Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
በሶማሌ ክልል ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ሊገነባ ነው

በሶማሌ ክልል ሊበን ዞን ጉራዳሞሌ ወረዳ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት እንደሚገነባ ተገለጸ።

ፕሮጀክቱ ከ49 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ተጠቁሟል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የፕሮጀክት ኮንትራት ውል ዛሬ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ዮናስ አያሌው ናቸው።

ፕሮጀክቱ ለድርቅ ተጋላጭ በሆነ አካባቢ የሚገነባ በመሆኑ በተቀመጠው የግንባታ ጊዜ ወቅቱን ጠብቆ በጥራት እንዲከናወን ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ዮናስ አያሌው በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ በተገባው ውል መሰረት ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የፕሮጀክቱ ወጪ የሚሸፈነው ከዓለም ባንክ የአንድ ቋት የመጠጥ ውሃ፣ሳኒቴሽንና የሃይጂን (One WaSH) ፕሮግራም ብድር እንደሆነ ተጠቁሟል።

የባለብዙ መንደር የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም ይችላል የተባለው የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ከ49ሺ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

የውል ስምምነቱ አጠቃላይ የሲቪል ግንባታና አሌክትሮሜካኒካል ስራዎችን እንዲሁም የመስመር ዝርጋታን እንደሚያካትት ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@etconp
👌5👍1
የአዲስ_አበባ_ዲዛይንና_ግንባታ_ስራዎች_ቢሮ_#የሚያዝያ_ወር_ዜና_መፅሄት.pdf
6.5 MB
👉የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የሚያዝያ ወር ዜና መፅሄት

🌟በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

Admin @ETCONpADMIN

♡ ㅤ   ❍ㅤ    ⎙ㅤ    ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ

╔═════
    🌐   join 👇
   @ETCONp
   @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆══════
❤5👍3
👉ብርሃን ባንክ ለዋና መሥሪያ ቤቱ ህንጻ ያሸነፈውን ዲዛይን ይፋ አደረገ

🚧ብርሃን ባንክ ለዋና መሥሪያቤቱ ህንፃ ግንባታ ዲዛይን ለማሠራት ባወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ አሸናፊ ሆኖ የተመሰጠውን ዲዛይን ይፋ አደረገ።

✨ባንኩ ባወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ ላይ 16 ኩባንያዎች የተሳተፉ ሲሆን ተሳታፊዎቹ ካቀረቧቸው ዲዛይኖች መካከል አሸናፊ የሆነው ዲዛይን ግንቦት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ምሽት በተካሄደ ፕሮግራም ላይ ይፋ ተደርጓል።

✨በዚህም መሠረት ባንኩ በሰንጋ ተራ አካባቢ በተረከበው 5400 ካሬ ሜትር መሬት ላይ ለሚያስገነባው ህንፃ MAE ኮንሰልቲንግ ኤንድ ኢንጂነርስ በተባለው ድርጅት የቀረበው ዲዛይን አሸናፊ ሆኖ ተመርጧል።

🌟በተመረጠው ዲዛይን መሠረት የሚገነባው የባንኩ ዋና መሥሪያቤት ህንፃ ከ 51 በላይ ወለሎች እንደሚኖሩት ታውቋል።

@etconp
👏7👍5
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በሚያስገነባው አዲስ ስቱዲዮ የመጀመሪያ ንድፍ ስራ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡

የቀድሞው ትምባሆ ሞኖፖል በመባል በሚታወቀው ተቋም ውስጥ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እንደአዲስ ለሚያስገነባው ዘመናዊ ስቱዲዮ መነሻነት በተዘጋጀው የመጀመሪያ መነሻ ንድፍ ከአሰሪ መስሪያቤት፣ከመጨረሻ ተጠቃሚ ተቋም እንዲሁም ዲዛይኑን ካዘጋጀው ድርጅት የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው ባለሞያዎች በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የባለቤትነት ሚናውን በመውሰድ ሊያከናውነው በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ስቱዲዮ ግንባታ የውስጥ ዲዛይኑን ባዘጋጀው ጥበብ ዲዛይን መነሻ ንድፉ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በመድኩ ላይ የመነሻ ንድፉን ሊያዳብሩ የሚችሉ በርካታ ሀሳቦች ከስራ ኃላፊዎቹ እና ከባለሞያዎቹ ቀርቧል፡፡

በመድረኩ ሀሳብ ያነሱት የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም እንዳሉት አዲሱ የሚዲያ ተቋሙ መገኛ በአፍሪካ ሕብረት አቅራቢያ እንደመሆኑ መጠን በርካታ የውጪ ሀገር ዜጎች አይን የሚያርፍበት እንደሆነና የከተማችንን ብቻም ሳይሆን የሀገራችንን ቀለም በሚገባ በሚወክል መልኩ መሰራት እንደሚኖርበት ገልፀው ይህንንም ዕውን ለማድረግ በሀገር ውስጥ ብቻም ሳይሆን ሌሎች አህጉር-ዓቀፍና ዓለም-ዓቀፍ የሚዲያ ተቋማት የተሰሩበትን ሁኔታ መቃኘት ተገቢ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

Via አዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ

@etconp
👍5❤1
Design_of_concrete_structures_by_David_Darwin_Charles_W_Dolan@OmranAbad.pdf
57.2 MB
👉Design Of Concrete

📍This PDF includs

📌 Design of Concrete Structures and Fundamental Assumptions
📌 Flexural Analysis and Design of Beams
📌 Shear and Diagonal Tension in Beams
📌 Short and Slender Columns
📌 Analysis, Idealization, and Preliminarily Design of Reinforced Concrete Beams and Frames
📌 Analysis and Design of One-Way and two-way Slabs
📌 Footings and Foundations
📌 Retaining Walls and Strut-and-Tie Method
📌 Design of Reinforcement at Joints
📌 Concrete Building Systems
📌 Seismic Design

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

@etconp
🙏5👍3❤1
የጠቅላይ ሚንስትሩ የቤተመንግሥት ፕሮጀክት ለሦስት ተቋራጮች ተሰጠ

የ”ጫካ” ፕሮጀክት የሚል ስያሜ ላለው እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርበት ለሚከታተሉት የአዲስ ቤተ መንግስት ግንባታ ተጨማሪ ሶስት ተቋራጮች መቀጠራቸው ተሰምቷል። ከቤተ መንግስት በተጨማሪ ፣ የቅንጡ መኖርያ እና መዝናኛ መንደርን የሚያካትተው ይህ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ፣ የካ ተራራን ታኮ የሚሰራው ፕሮጀክት እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በግዙፍነቱ የሚመዘገብ መሆኑ ሲነገርለት የቆየ ነው።

503 ሄክታር መሬት ላይ በሚያርፈው በዚህ ፕሮክጀክት እስካሁን ድረስ በአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የ29 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገድ እየተሰራ ሲሆን አብዛኛው የመንገድ ስራ ወደ መጠናቀቁ ተቃርቧል።

የ”ጫካ” የሚል ስያሜ ባለው ፕሮጀክት ውስጥ ሶስት ሰው ሰራሽ ሀይቆች የሚኖሩ ሲሆን ፣ እነዚህ ሰው ሰራሽ ሀይቆች ኢ ቶሎ በተባለ ተቋራጭ እየተሰሩ መሆናቸውን መረዳት ችለናል። ከሶስቱ ሀይቆች ውስጥም የአንዱ ሀይቅ የመሰረት ስራ መጠናቀቁን ከምንጮቻችን አረጋግጠናል። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ደግሞ በዚህ ግዙፍ ፕሮጀክት ውስጥ የሚሳተፉ ተጨማሪ ሶስት ተቋራጮች መቀጠራቸውን ዋዜማ ሰምታለች።

መንግስታዊው የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮስኮ) የዋናውን ቤተ መንግስት ግንባታ እንዲያከናውን ውል ተሰጥቶታል። የቻይናው መንግስታዊ የኮንስትራክሽን ኩባንያ ሲሲሲሲ ደግሞ በፕሮጀክቱ የሚካተተውን የቅንጡ ሆቴል ግንባታን ያከናውናል። ሆቴሉም “ስካይ ቪው” የሚል ስያሜ እንደሚኖረው ተነግሯል።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ደግሞ ከቤተ መንግስቱ እስከ የካ አባዶ የሚገነባውን መንገድ በተቋራጭነት ይሰራል። ይህ ግዙፍ ግንባታ በቀጣይ ተጨማሪ ተቋራጮች ይሳተፉበት እንደሁ ማረጋገጥ አልቻልንም።

የ”ጫካ” ፕሮጀክት ወጪ በትክክል ባይታወቅም ፣ 49 ቢሊየን ብር እንደሚያወጣ በስፋት ሲነገር ነበር። ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከወራት በፊት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ፕሮጀክቱ እንደሚባለው የ49 ቢሊየን ብር ብቻ ሳይሆን ከ300 እስከ 400 ቢሊየን ብር የሚያወጣ የ”ስማርት ሲቲ” ልማት አንዱ አካል ነው ሲሉ ማብራሪያ መስጠ ታቸው ይታወሳል።

የምዕራቡ ዓለም የዲፕሎማቲክ ምንጮች በበኩላቸው የጫካ ፕሮጀክት አሁን ባለው የምንዛሪ ተመን ከ850 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጣ መሆኑን እየተናገሩ ነው።

የገንዘቡን ምንጭ በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍንጭ አልሰጡም ። በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርብ ክትትል የሚሰራው ይህ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር የቅደም ተከተል ጥያቄ በተደጋጋሚ ሲነሳበት ቆይቷል።

ለግንባታው በአቅራቢያው የነበሩ ነዋሪዎች እንዲነሱ የተደረጉ ሲሆን ፣ በስፍራው መንግስት የሚያስቀምጠውን የቅንጡ መኖርያዎች ዲዛይንን አሟልተው ግንባታ ማከናወን የሚችሉ ግለሰቦች ብቻ መኖርያ ቤት መስራት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የጫካው ፕሮጀከት ከዚህም ሲያልፍ በሚሰራበት የየካ ተራራ አካባቢ በአቅራቢያ ካለችው እንቁ ልደታ ቤተ ክርስቲያን ጋር የወሰን ይገባኛል ጥያቄ ክርክር ውስጥ ገብቶ ፍርድ ቤት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ፈርዷል።

Via ዋዜማ ሬዲዮ

@etconp
👍20🤮5❤4
የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ህንፃ እና የሲኒማ ኮምፕሌክስ 4B+G+8 ግንባታዎችን ቀሪ ስራዎች ለማከናወን የሚያስችል አዲስ ውለታ የመፈራረም ስነስርዓት ተካሂዷል፡፡

ቀድሞ ግንባታውን ያከናውን የነበረው ስራ ተቋራጭ እቴቴ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶቹ በተለያየ አፈፃፀም ደረጃ ላይ እያሉ አቋርጦ በመውጣቱ ምክንያት ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ መነሻ ሆነው የቆዩት የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃ እንዲሁም የሲኒማ ኮምፕሌክስ ግንባታዎች አዲስ ውለታ የመፈራረም ስነስርዓት ተከናውኗል፡፡

ጉዳያቸው በፍርድቤት በመያዙ እንዲሁም በጨረታ ሂደቶች ምክንያት ለ16 ወራት ገደማ ተቋርጠው የቆዩት እነዚህ ፕሮጀክቶች የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጨረታውን ካሸነፈው ባማኮን ኢንጂነሪንግ ጋር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዛሬው ዕለት ውለታ የማሰር ስነ-ስርዓት አካሂዷል፡፡

የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ህንፃን ከ833 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም የሲኒማ ኮምፕሌክስ ቀሪ ስራዎች ከ954 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ የፕሮጀክት ውል መጠን ጨረታውን ያሸነፈው ባማኮን ኢንጂነሪንግ ስራዎቹን አጠናቆ ለማስረከብ የ6 ወራት ዕድሜ የተሰጠው ሲሆን ከፕሮጀክቱ አንገብጋቢነት አንፃር የሚሰጠው ቅድመ ክፍያ በጥምር ሂሳብ / Joint Account / የሚተዳደር ሆኖ ለግብዓት ግዢ ብቻ የሚውል መሆኑን ከስራ ተቋራጭ ጋር መግባባት ላይ እንደተደረሰና ይህም ወደፊት ሊከሰት ከሚችል የግብዓት ዋጋ ንረት እንደሚታደግ በስነ-ስርዓቱ ላይ ተጠቅሷል::

@etconp
👍10
Forwarded from Ethiopian Construction Vacancy & Tender (Itoophiyaa‍❤️)
👉የንድፍ ውድድር አሸናፊ

💫ብርሃን ባንክ ለዋና መሥሪያቤቱ ህንፃ ግንባታ ዲዛይን ለማሠራት ባወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ አሸናፊ ሆኖ የተመሰጠውን ዲዛይን ይፋ አደረገ።

🚧ባንኩ ባወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ ላይ 16 ኩባንያዎች የተሳተፉ ሲሆን ተሳታፊዎቹ ካቀረቧቸው ዲዛይኖች መካከል አሸናፊ የሆነው ዲዛይን ግንቦት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት በተካሄደ ፕሮግራም ላይ ይፋ ተደርጓል።

🚧በዚህም መሠረት ባንኩ በሰንጋ ተራ አካባቢ በተረከበው 5400 ካሬ ሜትር መሬት ላይ ለሚያስገነባው ህንፃ MAE ኮንሰልቲንግ ኤንድ ኢንጂነርስ በተባለው ድርጅት የቀረበው ዲዛይን አሸናፊ ሆኖ ተመርጧል።

🚧በተመረጠው ዲዛይን መሠረት የሚገነባው የባንኩ ዋና መሥሪያቤት ህንፃ ከ 51 በላይ ወለሎች እንደሚኖሩት ታውቋል።

🚧በዴጃው ኮንሰልቲንግ የተሰራው የህንፃ ዲዛይን ሁለተኛ ደረጃ አሸናፊ ሲሆን ፣ በአዲስ መብራቱ ኮንሰልቲንግ ኤንድ ኢንጂነርስ የቀረበው ዲዛይን ደግሞ ሦስተኛ ወጥቷል።

Via Ethiopian Reporter

@etconp
👍4
👉የንድፍ ውድድር አንደኛ አሸናፊ
ኤም ኤ ኢ አማካሪ ብርሀን ባንክ ያሰናዳውን የንድፍ ውድድር አንደኛ ወጥቶ አሸንፏል፡፡

አማካሪ ድርጅቱ በ2015 እኤአ በመስራቹና በዋና ስራ አሰኪያጁ በህንጻ ነዳፊው በምስክር አግዘው የተመሰረተ ነው፡፡

የውድድር ህንጻው የሚቆምበት መሬት ስፋት 5400 ካሬ ሜትር ሲሆን የውድድር ዳኞቹም

1 አቶ አለበል ደስታ (ህንጻ ነዳፊ)
2 አቶ ጌታቸው ማንደፍሮ (ህንጻ ነዳፊ)
3 አቶ ኪሩብ ገብረየሱስ (ህንጻ ነዳፊ) እንዲሁም
4 አቶ ኬንሞስ ተስፋዬ (የመዋቅር መሀንዲስ) ነበሩ፡፡

በአጠቃላይ 16 ንድፎች ለውድድር መቅረባቸው ታውቋል፡፡

ምስል ምንጭ ብርሀን ባንክ እና በይነ መረብ

@etconp
👍13
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎥Reinforcement steps of concrete columns by injection concrete jacket method in order to increase the bearing capacity

@etconp
❤5
👉የስብሰባ ጥሪ ለአክሱም ዩኒቨርስቲ የ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮችና አማካሪዋች በሙሉ!

📌ተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ይጠይቁ።

+251901297308
+251901297308
+251914744015
+251914292159

@etconp
🙏4❤1