Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉ከኮንስትራክሽን ዋስትና አፈጻጸም ወቅት በተግባር የሚስተዋሉ ተግዳሮቶች

✳️በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዲስትሪ ገና ዳዴ እያለ ያለ የኢኮኖሚ ዘርፍ ነው፡፡ ሆኖም ግን ዘርፋ ከጠቅላላው የአገር ውስጥ ምርት (Gross Domestic Product) ያለው ድርሻ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው፡፡

✳️ዳሩ ግን በዘርፋ የሚታዩ በርካታ ተግዳሮቶች አሉ፡፡ ከእነዚህ ችግሮችም ከኮንስትራክሽን ዋስትና ጋር የተያያዙም ይገኙበታል፡፡ ለምሳሌ፡-በመንግስት የጋራ ቤቶች ግንባታ የዋናው ገንዘብ መያዣ (retention) የፕሮጀክቱ ግንባታ ተጠናቆ የጊዜያዊ እና የመጨረሻ ርክክብ ከተፈጸመ በኋላ የተያዘው 5(አምስት) ፐርሰንት ገንዘብ አብዛኛውን ጊዜ ተመላሽ አይሆንም፡፡

✳️ሌላው በኢትዮጵያ አብዛኛው የግንባታ ውሎች የመንግስት ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ በተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች ከግዥ እና ውል አስተዳደር ያለው ከፍተኛ ሙስና እና ብልሹ አሰራር ከላይ የተባሉትን የዋስትና መንገዶች በአግባቡ እንዳይተገብሩ የሚያደርግበት ሁኔታ አለ፡፡

✳️ሌላው ድግሞ በፍ/ቤቶች ዘንድ የሚታዩ የአተረጓጎም ክፍተቶች ናቸው፡፡ ወሰኑ ያለየለት የኮንስትራክሽን ዋስትና በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ነው፡፡ ለምሳሌ፡-በአንድ የኮንስትራክሽን ፕሮጅክት አፈጻጸም የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትናን በተመለከተ በንግድ ሕግ ወይስ በፍትሐብሔር ሕግ ይገዛ የሚለው ነጥብ ነው፡፡ በተለይም የመድን ድርጅቶች ከሚሰጧቸው ዋስትናዎች ጋር ተያይዞ የሚነሳ ክርክር ነው፡፡ ይህም የሚሆነው በመድን ድርጅት የወጣ ቦንድን እንደ የመድን ሥራ አድርጎ የመቁጠር አዝማሚያ አለ፡፡

✳️በእርግጥ በአሁኑ ጊዜ የመድን ድርጅቶች ያለቅድመ ሁኔታ ዋስትናዎችን ጨምሮ የገንዘብ እዳ ማስከበሪያ ቦንድ ከማውጣት ቢከለከሉም በቅድመ ሁኔታ የተመሰረቱ ቦንዶች ማውጣት ይችላሉ፡፡ ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ስመለስ የሰው ዋስትናም ሆነ የመድን ውል ሁለቱም የካሳ ውሎች (contract of indemnity) ናቸው፡፡ እንዲሁም ምንጫቸው ከተለየ ልዩነታቸውን ማቋቋም የሚከብድ አይደልም፡፡

⏺የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና አብዛኛውን ጊዜ በችሮታ (gratuitous) ሊቋቋም ይችላል፡፡ በፋይናንስ ተቋማት በሚዘጋጅበት ጊዜ ድግሞ በክፍያ (consideration) ይሆናል፡፡ በዚህ ሳቢያ ለተባለው የፍይናንስ ተቋም ኮሚሽን ሊከፍል ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ተፈጻሚ ሊሆን የሚችለው የሕግ ማዕቀፍ የፍትሐብሔር ሕግ ከአንቀጽ 1920-1951 ያለው ነው፡፡ በእርግጥ የፍትሐብሔር ሕጉ ድንጋጌዎች በፍይናንስ ተቋማት በሚሰጡ ዋስትናዎች ላይ ሙሉ በሙሉ ባይፈጸምም የግዴታውን ሁኔታ ይገዛል፡፡

✳️በአንጻሩ ግን የመድን ግዴታ ቀዳማዊ እንጂ ደባል አይደለም፡፡ ተራ የውል ጥሰትም የመድን ውል ተፈጻሚ ሊያደርግ አይችልም ለምን ቢባል በቅን ልቡና መግባትን ጨምሮ የመድን የሚገባበት ጥቅም መኖር (insurable interest) ግድ ይላል፡፡ ስለሆነም ተገቢውን የሕግ ማዕቀፋ ከጉዳዩ አላማ ጋር ታይቶ ትርጉም ቢሰጠበት መልካም ነው፡፡

✳️ሌላው ደግሞ የመልካም ሥራአፈፃፀም ዋስትና በመድን ድርጅቶች በሚሠጥበት ወቅት እስከ -------- ብር ተብሎ የሚገለፅ ሲሆን፣ በአሠሪዎች በኩል ያለው ሃሣብ ግን ሙሉ ክፍያው ስለተሠራው ስራም ሆነ ስለደረሠው ጉዳት መጠን ከግምት ሣይገባ እንዲከፈል የሚጠየቅበት ሁኔታ እና የቅድሚያ ክፍያ ለሥራ ተቋራጩ በሚሠጥበት ጊዜ ስለተጨማሪ እሴት ታክስ መታከል ወይም ያለመታክል ወጥ አሠራር ያለመኖርን በተግባር ማየት ይቻላል፡፡

✳️በመጨረሻም በአገራችን የዋስትና ገበያ የመንግስት ክትትል አናሳ መሆን ነው፡፡ ለምሳሌ፡- በኮንስትራክሽን ዘርፍ ሥራ ተቋራጩ በርካታ ሠራተኞችን በሥሩ ቀጥሮ ሊያሰራ ይችላል፡፡ ዳሩ ግን በሠራተኞች የማጭበርበር ወይም ብልሹ አሰራር ምክንያት ለሚደርስበት ጉዳት ማካካሻ የሚሆን የመተማመን ዋስትና (Fidelity bond) አለመኖር ተጠቃሽ ነው፡፡ ⚠️በዚህ ሳቢያ ብዙ ሥራ ተቋራጮች የመክስር አደጋ ተጋርጦባቸዋል፡፡⚠️

🌟ማጠቃለያ
:-ዋስትና በውል አፈጻጸም ወቅት እንደ ተጨማሪ(ደባል) የሚቆጠር ግዴታ ነው፡፡ ባለዕዳው በውሉ መሰረት ላለበት ግዴታ ማስከበሪያ የሚሆን ዋስ ጠርቶ የባለገንዘቡን ስጋት የሚቀንስበት መንገድ ነው፡፡ ዋስትና ዓይነቱና መልኩ ይለያይ እንጂ ሁሉም ዓይነት ዋስትና ቀዳማዊው ግዴታ ባለመፈጸሙ የሚከተል ግዴታ ነው፡፡ ዋስትና ከሚሰጠው ፈርጀ ብዙ ጥቅም አንጻር የሰው፣ የንብረት፣ የፍይናንስ እንዲሁም የኮንስትራክሽን ብለን መፈረጅ እንችላለን፡፡ በእርግጥ የኮንስትራክሽን ዋስትና በአተገባበሩ በአንድ በኩል የሰው ዋስትና የሚመስል ይዘት ያለው ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ አብዛኛውን የኮንስትራክሽን ዋስትና የሚሰጠው በፋይናንስ ተቋማት በመሆኑ ወሰኑን በወል መለየት አዳጋች ያደርገዋል፡፡ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የታወቁ የዋስትና ዓይነቶች የሚባሉት የውል ማስከበሪያ፣ የጨረታ ማስከበሪያ፣ የቅድሚያ ክፍያ፣የዋናው ገንዘብ መያዣ እና የጥገና ብልሽት ዋስትናዎች ናቸው፡፡ ዳሩ ግን በተግባር አብዛኛውን ጊዜ የመንግስት ፕሮጀክቶች ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ውልን በሚያስተዳድሩና ጨረታን በሚመሩ ሰዎች ከሕግ የወጡ ሥራዎች ሲሰሩ ይስተዋላል፡፡ በተለይም የዋና ገንዘብ ዋስትና(retention) በጊዜዉ አለመመለስ አንዳንዴም የውሃ ሽታ ሆኖ መቅረት ተጠቃሽ ነው፡፡ ሌላው ጉልህ ችግር በሥራ ተቋራጮች ለሚደርሱ ከሠራተኛ ጋር የተያያዙ ጥፋቶችን ለመቀነስ
⏺የመተማመኛ ዋስትና (fidelity bond) ቢጀመር መልካም ነው፡፡

▶️በመጨረሻም መንግስት የዋስትናን ገበያ ከፍተኛ ድጋፋ ቢያደርግ እና የግሉን ዘርፍ ቢያጠናክር አሁን ያለውን የዋስትና ሽፋን ያጠናክራል የሚል እምነት አለኝ፡፡

#ConstructionLaw

@etconp
👍4❤2
👉አስገዳጁ የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ

✳️የመድን ውል ዓይነቶች በርካታ ናቸው፡፡ ለአብነት ያህልም የህይወት መድን፣የንብረት መድን፣የአደጋ መድን፣የባህር መድን፣የኮንስተራክሽን መድን ወ.ዘ.ተ በፖሊሲው የተመለከተውን ስያሜ በመያዝ ይጠራል፡፡

✳️የኮንስትራክሽን መድን የሚባለውም በግንባታ ወቅት ለሚደርሱ አደጋወች እንዲሁም ጉዳቶች በአሰሪው ወይም በሥራ ተቋራጮች የሚገቡት የኢንሹራንስ ሽፋን ነው፡፡

✳️በሃገራችን 🇪🇹በቅርብ ጊዜ የሚሰሩ ህንጻወች ለሚያደርሱት ጉዳት የመድን ሽፋን እንዲገቡ ለማሳሰብ እና ያሉትን ህግጋት ለመዳሰስ ያህል:-

1. 📌ጽንሰ ሃሳቡ

✳️ኢንሹራንስ ልክ እንደሌሎች የንግድ ግብይቶች ሁሉ በፖሊሲ መልኩ ሲቋቋም ተዋዋይ ወገኖችን የሚያስገድድ ውል ነው፡፡ በ1952ዓ.ምበወጣው የኢትዮጵያ የንግድ ህግም ኢንሹራንስን በተመለከት በአንቀጽ 654(1) ላይ የሚከተለውን ትርጉም ሰጥቶት እናገኛለን፡-

✳️"የኢንሹራንስ ፖሊሲ ውል ማለት ኢንሹራስ ሰጪ የሚባለው ባአንድ ወይም በብዙ የተመደበውን የኢንሹራንስ መግቢያ ዋጋ(ፕሪሚየም) ተቀብሎ በውሉ የተመለከተው አደጋ በደረሰ ጊዜ ኢንሹራንስ ለገባው ሰው የተወሰነ ገንዘብ ለመክፈል ግዴታ የሚገባበት ውል ነው፡፡ ”
✳️ከላይ በተሰጠው ትርጓሜ መሰረት ኢንሹራስ የሚከተሉት ባህሪያት አሉት፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ኢንሹራንስ የሚቋቋመው ቢያንስ ሁለት አካላት ማለትም ውል ሰጪው (የኢንሹራንስ ኩባንያ/insurer) እና ውል ተቀባዩ(insured) መካከል ነው፡፡ ሁለተኛ የኢንሹራንስ ውልየሚደረገው በጋራ ድርድር የሚዘጋጁ ውሎች(consultation contracts)ሳይሆን አስቀድሞ የተወሰነ ውል(Adhesive contract) ነው፡፡ በመሆኑም ውል ተቀባዩ አይቶ ከተመቸው የሚቀበለው ካልፈለገ ደግሞ የሚተወው ውል(accept or leave it) የሆነ ውል ሲሆን ውል ተቀባዩ የመደራደር አቅሙ ዝቅተኛ ነው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በትርጉም ወቅት መጣረስ ቢመጣ ውል ተቀባዩን በሚጠቅም መልኩ መተርጎም እንደአለበትየኢትዮጵያ ፍትሃብሄር ህግ አንቀጽ 1738 ንባብ መረዳት ይቻላል፡፡

✳️ሌላው መለያው የግራ ቀኙ ግዴታ ነው፡፡ ይህም የውሉ ዋና ጉዳይም አደጋ በሚደርስበት ጊዜ የኢንሹራንስ ኩባንያው ለተጎጅው በውሉ መሰረት መካስ ሲሆን በአንጻሩ ደግሞውል ተቀባዩ በየጊዜው በገባው ውለታ መሠረት አረቦን(Premium) የመክፈል ግዴታ እንዳለበት መረዳት ያስፈልጋል፡፡

✳️በሌላ በኩል Black’s Law dictionary (9ኛ እትም ገጽ 870) ላይ የሚከተለው ትርጉም አስፍሮ እናገኛለን፡-
“Insurance is a contract by which one party (the insurer) undertakes to indemnify another party (theinsured) against risk of loss, damage, or liability arisingfrom the occurrence of some specified contingency,and usuallyto defend the insured or to pay for a defenseregardless of whether the insured is ultimately foundliable. An insured party usuallypays a premium to theinsurer in exchange for the insurer's assumption of theinsured's risk.”

↪️በዚህም መሰረት ኢንሹራንስ ማለት አንድ አካል በየጊዜው ለሌላኛው አካል በሚከፍለው አረቦን መሰረት ውል ሰጭው (insurer) ለሚደርሱ ጉዳቶች ካሳ የሚከፍልበት ውል እንደሆነ መገንዘብ እንችላለን፡፡

በተመሳሳይ መልኩ የቢዝነስ ህግ መዝገበ ቃላት የሚከተለውን ትርጓሜ ሰጥቶት እናገኛለን፡-
“Insuranceis contract (i.e., insurance policy) under which the insurer (usually an insurance company) agrees for a fee (i.e., insurance premiums, normally paid at fixed intervals) to pay the insured party all or a portion of any loss suffered by accident, negligence or death. Insurance premiums vary according to the insurer’s estimate of the probability of the event insured against actually happening.”

ይህምበኢንሹራስ ፖሊሲው መሠረት አንድ የኢንሹራንስ ኩባንያ ለውል ተቀባዩ አደጋ በደረሰ ጊዜ ሊከፈል የሚገባው ውል እንደሆነና ውል ተቀባዩም በአንጻሩ በየጊዜው አረቦን ለመክፈል የሚገባው ውል እንደሆነ መዝገበ ቃላቱ ያስረዳናል፡፡

2. 📌የኢንሹራንስ መሰረታዊ መርሆች

✳️ኢንሹራንስ ከተለያዩ አገራት ህግጋት ልማድ (comparative study) እንዲሁም የፍርድ ውሳኔዎች ተሞክሮ አንጻር የሚከተሉት የታወቁ መሰረታዊ መርሆች እና አስተሳሰቦች አሉት፡፡

ሀ) የጉዳት ካሳ መርሆ(Principle of Indemnity): -ይህ መርሆ የሚያስገነዝበው የኢንሹራንስ ውል ዋስትና በተሰጣቸው አደጋዎች ምክንያት የሚደርስን የገንዘብ ጉዳትን ለመተካት እና ለመካስ የሚደረግ ውል ነው፡፡ ለዚህም ነው የኢትዮጵያ ንግድ ህግ በአንቀጽ 678 ላይ ኢንሹራንስ የገባ ዕቃ ማለት እቃው ካሳ ለመጠየቅ የተገባ ውል ነው በማለት ያስቀመጠው፡፡ ዳሩ ግን ካሳው ዕቃው አደጋ በደረሰበት ቀን ዋጋ በላይ ሊሆን አይችልም፡፡

ለ) ኢንሹራንስ ሊገባበት የሚችል ጥቅም መኖር መርሆ/insurable interest/፡-ይህ ደግሞ ኢንሹራንስ ለመግባት አንድ ሰው መብት ወይም ጥቅም ሊኖረው ይገባል፡፡ ይንን አስመልክቶም የንግድ ህጉ በአንቀጽ 675 ላይ የሚከተለውን ድንጋጌእናገኛለን፡-

✳️ዕቃውን ከጉዳት ለመጠበቅ የሚፈልግ ማነኛውም ሰው ኢንሹራንስ ሊያስገባው ይችላል፡፡
ጉዳት እንዳይደርስ በማለት ማነኛውም ቀጥተኛ ወይም ቀጥተኛ ያልሆነ ጥቅም ሁሉ ኢንሹራንስ ሊገባበት ይችላል፡፡
በአጠቃላይ በዚህ መርሆ መሰረት ኢንሹራንስ ለመግባት የሚከተሉት ጉዳዮች እንደ ቅድመ ሁኔታነት ይነሳሉ፡፡ ለምሳሌ፡-የንብረት መብት፣ጥቅም ፣በሕይወት መኖር እና ዋስትና መሻት፤ንብረቱ ወይም ጥቅሙ የኢንሹራንሱ ዋና አካል መሆን አለበት፤ኢንሹራንስ በተገባለት ጉዳይ እና በውል ተቀባዩ መካከል ህጋዊ ግንኙነት መኖር እንደ የንብረት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት…ወዘተ አስፈላጊ መሆናቸውን ይህ መርሆ ይጠቁመናል፡፡

ሐ) በቅን ልቡና መግባት መርሆ(Utmost good faith):-ኢንሹራንስ የሚገባ ማነኛውም ሰው ስለሚገባበት ጉዳይ ለኢንሹራንስ ኩባንያው በቅንነት እና በእውነት (latin: Uberrima fides)ላይ የተመሰረት ነገር መናገር ይጠበቅበታል፡፡ ይህም ጉዳይ በንግድ ሕጋችንከአንቀጽ 667-669 ተመልክቷል፡፡

መ) የዳረጎት መርሆ(The Principle of Subrogation):-ይህ መርህ የሚያስገነዝበው ኢንሹራንስ ኩባንያው ለሶስተኛ ወገኖች ጉዳት አላፊነት በመውሰደ ማለትም በእነሱ ስም ከተዳረገ (subrogation) በኋላ ጉዳት አድራሹን አካል የመጠይቅ ህጋዊ መብት አለው፡፡ ይህም በንግድ ህጉ አንቀጽ 683 በግልጽ እንደተመለከተው የኢንሹራንስ ኩባንያው ለደረሰው ጉዳት ለውል ተቀባዩ ከከፈለ በኋላ ጉዳት አድራሹን ሦስተኛ ወገን ለመጠየቅ መብት አለው፡፡👇👇👇
👍5❤2
3. 📌የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ ምንነት

✳️በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ኢንሹራንስ አንዱ የአደጋዎች (risks) ማስተላለፊያ መንገድ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ ዋና ዓላማ አደጋን በሚያጋጥምበት ጊዜአሰሪዎች፣ተቋራጮች፣ንዑስ-ተቋራጮች እንዲሁም በግንባታ ወቅት ድርሻ ያላቸው ሌሎች አካላት አደጋንወደ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሚያስተላልፉበት መንገድ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ኢንሹራንስ የአደጋ መከላከያ መንገድ እንጂ ምትክ አይደለም፡፡ ለምን ቢባል ኢንሹራንስ በአብዛኛው ጊዜየሚሸፍነውየታወቁ እና ሊካሱ የሚችሉ አደጋወችን ነው፡፡

✳️በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ ሲባል በፕሮጀክት ግንባታ ወቅት ለሚደርሱ ጉዳቶች የሚደረጉ የመድን ውሎች ሲሆን ኢንሹራንስም የአደጋ ማስተላለፊያ መንገድ ተብሎ ሲመረጥ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡
(C)onstruction insurance means all contracts of indemnity within the activities of the construction industry where insurance is chosen as the medium through which liabilities are shifted.”

✳️ምንም እንኳን የኢትዮጵያ የንግድ ህግ ስለ ኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ በግልጽ ባይደነግግም ከአንቀጽ 676 ምንባብ መረዳት እንደሚቻለው በኮንስትራክሽን ፕሮጀክቱ አፈጻጸም ወቅት ለሚደርሱ ጉዳቶች ሽፋን ሊያገኙ እንደሚችሉ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ነገር ግን በኢንሹራንስ ፖሊሲው በግልጽ ለእነዚህ አደጋዎች ተብሎ መገለጽ ይኖርበታል፡፡ ሌላው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በጣም ውስብስብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስን በተመለከተ ከመደበኛው የንግድ ሕግ ለየት ያሉ ሕግጋት ያስፈልጋል፡፡

✳️ አንድ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት በሚከተሉት ጉዳዮች ኢንሹራንስ ሽፋን ሊያገኝ ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡-ለንብረት ጉዳት፣ለሦስተኛ ወገን ጉዳት፣በጉዞ ላይ ላሉ ዕቃዎች/goods in transit/፣በሚገነባው ህንጻ ላይ ለሚደርሱ ጉዳቶች/damage to constructional plant/፣ታስቦ ለሚፈጸሙ አደጋዎች…ወዘተ መሰል ጉዳዮችን ያጠቃልላል፡፡

✔️ለማጠቃለል ያህል የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ ሲባል አደጋን ለመቀነስ በማሰብ ወይ በሥራ ተቋራጮች አሊያም በአሠሪወች ሥራው ከመጀመሩ በፊት የሚገባ የመድን ዓይነት ነው፡፡

4. 📌የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ ጠቀሜታ

✳️በ አንድ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ህንፃ ተደርምሶ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ሰምተናል በተለይም አብዛኛው የከተማዋ ህንጻዎች ግንባታቸው ሳይጠናቀቁ ወደ ስራ መግባታቸው የችግሩ ምንጭ መሆኑ እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡

✳🇪🇹️የኢትየጵያ 📕የሕንጻ አዋጅ ቁ.624/2001 በአንቀጽ 31 እንዲሁም አንቀጽ 32 ላይ በግንባታ ወቅት መወሰድ ስላለባቸው ጥንቃቄወች ይደነግጋል፡፡ በዚህም መሰረት ማነኛውም ግንባታ በግንባታው አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን፣የሚሰሩ ሠራተኞችን ወይም የሌሎችን ግንባታ እና ንብረቶችን ደህንነት በማያሰጋ መልኩ ዲዛይን መደረግ እና መገንባት ይኖርበታል፡፡ በተለይም ደግም የሕንጻ ደንብ ቁ.243/2003 አንቀጽ 29 ላይ የጥንቃቄ እርምጃዋችን በስፋት ይዘረዝራል፡፡ ህጉም እንዚህን የጥንቃቄ እርምጃወች አለመከተል ከፍትሃብሄር እና ከወንጀል ተጠያቂነት በተጨማሪ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚያስወስድ በደንቡ አንቀጽ 44 ላይ ይናገራል፡፡

✳️በዋናነት የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ ጠቀሚታው አንድም በግንባታ ወቅት የሚደርሱ አደጋወችን ለመቀነስ (proactive solution) በማሰብ ሥራ ተቋራጩ ወይም ባለቤቱ አስቀድመው ከመድን ድረጅቶች ጋር በሚገቡት ውል አማካኝነት ነው፡፡ ✳️ለምሳሌ፡-ስራ ተቋራጩ የኮንስትራክሽን መድን ውል ግዴታ ቢገባ በየጊዜው የሚከፍለው አረቦን በመኖሩ ምክንያት የሚገነባውን ህንጻ በጥንቃቄ ሊሰራ ይችላል፡፡ ሁለትም ጉዳት ከደረሰ በኋላ (reactive solution) ጉዳት የደረሰባቸውን አካላት ለይቶ በመድን ውሉ መሰረት መካስን ይጨምራል፡፡

✳️የኮንስትራክሽን አደጋን ምንግዜም ማስወገድ ባይቻልም መቀነስ እና ቅድመ-መከላከል ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህም ሊሆን ከሚችልባቸውመንገዶች ውስጥ አንዱ የኢንሹራንስ ሥርዓት ነው፡፡
የህንጻ መደርመስ በሚደርስበት ጊዜ ተቋራጩ ኢንሽራንሽ የገባ ከሆነ መልካም ነው አለበለዚያ ግን የሚደርሰው ጉዳት የከፋ ያደረገዋል፡፡

5. 📌የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ የሕግ ማዕቀፍ

✳️በ2001ዓ.ም የወጣው የኢትዮጵያ ሕንጻ አዋጅ ቁ.624/2001 አንቀጽ 26 እና 27 የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስ በአስገዳጅነት በይፋ መጀመሩን ያወጀ ህግ ነው፡፡ ይህንንም ተከትሎ የወጣው የሕንጻ ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁ.243/2003 አንቀጽ 19 እና 20 ላይ ዝርዝር ጉዳዮችን በመያዝ መውጣቱ የሚታወስ ነው፡፡

✳️ታዲያ እነዚህን ህግጋተ መሰረት አድርገው የግንባታ ውል ውስጥ የሚገቡ አካላት ዝርዝር ውሎችን ሊዋዋሉ ይችላሉ፡፡ በተለይም አገር-በቀል ኩባንያዎች እንዲሁም ዓለምአቀፍ ይዘት ያላቸውን ውሉች የሚገዛው የዓለምአቀፋ አማካሪ መሀንዲሶች ማህበር ወጥ ውል (FIDIC Red book 1999) የኮንስትራክሽን አደጋዎችን ለመቀነስ ከተቀመጡ መንገዶች አንዱ የሆነውን ማለትም ኢንሹራንስን በተመለከተ በአንቀጽ 18 በዝርዝር ያሰቀመጠበትን ሁኔታ እናገኛለን፡፡

✳️በተለይ በመጀመሪያው አንቀጽ መግቢያ ላይ የመድን ሽፋን ገቢ(“insuring party”) ማን ሊሆን እንደሚችል አስቀምጧል፡፡ በዚህም መሰረት የመድን ሽፋን ገቢው ሥራ-ተቋራጩ፣ ባለቤቱ(አሰሪው) ወይም በጣምራ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በፊዲክ ወጥ ውልም የተባለው መድን በተለይ በአንቀጽ 17(3) ላይ የአሰሪው አደጋዎች ተብለው ከተለዩት ለምሳሌ የጦርነት፣ሽብር ጥቃት፣ብጥብጥ፣የባለቤቱ ሰራተኞች የተባለሸ ስራ ወዘተ ዉጭ ሁሉንም ዓይነት ጥፋቶች እና አደጋዎች ሊሸፍን ይችላል፡፡

✳️በተለይ ፊዲክ በአንቀጽ 18(2)(ረ)ላይ የመደን ሽፋን ላያገኙ የሚችሉ ሁኔታዎችን በዝርዝር ያስቀምጣል፡፡ ለምሳሌ፡-የተበላሹ የዲዛይን ሥራዎች ወይም የፕሮጀክት ግብዓቶች ላይ ሺፋን አያገኙም፡፡
እርግጥ ነው የFIDIC ወጥ ውል ልክ እንደ ሌሎች ውሎች ወደውና ፈቅደው በታዋዋሉ ወገኖች ላይ አስገዳጅነቱ የታወቀ ነው፡፡

✳️በ1994 ዓ.ም የወጣው የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ወጥ ውል የኮንስተራክሽን ኢንሹራንስን በተመለከተ ለሥራ ተቋራጮች ብቻ በሚመስል መልኩ የተቀረጸ ይመስላል፡፡

በተለይ በአንቀጽ 21 ላይ እንደተመለከተው ሥራ ተቋራጩ በራሱ እና በአሰሪው ስም ለፕሮጀክቱ አፈጻጸም ሲባል እንዲሁም ለሚደርሱ ጉዳቶች የመድን ሽፋን የመግባት ግዴታ አለበት፡፡ ሆኖም ግን በወጥ ውሉአንቀጽ 20 ላይ በተዘረዘሩ ልዩ አደጋዎች ማለትም እንደ ጦርነት፣ብጥብጥ ወዘተ የመድን ሽፍን መግባት አይልም::

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮንስትራክሽን ኢንሹራንስን በተመለከተ በአስገዳጅነት የተደነገገው ህግ በ2001 ዓ.ም የወጣው የሕንጻ አዋጅ ነው፡፡

#ConstructionLaw

@etconp
👍8🙏1
👉የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ አሁናዊ ገጽታ‼️

🌟የኦሞ ወንዝን ተንተርሶ እየተገነባ ያለው የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ 1 ሺህ 800 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን ፕሮጀክቱ በ2.4 ቢሊዮን ዩሮ ግንባታው እየተከናወነ ይገኛል።

⏺መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም

@etconp
❤9👍3💯1
Behaviour of strap beam in combined footing


@etconp


SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC

📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
👍6
👉የድልድዮች ጽዳትና ጥገና ስራ እየተከናወነ ነው

🚧 የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለረጅም ጊዜ አገልግሎት በመስጠትና በተለያዩ ምክንያቶች ለከባድ ብልሽት የተዳረጉ ድልድዮችን እየጠገነ ነው፡፡

የወንዞችን ተፈጥሯዊ ፍሰት በማስተጓጎል ለድልድዮች ብልሽት ምክንያት እየሆኑ የሚገኙ የቆሻሻና የግንባታ ተረፈ-ምርት ክምችቶችን በማፅዳት እያስተካከለም ይገኛል፡፡

ባለስልጣኑ በዕቅድ ከያዛቸው ዘርፈ ብዙ የመንገድ መሰረተ ልማት ጥገና ስራዎች መካከል የድልድዮች ጥገና እና የጽዳት ስራ ይገኝበታል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የድልድይ ፅዳትና ጥገና ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የአባ ጃሌ ድልድይ አንዱ ሲሆን፣ ድልድዩ ለረጅም ጊዜያት አገልግሎት ሲሰጥ በመቆየቱ ምክንያት እና በድልድዩ አካባቢ በሚጣል ቆሻሻና የግንባታ ተረፈ ምርት ሳቢያ የድልድዩ ምሰሶ ለጉዳት ተጋልጧል፡፡

አሁን ላይ በድልድዩ ሥር የተከማቸውና የወንዙን ፍሰት ያስተጓጎለውን ቆሻሻ በማንሳትና የድልድይ ጥገና ሥራ በማከናወን የነበረውን ችግር መፍታት ተችሏል፡፡

በተመሳሳይም በቦሌ ክፍለ ከተማ፣ በተለምዶ ፍየል ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ድልድይ ከፍተኛ መጠን ባለው ደለል እና ቆሻሻ በመደፈኑ ምክንያት የወንዙ ውሃ ወደ አፋልት በመፍሰስ ለእግረኛ እና ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ ሆኖ ከመቆየቱም በተጨማሪ በንብረት ላይም ጉዳት አድርሷል፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ወንዙ መስመሩን ጠብቆ እንዲፈስ ለማስቻል በድልድዩ ስር የተከማቸውን ከፍተኛ መጠን ያለው ቆሻሻና ደለል የማንሳት ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

ሕብረተሰቡም የዝናብ ወቅት የጐርፍ አደጋ ምክንያት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለማስቀረትን እና በመንገድ ሀብት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል፣ በየአካባቢው በመንገድ ዳር የውሃ መፋሰሻ መስመሮች እና ወንዞች ውስጥ ቆሻሻና የግንባታ ተረፈ ምርት የሚደፉ አካላትን በመከላከል በኩል የድርሻውን እንዲወጣ ባለሥልጣኑ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

@etconp
👍6❤1
👉የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ 61% ደረሰ

🌟የኦሞ ወንዝን ተንተርሶ እየተገነባ ያለው የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ 1 ሺህ 800 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ወጭ 2.4 ቢሊዮን ዩሮ መሆኑ ተጠቅሷል።

▶️ግድቡ 6 ዩኒቲቶች እንደሚኖሩት እና እያንዳንዳቸው 300 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም እንደሚኖራቸው የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዓባይነህ ጌትነት ጠቅሰዋል።

▶️የማመንጫ ቤቱ ግንባታ 52% መድረሱም ተጠቅሷል።

🚧ግድቡ  201 ሜትር ቁመት  እንደሚኖረው የፕሮጀክቱ  ምክትል ሼል አስኪያጅ ኢንጂነር ዓባይነህ አብራርተዋል።

🚧130 ኪሎ ሜትር መሬት ላይ የሚንጣለል ሰው ሠራሽ ሐይቅ የሚኖረው ግድቡ 6.5 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ ይይዛል ብለዋል።

🚧ጠቅላላ ሰው ሠልሽ ሐይቁ 200 ስኩዌር ኪሎ ሜትር  እንደሚሸፍን ነው የገለጹት።

🌟የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብም ወደፊት የሚኖረው ሰው ሠልሽ ሐይቅ  አካባቢው ካለው የቱሪዝም ፀጋ ጋር ተዳምሮ ለዘርፉ ተጨማሪ መዳረሻ እና መስህብ እንደሚሆን ጠቅሰዋል።

🚧ግድቡ ዊ ቢዩልድ (በቀድሞ ስሙ ሳሊኒ) ተቋራጭነት እየተሠራ ነው። የዊ ቢዩልድ ፕሮጀክት ማናጀር ኢንጂነር ዞፒስ፣ የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች  አቅም በግድቦች ግንባታ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።

🌟በማሳያነትም በኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት ከጉልበት ሥራ እስከ ከፍተኛ ባለሙያ በተለያዩ ዘርፎች ላይ በኢትዮጵያዊያን እየተገነባ ነው ብለዋል።

Via EBC

@etconp
❤7👍5
👉በትግራይ ክልል በተካሄደው ጦርነት ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት የ ኣኽሱም ኣውሮፕላን ማረፍያ መጠገን የሚችሉ የ ስራ ተቋራጮች የመምረጥ ሂደት ላይ እንደሆነ የኢትዪጵያ ኣየር መንገድ ጉሩፕ ኣስታወቀ።

✈️ኣየር መንገዱ መስከረም 2 / 2016 ዓ/ም በድጋሜ ያወጣው የጨረታ ማስታወቅያ ደረጃ ሁለት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ጠቅላላ ስራ ተቋራጮች በመጋበዝ የ ኣኽሱም ኣውሮፕላን ማረፍያ መጠገን እንደሚፈልግ ይገልፃል።

📌ጨረታው እስከ መስከረም 28 / 2016 ዓ/ም እንደሚቆይም ይገልፃል።

@etconp
👍5❤4💔2
የኮንስትራክሽን_አማካሪዎች_የአሰራር_መመሪያ_1_1_1.pdf
10.1 MB
👉የ ኮንስትራክሽ ኣማካሪዎች ለሆናቹ በሙሉ ስለ አሰራር እና መምርያ ጋ የተያያዙ ፅሁፎች ታገኙበታላቹ አውርዳቹ ተጠቀሙበት❤

🔊እንዲሁም ለወዳጆቻቹ በማጋራት አግዙን🙏

@etconp
👍5🙏5
Matt foundation layout

@etconp


SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC

📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
👍6
👉በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለሠራዊቱ እና ለቋሚ ሲቪል ሰራተኞች የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ

▶️የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ እና የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለሠራዊቱ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ መሠረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።

⏺የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ለሠራዊቱ አባላት እና ቋሚ ሲቪል ሠራተኞች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በ26,673 ካሬ ሜትር ላይ ለ1000 አባወራ የሚተላለፍ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የሚገነባ መሆኑ ተገልጿል።

▶️የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ብርጋዲየር ጀኔራል ደረጄ መገርሳ እንደገለፁት ለሀገር ህልውና አስጠባቂ ለሆነው መከላከያ ሠራዊት ደረጃውን የጠበቀ የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት የዲዛይን ስራው ተጠናቆ ግንባታውም በያዝነው አመት ይጀመራል።

🚧የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ምክትል ስራ አስፈፃሚ ኮሎኔል ታደሠ ጌታቸው በበኩላቸው የጋራ መኖሪያ ቡሎኮቹ ከ16 እስከ 18 እንደሚደርሱ ገልፀው አንዱ ብሎክ እስከ G+12 የሚደርስ ባለ 1፣ ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ ቤቶችን አጠቃሎ እንደሚይዝ ተናግረዋል።

🚧የሠራዊቱ አመራሮች በቃሊቲ ክፍለ ከተማ በቁጥር 1 እና 2 ሳይቶች የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶችንም ጎብኝተዋል።

Via EBC

@etconp
👍10