Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉አንዳንድ እውነታዎች ስለ ታላቁ የ ህዳሴ ግድብ
.
🚧ግንባታው የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠበት እለት - መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም::
.
🚧የግንባታው ስፍራ፡-በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጉባ ወረዳ::
.
🚧የዋናው ግድብ ከፍታ - 145 ሜትር
.
🚧የዋናው ግድብ ርዝመት - 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር
.
🚧የዋናው ግድብ ውፍረት - የግድቡ ግርጌ 130 ሜትር ሲሆን የግድቡ ጫፍ ወይም የላይኛው
ክፍል 11 ሜትር
.
🚧ግድቡ የሚይዘው የውሃ መጠን - 74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር
.
🚧ግድቡ የሚሸፍነው የቦታ ስፋት 1 ሺህ 680 ስኩዌር ኪሎ ሜትር
.
🚧ሲጠናቀቅ ውሃ የሚተኛበት መሬት ርዝመት 246 ኪሎ ሜትር
.
🚧የኮርቻ ግድብ /Saddle Dam/ ከፍታ- 50 ሜትር

🚧የኮርቻ ግድብ /Saddle Dam/ ርዝመት 5 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር
.
🚧ግድቡ16 የኃይል ማመንጫ ዩኒቶች አሉት እያንዳንዱ ዩኒት የሚያመነጨው የኃይል መጠን ከ375 እስከ 400 ሜጋ ዋት::
.
🚧ጠቅላላ ግድቡ ሲጠናቀቅ የሚያመነጨው ኃይል መጠን 6 ሽህ 450 ሜጋ ዋት
.
🚧ከ500 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ማልማት ያስችላል::

🚧ከ10 ቶን በላይ ዓሳን ማምረት ያስችላል::

🚧74 ቢሊዬን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም አለው::

🚧ከ40 በላይ ደሴቶች ይኖሩታል።

🚧ከግድቡ የውሃ ላይ የትራንስፖርት፣ የአሳ ልማትና ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ አገልግሎት ይውላል።

🚧ታዳሽ ኃይል በመሆን የከባቢ ብክለትን ይከላከላል።

🚧የከተሞችን ተሞክሮ በመቀመር በአዲሱ የህዳሴ ሐይቅ ዙሪያ ዘመናዊ ከተማ ለመመስረት
ያስችላል።

🚧አጠቃላይ ግንባታው የደረሰበት ደረጃ- 93%

🚧ግድቡ በትልቅነቱ በአፍሪካ አንደኛ ደረጃን ይዟል።

🌟ይቀጥላል.....

ምንጭ፡-ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት

@etconp
👍26❤6
🌟በሐረሪ ክልል በ3.3 ቢሊየን ብር ባለ18 ወለል ያለው የመንግሥት ተቋማት ሕንፃ ለመገንባት አስፈላጊ ሂደቶች መጠናቀቃቸው ታውቋል።

ለሕንፃ ግንባታው የተወዳደሩ አለም አቀፍ ተጫራቾች እና ታዛቢዎች በተገኙበት የጨረታ ሰነድ ተከፍቷል።

በክልሉ የመጀመሪያው እና ግዙፉ ህንፃ 7ሺ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ G+18 ከ200 በላይ የመኪና ማቆሚያ ያለው እና የከተማውን ውበት የሚያጎላ እንዲሁም የክልሉን በኪነ ህንፃው የሚያስተዋውቅ ዘመናዊ እንደሚሆን ታውቋል።

በዛሬው እለትም ለህንፃ ግንባታ የሚሆን አለም አቀፍ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲወዳደሩ በማድረግ ባለድርሻ ተቋማት በተገኙበት ተከፍቷል።

ኮሚቴው በጨረታው የተወዳደሩ አሸናፊ ድርጅትን በቅርቡ የሚያሳውቅ ሲሆን፣ ይህ የሕንፃ ግንባታ በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።


@etconp
❤5👍2
በአዲስ አበባ በ30 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው የአረጋውያን መጠለያ ተመረቀ

የአረጋውያን የመጠለያ እና የመጦሪያ ማዕከል ግንባታ ተጠናቆ በዛሬው ቀን ተመርቆ አገልግሎት ጀምሯል።

ማዕከሉ 730 አረጋዊያንን የመቀበል አቅም ያለው ሲሆን በውስጡም የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ክሊኒኮችና መድሃኒት ቤት፣ ዘመናዊ ላውንደሪ፣ ማብሰያና መመገቢያ ስፍራዎች፣ የእደ ጥበብ መስሪያ ክፍል ይዟል። ማዕከሉን በቋሚነት በገቢ እንዲደግፍ ባለ ሶስት ወለል ህንፃም ይዟል ፤ከህንፃው የሚገኘው ገቢ ሙሉ በሙሉ ማዕከሉን የሚደግፍ ይሆናል።

ማዕከሉ ለ730 አረጋውያን እንክብካቤ የማድረግ አቅም አለው መባሉን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ማዕከሉ የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ክሊኒኮች፣ ፋርማሲ፣ ምግብ ማብሰያ፣ መመገቢያ አዳራሽ፣ መኝታ ቤት፣ የልብስና የአረጋውያን ንፅህና መጠበቂያ፣ የዕደ- ጥበብ መስሪያ እና የመዝናኛ ቦታዎችን ያከተተ መሆኑም ተጠቅሷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምረቃ ሥነ - ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ዛሬ የተመረቀው ማዕከልም በ630 ሚሊየን ብር የሰንሻይን ፊላንት ሮፒ ፋውንዴሽን ግንባታውን በጥራት በማጠናቀቅ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ስለተወጣ እናመሰግናለንም ብለዋል።

@etconp
❤9👍1
👉በ2016 በጀት ዓመት 902 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎች ለማከናወን ታቅዷል

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባስልጣን በ2016 በጀት ዓመት 902 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎችን ለማከናወን በዕቅድ ይዟል፡፡

በበጀት ዓመቱ 31.62 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 22.39 ኪ.ሜ የጋራ መኖሪያ ቤቶች መንገድ፣ 49.19 ኪ.ሜ የጠጠር፣ 48.36 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገዶች መልሶ ግንባታ ለማከናወን ታቅዷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ 95 ኪ.ሜ የኮብል ንጣፍ መንገዶች ግንባታ እና 1.88 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመር ግንባታ የሚከናወን ሲሆን፣ በጠቃላይ በበጀት ዓመቱ 248.44 ኪ.ሜ የሚሸፍን የመንገድ ግንባታ ሥራዎች ለማከናወን ታቅዷል፡፡

በሌላም በኩል ባለስልጣኑ በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ 102 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 35 ኪ.ሜ የጠጠር፣ 80 ኪ.ሜ የኮብል መንገዶች ጥገና ለማካሄድ ታቅዷል፡፡

ከአጠቃቀም ጉድለት በተደጋጋሚ ጉዳት እያጋጠማቸው የሚገኙትን የመንገድ ዳር የውሃ መፋሰሻ መስመሮች በመፈተሸ 349.36 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና ጥገና እንዲሁም 13.5 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ጥገና ይከናወናል፡፡

የትራፊክ አደጋን ከመቀነስ አኳያ 65.92 ኪ.ሜ የሚሸፍን የነባርና የአዳዲስ መንገዶች የትራፊክ ቀለም ቅብ ስራ እና 8 ኪ.ሜ የእግረኛ መከላከያ አጥር ስራ፤ በድምሩ 654 ኪ.ሜ ልዩ ልዩ የመንገድ ጥገና ስራ በበጀት ዓመቱ ለማከናወን ታቅዷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በቁጥር 22 ድልድዮች እና 16 ሺህ የመንገድ ዳር መብራቶች ጥገና በዕቅዱ ከተካተቱ ዋና ዋና ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

@etconp
👍5❤1
👉ETCONp TIP

🌟12 ways to get everything you want.

▪️1. Those who succeed in life are those who are not afraid to dream big and then take risks to fulfill their visions.

▪️2. When you are ready to give up, you are closer to the goal than you think.

▪️3. Why put off your greatness until later? Why wait for a better time to fulfill your dreams and those wonderful opportunities that life opens up for you? Why not take the first step today?

▪️4. Everything you think about comes true.

▪️5. Follow your dreams and the universe will open doors for you where there were only walls...

▪️6. Twenty years will pass, and you will regret more what you didn't do than what you did wrong. So put aside hesitation. Set sail and run away from safe harbor. Catch a fair wind. Explore. Dream. Make discoveries.

▪️7. It is much better to burn out in flight and crash down, pursuing a high goal, than to spend the best days of your life in front of the TV somewhere in the back of life. (Actual for 95% of the population).

▪️8. Everything that exists in the world was once just a dream...

▪️9. The one who does expects success. The one who “tryes” expects something to interfere with him.

▪️10. Take it and do it. If you don't know what to do, take a step forward.

▪️11. Having a goal is more important than having an opportunity.

▪️12. Bold and brightly drawn dreams come true at least 110%. You will always receive + 10% in the form of additional bonuses from Life at the exit of your dreams.

@etconp
👍12❤3
👉እንድታውቁት

🌟በድሬዳዋ አስተዳደር ኢንዱስትሪ መንደር የተገነቡ 253 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በእጣ ለእድለኞች ሊተላለፉ መሆኑን የኮንስትራክሽንና ቤቶች ቢሮ አስታውቋል።

🚧በዚህም መስፈርቱን ላሟሉ ቅድመ ቆጣቢዎች ዕጣ የሚተላለፈው መስከረም 20 / 2016 በኢትዮ ጣሊያን ኮሌጅ አዳራሽ ሲሆን የእጣ አወጣጥ ሥርዓቱን መከታተል እንደሚቻል ቢሮው አስታውቋል።

@etconp
👍5❤1🙏1
👉በዓባይ ግድብ ሃይል የሚያመነጩ ተርባይኖችን ቁጥር 7 ለማድረስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
*****
በዓባይ ግድብ ሃይል የሚያመነጩ ተርባይኖችን ቁጥር 7 ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡

በ2014 ዓ.ም ሃይል ማመንጨት ከጀመሩት ሁለት ተርባይኖች በተጨማሪ በያዝነው 2016 በጀት ዓመት 5 ተርባይኖችን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ነው፡፡ 5ቱ ተርባይኖች ወደ ስራ ሲገቡ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ያላትን 4 ሺህ 818 ሜጋ ዋት የሃይል አቅርቦት መጠን ከፍ ያደርገዋል ብለዋል ፡፡

ወደ ስራ ከገቡት ሁለት ተርባይኖች አንጻር ዘንድሮ ወደ ስራ የሚገቡት 5ቱ ተርባይኖች ሃይል መጠን የበለስ ፣የግልገል ጊቤ አንድና ሁለት እንዲሁም የተከዜ የሃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ከሚሰጧቸው አማካይ 1 ሺህ 180 ሜጋ ዋት ተመጣጣኝ ወይም የሚበልጥ ሃይልን ያመነጫሉ ብለዋል።

ይሁንና ከአቀማመጡና ከውሃ ፍሰቱ አኳያ የእነዚህን አምስቱ የሃይል ማመንጫ ተርባይኖች ሃይል የማመንጨት አቅም አሁን ላይ ይህን ያህል ነው ብሎ መናገር እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡

እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ የግድቡ ግንባታ ሲጠናቀቅ በ13ቱ ተርባይኖች 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይልን ወደ ብሄራዊ የሃይል ቋት እንደሚቀላቀልም ነው ሚኒስተሩ የገለጹት፡፡ በዚህም እያንዳንዳቸው ተርባይኖች በአማካይ ከ375 በላይ ሜጋ ዋት ሃይልን ያመነጫሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@etconp
👍12
👉የጨረታ ማስከበሪያ/bid bond/
 ለምን አስፈልገ?


🚧የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና አይነት ነው፡፡

➢ ለግንባታ ጉዳይ ጨረታ ተሳታፊ የሚሆን ተጫራች ተቋራጭ የሚያቀርበውና ተጫራቹ እንደፈለገ ጨረታውን አቋርጦ እንዳይቀር ለማድረግ እና ምናልባት ተቋራጩ በጨረታው ቢያሸንፍ ውል እንዲገባ ማስገደጃና ዋስትና እንዲሆን ጨረታውን ባወጣው አካል የሚያዝ ዋስትና ነው፡፡

☞ይህንኑ በሚደግፍ ሁኔታ በፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001ዓ.ም አንቀጽ 40 ላይ ተደንግጓል፡፡

➢የዚህ ድንጋጌ ይዘትም ተጫራቹ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት በኋላ ውሉን ለመፈረም ፈቃደኛ ካልሆነ ወይም እንዲያቀርብ የተጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ካላቀረበ ወይም የጨረታ ማስከበሪያው ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ተጫራቹ ራሱን ከውድድሩ ያገለለ እንደሆነ የጨረታ ማስከበሪያው ጨረታውን ባወጣው የመንግስት መስሪያ ቤት የሚወረስ ስለመሆኑ የሚገልጽ ነው፡፡

☞ጨረታ የሚያወጡ መስሪያ ቤቶችም በሚያዘጋጁት የጨረታ ሰነድ ላይ ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ አብረው ማቅረብ እንዳለባቸው ሊገለጽ ይገባል፡፡የጨረታ ማስከበሪያው መጠንም ጤነኛ ባልሆነ እና ቅንነት በጎደለው ሁኔታ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስቡትን ተጫራቾች ወደጨረታው እንዳይገቡ ከወዲሁ ለማስቀረት የሚያስችል መሆን ይኖርበታል፡፡

☞ለአሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በምን ሁኔታ መገለጽ አለበት?በህጉ አግባብ ያለመገለጽ ውጤቱስ?(Announcing the successful bidder)

☞ለአሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ መገለጽ ያለበት እና ሊደርሰው የሚገባ በጽሁፍ በደብዳቤ መልክ ነው፡

➢የደብዳቤውም ይዘት የመንግስት መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የተቀበለው ስለመሆኑ፣የአሸነፈበትን ዋጋ፣አሸናፊው ተጫራች ማቅረብ ያበትን የውል ማስከበሪያ መጠን(Amount of performance security) የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡(Federal public procurement directive:አንቀጽ 16.24 እና አዋጅ ቁጥር 649/2001ዓ.ም አንቀጽ 46) ስለዚህ በህጉ አግባብ አሸናፊነቱ ያልተገለጸለትን አሸናፊ ተጫራች ውል አልተዋዋለም በማለት የጨረታ ማስከበሪያ መውረስ የሚቻል አይሆንም ማለት ነው፡፡

#ConstructionLaw

@etconp
👍8🙏4❤2
🌟ሐላላ ኬላ ሪዞርት - ዳውሮ

ከአአ 450 ኪሜ በደቡብ ምዕራብ ክልል በዳውሮ ዞን በጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ አመካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ዳርቻ የሚገኘው የሀላላ ኬላ ቅንጡ ሪዞርት።

ይህ ሪዞርት የተገነባው ቦታ - ታላቁ የዳዉሮ ግንብ ካቲ ሃላላ፣ አስደናቂው ግልገል ግቤ ሶስት የሃይል ማመንጫ፣ ልብ የሚሰዉረዉ ጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ እንዲሁም በባህል የበለፀገው ፃራ ማህበረሰብ በአከባቢው የሚገኙ መስህቦች ናቸው።

ይህ ሪዞርት 12 ሄክታር ላይ ያረፈ የንጉስ ሃላላ ግንብና ለምለም ኮረብታዎች  ያጀቡት ጥንታዊ ቦታ ላይ የታነፀ ውብ ማረፊያ ነው።

ሪዞርቱ የአከባቢዉን ባህላዊ ስነ ህንፃ ከዘመናዊዉ ጋር ያማከለ የቤቱ ውስጣዊ ክፍል አየር በደምብ እንዲያገኝ ጣራው ከፍ ብሎ የተሰራ 2 ፕሬዚዳንሻል፣ 10 ፋሚሊ፣  2 የጥንዶች ማረፊያ እና 2 የዋና ገንዳ ስቲም ሳውና ማሳጅ ክፍሎች፣ ዘመናዊ ስብሰባ አዳራሽ፣ ሙዚየም ከሪዞርቱ በስተደቡብ ሳተላይት የእንግዳ መቀበያ በስተደቡብ ሳንሴት መዝናኛ ያሉት ድንቅ ሪዞርት ነው።

መልካም ቀን

@etconp
❤8👍7👏1
👉ተቋራጭን ከሳይት ስለማባረር/Expel right/  By: Gubaie A.
          ---------   ---------------   ----  
📜በዚህ ጽሁፍ ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብት ለማን የተሰጠ ነው?በየትኛው ህግ?በምን ሁኔታ?በየትኛው የውል አይነት?በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት?የሚሉትን በአጭሩ ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡

*ይህ መብት ያለው የትኛው አካል ነው? የሚለውን በተመለከተ ተቋራጭን ከግንባታ ሳይት/ከግንባታ ስፍራ ለማባረር መብት ያለው አሰሪው ነው ስለዚህ መብቱ የግንባታው ባለቤት ወይም የአሰሪው ነው፡፡

⏺ስለዚህ ይህን መብት ተቋራጮች ሆኑ አሰሪ ያልሆነ ሌላ አካል ተግባራዊ ሊያደርገው አይችልም ማለት ነው፡፡
.
*በየትኛው ህግ? ለሚለው ምላሹ በፍትሀብሄር ህጉ እና በጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት ነው፡፡በዝርዝር ሲታይ፡-

▶️በግንባታ ውሎች በተለይ ጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት መጠቀም የተለመደ ነው፡፡እነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች በራሳቸው ህግ አይደሉም፡፡እዚህ ላይ አንዳንድ የህግ ባለሙያዎች እንደ መመሪያ እና ህግ ስለሚቆጥሩት ይህ የግንዛቤ ክፍተት መታረም ይኖርበታል፡፡የግንባታ ውል ተዋዋዮች በስምምነታቸው እነዚህን ጀኔራል ኮንዲሽኖች የውሉ አካል ሲያደርጓቸው በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731 መሰረት በተዋዋዮች መካከል እንደ ህግ ሆነው ይቆጠራሉ፡፡እዚህ ላይ ሌላው ጉዳይ ስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ተብለው የሚቀመጡት ከጀኔራል ኮንዲሽኑ ድንጋጌዎች የተፈጻሚነት ቅድሚያ ይኖራቸዋል፡፡ለምሳሌ ከነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ውስጥ የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/Standard condition of contract for the construction of civil work projects/ አንዱ ነው፡፡ይህ ጀኔራል ኮንዲሽን በከተማ ልማት ሚኒስቴር በኩል የተዘጋጀ ሲሆን ይዘቱ በዋናነት ከFIDIC 1987 version የተወሰደ ነው፡፡

በአብዛኛው MoWUD 1994 ተብሎ ይጠራል፡፡ሆኖም ዋናው ነጥብ ተዋዋዮች ጥቅም ላይ ያዋሉትና የውላቸው አካል ያደረጉት የትኛውን ጀኔራል ኮንዲሽን እንደሆነ መለየትና ማወቅ የግድ ይላል፡፡

⏺ከዚህ አንጻር MoWUD 1994 ክሎዝ 63 ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብትን አስመልክቶ በዝርዝር አስቀምጦታል፡፡በዚህ ድንጋጌ መሰረት በዋናነት አማካሪ መሀንዲሱ ለአሰሪው የተቋራጩን እንደውሉ ያለመፈጸም ሲያሳውቅ በተለይም ተቋራጩ ስራውን እንደተወው አማካሪው ሲያስታውቅ፣ተቋራጩ በአማካሪ መሀንዲሱ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ለ28ቀናት ስራውን ሳይጀምር ሲቀር፣በመሀንዲሱ ተቀባይነት የላቸውም የተባሉ የግንባታ ቁሳቁሶችን በ28 ቀናት ውስጥ ከሳይት ያላስወጣ እንደሆነ፣በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ስራውን በውሉ አግባብ ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልሆነ እንደሆነ፣አማካሪ መሀንዲሱ እየከለከለው የስራውን ክፍል ለሌላ ተቋራጭ አሳልፎ የሰጠ እንደሆነ ወይም ተቋራጩ የከሰረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት ማባረር የሚችል ይሆናል፡፡በዚህ ጊዜ ውሉ ይቋረጣል ማለት ነው፡፡/Termination of contract/
በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3288 አና ተከታዮቹ ላይ የተደነገገውም ተቋራጩ የውል ግዴታውን ባልፈጸመ ጊዜ የግንባታ ባለቤት ለሆነው ለአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ስራውን ከተቋራጩ ለመንጠቅ እና ውሉ ሳይቋረጥ ስራው በስራ መሪ ስር ሆኖ እንዲቆይ ለማድረግ መብት ይሰጠዋል፡፡እንዲሁም ውሉ ሊሰረዝ የሚችልበት ፈቃጅ የውል ቃል በግንባታ ውሉ ላይ ያለ እንደሆነ አሰሪው ቀሪውን ስራ ለሌላ ተቋራጭ በጨረታ ወይም በስምምነት በማሰራት እንዲጠናቀቅ ማድረግ ይችላል፡፡/የፍ/ህ/ቁ 3291(1) በዚህም ምክንያት አሰሪው ለተጨማሪ ወጭ/Additional cost/ የተዳረገ እንደሆነ ከተቋራጩ ላይ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 3291(2) በግልጽ መብት ይሰጠዋል፡፡ሆኖም በውል ህግ ላይ አሰሪው የተቋራጩን ግዴታ በሚያከብድ ሁኔታ ቀሪውን ስራ ማከናወን እንደሌለበት የሚያስገነዝበውን ግዴታውንም ማክበር አለበት፡፡

በየትኛው የውል አይነት? ለሚለው በዋናነት የአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ውሎችን በሚመለከት ሊተገበር የሚችል ነው፡፡ በግል የግንባታ ውሎች/private construction contract/ በተለይ ከፍ/ህ/ቁ 2610 እና ተከታዮቹ እንዲሁም ከፍ/ህ/ቁ 3019 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ውስጥ ተቋራጭን ስለማባበር አስመልክቶ ግልጽ ድንጋጌ አለመኖሩ ይህ መብት ለግለሰቦች ለመተግበር አስቸጋሪ የመሆኑን ሁኔታ ታሳቢ ተደርጐ በህግ አውጭው በማወቅ/ፐርፐዝሊ/ የተተወ ይመስላል፡፡ተዋዋዮች የግንባታ ውል ሲዋዋሉ ጀኔራል ኮንዲሽን ቢጠቀሙና በዚህም ስለተቋራጭ የማባረር መብት ድንጋጌ ቢኖረውስ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል?ይሄን እንዴት ይተገብረዋል የሚለው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ውሉ ግን ለተዋዋዮች ህግ ስለሚሆን በተቻለ መጠን ሊተገበር ይገባዋል የሚል እሳቤ አለኝ፡፡  

በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት? ለሚለው በዋናነት በ MoWUD 1994 ክሎዝ 63(2) ላይ እንደተቀመጠው በግንባታ ሳይት ላይ የተገኘ ቁሳቁስ በሙሉ በዝርዝር መመዝገብና ዋጋ ወጥቶለት መጠኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡በተቋራጩ የተሰራው ስራ መጠን/level of work done/ በትክክል መታወቅና በዝርዝር መመዝገብ አለበት፡፡ተቋራጩ ያለበት እዳ/ከወሰደው የቅድሚያ ክፍያ ውስጥ ያልመለሰው ማለት ነው/ መታወቅ አለበት ለተቋራጩ የተከፈለው የስራ ክፍያ ሊታወቅ ይገባል፡፡
እነዚህን የሂሳብ ሁኔታዎች አመዛዝኖ እና ዋጋ አስቀምጦ ተቋራጩ የሚከፈለው ገንዘብ ካለ እንዲከፈለው ለአሰሪው የሚመልሰው ገንዘብ ካለም እንዲመልስ ሂሳብ የማስተሳሰብና ሪፖርት የማቅረብ ሀላፊነቱ የአማካሪ መሀንዲሱ ነው፡፡
በዚህ ረገድ አማካሪ መሀንዲሶች ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ሪፖርት ስለማያቀርቡ የግንባታ ክርክሮች ያልተሸከፉ ይሆኑና ለፍርድ ቤቶች ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ አስቸገሪ ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡

አሰሪው ይህን መብቱን ለመጠቀም ሀይል መጠቀም የሚችልበት ግልጽ ፈቃጅ ህግ ግን የለም፡፡

በመጨረሻም አሰሪና ተቋራጮች ለግንባታ ጥራት በመስራትና ለትክክለኛ እና እውነተኛ ነገር በመተባበር የኮንስትራክሽኑ ዘርፍ እድገት እንዲያሳይ ማገዝና አለመግባባቶችን በስምምነት መፍታት ቢችሉ ጠቀሜታው ለሀገርም ለራሳቸውም ነው፡፡

በአሰሪና ተቋራጭ ክርክር ብዙ ትምህርት ቤት እና የጤና ተቋም እንዲሁም ሌሎች መሰረተ ልማቶች ግንባታቸው ተቋርጦ ማህበረሰቡን ከተጠቃሚነት የሚያዘገይበት ሁኔታ ወደፊት ተቀርፎና ተቃልሎ ማየት የዘወትር ምኞታችን ነው፡፡

#ConstructionLaw

@etconp
👍17❤6🔥1