Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
earthquake response and behavior of buildings and other structures.

This is for instance pushover analysis

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

Youtube:- https://youtube.com/@Etconp432
👍9
👉እስቲ ስለ ኢሊቬሽን አለመንቶች ትንሽ እንይ

🚧ከርቮች ላይ ያለውን super elevation ፐርሰንት ካወቅን በኋላ ሱፐር ኢሊቬሽኑን ሙሉ ከርቩ ላይ ስለማናደርግ የት Station ላይ እንደሚገባና እንደሚወጣ ማወቅ አለብን፡፡

🚧በተጨማሪም ሙሉውን ያገኘነውን ፐርሰንት አንጠቀምም - መጀመሪያ ከዜሮ ይጀምርና ቀስ እያለ ሄዶ ሙሉ ሱፐር ኢሊቬሽን ይሆናል - የተወሰነ ርቀት ሙሉውን ከቀጠለ በኋላ እንደገና ቀሰ እያለ ወደ ዜሮ ይመለስና የኖርማል አስፓልቱን slope ይይዛል፡፡

🚧ካልኩሌት አድርገን ወይም ኤግል ፖይንት እራሱ ካልኩሌት አድርጎ እስቴሽኖቹን ማወቅ እንችላለን፡፡

🚧ያገኘናቸውንም እስቴሽኖች ሳይት ላይ ሱፐር ኢሊቬሽኑን ስናስቀምጥ እንጠቀምባቸዋለን፡፡

⭐️ኢለመንቶቹ በዛ ስለሚሉ እነዚህን እዚ ላይ መዘርዘር አስቸጋሪ ስለሆነ የተወሰኑትን በፎቶ ቀጣይ እናስቀምጥላቹዋለን ቀሪዎቹን ከERA Geometric Design Manual ላይ አንብቧቸው፡፡

📍ኤግል ፖይንት ላይ የምናስገባቸው SR, TR, X, Y ናቸው፡፡

#Highway

@etconp
👍16
👉ትንሽ ስለ Eiffel Tower😍

🚧የዚህ ታወር ዲዛይነርና ኮንትራክተር ኢንጂነር ጉስታቭ ኤፍል ይባላል፡፡

⭐️ታወሩ 324ሜ ርዝመት ሲኖረው ከሚገርሙኝ ነገሮች ውስጥ ታወሩ በግንባታ ላይ እያለ በጣም ትልቅ በመሆኑ ሌሎች ቅርሶቻችንን ይውጥብናል በማለት ከ300 በላይ ኢንጅነሮችና አርክቴክቶች ተቃውመው ለመንግስት petition አስገብተው ነበር (ለአንድ ሜትር - አንድ ኢንጂነር) አንዱ አርክቴክት እንደውም በጣም ተናዶ ምሳውን ሁሌ ታወሩ ላይ በሚገኝ ሬስቶራንት ነበር የሚመገበው፤ ለምን እዛ እንደሚበላ ሲጠይቁትም ‹‹ ፓሪስ ውስጥ ኤፍልን ላለማየት ከፈለክ ብቸኛው መፍትሄ እዛው ኤፍል ውስጥ መሆን ነው›› ይል ነበር😀

🚧ታወሩን በቀን 25 ሺህ በጠቅላላው ደሞ ከ250 ሚሊየን በላይ ቱሪስቶች ጎብኝተውታል

🚧ኢንጂነር ለሃገር ኢኮኖሚ እድገት በተጨማሪ የአንድ ሃገር symbol መሆን ይችላል - ፓሪስ ሲባል ኤፍል ታወር ማነው ትዝ የማይለው??

🙏መልካም ዕለተ ሰንበት ተመኝኑላቹ❤

@etconp
👍9💔5❤4🤔1
🏷በ ውስጥ መስመር በጣም ብዙ ሰዎች የ INTERNSHIP REPORT ሳምፕል ላኩልን ባላቹን መሰረት እንዲሁም ኣሁን ለምትሰሩት ኣጋዥ ይሆናሉ ብለን ያሰብናቸው የ INTERNSHIP REPORT SAMPLE እንካቹ ብለናል፡፡

⭐️ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።

@etconp
👍7
🏷Visual tests on cement, sand and reinforcements

🚧1 for cement

👉float test
👉date of packing
👉green Gray colour for OPC & blakishgrey for PPC
👉When hand is dipped in to bag of cement it should feel cool not warm

🚧2 for Sand

👉 golden yellow colour
👉 free from mineral salts
👉 free from organic impurities
👉silt content

🚧3 for reinforcements

👉presence of BIS certification mark
👉clear from rust layers, mud, oil paints etc
👉free from crack
👉have similar diameter
👉bend test

@etconp
🙏8👍4😭1
👉Afro Tsion Construction’s properties up for auction.

🚧Two commercial banks have put Afro Tsion Construction’s residential properties and hospitality business up for foreclosure.

🚧That is a big blow for the firm, which was formerly regarded as an industry leader in the construction sector due to its involvement in various public projects, including roads and government office buildings.

🚧The Commercial Bank of Ethiopia (CBE) is in the midst of foreclosing on Afro Tsion Construction Plc’s five-star resort in Semera, Afar Region.The resort was built and owned by the construction company in Semera, Afar, and operated by Boston Partners Plc, the operator of Kuriftu Resort & Spa.

🚧The CBE floated the bid two weeks ago. It is scheduled to open on March 21, 2023, with a floor price of 418.1 million birr. The property was built for resort and hotel services on 51,285sqm of land in Semera.

🚧Wegagen Bank has foreclosed on several properties owned by Afro Tsion, a first grade contractor. The bank declared the foreclosure of 12 of the company’s residential properties in a bid made public on March 5, 2015.Eleven of the houses are 250sqm in area, while the last one is 1,500sqm. The lowest floor price is 9.5 million birr, while the highest is 132.4 million birr. The auction will take place on April 5, 2023.

🏷Afro Tsion Construction, created in 1998 by engineering professional Sisay Desta with a capital of 50,000 birr, has been responsible for the construction of various big projects. Yigalem Industrial Park, a two billion birr general hospital for Addis Ababa Health Bureau in 2018, a stadium in Harari, and its own resort facility in Semera, Afar were among the projects.

🏷Afro Tsion’s five-star resort facility with 144 rooms was supposedly built in Afar at a cost of half a billion birr. It was run as Kuriftu Resort Semera since its inception in February of 2019 till it went out of business almost a year ago. Apart from standard rooms, the resort also had villas, ground tennis courts, a playground, and other amenities.

Via THE REPORTER

@etconp
👍16🎃3
👉እስቲ ኣሁን ደሞ ስለ Support ትንሽ ልበላቹ....
.
፩) FIXED Support = በፎርስ ምክንያት የሚመጡ Moment, Shear እና Horizontal Force support የሚያደርግ supporting system ነው፡፡

🚧ስለዚህ Analyze ስናረግ የምንፈልጋቸው Reaction ብዛት 3 ነው (M,V & Fh) Reactive ፎርሶቹ Displacement ስለሚከላከሉ Displacement = 0 Reactive ሞመንቱ Rotation ስለሚከላከል Rotation = 0

፪) PIN Support = Shear እና Horizontal Force የሚከላከል ሲስተም ነው፡፡

⭐️ሞመንት አይቋቋሙም ሰለዚህ Roation አለ ነገር ግን Displacement ዜሮ ነው፡፡

፫) ROLLER Support
Vertical Force ብቻ ነው የሚሸከመው፡፡

⭐️Rotation አለ but Displacement = 0

#theoryofStructure

@etconp
❤5👌4👍3
👉የ ኋሊት ኮንስትራክሽን ታሪክ

🚧ቸርችል ጎዳና

⭐️ቸርችል ጎዳና በ1963 ይህንን ይመስል ነበር።

💫የዘመናዊ ህንጻዎች ግንባታ ትልቅ ጡዘት ላይ የነበረበት ወቅት ሲሆን አጠቃላይ የአገሪቷ በግብርና የሚተዳደረው ብዙሀን ግን በተቃራኒው በብዙ ችግር የተተበተበ ነበር።

📍በከተማና በገጠር የነበረው ተቃርኖ እየሰፋ የሄደበት ታሪካዊ ክስተት ነበር።

⭐️Churchill road in Addis Ababa 1971

Via ታሪካችን

@etconp
👍10❤1🥰1
BID Herald.pdf
1.1 MB
#ማስታወቂያ

#የጨረታ_ሰነድ_መሸጥ_መጀመሩን_ስለማሳወቅ

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጥር 11/2015 ዓም ማለትም (January 19 /2023 G.C. ) በኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጣ አውጥቶት የነበረው የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ አርሶአደርና የከተማ ግብርና ልማት ማዕከል B+G+10 ግንባታ ዓለም-ዓቀፍ ጨረታ ከነገ መጋቢት 05/2015 ዓ/ም ጀምሮ የጨረታ ሰነድ መሸጥ እንደሚጀመር እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን በቢሮው 8ኛ ፎቅ በመምጣት እንድትገዙ እንጋብዛለን፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት መጋቢት 04/2015 ዓ/ም

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

Youtube:- https://youtube.com/@Etconp432
👍6🙏2
👉ደቡብ ሱዳን የምስራቅ አፍሪካ የትራንስፖርት ኮሪደርን ለመተግበር ስትራቴጂክ ፕላን ማዘጋጀቷ ተነገረ

🚧ከኬንያ ላሙ ወደብ በመነሳት በደቡብ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የሚደርሰውን የምስራቅ አፍሪካ የትራንስፖርት ኮሪደር ለመተግበር ደቡብ ሱዳን ስትራቴጂክ ፕላን ማዘጋጀቷ ተሰምቷል፡፡

🚧ደቡብ ሱዳን ቅድማያ ከምትሰጣቸው 16 ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ እንደሆነ የተነገረው ከሪደሩ፣ ምስራቅ አፍካን ከከምዕራብ አፍሪካ የሚያገናኝ ነው፡፡ የዚህ ኮሪደር አካል የሆነው ከላሙ ወደብ እስከ ኢሲሎ ያለው 500 ኪሎ ሜትር የሚረዝም መንገድ እየተገነባ ሲሆን፣ ከኢሲሎ በሞያሌ ሀዋሳ የሚደርስ 500 ኪሎ ሜትር የሚደርስ መንገድ ግንባታው ተጠናቅቋል፡፡

🚧ደቡብ ሱዳን ቅድሚያ የምትስጣቸውን 16 ፕሮጀክቶች አስመልክቶ ከአገሪቱ ሚንስትሮች ጋር እንደተወያዩ ያስታወቁት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የአፍሪካ ንግድ ማዕከል ዋና አማካሪ አዲይንካ አዲዬሚ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለአገሪቱ ድጋፍ እንደሚደርግ አስታውቀዋል፡፡

🚧ይሁንና የሚገነባው መንገድ ምን ያህል ርዝመት እንዳለውና ስለተመደበለት በጀት የተባለ ነገር የለም፡፡

🚧ኹሉም ፕሮጀክቶች የኮሪደሩን እንቅስቃሴ የሚያሳልጡ ናቸው ያሉት አማካሪው፣ ዓለም ባንከ በተለይም በመንገድ፣ ኃይልና ግብርና ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱን ተናግረዋል፡፡

🚧ከአዲስ አበባ ሀዋሳ ድረስ እየተገነባ ያለው የፍጥነት መንገድ የትራንስፖርት ኮሪደሩን ውጤታማነት ከፍ ያደርጋል የተባለ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ኬንያና ደቡብ ሱዳን የሚዘረጉ መሰረተ ልማቶች ከኬንያው ላሙ ወደብ በመነሳት ምስራቅ አፍካን ከምዕራብ አፍሪካ በየብስ ያገናኛሉ፡፡

Via አዲስ ማለዳ

@etconp
👍4👏2❤1
ቢሮው ለ28 አማካሪ ማህበራት የስራ ዕድል ፈጠረ፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በበጀት ዓመቱ ቀጣይ ወራት ሊያከናውናቸውበዕቅድ ይዞ በከፍተኛ ትኩረት እየተንቀሳቀሰባቸው የሚገኙትንና በርካታ ቁጥር ያላቸውን G+4 የመማሪያ ሕንፃዎች እንዲሁም G+0 የመስሪያ ቦታ ግንባታዎችን በቅርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ስራ ተቋራጭ ማህበራት በተለያየ ዙር መስጠቱን ተከትሎ እነዚህን ስራዎች የሚከታተሉ 28 አማካሪ ማህበራትን በዕጣ ደልድሏል፡፡

እንደየስራው ስፋትና ፕሮጀክቶቹ እንዳሉባቸው ቦታዎች ርቀት  ለያንዳንዱ ማሕበራት ሁለት እና ከዛ በላይ ፕሮጀክቶች እንዲከታተሉ የተሰጠ ሲሆን ፕሮጀክቶቹ በታለመላቸው የጊዜ ማዕቀፍ፣በተያዘላቸው በጀት  እንዲሁም በተቀመጠላቸው የጥራት ደረጃ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ የአማካሪ ማሕበራቱ ድርሻ የላቀ መሆኑ ተገንዝበው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ በመድረኩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡

Via የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ

@etconp
👍7
የሲሚንቶ ስርጭት እና ግብይትን ለመወሰን የወጣው መመሪያ ቁጥር 940/2015 በአግባቡ ተግባራዊ እየተደረገ እንዳልሆነ ተገለጸ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር  ሚኒስቴር ሚኒስትር  አቶ ገብረ መስቀል ጫላ በሲሚንቶ ስርጭትና ግብይት ሂደት ሲስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን ለመቅረፍ መመሪያ ወጥቶ ተግባራዊ እየተደረገ ቢገኝም ችግሩ ተቀርፏል የሚል እምነት የለም ብለዋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከአምራቾች እና አከፋፋዮች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱም ሚኒስትሩ  ለአብዛኛዎቹ አከፋፋዮች ትስስር አለመፈጠሩ የአንዳንድ ፋብሪካዎች  ለመመሪያው ተገዢ አለመሆን፤ የደላላዎች ጣልቃ ገብነት፤ተናቦ ያለመስራት ችግር፤የአከፋፋዮች እና የቸርቻሪዎች አለመተዋወቅ፤ ያለደረሰኝ የሚካሄድ ግብይት መበራከቱ ለችግሩ አለመቀረፍ በምክንያትነት  ከሚጠቀሱ ጉዳዮች ውስጥ ተጠቃሾቹ መሆናቸውን  ጠቁመዋል፡፡

የሲሚንቶ የችርቻሮ ዋጋ በሲሚንቶ አምራቾች ማህበር እንዲወሰን መደረጉን ተከትሎ በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ዋጋው ከ1200 ብር እንዳይበልጥ ቢደረግም በተደረገው የዳሰሳ ጥናት አንድ ኩንታል ሲሚንቶ እስከ 1850 ብር በመሸጥ ላይ እንደሚገኝም ተጠቅሷል፡፡

የዚህ መመሪያ ተግባራዊ መደረግ በጎ ጅማሮ ሆኖ ሳላ ነገር ግን አንዳንድ ፋብሪካዎች ለትክክለኛ አከፋፋዮች ያለመስጠት ችግር ይስተዋላል ያሉት በዉይይቱ የተሳተፉ አከፋፋዮች ለዚህም እልባት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

የሲሚንቶ አምራቾች በበኩላቸው በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ አብዛኛዎቹ ሲሚንቶ  አምራቾች ከአቅም በታች እያመረቱ በመሆኑ የፍላጎትና የአቅርቦት ያለመመጣጠን ችግር በመከሰቱ ለሁሉም አከፋፋዮች ሲሚንቶ በተፈለገው መጠን ማዳረስ እንዳልተቻለም አስረድተዋል፡፡

የንግድ ስርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተሻለ በልሁ በበኩላቸው የወጣውን መመሪያ ከመተግበር አኳያ ውስንነቶች  የተስተዋሉ በመሆኑ መንግስት የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ግዴታ ስላለበት  በእነዚህ ህገ ወጥ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቀዋል፡፡

በሲሚንቶ ስርጭትና ግብይት ስርዓት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የጋራ ስራ እንደሚያስፈግም በመድረኩ ተመላክቷል፡፡

@etconp
👍6❤2
👉የምትሰሩትን ያክል Member ብዙ አላገኛችሁም ብላችሁ ለጠየቃችሁን እንዲሁም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ይህ ቻናል ያለ እናንተ ድጋፍ የትም እንደማይደርስ የሚታወቅ ነው።

🚧ምን በማድረግ የቻናሉን ተከታዮች ቁጥር ማብዛት ይቻላል?

📍1 -  ቻናላችን አሁን ስልካቹ ላሉ የ ኮንስትራክሽን ቤተሰቦች INVITE ያርጉ።

📍2 - አሁን ይህን ለአስር ሰው Forward ያድርጉ

📍3 - ወደ ግሩፓች ሼር የምታደርጉ ከሆነ በቀላሉ እንበዛለን። 

⚡️አብረን እንብዛ

✌️መብዛታችን በሰፊው እንድንማማር ይረዳናል።

💫Click And Join It ⬇️

https://t.me/ETCONp

@ETCONp

🙏እናመሰግናለን🙏
👍3❤2
ለማኅበሩ አባላት በሙሉ!

ባለፈው የካቲት 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በተካሄደው የማኅበሩ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች እየተፈተንባቸው ስላሉ ተግዳሮቶቻችንን ከሚመለከታቸው መንግሥታዊ ባለድርሻ አካላት ጋር በሚደረግ የውይይት መድረክ ላይ ማቅረብ የምንችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ጥያቄውን ለከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አቅርበን ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ከኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር እና ከመንግሥት ግዥ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጋር በጋራ በመሆን ሊያወያዩን እንደፈቀዱ ገልፀን ጥሪ ሲደረግላችሁ እንድትገኙ ማሳሰባችን ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት ከታች በተገለፀው ቀንና ሰዓት እንድትገኙ ማህበሩ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ቀኑ -  መጋቢት 8 2015 ዓ.ም

ሰዓቱ - ከጠዋቱ 2፡30

የስብሰባው ቦታው - በከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር መ/ቤት 10ኛ ፎቅ

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር

@etconp
👍6