Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉 እዚህ ቻናል ላይ የተወያየንባቸውን ጉዳዮች በጥያቄ መልክ አቅርበናል... መልሶቹን እያንዳንዳቸው በቅርብ ቀን በ ሰፊው እንለቃለን...

✌ምን ያህሉን ይመልሳሉ??

👉መልስዎን በ @COTMp መወያያ Group ፃፉልን

1. Roller Compacted Concrete (RCC) ከኖርማሉ ኮንክሪት
በምን ይለያል?
.
2. Bending Moment ቢም ላይ ትልቅ ተፅእኖ የሚኖረው ምን
axis ላይ ነው? (x? y? ወይስ z? )
.
3. Centroid, Center of mass እና Center of gravity
ልዩነታቸው ምንድነው? አንድ ነጥብ ላይስ ሊያርፉ ይችላሉ?
.
4. Elastic እና Inelastic ማቴሪያሎች ልዩነታቸው ምንድነው?
Ductility ምንድነው?
.
5. Toughness ምንድነው?
.
6. Second Moment of Inertia ( Second moment of
Area) ምንድነው? ቢም ላይ የሚኖረው ተፅዕኖስ?
.
7. Mass moment of inertia እና Second Moment of
Inertia ልዩነታቸው ምንድነው?
.
8. Shear Force Diagram ምንድነው? Concentrated load
ሲሆን Constant, Linear ነው ወይስ Parabolic ቅርፅ
የሚኖረው? Distributed ሲሆንስ?
.
9. Bending Moment Diagram ምንድነው? Concentrated
load ሲሆን Constant, Linear ነው ወይስ Parabolic ቅርፅ
የሚኖረው? Distributed ሲሆንስ?
.
10. SFD ከፖዘቲቭ ወደ ኔጌቲቭ የሚቀየርበት ነጥብ ላይ
Moment Maximum ነው ወይስ Minimum ?ከኔጌቲቭ ወደ
ፖዘቲቭ የሚቀየርበት ነጥብ ላይስ?

11. አንድ ህንፃ እኛ ዲዛይን ካደረግንበት ባነሰና በጣም ትንሽዬ በሆነ ሎድ ሊፈርስ ይችላል?? እንዴት??

12. Creep እና Fatigue
ምንድናቸው??

t.me/COTMp
👍17❤1👌1
የድሬዳዋ የሠራዊት የጋራ መኖሪያ ቤት አፓርትመንት ህንጻ ግንባታ አጠናቆ ለማስረከብ ማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ ደርሷል
****
የ
መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የግንባታ ልምዱን ተጠቅሞ ከትርፍ ይልቅ
ለግንባታ ጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአነስተኛ ወጪ የግንባታ ሂደቱን ማጠናቀቅ የሚችል ድርጅት ነው፡፡

ድርጅቱ ከያዛቸው የግንባታ ሥራዎች መካከል በድሬዳዋ ከተማ በሰባተኛ አየር ኃይል ካምፕ ውስጥ እየገነባ ያለው የሠራዊት የጋራ መኖሪያ አፓርትመንት
ህንጻ ግንባታ አጠናቆ ለተጠቃሚዎች ለማስረከብ የማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡

የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር እንዳልካቸው ታዬ እንደገለጹት፣ የድሬዳዋ የሠራዊት የጋራ መኖሪያ ቤት የአፓርትመንት ህንጻ ግንባታ በአንድ ምዕራፍ የሚገነባ ነው፡፡

20 ብሎኮችን የያዘው የጋራ መኖሪያ ቤት ባለ አንድ መኝታ አምስት ብሎኮች በአጠቃላይ 200 አባዎራዎችን ይይዛል፡፡

ባለሁለት መኝታ ስምንት ብሎኮች 288 አባወራዎችን ይይዛል፡፡ ባለ ሶስት መኝታ ሰባት ብሎኮቹ ደግሞ 280 አባዎራዎችን እንዲይዝ ተደርጎ የተገነባ ሲሆን በአጠቃላይ 768 አባዎራዎችን የሚይዝ ሲሆን ሁሉም ብሎኮች ባለ
አራት ወለል ናቸው፡፡

ከመኖሪያ ቤቶቹ በተጨማሪ ለማህበራዊ አገልግሎት የሚውሉ የጋራ መጠቀሚያ ቤቶች የተገነቡለት ሲሆን አፓርታማዎቹ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ሥራ እየተሰራላቸው ነው፡፡

ሁሉም ብሎኮች ግባታቸው ማጠቃለያ ላይ ያሉ ሲሆን ቀሪው የፊኒሽንግ ሥራዎችን በመሰራት ላይ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ግንባታ በከፍተኛ ትኩረትና ፍጥነት በመከናወን ላይ በመሆኑም በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታቸው ይጠናቀቃል ሲሉ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር እንዳልካቸው ታዬ ገልጸዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ባለቤት በመከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ሲሆን ዲዛይንና ቁጥጥሩን የሚያከናውነው ደግሞ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
ነው፡፡

የድሬዳዋ የሠራዊት የጋራ መኖሪያ ቤት በአፓርትመንት ህንጻ ግንባታ 300 ለሚደርሱ ዜጎች በቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድል ፈጥሯል፡፡

@etconp
👍7❤1
የአርክቴክቸር ተማሪዎች የጥበብ ሥራዎቻቸውን ለኤግዚቪሽን አቀረቡ

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመሬት አስተዳደር ኢንስቲትዩት ስር የሚገኘው የአርክቴክቸር ትምህርት ክፍል የ5ኛ ዓመት ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲውን 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ የአርክቴክቸር ፕሮጀክቶችንና የጥበብ ስራዎቻቸውን ከግንቦት 03 እስከ 05/09/2015 ዓ.ም ድረስ ለእይታ የሚቆይ ኤግዚቪሽን በግሽ ዓባይ ግቢ ተከፍቷል፡፡

ኤግዚቪሽኑ በይፋ መከፈቱን ያበሰሩት የግቢው ማኔጅግ ዳይሬክተር አቶ ፈለገህይወት ዘገየ እና የመሬት አስተዳደር ኢንስቲትዩት ም/ዲን አቶ ፀጋዬ ካሳይ ናቸው፡፡

አቶ ፀጋዬ ካሳ ትምህርት ክፍሉ በ2004 ዓ.ም የተቋቋመና ለሃገሪቱ በሙያው የበለፀጉ ሙያተኞችን በማፍራት ጉልህ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ የሚገኝ ትምህርት ክፍል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ም/ዲኑ በማስከተል ዩኒቨርሲቲው 60ኛ ዓመቱን በማክበር ላይ እያለ ይህን ምክንያት በማድረግ ከሌሎች ግቢዎች በግንባር ቀደምትነት የኤግዚቪሽን ፕሮግራሙ መዘጋጀቱ ይበል የሚያሰኝ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኤግዚቪሽኑ ግንቦት 5/2015 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ሲሆን የመዝጊያ መርሃ ግብሩ በጥበብ ህንፃ ለእይታ እንደሚቀርብ አስገንዝበው የጥበብ ባለቤቶች እንዲበረታቱ አሳስበዋል፡፡

የትምህርት ክፍሉ መምህርና ሰዓሊ አቶ እያዩ ገነት ጥሪውን አክብረው ለመጡት ተመልካቾች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው ለኤግዚቪሽኑ መሳካት ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከቱትን አመስግነው ኪነ ጥበብ ወይም ኪነ ህንፃ የምንኖርበት ዓለም ማለት መሆኑንና የጥበብ ስራ እንደ ቃላት ሁሉ የሚናገር፣ መልዕክት የሚያስተላልፍና ስሜትን የሚያነቃቃ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በኤግዚቪሽኑ ጉብኝት የ5ኛ ዓመት ተመራቂ ተማሪ የሆኑት ተማሪ አማኑኤል ደምስ፣ ጺዮን ፍቅሩ እና ሌሎችም ለተመልካቹ ገለፃ በማድረግ የጥበብ ስራዎቻቸውን ለተመልካች አስጎብኝተዋል፡፡

@etconp
👍9❤6🎃2
👉Purpose of chicken mesh

🚧To prevent crack in plastering work we use chicken mesh at junction of different material such as between wall and column  junction where coefficient of thermal expansion of different material is different and due to that chances of crack after plastering is bound to occur that’s why we use chicken mesh

@etconp
👍11❤6
👉የኮንስትራክሽን ውል አደጋዎች ‼️

🚧የኮንስትራክሽን ኮንትራትን መንደፍ ወይም ማርቀቅ በየደቂቃዎች ውስጥ
ከመፈራረም አንድ ሚሊየን ዕጥፍ አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ከኮንትራት ውል ውስጥ በስህተት የገባ ሀረግ ወይም ሳይፃፍ የቀረ አንድ አንቀጽ ወደ ፍርድ ቤት የሚያመላልስ ከፍተኛ ጦስ ሊያስከትል ስለሚችል ነው፡፡ የኮንስትራክሽን ኮንትራትን መንደፍ ወይም ማርቀቅ፣ አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ባለመዘንጋት በተወሰነ ደረጃ ረቂቅ ከመዘጋጀቱ በፊት የሥራውን ሂደት በጀቱን እና ኘላኑን በተመለከተ ፕሮጀክቱን እንዲያካሂድ ከተመረጠው ኮንትራከተር ጋር መወያየት ጠቀሜታ ቢኖረውም፣ አንድ አስገንቢ የኮንትራት ውል ሲያረቅ የሚከተሉትን አምሰት ዋና ነጥቦች ማስወገድ እንደሚኖርበት የዘርፉ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

🚧ለህግ አስቸጋሪ የሆኑ ቴክኒካል ዝርዝሮች በረቂቅ ውስጥ በህግ አግባብ ለመፍታት አስቸጋሪ የሆኑ፣ በመደበኛ የህግ አንቀጽ ውስጥ ያልተካተቱ ቴክኒካል ዝርዝሮችን በውሉ ላይ ማካተት በቀጣይ
ችግር ቢከሰት እንኳ ለመፍታት በጣም አስቸጋሪ ስለሚሆኑ ማስወገድ አስፈላጊ ነው፡፡ ምከንያቱም አንዳንድ ቴክኒካል አሠራሮች እና ቃላቶች ለህግ ባለሞያዎች አስቸጋሪ በመሆናቸው ነው፡፡ ስለዚህ በኮንትራክተሮች በቀላሉ የሚታወቁ እና የዘርፉ ባለሙያዎች በህግ ፊት ቀርበው ሊመሰክሯቸው የሚችሏቸውን ቴክኒካዊ ቃላት በውሉ ማካተት አይገባም፡፡

🚧ረጃጅም አረፍተ ነገሮች ዋናውን ነጥብ በቀጥታ ከመጥቀስ ባለፈ፣ ዝርዝር ሀተታ ማስቀመጥ ረጃጅም አረፍተ ነገር መፃፍ አላስፈላጊ አይደለም::

🚧ተደጋጋሚ ቃላትና አረፍተ ነገር መጠቀም ቀደም ብሎ የሠፈሩ ቃላት እና አረፈተ ነገሮችን ልዩ አንቀጽ እየደጋገሙ ማስፈር አያስፈልግም፡፡
አስፈላጊ ከሆነ የሠፈረበትን አንቀጽ መጥቀስ ብቻ በቂ ነው፡፡

📌የዲዛይን ለውጥን በቃል መፈጸም

🚧ማንኛውም የዲዛይን ወይም የአሠራር ለውጥ ሲደረግ በቃል ሥምምነት ብቻ እንዲፈጸም ማድረግ ችግር ቢፈጠር በህግ አግባብ ለመፍታት እንዳይቻል የሚያደርግ እንቅፋት ስለሚፈጥር ማንኛውንም የዲዛይን እና የለውጥ
ስምምነቶች በጽሑፍ መሥፈርት እና የእያንዳንዱ አባል ፊርማ፣ አሻራ ባረፈበት የህግ አግባብ መፈጸም ይገባል፡፡

🚧ሊለወጥ የማይችል ቋሚ ውል አለመፈራም በሥራ ሂደት በጊዜ ሁኔታ ሊፈጠር የሚችለውን ነገር ቀደም ብሎ መረዳት አስቸጋሪ በሚሆንባቸው የሥራ ዘርፎች አንዱ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ነው፡፡
ስለዚህ የኮንትራት ውል ሲረቀቅ እና ሲፈረም ውሉ እንደአስፈላጊነቱ የሚለወጥበት እና የሚታደስበትን የህግ አንቀፅ በውሉ ላይ ማስፈር ተገቢ ነው፡:

#ConstructionLaw

@etconp
👍13❤1
👉Normal Concrete

▶️The concrete in which common ingredients i.e. aggregate, water, cement are used is known as normal concrete. It is also called normal weight concrete or normal strength concrete.

▶️It has a setting time of 30 - 90 minutes depending upon moisture in atmosphere, fineness of cement etc.

▶️The development of the strength starts after 7 days the common strength values is 10 MPa (1450 psi) to 40 MPa (5800 psi). At about 28 days 75 - 80% of the total strength is attained.

⏺Almost at 90 days 95% of the strength is achieved.

▶️Properties of Normal Concrete Its slump varies from 1 - 4 inches.

▶️Density ranges from 140 pcf to 175 pcf.

⏺It is strong in compression and weak in tension.

⏺Air content 1 - 2 %.

✨Normal concrete is not durable against severe conditions e.g. freezing and thawing.

@etconp
👍14
📜ሀሳብ ልስጥበት

ይህ የከተማችን ውዱ መንገድ ነው። በወሎ ሰፈርና በሩዋንዳ መካከል ይገኛል።

በአካባቢው ከሚካሄድ ግንባታ ጋር በተያያዘ መንገዱ በዚህ መልክ ጨቅይቶ ተበላሽቷል።

እነዚህ ዝርክርክ ነገሮች የመንገድን ዕድሜ በማሳጠር ዋነኛ ተጠቃሽ ናቸው።

ቻይናዎች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያህል ግዙፍ ሕንፃ ሲገነቡ አካባቢውን በቆሻሻ እና አፈር ሲያውኩና ሲያወድሙ አልታዩም።

የቻይና ተቋራጮች ፕሮጀክቶች አካባቢን ሳይበክሉና ሳያራቁቱ ግንባታን ማካሄድ እንደሚቻል ጉልህ ምስክሮች ናቸው።

ወደ እኛ አገር ስንመለስ ፕሮጀክቶች ሲካሄዱ መንገድን በሰፊው ካላዘጉ፣ የሰውን ጆሮ ካላደነቆሩ፣ የውኃና የኤሌክትሪክ መሥመር ቆራርጠው ካልጣሉ የሚካሄድ የማይመስላቸው ተቋራጮች ብዙ ናቸው።

አካባቢን ሳይበክሉ ግንባታን የሚያካሂዱ ተቋራጮች መመስገንና ዕውቅና ሊሰጣቸው እንደሚገባው ሁሉ፣ አካባቢን የሚበክሉ በአርማታና በአፈር መንገድን ከጥቅም ውጪ የሚያደርጉ ሊቀጡና ሃይ ሊባሉ ይገባል።

Via Abraham Tolosa

@etconp
👍25❤1
የጎንደር አዘዞ የአስፓልት መንገድ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዶ አራት ዓመታትን በማስቆጠሩ ነዋሪዎች ለችግር እንዳጋለጣቸው ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ።

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፤ የጎንደር አዘዞ የአስፓልት መንገድ 12.6 ኪ.ሜ ርዝማኔ ያለው ሲሆን፣ ራማ መንገድ ሥራዎች ተረክቦ በ2011 ወደ ሥራ ገብቶ በነሃሴ ወር 2012 ይጠናቀቃል ቢባልም እስከ አሁን ድረስ ባለመጠናቀቁ ለከተማዋ አንገብጋቢ ጉዳይ እንደሆነና ሕዝቡን እንዳስቆጣ ተናግረዋል።

በፌደራል መንግሥት በጀት እየተሰራ ያለው ይህ መንገድ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተለያዩ ወቅቶች ወደ ጎንደር ከተማ ሲያቀኑ ሥራው ቶሎ ባለመጠናቀቁ ጥያቄ እንዳያስነሳ በማሰብ የግንባታ መሳሪያዎችን አስፓልት ዳር አውጥቶ ያልሰሩትን እየሰሩ በማስመሰል እንዲታይላቸው እያደረጉ መሆናቸውን ነው የከተማዋ ነዋሪዎች የገለጹት።

<<ትልልቅ ባለስልጣናት ወደ ከተማዋ ሲገቡ ተቋርጦ የነበረው የመንገድ ሥራ በአንዳንድ አካባቢዎች ይጀመርና መልሰው ሥራውን ያቆሙታል።>> የሚሉት ነዋሪዎቹ፤ <<ይህ ድርጊታቸው የጎንደርን ሕዝብ እንደመናቅ ይቆጠራል>> ሲሉም አክለዋል።

ይህ የአስፓልት መንገድ በፊት የነበረውን የአስፓልት መንገድ በተሻለ ጥራት ለመስራት በ2011 የተጀመረ ሲሆን፤ በመንገዱ ሥራ ምክንያት ቤታቸው የፈረሰባቸው፣ ካፌና ሬስቶራንታቸው እንዲሁም የቴሌና የውሃ ሙሉ አገልግሎት የማያገኙ የማሀብረሰብ ክፍሎች አሉ፡፡

ነገር ግን መንገዱ በአጭር ጊዜ እንደሚያልቅ ተስፋ ሰንቀው ሲጠባበቁ የነበሩ ነዋሪዎቹ ተስፋቸው ጨልሞ ችግር ላይ እንደወደቁ ነግረውናል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በፌደራል መንግሥት በጀት ከጎንደር አዘዞ እየተገነባ ያለውን የአስፓልት መንገድ በፍጥንት እንዲጠናቀቅ ማሳሰባቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር አካባቢ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ቡድን መሪ ኢንጅነር ዳንኤል ንጉሴ የመንገድ ሥራውን እስከ ሰኔ 30 እናጠናቅቃለን ቢሉም በማህበረሰቡ ዘንድ እንደማይጠናቀቅ በመታወቁ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱን ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

አዲስ ማለዳ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ የሆኑትን ባዮህ አቡሃይን እና የራማ መንገድ ሥራዎችን ለማነጋገር ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም።

@etconp
👍9🤣4💔1
👉ታሪካዊ ህንጻ

🌟ቁልቢ ገብርኤል ቤተክርስትያን፡፡

📍ቁልቢ ገብርኤል ቤተክርስትያን በጣልያናዊው ቪቶርዮ ስፒኔሊ የተገነባ ሲሆን ለማየት ቢያስቸግርም ገንቢው በምስሉ ላይ በጉልላቱ ላይ ቆሞ እየሰራ ይታያል፡፡

💫በተጨማሪም ቪቶርዮ ለመጨረሻ ግዜ በስራው ቦታ ላይ የተነሳውን ምስልም ተያይዟል፡፡

📸ምስል ምንጭ ኤርነስቶ ስፒኔሊ

@etconp
❤10👍7
Forwarded from Ethiopian Construction Vacancy & Tender (Itoophiyaa‍❤️)
EXTERNAL V- ACANCY.pdf
161.8 KB
#NEW

👉External Vacancy

🌟ማሳሰቢያ፡- የሥራ ልምድ ከተጠየቀው ትምህርት ደረጃ በኋላ የተገኘ ብቻ ይሆናል፡፡

✨አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ ማለት በተጠቀሰው የሙያ መስመር አገልግሎት ሲሆን፣ የሚቀርበው የሥራ ልምድ ማስረጃ የስራ ግብር የተከፈለበት፣ ደመወዝና አገልግሎት ከመቼ እስከ መቼ እንደተሰጠ የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡

👩‍⚕ሴት አመልካቾች ይበረታታለ

💫አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ የትምህርትና ሥራ ልምድ ማስረጃዎችን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የሰው ኃይል ቅጥር እና መረጃ አያያዝ ቡድን ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችለ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

📍አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ህንፃ ወይም ከበሻሌ ሆቴል ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ፣

☎️ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር

0116676385 / 0118698910

@ETCONpWORK
👍13❤1
👉ኮንስትራክሽን

🚧አስገዳጁ ረቂቅ አዋጅ . . .

🌟የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ፤ ትላልቅ ተቋራጮች ከአነስተኛ የግንባታ ተቋራጮች ጋር በጥምረት እንዲሠሩ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

ረቂቁ በሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ቀርቦ እንደሚገመገም ተገልጿል።

ረቂቁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ ሲደረግ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማረም በአገሪቱ የሚገኙ ትላልቅና ዋና ዋና ተቋራጮች ከአነስተኛ ትናንሽ ተቋራጮች በጥምረት እንዲሠሩ ዕድሉን የሚፈጥር ነው ተብሏል።

ረቂቅ ህጉን በአስገዳጅነት እንዲዘጋጅ የተደረገው አነስተኛ አቅም ያላቸው ተቋራጮች ሰፊ ልምድና አቅም ካላቸው ተቋራጮች ጋር በመሥራት ልምድ እንዲያገኙና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ በማሰብ ነው ተብሏል።

አነስተኛ ደረጃ ያላቸው ተቋራጮች ያልተገባ ተግባር ሲፈጽሙ ተጠያቂ እንዲሆኑ እና ክፍያ ላይም ምንም ዓይነት ችግር እንዳይገጥማቸው የሚያስችል ሕግ መሆኑ ተገልጿል።

አዋጁን በማርቀቅ ሂደት ፦
- የሕንፃ አማካሪ ድርጅቶች፤
- የሕንፃ ተቋራጭ ማህበራት፤
- በአገሪቱ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች፤
- ፕሮጀክት ያላቸው አካላት፤
- የገንዘብ ሚኒስቴር፤
- የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
- በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚሠሩ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እንደተሳተፉበት ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ፤ አነስተኛ ደረጃ ያላቸው የግንባታ ተቋራጮች እራሳቸውን ብቁ አድርገው መንግሥት በሚያሰማራቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ድርሻ ይዘው ለመሥራት ከወዲሁ ዝግጅት ያድርጉ ብሏል።

Via EPA

@etconp
👍9❤2👌1
👉ማስታወቂያ

✨ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም

🌟የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በአለም አቀፍ የሀገር ውስጥ ጨረታ (ICB) የሀገር በቀል የኮንስትራክሽን
ኩባንያዎችን የገበያ ድርሻ የሚያሳይ መረጃ ለማደራጀትና የቀጣይ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የሚስችሉ መረጃዎችን በማደራጀት ላይ ይገኛል፡፡

🌟የሀገርበቀል አለም አቀፍ ተጫራቾች መረጃ በተደራጀ መልኩ á‰°áˆ˜á‹áŒá‰ á‹ መደራጀታቸው በቀጣይ እንደሀገር ለሚኖረው እንቅስቃሴ á‹áŒ¤á‰łáˆ› ሾል ለመስራት የሚያስችል በመሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ባለድርሻዎች መረጃዎቻቸውን እንዲያስመዘግቡ ይጠይቃል፡፡

💫1. በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ፕሮጀክቶቻቸው የታየ ወይም እየታየ ያሉ ኩባንያዎች

💫2. በዓለም ዓቀፍ የሀገር ውስጥ ጨረታ (ICB) የተወዳደሩ ወይም ያሸነፉ ኩባንያዎች

💫3. በአህጉር ደረጃ በሚወጣ ጨረታ (ICB) እና ተያያዥ ውሎች ላይ የተሳተፉ የሀገር በቀል የኮንስትራክሽን
ኩባንያዎች በሙሉ

📍አዋሬ አደባባይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋናው መስሪያ ቤት 6ኛ ፎቅ ሀገር አቀፍ የኮንስትራክሽን መረጃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ እንድታስመዘግቡ እናሳውቃለን፡፡

☎️ለበለጠ መረጃ á‰  0911409508 ይደውሉ።

@etconp
👍5
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ የሲሚንቶ áŠĽáŒĽáˆ¨á‰ľ ከፍተኛ ችግር መሆኑ ተነገረ

ለመጀመሪያ ጊዜ 26 የአለም ሀገራት የሚሳተፉበት የኮንስትራክሽን አውደርእይ ሊካሄድ ነው

ይሄ የተባለው በዛሬው እለት የከተማ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ጫልቱ ሳኒ የኮንስትራክሽን አውደርእይ በተመለክተ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ።በመገለጫቸው የኮንስትራክሽን ዘርፉ 19 በመቶ ያህል በኢኮኖሚ  እድገት ላይ áŠ áˆľá‰°á‹‹áŒ˝áŠŚ እንደሚያበረክት ጠቅሰው ሆኖም የተለያዩ የግብአት ችግሮች በተለይ የሲሚንቶ እጥረት  ለዘርፉ ማነቆ መሆኑን መግለፃቸው ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

ይህንን እና መሰል ችግሮችን ይቀርፋል የተባለለት ቢግ 5 ኮንስትራክሽን ሲምፖዚየም እና የንግድ ትርኢትን መዘጋጀቱን ሚኒስትሯ ገልፀዋል። á‹­áˆ…ም የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ DG ኢቨንትስ እና ከሀገር አቀፉ አጋር ኢትኤል ኢቨንት እንዲሁም የሲምፖሲየሙ ስትራቴጂክ አጋር ከሆነው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ በመሆን ከግንቦት 10 እስከ 12 ቀን 2015 በሚሊኒዬም አዳራሽ  በጋራ እንደሚያካሂዱት አንስተዋል።

ይሄ ለመጀመሪያ ጊዜ  የሚካሄደው ሲምፖዚየም 26 የአለም ሃገራት ብሎም  116 አለም አቀፍ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ሲሆን 6000 ተሳታፊዎች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የግንባታው ዘርፍ ማነቆ የሆነውን ከአቅም ውስንነት ጋር የሚያያዙ ችግሮችን በቴክኖሎጂ ሽግግር ያለው ክፍተት የሚፈታበት ይሆናል ሲሉ አክለዋል።

ይህ ኮንስትራክሽን ዘርፉ ማነቆ የሆነበትን የግብአት  እጥረት በተለይ የሲሚኒቶ እጥረት ዙሪያ
አለም የደረሰበትን  የአመራረት ሂደት በዘርፉ ከተሰማሩት ልምድ እንዲወስዱ እድል ይሰጣል።

በመርሃ ግብሩ አምራች ተመራማሪዎች ፣ገዢና አቅራቢዎች ፣ከቱሪዝም ብሎም ከተማን ከማነቃቃት አኳያ እንዲሁም የኢትዮጲያን የገጽታ ግንባታ የምናሳይበት ነው ሲሉ ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል።

Via ቤተልሄም እሸቱ

@etconp
👍13❤2
📌የ ምስራች ዜና ለ ኮንስትራክሽን ተቋራጮች በ ሙሉ

🏗በ ኮንስትራክሽን ዘርፍ በ ተቋራጭነት፣በ ኢንተርየር ዲዛይን፣በ ሰብ ኮንትራክት፣በ ብረታ ብረት፣በ እንጨት ስራ እና የ ህንፃ ግንባታ ተያያዥ ስራዎች ያላቹ በ ሙሉ

🗞አዳዲስ ጨረታዎች ሲወጡ፣ ዕለታዊ የማተርያል ማሽነሪ Cost ለማወቅ በቀላሉ በ Private ቴሌግራም ቻናል እና በ ኢመይል አድራሻቹ አመቱን ሙሉ በ ማይታመን ዋጋ áŠĽáŠ•á‹˛á‹°áˆ­áˆłá‰š ለምትፈልጉ ከታች ባሉት አደራሻዎች አናግሩን።

🚧ለመመዝገብ @Philemona7 ወይም @etconpworks ያናግሩን።

☎️ለ በለጠ መረጃ በ +251925446661 ወይም 0707444849 ይደውሉ

🙏እናመሰግናለን🙏

@etconp
🙏9👍3
👉ብዙ የኮንስትራክሽን ባለሞያዎች መሰንጠቅ በ Mix design ትክክል አለመሆን ብቻ የሚመጣ ይመስላቸዋል ነገር ግን ለመሰንጠቅ (cracking ) ምክንያት የሚሆኑ መንስኤዎችን ከዚህ በታች እንዲህ ዳስሰናል :-

[1] - አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ
.
አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ መሰንጠቅ (cracking ) ይፈጠራል ስለዚህ የምንጠቀማቸውን ለኮንክሪት ግብዓት የሚሆኑ ቁሶችን (ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ኮረኮንች) ጥራት መፈተሽ አለብን ኮንክሪቱ የብረት መዋቅር (reinforcement ) ያለው ከሆነ የብረቱን ጥራት መገምገም አለብን።
.
[2] - መኮማተር (Shrinkage )
.
ኮንክሪቱን በምንደባልቅበት እና ውሃ በምናጠጣበት ግዜ (Curing ) ተገቢውን ጥንቃቄ ካልወሰድን መኮማተር (shrinkage) መሰንጠቅን(cracking)   ያስከትላል ።
መኮማተር (shrinkage) ለትልቅ የኮንክሪት ጥንካሬ በጣም አስፈላጊ ነው አስፈላጊውን የውሃ-ሲሚንቶ መመዛዘን (water cement ratio) ካልተጠቀምን በመኮማተር አማካኝነት መሰንጠቅ ሊፈጠር ይችላል ።
.
[3] - ጥራት ያለው Aggregate የማንጠቀም ከሆነ
.
Aggregate የኮንክሪትን አጠቃላይ ጥንካሬ ይወስንልናል ጥራቱ ጥሩ ያልሆነ Aggregate የምንጠቀም ከሆነ ከሲሚንቶ ጋር ተፈላጊውን ጥምረት (bond) ስለማይፈጥር ግንባታችን ሊሰነጠቅ ይችላል።
.
[4] - መዋቅራችን ከአቅም በላይ የሆነ ክብደት ሲያስተናግድ
.
ግንባታው / መዋቅሩ ተገቢውን ጥንካሬ ሳያገኝ በፊት ለትልቅ ክብደት የሚጋለጥ ከሆነ መሰንጠቅ ይከሰታል። በተጨማሪም መቀሰቻዎችን እና ቅስቱን (formwork ) ያለጊዜው የሚነሳ ከሆነም ግንባታችንን ለስንጣቆ ያጋልጠዋል።

.
[5] - በትክክል ውሃ እንዲጠጣ የማይደረግ ከሆነ (improper curing )
.
ይህ በአገራችን ከሚስተዋሉ ለመሰንጠቅ ከሚዳርጉ ምክንያቶች ቀዳሚው ነው - ውሃ በትክክል አለማጠጣት።
ኮንክሪት እንደተገነባ በተገቢው ጊዜ እና መጠን ውሃ መጠጣት አለበት ።
«ወንድና ሲሚንቶ ካልጠጣ ይሰነጠቃል» አይደል ሚሉት ሰካራም ወንዶች😁
.
[6] - የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) አለመመጣጠን
.
በጣም ትልቅ የሆነ የብረት መዋቅርን Mix ratioው ትንሽ በሆነ ኮንክሪት የሙሌት ስራ ስንሰራ በብረቱ እና በኮንክሪቱ መካከል ያለ የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) non linear ይሆናል ይህ ደግሞ መሰንጠቅን ያስከትላል።
.
[7] - በሳይት ላይ የሙሌት (casting ) ስራ ሲሰራ ተገቢ ጥንቃቄ ካልተደረገ እና ለስራው ተገቢ የሆነ ባለሞያ (የቀን ሰራተኛን ጨምሮ) ካልተመደበ መሰንጠቅ (cracking) በሚሰራው ኮንክሪት ላይ መፈጠሩ አይቀርም።

@etconp
👍11❤7🙏3👌3🐳1
ዛሬ ዘለግ ያለ ፅሁፍ ይዘን መጥተናል

ETCONp አርኣያ ሰብ

በገበታ ለሀገር ከእየተገነቡ ካሉ የተለያዩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የሚገኝበት የኮንታ ዞን በተፈጥሮ ሀብቶች የታደለው ነው።

ኮንታ ግን በተፈጥሮ ሀብት ብቻ ሳይሆን በሙያቸው የተካኑ አርክቴክቶችም አግኝቷል።

በ እነዚህ አርክቴክቶች ዲዛይን የተደረገው እና በቅርቡ ተመርቆ ይፋ የተደረገው የሃላላ ኬላ ሪዞርት በርካቶችን አስደምሟል።

በደቡብ ምዕራብ ክልል፣ በኮንታ ዞን የኮይሻ ፕሮጀክት ይገኛል። ታድያ ከዚህ ፕሮጀክት ጀርባ እነማን አሉ? ቢቢሲ ከእነዚህ መካከል ወጣቱን አርክቴክት ኃይሌ ታደሰን አግኝቷል።

በቅድሚያ ግን ስለ ኮይሻ ፕሮጀክት ጥቂት ነገር እንበል።

Via BBC Amharic

@etconp
👍8❤2