Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
📜ሀሳብ ልስጥበት

ይህ የከተማችን ውዱ መንገድ ነው። በወሎ ሰፈርና በሩዋንዳ መካከል ይገኛል።

በአካባቢው ከሚካሄድ ግንባታ ጋር በተያያዘ መንገዱ በዚህ መልክ ጨቅይቶ ተበላሽቷል።

እነዚህ ዝርክርክ ነገሮች የመንገድን ዕድሜ በማሳጠር ዋነኛ ተጠቃሽ ናቸው።

ቻይናዎች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያህል ግዙፍ ሕንፃ ሲገነቡ አካባቢውን በቆሻሻ እና አፈር ሲያውኩና ሲያወድሙ አልታዩም።

የቻይና ተቋራጮች ፕሮጀክቶች አካባቢን ሳይበክሉና ሳያራቁቱ ግንባታን ማካሄድ እንደሚቻል ጉልህ ምስክሮች ናቸው።

ወደ እኛ አገር ስንመለስ ፕሮጀክቶች ሲካሄዱ መንገድን በሰፊው ካላዘጉ፣ የሰውን ጆሮ ካላደነቆሩ፣ የውኃና የኤሌክትሪክ መሥመር ቆራርጠው ካልጣሉ የሚካሄድ የማይመስላቸው ተቋራጮች ብዙ ናቸው።

አካባቢን ሳይበክሉ ግንባታን የሚያካሂዱ ተቋራጮች መመስገንና ዕውቅና ሊሰጣቸው እንደሚገባው ሁሉ፣ አካባቢን የሚበክሉ በአርማታና በአፈር መንገድን ከጥቅም ውጪ የሚያደርጉ ሊቀጡና ሃይ ሊባሉ ይገባል።

Via Abraham Tolosa

@etconp
👍25❤1
የጎንደር አዘዞ የአስፓልት መንገድ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዶ አራት ዓመታትን በማስቆጠሩ ነዋሪዎች ለችግር እንዳጋለጣቸው ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ።

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፤ የጎንደር አዘዞ የአስፓልት መንገድ 12.6 ኪ.ሜ ርዝማኔ ያለው ሲሆን፣ ራማ መንገድ ሥራዎች ተረክቦ በ2011 ወደ ሥራ ገብቶ በነሃሴ ወር 2012 ይጠናቀቃል ቢባልም እስከ አሁን ድረስ ባለመጠናቀቁ ለከተማዋ አንገብጋቢ ጉዳይ እንደሆነና ሕዝቡን እንዳስቆጣ ተናግረዋል።

በፌደራል መንግሥት በጀት እየተሰራ ያለው ይህ መንገድ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተለያዩ ወቅቶች ወደ ጎንደር ከተማ ሲያቀኑ ሥራው ቶሎ ባለመጠናቀቁ ጥያቄ እንዳያስነሳ በማሰብ የግንባታ መሳሪያዎችን አስፓልት ዳር አውጥቶ ያልሰሩትን እየሰሩ በማስመሰል እንዲታይላቸው እያደረጉ መሆናቸውን ነው የከተማዋ ነዋሪዎች የገለጹት።

<<ትልልቅ ባለስልጣናት ወደ ከተማዋ ሲገቡ ተቋርጦ የነበረው የመንገድ ሥራ በአንዳንድ አካባቢዎች ይጀመርና መልሰው ሥራውን ያቆሙታል።>> የሚሉት ነዋሪዎቹ፤ <<ይህ ድርጊታቸው የጎንደርን ሕዝብ እንደመናቅ ይቆጠራል>> ሲሉም አክለዋል።

ይህ የአስፓልት መንገድ በፊት የነበረውን የአስፓልት መንገድ በተሻለ ጥራት ለመስራት በ2011 የተጀመረ ሲሆን፤ በመንገዱ ሥራ ምክንያት ቤታቸው የፈረሰባቸው፣ ካፌና ሬስቶራንታቸው እንዲሁም የቴሌና የውሃ ሙሉ አገልግሎት የማያገኙ የማሀብረሰብ ክፍሎች አሉ፡፡

ነገር ግን መንገዱ በአጭር ጊዜ እንደሚያልቅ ተስፋ ሰንቀው ሲጠባበቁ የነበሩ ነዋሪዎቹ ተስፋቸው ጨልሞ ችግር ላይ እንደወደቁ ነግረውናል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በፌደራል መንግሥት በጀት ከጎንደር አዘዞ እየተገነባ ያለውን የአስፓልት መንገድ በፍጥንት እንዲጠናቀቅ ማሳሰባቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር አካባቢ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ቡድን መሪ ኢንጅነር ዳንኤል ንጉሴ የመንገድ ሥራውን እስከ ሰኔ 30 እናጠናቅቃለን ቢሉም በማህበረሰቡ ዘንድ እንደማይጠናቀቅ በመታወቁ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱን ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

አዲስ ማለዳ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ የሆኑትን ባዮህ አቡሃይን እና የራማ መንገድ ሥራዎችን ለማነጋገር ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም።

@etconp
👍9🤣4💔1
👉ታሪካዊ ህንጻ

🌟ቁልቢ ገብርኤል ቤተክርስትያን፡፡

📍ቁልቢ ገብርኤል ቤተክርስትያን በጣልያናዊው ቪቶርዮ ስፒኔሊ የተገነባ ሲሆን ለማየት ቢያስቸግርም ገንቢው በምስሉ ላይ በጉልላቱ ላይ ቆሞ እየሰራ ይታያል፡፡

💫በተጨማሪም ቪቶርዮ ለመጨረሻ ግዜ በስራው ቦታ ላይ የተነሳውን ምስልም ተያይዟል፡፡

📸ምስል ምንጭ ኤርነስቶ ስፒኔሊ

@etconp
❤10👍7
Forwarded from Ethiopian Construction Vacancy & Tender (Itoophiyaa‍❤️)
EXTERNAL V- ACANCY.pdf
161.8 KB
#NEW

👉External Vacancy

🌟ማሳሰቢያ፡- የሥራ ልምድ ከተጠየቀው ትምህርት ደረጃ በኋላ የተገኘ ብቻ ይሆናል፡፡

✨አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ ማለት በተጠቀሰው የሙያ መስመር አገልግሎት ሲሆን፣ የሚቀርበው የሥራ ልምድ ማስረጃ የስራ ግብር የተከፈለበት፣ ደመወዝና አገልግሎት ከመቼ እስከ መቼ እንደተሰጠ የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡

👩‍⚕ሴት አመልካቾች ይበረታታለ

💫አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ የትምህርትና ሥራ ልምድ ማስረጃዎችን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የሰው ኃይል ቅጥር እና መረጃ አያያዝ ቡድን ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችለ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

📍አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ህንፃ ወይም ከበሻሌ ሆቴል ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ፣

☎️ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር

0116676385 / 0118698910

@ETCONpWORK
👍13❤1
👉ኮንስትራክሽን

🚧አስገዳጁ ረቂቅ አዋጅ . . .

🌟የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ፤ ትላልቅ ተቋራጮች ከአነስተኛ የግንባታ ተቋራጮች ጋር በጥምረት እንዲሠሩ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

ረቂቁ በሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ቀርቦ እንደሚገመገም ተገልጿል።

ረቂቁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ ሲደረግ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማረም በአገሪቱ የሚገኙ ትላልቅና ዋና ዋና ተቋራጮች ከአነስተኛ ትናንሽ ተቋራጮች በጥምረት እንዲሠሩ ዕድሉን የሚፈጥር ነው ተብሏል።

ረቂቅ ህጉን በአስገዳጅነት እንዲዘጋጅ የተደረገው አነስተኛ አቅም ያላቸው ተቋራጮች ሰፊ ልምድና አቅም ካላቸው ተቋራጮች ጋር በመሥራት ልምድ እንዲያገኙና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ በማሰብ ነው ተብሏል።

አነስተኛ ደረጃ ያላቸው ተቋራጮች ያልተገባ ተግባር ሲፈጽሙ ተጠያቂ እንዲሆኑ እና ክፍያ ላይም ምንም ዓይነት ችግር እንዳይገጥማቸው የሚያስችል ሕግ መሆኑ ተገልጿል።

አዋጁን በማርቀቅ ሂደት ፦
- የሕንፃ አማካሪ ድርጅቶች፤
- የሕንፃ ተቋራጭ ማህበራት፤
- በአገሪቱ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች፤
- ፕሮጀክት ያላቸው አካላት፤
- የገንዘብ ሚኒስቴር፤
- የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
- በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚሠሩ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እንደተሳተፉበት ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ፤ አነስተኛ ደረጃ ያላቸው የግንባታ ተቋራጮች እራሳቸውን ብቁ አድርገው መንግሥት በሚያሰማራቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ድርሻ ይዘው ለመሥራት ከወዲሁ ዝግጅት ያድርጉ ብሏል።

Via EPA

@etconp
👍9❤2👌1
👉ማስታወቂያ

✨ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም

🌟የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በአለም አቀፍ የሀገር ውስጥ ጨረታ (ICB) የሀገር በቀል የኮንስትራክሽን
ኩባንያዎችን የገበያ ድርሻ የሚያሳይ መረጃ ለማደራጀትና የቀጣይ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የሚስችሉ መረጃዎችን በማደራጀት ላይ ይገኛል፡፡

🌟የሀገርበቀል አለም አቀፍ ተጫራቾች መረጃ በተደራጀ መልኩ á‰°áˆ˜á‹áŒá‰ á‹ መደራጀታቸው በቀጣይ እንደሀገር ለሚኖረው እንቅስቃሴ á‹áŒ¤á‰łáˆ› ሾል ለመስራት የሚያስችል በመሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ባለድርሻዎች መረጃዎቻቸውን እንዲያስመዘግቡ ይጠይቃል፡፡

💫1. በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ፕሮጀክቶቻቸው የታየ ወይም እየታየ ያሉ ኩባንያዎች

💫2. በዓለም ዓቀፍ የሀገር ውስጥ ጨረታ (ICB) የተወዳደሩ ወይም ያሸነፉ ኩባንያዎች

💫3. በአህጉር ደረጃ በሚወጣ ጨረታ (ICB) እና ተያያዥ ውሎች ላይ የተሳተፉ የሀገር በቀል የኮንስትራክሽን
ኩባንያዎች በሙሉ

📍አዋሬ አደባባይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋናው መስሪያ ቤት 6ኛ ፎቅ ሀገር አቀፍ የኮንስትራክሽን መረጃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ እንድታስመዘግቡ እናሳውቃለን፡፡

☎️ለበለጠ መረጃ á‰  0911409508 ይደውሉ።

@etconp
👍5
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ የሲሚንቶ áŠĽáŒĽáˆ¨á‰ľ ከፍተኛ ችግር መሆኑ ተነገረ

ለመጀመሪያ ጊዜ 26 የአለም ሀገራት የሚሳተፉበት የኮንስትራክሽን አውደርእይ ሊካሄድ ነው

ይሄ የተባለው በዛሬው እለት የከተማ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ጫልቱ ሳኒ የኮንስትራክሽን አውደርእይ በተመለክተ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ።በመገለጫቸው የኮንስትራክሽን ዘርፉ 19 በመቶ ያህል በኢኮኖሚ  እድገት ላይ áŠ áˆľá‰°á‹‹áŒ˝áŠŚ እንደሚያበረክት ጠቅሰው ሆኖም የተለያዩ የግብአት ችግሮች በተለይ የሲሚንቶ እጥረት  ለዘርፉ ማነቆ መሆኑን መግለፃቸው ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

ይህንን እና መሰል ችግሮችን ይቀርፋል የተባለለት ቢግ 5 ኮንስትራክሽን ሲምፖዚየም እና የንግድ ትርኢትን መዘጋጀቱን ሚኒስትሯ ገልፀዋል። á‹­áˆ…ም የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ DG ኢቨንትስ እና ከሀገር አቀፉ አጋር ኢትኤል ኢቨንት እንዲሁም የሲምፖሲየሙ ስትራቴጂክ አጋር ከሆነው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ በመሆን ከግንቦት 10 እስከ 12 ቀን 2015 በሚሊኒዬም አዳራሽ  በጋራ እንደሚያካሂዱት አንስተዋል።

ይሄ ለመጀመሪያ ጊዜ  የሚካሄደው ሲምፖዚየም 26 የአለም ሃገራት ብሎም  116 አለም አቀፍ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ሲሆን 6000 ተሳታፊዎች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የግንባታው ዘርፍ ማነቆ የሆነውን ከአቅም ውስንነት ጋር የሚያያዙ ችግሮችን በቴክኖሎጂ ሽግግር ያለው ክፍተት የሚፈታበት ይሆናል ሲሉ አክለዋል።

ይህ ኮንስትራክሽን ዘርፉ ማነቆ የሆነበትን የግብአት  እጥረት በተለይ የሲሚኒቶ እጥረት ዙሪያ
አለም የደረሰበትን  የአመራረት ሂደት በዘርፉ ከተሰማሩት ልምድ እንዲወስዱ እድል ይሰጣል።

በመርሃ ግብሩ አምራች ተመራማሪዎች ፣ገዢና አቅራቢዎች ፣ከቱሪዝም ብሎም ከተማን ከማነቃቃት አኳያ እንዲሁም የኢትዮጲያን የገጽታ ግንባታ የምናሳይበት ነው ሲሉ ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል።

Via ቤተልሄም እሸቱ

@etconp
👍13❤2
📌የ ምስራች ዜና ለ ኮንስትራክሽን ተቋራጮች በ ሙሉ

🏗በ ኮንስትራክሽን ዘርፍ በ ተቋራጭነት፣በ ኢንተርየር ዲዛይን፣በ ሰብ ኮንትራክት፣በ ብረታ ብረት፣በ እንጨት ስራ እና የ ህንፃ ግንባታ ተያያዥ ስራዎች ያላቹ በ ሙሉ

🗞አዳዲስ ጨረታዎች ሲወጡ፣ ዕለታዊ የማተርያል ማሽነሪ Cost ለማወቅ በቀላሉ በ Private ቴሌግራም ቻናል እና በ ኢመይል አድራሻቹ አመቱን ሙሉ በ ማይታመን ዋጋ áŠĽáŠ•á‹˛á‹°áˆ­áˆłá‰š ለምትፈልጉ ከታች ባሉት አደራሻዎች አናግሩን።

🚧ለመመዝገብ @Philemona7 ወይም @etconpworks ያናግሩን።

☎️ለ በለጠ መረጃ በ +251925446661 ወይም 0707444849 ይደውሉ

🙏እናመሰግናለን🙏

@etconp
🙏9👍3
👉ብዙ የኮንስትራክሽን ባለሞያዎች መሰንጠቅ በ Mix design ትክክል አለመሆን ብቻ የሚመጣ ይመስላቸዋል ነገር ግን ለመሰንጠቅ (cracking ) ምክንያት የሚሆኑ መንስኤዎችን ከዚህ በታች እንዲህ ዳስሰናል :-

[1] - አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ
.
አነስተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሶች የምንጠቀም ከሆነ መሰንጠቅ (cracking ) ይፈጠራል ስለዚህ የምንጠቀማቸውን ለኮንክሪት ግብዓት የሚሆኑ ቁሶችን (ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ኮረኮንች) ጥራት መፈተሽ አለብን ኮንክሪቱ የብረት መዋቅር (reinforcement ) ያለው ከሆነ የብረቱን ጥራት መገምገም አለብን።
.
[2] - መኮማተር (Shrinkage )
.
ኮንክሪቱን በምንደባልቅበት እና ውሃ በምናጠጣበት ግዜ (Curing ) ተገቢውን ጥንቃቄ ካልወሰድን መኮማተር (shrinkage) መሰንጠቅን(cracking)   ያስከትላል ።
መኮማተር (shrinkage) ለትልቅ የኮንክሪት ጥንካሬ በጣም አስፈላጊ ነው አስፈላጊውን የውሃ-ሲሚንቶ መመዛዘን (water cement ratio) ካልተጠቀምን በመኮማተር አማካኝነት መሰንጠቅ ሊፈጠር ይችላል ።
.
[3] - ጥራት ያለው Aggregate የማንጠቀም ከሆነ
.
Aggregate የኮንክሪትን አጠቃላይ ጥንካሬ ይወስንልናል ጥራቱ ጥሩ ያልሆነ Aggregate የምንጠቀም ከሆነ ከሲሚንቶ ጋር ተፈላጊውን ጥምረት (bond) ስለማይፈጥር ግንባታችን ሊሰነጠቅ ይችላል።
.
[4] - መዋቅራችን ከአቅም በላይ የሆነ ክብደት ሲያስተናግድ
.
ግንባታው / መዋቅሩ ተገቢውን ጥንካሬ ሳያገኝ በፊት ለትልቅ ክብደት የሚጋለጥ ከሆነ መሰንጠቅ ይከሰታል። በተጨማሪም መቀሰቻዎችን እና ቅስቱን (formwork ) ያለጊዜው የሚነሳ ከሆነም ግንባታችንን ለስንጣቆ ያጋልጠዋል።

.
[5] - በትክክል ውሃ እንዲጠጣ የማይደረግ ከሆነ (improper curing )
.
ይህ በአገራችን ከሚስተዋሉ ለመሰንጠቅ ከሚዳርጉ ምክንያቶች ቀዳሚው ነው - ውሃ በትክክል አለማጠጣት።
ኮንክሪት እንደተገነባ በተገቢው ጊዜ እና መጠን ውሃ መጠጣት አለበት ።
«ወንድና ሲሚንቶ ካልጠጣ ይሰነጠቃል» አይደል ሚሉት ሰካራም ወንዶች😁
.
[6] - የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) አለመመጣጠን
.
በጣም ትልቅ የሆነ የብረት መዋቅርን Mix ratioው ትንሽ በሆነ ኮንክሪት የሙሌት ስራ ስንሰራ በብረቱ እና በኮንክሪቱ መካከል ያለ የውጥረት ስርጭት (stress distribution ) non linear ይሆናል ይህ ደግሞ መሰንጠቅን ያስከትላል።
.
[7] - በሳይት ላይ የሙሌት (casting ) ስራ ሲሰራ ተገቢ ጥንቃቄ ካልተደረገ እና ለስራው ተገቢ የሆነ ባለሞያ (የቀን ሰራተኛን ጨምሮ) ካልተመደበ መሰንጠቅ (cracking) በሚሰራው ኮንክሪት ላይ መፈጠሩ አይቀርም።

@etconp
👍11❤7🙏3👌3🐳1
ዛሬ ዘለግ ያለ ፅሁፍ ይዘን መጥተናል

ETCONp አርኣያ ሰብ

በገበታ ለሀገር ከእየተገነቡ ካሉ የተለያዩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የሚገኝበት የኮንታ ዞን በተፈጥሮ ሀብቶች የታደለው ነው።

ኮንታ ግን በተፈጥሮ ሀብት ብቻ ሳይሆን በሙያቸው የተካኑ አርክቴክቶችም አግኝቷል።

በ እነዚህ አርክቴክቶች ዲዛይን የተደረገው እና በቅርቡ ተመርቆ ይፋ የተደረገው የሃላላ ኬላ ሪዞርት በርካቶችን አስደምሟል።

በደቡብ ምዕራብ ክልል፣ በኮንታ ዞን የኮይሻ ፕሮጀክት ይገኛል። ታድያ ከዚህ ፕሮጀክት ጀርባ እነማን አሉ? ቢቢሲ ከእነዚህ መካከል ወጣቱን አርክቴክት ኃይሌ ታደሰን አግኝቷል።

በቅድሚያ ግን ስለ ኮይሻ ፕሮጀክት ጥቂት ነገር እንበል።

Via BBC Amharic

@etconp
👍8❤2
ገፅ 1

ይህ የመዝናኛ ስፍራ ልማት የኮይሻ ዓለም አቀፍ የቱሪስት መዳረሻ ልማት የሚባለው ትልቅ ፕሮጀክት አካል ሲሆን በክልሉ የተለያዩ ዞኖች ውስጥ የሚገኝ ነው።

አካባቢው የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ መገኛ ሲሆን፣ የተለያዩ ማኅበረሰቦችም መኖሪያ ነው።

በሚያዝያ ወር መጀመርያ ላይም በደቡብ ምዕራብ ክልል ውስጥ የሚገኘው የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነው የሐላላ ኬላ ሪዞርት በይፋ ተመረቋል።
ገበታ ለሀገር በሚባለው ፕሮጀክት ስር የሆነው እና አዲስ በተመሠረተው ክልል ውስጥ የሚገኘው ይህ የመዝናኛ ስፍራ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተመርቆ ተከፍቷል።

ይህ ሪዞርት ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የህወሓት ተወካዮች ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት በመገናኘት የተነጋገሩበት ስፍራ ነው።

“ይህ ፕሮጀክት የአካባቢውን ታሪክ እና ባህል የተፈጥሮን እና የሰው ሰራሽ ሀብቶች አጣምሮ የያዘ ነው” ይላል ፕሮጀክቱን ዲዛይን ያደረገው አርክቴክት ኃይሌ።

በክልሉ እየተሰሩ ካሉ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ውስጥ ትልቁ የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ መሆኑን አርክቴክቱ አክሎ ይናገራል።

ከዚህም ባሻገር ረዥም እድሜ ያስቆጠረው እና ሰው ሰራሹ ልማት ሃላላ ኬላ የተባለው የድንጋይ ካብ እዚሁ ውስጥ ይገኛል።

“በዳውሮ ሕዝብ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ የተገነባው የድንጋይ ካብ ወይንም ኬላ በግምት 1200 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ነው።

መጠሪያውንም ከመጨረሻው ንጉሣቸው ያገኘ ነው። እነርሱ ‘ካቲ ሃላላ ኬላ’ ይሉታል።”

በተጨማሪም የግልገል ጊቤ ሦስት ግድብ፣ እንዲሁም የኮይሻ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ የዚሁ ትልቁ ፕሮጀክት አካል ናቸው።
በሃላላ ኬላ ፕሮጀክት ውስጥ በአምስተኛነት ደረጃ የታቀፈው ፕሮጀክት ጫራ የሚባል ማኅበረሰብን ማዕከል ያደረገ ነው።

“የጫራ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ ከአፈር ውስጥ ብረት የማውጣት እውቀት ያለው ሲሆን፣ እስከ ዛሬ ድረስም ይህንን ሙያ እየሰሩ ይገኛሉ። ይህ ማኅበረሰብ የራሱ የሆነ ባሕል እና ክህሎት ያለው ሕዝብ ነው።”
እነዚህ ልማቶች በአምስት ክላስተሮች በመክፈል ዲዛይኑን እንደሰሩ አክርቴክት ኃይሌ ይናገራል።

ከዚህ በተጨማሪ እነዚህን የልማት መዳረሻዎችን ደረጃ በደረጃ እስከ 25 ዓመታት በሚደርስ ጊዜ ውስጥ ሠርቶ ለማጠናቀቅ ታቅዷል።

ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ “በአጭር ጊዜው የሦስት ዓመት ፕሮጀክት ውስጥ ሃላላ ኬላ እና ጨበራ ሪዞርቶች ይገኛሉ።”


Via BBC Amharic

@etconp
👍3🙏2🤮1
ገፅ 2

አርክቴክት ኃይሌ ማን ነው?

አርክቴክት ኃይሌ ታደሰ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በግንደ በረት ወረዳ ውስጥ በምትገኘው ካቺሲ ውስጥ ነው ተወልዶ ያደገው።

የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም ተምሮ ያጠናቀቀው በትውልድ አካባቢው ነው።

በኋላም በወለጋ ዩኒቨርስቲ በአርክቴክቸር የትምህርት ዘርፍ አምስት ዓመት ካጠና በኋላ በከፍተኛ ውጤት ተመርቋል።

ከተመረቀ በኋላም ለሁለት ዓመታት በሐዋሳ እና በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲዎች በመምህርነት አገልግሏል።

ከዚያም የሁለተኛ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአርክቴክቸራል ኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፍ አጠናቅቋል።

ተመርቆ እንደጨረሰም የራሱን የግል ድርጅት ‘ሉላ ኢንጂነሪንግ’ በሚል ስያሜ በማቋቋም እየሠራ መሆኑን ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል።

“ተወልጄ ያደግኩት ገጠር ውስጥ ነው” የሚለው ኃይሌ፣ በኮንታ አካባቢ ያለው የተፈጥሮ ውበት እንደሚማርከው ይናገራል።

“የአፍሪካ ተራራዎች ተሰብስበው ዳውሮ ከትመዋል ይላሉ ሰዎች” በማለት አካባቢው በተፈጥሮ ሀብት የታደለ መሆኑን ይገልጻል።

በሌላ በኩል የዳውሮ ሕዝብ ያለው ባህል፣ ትውፊት እና ሕግጋት ከዚህም ባሻገር በአካባቢው ያለው ሰላም አስተማማኝ መሆኑንም ይጠቅሳል።
ከዚህ በተጫመሪ ሕዝቡ ለእንግዳ የሚያደርገው አቀባበል የተለየ መሆኑ አካባቢው ለጎብኚ ምቹ እና ሁሉን የያዘ እንደሆነ ይመሰክራል።

አርክቴክት ኃይሌ እንደሚለው ለእነዚህ ፕሮጀክቶች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት አማካኝነት በቅርበት የሚደረገው ክትትል እና የአካባቢው ሰላም ሥራዎቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ አስተዋጽኦ አድርጓል።

Via BBC amharic

@etconp
👍7🤣1
ገፅ 3

የአርክቴክት ኃይሌ ሚና ምን ነበር?

አርክቴክት ኃይሌ ታደሰ ከዓመታት በፊት በመሠረተው ድርጅቱ አማካይነት በዚህ ፕሮጀክት እና በሌሎችም ትላልቅ ፕሮጀክቶች ላይ ከተሳተፉት አካላት መካከል ነው።

‘ሉላ ኢንጂነሪንግ’ የተባለው የእርሱ ድርጅት እና ሌላ ‘ስታዲያ ኢንጂነሪኒግ’ የተባለው ድርጅት በጥምረት የእነዚህን ፕሮጀክቶች ዲዛይን በመሥራት እንዲሁም ቁጥጥር በማድረግ ተሳትፈዋል።

“እነዚህን በክላስተር የተከፈሉትን ዲዛይኖች ‘ኮንሰፕት ዲዛይን’ ከማዘጋጀት ባለፈ የዲዛይን ቁጥጥር እና ክትትል እንድንሰራ ነው ኮንትራት የገባነው” ይላል።

እንደ ግሉ ደግሞ ኃይሌ የአርክቴክቸራል ቡድን መሪ በመሆን እነዚህ ፕሮጀክቶች ላይ ተሳትፎ ማድረጉን ይናገራል።
“እድሜዬ 31 ነው፤ ዛሬ ደረስኩባቸው ብዬ የማስባቸው ነገሮች፣ ፍላጎቴን እና ጥረቴን አንድ ላይ አጣምሬ ሳያቸው ትንሽ የዘገየሁ ይመስለኛል” በማለት በራስ መተማመን በዚህ ፕሮጀክት ላይ መሳተፉን ይናገራል።

“ትልቁ ነገር ጠንክሮ መሥራት ነው” የሚለው ይህ ወጣት፣ ከልጅነቱ ጀምሮ ለአርክቴክቸር ትምህርት፣ ፍቅር እና ልዩ የሆነ ፍላጎት ማሳደሩ አሁን ለደረሰበት ደረጃ ለመብቃት ረድቶታል።

አርክቴክት ኃይሌ በትምህርት እና በሥራው ላይ ከመበርታቱ ባሻገር በዚህ ዘርፍ በተቻለው መጠን ሌሎች ቦታዎች ያሉ ተሞክሮዎችን ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል።

“ይህንን ፕሮጀክት ከማግኘቴ በፊት ኬንያ እና ታንዛኒያ ሄጄ ነበር። የእኛ አገር ፓርኮች እንዴት መልማት አለባቸው የሚለውን ተሞክሮ ለመውሰድ ማሳይ ማራ እና ሰረንጌቲ ፓርኮችን ጎብኝቻለሁ።”

ከዚህ በተጨማሪም እንደሀገር ተይዞ እየተሠራ ያለውን በአማራ ክልል የሚገኘውን የጎርጎራ የቱሪዝም ልማት መዳረሻ ዲዛይንንም እንደሠራ ጠቅሷል።
አርክቴክት ኃይሌ የዚህን ፕሮጀክት ዲዛይንንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገኙበት በኮይሸ ተገኝቶ ማቅረቡንም ተናግሯል።

ቀጣይነት ያለው ዲዛይን አርክቴክት ኃይሌ ስለ ወደፊት ህልሙ እና አሁን እየሠራው ስላለ ሥራ ሲጠየቅ ቀጣይነት ስላላቸው ፕሮጀክቶች በተደጋጋሚ ይናገራል።

“አባቶቻችን ማንኛውንም ልማት ሲሰሩ ከተፈጥሮ ጋር እንዲስማማ አድርገው ነው። ተፈጥሮን የሚጎዳ ማንኛውንም ነገር አያበረታቱም” የሚለው ኃይሌ፣ ከአየር ብክለት ጋር በተያያዘ ዓለማችን ፈተና እየገጠማት እንደሆነ ያስታውሳል።
አክሎም “ቀጣይነት ባላቸው ነገሮች እሳቤ ከዚህ በፊት የተበላሸው ወደኋላ እንዲመለስ፣ እንዲሁም ዛሬ እየተገነባ ያለው ደግሞ ተሻሽሎ አንዲገነባ ይታሰባል።”

ነገር ግን እሱ እንሚታዘበው ከሆነ በአሁኑ ጊዜ እየተገነቡ ያሉ የተለያዩ አይነት ግንባታዎች የተበላሸውን ለማስተካከል፣ የወደፊተንም ለመጠበቅ መደረግ ያለበትን ማዕከል ያደረጉ አይደሉም።
“ፕሮጀክቶች ያለጥናት ይታቀዳሉ። ይገነባሉ። መጀመሪያ እና መጨረሻቸው አይታወቅም። ወደፊት ለምትሄደው ዓለምም እየሠራን አይደለም። አባቶቻችን ያወረሱንንም ያህል እየሠራን አይደለም። እንደ አገር መካከል ላይ [ተንጠልጥሎ] የቀረ ነገር አለን።”

አርክቴክት ኃይሌ ታደሰ እንደሚለው በኦሮሞ አባቶች ባሕል መሠረት “. . . አምስቱ ኦዳዎች በማለት ለእኛ እንዳወረሱን፣ እኛም ደግሞ ለመጪው ትውልድ መቆየት የሚችሉ ቀጣይነት ያላቸው ግንባታዎችን ማቆየት አለብን የሚል ፍላጎትም ተስፋም አለኝ::

ተፈፀመ

Via BBC Amharic

@etconp
👍9🤣1
In designing a structure with a shear wall, the most important point is choosing the location of the wall. To reduce the drift of the structure by reducing the distance between the center of mass and the center of stiffness.

@etconp
🙏6👍4❤1