AND I made the model too

#sketchup3d #autocad #etabs #structuraldesign #structuralengineering

If you want to watch the video you get link down below

👇🏿 👇🏿 👇🏿

Link:- https://youtu.be/CsosNtq0vzk
👏13👍5👌2🥴2💔2
Earthquake resistant building design state-of-art!

@etconp
👍5