👉ግጭቶችን የመፍታት ሂደት ላይ የፍርድ ቤት ውሳኔ ተግባቦት (Arbitration)
🌟በኮንስትራክሽን ውሎች አፈጻጸም ላይ የሚከሰቱ ያለመግባባቶች ሊፈቱ ከሚችልባቸው ዘዴዎች አንዱ የሆነው የግልግል ሥርዐትም (Arbitration) አከራካሪነቱ የሰፋ ነው።
🚧የፍትሐ ብሔር ስነስርዓት ሕጋችንና ሌሎች የግልግል ስርዓትን የሚገዙ ህጎቻችን የማይጣጣሙባቸው አጋጣሚዎች ያሉ መሆኑ ይታወቃል።
⏺የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 315(2) (4) ሲታዩ የአስተዳደር ውሎች በግልግል የማይታዩ መሆናቸውን ሲያስገነዝቡ የፍትሐ ብሔር ህጉና ሌሎች በሥራ ላይ ያሉት የመንግሥት ተቋማት ማቋቋሚያ ደንቦች ግን በዚህ ረገድ ግልጽ ክልከላ አላደረጉም።
▶️እንዲሁም የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁጥር በሰ/መ/ቁ 16896 በቀን 16/02/1998 ዓ.ም (ቅጽ 2 ገጽ 75-78 ይመለከታል)።
⏺የአስተዳደር ውሎችን በግልግል ለመጨረስ ስምምነት ማድረግ የሚቻል መሆኑን የሚአይስገነዝብ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶ የነበረ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ደግሞ የቀደመውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም በግልጽ ሳይሻር የአስተዳደር ውሎች የግልግል ሊታዩ የማይችሉ መሆኑን የሚያሳይ ትርጉም በሰ/መ/ቁጥር 127459 መስከረም 23/2010 ዓ.ም በዋለው ችሎት ሰጥቷል።
▶️የዚህ ውሳኔ ይዘቱ ሲታይም የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቂ 315 (2) የአስተዳደር ውልን አስመልክቶ የሚነሳ አለመግባባትን ለመዳኘት የማይችለው የግልግል ዳኝነት አካል ወይም (Arbitrator) ነው የሚል ነው።
⏺ይህ ችሎት በአዋጅ ቁጥር 454/97 የታሰበውን የውሳኔዎች ተገማችነት ዓላማ የሚቃረን ውሳኔ መስጠቱን ከማሳየቱም በላይ በኮንስትራክሽን ውሎች የሚፈጠሩ አለመግባባቶች የሚፈቱባቸውን መንገዶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳርፍ እና ዓለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታ ጋርም አብሮ የማይሄድ ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ጉዳይ ነው (አልማው ወሌ, 2019)
#ConstructionLaw
https://t.me/ETCONpWORK

Telegram
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World
Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK
📩 @Philemona7

👍9
What type of bridge 🌉 is this ?
Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=OGQ5ZDc2ODk2ZA==
Facebook:- https://www.facebook.com/etconp?mibextid=LQQJ4d
@etconp
SPONSOR
ELEGAS ENGINEERING PLC
Elevator and Escalator
📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69
Office:- Bulgariya street awebane trading S.C Bulding 1st floor
Website:- www.elegas.com.tr
Email:- ethiopia@elegas.com.tr

👍3🙏1
👉የደምበል ሐይቅ ዳርቻ በ3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር እየለማ ነው
🌟ሁለተኛ ምዕራፍ የደምበል ሐይቅ ዳርቻ ልማት በሦስት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር ወጪ በተለያዩ ባለሀብቶች አማካኝነት እየተገነባ መሆኑን የባቱ ከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ።
🚧የባቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመዲን ኡስማኢል ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የባቱ ደምበል ሐይቅ ዳርቻ ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ በሦስት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር ኢቨስትመንት በስድስት ባለሀብቶች እየለማ ነው።
🚧እንደ አቶ አህመዲን ገለጻ፤ የደምበል ሐይቅ ዳርቻ ፕሮጀክት በተያዘው ዓመት መጨረሻ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
🚧በከተማ አስተዳደሩ 120 ሚሊዮን ብር ወጪ በመጀመሪያው ምዕራፍ ሐይቁን የማልማት ሥራ ሰርቷል ያሉት ከንቲባው፤ በፕሮጀከጅቱ አሳ መሸጫ ሼዶች፣ በመንገድና መዝናኛ ቦታዎች በመገንባትና ሐይቁን በማስዋብ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል ብለዋል።
🚧በሁለተኛው ምዕራፍ የደምበል ሐይቅ ዳርቻን ለማልማት ከባለሀብቶች ጋር በመሆን ፕሮጀክቶች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆናቸውን ተጠቅሰዋል።
Via ኢ ፕ ድ

👍14❤2
What do we call this structure?
Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=OGQ5ZDc2ODk2ZA==
Facebook:- https://www.facebook.com/etconp?mibextid=LQQJ4d
@etconp
SPONSOR
ELEGAS ENGINEERING PLC
Elevator and Escalator
📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69
Office:- Bulgariya street awebane trading S.C Bulding 1st floor
Website:- www.elegas.com.tr
Email:- ethiopia@elegas.com.tr
Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=OGQ5ZDc2ODk2ZA==
Facebook:- https://www.facebook.com/etconp?mibextid=LQQJ4d
@etconp
SPONSOR
ELEGAS ENGINEERING PLC
Elevator and Escalator
📞 +251 971 71 71 71
📞 +251 994 69 69 69
Office:- Bulgariya street awebane trading S.C Bulding 1st floor
Website:- www.elegas.com.tr
Email:- ethiopia@elegas.com.tr
👍4
Normal Concrete
The concrete in which common ingredients i.e. aggregate, water, cement are used is known as normal concrete. It is also called normal weight concrete or normal strength concrete.
It has a setting time of 30 - 90 minutes depending upon moisture in atmosphere, fineness of cement etc.
The development of the strength starts after 7 days the common strength values is 10 MPa (1450 psi) to 40 MPa (5800 psi). At about 28 days 75 - 80% of the total strength is attained.
Almost at 90 days 95% of the strength is achieved.
Properties of Normal Concrete
Its slump varies from 1 - 4 inches.
Density ranges from 140 pcf to 175 pcf.
It is strong in compression and weak in tension.
Air content 1 - 2 %.
Normal concrete is not durable against severe conditions e.g. freezing and thawing.
╔═════
🌐 join 👇
@ETCONpWORK
╚══ ☆☆☆☆☆══════

👍12👌3
👉ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ (Design bid build)(DBB) VS ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB)
🌟1, ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(Design bid build)(DBB)
✨በኮንስትራክሽን ጉዳይ በአብዛኛው በሀገራችን የሚሰራበት የፕሮጀክት አይነት ዲዛይኑን አሰሪው በራሱ መንገድ እንዲዘጋጅ ካደረገ በኃላ ግንባታውን በተቋራጭ እንዲከናወን የሚያደርግበት ነው ይሄውም ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ (Design bid build)(DBB) በመባል ይታወቃል፡፡
⏺በዚህ የፕሮጀክት አይነት የታቀደውን ግንባታ ዲዛይኑን አሰሪው በራሱ አርክቴክት ወይም በሌላ ሶስተኛ ወገን/ በሌላ አርክቴክት ድርጅት/ እንዲከናወን ያደርጋል፡፡
⏺በመቀጠልም በተዘጋጀው ዲዛይን መሰረት ግንባታውን የሚያከናውን ተቋራጭ ወደመምረጥ ሂደት ይገባል፡፡
⏺የግንባታው ባለቤት የመንግስት መስሪያ ቤት የሆነ እንደሆነ ግንባታውን የሚያከናውን ተቋራጭ የመምረጡ ስራ የሚከናወነው በግዥ ህግ መሰረት ይሆናል፡፡ይሄ አይነቱ ፕሮጀክት በሀገራችን የተለመደ ነው፡፡
🌟2, ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB)
✨በሌላ በኩል ደግሞ ተቋራጩ ዲዛይኑን እና ግንባታውን በራሱ የሚያከናውንበት የፕሮጀክት አይነትም አለ።ይሄውም ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB) ይባላል፡፡
⏺በዚህ የፕሮጀክት አይነት ተቋራጩ የታቀደውን ግንባታ ዲዛይኑን በራሱ አርክቴክት ወይም በሌላ የአርክቴክት ድርጅት አማካይነት ያከናውናል፡፡
⏺የአርክቴክት ስራው የሚያስከትለው ሀላፊነት የተቋራጩ ይሆናል፡፡
⏺ከዲዛይን ስራው ጋር የተያያዘ ችግር የሚያስከትለው ሀላፊነት አሰሪውን/የግንባታውን ባለቤት አይነካውም፡፡
⏺ሆኖም ተቋራጩ ዲዛይኑን ያሰራው በሌላ የአርክቴክት ድርጅት አማካይነት የሆነ እንደሆነ ከአርክቴክቸር ስራው ጋር በተያያዘ ተቋራጩ ለአሰሪው የሚኖርበት ሀላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ አርክቴክቱም ለተቋራጩ በፍትሀብሄር ህጉ ስለእውቀት ስራ ውል በተደነገገው አግባብ ሀላፊነት ይኖርበታል ማለት ነው፡፡
▶️በዚህ አይነት ፕሮጀክት የግንባታው ባለቤት/አሰሪው ሙሉ በሙሉ የኮንስትራክሽን ስጋቶችን/risks/ ወደ ተቋራጩ ያስተላልፋል፡፡
▶️ይህ ማለት አሰሪው ውጤቱን ማለትም ግንባታውን በመጀመሪያ በቀረበለት ዲዛይን አግባብ በጥራት ተከናውኖለት ከመረከብና በውሉ የተቀመጠውን የግንባታ ዋጋ ከመክፈል ባለፈ ማናቸውም አይነት ሀላፊነት አይኖርበትም ማለት ነው፡፡ለአብነት ለመጥቀስ ያህል የኢትዮጽያ መንገዶች ባለስልጣን (ERA) ዲዛይን ቢዩልድ የመንገድ ፕሮጀክት ሲኖረው ተወዳዳሪ ተቋራጮች የሰርቨየይንግና ዲዛይን ስራዎችን በራሳቸው ከሰሩ በኋላ በዋጋ ይወዳደራሉ፡፡
⏺ተቋራጮቹ ዲዛይኑን ሲሰሩ አሮጌ ድልድዮች ካሉ እና ተጠግነው በአዲስ ድልድይ የጥራት ደረጃ መድረስ የሚችሉ ከሆነ ተቋራጮች እንደየፍላጐታቸውና ሙያዊ ምርመራቸው/ምክንያታቸው ተጠጋኝ ድልድይ እና በአዲስ የሚገነባ ድልድይ እያሉ በዝርዝር በዲዛይን አካተው የሚያቀርቡ ሲሆን ምንም ሆነ ምን በውጤት ደረጃ አሰሪው በሚፈልገው የጥራት ደረጃ/ስታንዳርድ መገንባቱ እና ይሄውም በአማካሪው መረጋገጡ ግን የግድ ነው፡፡
⏺ምናልባት ተጠግኖ በሚፈለገው የጥራት ደረጃ ይደርሳል የተባለው አሮጌ ድልድይ በጥገና ወቅት ቢፈርስ እንኳ አሰሪውን ክፍያ የመጨመር ሀላፊነት አያስከትልበትም፡፡
⏺ስለዚህ ዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት ለአሰሪዎች ሪስክ ፍሪ/ከስጋት ነጻ የሆነ የፕሮጀክት አይነት ነው፡፡
⚡️ሌላው ሁለቱም የፕሮጀክት አይነቶች ለኮንስትራክሽን ውላቸው የሚጠቀሙት ጀኔራል ኮንዲሽን የተለያየ ነው።FIDIC በዚህ ረገድ የግንባታ ውል ዝግጅትን በማቅለል ለአለማችን ትልቅ ስጦታ ነው። አለበለዚያ አሰሪና ተቋራጭ በየአንዳንዱ ውል ዝግጅት ወቅት በሁሉም የውል ሁኔታወች ላይ መደራደርን ይጠይቃቸው ነበር።
⏺ዛሬ ላይ ግን ለውሉ ጥቅም ላይ የሚውለውን ጀኔራል ኮንዲሽን አስመልክቶ FIDIC ቨርሽን መረጣ እና በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት በሚካተቱ ነጥቦች ላይ ብቻ መወያየት በቂ ነው።
✨በተጨማሪም በዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት የኮንስትራክሽን ስጋት/ሪስክ ሙሉ በሙሉ ወደ ተቋራጩ የሚተላለፍ በመሆኑ ልዩ የዋስትና ሽፋን ያስፈልገዋል፡፡ስለዚሁም ተቋራጩ በግንባታው ዋጋ ልክ All risk insurance እንዲገባ እና ለዲዛይን ስህተት፣ለስራው ብልሽትና በተቋራጩ ባለሙያወች የስራ ስህተት ለሚከሰት ጉዳትና ኪሳራ ደግሞ professional indemenity insurance እንዲገባ FIDIC ዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት ኮምፖቴብል የሆነው ተርንኪ ጀኔራል ኮንዲሽን ግዴታ ያስቀምጣል።
✨በሀገራችን ዲዛይን ቢዩልድ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ብዙም የተለመደ አይደለም።
⏺ሆኖም በመንገድ ግንባታ ውሎች የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አልፎ አልፎ ይጠቀምበታል።
⚡️በአጠቃላይ በሀገራችን በኮንሰትራክሽን ዲዛይኒንግ እና የውል አስተዳደር ረገድ ሰፊ የእውቀት ክፍተት ያለ በመሆኑ እና ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ገንዘብ የማይጠናቀቁበት ሁኔታ በሰፊው የሚስተዋል እንደመሆኑ ሙሉ የኮንስትራክሽን ሪስክ/ስጋት ወደ ተቋራጩ በማስተላለፍ መንግስታዊ ግንባታዎችን በዲዛይን ቢዩልድ የፕሮጀክት አይነት እንዲከናወኑ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ሊሆን እንደሚችል ለመጠቆም እወዳለሁ።
#ConstructionLaw
📍ለበለጠ የ ኮንስትራክሽን ጨረታ እና ስራ ቅጥሮች ከታች ባለው ሊንክ ይወዳጁን

👍18❤10🙏2
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ
፦ፕሌት 1mm-30mm any size ቆርጠን በስተን ጣጣዉን ጨርሰን እናስረክቦታለን
፦jbolt 12mm-32mm በፈለጉት ቁመት ጥርስ አዉጥተን አጥፈን እንሰጦታለን
፦ankerbolt
፦stafa(ስታፋ ባለ 6 እና ባለ 8)በየትኛዉም size የተዘጋጀ አለን
፦ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን
፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን
አድራሻችን
ቁ.1 መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ
0904040477
0911016833
0994941706
ይደዉሉልን ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም ቢሆኑ ካሉበት እንልክልዎታለን።

👉ኮንስትራክሽን "Construction” ስለሚለው ቃል የኢትዮጵያ ሕጎች ይስማማሉ ወይ?
🌟የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል “ለመኖሪያም ሆነ ለሌላ አገልግሎት እንዲሆን ከድንጋይ ከሸክላ ከብረትና ከመሳሰሉት ነገሮች የሚሰራ ፎቅ ያለው ወይም የሌለው ቤት” ሕንጣ ይባላል እንጂ ኮንስትራክሽን የሚል ስያሜ አልሰጠውም (የኢ.ቋ.ጥናትና ምርምር, 1993)።
⏺በተጓዳኝ ደግሞ BATCODA Specification በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 327/1979 አንቀጽ 2(1) ኮንስትራክሽን የሚለውን ቃል ለሁለት ክፍል ሰጥቶ የሕንጻ ኮንስትራክሽን እና የመንገድ ኮንስትራክሽን በማለት ይከፍለዋል።
▶️የሕንጻ ኮንስትራክሽን የሚለውን ሀረግ “ማንኛውም በከፊል ወይም በሙሉ የወለል የግድግዳና የጣሪያ ሥራ ያለው ለመኖሪያ ወይም ለሌላ አገልግሎት የሚውል ሕንጻና ተዛማጅ ሥራዎችን የመስራት ወይም የማሻሻል ሥራ ው” የሚል ብያኔ የሰጠ ሲሆን በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 327/1979 አንቀጽ 2(2) ሥር የትራንስፖርት ኮንስትራክሽን በሚል ዘርፍ “የሐረግ መንገዶች፣ ድልድዮች፣ የባቡር ሀዲዶች፣ የአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ የወደቦችና የየብስ ማመላለሻ ተርሚናሎች የመሥራት ወይም የማሻሻል ሥራ” እንደሆነ ተርጉሟል።
⏺የኢ.ፌ.ድ.ሪ መንግሥት የግንባታ ግዢና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 430/1997 አንቀጽ 2(ሐ) እና አዋጁን በሻረው አዋጅ ቁጥር 649/2001 አንቀጽ 2(3) “የግንባታ ዘርፍ” ለሚለው ትርጉም “የግንባታ ዘርፍ ሥራ ማለት ከሕንጻ፣ ከመንገድ ወይ ከመሰረተ ልማት ሥራ ጋር በተያያዘ የሚከናወን አዲስ ግንባታ፣ የመልሶ ግንባታ፣ ደረጃ የማሳደግ፣ የማፍረስ፣ የጥገና፣ የማደስ ሥራ እንዲሁም ተጓዳኝ የሆነና ከዋናው ሥራ ያልበለጠ ዋጋ ያለው አገልግሎት ሲሆን፣ የመገንባት፣ በባለቤትነት የመያዝ፣ ሥራውን የማንቀሳቀስ፣ የማስተላለፍ ወይም የመገንባት፣ የማንቀሳቀስ የማስተላለፍ ወይም የመገንባት፣ በባለቤትነት የመያዝ የማንቀሳቀስ ውል” በማለት ኮንስትራክሽን የሚለውን ቃል ምን ያክል ሰፊ እንደሆነ በሚያስገነዝብ መልኩ አስቀምጦታል።
▶️በ2006 ዓ.ም በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ ደግሞ “ኮንስትራክሽን ማለት የመሬት ውስጥ ወይም ከመሬት በላይ ያለ ንብረትና አገልግሎትን የሚፈልግ የማሳደግ፣የማስፋፋት፣ የመዘርጋት፣ የመልሶ ግንባታ፣ የጥገና፣ የዕድሳት፣ የማበልጸግ፣ የመቀየር፣ የቁፋሮ፣ የመንቀል ወይም የማፍረስ የሕንጻ ወይም የማንኛውም ምህንድስና ሥራ ነው - Construction” means a provisions of combination of goods and services carried out under or over ground for the development, extension, installation, repair, maintenance, renewal, renovation, alteration, excavation, dismantling or demolition of a fixed asset including building and engineering infrastructure.” ይላል።
🚧በ2001 ዓ.ም የወጣው የሕንጻ አዋጅ ቁጥር 324/2001 አንቀጽ 2(9) ደግሞ ግንባታ ማለት አዲስ ሕንጻ መገንባት ወይም ነባር ሕንጻ ማሻሻል ወይም አገልግሎቱን መለወጥ ነው - Construction" means the construction of a new building or the modification of an existing building or alteration of its use” በማለት አስቀምጧል።

👍12❤3
በአዲስ አበባ የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ በቅርቡ ይጀመራል
በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ የማረጋገጥ ሥራ በቅርቡ እንደሚጀመር የከተማዋ የመሬት፣ ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ። እስከ 2016 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ330 ሺህ በላይ ቁራሽ መሬቶችና የጋራ መኖሪያ ቤቶች በካዳስተር ሥርዓት እንደተመዘገቡም ተገልጿል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ግፋወሰን ዴሲሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በከተማዋ በ80 ሺህ የመሬት ይዞታዎችን እና 80 ሺህ ባለመብቶችን የማረጋገጥ ሥራ በቅርቡ ይጀመራል።
የመሬት ይዞታ የማረጋገጥ ሥራው ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በስተቀር በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተግባራዊ ይደረጋል ያሉት አቶ ግፋወሰን፤ ይህ የይዞታ ማረጋገጥ እወጃ ከተላለፈ ከአሥራ አምሥት ቀን በኋላ የይዞታ ይረጋገጥልኝ ጥያቄዎች ማቅረብ ይቻላል ብለዋል።
Via ኢፕድ

👍6❤1
👍6🙏3❤1
👉Big 5 Global Construction Exhibition kicks off
🌟The annual Big 5 Global Construction Exhibition has officially been opened at Dubai's World Trade Center in the United Arab Emirates.
🚧Ethiopian Construction Works Corporation is among the thousands of exhibitors in this annual hub for the global construction industry which attracts attendees from more than 150 countries.
🚧By being an exhibitor, the corporation has found the event very relevant for showcasing and forging partnership in the industry.
🌟This year's Big 5 Global Construction Exhibition lasts for the next four consecutive days.
🖱Big 5 Global Construction Exhibition is believed to be the largest and most influential event for the construction industry.

👍7❤1
👉የግንባታ ቦታ ነጥቦችን መለየት (Site Setting Out) ልየታ ላይ ተቆጣጣሪ መሐንዲሱ ማረጋገጥ ያለበት ነጥቦች
🚧በግንባታ ሥራ ከቦታ መጥረግ ቀጥሎ የሚሰራው ሥራ የግንባታ መስመሮችን (Axis) እና የስትራክቸር መሰረታዊ ማዕከላዊ ነጥቦችን (Center of structures/column) መለየት ነው። ይህ ሥራ የግንባታ ቦታ ነጥቦችን መለየት የሚባል ሲሆን መሐንዲሱ ማረጋገጥ ያለበት ነጥቦች፦
⏺1) የተዘጋጀ ቦታ መሆኑን ፦ የግንባታ ቦታ ነጥቦችን መለየት (Site Setting Out) ከመከናወኑ በፊት ሲባጎ የሚወጠሩባቸው ችካሎች ወይም የጂፒኤስ (GPS) መሳሪያ የሚያመለክትባቸው ነጥቦች ከፍታ (Elevation of setting out strings) በውል እንዲታወቅ እና ተፈጥሯዊ የላይኛው የመሬት ክፍል ያለበት ክፍታ (Top Surface /Elevation/ of Original Ground Level) የተለየ መሆን ስላለበት የግንባታ ቦታ ጠረጋ በሚገባ የተከናወነ መሆኑን እና ተፈጥሯዊ የመሬት የላይኛው ክፍል የተደረሰበት መሆኑ ማረጋገጥ አለበት።
⏺2) መሪ ንድፍ (site plan) መኖሩን እና በዚያ መሰረት እየተከናወነ መሆኑን፦ መሐንዲሱ አንድ ሕንጻ የሚያርፍባቸውን መሰረታዊ ነጥቦት (Axis & Center) ልየታ በሚከናወንበት ሰዓት ሕጋዊ የሆነ መሪ የቦታ ንድፍ (site plan) ያለው እና በግንባታ ቦታው ላይ የሚገኝ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።
⏺3) ዋና ዋና ፍርግርግ መስመሮች (main grid/Axis/ lines)፦ የግንባታው ሁለትዮች አቅጣጫዎች (X-axis and Y-axis) የሚገናኙበትን የሚያመለክቱ ፍርግርግ መስመሮች መኖራቸውን፣ ከፍታ ልዩነት አለመኖሩን (water level) ማረገግጥ አለበት። በዚህም መሰረት እርስ በእርሳቸው የሚገናኙበት አንግል እና አንዱ ከሌላው ያለው ማዕከላዊ ርቀት (centerline dimensions) በስትራክቸራል የመሰረት አቀማመጥ ዲዛይኑ (Structural foundation layout) ላይ በተመለከተው ልኬት መሰረት ምንም አይነት የልኬት ክፍተት የሌለባቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ አለበት።
⏺4) የስትራክቸር ክፍሎች መገኛ (Location of Structural Elements):- በዋናነት እያንዳንዱ የስትራክቸሩ ምሰሶዎች/ቋሚ አምዶች ማዕከላዊ ነጥብ(Columns centerline)፣ እና የስትራክቸሩ ምሰሶዎች የሚያርፉባቸውን አካላይ ነጥቦት (Coordinate points)፣ የምሰሶ ጫማ ስፋት (Footings coverage area) የሚያመለክት መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።
⏺5) የአጥር ሥራ (fencing or barbed)፦ በሚቆፈረው የመሬት ክፍል ውስጥ ማየት የተሳናቸው፣ ሕጻናት፣ በጨለማ የሚጓዙ መንገደኞች፣ እንስሳት እንዳይወድቁና አካላዊ ጉዳት እንዳይደርስ፤ በተጨማሪም በግንባታው ክልል ውስጥ የሚገኙ እንደ ሚስማር፣ ብረት፣ እንጨት አይነት ግብአቶች እንቅፋት በመሆን ጉዳት እንዳያስከትሉ፣ ወይም በግንባታ ቦታው ውስጥ ያሉ የግንባታ ግብአቶች፣ ማሽኖች፣ እቃዎች፣ እና ሌሎች ንብረቶች እንዳይዘረፉ ለመከላከል የግንባታ ቦታው የታጠረ ወይም የተከለለ መሆኑ ማረጋገጥም የክትትል መሐንዲሱ ሥራ ነው።

👍16👌3❤2💯1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉ለመገንባት የፈጀው 2.5 ቢሊዮን ዶላር ስለሆነው፣ የውጪ አካሉ በ1.2 ሚሊዮን LED የታጀበና ባለ 54ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት (ወይንም 10 የኳስ ሜዳዎችን የሚያክል ስፋት ያለው) HD ቪዲዮ ማጫወት የሚችል ስክሪን ስለለበሰው፣ ውስጡ 18 ሺህ ሰው ማስቀመጥ የሚችልና 15 ሺህ ክሬ ሜትር ስፋት ያለው 360 ዲግሪ እይታን የሚሰጥ ባለ 16K HD ስክሪን ስላለው፣ 167ሺህ ስፒከር ያለው ሳውንድ ሲስተም ስለተካተተለት እና በላስ ቬጋስ ውስጥ በቅርቡ ተገንብቶ አገልግሎት ስለጀመረው Sphere ስለተሰኘው ክብ ቅርጽ ስላለው አዳራሽ አስደናቂ የስነ-ህንፃ፣ የምህንድስና፣ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ጥምረት የሚያስቃኘውን ፕሮግራም ነው ተጋበዙልን።
⚡️162 MB ስለሆነ WIFI ቢጠቀሙ🙏
Via Tech Talk With Solomon
@etconp
⚡️162 MB ስለሆነ WIFI ቢጠቀሙ🙏
Via Tech Talk With Solomon
@etconp
❤4👍2
Forwarded from Ethiopian Construction Vacancy & Tender
👉ማሳሰብያ ለ ውድ ቤተሰቦቻችን
🌟በ @ETCONpWORK በኩል ስራ ስታገኙ እና ያገኛቹ በ @ETCONpBOT አሳውቁን።
📩በዚህ አጋጣሚ የ ኮንስትራክሽን ባለሞያዎች የምትፈልጉ ድርጅቶች እንደ ሁሌው ላኹልን በነፃ እንለጥፍላቹዋለን።

👍10❤1
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ
፦ፕሌት 1mm-30mm any size ቆርጠን በስተን ጣጣዉን ጨርሰን እናስረክቦታለን
፦jbolt 12mm-32mm በፈለጉት ቁመት ጥርስ አዉጥተን አጥፈን እንሰጦታለን
፦ankerbolt
፦stafa(ስታፋ ባለ 6 እና ባለ 8)በየትኛዉም size የተዘጋጀ አለን
፦ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን
፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን
አድራሻችን
ቁ.1 መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ
0904040477
0911016833
0994941706
ወይም @heavenic1 ፃፉልን

👍2
👉አንድ ከመሬት ወለል ውጪ ያለ ኮንክሬት ወለል ፎርምወርክ ሥራ ላይ መሐንዲሱ ቁጥጥር ማድረግ ያለበት መሰረታዊ ነጥቦች
🚧1. ልኬቱ ከንድፉ ጋር ስለመስማማቱ/Size as per drawing/
⏺የተሰራው የወለል ፎርምወርክ የሚሸፍነው የአየር ክልል በአርክቴክቸራል እና በስትራክቸራል ዲዛይኑ ላይ ከተመለከቱት የተጓዳኝ ወልል ስፋት (Respective floor area) ጋር የተጣጣመ መሆኑ ማረጋገጥ አለብን።
🚧2. የቀጤነት እና አግዳማዊ አንግል መጠበቁን (Horizontal and Vertical angles as required)
⏺ብዙ ሕንጻዎች ቀጥታ በአግዳማዊ ገንዴላ (beam) የታጠሩ አይደሉም።
▶️ከቢም ውጪ የሆኑ ተንጠልጣይ ባለ ሦስት ጎን፣ ወይም ግማሽ ክብ፣ ወይም ሌላ ቅርጽ ያላቸው የኮንክሬት ወለሎች አሉ እነዚህ የኮንክሬት ወለሎች የሚሰሩበት ፎርምወርክ ትክክለኛውን በዲዛይን ላይ የተመለከተ አንግል መከተላቸውን ማረጋገጥ ይገባል በተለይ የወለል ፎርምወርክ ውሃልክ መጠበቅ፣ እንዲሁም የዶም፣ ትራፒዞይድ እና ሦስት ጎን ቅርጽ ያላቸው ወለሎች ልኬት ምንም አይነት ስህተት የማይታገሱ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
🚧3. የጠበቀ ሥራ መሆኑን/rigidity/
⏺የኮንክሬት ወለል ለመስራት የተሰራው ፎርምወርክ የተሸካሚውን ጥብቅነትና ቻይነት (scaffolding rigidity and material capability)፣ የወለል ፎርምወርክ ጥብቅነት እና የመሸከም አቅም አግባብነት (Formwork rigidity and appropriateness of materials) ማረጋገጥ አለብት።
▶️እንደሚታወቀው የኮንክሬት ወለል ሲሰራ የኮንክሬት ክንደት፣ የብረት ክብደት፣ የሰራተኛ ክብደት፣ የማሽን እና ዕቃዎች ክብደት፣ የንፋስ ጫና እና ሌሎች የሚደርሱበትን ግፊት መቋቋም መቻል ያለበት መሆኑ ማረጋገጥ ተገቢ ነው።
🚧4. ፎርምወርኩን ከብረቱ ጋር መለያ በአግባቡ መቀመጡን (Spacer)
⏺የወለል ኮንክሬት ሙሌት ከመከናወኑ በፊት በብረት /ፌሮ/ እና በታችኛውና በጎንዮሽ የወለል ፎርምዎርክ መካከል (between reinforcement and formworks panels) በየትኛውም የወለል ነጥብ ላይ ቢያንስ 2.5ሴ.ሜ የሆነ ክፍተት (space) መኖር አለበት።
▶️ይህ የሚረጋገጠው የመለያ ግብአቶች (spacers) በአግባቡ እና በተመጣጣኝ ርቀት (appropriately and in reasonable distance) ላይ ከተቀመጡ ብቻ ነው።
🚧5. ፎርምወር ግብአት ትክክለኛነት (Formwork panels compatibility)
⏺ለፎርምወርክ ግብአትነት የምንጠቀመው ግብአት አንድ ከሌላው የተጣጣመ፣ የተስማማ መሆን አለበት። በተናጠል ደግሞ የፎርምወርክ ፓኔሎቹ ያልተመሙ፣ አባጣ ጎባጣ ያልሆኑ፣ በዲዛይኑ የተቀመጣ ካልሆነ በቀር አንዱ ከሌላው የከፍታ ልዩነት የሌላቸው መሆን አለባቸው።
🚧6. የወለል መለያ (expansion joint)
⏺በኮንክሪት ወለል መካከል እንደአስፈላጊነቱ ስንጥቆችን ለመከላከል የመለያ መገጣጠሚያዎች አስፈላጊ ናቸው።
▶️ኮንክሪት ከተፈሰሰ በኋላ በስንጥቅ ለመጋለጥ በጣም የተጋለጠ የሚሆንበት ጊዜ ይኖራል በዚያን ሰዓት እንደየአካባቢው ሙቀት መጠን የሚስፋፋውን የመለያ መገጣጠሚያዎች የተቀመጡ ከሆነ የእነርሱን መገኛ ቦታ፣ መጠን እና ትክክለኛነት መለካት ግድ ነው።
🚧7. የዘይት ቅብእ ሥራ (Oiling of shuttering)
⏺የወለል ፎርምወርክ ኮንክሬቱ በሚያገኘው የውስጠኛው ክፍል በሙሉ በተለምዶ ኦሊዮ (Olio) የምንለውን ወይም ኮንክሬቱ ከፎርምወርኩ ጋር የሚፈጠረው ጠንካራ ትስስር እንዳይኖር የሚያደርግ (preventing bonding contact of concrete with formwork surface) ዘይት መቀባቱን ማረጋገጥ አለበን።
🌟ሌላው የ ቅጥር እና ጨረታ የሚወጡበት የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል
https://t.me/ETCONpWORK
📩ሊያገኙን ካሰቡ @ETCONpBOT ይጻፉልን።

👍9❤3