Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉Difference Between Main Bars and Distribution Bars

🚧Main reinforcement normally used at the bottom of the slab.

🚧Distribution bars placed on top of the main bar.

⭐️Main Reinforcement bars are placed in shorter direction and Distribution bars placed in longer span direction

⭐️Main Reinforcement Bars are used to transfer the bending moment developed at the bottom of the slab.

🏷Distribution Bars are used to hold the slabs on either way and to resist the cracks and shear stress developed at the top.

╔═══════
 🌐  join 👇
Channel @ETCONpWORK
Group @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆═══════
👍11❤2
🏷የአዲሱ የዓባይ ድልድይ የመገጣጠሚያ ሙሊት ሥነ ሥርዓት በትናንትናው ዕለት ተካሂዷል።

⚡ከዓባይ ወንዝ በሁለቱም አቅጣጫ  ሲሠራ የቆየውን ድልድይ የመጨረሻ የማገናኘት የሙሊት ሥራ  ከሁለቱም አቅጣጫ ሲሠራ የነበረውን የድልድይ ግንባታ የመገጣጠምን ሙሌት አስመልክቶም የማብሠሪያ ሥነ ሥርዓት በቦታው ላይ ተከናውኗል።

⚡3 መቶ 80 ሜትር የሚረዝመው አዲሱ የዓባይ ድልድይ ከሁለቱም በኩል ሲሠራ ቆይቶ ትላንት መጋቢት 10 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት የመገጣጠሚያ ሙሊት ሥራው እንደተከናወነም ለማወቅ ተችሏል ።

@etconp
👏5👍4
👉A cofferdam is an enclosure built within a body of water to allow the enclosed area to be pumped out.

🚧This pumping creates a dry working environment so that the work can be carried out safely.

🚧Cofferdams are commonly used for construction or repair of permanent dams, oil platforms, bridge piers, etc., built within or over water

╔═══════
 🌐  join 👇
Channel @ETCONpWORK
Group @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆═══════
👍8
👋ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች፣ብዙዎቻቹ በጠየቃችሁን መሠረት ተከታታይ ይዘት ያለው በተግባርም የተሰራ ፕሮጀክት በ አማርኛ እንዲሁም በአገራችን ኮድ እና ስታንዳርድ እንደ TAKE OFF SHEET፣BOQ፣MS PROJECT እና ሌሎች ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ትምህርቶች እና አሰራሮች ይዘን በ YOUTUBE ለእናንተ ለማድረስ  ዝግጅታችንን  እያጠናቀቅ ሰለሆነ  በጣም አጭር በሚባል ጊዜ ውስጥ  ማለትም 1000 SUBSCRIBER ሲደርስ የምንጀምር ይሆናል።

🌟እስከዛው ግን እናንተ ቤተሰቦቻችን የምንጠይቃቹ ከታች ያለውን YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE  በማድረግና ለጓደኞቻቹ በመላክ  ቤተሰብ  እንዲሆኑ ያግዙ።

💫ሊንኩ ይሄው 👇👇👇

https://youtu.be/qIpy-LMQ8QE
👍5❤4🎉2👌2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉Automatic Wall Plastering Machine

🚧1. The Automatic wall plastering machine utilize the conveyor taking mortar forwardly and upwardly, the conveyor can take mortar or stop in any position by hand control. It can render to the roof by all direction.

🚧2. It can make the machine installation fast and stable The hydraulic telescopic rod can make the machine installation in 10 seconds.

🚧3. There are min-vibrators after the spatula, thus there is no need to worry about hollowing and adhesion.

🚧4. The rendering machine can saving more than 20% raw material (cement& sand).

╔═══════
 🌐  join 👇
Channel @ETCONpWORK
Group @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆═══════
👍10💔2🕊1
👉ጥናታዊ ጽሁፍ ስታዘጋጁ እነዚህን 15 ነጥቦች ልብ በሉ

⭐️የጥናት/ሪሰርች ይዘት፣ ስፋትና ጥልቀት ሊለያይ ይችላል ተጨባጭ ችግርን ለመፍታት ይሁን የተደበቀ ምስጢርን ፈልፍለን ለማግኘት ወይንም ከዚሁ ለተለየ ዓላማ ጥናት ሊታቀድና ሊከናወን ይችላል፡፡

🚧በዚሁ መሰረት አንድ ጥናት/ሪሰርች ሲዘጋጅ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ብዙዎች ዘንድ የተለመዱ ዋና ዋና ይዘቶችን ሊያካትት ይችላል፡፡

🏷ዝርዝሩን ተመልከቱት

⏺ የጥናቱ ርዕስ/ Topic
የጥናት ርዕስ ቃላት ጥንቃቄ ይፈልጋል፡፡ ትክክለኛ ስዋሰው፣ ገላጭ ቃላት፣ የጥናቱን ችግር፣ ሥፍራ/ቦታ በተቻለ መጠን በሚስብ ሁኔታ ቢጻፍ ይመረጣል፡፡ ርዕሱን የሚያነብ ሰው የጥናቱን ይዘት በቀላሉ እንዲረዳ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በዚሁ በፊት ገጽ ላይ ከርዕስ በተጨማሪ፣ የአጥኚው/ዎቹ ሙሉ ሥም፣ ጥናቱ የሚቀርብለት ሠው/ተቋም፣ጥናቱ የተዘጋጀበት ወቅትና ሥፍራ ይጠቀሳሉ፡፡
⏺ ምስጋና/ Acknowledgement
የምሥጋና መልዕክት ግልጽ ነው፡፡ ጥናቱ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ በተለያዩ መልኩ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሠዎች የሚመሰገኑበት ክፍል ነው፡፡ ሠው ብቻ ላይመሰገንበትም ይችላል፡፤ ሥፍራዎች፣ ሁኔታዎች፣ ወቅቶችና ሌሎች ጉዳዮች በዚህ ክፍል ሊመሰገኑ ይችላሉ፡፡
⏺ ማውጫ/Table of content
በማውጫ የጥናቱ የተለያዩ አቢይና ንዑስ ክፍሎች የሚገለጽበት ገጽ ይጠቀሳል፡፡
⏺ መግቢያ/ Introduction
በዚህ ክፍል የጥናቱን መነሻ ለአንባቢዎች መረጃ የሚሰጥበት ነው፡፡ መግቢያ መንዛዛት የለበትም፡፡ አንድ ገጽ ይበቃል፡፡ ዞሮ ዞሮ የአንድ ጥናት መግቢያ የአንባቢውን ስሜት የሚቀሰቅስ፣ የጥናቱን ወሰንና አቅጣጫ የሚያመላክት፣ጥናቱን እንዴት እንደሚሰራና የጥናቱን ጭብጥ የሚያሳይ ይዘት እንዲኖረው ተደርጎ ይዘጋጃል፡፡
⏺ የጥናቱ ዓላማ /Objective
የጥናት ዓላማ ከተለያዩ ርዕሶች ጋር ጥልቅ ቁርኝት አለው፡፡ የጥናት ዓላማ፣ ከጥናቱ ችግሮች፣መላ ምቶች መረጃና ውጤት አቀራረብና አተናተን፣ ማጠቃለያና መደምደሚያ ጋር ይተሳሰራል፡፡ የጥናት ርዕሰ ከተመረጠ በኋላ፤ በጉዳዩ ዙሪያ ያሉ ችግሮችን በሚገባ ከተረዳን በኋላ የጥናት ዓላማዎች ይዘጋጃሉ፡፡
የጥናት ዓላማዎች አቢይና ዝርዝር ተብለው ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ ዞሮ ዞሮ ዓላማዎች በጥናቱ የተጠቀሱ ቁልፍ ችግሮችን ወይንም መላምትን መሰረት ተደርገው ይቀረጻሉ፡፡
⏺ Statement_of_the_problem ፦ ይኸኛው ዋና መሠረት ነው። ትክክለኛ ገለጻም ይጠይቃል። “የጥናቱ ርዕስ ለመስራት ያነሳሳህ/ሽ ምን ችግር ኖሮ ነው[what is the problem that initiate you to apply your research over this title?.....]” ለሚል ጥያቄ ተገቢ መልስ የምትሰጡበት የጥናት ሰነድ ክፍል ነው። ለጥናት የተሰማራችሁበትን ችግር ወይም የአንድ ነገር እጥረት ለማስቀመጥ ሞክሩ። ገለጻችሁም "There is lack of/a problem of/ ____" የሚል አይነት ቢሆን መልካም ነው።
⏺ የጥናቱ አስፈላጊነት/ Significance of the study
ጥናት ለተለያየ አገልግሎት ይውላል፡፡ በዚህ ክፍል የዚህን ጥናት ውጤት አስፈላጊነት ግልጽ በሆነ መልኩ በዝርዝር ይቀመጣል፡፡
የጥናቱን ወሰን/ Scope of the study
በዚህ ንዑስ ክፍል የጥናቱ አጠቃላይ ስፋት፣ ርዝመትና ጥልቀት ይገለጻል፡፡ ለምሌ ያህል፣ ጥናቱ የት እንደሚሰራ፣ በእነማን ላይ እንደሚሰራ፣ ጊዜና የመሳሰሉ ወሰኖች በግልጽ ይቀመጣሉ፡፡ ወሰን ያልተበጀለት ጥናት መጀመሪያውንና መጨረሻውን ማወቅ ይቸግራል፡፡
⏺ የጥናቱ ታሳቢ ክፍተቶች/ Limitation
አንድ ጥናት ሲካሄድ ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ ሊሆን አይችልም፡፡ የተለያዩ ክፍተቶች ሊፈጠሩ ይችላሉና በዚህ ክፍል በጥናቱ ወቅት ሊገጥሙን የሚችሉ ችግሮች ይጠቀሳሉ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ችግሮች ከአጥኚው አቅም በላይ ሊሆኑ ይገባል እንጂ ሁሉንም ችግር መጥቀስ አይገባም፡፡ ታዲያ በዚህ ክፍል ክፍተቶቹን ለማጥበብ በአጥኚው ሊደረጉ የሚገቡ ጥረቶችም ሊካተቱ ይገባል እንጂ ክፍተቶችን ብቻ ጠቅሶ እጅን አጣጥፎ መቀመጥ አይገባም፡፡
⏺ የጥናቱ ዘዴና አካሄድ/ Methodology of the study
የአንድ ጥናት ዘዴና አካሄድ/ Methodology እንደየ ጥናቱ ጠባይ፣ችግር፣አይነትና ዓላማ የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡ ዘዴና አካሄድ መጥቀስ ማለት በአጭሩ ጥናቱ እንዴት እንደሚሰራ፣ የት እንደሚሰራ፣ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ፣ የመረጃውም መሰብሰቢያ ዘዴ እንዴት አንደተዘጋጀ፤ ምን አይነት ጥናት እንደሆነ፣ የናሙና ይዘት፣ አመራረጥና መጠን (ናሙና ያለው እንደሆነ) ፣ ውጤቱ እንዴት እንደሚተነተን፣ውጤቱ እንዴት እንደሚሰራጭና የመሳሰሉ የጥናቱን አጠቃላይ አሰራርና አካሄድ መግለጽ ማለት ነው፡፡
⏺ የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ/ Literature Review
በዚህ ክፍል ከዚህ በፊት የተደረጉ ጥናቶችንና ስምምነቶችን የተቀመጡ ንድፈ-ሃሳቦችን በጥልቀት ይመረመራሉ፡፡ ተዛማጅ ጽሁፍ በጥናት ውስጥ በተለያየ መልኩ ማካተት የሚስችል የጥና ጽሁፍ ምልከታ አጻጻፍ አለ፤ ከዚህ ውስጥ የሚስማማንን መርጠን መጠቀም የእኛ ምርጫ ነው፡፡ የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ ሥራ ሰፊና ጥልቅ ነውና በዚህች አጭር ንዑስ ርዕስ ሁሉን መግለጽ ይከብዳል፡፡
⏺ የጥናት ግኝት አቀራረብ ትንተና/ Data analysis & Interpretation
የአንድ ጥናት ውጤት እንደ ጥናቱ አይነትና የመረጃ ማጠናቀሪያ ሥልት ሁኔታ፣ በተለያየ መልክ ሊቀርብና ሊተነተን ይችላል፡፡ አንድን ጥናት ጥናት የሚያሰኘው አጥኚው የሳይንስና የሎጂክን ስልት በመከተል በግኝቶቹ ላይ የሚደረገው ትንታኔና ትርጉም እንጂ ጥሩ የሆኑ መረጃ ማቅረብ ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡
በመሆኑም በግኝት አቀራረብና አተናተን ወቅት አስተያየትን ከተጨባጭ ሁኔታ መለየት፤የጥናቱን ወሰን ማስታወስ እንዲሁም የተሳሳተ ትንታኔና ትርጉም ላለመስጠት ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
⏺ ማጠቃለያ/ Conclusion
ጥናቶች የተለያየ ስፋትና ጥልቀት አላቸው፡፡ ታዲያ ይህ ክፍል ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ያሉ የወቅቱን ሁኔታና ግኝቶች በማጠቃለል አጠር ተደርጎ የሚቀርበት ነው፡፡
⏺ የመፍትሔ ሐሳብ/ Recommendation
በጥናቱ የተለዩ ችግሮችና መንስዔዎቻቸው ከታወቁ በኋላ የመፍተሄ ሃሳቦች በዝርዝር ይቀመጣሉ፡፡ ስለዚህ የመፍተሄ ሃሳቦችን ከማቅረባችን በፊት ችግሮቹን በሚገባ መረዳት ይገባል፡፡
በዚህ ክፍል ሁሉም የመፍሔ ሀሳብ ሊገለጽ አይገባም፡፡ ተጨባጭ ሁኔታን በመረዳት ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉትን በመለየት በቅደም ተከተል ማቀመጥ ያስፈልጋል፡፡
⏺ አባሪ/ Appendices
በዚህ ክፍል ለጥናቱ የተገለገልንባቸውን ዝርዝር የመረጃ ማጠናቀሪያ ቅጾችና ሌሎች ዝርዝር ግብዓቶች ይቀመጣሉ፡፡
ጥናቱ ለማካሄድ የተጠቀምናቸውን መረጃዎች ማለትም መጠይይቆች፤ የተለያዮ ፕሮግራሞች እና ሌሎች ፎርማቶች ከጥናቱ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡበት ነው፡፡
⏺ ማጣቀሻ /Reference
ይህ ክፍል ለጥናቱ የተጠቀምናቸው መረጃዎች የሚገለጽበት ነው፡፡ መረጃዎቹ በማን፣ መቼ፣የት እንደተጻፉ በግልጽ መቀመጥ አለባቸው፡፡ ስምምነት የተደረሰባቸው የተለያዩ ማጣቀሻ አጻጻፍ ስልቶች አስተምህሮዎች አሉና በተፈላጊው ስልት ማጣቀሻን በግልጽ በማስቀመጥ የጥናቱ እውነተኛነት በዚህ ክፍል ይረጋገጣል፡፡

@etconp
👍13❤2👌2
🏷የጥናትና ምርምር ቅደም ተከተላዊ ይዘቶች/ደረጃዎች/

⭐️በሁሉም የጥናትና ምርምር ዓይነቶች ተቀራራቢ ይዘት/ደረጃዎች/ የሚኖራቸው ቢሆንም የተወሰኑ ልዩነቶች ይኖራሉ፡፡

*⃣ ነገር ግን በተለይ በተግብራዊ ጥናትና ምርምር ውስጥ የመጀመሪያው ክፍል መግቢያ /Introduction/ ሲሆን በዚህ ውስጥ የጥናቱን ርዕስ ከመምረጥ
ጀምሮ የጥናቱን አጠቃላይ ሁኔታ የሚገልጽ ፅንሠ ሀሣባዊና ታሪካዊ ዳራ፣ የጥናቱ ዓላማ፣ አስፈላጊነት፣ የጥናቱ ችግር ምንነትና የጥናቱ ወሰን ወዘተ ይገለጽበታል፡፡

✅ ሁለተኛው ክፍል የተዛማጅ ጽሑፍ ክለሣ ሲሆን በዚህም ከጥናቱ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ጽሑፎች የሚገመገሙበት፣ የሚነፃፀሩበትና ልምድ የሚወስዱበት ክፍል ይሆናል፡፡

✅ 3ኛው ክፍል የጥናቱን ዘዴ ( Methodology) የሚገለጽበት ነው፡፡

✅ 4ኛው ደግሞ የተሰበሰበው መረጃ የሚተነተንበትና የሚተረጐምበት ሲሆን 5ኛው ማጠቃለያ እና የውሣኔ አስተያየት የሚሠጥበት ክፍል ነው፡፡


✅ ከነባራዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች መረዳት እንደተቻለው ብዙ ሰዎች በትምህርት ነክ ችግሮች ላይ ጥናትና ምርምር ማድረግ ይፈልጋሉ፡፡

✅ በምን መልክ የምርምር ሥራ መሥራትም እንዳለባቸው ይወስናሉ፡፡ ዋነኛው ችግር ግን ምርምር የሚያደርጉበትን ርዕስ ማወቅና መወሰኑ ላይ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የዚህ ችግር ምንጭ ነው ተብሎ የሚገመተው ሰዎች መሥራት የሚፈልጉት ጥናት አዲስ፣ ልዩ የሆነ በጣም አስፈላጊና ጠቃሚ ምርምር እንዲሆን ስለሚፈልጉ ነው፡፡ ፍላጐቱና ሃሣቡ ጥሩ ሆኖ ሳለ የዚህ ዓይነት ሃሣብ ተመራማሪውን በጣም ከባድና መረጃ አልባ ወደሆነ መስክ ይመራውና ችግር ላይ ይጥለዋል፡፡

✅ እዚህ ላይ እንድንረዳው የሚያስፈልገን ዋነኛ ነጥብ ማንኛቸውም የምርምር ፕሮጀክቶች ከማንም አያንሱም፡፡ የሌሎች የምርምር ውጤቶችን ማንበብና ማጤን አዲስ አሠራርን እንድንፈጥር ወይም ለሌሎች አዳዲስ ግኝቶች እንድንጓጓ ወይም ግኝቶችን በተለየና አዲስ በሆነ መልክ ለመጠቀም ምርምር እንድናደርግ ይገፋፋናል፡፡

✅ በአጠቃላይ የምርምርን ርዕስ ለመወሰን በመስኩ ጠለቅ ያለ እውቀት እንዲኖር መጣርን ይጠይቃል፡፡ አንድን ጥናት ወይም ምርምር ለማድረግ ከሚገፋፉ ምክንያቶች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

✅ 1. በአንድ በተወሰነ የጥናት መስክ የታወቀው ነገር ውሱን ሆኖ ሲገኝና ሰፋ ያለ እውቀትና ግኝት እንዲኖር ሲያስፈልግ፣
✅ 2. በጥልቀት ያልተጠና ዕውቀት በመኖሩ ጅምር አስተሳሰብን ፍፃሜ ለማድረስና የተሟላ እውቀት ማግኘት አስፈላጊ ሲሆን፣
✅ 3. የዕውቀት መረጃዎች ያሉና የታወቁ መስለው ነገር ግን ያልተረጋገጡ ሆነው ይህን መሥራት የግድ ሆኖ ሲገኝ፡፡
✅ 4. እየሠራነው ላለው ተግባር ለውጥ/ውጤት ስለመምጣቱ ለማረጋገጥ ስንፈልግ ወይም ለውጥ አለማምጣታችንን ስናረጋጥ ምክንያቱን ለማወቅ ስንፈልግ ፣ ከላይ በርዕሱ እንደተገለፀው የምርምር ዋና ዋናዎቹ ቅደም ተከተላዊ ደረጃዎች ምንድን ናቸው የሚለውን ነጥብ ስናነሣ የሚከተሉትን ደረጃዎች ማንሣት ይቻላል፡፡

✅ 1.7.1. የምርምርን ርዕሰ ጉዳይን በሚገባ መግለጽ/ Statement of the problem/
ከላይ እንደተገፀው ማንም ሰው የምርምር ርዕስ ነው በሚል አስተሳሰብ አንድን ርዕስ እንደመሰለው ማስቀመጥ ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጉዳዩን በትክክልና በጥልቀት አውጥተው አውርደው በአእምሮ ውስጥ ጉልህ የሆነ ግንዛቤ/ምስል እንዲፈጥር ማድረግ
ካልተቻለ ማንኛውም ርዕስ ለምርምር ብቁ ርዕስ ላይሆንልን ይችላል፡፡ ስለዚህ ምርምር የሚደረግበት ርዕስ ጉልህና አሻሚ ትርጉም የሌለበት ሆኖ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡

✅ ማንኛውም ተማራማሪ የምርምሩን ርዕስ በትክክል ለመግለጽ በሚፈልግበት ጊዜ በአጽህኖት ሊያስታውሳቸው የሚገባ ሁለት መሠረታዊ ነጥቦች አሉ፡፡ እነዚህም፡-

✅ 1.7.2. መላምት /Hypotheses of the study/
መላምት / Hypotheses/ ተመራማሪው ምርምሩን ለመተግባር ሲነሳ በመጀመሪያ አንዳንድ ጥርጣሬያዊ ጥያቄዎችና መልሶች ወይም መፍትሔዎች ይሆናሉ ብሎ የሚያስባቸው ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም ባቀረብነው ምሳሌ የተማሪውን የሥነ ምግባር ጉድለት መንስኤዎች ብናስታ የቤተሰብ አያያዝ

✅ በትምህርት ዝቅተኛ ውጤት ማምጣትና ተስፋ መቁረጥ ወዘተ….
የሚሉት ለተማሪው የጠባይ መበላሸት ምከንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው በመላምት መልክ የቀረቡ ሃሳቦች ናቸው፡፡ እነዚህም በጥናቱ ውስጥ ሊረጋገጡ ወይም ሊሻሩ የሚችሉ ናቸው፡፡ መላምት በጥያቄ ወይም በዓረፍተ ነገር መልከ ሊቀርብ ይችላል፡፡

✅ ለምሣሌ፡ መላምት 1፡ ተማሪውን በጥባጭ ያደረገው የቤተሰብ አያያዝና አስተዳደር መበላሸት ነው ፡፡ /ዓረፍተ ነገር/

✅ መላምት 2፡ በተማሪው ጠባይ ላይ ተጽእኖ ያደረገው የጓደኞቹ ግፊት ይሆን? /በጥያቄ መልክ/

✅ 1.7.3. መሠረታዊ ጥያቄዎች /Basic Research Questions/
እነዚህ በጥናቱ ውስጥ በተለያዩ ዘዴዎች መረጃዎችን በማሰባሰብ መመለስ ያለባቸው ጥያቄዌች ናቸው፡፡ የእነዚህ መሠረታዊ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት የመላምቶችን እውነተኛነት ወይም ሃሰተኛነት ግልጽ ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ ከላይ የተቀጠሰውን ተማሪ ሁኔታ ብናይ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መመለስ ጠቃሚ ይሆናል፡፡

✅ የትምህርት ውጤቱ ምን ይመስላል የቤተሰቡ አያያዝና አስተዳደር ምን ይመስላል ወዘተ እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን ተመራማሪው መመለስ ከቻለ ለልጁ ጠባይ መበላሸት መንስኤ የሆነውን ነገር ማግኘት ይችላል፡፡ ስለዚህ በምርምር አለም ተመራማሪው በጥናቱ ሂደት ውስጥ አጥጋቢ ምላሽ ሊያገኝላቸው የሚገባው አብይ ነጥቦችና ጥያቄዎች እንዳሉ መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡ ከላይ የተገለፁት ሁለት ጉዳዮች ተመሣሣይ አገልግሎት ያላቸው በመሆኑ አጥኝዎች ከሁለቱ አንዱን ብቻ በመውሰድ ሲጠቀሙበት ይታያል፡፡ ሰለዚህ እኛም በጥናታችን የሚመቸውን አቀራረብ በምረጥ አንድም በመላ ምት ወይም በመሠረታዊ ጥያቄዎች ላይ መሠረት አድርገን መነሣት እንችላለን፡፡

✅ 1.7.4. የጥናቱ አስፈላጊነት /Significance or Justification of the study/
አንድ ጥናታዊ ምርምር ሲደረግ /በተለይም በተግባር ተኮር ጥናትና ምርምር/ በማንኛውም መልኩ ቢሆን የጥናቱ ዋነኛ ዓላማና ግብ የችግሮችን መፍትሔ ለማግኘት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚሁም መሠረት እንደ ችግሮቹ አንገብጋቢነት ደረጃ በወቅቱ መፍትሔ ቢሰጣቸው ምን ያህል ጠቃሚ እንደሚሆን መገለጽ ይኖርበታል፡፡ ገለፃው ከግል፣ ከቡድን፣ ከብሔራዊና ከዓለም አቀፋዊ አኳያ ሊታይ ይችላል፡፡ ከማንኛወም አንፃር ቢሆን ጥናቱና ምርምሩ በውጤቱ ማኀበራዊ ጠቀሜታ እንዲኖረው ያስፈልጋል፡፡

✅ ስለዚህ አንድ ተመራማሪ በአንድ ጉዳይ ላይ የሚያደርገው ምርምር በዘፈቀደ ለሱ እንደተሰማው ሳይሆን የችግሩን አንገብጋቢነት ከማኀበራዊ ጠቀሜታ አኳያ በመገምገምና ስለጥናቱም ያለውን ምክንያት በግልጽ በስቀመጥ መሆን ይኖርበታል፡፡

✅ 1.7.5. የጥናትና ምርምር ክልልን መወሰን ( Delimitation)
ከብዙ ጥናታዊ ምርምር ግምገማ መረዳት እንደተቻለው የብዙ ጀማሪ ተመራማሪዎች ችግር የጥናትን ክልል መወሰን አለመቻል ነው፡፡ አንድ ተመራማሪ የምርምር ርዕሱን በሚገባ ከገለፀ በርዕሱ ስለተገለፀው ጉዳይ ከተለያዩ ገጽታዎች አንፃር በአንድ ወቅት በጥልቅ ማየት/ማጥናት/ ይቸግረው ይሆናል ወይም የአንድን ጉዳይ ሁለንተናዊ ገጽታ ላጥና ብሎ ቢነሳም ምርምሩ ከጥልቀት ይልቅ ስፋት ብቻ ይኖረውና እያንዳንዱ ነጥብ በተሟላና በጥልቀት ሳይዳሰስ ሊታለፈ ይችላል፡፡
👍5🍌1
👉አንድ ፕሮጀክት ስንቀርጽ ማካተት ያለብን ጭብጦች

✅1 ማጠቃለያ /Executive Summary

⭐️የንግድ እቅዱ አጠቃላይ ይዘትና ጠቀሜ፤ የምርት ጥራትና አቅርቦት፤ የገብያ ሁኔታ፤ የገብያ ፉክክር፤ ወጪና ገቢ፣ የገንዘብ ፍሰት፣ የሀብትና እዳ አጠቃላይ ትንበያ፣ የፕሮጀክቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳና መሰል ጉዳዮችን በአጭሩ ይዳስሳል።

✅ 2 የፕሮጀክቱ ዳራ

⭐️ስለ አመልካቹና ፕሮጀክቱ አጠቃላይ መረጃዎችን ማለትም የአመልካቹን አድራሻ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ እንዲህውም የድርጅቱን አድራሻ፣ የቢዝነሱን አመሠራረት(በግለሰብ ደረጃ፣ በሽርክና ወይስ በአክሲዮን ማህበር ብሎ በመለየት) ማካተት አለበት።

✅ 3 የገብያ ትንተና

⭐️የፕሮጀክቱን ታርጌት ማርኬት፣ ገብያው ውስጥ ያለውን የምርትና አገልግሎት አቅርቦትና ፍላጎት ዳሰሳ፣ የተዋዳዳሪነት ትንተና፣ የገብያ ስልት ትንተና (ቦታ፣ ዋጋ፣ ማስታወቂያና ምርት በተመለከተ) የዋጋ ትመና፣ የጥንካሬ ድክመት መልካም አጋጣሚና የስጋት ትንተና ማካተት ይኖርበታል።

✅ 4 የቴክኒክ ጥናት

⭐️በዚህ ክፍል የሚካታቱ ሀሳቦች፦ የፕሮጀክቱ ሳይት፣ የፕሮጀክቱ ኢንጅነሪግ መግለጫ፦ የማምረቻ ቦታው ሲቪል ስራዎች፣ የሚያስፈልጉ ማሽነሪና ቁሳቁሶች፣ የመገልገያና መሠረተ ልማት አቅርቦት፣ የምርት ሂደት፣ የአካባቢ ተጽኖ ግምገማ

✅5 አደረጃጀት

⭐️ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግ የሚያስፈልገው የሰው ሀይል፤ ለስራ መደቡ የሚያስፈልገው ዝቅተኛ የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ፤ ለስራ መደቦች የተቀመጠ የስራ ዝርዝር፤ ድርጅታዊ መዋቅር፤ ደመወዝና ጥቅማጥቅም፤ የምልመላ መረጣና ቅጥር አፈፃፀም ዕቅድ፤ የትምህርትና ስልጠና ዕቅድ፤ ገብያው ውስጥ ያለው የሰው ሀብት ፍላጎትና አቅርቦት ጥናትን ማካተት ይኖርበታል።

✅ 6 የፋይናንስ እቅድ

⭐️ለካፒታል እቃዎች ግዥ፣ አሰተዳደራዊና ለክዋኔ የሚያስፈልጉ ወጪዎች የፕሮጀክቱን የፋንናስ ምንጭ
አጠቃላይ የአምስት ወይም የሶስት አመት የሽያጭ/ገቢ ትንበያ ወጪና ገቢ፣ የገንዘብ ፍሰት፣ የሀብትና እዳ አጠቃላይ ትንበያን ማካተት ይኖርበታል።

✅ 7 ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ

⭐️ፕሮጀክቱ ሲተገበር ለስንት ሰዎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ፕሮጀክቱ ከአመታዊ ሽያጩ ላይ ምን ያህል ግብር ለመንግስት ሊከፍል እንደሚችል
ፕሮጀክቱ ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት ከህብረተሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት እና የሚሰጠው ጥቅም ፕሮጀክት ከውጭ የሚገቡ እቃወችን በሀገር ውስጥ ለመተካት ጥረት በማድረግ የውጭ ምንዛሬ ለማዳን የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ እና መሠል ጉዳዮችን በዝርዝር ማካተት ይኖርበታል ።

✅ 8. መደምደሚያና አስተያየት

⭐️ከላይ የቀረቡ ማሳመኛ ሀሳቦችን መሰረት በማድረግ የማጠቃለያና የመፍትሔ ሀሳቦች በማቅረብ ፕሮጀክቱ የሊዝ ወይም ሌሎች አይነት ፋይናንስ ብድር አገልግሎት እንደሚያስፈልገው ማሳየት ያስፈልጋል።

@etconp
👍7👌2
👉Ferrocement in construction:

⭐️Ferrocement is a construction material, specially reinforced cement concrete(RCC), comprising cement mortar and wire meshes. Ferrocement is widely used in the construction industry due to its low self-weight and because it does not need skilled workers and standard frameworks.

@etconp
👍1
📢በነገራችን ላይ

🫵  የ ETCONp ድርጅት የሆነው ETCONp WORK የኮንስትራክሽን አቅርቦት ክፍተትን ለሞሞላት ከኮንስትራክሽን አቅርቦት ጋር የተያያዙ ስራዎችን ላይ በ መስራት እንደሚገኝ ሰምተዋል?

🌟የኮንስትራክሽን ባለሞያዎች ማለትም አናጺ፣ግንበኛ፣ፌራዩ፣ፎርማን እና ተዛማጅ ስራ የሚሰሩ ምታገኙበት
🌟 ኮንትራክተሮች  እና የኮንስትራክሽን ንግድ ውስጥ የተሰማሩ ሰዎች በ ቀላሉ የሚያገኙበት
🌟የ ኮንስትራክሽን ስራ እና ጨረታ የሚለጠፍበት
🌟የኮንስትራክሽን ማሽነሪ እና ማቴርያል አከራዮችም ከፈለጉ ከታች ባለው ቻናል ይቀላቀሉን።

⚡እንዲሁም አብረውን ለመስራት ካሰቡ ያግኙን

https://t.me/ETCONpWORK
❤1
What Is Grillage Foundation?

A Grillage foundation is a type of shallow foundation generally provided at the base of the columns to distribute heavy structural loads of columns, piers, or scaffolds over a larger area.
The load is distributed using layers or tiers of joists; each tier is placed at right angles to the adjacent tier. Grillage foundation is most suitable for soil having low bearing capacity.


This foundation helps avoid deep excavations as the necessary base area is provided for the transmission load. The depth of the foundation is limited from 1000 mm to 1500 mm.
Grillage foundation consists of the following components: grillage beams, spacing or spandrel beams, and foundation bolts. The grillage beam is made from steel or wooden bars bolted together to form a solid base.
The spacing or spandrel beam is placed perpendicularly to the grillage beam on each side and provides additional support for lateral loads.

@Etconp
@etconpwork
👍11❤1
Ethio Construction Engineering
PART 2 Design and analysis የመዋቅር ንድፍ ስናወጣ ዋፍል ሶሌታን እንደ flat slab ነው የምናስበው ግን ቅድም ከ ribbed slab ጋር ልዩነቱ ዋፍል ሶሎታ two way ነው ብዬ ነበር አይጣረስም ወይ ልትሉኝ ትችላላችሁ ይኸውላችሁ የ ዋፍል ሶሌታ torsional stiffness (አልጠመዘዝ ባይነቱ) ተመሳሳይ ይዞታ ካለው two way solid slab ጋር ስናነፃፅር የ ዋፍል…
👉🏻 Ribbed slab

ብሎኬት የሚረበረበው የሶሌታ አይነት

ይህኛው የሶሌታ አይነት ከሌላው ሚለየው Panelኦቹ በ አርማታ ሳይሆን የሚሞሉት በ ብሎኬት ነው። ቢሞቹ RC ናቸው የሶሌታ panel ግን ብሎኬት ነው። ይሄ እንዴት ይሆናል 🤔? መጀመሪያ ፎርምወርካችንን እናነጥፍና የቢማችንን ዘርግተን እንደጨረስን ብሎኬት (ድርግዳ ምንሰራበት አይነት ብሎኬት ሳይሆን የተለየ አይነት) እንደረድራለን ከዛን U-bar እንደጥላ ይደረደራል ከዛም U-bar ጎድጓዳማ ቦታ ውስጥም ከላይም ፎሮዎች ይዘረጋሉ ከ ቢሞቹ ብረት ጋር ይታሰራሉ ከዛም አብረው ይሞላሉ።

PART 1

@etconp

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=
👍14❤3🐳1
ADDIS ABABA’s tallest buildings 🏙️
የ አዲስ አበባ ረዣዥም ህንፃዎችን
፩.(CBE headquarter) ንግድ ባንክ
- 54 story 💵 $303.5M 🏗️ by 🇨🇳
📍ብሄራዊ

፪.(NIB BANK) ንብ ባንክ
- 43 story 💵 $50M 🏗️ by 🇨🇳
📍 ሜክሲኮ

፫.ህብረት ባንክ designed by Eskinder Architects
- 40 story 💵 $36.3M 🏗️ by 🇨🇳
📍 ሜክሲኮ

፬. ዘመን ባንክ
- 36 story 💵 $21.8M 🏗️ by 🇨🇳
📍 ሜክሲኮ




@etconp

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=
👍13❤1
Ethio Construction Engineering
👉🏻 Ribbed slab ብሎኬት የሚረበረበው የሶሌታ አይነት ይህኛው የሶሌታ አይነት ከሌላው ሚለየው Panelኦቹ በ አርማታ ሳይሆን የሚሞሉት በ ብሎኬት ነው። ቢሞቹ RC ናቸው የሶሌታ panel ግን ብሎኬት ነው። ይሄ እንዴት ይሆናል 🤔? መጀመሪያ ፎርምወርካችንን እናነጥፍና የቢማችንን ዘርግተን እንደጨረስን ብሎኬት (ድርግዳ ምንሰራበት አይነት ብሎኬት ሳይሆን የተለየ አይነት) እንደረድራለን ከዛን…
PART 2

Ribbed slab

- it’s flat slab where there is no flange beam sometimes there is flange at the edge of the building to brace columns moreover the width of the beams are greater than the depth of the beams in this type of column …. It’s often economical in our (ETHIOPIA CASE) because you don’t need to hatch the surface and it’s usually one way slab

- ለጥ ያለ የሶሌታ አይነት ሲሆን ጥልቀት ያላቸው ቢሞች (flanged) የሆኑትን ዙሪያውን ነው በ አብዛኛው የሚሰራው ኮለኖቹን brace ለማረግ ፣ በዚህኛው የሶሌታ አይነት የቢሞቹ ስፋት ከ ጥልቀታቸው ይበልጣል። ወጪ ቆጣቢ የሆነ የሶሌታ አይነት ነው ለምን ብትሉ በትንሹ አንቆረቁርም ቀጥታ ወደልስን ነው። one way slab ነው።

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

Telegram:- https://t.me/ETCONp

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
👍11❤4😱1
Ethio Construction Engineering
Next I’ll be presenting you about post-tensioning In Detail / በቀጣይ ስለ ፖስትቴንሽኒንግ በጥልቀት አቀርባለው

What do you know about post- tensioning ? ስለፖስት ቴንሽን ምን ያውቃሉ?
ይህ የምትመለከቱት prototype ምን ይበላል ?

1️⃣. Steel bar
2️⃣. Jack hammer
3️⃣. Tendon
4️⃣. Modern pipeline

@etconp


YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

Telegram:- https://t.me/ETCONp

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/
👍13
የጎርጎራ ፕሮጀክት በአራት ወራት ውስጥ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል

👍 ሰው ሰራሽ ወደብ
***********************
@etconp
👍22👏2
Ethio Construction Engineering via @like
ይህ የምትመለከቱት prototype ምን ይበላል ? 1️⃣. Steel bar 2️⃣. Jack hammer 3️⃣. Tendon 4️⃣. Modern pipeline @etconp YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432 Telegram:- https://t.me/ETCONp Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y= Facebook:…
🪡 Post tension

ከቃሉ ስንነሳ post - ድህረ ማለት ነው። concrete ከተሞላ በኋላ ብረቱን ስንወጥር post tension (ድህረ መወጠር) concrete ከመሞላቱ በፊት ደግሞ ሲወጠር pre-tension ይባላል። ልዩነቱን ሌላ ጊዜ በሰፊው አብራራለው ዛሬ ስለ post tension እናውጋ!

Post tension እዛው መስክ(site) ላይ የምናከናውነው የግንባታ ዘዬ ነው pretension ግን በ precast ማምረቻ warehouseኦች ላይ ሚተገበር ነው።

በpost tension ጊዜ መጀመሪያ ብረት እናነጥፋለን(bottom bar) ኮለኖች አካባቢ lower reinforcement እናበጃለን ከዛም ኮለኖች አካባቢ punching shear reinforcement እናበጃለን (drop panel in exceptional case ካልሆነ አንጠቀምም) ከዛም chair bar (“ከበሌቶ”) ካረግን በኋላ strand እንዘረጋለን ከዛም በ side formwork በኩል መወጠሪያ ብረቶቻችንን ካወጣን በኋላ anchorage እና grout vent እንዘረጋለን ከዛም እናጠብቃቸዋለን ከዛም top reinforcement (minimum reinforcement ለ shrinkage እና ለ temperature) ከዛም ኮንክሪት መሙላት ከዛም ያወጣነውን ቴንደን መወጠር ከዛም የተመዘዘውን መጠን መለካት ( measuring elongation) ከዛም የወጡትን የ strand ጫፎች መለካት ከዛም ክፍተቱን (void) በሲሚንቶ (cement screed) መሙላት።

PART 1


YouTube :- https://youtube.com/@Etconp432

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=
👍12❤2🎃1