Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉የቤት ባለቤትነት ማረገገጫ/ካርታ/ ለምን ይመክናል?

▶️ካርታ ማምከን ማለት ፡- ከዚህ በፊት በተለያየ አግባብ ተሰጥቶ የነበረ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ በህግ ፊት የፀና እንዳይሆን ወይም ለማንኛውም ህጋዊ አገልግሎት እንዳይውል ማድረግ ማለት ነው።

⏺በማናቸውም ጊዜ የወጡ ካርታዎች ካርታውን ሊያመክን የሚችል ጉዳይ ሲገኝ በየትኛውም ጊዜ እንዲመክኑ ይደረጋል።

▶️ካርታ ሊመክን የሚችልባቸው ዋና ዋና ምክኒያቶች አራት ናቸው።

1ኛ. አንደኛው ምክኒያት ካርታው ወይም ይዞታው በተጭበረበረ ወይም ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ አሰጣጥን ባልተከተለ መንገድ የተገኘ መሆኑ ሲረጋገጥ

2ኛ. ሁለተኛው ምክኒያት ደግሞ በተለያየ ህጋዊ ምክኒያት የሊዝ ውሉ ሲቋረጥ ነው፡፡

3ኛ. ሶስተኛው በባለይዞታው ዕጅ መኖር ያለበት ካርታ መጥፋቱ ሲረጋገጥ በምትኩ ካርታ መስጠት ተገቢ ሆኖ ሲገኝም ካርታ ሊመክን ይችላል፡፡

4ኛ. አራተኛ በከተማው ካቢኔ ሲወሰን ቀደም ሲል የወጣው ካርታ እንዲመክን ይደረጋል።

🚧የአንድ ካርታ ይምከንልን ጥያቄ ጥቆማ ሲቀርብ ተገቢው ማጣራት ሳይደረግበት ጥቆማው ወይም በጥያወቄው መሰረት ብቻ ካርታ አይመክንም።

⏺ሌላው ከዚህ ጋር ተያይዞ የምንመለከተው ጉዳይ ካርታን አግዶ ስለማቆየት ይሆናል።

⏺አንድ ካርታ ወሳኔ ሳያገኝ በዕግድ ሊቆይ የሚችለው ከሶስት ወር ላልበለጠ ጊዜ ብቻ ሲሆን አንድን ካርታ ለማምከን በቅድሚያ ጉዳዩ ተጣርቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ካርታው ታግዶ እንዲቆይ ለባለይዞታው እና ለሚመለከታቸው አካላት በክ/ከተማው ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ አማካኝነት ምክንያቱ ተጠቅሶ በጽሁፍ እንዲያውቁት ማድረግ ይኖርበታል።

▶️በክፍለ ከተማ ደረጃ የተሰጠው የካርታ ይምከን ውሳኔ ላይ የሚነሳ ቅሬታ ለከተማው ፕሮጀክት ጽ/ቤትና ለቢሮው በቅደም ተከተል ቀርቦ ሊታይ ይችላል።

▶️ቅሬታው ተቀባይነት ካገኘ የመከነው ካርታ የዕግድ ደብዳቤ እንዲነሳ ወይም ወደ አገለግሎት እንዲመለስ ይደረጋል። {የይዞታ አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ቁ 12/2004፣ አንቀፅ 16}

🌟የ ኮንስትራክሽን ስራ እና ጨረታ ምንለቅበት የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል

https://t.me/ETCONpWORK
👍12❤5
👉የንድፍ ውድድር አውደርዕይ

🌟የዘመንባንክ የዋናው መስርያቤት ማስፋፍያ ንድፍ ውድድር ተወዳዳሪ ንድፎች በዘመንባንክ ዋናው መስርያቤት በምድርቤት መዳረሻ አዳራሽ ውስጥ ለአውደርዕይ ቀርበዋል።

🫵እስከ ታህሳስ 13 ቀን 2016 ዓም ድረስ በአውደርዕይ መልክ ለተመልካቾች ይቀርባሉ።

🚧ሁላችሁም ተጋብዛችኋል🙏

📸የአውደርዕዩ ምስል ተያይዟል

@etconp
👍12
👉በ168 ሚሊዮን ዶላር የአፍሪካ ሀገራትንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ሊገነባ ነው

🚧በወላይታ ሶዶ ከተማ ከ168 ሚሊዮን ዶላር የአፍሪካ ሀገራትንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ሊገነባ መሆኑ ተገለጸ፡፡

🚧የሔልዝ ኤንድ ሆልነስ ኢትዮጵያ (HAWE) መስራችና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አለውበል አልማው ስለፕሮጀክት ዓላማና አተገባበር ላይ ገለጻ አድርገዋል።

🚧ኢንተርናሽናል ሆስፒታሉ ከ168 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ የሚገነባ መሆኑንና የመጀመሪያው ደረጃ ህንጻ በ20,000 ካሬ ሜትር መሬት ላይ እንደሚያርፍ ጠቅሰዋል።

🚧ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በባህርዳር እና ወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገነባ ሲሆን ሔልዝ ኤንድ ሆልነስ ኢትዮጵያ (HAWE) የተሰኘ አለም አቀፍ እውቅና ያለው ድርጅት ድጋፍ የሚተገበር መሆኑን ገልጸዋል።

🚧ፕሮጀክቱ የአፍሪካ ሀገራትን ጨምር ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን የኩላሊት ንቅለ ተከላ፣ የኦክስጅን ማምረት፣ የጤና ምርምር ማዕከል፣ የኢንተርናሽናል ስብሰባ አድራሻ የያዘ ነው ብለዋል።

🚧ፕሮጀክቱ ከሁለት ዓመት ከስድስት ወር እንደሚጠናቀቅ የተናገሩት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ግንባታው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር ውሉን በማጠናቀቅ በቅርቡ እንደሚጀምርም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

Via አዲስ ዋልታ

@etconp
👍17❤5
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ

፦ፕሌት 1mm-30mm any size ቆርጠን በስተን ጣጣዉን ጨርሰን እናስረክቦታለን

፦jbolt 12mm-32mm በፈለጉት ቁመት ጥርስ አዉጥተን አጥፈን እንሰጦታለን

፦ankerbolt

፦stafa(ስታፋ ባለ 6 እና ባለ 8)በየትኛዉም size የተዘጋጀ አለን

፦ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን

አድራሻችን
ቁ.1  መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር  ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ
0904040477
0911016833
0994941706

ወይም @heavenic1 ፃፉልን

ይደዉሉልን ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም ቢሆኑ ካሉበት እንልክልዎታለን።
👉በፕሮጀክቶች ላይ ለሚፈጠሩ አለመግባባቶች አማራጭ የግጭት አፈታት አገልግሎትን ያግኙ

🚧 “በብዙ የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፎች አለመግባባት ተፈጥሮአዊ መሆኑ ተደጋግሞ የተገለፅ እውነታ ነው፡፡ በህግ ወይንም በውል የተገለፁ መብቶች ያለመከበር እና የይገባኛል ጥያቄዎች ለእነዚህ አለመግባባቶች መፈጠር መሰረታዊ ምክንያት ናቸው፡፡ መሰል ይገባኛል ጥያቄዎችን በአግባቡ መፈታት ያልተቻለ እንደሆነ ጉዳዩ ወደ አለመግባባት ደረጃ የማደግ እድሉ ሰፊ ነው፡፡ ስለሆነም ያለመግባባቶች ከፍ ወዳለ ደረጃ ከማደጋቸውና ለፕሮጀክቶች አፈጻጸም እንቅፋት ከመሆናቸው በፊት መታረም መቻላቸው አስፈላጊ ነው፡፡

ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ በተያዘላቸው በጀት ለማጠናቀቅ ይቻል ዘንድ የተለያዩ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ተጠቅሞ ያጋጠሙ አለመግባባቶችን መፍታት አሁን አሁን ይበልጥ እየታመነበት የመጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡ የግንባታ ዘርፉም ከግጭቶች/ ካለመግባባቶች የፀዳ ባለመሆኑ በተመሳሳይ ዕይታ የሚታይ እና መፈታት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

የግንባታ ሂደት በውስጡ ከሚሳተፉ ባለድርሻዎች፣ ከሚፈስበት መዋዕለ ነዋይ እንዲሁም ከሚወስደው ጊዜ ውስብስብነት ወዘተ አንፃር አለመግባባት መፈጠሩ የሚጠበቅ ነው፡፡ በግንባታ ሂደቶች ውስጥ የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችን መፍታት ፈርጀ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የዘርፉ ባለሙያዎች በስፋት ይገልጻሉ፡፡

ስለሆነም ግጭቶች/ አለመግባባቶች/ ወደ ፍርድ ቤት ከመሄዳቸው በፊት አማራጭ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ሊያጋጥሙ የሚችሉ አለመግባባቶችን መፍታት በተከራካሪ ወገኖች መካከል መልካም ግንኙነትን ከማስቀጠል አኳያ፣ ከህግ ሙያ ውጪ ያሉ ሌሎች ባለሙያዎችን ከማሳተፍ በተጨማሪ ጊዜን፣ ወጪን እና በዳኝነት ተቋማት ላይ የሚፈጥረውን ጫና የሚቀንስ በመሆኑ ይህ አሰራር በግንባታ ዙሪያ የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ ነው፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፌዴራል መንግስት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 1263/2014 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የተቋቋመ እና ስልጣኑንና ተግባሩንም ለመወሰን እንደዚሁ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 524/2015 መሰረት አድርጎ መቋቋሙ ይታወቃል፡፡

ይህን መነሻ በማድረግ በኢትዮጵያ የዳኝነት እና የዕርቅ አሰራር ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1237/2013ን መሠረት በማድረግ እና በደንብ ቁጥር 524/2015 አንቀጽ 5 (16) የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በመንግስት ኮንስትራክሽን ስራዎች ለሚፈጠሩ የውል አለመግባባቶች በሚዘረጋው አሰራር ስርዓት ፕሮጀክቶች/ ተዋዋዮች በአማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች መፍትሄ እንዲያገኙ የማድረግ ስልጣንና ተግባር ተሰጥቶታል፡፡

በዚህም መነሻነት፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በመንግስት ኮንስትራክሽን ስራዎች ለሚፈጠሩ የውል አለመግባባቶች በዘረጋው የአሰራር ስርዓት በአማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች መፍትሄ እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን እየገለፅን ማንኛውም የህንጻና የመሠረት-ልማት ፕሮጀክቶችን የሚያስገነቡ እና እያስገነቡ ያሉ የመንግስት አስፈጻሚ ተቋማት እና የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት በመደበኛ ፍርድ ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶች እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አለመግባባቶችን በአማራጭ የግጭት አፈታት ዘዴዎች መፍታት የሚፈልጉ የመንግስት ተቋማት ወይም ግጭቶችን በአማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴዎች ለመፍታት የህግ ስልጣን ያላቸው ተቋማት አገልግሎቱን ከባለስልጣን መ/ቤቱ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን

@etconp
👍9❤1
👉የአፈርን የመሸከም አቅም (BEARING CAPACITY) እንዴት እንጨምር?

🚧ሶስት አይነት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከያ ቴክኒኮች አሉ እነሱም mechanical, chemical & other stabilization techniques

🌟A) ሜካኒካል ውስጥ :-

▶️1. Compaction - አፈሩን ስንጠቀጥቀው density/ unit
weight ይጨምራል ያ ማለት ደግሞ አፈርን የመሸከም አቅም ጨመረ ማለት ነው::

▶️2. Excavation and Replacement:- expansive soil ከሆነ ወይም ሌላ አስቸጋሪ አፈር ከሆነ ይህን መጠቀም እንችላለን

▶️3. Mixing of Different Soils - ሳይታችን ላይ ያለው አፈር coarse ወይም fine ብቻ ከሆነ ወይም ደግሞ አፈሩ አንድ አይነት ብቻ ፀባይ ካለው ከተለያዩ አፈሮች ጋር በመደባለቅ የተሻለ የአፈር ፀባይ ማግኘት እንችላለን

🌟B) ኬሚካል :-

▶️1. Lime stabilization - ይህንን የምንጠቀመው በአብዛኛው ለ expansive soil ነው አፈሩን ከ Lime ጋር በመደባለቅ plasticity መቀነስ እንችላለን የlime መጠኑ ከሚያስፈልገው በላይ ከበዛ ግን B.C. ይቀንሳል፡፡

▶️2. Cement stabilization - ሲሚንቶን ከአፈር ጋር በመደባለቅ የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት መንገድ ነው፡፡

⏺concrete pavement ስር መጠቀም እንችላለን በአብዛኛው ለአየር
መንገዶች ፤ ለአውራ ጎዳናዎች ፤ ግድቦችን ከሽርሸራ ለመከላከል ወ.ዘ.ተ. መጠቀም እንችላለን፡፡

▶️3. Asphalt stabilization - አስፓልትን ከአፈር ጋር በመደባለቅ
የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት ዘዴ ነው በተለይም ለcohesive አፈሮች፡፡

⏺አፈሩን water proof በማድረግና ውሃማነትን በመቀነስ B.Cን መጨመር እንችላለን፡፡ በአብዛኛው ይህንን ድብልቅ
ለመንገዶች እንደ base course መጠቀም እንችላለን፡፡

🌟C) ሌሎች የአፈርን ባህሪ ማስተካከያ መንገዶች:-

▶️1. Drainage - ፓይፖችን አፈር ውስጥ በመቅበር ወይም ጉድጓዶችን በመጠቀም ground water የምንቆጣጠርበት ነው

▶️2. Precompression - ግንባታ ከመጀመራችን በፊት አፈሩ ላይ
ሎድ በመጫን ኮምፓክት የምናደርግበት ዘዴ ነው

▶️3. Dynamic Stabilization

✨ሀ) Blasting - ቦምብ ወደውስጥ በመቅበር በፍንዳታው አፈሩ ይጠቀጠቃል::

✨ለ) Compaction Piles - ፓይሎችን ወደውስጥ በማስገባት አፈሩ ወደ ጎን እንዲሸሽና እንዲጠቀጠቅ ማድረግ ይቻላል፡፡
⏺ፓይሉን ስናስወጣውም በተቦረቦረው ጉድጓድ ውስጥ የተሻለ አፈር በማስገባት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከል እንችላለን፡፡

▶️4. Injection And Grouting - አፈሩን በሲሚንቶ ወይም በተለያዩ chemical ውህዶች በpressure በመምታት ground water ና settlement መቆጣጠር እንችላለን፡፡

🫵የተሻለውን ዘዴ ለመምረጥ የአፈሩንና የአካባቢውን ሁኔታ ፤
ኢኮኖሚ ፤ ሴፍቲና የመሳሰሉትን ነገሮች ማጤን አለብን፡፡

@etconp
👍18❤6🙏6👌1
👉የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም በ1936 ዓ.ም ተቋቋመ የቀደመ ስሙም አርኪዮሎጂ ሙዚየም በመባል ይታወቃል በዚህ ሙዚየም ውስጥ በርካታ ቅርሶች ይገኛሉ ከቅርሶቹ መካከልም የአርዲን የሰላምን እና 3.4 ሚሊዮን እድሜ ያላትን የሉሲን  ቅሬተ አካሎች እናገኛለን ከተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች  የተሰበበሰቡ ቅርሶች ስላሉትም ትንሿ ኢትዮጵያ እየተባለ ይጠራል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሙዚየም አጀማመር

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሙዚየም በ1936 ዓ.ም የብሔራዊ ቤተ መፃህፍት አካል ሆኖ ተከፍቷል በዚህም ከነገስታቱ ቤተሰቦችና ባለሟሎቻቸው በስጦታ መልክ የተበረከቱ ጥቂት የክብርና የማዕረግ መግለጫ ቅርሶች ለመጀመሪያ ጊዜ በአውደ ርዕይ መልክ ቀርበዋል ከዚህ ጋር ተያይዞ በአርኪዎሎጂ ኢንስቲትዩት በ1946 ዓ.ም áˆ˜áˆ˜áˆľáˆ¨á‰ľ ለሙዚየሙ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡
ይህም በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የፈረንሳይ አርኪዎሎጂስቶች ተልዕኮ ውጤታማ ስራዎችን በማከናወን ጠቃሚ ታሪካዊና የአርኪኦሎጂ ግኝት ለማግኘት አስችሏል በቀጣይነትም ሙዚየሙ የተዛወረው በአሁኑ ሰዓት የብሔራዊ ባንክ ሰራተኞች ክበብ ሆኖ ወደሚያገለግለው ህንፃ  ሲሆን ቀስ በቀስም በ1958 ዓ.ም ወደ አሁኑ ይዞታው መጥቷል፡፡

በ1947 ዓ.ም የተቋቋመው የአርኪዎሎጂ  ሙዚየም ስራውን የጀመረው ከሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተገኙ የአርኪዎሎጂ ውጤቶችን ለእይታ በማቅረብ ነበር ሆኖም በ1958 ዓ.ም ብሔራዊ ሙዚየም የማቋቋም ሀሳብና የኢትዮጵያ የጥንታዊና ታሪካዊ ቅርስ አስተዳደር መመስረት መንግስት ለጉዳዩ ትኩረትና ድጋፍ እንዲሰጥ አድርጎታል፡፡

በመቀጠልም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም በአዋጅ ስራውን የጀመረ ሲሆን ይህም ለጥንታዊ ቅርሶች ጥበቃና እንክብክቤ ህጋዊ ከለላ በማግኘት የአገሪቱን አርኪዎሎጂካዊና ፓሊዩንቶሎጂካዊ  መገኛዎች እንዲሁም የጥንታዊ ህንፃዎችና ሀውልቶች የመጠበቅና የማቆየት ስልጣን አግኝቷል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በሙዚየሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘው አሮጌው ህንፃ የተገነባው በ1928 ዓ.ም ፋሽስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ሲሆን የተገነባውም በወቅቱ ከፋሽስት ኢጣሊያ የጦር መሪዎች አንዱ ለሆነው እና አዲስ አበባን ሲያስተዳደር ለነበረው መኖሪያ ቤት እንዲሆን ነበር፡፡

የፋሽስት ኢጣሊያ የወረራ ዘመን ካበቃ በኋላ ህንፃው ለቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ልጅ ለልዑል መኮንን በመኖሪያነት ሲያገለግል ቆይቶ በመቀጠልም ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተሰጠ በመጨረሻም በ1957 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሁን ወደሚገኝበት ቦታ ሲዛወር ህንፃው ለሙዚየም አገልግሎት እንዲውል ተደረገ፡፡

አዲሱ ቋሚ የትርኢት አዳራሽ ወይም የሙዚየም ህንፃ የተገነባው በዩ.ኤስ.ኤይድ ድጋፍና በግንባታ ሚኒስቴር ተቆጣጣሪነት እ.ኤ.አ ከ1978 እስከ 1981 ዓ.ም ዓ.ም ነው በህንፃው ግንባታ ወቅት የዬኒስኮ አማካሪዎች በኢግዚቢሽን አደረጃጀትና በትርኢት አቀራረብ ከፍተኛ የማማከር ሾል ሰርተዋል ይህ ህንፃ በአሁኑ ወቅት ቋሚ  የትርዒት አዳራሽ በመሆን እያገለገለ ይገኛል፡፡በውስጡም በርካታ ቅርሶች ሲኖሩ ከእነዚህ መካከል በአብዛኛው የአርኪዎሎጂካዊ ግኝቶች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ፡፡

በአለምአቀፍ ደረጃ በጥሬ ኪነህንጻ ሾል መዝገብ (Brutalist architecture) ሰፍሮ የሚገኘዉ ይህ አዲሱ ቋሚ የትርኢት አዳራሽ በነፍሰሔር ህንጻ ነዳፊ በጋሻውበዛ ተስፋሚካኤል የተነደፈ ሲሆን ስራዉ ደግሞ ይህ ህንጻ በአገራችን ከሚገኙት  አይነተኛ ጥሬ ህንጻዎች መካከል  ግንባር ቀደሙ ምሳሌ ነዉ። ገጽታዉ ባልተቀባ አርማታ መጨረሱ፣ መዋቅራዊ አካሎቹ በግላጭ በገጽታዉ መንጸባረቃቸዉ እንዲሁም የመስኮት ክፍተቶች ሳይበዙ ድፍን ያለ ግድግዳ መብዛቱና ጠንካራ ማንነት ያለዉ የዉጭ ደረጃ መጠቀሙ ለስራዉ አለማቀፍ ታዋቂነትን አስገኝቶለታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ስር ካሉት ስራ አስፈፃሚዎች በብሔራዊ ሙዚየም ስራ አስፈፃሚ ስር የሚገኝ ሲሆን የሚገኘውም በአዲስ አበባ ከተማ 5ኪሎ አካባቢ ከቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አጠገብ ነው፡፡

በ1992 ዓ.ም የሙዚየሙ ቋሚ ትርዒት ከአሮጊው ህንፃ ወደ አዲሱ ህንፃ  ተዛውሮ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ዋቢ ኢትዮዽያ ቅርስ ባለስልጣን

#ConstructionHistory

@etconp
👍7👌3👏2
👉በጋራ የኮንስትራክሽን ሥራ ንግድ ፍቃድ ስታወጡ ስለስያሜው
{ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (PLC) እና የአክሲዮን ማህበር (SC) ተመሳሳይነትና ልዩነት}


🚧በኮንስትራክሽን ሥራ ውስጥ አክሲዮን ማኅበር፣ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ሽርክና የሚባሉ ከአንድ በላይ የሆኑ አባላት በጋራ ሆነ ንግድ ፍቃድ የሚያወጡባቸው ዘርፎች አሉ እነዚህ ስያሜዎች በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ዉስጥ ካሉት የንግድ ማህበራት መካከል የሚጠቀሱ ሲሆን በዚህ ክፍል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር—ኃ.የተ.የግ.ማ (Private Limitted Company - PLC) እና የአክሲዮን ማህበር - አ.ማ (Social Company - SC) ያላቸውን አንድነትና ልዩነት እንመለከታለን። ሁለቱም ማህበራት አክሲዮን ያላቸዉ ወይም ካምፓኒዎች ሲሆኑ ተመሳሳይነትና ልዩነት አላቸዉ።

🌟ተመሳሳይነታቸዉ

• ህጋዊ ሰዉነት ያላቸዉ መሆኑ ፣
• የራሳቸዉ ንብረት ያላቸዉ መሆኑ፣
• የራሳቸዉን ትርፍና ኪሳራ ተጠያቂነት ያለባቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም ትንሹ የአባላት ብዛትና የመነሻ ካፒታል ያላቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም በቦርድና በማናጀር መመራት የሚችሉ መሆኑ ነገር ግን ለ PLC አሰገዳጅ አለመሆኑ፣
• የሁለቱም ተጠያቂ በተዋጣዉ የገንዘብ መጠን (አክሲዮን ) መሆኑ ፣
• ሁለቱም የሙያ መዋጮን የማይቀበሉ መሆኑ
• በሁለቱም ካፒታል ማሳደግና መቀነስ የሚቻል መሆኑ ፣
• በሁለቱም አክሲዮኖች በመያዣ /በዋስትና / መያዝ ሚችሉ መሆኑ ፣

🌟ልዩነታቸዉ

⏺አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር / PLC/ private Limited Company/ ለማቋቋም የአባላት ብዛት ከሁለት ማነስ የማይችሉ መሆኑ እንዲሁም ከሀምሳ መብለጥ እንደማይችሉ በንግድ ህጉ ተገልጿል። የአክሲዮን ማህበርን (share company) በተመለከተ ለማቋቋም ከ5 አባላት ማነስ የማይችል ሲሆን ብዛት ግን ገደብ የሌለዉ መሆኑን በንግድ ህጉ ላይ ይገኛል።

〰️ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መነሻ ካፒታል 15000 ሺህ ብርና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋም በኢትዮጵያ ብር አንድ በመቶ ማነስ አይችልም።
〰️ አክሲዮን ማህበር መነሻ ካፒታል 50000 ሺህ እና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋ ከአንድ መቶ ብር በታች መሆን አይችልም
〰️ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ካፒታሉ ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የተከፈለ ሲሆን የአክሲዮን ማህበር ግን ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የሚከፈል አይደለም ነገር ግን ከተፈረሙ አክሲዮኖች ቢያንስ 1/4 (25%) መከፈል አለበት የቀረዉ በሂደት የሚከፈል ይሆናል
〰️ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የአክሲዮኖች ሽያጭ ለህዝብ ክፍት የሚደርግ አይደለም  ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ለህዝብ ክፍት የሚደረግ ነዉ
〰️ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC) ላይ አክሲዮን ማህበር ዉስጥ ያለ ሰዉ አክሲዮኑን ለሶስተኛ ሰዉ ማስተላለፍ አይችልም ምክንያቱም መተዳደሪያ ደንቡ ላይ አባላት ይህን እስካልፈቀዱ ድረስ በህጉ መሰረት sale freely transfrable አይደለም። ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ላይ አክሲዮን ማስተላለፍን በተመለከተ አክሲዮን የገዛ ሰዉ አክሲየኑን ለሌላ አባል ላልሆነ ሰዉ በቀላሉ ማስተላለፍ ይችላል ። ስለዚህ አክሲዮን ማስተላለፍ ከተፈለገ በቀላሉ የአክሲዮን ማህበርን መምረጥ ያስፈልጋል ማለት ነዉ።
〰️ አስተዳደራዊ አካል (ቦርድ) ን በተመለከተ አክሲዮን ማህበራት ሁሉ ከ3-12 ሰዉ የሚይዝ ቦርድ ኦፍ ዳይሬክተር ሲቋቋም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (plc) ዉስጥ የቦርድ መዋቅር ግዴታ አይደለም።

🖱ምንጭ፦ ሳሙኤል ግርማ  — የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ

🌟የኮንስትራክሽን ስራ እና ጨረታ በ ትኩሱ እንዲደርሶ ከታች ባለው ሊንክ ይወዳጁን

https://t.me/ETCONpWORK
👍35
👉የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱን 5 ቢሊየን ዶላር ሚያወጣ ‘የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተማ’ ግንባታ በአራት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሠራ መሆኑን ገለጸ፡፡

🌟አየር መንገዱ “ኤርፖርት ሲቲ” ብሎ የሚጠራውን ግንባታ ለመጀመር ከጫፍ የደረሰው እየጨመረ የመጣውን የደንበኞች ፍላጎት ለማርካት መሆኑን የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የንግድ ሥራ ዘርፍ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ለማ ያደቻ ተናግረዋል፡፡

🚧የ ‘አየር መንገድ ከተማው’ ካልተገነባ ዓየር መንገዱ በዘርፉ እያስመዘገበ ካለው ፈጣን ዕድገት አንጻር እንደሚፈተን ከግምት ውስጥ በማስገባት ፕሮጀክቱ መታቀዱን አብራርተዋል፡፡

🚧ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 5 ቢሊየን ዶላር በጀት የተያዘለት ሲሆን፥ በዓመት 100 ሚሊየን መንገደኞችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።

🚧አሁን ላይ አየር መንገዱ በኦሮሚያ ክልል ከቢሾፍቱ ከተማ ጥቂት ወጣ ብሎ በሚገኝ ሥፍራ የመጀመሪያውን የ ‘አየር መንገድ ከተማ’ ግንባታ ለማስጀመር በዝግጅት ላይ ነው፡፡

🚧ፕሮጀክቱ ዘመናዊ ሆቴሎች ፣አፓርትመንቶች፣ ከቀረጥ ነፃ የግብይት ሥፍራና የካርጎ ሎጂስቲክስ ማዕከል እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡

✨የአዋጭነት ጥናቱን በማጠናቀቅም ለዓለም አቀፍ ጨረታ ለማውጣት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል፡፡

@etconp
👍9😢7❤4
👉የመንግሥት መሥሪያ ቤት በሚያስገነባቸው ግንባታዎች ላይ ትዕዛዝ መሥጠት

🚧“አንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት በሚያስገነባቸው ግንባታዎች ላይ በግንባታ ሒደት ውስጥ ለተቋራጩ የስራ ትዕዛዞችን እየሰጠ፣ የስራዎቹን አካሄድ የመወሰንና ስራው በሚፈቅደው አይነት እንዲፈፀም የስራ ተቋራጩን የማዘዝ ሥልጣን ያለው ሲሆን፣ ተቋራጩ በበኩሉ በአሠሪው የመንግሥት መሥሪያ ቤት በተሰጡት ፕላኖች አይነቶችና የዋጋና የስራ ማስታወቂያ መሰረት ጠንቅቆ የግንባታ ሥራውን የመስራት ግዴታ እንዳለበት በፍ/ብሔር ህግ ቁጥር 3252 ንዑስ አንቀጽ 1 እና ንዑስ አንቀጽ 2 በግልፅ ተደንግጓል።

🌟ነገር ግን የጨረታ ሰነዱ በሚወጣበት ጊዜ በግንባታ ዲዛይኑ ላይ ከተመለከተው ልኬት በታች ሆኖ በኋላ በዲዛይኑ መሰረት ለሚሰራ ግንባታ የሥራው ባለቤት በግንባታው ሥራ ውል ሰነዱ ላይ ከተመለከተው ክፍያ ውጪ በተጨማሪነት በባለቤቱ ፈቃድና ትዕዛዞች መሠረት ለተሠሩ ሥራዎች ክፍያ ለመክፈል የሚገደድ ሲሆን በህጉ አግባብ በባለቤቱ የተሰጡ ተጨማሪ የሥራ ትዕዛዞች የሥራ ውሉ አካል ተደረገው የሚወሰዱ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ.3244, 3225,(1)(2), 3152(1), 3266(1), 3263, 3265(3) በዝርዝር ተዳስሰዋል።

⏺በተለይ አሠሪው መሥሪያ ቤት በሚመለከተው ክፍል ማህተም ያለበት ደብዳቤ ተጠቅሞ አልያም በተመደበው ተቆጣጣሪ ፊርማ ሥራዎችን እያጸደቀና እያዘዘ እንዲሰሩ የተደረጉ ሥራዎች በፍ/ብሔር ሕግ ቁጥር 3152 ንዑስ አንቀጽ 1 እና በፍ/ብሔር ህግ ቁጥር 3266(1) ድንጋጌዎች መሰረት የሰጣቸው ተጨማሪ የስራ ትዕዛዞች የግንባታ ሥራ ውሉ አካል ተደርገው የሚያዙ ናቸው።

🚧የ መወያያ ግሩፓቹ ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ ቤተሰብ ይሁኑ

https://t.me/COTMp
👍9🏆2
👉"የቤት ዋጋ በኢትዮጵያ በመቀነስ ላይ ነዉ" - ኪ ሃዉሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን

🌟
ኪ ሃዉሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን የቤት ችግር ችግርን ለመቅረፍ አዲስ በጀመረዉ አሰራር ተጠቃሚ የሆኑ ደምበኞቹን የቤት ባለቤት ለማድረግ በዛሬዉ እለት ከሪስልስቴት አልሚ ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሷል።

🚧ተቋሙ በመጪው ታህሳስ 27 ባለእድለኛ ለሆኑ ደምበኞቹ በቁጥር ያልተጠቀሱ ቤቶችን እንደሚያስተላልፍ አስታዉቋል።

🚧ከተቋሙ ጋር በጋራ የሚሰራዉ የብሉ ዞን ማርኬቲንግ ስራ አስኪያጅ አቶ ቸርነት መንግስቴ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ፤ በኢትዮጵያ በመተዋወቅ ላይ ባሉ አዳዲስ የግንባታ ጥበቦች እና ቴክኖሎጂን መጠቀም መጀመር ምክኒያት በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ላይ ቅናሽ እያሳየ መሆኑን ገልጸዋል።

🌟ለአብነትም ፕራይም ኮት የተሰኘ የሲሚንቶ ልስንን የሚያስቀር አሰራር እስከ 12 በመቶ አጠቃላይ የግንባታ ወጪን እንደሚቀንስ ተናግረዋል። በተጨማሪም አልሙኒየም ፎርዎርክ በዘርፉ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እያሳደረና ወጪ እየቀነሰ መምጣቱን ገልጸዋል። በአሁኑ ሰዓት ከአስፈላጊ የግንባታ እቃዎች ዉስጥ ከ 60 በመቶ በላይ ያህሉ በሀገርቤት ይመረታል ያሉት አቶ ቸርነት ፤ ይህም ለቤት ዋጋ ቅናሽ ማሳየቱ የራሱን ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚወጣ አስረድተዉናል።

🚧ኪ ሃዉሲንግ ፋይናንሻል ሶሉሽን ወደ ስራ ከገባ በኋላ ከ 10 ሺህ በላይ ደምበኞችን የመዘገበ ሲሆን በ 30 አመት ዉስጥ ተከፍሎ በሚያልቅ ወርሃዊ የ 2ሺህ ብር ቁጠባ የቤት ባለቤት የሚሆኑበትን አሰራር አስተዋዉቋል። ብስራት ለአቶ ቸርነት በርካታ ጥያቄዎችን ያቀረበ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ የዋጋ ንረት ቢከሰት የወርሃዉ ክፍያዉ ላይ ጭማሪ ሊደረግ ይችላል ወይ? የሚለዉ ላይ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

🚧በየጊዜው የሚፈጠሩ ኢኮኖሚያዊ ክስተቶችን ታሳቢ ያደረገ ወርሃዊ ክፍያን ወስነናል ያሉት አቶ ቸርነት ጭማሪ የሚደረግባቸዉ ሁኔታዎች ቢፈጠሩ እንኳ የጎላ ልዩነት የማይታይባቸዉ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም ደምበኞች ክፍያዉ ከአቅማቸዉ በላይ ቢሆንባቸዉ አቋርጠዉ የሚወጡበት እንዲሁም ድርሻቸዉን መሸጥ መለወጥ የሚችሉበትን አማራጭ መያዛቸዉን ተናግረዋል።

⏺ታህሳስ 27 እጣቸዉ ይወጣል የተባለላቸዉ ቤቶች ተቋሙ ከሰበሰባቸዉ 2 ሺህ ቤቶች ዉስጥ የተወሰኑት ሲሆኑ በጋርመንት ፣ አያት ፣ እሪ በከንቱ እና ሰሚት አካባቢዎች የሚገኙ መሆናቸዉን አቶ ቸርነት መንግስቴ ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

@etconp
👍18❤1