Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
Only in Ethiopia 🇪🇹 😂

chariot trailing concrete mixer

@etconp

Captured by :-JORDANOJOMOLE
😁15👍4😢4
👉በሰመራ በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባ ሪፈራል ሆስፒታል የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባው ደረጃውን የጠበቀ ሪፈራል ሆስፒታል በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

ርዕሰ መስተዳደር አወል ሆስፒታሉ ለህብረተሰቡ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዲሰጥና ለከተማዋ የሚመጥን ተደርጎ እንደሚገነባ ተናግረዋል።

በዋናው የአገሪቱ አውራ መንገድ ላይ የምትገኘው ሰመራ ከተማ ላለፉት ዓመታት የሪፈራል ሆስፒታል ሳይኖራት መቆየቷን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ የሚገነባው ሆስፒታል ከከተማዋ ነዋሪዎች ባለፈ የከተማዋን ዋናው ጎዳና ለሚጠቀሙ አካላትም እንደሚያገለግል መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ ስርዓት ላይ የተገኙት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ያሲን ሃቢብ በበኩላቸው እንዳሉት ሆስፒታሉ በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ ደረጃውን ጠብቆ ይገነባል።

የሰመራና የአካባቢው ነዋሪዎች ለዓመታት ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ደሴ፣ መቀሌ፣ አዳማ እንዲሁም አዲስ አበባ እንደሚጓዙ አስታውሰው፣ "የሆስፒታሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ ወደተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ለሕክምና የሚደረገውን ጉዞ ያስቀራል" ብለዋል።

የሪፈራል ሆስፒታሉ በመንግስት በጀት፣ በአጋሮች ተሳትፎ እና በህብረተሰቡ የተጠናከረ ትብብር እንደሚገነባም አመልክተዋል።

ሆስፒታሉ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ለሰመራ ሎጊያና አካባቢው ማህበረሰብ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን እንደሚሰጥ ተመላክቷል።

@etconp
👍8❤1
Which one is sky bridge and which one is tower bridge ?


@etconp

ማሳሰቢያ/ Announcement 📢

11 days left / 11 ቀን ቀረው አሁንም አልረፈደም ተወዳደሩ


500 birr give away question is posted on our Facebook page

የሽልማት ጥያቄው አሸናፊውን የምንለየው November 20- 2023 ሲሆን ሽልማቱ 500 ብር ነው።

ጥያቄው የተለቀቀው በፌስቡክ ገፃችን እና በ ኢኒስታግራም ገፃችን ነው።

አሸናፊው የሚለየው ለመልሶቹ ብዙ ላይክ ያገኘ ነው። በትንሹ 30 ላይክ ሊኖረው ይገባል

አሁንም አልረፈደም

ጓደኞቻችሁን የለጠፋችሁትን ፎቶ ላይክ አስደርጉ

የ ኢንስታግራሙ ጥያቄ ሊንክ:- https://www.instagram.com/p/Cy72qOlsKm0/?igshid=MzRlODBiNWFlZA==

የፌስቡኩ ጥያቄ ሊንክ:- https://www.facebook.com/100064135238834/posts/pfbid033h5xCMU2QNC1taixH6W25gPnUFakMD5RMX4dcEnd3E6M1HCjmhL1UqHYMkEMMiNEl/?app=fbl

SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC
Elevator and Escalator

📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69

Office:- Bulgariya street awebane trading S.C Bulding 1st floor

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
👍4❤1
👉ዜና ሹመት

🌟ኢንጅነር ቶማስ ደበሌ በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የቤት ማስተላለፍ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

🚧ኋላፊው ከዚህ ቀደም የኮርፖሬሽኑ የግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር የነበሩ  ሲሆን በግንባታ ዘርፉ በርካታ አመርቂ ስራዎችን መስራታቸው የሚታወቅ ነው።

🖱እንዲሁም

🌟ኢንጅነር ስጦታው አካለ በአዲስ አበባ  ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

@etconp
👍4😢2
👉ቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ለደረሳባቸው ዜጎቿ ቤት ልታስረክብ ነው

🌟ቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ለተጎዱ ዜጎች 17 ህንጻዎችን ገንብታ ነው ለማስረከብ ዝግጁ ያደረገችው።

🚧399 ቤቶችን ያያዙት 17 ህንጻዎች አረንጓዴ ቦታዎች፣ የእግር መንገድና የስፖርት መስኮችን የያዘ መሆኑ ተጠቁሟል።

🚧የቤቶቹ ግንባታ በተካሄደበት ግዛት የምዕተ ዓመቱ አደጋ ነው የተባለ የመሬት መንቀጥቀጥ ማጋጠሙ አይዘነጋም።

🚧ይህንን አካባቢ በጥቂት ወራት ውስጥ ዘመናዊ ቤቶችን ገንብቶ ለዜጎች ለማስተላለፍ በተሰራው ስራ ራሱን የቻለ ከተማ እየተገነባ መሆኑ ተገልጿል።

Via EBC

@etconp
👍7❤6
👉ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ

🫵የአገልግሎታችንን አድማስ በማስፋት የክቡራን ደንበኞቻችንን ፍላጎት ለማርካት በታማኝነት እንተጋለን

🖱ፕሌት 1mm-30mm any size

🖱jbolt 12mm-32mm

🖱anker bolt

🖱stafa

🖱any modefic work

🚧ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን

📩 @heavenic1 ፃፉልን

ቁ.1  መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር  ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ

0904040477
0911016833
0994941706 ይደውሉ።
👍5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉Soil nailing

🌟Soil nailing uses grouted, tension-resisting steel elements (nails) to reinforce in situ soils and creating a gravity retaining wall for permanent or
temporary excavation support.

🌟Common uses
- Stabilize slopes and landslides
- Support excavations
- Repair existing retaining walls

🌟Process
Soil nail walls are generally constructed from the top down. Typically, soil is excavated in three to six feet deep stages. After each excavation stage, near-horizontal holes are drilled into the exposed face at typically three to six foot centres

Tension-resisting steel bars are inserted into the holes and grouted in place. A drainage system is installed on the exposed face, followed by the application of reinforced shotcrete wall facing. Precast face panels can also be used. Bearing plates are then fixed to the heads of the soil nails. This installation process is repeated until the design wall depth is reached.

The finished soil nails then produce a zone of reinforced ground.

#Geotechnical

@etconp
👍9😢1
Forwarded from Ethio Construction Engineering (जॉर्डनो ג׳ורדנו ጆርዳኖ جوردانو จอร์แดโน่ JORDANO Ιορδάνοςஜார்டானோ)
Pile foundation depending on their their function divided into two
A. Bearing pile
B. Friction pile


@etconp

@etconp

ማሳሰቢያ/ Announcement 📢

10 days left / 10ቀን ቀረው አሁንም አልረፈደም ተወዳደሩ

500 birr give away question is posted on our Facebook page

የሽልማት ጥያቄው አሸናፊውን የምንለየው November 20- 2023 ሲሆን ሽልማቱ 500 ብር ነው።

ጥያቄው የተለቀቀው በፌስቡክ ገፃችን እና በ ኢኒስታግራም ገፃችን ነው።

አሸናፊው የሚለየው ለመልሶቹ ብዙ ላይክ ያገኘ ነው። በትንሹ 30 ላይክ ሊኖረው ይገባል

አሁንም አልረፈደም

ጓደኞቻችሁን የለጠፋችሁትን ፎቶ ላይክ አስደርጉ

የ ኢንስታግራሙ ጥያቄ ሊንክ:- https://www.instagram.com/p/Cy72qOlsKm0/?igshid=MzRlODBiNWFlZA==

የፌስቡኩ ጥያቄ ሊንክ:- https://www.facebook.com/100064135238834/posts/pfbid033h5xCMU2QNC1taixH6W25gPnUFakMD5RMX4dcEnd3E6M1HCjmhL1UqHYMkEMMiNEl/?app=fbl

SPONSOR

ELEGAS ENGINEERING PLC
Elevator and Escalator

📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69

Office:- Bulgariya street awebane trading S.C Bulding 1st floor

Website:- www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr
👍2❤1
👉ኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ አንድ ሺሕ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶችን ልትገነባ ነው ተባለ

🚧ኢትዮጵያ በ23 ከተሞች የውሃ አያያዝና አቅርቦትን ለማሻሻል የ523 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት መጀመሯ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም ፕሮጀክት በመላ አገሪቱ 1 ሺሕ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች መገንባትን እንደሚያካትት ተነግሯል፡፡

🚧ለዚሁ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያም የዓለም ባንክ የ460 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ቀሪውን 63 ሚሊየን ዶላር ደግሞ በሌሎች ለጋሽ ተቋማት ይሸፈናል ተብሏል።

🚧ፕሮጀክቱ በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባትን የመቀሌ ከተማ የሚያካትት መሆኑን አዲስ ማለዳ ከአለም አቀፍ ኮንስትራክሽን ሪቪዉ ያገኘችዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

🚧ኢትዮጵያ በከተማዋ የውሃ መሰረተ ልማቶችን ለማዳረስ እንዲሁም የኤሌክትሪክ ፓምፖች ለመግዛት 1 ሚሊየን ዶላር ወጪ ማድረጓም ተነግሯል፡፡

🚧በፈረንጆቹ 2018 ግሎባል ዋተር ኢንተለጀንስ የተሰኘው ተቋም አደረኩት ባለው ጥናት መሰረት፤ በአገሪቱ ዘመናዊ መጸዳጃ የሚጠቀሙ የከተማ ነዋሪዎች 12 በመቶ ብቻ መሆናቸውን አመላክቷል።

@etconp
👍5
👉የሲሚንቶና የብረት ዋጋ ቅናሽ አሳየ

🌟በሲሚንቶ፣ በብረትና ሌሎች የግንባታ እቃዎች ላይ የዋጋ ቅናሽ መታየቱን በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾችና ነጋዴዎች ገልጸዋል፡፡

🚧በከተማዋ የ1 ኩንታል ሲሚንቶ ዋጋ ከ800 ብር እስከ 500 ብር ቅናሽ እንዲሁም 1 ቤርጋ ፌሮ በኪሎ የ15 ብር ቅናሽ ማሳየቱ ተሰምቷል፡፡

🚧ቀደም ሲል ግብይቱ በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተመን ወጥቶለት ሲሸጥ የቆየ ቢሆንም ከታህሳስ ወር 2015 ዓ.ም ወዲህ  ግን በነጻ ገበያ መርህ ፋብሪካዎች ባቀረቡት ዋጋ  ግብይትት መካሄድ መቀጠሉን በቅኝቱ ወቅት ለማወቅ ተችሏል፡፡

🚧ከዚህ ቀደም ሲሚንቶ ከ1 ሺህ 800 እስከ 2 ሺህ ሲሸጥ የቆየ ቢሆንም  አሁን ላይ ግን ኢትዮ ሲሚንቶ ከ1 ሺህ 250 እስከ 1 ሺህ 270፣ ሀበሻ ሲሚንቶ በ1 ሺህ 300 ብር እና ሙገር ሲሚንቶ በ1 ሺህ 350 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡

🚧በተመሳሳይ የብረት ገበያም ቅናሽ የታየበት ሲሆን ለአብነትም 10 ቤርጋ ብረት 1 ሺህ 332 ሲሸጥ የቆየ ሲሆን አሁን ላይ 1 ሺህ 36 ብር፣ 14 ቤርጋ ፌሮ ብረት 3 ሺህ 412 ብር ይሸጥ የነበረ ሲሆን  አሁን 2 ሺህ 654 ብር  በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡

🚧በዘርፉ ላይ የተሰማሩት አምራቾችና ነጋዴዎች ሲሚንቶ፣ ብረትና ሌሎችም የግንባታ እቃዎች ሸማቾች ቁጥር መቀነሱንም አመላክተዋል።

Via FBC

@etconp
👍12❤2
👉የቻይና መንግስት  ለባቡር ሀዲድ መጠገኛ የሚሆን ሶስት ሚሊዮን ዶላር ለኢትዮጵያ መስጠቱ ተገለጸ

🌟በ2015 ዓ.ም የማክሮ ፋይናንስ  እና የቻይና መንግስት ከተፈራረሙት አንደኛዉ የመለዋወጫ እቃ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ የመጀመሪያዉ ምዕራፍ ሶስት ኮንቴነር የእቃ መለዋወጫ መግባቱ ነዉ የተገለጸዉ።

🚧የገባዉ የገንዘብ መጠንም በዚህ ምዕራፍ ከታሰበዉ ሀያ ሁለት ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ሶስት ሚሊየን የሚሆነው  መግባቱን  የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፓርት አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን  አሰፋ ተናግረዋል።

🚧ከገቡት ሶስት ኮንቴነር የእቃ መለዋወጫ በተጨማሪ ከሶስት ወር በኃላም ተጨማሪ  የባቡር መለዋወጫዎች እንደሚገቡ የገለጹልን ኃላፊዉ አጠቃላይ የባቡር መለዋወጫ ችግርን ለመፍታት በዚህ እርዳታ ብቻ የሚፈታ አለመሆኑን በመግለጽ ለዚህም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጥልቅ የሆነ ጥናት በቀላል ባቡር ባለሙያዎች መጠናቱን አስታውቀዋል፡፡

Via መናኸሪያ ሬዲዮ

@etconp
👍9❤2
👉በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ረቂቅ የህግ ማዕቀፎች ላይ የሚመክር የግብኣት ማሰባሰቢያ መድረክ በመካሄድ ላይ ነው

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ማሻሻያ ረቂቅ ሠነድ፣ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ረቂቅ አዋጅ፣ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ረቂቅ የስነ-ምግባር ደንብ እና የግንባታ ቦታ ደህንነት፣ ጤና እና አካባቢ ጥበቃ ደንብ ረቂቅ ሠነዶች ላይ ግብአታ ለማግኘት የሚያስችል የግብኣት ማሰባሰቢያ የጋራ የውይይት መድረክ በሚኒስቴር መ/ቤቱ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት በከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር፣ የኮንስትራክሽንና መሠረተ-ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ፣ ወ/ሮ መዲና መሀመድ እንደተናገሩት የኮንስትራክሽን ዘርፉን  በስነ ምግባርና በአሠራር ስርዓት እንዲደገፍ ለማድረግ የህግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት አስፈላጊ እንደሆነና በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታትና ዘርፉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች ሙያዊ አተያይ የማይተካ ሚና እንዳለው በማስታወስ ከተሳታፊዎች በርካታ ሀሳብና አስተያየት እንደሚገኝ ሙሉ እምነት እንዳላቸው በመግለጽ ተሣታፊዎች ጥሪውን አክብረው ስለተገኙ ያላቸውን አክብሮትና ምስጋና ገልጸዋል፡፡

የእርሳቸውን ንግግር ተከታትሎ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር ዓባላት ላይ በሚያቀርቡት የሠነድ ማዳበር ውይይት ላይ የጋራ አረዳድ ይዞ ለመውጣት እንዲያስችል  በአማካሪነት የሙያ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ የማህበሩ ዓባል፣ ተስፋዬ ያለው (ኢንጅነር)  ባቀረቡት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ረቂቅ አዋጅ ማስተካከያ ላይ ገለጻ ተደርጎ የጋራ ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀሪዎቹ ረቂቅ ሠነዶች ላይም በሌሎች የማህበሩ ዓባላት የታዩ የማሻሻያ ሀሳቦች ቀርበው የጋራ ውይይት የሚደረግባቸው ይሆናል፡፡

ከማህበር የተወከሉ ኢንጂነሮች ከሚኒስቴር መ/ቤቱ የተላከላቸውን ረቂቅ ሠነድ ሙያዊ አተያይን በተከተለ መንገድ የዓለም አቀፉን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ በሙያው ውስጥ የገጠሟቸውን የአሠራር ችግሮች በማሳያነት በመጥቀስ ግብኣት የሚሆኑ በርካታ ሀሳብና አስተያየቶችን አቅርበው በተሰጡት የማስተካከያና የማሻሻያ ሀሳቦች ላይ የጋራ አረዳድ ለመያዝ የሚያስችሉ የጋራ ውይይቶች በመደረግ ላይ ናቸው፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር ዓባላት ፣ የህግ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ፣ የፖሊሲ፣ ስትራቴጂ ጥናትና ምርምር ስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የስራ ክፍሉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ከመንግስት አካሉና ከግሉ ዘርፍ ማህበራት የተወከሉ ተሳታፊዎች የሰጧቸው ግብአቶች የተዘጋጁትን የህግ ማዕቀፎች ለማሻሻልና ጸድቀው ተግባር ላይ እንዲውሉ በማድረግ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት እንዲችሉ ይህ የግንኙነት አግባብ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ይጠበቃል፡፡

@etconp
👍5❤1🙏1
👉የኢትዮ-ጅቡቲ ትራንስፖርት ኮሪደር ፕሮጀክት አካል የሆነው የአዳማ - አዋሽ ምዕራፍ አንድ አዳማ ኪሎ ሜትር 60 የፍጥነት መንገድ የአስፋልት የማንጠፍ ሥራ ተጀመረ።

🚧የአዳማ-አዋሽ ምዕራፍ አንድ አዳማ ኪሎ ሜትር 60 የፍጥነት መንገድ 61.5 ኪሎ ሜትር  እርዝማኔ  ያለው  ሲሆን ፣ ግንባታው ከአፍሪካ ልማት  ባንክ  እና  ከኢትዮጵያ  መንግሥት  በተገኘ በ 6.6 ቢሊየን  ብር ወጪ  እየተከናወነ ነው። 

🚧ግንባታውን  የሚያከናውኑት  ጂ. ኤም.ሲ  እና  ኤል.አር .ቢ.ሲ.ኤል  የሚባሉ  አለም አቀፍ  ተቋራጮች  በጋራ  ሲሆን የማማከሩን ሥራ የሚያከናውኑት  ደግሞ  ኤል.ኤ.ኤስ.ኤ  እና  ዩ.ኒ.ኮን ናቸው።

🚧ይህ 61 ኪ.ሜ የሚሸፍነው የፍጥነት መንገድ አገናኝ መንገዶችን ፣ ማሳለጫ መንገዶችን ፣ የክፍያ ጣቢያዎችን ፣ የመኪና እና የእግረኛ መሸጋገሪያ ድልድዮችን ያካትታል።

🌟የፕሮጀክቱ አሁናዊ አፈጻጸም 12.5 በመቶ ሲሆን፣ በዚህም የአፈር ጠረጋ፣ የቆረጣ ሥራ፣ የአፈር ሙሌት፣ የሰብ ቤዝ እና ቤዝ ኮርስ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን በእስካሁኑ 1.6 ኪሎ ሜትር የአስፋልት  ማንጠፍ ስራ ተከናውኗል። ከአፈጻጸም ጋር በተያያዘ የሚታዮ መስተጓጉሎችን በመቅረፍ በቀጣይ በተሻለ ፍጥነት እንዲከናወን ከፍተኛ ክትትል እና ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል።

🚧መንገዱ ትልልቅ የድልድይ ግንባታ ፣ ማሳለጫዎችና ማቋረጫዎች ፣ የአቃፊ ግንብ ፣ የመንገድ ዳር የትራፊክ ምልክቶች ፣ የደህንነት ካሜራዎችን ፣ ሌሎች ተጨማሪ ሥራዎችን አካቶ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

🌟ከአዲስ አበባ እስከ አዳማ የሚዘልቀው 80 ኪሎ ሜትር የአዲስ-አዳማ የፍጥነት መንገድ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል ፤  የዚህ መንገድ ቀጣይ ምዕራፍ የሆነው የአዳማ-አዋሽ የፍጥነት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ የመስመሩን የትራፊክ ፍሰት ለማቀላጠፍ ብሉም የተሽከርካሪዎች የጉዞ ጊዜና ዋጋ በመቀነስ አዎንታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር ይሆናል፡፡

🚧ከዚህም ባሻገር የዚሁ የፍጥነት መንገድ አካል ለሆነው የአዋሽ - ሜኦሶ - ድሬዳዋ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የአለም ባንክ የ730 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ማጽደቁ ይታወቃል፡፡

🚧ይኸው የአዳማ-አዋሽ-ሜኦሶ-ድሬዳዋ የፍጥነት መንገድ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ከድሬደዋ-ደወሌ የክፍያ መንገድ ጋር በመተሳሰር ለአዲስ አበባ-ሰመራ-ጋላፊ መንገድ አማራጭ ሆኖ በማገልገል የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ወጪና ገቢ ንግድ ይበልጥ እንዲጠናከር ያስችላል።

@etconp
👍11❤1
👉ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ

🫵የአገልግሎታችንን አድማስ በማስፋት የክቡራን ደንበኞቻችንን ፍላጎት ለማርካት በታማኝነት እንተጋለን

🖱ፕሌት 1mm-30mm any size

🖱jbolt 12mm-32mm

🖱anker bolt

🖱stafa

🖱any modefic work

🚧ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን

📩 @heavenic1 ፃፉልን

ቁ.1  መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር  ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ

0904040477
0911016833
0994941706 ይደውሉ።
👍4🏆2❤1
👉የመቐለ የውሃ ፕሮጀክትን እንደገና ለማስጀመር የአንድ ሚሊዮን ዶላር ዕቃዎች ግዢ ተፈፀመ!

🚧በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን የ መቐለ ከተማን የውሃ ፕሮጀክት እንደገና ለማስጀመር የአንድ ሚሊዮን ዶላር ዕቃዎች ግዢ መፈፀሙን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

🌟በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሳኒቴሽን መሠረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኑረዲን መሐመድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ በክልሉ በተለይ በመቐለ እና ዓዲግራት አካባቢዎች በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጠው የቆዩ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች አሉ፡፡ ፕሮጀክቶቹን ለማስጀመር መንግሥት በትኩረት እየሠራ ነው፡፡

🌟ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከያዛቸው ሁለት ትላልቅ ፕሮግራሞች መካከል በከተሞች ላይ የንፁህ ውሃ እና ሳኒቴሽን ግንባታ እንደሆነ የጠቀሱት ኃላፊው፤ የተቋረጡ የመቐለ እና ዓዲግራት የውሃ ፕሮጀክቶችን ማስቀጠል የዚህ ፕሮግራም አካል ናቸው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

🌟በከተሞቹ ላይ የሚደረገው ግንባታ እስከ አሁን የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች የተቃጠሉ ፓምፖች ለመተካት የግዢ ኮንትራት ተፈርሞ በአስቸኳይ ወደ ግዢ መገባቱን አመላክተዋል፡፡በዚህም የመቐለ ከተማን የውሃ ፕሮጀክት ለማስቀጠል የአንድ ሚሊዮን ዶላር ዕቃዎች ግዢ መፈፀሙን አመላክተው፤ ዓዲግራት የውሃ ፕሮጀክትን የማስቀጠል ሥራም የግዢ ሂደት ላይ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡

🌟እነዚህ ፕሮጀክቶች የውሃ ችግር ቁልፍ መፍትሄ እንደሚያመጡ የጠቆሙት ኃላፊው፤ ሌላ በወረዳ እና አነስተኛ ከተሞች ትኩረት በማድረግ የሚሠራ ፕሮጀክት እንዳለ በመጥቀስ፤ ሥራውን ለመቀጠል የተወሰነ ሲሆን፤ ተግባራዊ የሚደረገውም በራሱ በክልሉ እንደሆነና ገንዘብ ተመድቦ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

🌟ፕሮጀክቱ የጋራ መፀዳጃ ቤቶች ግንባታም የሚያጠቃልሉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ፕሮጀክቱ በአፋጣኝ የውሃና ሳኒቴሽን ችግሮችን እንዲቀርፉ ለማስቻል እየተሠራ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው፤ ቀደም ሲል በክልሉ ላይ ተበላሽተው የነበሩት ትላልቅ የውሃ ፓምፖች እና ጄኔሬተሮች ግዢ ተደርጎ ሥራ እንዲጀምሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡

🌟በተመሳሳይ ፕሮጀክቱ በድርቅ እና በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች በተለይ ቦረና፣ አፋር እና አማራ ክልል ላይም ትኩረት በመስጠት በመንግሥትና በአፍሪካ ልማት ባንክ ፋይናንስ ተደርጎላቸው ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

Via EPA

@etconp
👏5❤2👍2😢1