Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
PPA 2011 Contract.docx
153.4 KB
👏5❤1👍1
👉የግንባታ ኢንደስትሪው ሀብቶች

1.የገንዘብ ሀብት/Financial Resource or fund/:-

የግንባታ ሥራው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚጠይቀው የገንዘብ ወጪ ነው፡፡ ይህም ከተቀማጭ በቀጥታ፣  በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ከብድር፣ወይም ከስጦታ ወይም ከሌላ ህጋዊ ከሆነ የገንዘብ ምንጭ የሚገኝ ሊሆን የሚችል ሲሆን የግንባታ ፕሮጀክት ለማከናወን ከሚያስፈልጉ ሀብቶች አንዱ መሰረታዊውና ዋነኛው ነው፡፡

2. የሰው ሃይል ሀብት/Human Resource/Labour or Workmanship/:-

እነዚህም ከዘርፉ ቀጥተኛ የሰለጠኑ ባለሞያዎች/Proffesionals/ ፣ በፕሮጀክት አመራር ውስጥ አጋዥ ወይም ደጋፊ የሥራ ዘርፍ ባለሞያዎችንና እስከታችኛው እርከን የሚወርዱ የሥራው ቀጥታ ተሳታፊ የሆኑ በከፊል የሰለጠኑና/Semi skilled/ ስልጠና የሌላቸው የጉልበት ሰራተኞችን/Unskilled/ ሁሉ ያጠቃለለ ነው፡፡የሰው ሃይል ሀብት ለግንባታ ሥራ ከሚመደበው የገንዘብ ሀብት ወይም ባጀት ከ5-7% የሚሆነውን የሚቋደስ ነው፡፡

3. የመረጃ ሀብት/Information Resource/:-

ይህ ዓይነቱ ሀብት ከፕሮጀክት ጥናት ጀምሮ በዲዛይን ሼል ብሎም ወደግንባታ ሼል ለመግባትና፣ በፕሮጀክት ሼል ክንውን ወቅት በሚደረጉ ጉዞዎች ሁሉ አስፈላጊና ለፕሮጀክቱ ዘላቂ ደህንነት መረጋገጥ የሚጠቅሙ፣ የግንባታ ሥራን  አዋጭና በተያዘለት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የሚረዱ መረጃዎች ናቸው፡፡
መረጃዎች ሳይሰበሰቡ የሚደረግ የዲዛይንና የግንባታ ሥራ ሁሉ አጠራጣሪ ወይም አስጊነቱ የማይካድ ነው፡፡

4. አካላዊ/ግዘፍ ሀብቶች/Physical Resources/:-

አካላዊ ወይም ግዘፍ ሀብቶች የሚባሉት የግንባታ ግብዓት ዕቃዎችና የግንባታ ሥራ ማሽነሪዎች /Materials and Machinaries/ ናቸው፡፡ እነዚህ ሀብቶች ከፍተኛ ግዢ የሚካሄድባቸውና፣ የአንድ ፕሮጀክት አብዛኛውን የገንዘብ ሀብት ወይም ባጀት የሚቋደሱ ወይም የሚይዙት ናቸው፡፡ለምሳሌ የግንባታ ግብዓቶችን ብቻ አንኳን ብንመለከት ከ50-65% የሚሆነውን የግንባታ ሥራ በጀት የሚይዙ ናቸው፡፡

5. የአገልግሎትና አስተዳደራዊ አቅርቦቶች ሀብቶች/Survices and Management/:-

የመሬት አቅርቦት፣ የውሃ አቅርቦት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ የስልክ መገናኛ አገልግሎት አቅርቦቶችና የመሳሰሉትን የሚያካትት ሆኖ የግል ወይም የመንግስት አገልግሎት አቅራቢ ተቋማትን አስተዳደራዊ ፈቃድ የሚጠይቁና የሚቀርቡ፤ የግንባታ ሥራዎች ጥራት፣ ቅልጥፍናና የተሻለ አዋጭነት ባለው መልኩ እንዲከናወንና እንዲጠናቀቅ የሚረዱ ሀብቶች ናቸው፡፡

https://www.facebook.com/etconp/

https://youtube.com/@Etconp432
👍4
👉የግንባታ ሼል  ውል አፈጻጸም ውስጥ ተሳታፊ የሚሆኑ ዋና ዋና  ባለድርሻ አካላት፡

የስራው ባለቤት/Client/Employer:-

ግለሰብ ወይም ማህበር ወይም ድርጅት ወይም የመንግስት ተቋም ሊሆን የሚችል ሲሆን የሥራው ባለቤት ከመሆኑ አንጻር ሥራውን ለማከናወን የሚችል ሥራ ተቋራጭና አማካሪ መሃንዲስ መቅጠር እና ለግንባታ ሥራው የሚያስፈልገውን የገንዘብ ሀብት የሚያዘጋጅና ዋጋ የመክፈል ሃላፊነት ያለበት አካል ነው፡፡

ሥራ ተቋራጭ:-

ይህ ባለድርሻ አካል ከባለቤት ጋር በፈጸመው ውል ስምምነት መሰረት ለሥራው አስፈላጊ የሆኑትን ግብዓቶች በሙሉ በሟሟላት የግንባታ ሥራውን  በተባለው ጊዜና በተቀመጠው የጥራት ደረጃ ለመስራት ተዋውሎ የሚሰራ ነው፡፡

መሃንዲስ(አማካሪ):-

ይህ ባለድርሻ አካል ከባለቤት ጋር በፈጸመው ውል ስምምነት መሰረት ውለታውን እንዲያስተዳድር የሚቀጠር ነው፡፡ምንም እንኳን አማካሪ መሃንዲሱን የሚቀጥረውና ክፍያ የሚፈጸምለት በአሰሪው ቢሆንም፤ አማካሪው ውሉን በማስተዳደር ሂደት ውስጥ በቅን ልቡና በፍጹም ፍትሃዊነት ለሁለቱም የሚሰራ ነው፡፡

የመድን ዋስትና ሰጪ ድርጅቶች (Insurance Companies):-

አንድ ሥራ ተቋራጭ በጨረታ ለመሳተፍ፣ ወደውል ለመግባት፣ ክፍያዎች ለማግኘትና በሌሎች አሰሪው ድርጅት ለደህንነቱ መጠበቂያ ከስራ ተቋራጩ እንዲቀርብለት የሚጠይቀውን የመተማመኛ የመድን ዋስትናዎች ለሥራ ተቋራጩ የሚያቀርብ አካል ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሥራ ተቋራጩ በአጠቃላይ ለንብረቱ፣ ለገንዘቡ፣ ለስራውና ለሰራተኞቹ ደህንነት የሚጠይቃቸውን የመድን ዋስትናዎችንም (for Contractor’s all risks) የሚያቀርብ ይሆናል፡፡ አንድ የመድን ዋስትና ሰጪ ድርጅት አይነቱ ተለይቶ ለታወቀ ጉዳይ ለሥራ ተቋራጩ የመድን ሽፋን ሰጠ ማለት በአሰሪው ድርጅትና በሥራ ተቋራጩ በኩል ሊኖር የሚችለውን የአደጋ ስጋት ለመሸከም ሃላፊነት የሚቀበል ይሆናል ማለት ነው፡፡ ለወደፊት ስለግንባታ ፕሮጀክቶች የመድን ዋስትናዎች (Construction Insurances) በተብራራ ሁኔታ በምናቀርበው ጽሁፍ የምናየው ይሆናል፡፡

ባንኮች:-

ለሾል ተቋራጩም ይሁን ለስራው ባለቤት ለፕሮጀክቱ ማከናወኛ የገንዘብ ፍላጎቶችን በማመቻቸት የሚሰሩ ናቸው፡፡ ባንኮች እንደ የጨረታ ማስከበሪያና የውል ማስከበሪያ የባንክ ዋስትናም በመስጠት የሚሰሩ ናቸው፡፡ 

አቅራቢዎች (Suppliers):-

እነዚህ ባለድርሻ አካላት ለግንባታ ሼል ከመጀመሪያ እስከ ሥራው ፍጻሜ የሚያስፈልጉ ማናቸውንም ዓይነት የግንባታ ሼል ግብዓቶችን፣ ማሽነሪዎችን ወይም የግንባታ ሼል ቁሳቁሶችን በሽያጭና በኪራይ  የሚያቀርቡ ናቸው፡፡

ፈቃድ ሰጪ አካላት (Permitting bodies):-

ለግንባታ ሥራው የግንባታ ቦታ በመፍቀድ፣ የግንባታ ፈቃድ በመስጠት፣ የግብዓት ማውጫ ካባዎችን ፣የማምረቻ የማከማቻና የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ፈቃድ በመስጠት የሚሰሩ ናቸው፡፡

የመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅራቢ ተቋማት (Public):-

ለግንባታ ሥራው እንደ ውሃ፣መብራት፣ስልክ የመሳሰሉ ለግንባታ ሥራዎች የመሰረታዊ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ አካላት ናቸው፡፡

https://www.facebook.com/etconp/

https://youtube.com/@Etconp432
👍12🏆1
👍5❤2
👉ከ 90 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የሐዋሳ ከተማ መግቢያ ሚሊኒየም ፓርክ በነገው ዕለት እንደሚመረቅ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ አስታወቀ፡፡

የመምሪያው ምክትል ኃላፊ ታሪኩ ታመነ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በከተማው በ2014 የተጀመሩትን አብዛኛዎቹን ፕሮጀክቶች በዚህ ዓመት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ታቅዶ እየተሠራ ነው፡፡

በከተማ በተለይም በUIIDP የሚደገፉ 29 ፕሮጀክቶች መኖራቸው ጠቁመው፤ ከአስፋልት መንገድ ግንባታ ውጪ ያሉት ሌሎች ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቁ ገልጸዋል፡፡

ከኹሉም ለየት የሚለውና ጥቁር ውሃ መግቢያ በር ላይ እየተገነባ የሚገኘው ሚሊኒየም ፓርክ ሪስቶሬሽን ፕሮጀክት ለከተማውና ለክልሉ እንዲሁም እንደ አገርም ትልቅ ትርጉም ያለው ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡

ሰኔ 2014 የአንድ ዓመት የግንባታ ውል የተገባለት ፕሮጀክት ከ90 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበትም ገልጸው፤ ግንባታው በተያዘለት ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ግንባታ የሲዳማን ባህላዊ ዕሴቶችን ማሳየት የሚችልና በአሁኑ ወቅት ዓለም የደረሰበትን ሙሉ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የተገነባ እንደሆነም ያስረዱ ሲሆን፤ ወደ ሐዋሳ ከተማ መግቢያ በር የሆነው ፕሮጀክት በአገሪቱ ካሉት መሰል ፕሮጀክቶች የመጀመሪያው ይሆናል ብለዋል።

በጥቁር ዉሃ ዳቶ ሐዋሳ መግብያ በር ሙሉ በሙሉ ዲጂታል ተክኖሎጂ የተገጠመለት በመሆኑ ወጪና ገቢ የትራፊክ ፍሰት ከመቆጣጠሩም በላይ የከተማዉን ብሎም የህብረተሰቡን ደህንነት ለተጠበቀ ያግዛል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የመግቢያ በሩ በነገው ዕለት ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት በተገኙበት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል።

@etconp
👍7❤1
Forwarded from Ethio Construction Engineering (जॉर्डनो ג׳ורדנו ጆርዳኖ جوردانو จอร์แดโน่ JORDANO Ιορδάνοςஜார்டானோ)
Personal Information (ግላዊ መረጃ) ጨርሳችሁ ከዛም personal ability proof (የግል ብቃት ማረጋገጫ) ጨርሳችሁ ከሞላችሁ በኋላ ከዛም sample ካስቀመጣችሁ በኋላ ስራ ሲመጣላችሁ እንዲ ነው።

አሁንም አልረፈደም ተመዝገቡ አስፈላጊውን መረጃ አሟሉ ተጠቀሙ እራሳችሁን ገበያ ውስጥ ክተቱ

መመዝገብ ማለት ስም እና ስልክ አስቀምጦ መውጣት አይደለም ይሄ አቴንዳስ አይደለም ስራ ነው ስለዚህ እያነበባችሁ የተጠየቃችሁትን ግላዊ መረጃ እና የብቃት ማረጋገጫ በሙሉ አስገቡ አለበለዚያ incomplete ይሆናል እሱ ደግሞ ብዙ ተፎካካሪዎች ባሉበት መስክ ተመራጭ አያደርጋችሁም

ሊንክ:-https://m.buildmost.com/#/main_Promotion_page?code=U3WB0Y

ከዛም free register
👍2
Forwarded from Ethio Construction Engineering (जॉर्डनो ג׳ורדנו ጆርዳኖ جوردانو จอร์แดโน่ JORDANO Ιορδάνοςஜார்டானோ)
እንደምትመለከቱት ነው ሁሉም unsubmitted ነው ሚለው ….. እንዲህ አይነት ውዥንብሮችን ለማጥራት ቪዲዮ ያስፈልጋል ችግር የለውም እንሰራለን

እስከዛ ተመዝገቡ ከዚህ ሊንክ:- https://m.buildmost.com/#/main_Promotion_page?code=U3WB0Y
👉በግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ስለሚነሱ ቅሬታዎች /Claim/

🌟ክፍል አንድ

▶️ማንኛውም ሰው በማህበራዊ ኑሮ ውስጥ በሚገጥመው መስተጋብር የተለያዩ ጥያቄዎች ወይም መብቶች ሊኖረው ይችላል፡፡

ከዚህ ንድፈ ሃሳብ በመነሳት በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውም በርካታ ቅሬታዎች ወይም የመብት ጥያቄዎች መነሳታቸው  የማይቀር ክስተት ነው፡፡

እንደሚታወቀው የግንባታው ዘርፍ ብዙ ባለድርሻ አካላትን ማሳተፋ ብቻ ሳይሆን በተለያየ ሙያ ዘርፍ ውስጥ ያሉ ሰዎችንም  ጭምር የሚያሳትፍ ነው፡፡

ይህም በመሆኑም ከየባለድርሻ  አካላት በርካታ ቅሬታዎች መነሳታቸው የታወቀ ነው፡፡ ከዚህ ብሂል በመነሳት አንዳንዶች ከውል በመነጨ ጉዳይ የውል ቅሬታዎችን የሚያነሱ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ሕጉ አስቀድሞ ባስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ መሠረት ውል ሳይኖር አላፊነት በመኖሩ ምክንያት መብታቸውን ከውል ውጭ ሲጠይቁ ይስታዋላል፡፡

በሀገራችን ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ለሚነሱ አለመግባባቶች እና ቁርሾዎች እንደ ምክንያትነት የሚነሣው የቅሬታዎች ወይም መብቶች ጥያቄ ጉዳይ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም ቅድሚያውንም የሚወስዱት የቅሬታ መነሻዎች በተለይም ከሥራ ርክክብ መዘግይት እንዲሁም ከውል መለወጥ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጉዳዮች ናቸው፡፡

በሃገራችንም ምንም እንኳን ልማዱ በዓለም አቀፍ ሥራ ተቋራጮች በርከት ቢልም ቅሉ፤ የሃገር ውስጥ ሥራ ተቋራጮችም ቢሆን አሁን አሁን የተለያዩ የኮንስትራክሽን የመብት ጥያቄዎች ሲያስተጋቡ ይስተዋላል፡፡

በዋናነትም ለነዚህ የኮንስትራክሽን ሥራ ቅሬታዎች ወይም የመብት ጥያቄዎች መበራከት እንደ መነሻነት የሚቆጠሩት አንድም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ውስብስብነት፣ ከፍተኛ ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት መሆን እንዲሁም አሁን አሁን ሥራ ተቋራጮችም ሆነ ባለቤቶች ወደ ክስ እና ሙግት ሥነ ሥርዓት ልማድ ማድረግ እንደ ምክንያትነት ይወሰዳሉ፡፡

ከዚህ በመቀጠል የግንባታ ሥራዎች ላይ ስለሚነሱ ቅሬታዎች ምንነት ብሎም ፍረጃ እንዲሁም የኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ልማድ በሚከተሉት ክፍሎች በአጭሩ የምንዳስስ ይሆናል፡፡

🚧ትርጉም

⏺የግንባታ ስራ ላይ ቅሬታዎች ከተለያየ ምንጮች ሊመጡ ይችላሉ፡፡ ከውል፣ ከውል ውጪ እንዲሁም ከሕግ ሊመነጩ ይችላሉ፡፡

▶️ቅሬታ ማለት ምን ማለት ነው?     
  
Black’s law dictionary 9th edition የሚከተለውን ትርጉም ሰጥቶት እናገኛለን፡፡ â€œclaim is the aggregate of operative facts giving rise to a right enforceable by a court.” á‰…áˆŹá‰ł ማለት በፍርድ ቤት ሊፈጸም የሚችል በፍሬ ነገሮች የተደገፈ የመብት ጥያቄ ነው፡፡

ቪሰንት ስሚዝ የተባሉ ምሁር (civil Engineering Claims,1989) በሚለው መጽሐፋቸው የመብት ጥያቄ (Claim) የሚለውን ቃል እንደሚከተለው አብራርተውታል፡-

[C]laims are a general term for the assertion of a right to money, property or a remedy… [Sic] In relation to construction industry, claims means, a demand by a contractor for extension of time or for an extra payment of an item of work carried out by him on behalf of the employer for which a readily identifiable amount cannot be ascertained under the term of contract.”

እንደ ስሚዝ ገለጻ ከሆነ ቅሬታ ባጠቃላይ የገንዘብ፣ የንብረት እንዲሁም የካሳ ጥያቄ የሚስተናገድበት ሥርዓት መሆኑን ከገለጸ በኋላ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውም ሥራ ተቋራጩ አሰሪውን ለተጨማሪ ሥራው ተጨማሪ ገንዘብ እንዲሁም ጊዜ እንዲጨመርለት የሚጠይቅበት መንገድ እንደሆነ ያብራራሉ፡፡

ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው የመብት ጥያቄ የሚባለው አንድ ሕጋዊ የሆነን ነገር የምንጠይቅበት ሥርዓት መሆኑን አይተናል፡፡

እንደ ሲርስ ክላፍ (2008) እይታ ከሆነ አብዛኛውን ጊዜ የግንባታ ሥራ ቅሬታዎች የሚነሱት ከመጠን በላይ ያልተጠበቀ ወጪ ሲያጋጥም፣ ሥራው ያለአግባብ ሲሰራ፣ የሕጉ መወሳሰብ (legal entanglement) እንዲሁም የተለያዩ ሥራ ተቋራጮች አሉታዊ እንቅስቃሴዎችን እንደ ምክንያትነት ያስቀምጣል፡፡

የሚገርመው ነገር አልፎ አልፎ የመብት ጥያቄዎች በባለሃብቶች እና ማህንዲሶች ዘንድ በአይነ ቁራኛነት ሲስተዋል እናያለን ለምን ቢባል ይህ መንገድ አብዛኛውን ጊዜ የሥራ ተቋራጮች በመብት ጥያቄ ሽፋን አስቀድመው ያላነሷቸውን መብቶች ወይም ስህተቶች መሸፈኛ ስትራቴጂ ስለሆነ ጭምር ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የግንዛቤ እጥረት እንጅ እንደ ትክክለኛ አመክንዮ አይወሰድም ለምን ቢባል እንደሚታወቀው የመብት ጥያቄ የኮንስትራክሽን ሂደት አንኳር አካል ከመሆኑ በላይ ጥሩ የሚባል የመብት ጥያቄ እና የግጭት አፈታት ሥርዓት መኖር ለጥሩ ምህንድስና ብቻ ሳይሆን ለጠቅላላው ንግድም ሰናይ ነው፡፡

በቀጣይ ክፍል...

በግንባታ ፕሮጀክቶች፣ ቅሬታ ሊያስነሱ ስለሚችሉ ዋና ዋና ምክንያቶች

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

Twitter :- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
👍15
👉በግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ስለሚነሱ ቅሬታዎች/Claim/

🌟ክፍል ሁለት

▶️በግንባታ ፕሮጀክቶች የቅሬታ መነሻ ምክንያቶች

⏺በግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ቅሬታዎች የተለያየ መነሻ ምክንያት ይኖራቸዋል፡፡

የቅሬታ መነሻ ምክንያቶችን ጠንቅቆ ማወቅ፣ ቅሬታዎችን ለማስቆም ወይም ለመቅረፍ በምናደርገው ሂደት ውስጥ የመጀመሪያውን ደረጃ እንደመጓዝ
ይቆጠራል።

በግንባታ ፕሮጀክቶች፣ ቅሬታ ሊያስነሱ የሚችሉ ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

*በግንባታ ወይም በግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ መዘግየት ምክንያት/Delays in construction and completion of the contract/

*በግንባታ ግብዓቶች አቅርቦት መዘግየት ምክንያት/Delays in the delivery and supply of materials/

*የስራ ሂደት ሊያስተጓጉል የሚችል የአየር ንብረት ለውጥ ሲያጋጥም /Weather which slows down or prevents construction from proceeding/

*የአሰሪ የለውጥ ስራ ፍላጎት /Owner requested changes/

*ከአሰሪ ፍላጎት ውጪ የሚፈጠር አስገዳጅ የለውጥ ስራ/Changes which occur not at the request of the owner/

*ደካማ የሥራ አመራርና አስተዳደር/Poor management and administration of the construction site/

*የግንባታ ሥፍራው ሁኔታዎች/ Site conditions/ከተጠበቀው የተለየ ሁኔታ ሲያጋጥም ስራው ፈፅሞ ለመስራት አዳጋች ወይም ከባድ ሆኖ ሲገኝ/ The work becomes impossible to perform/

*የዕቅዶች እና መመዘኛዎች በበቂ ሁኔታ አለመቅረብ/Insufficient plans and specifications/

*ከባለድርሻ አካለት አንዱ ፣ለስራው አስፈላጊ ወይም ወሳኝ የሆነን መረጃ በጊዜው ሳያሳውቅ  መዘግየት ሲፈጠር
የግንባታ ፕሮጀክቱን ለማከናወን ማናቸውም ባለድርሻ አካላት ወይም ተሳታፊዎች መካከል በሚፈጠሩ ቅጭቶች ምክንያት/Conflicts between those involved in the construction of a project/

*በአሰሪው ወይም በሥራ ተቋራጭ በኩል ውል ለማቋረጥ መጠየቅ  /Termination of the contract by the owner or the contractor/

*ከውል መርሃ ግብር ውጪ በተፋጠነ የስራ ክንዋኔ ምክንያት/Acceleration of the work/

*በበቂ ሁኔታ አለማቀድና ሥራን አስተባብሮ መምራት አለመቻል ሲፈጠር/Failure to adequately schedule and coordinate the work/ እና

*የባለድርሻ አካላት መካከል ተናቦ ያለመስራት ወይም ያለመናበብ ችግር ሲፈጠር/Failure of parties to cooperate with each other in the performance of the work.

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

Twitter :- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
👏9👍7
👉ከግንባታ ፕሮጀክቶች ጋር ተያይዞ ስለሚሰጡ የዋስትና ዓይነቶች መጠነኛ ገለጻ [Construction Security]

🌟ክፍል አንድ

▶️በውል አፈጻጸም ወቅት የተለያዩ ዋስትናዎች ሲተገበሩ ይስተዋላል፡፡

⏺ለምሳሌ፡-
-የግምጃ ቤት ሰነድ (treasury bill)

-ማገቻ(bond)

-በቅድመ ሁኔታ የሚሰጡ ዋስትናዎች (conditional guarantees)

-ያለቅድመ ሁኔታ የሚሰጡ ዋስትናዎች (on demand/Unconditional guarantees)

- የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና (Bid security)

-የቅድመ ክፍያ ዋስትና((Advance security bond)

-የሰው ዋስትና (surety ship)

-የንብረት ዋስትና (pledge or mortgage)

-ራሳቸውን የቻሉ የብድር ሰነዶች ወይም ክሬዲት (Standby letters of credit) ወዘተ የመሳሰሉት ናቸው፡፡

አብዛኛውን ከላይ የተባሉት የዋስትና ሰነዶች በገንዘብ አበዳሪ ተቋማት እና ኢንሹራንስ ድርጅቶች ይዘጋጃሉ፡፡

ነገር ግን የሰው እና የንብረት ዋስትና ግን በግራ ቀኝ ተዋዋይ ወገኖች በራሳቸው አሊያም በሌላ ሦስተኛ ወገን አላፊነት ሊከናወኑ ይችላል፡፡

በውል አፈጻጸም ወቅት የዋስትና መኖር በተዋዋዮች ዘንድ ከፍተኛ መተማመን እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ሌላው የውሉን አፈጻጸም ተጠባቂ (predictable) እንዲሆን ያደርጋል፡፡

በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪም አንድ የፕሮጀክት ባለቤት ሥራው በተያዘለት ጊዜ እንዲያልቅ በማሰብ የፕሮጀክት አፈጻጸም ዋስትና አስፈላጊነት ትዝ ካለው፤ ለፕሮጅቱ የሚመቸውን የዋስትና ዓይነት ማለትም የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና፣ በገንዘብ አበዳሪ ተቋማት የሚዘጋጅ ዋስትና ወይም ክሬዲ አንዳንዴ ደግሞ የፕሮጀክቱን ክፍያ ገንዘብ በፐርሰንት መያዝ (retention) እንዲኖር ሊያስብ ይችላል፡፡

የሆነው ሆኖ እነዚህ የዋስትና መንገዶች ተመሳሳይ ዓላማ አላቸው፡፡ ይህም በተዋዋዮች መካከል መተማመን እና ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎች (risk) በመቀነስ ግብይትን ማፋጠን ነው፡፡ ዳሩ ግን እያንዳንዳቸው የራሳቸው ባህሪይ አላቸው ብሎም በአፈጻጸም እና አተገባበር የተለያዩ ናቸው፡፡ ስለሆነም አሰፈላጊነታቸው መታየት ያለበት እንደየ ፕሮጀክቱ አካሄድ፣ መጠን እና ጊዜ ሊሆን ይቻላል፡፡

በዓለምአቀፍ ደረጃ ባሉ ግብይቶችም የዋስትና ሰነዶች በጣም የተለመዱ ናቸው፡፡ በተለይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) የዋስትና ወረቀቶች እና ክሬዲ ሥምምነት (UN Convention on Independent Guarantees and Standby Letter of Cedit) በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ነው፡፡

ይህ ዓለምአቀፍ ሥምምነት እኤአ በ1995 በአሜሪካዋ የኒዮርክ ከተማ ለሥምምነት ክፍት የሆነ ሲሆን 8 (ስምንት) አገራት በመፈረምና በማጽደቅ ተቀብለውታል፡፡ ኢትዮጵያ ግን የዚህ ሕግ ፈራሚ አገር አይደለችም፡፡

ሆኖም ግን ይህ ሥምምነት በዓለምአቀፉ የንግድ ሕግ ኮሚሽን (United Nations Commission on International Trade Law/UNCTRAL) እንደመዘጋጀቱ መጠን ዋስትናን በተመለከተ በቀጣይ ሌሎች የዓለም ሀገራት ለሚያዘጋጇቸው ዝርዝር ህጎች በሞዴልነት እንደመነሻ ሊያገለግል ይችላል፡፡ በተለይ ስምምነቱን የፈረሙ አገራት በዓለምአቀፍ ደረጃ ለሚያከናውኗቸው የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ላይ ዋስትናን በተመለከተ ይህ ሕግ ተፈጻሚ ነው፡፡

ሌላው ዋስትና ሲነሳ ምንጊዜም ቢሆን አብሮ የሚነሳው የመድን ውል (insurance) ነው፡፡ ዋስትናም (security/guarantee) ሆነ መድን አንድ የሚያደርጋቸው ነገር አለ፡፡ ይህም ሁለቱም ባለመብቱን ሊደርስ ከሚችል የአደጋ ስጋት መጠበቃቸው ነው፡፡

ሆኖም ግን በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ሁለቱም የተለያየ የሕግ ውጤት ያላቸው ተግባራት ናቸው፡፡

ዋስትና:
በዋስትና ተግባር ዋስ የሚሆነው ግለሰብ የሚጠበቅበት ግዴታ ቢኖር ባለእዳው ለባለገንዘቡ በውል መሰረት ካልከፈለ ወይም መክፋል ካልፈለገ በሕግ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን ጠብቆ በባለእዳው እግር ተተክቶ ዕዳውን ሊወጣ የሚችልበት ሁኔታ ነው፡፡

መድን: 
መድን የገባ ሰው  መደበኛ የሆነ አረቦን (premium) መክፈል እንደተጠበቀ ሆኖ መድን በተገባለት ጉዳይ ሊደርሱ የሚችሉ  አደጋዎችን ይፋ ማድረግን ጨምሮ የመድን ጥቅም (insurable interest) ሊኖረው ግድ ይላል፡፡

በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪም ከላይ የጠቀስናቸው የዋስትና ዓይነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ አስፈላጊነታቸው እየታመነበት ስለመጣ በፕሮጀክት አፈጻጸም ወቅት ሲተገበሩ ይታያል፡፡

📌በ ክፍል ሁለት የዋስትና ምንነት ትርጉም እናያለን።

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

Twitter :- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
👍15