Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉"ፏፏቴ" ሕንፃ በቻይና

🚧ቻይና በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ ያስመዘገበችው ስኬት በአገሯ ብቻ ሳይሆን አሻራዋን በመላው አለም በማሳረፍ ትታወቃለች።

🌟ስሞኑን ደግሞ ከቻይና የተሰማው ወሬ "ወይ ጉድ ይኸች አገር" ብለን አፋችንን በእጃችን እንድንይዝ የሚያደርግ ነው።

🚧አሁን አሁን የቻይና የግንባታ ባለሙያዎች ከተለመደው የግንባታ ልማድ ወጣ ባለ መልኩ፣ አዳዲስ ፈጠራዎችን በሁሉም የግንባታ ሥራዎቻቸው ውስጥ ለማሳረፍ እየተጉ ይገኛሉ።

🚧በቅርቡም አዲስ የተገነባው ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ወደ ምድር የሚወረወር ፏፏቴ እንዲኖረውም አድርገው ገንብተውታል።

🚧ባለፏፏቴው ሕንፃ ከ350 ማይልስ ወይም ከ106 ሜትር የሚምዘገዘግ ፏፏቴ አለው። ውሃውን ወደ ላይ ለመውሰድ አራት ፓምፖች ተግባራቸውን ይወጣሉ።

🚧ከሁሉም ከላይ የሕንፃው ባለቤት "Guizhou Ludiya Property Management" እንደ ችግር ያስቀመጠው የኤሌክትሪክ ፍጆታውን ነው። ፏፏቴውን በሥራ ላይ ለማቆየት በሰአት 100 ዶላር ክፍያ አለበት።

🚧በዚህ የተነሳ ፏፏቴውን ሁሌም አንዲሰራ ማድረግ አዋጪ አይደለም። በአላትን እና ልዩ ፕሮግራሞችን ታሳቢ እየተደረጉ ፏፏቴው እንዲሰራ ይደረጋል ተብሎል። ሕንፃው የተገነባባት የጉያንግ ከተማ ከወዲሁ የቱሪስቶችን ቀልብ መሳብ ጀምራለች።

@etconp
👍13❤2
👉የኪነህንጻ ተማሪዎች አገር አቀፍ ማህበር

🚧የአሜሪካ ኪነህንጻ ተማሪዎች ማህበር ወይም American Institute of Architecture Students በ1956 እኤአ የተቋቋመ ጠንካራ የተማሪዎች ማህበር ሲሆን በአሜሪካ በኪነህንጻ ትምህርት ዙሪያ ከተቋቋሙ አምስት ጠንካራ ተቋማት አንዱ ነው።

🌟አላማውን ተልእኮውንና ራዕዩን በተመለከተ ከታች የተያያዘውን ድረገጽ ማየት ይቻላል።

🚧በተረፈም በአሜሪካን ግዛቶች ባሉ ሁሉም የኪነህንጻ ትምህርት ቤቶች በተያያዘው ምስል መልክ የአባልነትና የተሳትፎ ጥሪ ያቀርባል።

🫵የአገራችንም የኪነህንጻ ተማሪዎች ከዚህ አንጋፋ ማህበር ትምህርት ቀስመው አገርአቀፍ ማህበር ሊፈጥሩ ይችላሉ።

https://www.aias.org/

@etconp
👍8
የህዳሴው ግድብ የቴክኒክ ባለሙያዎች የሶስትዮሽ ድርድር ዳግም ተጀመረ

ኢትዮጵያ የግድቡን የዘንድሮ ውሀ ሙሌት ወደ መስከረም አራዝሜያለሁ ማለቷ ይታወሳል

ኢትዮጵያ በድንበር ተሻጋሪው አባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በተለያዩ ምክንያቶች መቋረጡ ይታወሳል።

በሱዳን እና በኢትዮጵያ የተከሰተው የፖለቲካ አለመረጋጋት ለሶስትዮሽ ድርድር አለመቀጠል እና የግብጽ ተለዋዋጭ አቋም ማሳየት ለድርድሩ አለመሳካት ዋነኞቹ ምክንያቶች ነበሩ።

ከአንድ ወር በፊት በግብጽ ካይሮ በሱዳን ለተከሰተው ጦርነት እልባት ለመፈለግ በሚል በተካሄደው የጎረቤት ሀገራት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ወደ ስፍራው ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) እግረ መንገዳቸውን ከፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ  አልሲሲ ጋር መክረዋል።

በዚህ ስምምነት መሰረትም የሶስቱ ሀገራት የህዳሴ ግድብ የቴክኒክ ባለሙያዎች በግብጽ መዲና ካይሮ ተገናኝተዋል።

የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን በዛሬው ውይይታቸው በቀጣይ ስለሚደረጉ ድርድሮች፣ የመወያያ አጀንዳዎች፣ እና በሶስቱ ሀገራት ልዩነቶች ዙሪያ እንደሚወያዩ ተገልጿል።

ከ12 ዓመት በፊት የተጀመረው ታላቁ የህዳሴው ግድብ ግንባታ 84 በመቶ ደርሷል የተባለ ሲሆን የግድቡ ሁለት ተርባይኖች ሀይል በማመንጨት ላይ ናቸው።

በጣልያኑ ሳሊኒ የግንባታ ተቋራጭ ኩባንያ እየተገነባ ያለው የህዳሴው ግድብ አራተኛው የግድቡ ውሀ ሙሌት ከቀናት በኋላ እንደሚጀመር ይጠበቃል።

@etconp
👍14❤1
👉የግንባታ ወጪን ለመቀነሰ የሚረዱ አማራጭ ዘዴዎች

🌟ለህንፃ ግንባታ የሚያስፈልጉ እንደ ብረት፣ ሲሚንቶ፣ ብሎኬት፣ ጠጠር ያሉ ጥሬ ዕቃዎች ዋጋ እ.ኤ.አ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ከ1000 ፐርሰንት በበለጠ ዋጋ እየጨመረ የመሄዱ ጉዳይ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡

⏺ለዚህ መንስኤ በዋነኝነት የሚጠቀሱት የማምረቻ፣ የሠራተኛ ጉልበት፣ የትራንፖርት ዋጋ መጨመር እና ተያያዥነት ያለው የዋጋ ግሽበት ናቸው፡፡

▶️የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ልዩ ባህሪ ደግሞ ጥሬ ዕቃዎችን በመግዛት እና በመደባለቅ፣ ጠንካራ ረጅም ዕድሜ የሚኖረው እና ውብ የሆኑ ህንፃዎችን መገንባት ነው፡፡

▶️ከዚህ በመነሳት የኮንስትራክሽን ኤክስፐርቶች የጥሬ ዋጋ ንረትን በመቋቋም ወጪን ለመቀነስ ያስችላሉ ብለው በቀዳሚነት ያስቀመጧቸውን አሠራሮች መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

🚧 ጠንካራ የዕቅድ ፕላን መዘርጋት

እንደ ማንኛውም የንግድ ዘርፍ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ የመጨረሻ ልብ ማትረፍ ነው፡፡ ይህንን ትርፍ ለማግኘት ለግንባታው የሚያስፈልገውን በጀት እና ዝርዝር የግንባታ ሂደቶች የተመለከተ ጠንካር ያለ የዕቅድ ፕላን መቀየር ነው፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከሚያስችሉ ጠንካር ያሉ የዕቅድ ፕላኖች ውስጥ ጥሬ ዕቃዎችን ካለው  ነባራዊ ሁኔታ በመመርመር ቀደም ብሎ ማከማቸት በእያንዳንዱ የግንባታ ሂደት የሚያስፈልጉ ግብዕቶችን ቀደም ብሎ ማዘጋጀት ናቸው፡፡

🚧 መደበኛ የሆነ እና የሚደጋገም ዲዛይን

አንድ ህንፃ ከመሬት ተነስቶ እያደገ በሄደ ቁጥር፣ የሚይዛቸው የክፍል ገፅታዎች መደበኛ የሆነ ስፋት እና ገፅታ የተለበሱ እንደሆኑ ማድረግ ዋጋን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

ህንፃው ባደገ ቁጥር የውስጥ ገፅታ ዲዛይን የሚለዋወጥ ከሆነ፣ የጥሬ ቁስ ብክነት ያስከትላል፡፡ ለተለዋጭ ዲዛይን የሚሆን ሌላ ጥሩ ቁስ መግዛትን ይጠይቃል፡፡

እስከ ዘለቄታው ለግንባታ የሚያገለግሉ ቁሶችን ቀደም ብሎ ማከማቸት እንዳይቻል ያደርጋል፡፡ ለግንባታ የሚያስፈልጉ መሣሪያዎች በየጊዜው እንዲለዋወጡ ያደርጋል፡፡ የሥራ ፍጥነት እና ሂደትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ጋሬጣ ይፈጥራል፡፡

🚧 አማራጭ ቁሶችን መጠቀም

በህንፃ ግንባታ ህንፃው ለወደፊት የሚሰጠውን አገልግሎት ከግምት በማስገባት ረሳይክልድ የሆኑ ብረቶችን ከጂፕሰም እና ከጣውላ የሚዘጋጀ የውስጥ ማከፋፈያ ግርግዳዎችን መጠቀም፣ ተገጣማሚ ብሎኬቶች እና ግርግዳዎችን መጠቀም የህንፃው የግንባታ ዋጋ እንዲቀነስ ያደርጋሉ::

🚧 የግንባታ ባለሙያዎች ወጪን መቀነስ

የግንባታ ሂደትን በጊዜ ሰሌዳ ሸንሽኖ አስፈላጊውን ቁስ ቀደም ብሎ በማሟላት፣ ለግንባታው የሚያስፈልገውን ባለሙያ በጊዜው በመቅጠር ግንባታ የሚያስፈልግ የጉልበት (የሙያ) ክፍያ ወጪን በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ ይረዳል::

🚧 ጊዜ እና ገንዘብን መቆጠብ

ለግንባታ የሚያስፈልጉ እና ሥራን የሚያቀላጥፉ እንደ ሎደር፣ ኤክስካቫተር፣ ፓሌት (የብረት ምንጣፍ) የኮንክሪት ምንጣፍ ተሻካሚ፣ ተገጣጣሚ ብረቶችን፣ ግንባታው ሳይቋረጥ በሚፈለግበት ጊዜ ወዲያው የሚቀርቡበትን ቀደም ያለ ዝግጅት ማድረግ ለግንባታ የሚያስፈልግ ጊዜ በመቆጠብ፣ በፍጥነት ወደሚፈለገው ትርፋማ ጉዞ ለማምራት በተዛማጅነትም ወጪን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ ብርሃን የሚያስገቡ መስታወቶችን እና የፀሀይ ብርሃንን ወደ ኤሌክትሪክ የሚለውጡ ግርግዳዎችን ማካተት፣ ህንፃው ከተጠናቀቀ በኃላ ዘላቂ የኃይል ፍጆታ (ገንዘብ) እንዲቆጠብ ያደርጋል፡፡

@etconp
👏5👍4
👉 የሕዳሴ ግድብን አራተኛ ዙር የውሃ ሙሌት መጀመሩን ተሰማ።

🌟የግድቡ የዘንድሮ ክረምት ውሃ ሙሌት በነሃሴና መስከረም እንደሚካሄድ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እንዲኹም ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ ቀደም ሲል መናገራቸው ይታወሳል።

🚧የውሃ ሙሌቱ በሰከንድ 1 ሺህ 200 ሜትር ኪዩብ መኾኑን ዋዜማ ተረድታለች።

🚧መንግሥት ግድቡ በዘንድሮው ክረምት እንዲይዝ ያቀደው የውሃ መጠን፣ ከ10 ነጥብ 8 እስከ 11 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ ነው።

Via wazema Radio

https://youtube.com/@Etconp432
❤3👍2
👉ጃካርታ -ኢንዶኔዢያ፤ አሁን ይህ የሚያምር የደሴት ከተማ ነው እየሰመጠ በመሄድ ላይ የሚገኘው

🌟ውብ ቀን ተመኘን❤

@etconp
👍8💔7😢2🏆1
"Oresund Bridge" ይባላል። በሲዊዲን እና ዴንማርክ መካከል ነው የሚገኘው። ይህ ድልድይ በአውሮፖ አህጉር በባህር ውስጥ የተገነባ ረጅሙ ነው።

ድልድዩ መነሻውን ከሲዊዲን ያደርግና በባህር ውስጥ የውስጥ ለውስጥ ዋሻ አድርጎ ዴንማርክ ውስጥ ብቅ ይላል።

ሁለቱም አገሮች ለዚህ ድንቅ ኢንጂነሪንግ አበርክቶአቸው ላቅ ያለ ነው። በጠቅላላው የድልድዩ ርዝመት 16 ኪሎ ሜትር ሲሆን፣ ሁለቱን አገሮችን በኦሬሱንድ ሰርጥ በኩል እንዲገናኙ ያደረገ ነው።

ድልድዩ የተገነባው እ.ኤ.አ በ2000 ዓ.ም ነው።  በመርከብ ብቻ ይገናኙ የነበሩት ሁለቱ አገሮች ከዚያ በኃላ መንገደኞችን በሚያጎጉዙ ባቡሮችና መኪናዎች አገልግሎት እያገኙ ነው።


@etconp
❤10👍7
👉ስለ ኮንስትራክሽን ይህን ያውቁ ኑሮዋል?

1. የዓለማችን ረዥሙ ክሬን 53.3 ሜትር ድረስ ከፍ ማለት ይችላል።  ብራንዱም Liebherr type HC-L ነው።

2. በ2018 በመላው ዓለም ለኮንስትራክሽን የወጣው ገንዘብ 11.4 ትራሊየን ዶላር ሲኾን በ2030 17.5 ትሪሊየን ዶላር እንደሚደርስ ይገመታል።

3. በኤምፓየር ስቴት ሕንጻ ላይ 10 ሚሊየን ጡቦች ይገኛሉ።

4. ከግንባታ ዕቃዎች መካከል በቀዳሚነት ጥቅም ላይ የሚውለው ኮንክሪት ነው።

5. በዓለም ዙሪያ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚሠሩ ሰዎች ቁጥር 180 ሚሊየን ይገመታል
።

@etconp
❤8👍2
Flood got into commercial building in Uganda 🇺🇬

በ ኡጋንዳ ጎርፍ የንግድ ማእከል ውስጥ ገባ

@etconp

To watch the video:- https://youtube.com/shorts/jD6o9sy53rc?si=sX4CmB8VFm2xPTDB

ቪዲዮ ለመመልከት:- https://youtube.com/shorts/jD6o9sy53rc?si=sX4CmB8VFm2xPTDB
👍3👏2
👉ይህንን ያውቃሉ?

🚧የዓለማችን ረጅሙ ድልድይ

🌟ዱግ ድልድይ የሚገኘው በቻይና ሲኾን የጉይዡና ዩናን ግዛቶች መካከል ቤይፒን ወንዝ ላይ የተሠራ ነው።

▶️ከወንዙ በላይ ያለው ከፍታ 565 ሜትር ያህል ሲኾን ይህም ከዓለማችን ድልድዮች በከፍታ አንደኛ ደረጃ ላይ አስቀምጦታል።

⏺ይህ ከፍታ በህንጻ ይመሰል ቢባል ከባለ 200 ወለል ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ጋር መሳ ለመሳ ይኾናል።

⏺ምስራቃዊ የድልድዩ ተሸካሚ ማማም 269 ሜትር ከፍታ በመያዝ ከዓለም ከቀዳሚዎች ተርታ የተመዘገበ ኾኗል።

⏺የድልድዩ ርዝመት 1341 ሜትር ሲኾን ይህም ከተንጠልጣይ ድልድዮች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጠዋል።

▶️ግንባታው በ2012 ተጀምሮ በ 2016 ነው የተጠናቀቀው።

@etconp
❤7👍4👌1
🌟ዘሕጉስ ብስራት

👉ኣብ ክልል ትግራይ እትነብሩ ቤተሰብና እትደልይዎ ዝኾነ ይኹን ዓይነት ናይ ኮንስትራክሽን ፋይል ማለት እውን ሶፍትዌር ምስ ቲቶርያል ከምኡ ውን ናይ ትምህርታውን ሞያውን PDF እንተደሊኹም ብ ውሽጢ መስመር ርኸቡና።

📩 @Philemona7 ፀሓፉልና🙏

🚧ናብ ኩለን ዩኒቨርስታት ትግራይ ክባፃሕ Share ግበሩልና።

🌟በ ትግራይ ክልል የምትኖሩ የ CIVIL፣COTEM፣ARCHITECTURE እና በመሳሰሉ ለተሰማራቹ ተማሪዎች እና ባለ ሞያዎች የምትፈልጉት ማነኛውም ፋይል ጠይቁን

@etconp
🙏10👍5👌2
👍9
👉የፕሮጀክት ማናጀሮች የበጀት እጥረት

🌟በአገራችን ውስጥ የግንባታ ፕሮጀክት ማናጀሮች ከሚገጥማቸው ችግሮች አንዱ ለግንባታ የተመደበ በጀት መቀነስ ወይም የበጀት ዕጥረት ነው፡፡

▶️አንድ የፕሮጀክት ማናጀር በጀት ሲቋረጥበት ወይም ሲቀነስበት በተረጋጋ መንገድ ፕሮጀክቱ ሥራውን እንዲቀጥል ለማድረግ ከሚረዱት መንገዶች አምስቱ የሚከተሉት ናቸው፡፡

🚧1. አለመደናገጥ

⏺የፕሮጀክት ማናጀሩ የበጀት መቀነስ መረጃ ሲደርሰው በቅድሚያ ማድረግ የሚገባው ችግሩ የተለመደ እና የሚያጋጥም መሆኑን በመቀበል መረጋጋት ነው፡፡ አለበለዚያ የፕሮጀክቱ ማናጀሩ ድንጋጤ እና ግራ መጋባት የሚመራውን የግንባታ ቡድን ተስፋ እንዲቆርጥ እና ቀና አለመካከት እንዲያጣ በማድረግ፣ ሠራተኞች ሥራውን ለቀው ሌላ አማራጭ እንዲፈለጉ እና ግንባታው እንዲስተጓጎል የሚያደርግ ተፅእኖ ውስጥ ይወድቃል፡፡

🚧2. በጀቱ የተቀነሰበትን ምክንያት መረዳት

⏺ማናጀሩ ራሱን በማረጋጋት የሥራው ሂደት በተረጋጋ መንፈስ እንዲካሄድ ካደረገ በኃላ፣ ቀጣይ ሥራው በጀቱ የተቀነሰበትን ምክንያት መረዳት እና ራሱን እንደ ውሳኔው አካል በመቁጠር ከሠራተኞች ለሚቀርብለት ጥያቄ ተአማኒነት ያለው መረጃ መስጠት ነው፡፡

🚧3. ሥራው እንዲቀጥል ርምጃዎችን መውሰድ

⏺በበጀት መቀነስ ምክንያት ሥራው እንዳይቋረጥ ለማድረግ መወሰድ ከሚገባቸው ፈጣን ርምጃዎች ውስጥ፣ በቀጣይ ሂደት የፕሮጀክቱን ግንባታ የማያስተጓጉሉ ወጪዎችን እና የሠራተኛ ኃይል መቀነስ ይሆናል፡፡

🚧4. ከአስገንቢ ድርጅቶች ጋራ ተቀራርቦ መሥራት

⏺ከአስገንቢ ድርጅት ባለሃብት ወይም ከመንግስት አካል ጋር ተቀራርቦ በመሥራት ጉድለቱን የሚሸፍኑ አበዳሪ እና ስፖንሰሮችን በማፈላለግ ሥራው እንዳይቋረጥ ማድረግ ይገባዋል፡፡

🚧5. በቀረው በጀት ፕሮጀክቱ የሚጠናቀቅበትን መላ መዘየድ

⏺ፕሮጀክቶች ከመነሻው ሲቀረፁ በሂደት ሊገጥሙ የሚችሉ እንቅፋቶችን ታሳቢ ተደርገው ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ የታሰበው በጀት ባይገኝ፣ ፕሮጀክቱን በጊዜው እንዴት ማጠናቀቅ ይቻላል የሚል ነው፡፡

▶️ከዚህ መሠረታዊ አሠራር በመነሳት የበጀት እጥረት የገጠመው የፕሮጀክት ማናጀር፣ ለግንባታ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን የሚቀንሱ አማራጮችን በመጠቀም እና በተለያዩ ምዕራፎች በመከፋፈል ሥራውን የሚያጠናቅቅበትን መፍትሄ በፍጥነት በመዘየድ ሥራውን ማስቀጠል ይጠበቅበታል፡፡

📩እርስዎም ሀሳብዎን ያጋሩ

@etconp
👍9👏3❤2😢1🏆1
👉የ Scholarship ጥቆማ

🟨Qatar University Graduate Scholarships 2023-24 Details:
➖️University: Qatar University
➖️Degree level: Master’s, PhD, PharmD, Diploma
➖️Scholarship coverage: Fully Funded
➖️Eligible nationality: International
➖️Award country: Qatar
➖️Last Date: 5 October 2023

🟨Types of Scholarships in Qatar University:
Multiple Scholarships are offered at Qatar University. The Details of each scholarship at the Qatar University is given below:

🟨Competitive Scholarships
➖️Qatar University Scholarship (Internal Scholarships, External ➖️Scholarships)
➖️H.H. the Emir of Qatar’s Scholarships for Academic Excellence
➖️Outstanding Performance Scholarship

🟨Non-Competitive Scholarships
➖️GCC States Scholarships (Embassies)
➖️GCC Qatari Certificate Scholarships
➖️Children of Qatar University Employees Scholarships

🟨Other Scholarships
➖️College of Education Diploma Scholarships
➖️Short Scholarships for the Arabic Program for Non-Native Program

➖️International Students and Qatar Residents are Eligible. All Nationalities are Welcome.
➖️Applicants who have earned a Bachelor’s or Graduate Degree from an accredited institution of higher education.

Apply here:
https://mybanner.qu.edu.qa/PROD/bwskalog.P_DispLoginNon

Official website:
http://www.qu.edu.qa/students/admission/graduate/application-timeline

Image: University of Qatar.
Aug. 30. 2023!

Good luck and have a good day!
👍3🙏2