Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
🚧Picture Of The Day

🌟Different beam name at the different positions

@etconp
👍3👏1
👉የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም

🌟ሰሜን ሸዋ ልዩ ቦታው የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም

⏺ወጪ:- 320 ሚሊዮን ብር
⏺አማካሪው:- SAY Consult
⏺ዋና ህንጻውን የነደፈው:- ሳሙኤል አፈወርቅ ለማ

▶️ነዳፊው የቤቷክርስትያኗን  ኪነህንጻ ከሀያኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ከውጭ ማለትም ከህንድ፣ ከአርመን፣ ከጣልያን፣ ከግሪክ ወዘተ  በቀጥታ ተቀድተው የመጡትን የንድፍ ትእምርቶች፣ ቅርጽና ደርዞች ሳይመረኮዝ በመስራቱ ሊደነቅ ይገባል።

🚧በ20ኛው ክፍለዘመን መጀመርያ ላይ  የኒዮክላሲካል (አራዳ ጊዮርጊስ)፣ የኒዮ ባሮክ (ቅድስት ስላሴ) እንዲሁም የአርመን እና የህንድ ንድፍ ዘይቤዎች  (አብዛኞቹ  በ1900 መጀመርያ በአዲስ አበባ የተገነቡት አብያተክርስትያናት) የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. ህንጻ ንድፎች ላይ ተጽእኖአቸውን ያሳረፉ ሲሆን በዘመናችን ደግሞ ፔዲመንትና አእማዶችን  ጭምር ከግሪኮ ሮማን ኪነህንጻ ቋንቋ በብዛት ተውሶ የመስራት ዝንባሌ ይታያል።

🚧የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. እጅግ ብዛት ያለው የእይታ  ጥበብና የቤተክርስትያን ንድፍ ሀብት ስላላት ያንን ሀብት በዘመናችን ተርጉመው የሚነድፉ ነዳፊዎች ያስፈልጓታል።

ምስል ምንጭ በይነ መረብ

@etconp
❤16👍7😢1
የውሃ ጋኖች (water supply Reservoir)
.
የውሃ ጋኖች ከጥቅማቸው አንፃር ለ ሶስት ይከፈላሉ
.
1-Collector reservoir
2-Service reservoir
3-Supply reservoir
.
እያንዳንዱ ጥቅማቸው ምንድነው……
.
[Collector reservoir ]
.
ይህ የጋን አይነት ዋና ስራው ውሃው ከሚመነጭበት (የገጸ ምድር ወይም የከርሰ ምድር ውሃ) ቦታ ህክምና ከተደረገለት በኋላ የሚቀመጥበት ጋን ነው፡፡ ጥቅሙ የተሰበሰበውን ውሃ ወደተለያዩ ጋኖች እስኪሰራጭ በጊዜያዊነት እንዲቀመጥና ውሃው ለጋኖቹ እንዲደርስ የሚያደርገውን ጉልበት እንዲያገኝ ይረዳዋል፡፡ ብዙን ጊዜ ውሃው ከሚመነጭበት ቦታ አቅራቢያ ይተከላል፡፡ ውሃ ፈሳሽ እንደመሆኑ ብዙን ግዜ ሚፈልቀው ከፍታቸው ካነሱ ቦታዎች ስለሆነ ከሌሎች ጋኖች ይልቅ የዚህ ጋን ከፍታ (elevation) ያንሳል፡፡
.
[Service reservoir]
.
ይህ የጋን አይነት በቋሚነት ከcollecter reservoir የተቀበለውን ውሃ የሚያርፍበት ነው፡፡ አሰራሩም ከሌሎቹ ጋኖች ለየት ይላል ፡፡ ውሃው የሚያደርስበትን ግፊት ለመቋቋም የሚያስቸለውን መካች ጉልበት(reaction force) በበቂ ሁኔታ እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ በቁመትም በመጠንም ትልቅ ነው፡፡ ወጪ ለመቀነስ ከፍ ካለ ቦታ ይተከላል (ውሃ በ3 አይነት መንገድ ይከፋፈላል
.
1-የሞተር ሀይልን በመጠቀም

2-የመሬት የመሳብ ሃይልን (gravity force) በመጠቀም።

3-የሞተር ሃይልንና የመሬት የስበት ሃይልን በማጣመር በመጠቀም እንዲሰራጭ ይደረጋል ፡፡

በአሁን ጊዜ ሶስተኛው አማራጭ በስፋታ አገልግሎት ላይ ይውላል ይህ አማራጭ ከወጪም አንፃር በጣም ተመራጭ ነው ለዚህ ዘዴ ተመራጩ ደግሞ የservice reservoir ከፍ ካለ ቦታላይ መተከል ወሳኝነት አለው፡፡)
ከዚህ ጋን ቀጥታ ለስርጭት ቧንቧ አይገጠምም ምክንያቱም ከጋኑ የሚወጣው ውሃ ከፍተኛ ጉልበት ስላለው የማሰራጫ ቱቦዎችን ሊያፈነዳ ይችላል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት ቀጣዩን የጋን አይነት መገንባት አስፈላጊ ነው፡፡
.
[Supply  reservoir]
.

የዚህ ጋን ዋና ጥቅም ውሃውን ለስርጭት ወደ ስርጭት ቱቦዎች እንዲገባ ማድረግ ነው፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት ከሰርቪስ ጋን ቀጥታ ወደ ስርጭት ቧንቧ ውሃ አይገባም ምክንያቱም ከፍተኛ ሀይል ስላለው የቧንቧዎቹን የመቆየት አቅም ያሳጥራል ብሎም እስከ ማፈንዳት ያደርሳል፡፡ ይህ እንዳይከሰት የሳፕላይ ጋኖች ይገነባሉ፡፡ ይህ ጋን በቱቦዎቹ የሚያልፈውን ውሃ ግፊት በመቀነስና ፈጥነቱን (velocity) ከ 0.5-2 m/s በማድረግ እና ወደ ቱቦዎቹ የሚገባን ሃይል በመቀነስ (Energy dissipate ) ቱቦዎቹ  ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ያስወግዳል፡፡ ይህ ጋን ከፍ ባለ ቦታ ይተከላል ነገር ግን ከፍታው ከService reservoir ያነሰ ነው።
.
Like | Share | Comment

#Hydraulics

@etconp
👍22
👊Picture Of The Day

✍Put The Reason @COTMp

@etconp
❤2
ግድብ (Dam) ማለት ገዝፈ አካል ሲሆን የውንዝን ሸለቆ ላይ ተገንብቶ የውሃን ተፋሰስ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሚገታ ነው።

ይህ መግታት (blockage) በውሃ ተፋሰስ ላይ መታቆርን (reservoir) ይፍጥራል ይህም ወሃውን ለተፈለገው አገልግሎት እንዲውል ቀሊል ያደርገዋል ። ይህ አጋጅ ገዝፈ አካል ወይም ግድብ ከተለያዩ ቁሶች ይሰራል ፦ ኮንክሪት፣ የድንጋይና አፈር መደምደም (compaction) ወዘተ...
.
ግድም በዋነኛነት ለነዚህ አገልግሎቶች ይገነባል፦
1- ጎርፍን ለመቆጣጠር - for flood control
2- ለውሃ አቅርቦት እና የመስኖ ስራ - for water supply and irrigation
3- የኤሌትሪክ ሃይልን ለማመንጨት - for electric power generation
4- የአንድን ወንዝ ፍሰት ለመመጠን እና ለመቆጣጠር - for regulation or balancing of a river flow

#Hydraulics

@etconp
👍17
📌የ ምስራች ዜና ለ ኮንስትራክሽን ተቋራጮች በ ሙሉ

🏗በ ኮንስትራክሽን ዘርፍ በ ተቋራጭነት፣በ መንገድ ስራ፣በ ኢንተርየር ዲዛይን፣በ ሰብ ኮንትራክት፣በ ብረታ ብረት፣በ እንጨት ስራ እና የ ህንፃ ግንባታ ተያያዥ ስራዎች ያላቹ በ ሙሉ

🗞አዳዲስ ጨረታዎች ሲወጡ፣ ዕለታዊ የማተርያል ና ማሽነሪ Cost ለማወቅ በቀላሉ በ Private ቴሌግራም ቻናል አመቱን ሙሉ በ ማይታመን ዋጋ እንዲደርሳቹ ለምትፈልጉ ከታች ባሉት አደራሻዎች አናግሩን።

👊እስካሁን ከ ደረጃ 1 እስከ 10 በዛ ያሉ
በየቀኑ አዳዲስ ጨረታዎች እየለጠፍን እንገኛለን (ማረጋገጫ አሁናዊ የ ቻናሉ ገፅታ በ ምስል አያይዘንላቹዋል)

🚧ለመመዝገብ @Philemona7 ወይም @etconpworks ያናግሩን።

☎️ለ በለጠ መረጃ በ +251925446661 ወይም 0707444849 ይደውሉ

🙏እናመሰግናለን🙏

@etconp
👍4
Given the structural drawing of column detail and assume there are 13 columns and you are expected to compute the bar quantity from FOUNDATION LEVEL to BASEMENT FLOOR LEVEL

A. the length of the bar (Total length for 13 columns) and the diameter of the bar

B. Quantify the the total weight of the bar for 13 columns in kilogram (KG)

C. Quantify the total length in BERGA

D. Quantify the stirrup (total length, total weight and in berga) for 13 columns
(ENG)

የኮለን ምሶሶ መዋቅራዊ ስእልተሰጥቷችኋል 13 ኮለን ምሶሶዎችን አሉ ብላችሁ አስቡ በዚህ መሰረት ከ መሰረቱ (foundation level) እስከ ቤዝመንት ያላችሁን ኮለን ማለትም ለfoundation ኮለኖቹን ምን ያህል ብረት እንደሚያስፈልግ አስሉ

ሀ. ለ 13ቱ ኮለን ምን ያህል ርዝመት ያለው ብረት ያስፈልጋል ባለ ስንት ውፍረት ብረት ነው ሚያስፈልገን

ለ. በ ኪሎ (በኬጂ) ግለፁ

ሐ. በ ቤርጋ ግለፁ

መ.ለ ስታፋውም በተመሳሳይ እንደ ሀ,ለ,ሐ ግለፁ

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Twitter :- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

YouTube :- https://youtube.com/@Etconp432
👍16❤3
በቤቶች ግንባታ ዘርፍ ለሚታዩ ችግሮች ሳይንሳዊ ጥናቶችን መሰረት ያደረጉ መፍትሔዎችን ማቅረብ እንደሚገባ ተጠቆመ 

በቤቶች ግንባታ ዘርፍ ለሚታዩ መሰረታዊ ችግሮች ሳይንሳዊ የሆኑ ጥናቶችን መሰረት ያደረጉ መፍትሔዎችን ማቅረብ እንደሚገባ የኢፌዴሪ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሰረተ-ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጠቁሟል። 

ቋሚ ኮሚቴ ይህንን የጠቆመው፤ በወጪ ቆጣቢ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ የግብዓት፣ የወጪ አጠቃቀም እና የዲዛይን ሂደት ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችና ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን ለመለየት በሚያስችለው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠንቶ በቀረበው ጥናትና ምርምር ዙሪያ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው። 

በውይይት መድረኩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከአርክቴክቸርና የሕንፃ ኮንስትራክሽን ክፍል እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው በዘርፉ የካበተ ልምድና እውቅና ያላቸው አንጋፋ ምሁራን ተሳታፊ ሆነዋል። 

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በውይይቱ ወቅት እንደገለፁት፤ የመጠለያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል የወጪ ቆጣቢ ቤት በመገንባት ሂደት የሚያስፈልጉ የግብዓት እቃዎች አቅርቦት፣ የፕላንና ዲዛይን ቅየሳ፣ የፋይናንስ አቅርቦት ዙሪያ የሚያጠነጥነው ጥናታዊ ጹሑፍ ቋሚ ኮሚቴው በሚያደርገው የክትትልና የቁጥጥር ስራ በተጨባጭ መረጃ እና እውነታ ላይ የተደገፈ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል። 

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ እሸቱ ተመስገን (ዶ/ር) በአሁኑ ወቅት እንደ ሀገር ችግር የሆነውን የመጠለያ  ቤት እጥረት ከመሰረቱ ለመፍታት የሚያስችሉ በሳይንሳዊ ጥናቶች የተደገፉና የዳበሩ ግብዓቶችን በመጠቀም የሚወጡ አዋጆችና ፖሊሲዎች ያስፈልጉናል ያሉ ሲሆን፤ ከዲዛይን፣ ከግብዓት አቅርቦት እና ከዋጋ አንፃር የሚታዩ ችግሮችን በመለየት መፍትሄ ለማስቀመጥ ጥናቱ ጉልህ ሚና ይጫወታል ብለዋል።  

የቋሚ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው ለሕብረተሰቡ ተደራሽ የሚሆኑ ወጪ ቆጣቢ፣ ጥራታቸው እና ዲዛይናቸው ተጠብቆ የሚሰሩ የመሰረተ-ልማት ዝርጋታ ስራዎች ከምንጊዜውም በላይ ለዜጎቻችን ያስፈልጋሉ ያሉ ሲሆን፤ ይህንንም ከግምት ያስገባ የሁሉንም አቅም ያማከለ የቤት ግንባታዎችን ተደራሽ ከማድረግ እና በግንባታ ሂደት ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችን በመለየትና የመፍትሔ ሀሳብ በማስቀመጥ ለሚመለከታቸው የመንግስት እና ባለድርሻ ተቋማት ለማቅረብ ጥናቱ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል። 

በውይይቱም በከተማ አካባቢ የሚገነቡ ቤቶች ከወጪ፣ ከጥራትና ዲዛይን እንዲሁም የዜጎችን ፍላጎት ያማከለ ከመሆኑ አንጻር በዓለማቀፍ ደረጃ ያሉ ተሞክሮዎችና ልምዶች በምሁራን የቀረቡ ሲሆን፤ ከዚህም ልምድና ተሞክሮ ተነስተው በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያስገባ የመፍትሔ ሃሳብ ለማምጣት ጥናቱ ትልቅ ድርሻ እንዳለውም በጥናቱ የተሳተፉ ምሁራን ገልጸዋል። 

@etconp
👍10
👉የዊንዶው ኦፍ አፍሪካ ፓርክ ግምባታ ተጀመረ

🌟በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ከቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አጠገብ ቀደም ብሎ ለፓርክነት ተከልሎ በነበረው ስፍራ ላይ የሚገባው ፓርኩ አጠቃላይ 84 ሄክታር  መሬት ይሸፍናል።

🌟በመጀመሪያው ምዕራፍ በ14.5 ሄክታር መሬት ላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ፣ የመዝናኛ ፣ የመናፈሻ ፣ የአረንጓዴ ስፍራዎች ፣ ሰው ሰራሽ ሀይቅ እና መዋኛ ገንዳዎች እንዲሁም መንገዶች እና የተሽከርካሪ ማቆሚያዎችን እና የህጻናት መጫዎቻ ስፍራዎችን በውስጡ የሚይዝ ይሆናል።

🌟በፕሮጀክቱ የእያንዳንዱን የአፍሪካ ሀገር ባህልና ማንነት የሚያንጸባርቁ ቅርሶች እንደሚቀመጡም ነው የተገለጸው።

✨በፓርኩ አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና መሆኗን እና የቦሌ አየር መንገድም የአፍሪካ መግቢያ በር መሆኑን የሚያሳይ ታላቅ የዊንዶው ኦፎ አፍሪካ ማማ እና የአፍሪካ ሙዝየም እንዲሁም ሆቴሎችና የንግድ ህንጻዎችን የሚያካተቱ ይሆናል።

✨በአይነቱ እና በግዝፈቱ ታላቅ ነው የተባለለትን ይህንን ፖርክ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ቻይና ፈርስት ሀይ ዌይ ኢንጅነሪንግ ካምፓኒ የተባለ ተቋራጭ የሚገነባው ሲሆን በ18 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎም ይጠበቃል።

@etconp
👍14👌2