Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉ሲሚንቶ በኩንታል እስከ 300 ብር ቅናሽ አሳይቷል

🚧በአዲስ አበባ የተለያዩ ሲሚኒቶዎች በችርቻሮ ዋጋ ከ 1,200 ብር እስከ 1,600 ብር እየተሸጡ ነው።

🌟በአማካኝም ሲሚንቶ በወራት ጊዜ ውስጥ በኩንታል እስከ ሶስት መቶ ብር ቅናሽ አሳይቷል ።

🌟ለዋጋው መቀነስ የባንኮች ብድር መቀነስ የግንባታ ስራዎች በማዳከሙ የሲሚኒቶ ግዢ ፍላጎቱን በመቀነሱ እንጂ የዋጋው መቀነስ ከምርት መጨመር ጋራ የተያያዘ ነው ብለው እንደማያምኑ በዘርፉ ላይ የሚሰሩ ሁለት ነጋዴዎች ለፊደል ፖስት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

@etconp
👍13❤1
👉445 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚፈጀው አዲሱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አዲስ የሚያስገነባውን የዋና መስሪያ ቤት ባለ 62 ወለል ሕንጻ ዲዛይን፤ የአረንጓዴ ሕንጻ የወርቅ ደረጃ ሰርትፊኬት እንዲያገኝ በሚያስችል መልኩ እየተሥራ መሆኑን ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ አስታወቀ፡፡

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ በኃይሉ ታደለ እንደገለጹት፤ የተቋሙ ሕንጻ ዲዛይን በአሜሪካ የአረንጓዴ ሕንጻዎች ካውንስል በሚመራው የኢነርጂና የአካባቢ ዲዛይን (LEED) ሥርዓት መሰረት የወርቅ ደረጃ መስፈርቶችን የሚያሟላ ነው፡፡

የሕንጻው ዲዛይን ሃይል ቆጣቢ፣ በሰውና በአካባቢ ላይ ምንም አይነት ተፅዕኖ የማያሳድር እንዲሁም ለሥነ-ምህዳር ተስማሚ የሆኑ የአረንጓዴ ሥፍራዎች የተካተቱበት በመሆኑ የሚሰጥ የዕውቅና ሰርትፊኬት ነው ብለዋል።

ሜክሲኮ በሚገኘው በተቋሙ ቅጥር ግቢ የሚገነባው ባለ 62 ወለል ሰማይ ጠቀስ ሕንጻ ተቋሙን የሚገልፁ፤ ከፀሐይ እና ከንፋስ ኃይል በማመንጨት ለሕንጻው ፍጆታ ኃይል ማቅረብ የሚያስችሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እንደሚኖሩት ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡

ግንባታው 445 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚፈጅ ሲሆን፤ በ4 ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

Via አዲስ ማለዳ

@etconp
👍12❤3😁2
👉17ኛው ኢቲኮን አለም አቀፍ የኮንስትራክሽን አውደርዕይ ተከፈተ

🚧17ኛው ኢቲዮ-ኮን አለም አቀፍ የኮንስትራክሽን አውደርዕይ ትላንት ጥቅምት 1 ተከፍቷል፡፡

🌟ለ 4 ተከታታይ ቀናት የሚቆየው ይህ ውደርዕይ የዘርፉ ቴክኖሎጂ የደረሰበትን የእድገት ደረጃ ለማሳየት እና የገበያ ትስስርን ለመፍጠር የሚያግዝ መሆኑን የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር ፕሬዝደንት ኢነጂነር ግርማ ሀ/ማሪያም ገልፀዋል፡፡

🌟የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በበኩላቸዉ በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ዘርፍ የሚከናወኑ ስራዎች የሀገሪቱን የብልፅግና ጉዞ በማሳካት ሂደት ውስጥ ጉልህ ድርሻ እንዳለው ገልፀዋል፡፡

🌟በዘርፉ አውደርይዕይ መዘጋጀቱ ከአዳዲስ ቴክሎጂዎች ጋር ለመላመድ እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋልም ነው ያሉት፡፡

🌟በአውደርዕዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ኮንስትራክሽን ድርጅቶች ምርት እና አገልግሎታቸውን ይዘው ቀርበዋል፡፡

Via ግርማ ሁንዴ

@etconp
❤5👍5
👉በቀጣዮቹ አስር አመታት 80 በመቶ የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በአገር ውስጥ ለማምረት ታቅዷል-የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር

በዘርፉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ለእይታ የቀረቡበትና ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ቀናት የሚቆየው 17 ኛው "ኢትዮ-ኮን" ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማእከል ተከፍቷል።

በኤግዚቢሽኑ የአገር ውስጥ እና የውጭ አለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ተሳታፊ ሆነዋል።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ወንድሙ ሴታ፤ ኤግዚቢሽኑን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ዘርፉ ለሀገራዊ እድገት አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም የኮንስትራክሽን ዘርፉ ለአገራዊ የምርት እድገት /GDP/ አሁን ላይ የ470 ቢልዮን ብር አስተዋጽኦ እያበረከተ ስለመሆኑ አንስተዋል።

ከግብርና ዘርፍ በመቀጠል ከፍተኛ የስራ እድል የሚፈጠርበት መስክ መሆኑንም ገልጸዋል።

በመሆኑም 17 ኛው "ኢትዮ-ኮን" ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ኤግዚቢሽን፤ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ለእይታ የቀረቡበት ሁሉም ሊጎበኘው የሚገባ ሁነት መሆኑን ጠቁመዋል።

የፖሊሲ ማሻሻያ ከማድረግ ጀምሮ የተለያዩ ማነቆዎችን በመፍታት ረገድ ሚኒስቴሩ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን አስታውሰው ይበልጥ ስኬታማ ለማድረግም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ለኮንስትራክሽን ግብዓትነት የሚውሉ በበቂ ሁኔታ በአገር ውስጥ መኖራቸውን ገልጸው ወደ ግብዓትነት ለመለወጥ ውስንነቶች መኖራቸውን አመላክተዋል።

ከኮንስትራክሽን ግብዓት 65 በመቶ የሚሆነው ከውጭ የሚገባ በመሆኑ አገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የምታወጣበት መሆኑንም ገልጸዋል።

በመሆኑም በቀጣዮቹ አስር አመታት ከዋና ዋና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች 80 በመቶ የሚሆነውን በአገር ውስጥ ለማምረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ግርማ ሀብተማርያም፤ ዘርፉ በግብዓት አቅርቦት የዋጋ ንረት እየተፈተነ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የግብይት ስርዓቱ ያልተስተካከለ መሆንና ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎችም ሌላኛው ፈተና መሆኑን አብራርተዋል።

በመሆኑም የዘርፉን ችግሮች በጋራ መፍታትና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት መጠቀም ይገባል ነው ያሉት።

Via ኢዜአ

@etconp
👍11👌2
👉በ 18 ቢሊየን ብር በአዲስ አበባ በ11 ክፍለ ከተማ የአርቲስቶች መንደር ሊገነባ ነው!

🚧በኢትዮጵያ ያለውን የኪነ-ጥበብ እድገት ከዚህ በፊት ከነበረው ሁኔታዎች በተሻለ ሁኔታ ለመስራት እንዲቻል መንግስትን፣ ባለሀብቶችን የተቀረውን ህዝብ በማስተባበር ሦስት ዋና ዋና ተግባራትን ለመስራት ታስቧል፡፡

🚧እነሱም የጥበብ ውለታ የጋራ የመኖሪ መንደር፤ የጥበብ ውለታ ኢንተርናሽናል ት/ቤት፤ የጥበብ ውለታ የመመጋቢያ የመዝናኛ ማዕከል በማስገንባት የጥበብ ቤተሰብ ከልመና እና ከችግር የሚወጣበትን ስራ ለመስራት እንቅስቃሴ እየተደረግ እንደሆነ ዛሬ ጥቅምት 02/2016 ዓም በቤስት ዌስተርን ፔርል አዲስ ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጻል፡፡

🌟የጥበብ ውለታ ሦስቱም ዓላማ በአዲስ አበባ ባሉት በ11 ክፍለ ከተማ ላይ ተግባራዊ እንዲሆን የሚሰራ ሲሆን የቤቱን ብቻ ብንመለከት 990 የጥበብ ሰዎች የቤት ባለቤት የሚሆኑበትን እድል የሚፈጥር ይሆናል ተብሏል፡፡

🌟በአንድ ክፍለ ከተማ ላይ የጥበብ ውለታ የጋራ የመኖሪያ መንደር ሲገነባ 90 አርቲስቶችን የቤት ባለቤት የሚያደርግ ሲሆን 500,000,000 (አምስት መቶ ሚሊየን) ብር ወጪ ያስፈልጋል ለጥበብ ውለታ ኢንተርናሽናል ት/ቤት 700,000,000/ ሰባት መቶ ሚሊዮን ብር ይፈልጋል፤ የጥበብ ውለታ የመመጋቢያ የመዝናኛ ማዕከል ደግሞ 600,000,000/ ስድስት መቶ ሚሊየን ብር ያስፈልጋል፡፡

🌟በአጠቃላይ የጥበብ ውለታ ዓላማን ለማሳካት በአንድ ክፍለ ከተማ ላይ 18,000,000,000 (አስራ ስምንት ቢሊየን) ብር የሚያስፈልግ መሆንን እንደሚያስፈልግ ነው በመግለጫው የተገለጸው፡፡

Via Fast mereja

@etconp
👍5❤3😁3🙏1
Cylinder strength of concrete as compared with cube is:

1️⃣. 70%
2️⃣. 80%
3️⃣. 90%
4️⃣. 100%

@etconp

SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC
Elevator and Escalator

📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69

Office:- Bulgariya street awebane trading S.C Bulding 1st floor

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
❤2🕊1
A 6mX8m slab si designed as:
1️⃣. One way
2️⃣. Two way
3️⃣. Three way
4️⃣. None

@etconp

SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC
Elevator and Escalator

📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69

Office:- Bulgariya street awebane trading S.C Bulding 1st floor

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
👍7❤1🙏1
👉DO YOU KNOW ???

▶️Do you know that a doubly reinforced column base gives more rigidity, stability and the ability to transmit and distribute the load effectively to the soil beneath. The secondary reinforcement base provides resistance to punching stress as a result of an imposed load. Good morning peoples.

▶️Do you know that a weak footing of a structure can be strengthened through a means know as jacketing. However, the new footing base helps to establish a better platform for the effective distribution of imposed load substructurally without any form of deformation.

⚡አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ

@etconp
👍7👌5
👉ለኮንስትራክሽን ሙያተኞች ዓለም አቀፍ ነፃ ስልጠና!

🌟ለረዢም አመታት ልምድና ሰፊ እውቀት ባላቸው የዘርፉ ሙያተኞች የሚሰጠውን የዋተር  ፕሩፊንግ ፣ ፎሎሪንግ እና አድሜክስቸር ስልጠና በነፃ በኢትዮ-ኮን2023 ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ኤግዚቢሽን ላይ ይውሰዱ።

⏺ቀን፡ እሁድ ጥቅምት 4 ቀን 2016
⏺ዓ.ም ሰአት: ከ4:00 - 6:00 ሰአት
⏺ቦታ: አዲስ አበባ ኤግዝቢሽን ማዕከል ፤ አዳራሽ ቁጥር 2

🚧ይሰልጥኑ ፤ ሙያዎትን ከፍ ያድርጉ!!!

🖱ለተጨማሪ መረጃ: 📞 0912 77 77 77

🫶በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር እና ማፔይ ዩኬ ትብብር የተዘጋጀ።

@etconp
🙏4👍2
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዲሱ ህንጻ በየካቲት ወር 2017 ለማጠናቀቅ እየተሠራ ይገኛል ተባለ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሕንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ከኹለት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እየተከናወነ መሆኑን የፌደራል መንግሥት ሕንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ግንባታው ሲጠናቀቅ ኹለት ሺሕ 400 መቶ ሰዎችን ማስተናገድ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

የጽህፈት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሃራ አብዱልሃዲ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የብሔራዊ ቴአትሩ አዲስ ሕንጻ ግንባታ ዘጠኝ በመቶ የደረሰ ሲሆን፤ በየካቲት ወር 2017 ለማጠናቀቅ እየተሠራ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ፕሮጀክቱን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ የግንባታው ሂደት በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ግንባታው ሲጠናቀቅ ኹለት ሺሕ አራት መቶ ሰዎችን ማስተናገድ ያስችላል ብለዋል፡፡

በፕሮጀክቱ ሦስት የመሰብሰቢያና አንድ ኹለገብ ክፍሎች እንደሚገነቡ ያስታወቁት ሥራ አስኪያጇ፤ ለተለያዩ የሥነ-ጥበብ ነክ ክንውኖች የሚውሉና የተለያዩ ኹነቶችን የሚያስተናግዱ የመሰብሰቢያ ቦታዎች መካተታቸውን ገልጸዋል።

በግንባታው ሂደት ለመድረክ ሥራውና ከመድረኩ ጋር ተያይዞ ለሚያስፈልጉ ቴክኖሎጂዎች ሲባል የዲዛይን ክለሳ መደረጉን ገልጸው፤ በአገር ውስጥና የውጭ አገር ባለሙያዎች ጥረት ግንባታው እየተከናወነ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

በአዲሱ ዘመናዊ ሕንጻ ዓለም አቀፍ የቴአትር ቤት መስፈርቶችን ማሟላት የሚያስች የመብራት፣ የድምፅና፣ የመድረክ ግንባታ እንደሚካሄድ የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፤ ቴክኖሎጂን ማዕከል በማድረግ በጥንቃቄ ግንባታው እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።

ግንባታው ሲጠናቀቅ ለአርቲስቶች የተሻለ የመድረክ አጠቃቀምን ተግባራዊ የሚያደርጉበት ምቹ ኹኔታ እንደሚፈጥርም አመላክተዋል።

ግንባታው ሲጠናቀቅ ቴአትር ቤቱ ኦፔራን ጨምሮ የተለያዩ ትርዒቶችን ማዘጋጀት የሚችል ትልቅ መድረክ እንደሚኖረው ጠቁመው፤ የቴአትር ቤቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የቱሪስት መስህብ የሚሆን ድንቅ ፕሮጀክት እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር አዲስ ዘመናዊ የሕንጻ ግንባታ በስድስት ሺሕ 200 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ መሆኑን አስታውቀዋል። ግንባታው ከምድር በታች ኹለት ወለል ያለውና ባለ 11 ወለል ከፍታ እንዲኖረውና ተደርጎ በጥራት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

አሁን ላይ ግንባታው እየተከናወነ ያለው አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዘመናዊ ሕንፃ ከነባሩ ቴአትር ቤት ጎን እየተገነባ ይገኛል።

@etconp
🏆3
በከተሞች ህጋዊ የካዳስተር ስርአት እና የሪል ፕሮፐርቲን ተግባራዊነት ለማረጋገጥ ሁሉም የህግ ማዕቀፎች በአግባቡ ሊተገበሩ እንደሚገባ ተገለጸ

ከመላው ሀገሪቱ ለተውጣጡ በከተማ መሬት ዘርፍ ለሚሰሩ ከ200 በላይ አመራሮችና ባለሙያዎች በተዘጋጁ ሰነዶችና የሀግ ማዕቀፎች ዙሪያ ከጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአዳማ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ኢየተሰጠ ነው፡፡

ማንኛውም የሥርዓት ግንባታ መነሻው የሕግ ማዕቀፍ፣ ስታንዳርድ እና እንዲመጣ የሚፈለገው የአገልግሎት አይነት ጥናት ከመሆኑ አንፃር የሚገነባው ፍላጎት ጥናቱ ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ በመሆኑም የሕግ ማዕቀፉ ሀገራዊ ተፈጥሮ እና አተገባበር ይዞ፤ ይህን ማስተግበሪያ አቅም እንዲኖረው በማድረግ በዘመናዊ የመረጃ ስርዓት መደገፉ አስፈላጊ ነው፡፡

የመሬት ይዞታ ምዝገባ (ካዳስቴር) ዓላማዎች ከተሞች ያላቸውን መሬት ቆጥረው ማወቅ እንዲችሉ በማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተናባቢ የሆነ የመሬት ይዞታ መረጃ እንዲኖ በማስቻል አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመገንባቱን ሂደት ማገዝ፤ ይዞታ መብትን በምዝገባ በማረጋገጥ፣ የባለይዞታውን የመሬት ይዞታ ተጠቃሚነት ዋስትና እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት መብትን እውቅና በመስጠት የከተሞችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊ እና አካባቢያዊ ልማትን ማፋጠን፤ ከተሞች ያላቸውን መሬት ቆጥረው ማወቅ እንዲች በማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተናባቢ የሆነ የመሬት ይዞታ መረጃ እንዲኖር በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ድርሻ አለው፡፡

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒሰቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን በስልጠናው መድረክ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት በከተሞች መሬትና መሬት ነክ ሀብት በሀገራችን ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው እጅግ የጎላ ነው፡፡

በከተሞች ፈጣን የህዝብ እድገት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ ለዜጎች አስፈላጊውን ሁሉ የመሠረተ-ልማት ለማሟላት መሬትን በዘመናዊ የመረጃ ስርአት(ካዳስቴር) መዝግቦ በመያዝ ለተሻለ የኢንዱስትሪ ልማት ዝግጁ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም በከተሞች የዜጎችን ቅሬታና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ መሬትን ህጋዊ የካዳስተር ስርአትን እውን በማድረግ ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖርና የዜጎችን የሀብት ባለቤትነት ማረጋገጥ እንደሚቻል ጠቅሰው ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የሚወጡ አጠቃላይ የህግ ማእቀፎች፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሚገኙ ተሞክሮዎችን ሁሉም ክልሎች ተግባራዊ ሊያደርጓቸው እንደሚገባ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

በስልጠናውም ከመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የሊዝ አዋጅ፣ የመሬት ምዝገባና ማረጋገጫ አዋጅ፣ የቅየሳ ስታንዳርድ ጋይድ ላይን፣ የከተማ መሬት ባንክ አሰራር ማንዋል፣ የአድራሻ ሥርዓት ስታንዳርድ፣ የካሳ አዋጅና ደንብ ፣ የመልሦ ማልማት ኦፖሬሽናል ማንዋል፣ የሪል ፕሮፖርቲ ግብይት ግመታና ፈቃድ አሰጣጥ ፅንሰ ሀሳብ፣ የሪል ፕሮፐርቲ ልማት ግብይትና ግመታ አዋጅ፣ የቦታ ደረጃ ሰነድ እና የእሴት እርከን መወሰኛ መስፈርትና ሌሎች የክልሎች ተሞክሮዎች ለተከታታይ ሶስት ቀናት በተለያዩ ባለሙያዎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ከመርሃ ግብሩ ማወቅ ችለናል፡፡

Via ሞገስ ዓሊ

@etconp
👍5❤2
ኮስሞፖሊታን ሪል እስቴት ዘመናዊ አፓርታማ አስመረቀ

ኮስሞፖሊታን ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በቦሌ ጃፓን ኤምባሲ አቅራቢያ ተሰርቶ የተጠናቀቀውን ጂ+11 የሆነ በ700 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ዘመናዊ ባለ ምቾት አፓርታማ የቤት ገዢዎችን ፍላጎት ያሟላ ዛሬ ጥቅምት 3/2016 ዓ.ም የክብር እንግዶች በተገኙበት በድምቀት አስመርቋል።

ህንፃው የስፖርት ማዘውተሪያ ጂም፣ ሳውናና ስቲም የተሟላለት የ24 ሰዓት ኤሌክትሪክ የተመቻቸላቸው በሙያው የላቀ ልምድ ባካበቱ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሙያዎች የተገነቡ ሲሆን የቤቶቹ የአሠራር ጥራት ደረጃውን የጠበቀ እና ዋጋቸውም ተመጣጣኝ  ናቸው ተብሏል።

ኮስሞፖሊታን ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአሁኑ ሰዓት በአገራችን በቤቶች ግንባታ እና በሌሎች ዘርፎችም ላይ ተሠማርቶ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ኦሎምፒያ ጂ+17 ህንጻ እንዲሁም በፒያሳ ካቴድራል አካባቢ ለሱቅና ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የገበያ ማዕከል ግንባታ የሚጀምር ሲሆን ይህም ለበርካታ ኢትዮጵያዊያን የስራ ዕድል ይፈጥራል ከዚህ ፊት በሶስቱ ፕሮጀክቶች ለ25ዐ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል።

በይፋ ከተመሠረተ አምስት ዓመታትን ያስቆጠረው ኮስሞፖሊታን በአስመጪና ላኪነት፣ በቤት እና በቢሮ እቃዎች፣ በወረቀት ማምረት እንዲሁም በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ ለደንበኞቹ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለ ድርጀት ነው እንደሆነ ተገልፇል።

@etconp
👍6❤1
👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስገነባቸው 9 የመንገድ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

በዛሬው ዕለት የተመረቁት የመንገድ ፕሮጀክቶች 2 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጎባቸዋል ተብሏል።

የመንገድ ፕሮጀክቶቹ የቦሌ ሚካኤል ተሻጋሪ ድልድይን ጨምሮ ከአራራት ሆቴል - ኮተቤ ኮሌጅ፣ ከኮተቤ ኮሌጅ - ካራ (ሎት2)፣ ከቄራ ከብት በረት - ጎፋ መብራት ኃይል፣ ከቀጨኔ - ቁስቋም፣ ከየካ አማኑኤል ሆስፒታል - ኮተቤ እንዲሁም ሰሚት 40/60 ኮንዶሚኒየም፣ አያት 2 ኮንዶሚኒየም፣ አያት መሪ ሳይት 4 ናቸው።

ዛሬ የተመረቁት መንገድ ፕሮጀክቶች በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ በማቃለል የተሳለጠ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ያስችላል ተብሏል።

በምረቃ መርኃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ ጨምሮ የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

@etconp
👍6
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ

፦የአገልግሎታችንን አድማስ በማስፋት የክቡራን ደንበኞቻችንን ፍላጎት ለማርካት በታማኝነት እንተጋለን

፦ፕሌት 1mm-30mm any size

፦jbolt 12mm-32mm

፦ankerbolt

፦stafa

፦any modefic wor

፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን

ቁ.1  መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር  ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ
0904040477
0911016833
0994941706
👍1🏆1
DEBUB GLOBAL BANK HEADQUARTER DESIGN

DESIGNED BY :- AHAA DESIGN

@etconp

SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC
Elevator and Escalator

📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69

Office:- Bulgariya street awebane trading S.C Bulding 1st floor

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
👍5❤1