Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉በ168 ሚሊዮን ዶላር የአፍሪካ ሀገራትንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ሊገነባ ነው

🚧በወላይታ ሶዶ ከተማ ከ168 ሚሊዮን ዶላር የአፍሪካ ሀገራትንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ሊገነባ መሆኑ ተገለጸ፡፡

🚧የሔልዝ ኤንድ ሆልነስ ኢትዮጵያ (HAWE) መስራችና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አለውበል አልማው ስለፕሮጀክት ዓላማና አተገባበር ላይ ገለጻ አድርገዋል።

🚧ኢንተርናሽናል ሆስፒታሉ ከ168 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ የሚገነባ መሆኑንና የመጀመሪያው ደረጃ ህንጻ በ20,000 ካሬ ሜትር መሬት ላይ እንደሚያርፍ ጠቅሰዋል።

🚧ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በባህርዳር እና ወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገነባ ሲሆን ሔልዝ ኤንድ ሆልነስ ኢትዮጵያ (HAWE) የተሰኘ አለም አቀፍ እውቅና ያለው ድርጅት ድጋፍ የሚተገበር መሆኑን ገልጸዋል።

🚧ፕሮጀክቱ የአፍሪካ ሀገራትን ጨምር ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን የኩላሊት ንቅለ ተከላ፣ የኦክስጅን ማምረት፣ የጤና ምርምር ማዕከል፣ የኢንተርናሽናል ስብሰባ አድራሻ የያዘ ነው ብለዋል።

🚧ፕሮጀክቱ ከሁለት ዓመት ከስድስት ወር እንደሚጠናቀቅ የተናገሩት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ግንባታው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር ውሉን በማጠናቀቅ በቅርቡ እንደሚጀምርም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

Via አዲስ ዋልታ

@etconp
👍17❤5
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ

፦ፕሌት 1mm-30mm any size ቆርጠን በስተን ጣጣዉን ጨርሰን እናስረክቦታለን

፦jbolt 12mm-32mm በፈለጉት ቁመት ጥርስ አዉጥተን አጥፈን እንሰጦታለን

፦ankerbolt

፦stafa(ስታፋ ባለ 6 እና ባለ 8)በየትኛዉም size የተዘጋጀ አለን

፦ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን

አድራሻችን
ቁ.1  መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር  ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ
0904040477
0911016833
0994941706

ወይም @heavenic1 ፃፉልን

ይደዉሉልን ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም ቢሆኑ ካሉበት እንልክልዎታለን።
👉በፕሮጀክቶች ላይ ለሚፈጠሩ አለመግባባቶች አማራጭ የግጭት አፈታት አገልግሎትን ያግኙ

🚧 “በብዙ የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፎች አለመግባባት ተፈጥሮአዊ መሆኑ ተደጋግሞ የተገለፅ እውነታ ነው፡፡ በህግ ወይንም በውል የተገለፁ መብቶች ያለመከበር እና የይገባኛል ጥያቄዎች ለእነዚህ አለመግባባቶች መፈጠር መሰረታዊ ምክንያት ናቸው፡፡ መሰል ይገባኛል ጥያቄዎችን በአግባቡ መፈታት ያልተቻለ እንደሆነ ጉዳዩ ወደ አለመግባባት ደረጃ የማደግ እድሉ ሰፊ ነው፡፡ ስለሆነም ያለመግባባቶች ከፍ ወዳለ ደረጃ ከማደጋቸውና ለፕሮጀክቶች አፈጻጸም እንቅፋት ከመሆናቸው በፊት መታረም መቻላቸው አስፈላጊ ነው፡፡

ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ በተያዘላቸው በጀት ለማጠናቀቅ ይቻል ዘንድ የተለያዩ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ተጠቅሞ ያጋጠሙ አለመግባባቶችን መፍታት አሁን አሁን ይበልጥ እየታመነበት የመጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡ የግንባታ ዘርፉም ከግጭቶች/ ካለመግባባቶች የፀዳ ባለመሆኑ በተመሳሳይ ዕይታ የሚታይ እና መፈታት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

የግንባታ ሂደት በውስጡ ከሚሳተፉ ባለድርሻዎች፣ ከሚፈስበት መዋዕለ ነዋይ እንዲሁም ከሚወስደው ጊዜ ውስብስብነት ወዘተ አንፃር አለመግባባት መፈጠሩ የሚጠበቅ ነው፡፡ በግንባታ ሂደቶች ውስጥ የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችን መፍታት ፈርጀ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የዘርፉ ባለሙያዎች በስፋት ይገልጻሉ፡፡

ስለሆነም ግጭቶች/ አለመግባባቶች/ ወደ ፍርድ ቤት ከመሄዳቸው በፊት አማራጭ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ሊያጋጥሙ የሚችሉ አለመግባባቶችን መፍታት በተከራካሪ ወገኖች መካከል መልካም ግንኙነትን ከማስቀጠል አኳያ፣ ከህግ ሙያ ውጪ ያሉ ሌሎች ባለሙያዎችን ከማሳተፍ በተጨማሪ ጊዜን፣ ወጪን እና በዳኝነት ተቋማት ላይ የሚፈጥረውን ጫና የሚቀንስ በመሆኑ ይህ አሰራር በግንባታ ዙሪያ የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ ነው፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፌዴራል መንግስት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 1263/2014 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የተቋቋመ እና ስልጣኑንና ተግባሩንም ለመወሰን እንደዚሁ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 524/2015 መሰረት አድርጎ መቋቋሙ ይታወቃል፡፡

ይህን መነሻ በማድረግ በኢትዮጵያ የዳኝነት እና የዕርቅ አሰራር ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1237/2013ን መሠረት በማድረግ እና በደንብ ቁጥር 524/2015 አንቀጽ 5 (16) የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በመንግስት ኮንስትራክሽን ስራዎች ለሚፈጠሩ የውል አለመግባባቶች በሚዘረጋው አሰራር ስርዓት ፕሮጀክቶች/ ተዋዋዮች በአማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች መፍትሄ እንዲያገኙ የማድረግ ስልጣንና ተግባር ተሰጥቶታል፡፡

በዚህም መነሻነት፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በመንግስት ኮንስትራክሽን ስራዎች ለሚፈጠሩ የውል አለመግባባቶች በዘረጋው የአሰራር ስርዓት በአማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች መፍትሄ እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን እየገለፅን ማንኛውም የህንጻና የመሠረት-ልማት ፕሮጀክቶችን የሚያስገነቡ እና እያስገነቡ ያሉ የመንግስት አስፈጻሚ ተቋማት እና የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት በመደበኛ ፍርድ ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶች እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አለመግባባቶችን በአማራጭ የግጭት አፈታት ዘዴዎች መፍታት የሚፈልጉ የመንግስት ተቋማት ወይም ግጭቶችን በአማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴዎች ለመፍታት የህግ ስልጣን ያላቸው ተቋማት አገልግሎቱን ከባለስልጣን መ/ቤቱ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን

@etconp
👍9❤1
👉የአፈርን የመሸከም አቅም (BEARING CAPACITY) እንዴት እንጨምር?

🚧ሶስት አይነት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከያ ቴክኒኮች አሉ እነሱም mechanical, chemical & other stabilization techniques

🌟A) ሜካኒካል ውስጥ :-

▶️1. Compaction - አፈሩን ስንጠቀጥቀው density/ unit
weight ይጨምራል ያ ማለት ደግሞ አፈርን የመሸከም አቅም ጨመረ ማለት ነው::

▶️2. Excavation and Replacement:- expansive soil ከሆነ ወይም ሌላ አስቸጋሪ አፈር ከሆነ ይህን መጠቀም እንችላለን

▶️3. Mixing of Different Soils - ሳይታችን ላይ ያለው አፈር coarse ወይም fine ብቻ ከሆነ ወይም ደግሞ አፈሩ አንድ አይነት ብቻ ፀባይ ካለው ከተለያዩ አፈሮች ጋር በመደባለቅ የተሻለ የአፈር ፀባይ ማግኘት እንችላለን

🌟B) ኬሚካል :-

▶️1. Lime stabilization - ይህንን የምንጠቀመው በአብዛኛው ለ expansive soil ነው አፈሩን ከ Lime ጋር በመደባለቅ plasticity መቀነስ እንችላለን የlime መጠኑ ከሚያስፈልገው በላይ ከበዛ ግን B.C. ይቀንሳል፡፡

▶️2. Cement stabilization - ሲሚንቶን ከአፈር ጋር በመደባለቅ የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት መንገድ ነው፡፡

⏺concrete pavement ስር መጠቀም እንችላለን በአብዛኛው ለአየር
መንገዶች ፤ ለአውራ ጎዳናዎች ፤ ግድቦችን ከሽርሸራ ለመከላከል ወ.ዘ.ተ. መጠቀም እንችላለን፡፡

▶️3. Asphalt stabilization - አስፓልትን ከአፈር ጋር በመደባለቅ
የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት ዘዴ ነው በተለይም ለcohesive አፈሮች፡፡

⏺አፈሩን water proof በማድረግና ውሃማነትን በመቀነስ B.Cን መጨመር እንችላለን፡፡ በአብዛኛው ይህንን ድብልቅ
ለመንገዶች እንደ base course መጠቀም እንችላለን፡፡

🌟C) ሌሎች የአፈርን ባህሪ ማስተካከያ መንገዶች:-

▶️1. Drainage - ፓይፖችን አፈር ውስጥ በመቅበር ወይም ጉድጓዶችን በመጠቀም ground water የምንቆጣጠርበት ነው

▶️2. Precompression - ግንባታ ከመጀመራችን በፊት አፈሩ ላይ
ሎድ በመጫን ኮምፓክት የምናደርግበት ዘዴ ነው

▶️3. Dynamic Stabilization

✨ሀ) Blasting - ቦምብ ወደውስጥ በመቅበር በፍንዳታው አፈሩ ይጠቀጠቃል::

✨ለ) Compaction Piles - ፓይሎችን ወደውስጥ በማስገባት አፈሩ ወደ ጎን እንዲሸሽና እንዲጠቀጠቅ ማድረግ ይቻላል፡፡
⏺ፓይሉን ስናስወጣውም በተቦረቦረው ጉድጓድ ውስጥ የተሻለ አፈር በማስገባት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከል እንችላለን፡፡

▶️4. Injection And Grouting - አፈሩን በሲሚንቶ ወይም በተለያዩ chemical ውህዶች በpressure በመምታት ground water ና settlement መቆጣጠር እንችላለን፡፡

🫵የተሻለውን ዘዴ ለመምረጥ የአፈሩንና የአካባቢውን ሁኔታ ፤
ኢኮኖሚ ፤ ሴፍቲና የመሳሰሉትን ነገሮች ማጤን አለብን፡፡

@etconp
👍18❤6🙏6👌1
👉የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም በ1936 ዓ.ም ተቋቋመ የቀደመ ስሙም አርኪዮሎጂ ሙዚየም በመባል ይታወቃል በዚህ ሙዚየም ውስጥ በርካታ ቅርሶች ይገኛሉ ከቅርሶቹ መካከልም የአርዲን የሰላምን እና 3.4 ሚሊዮን እድሜ ያላትን የሉሲን  ቅሬተ አካሎች እናገኛለን ከተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች  የተሰበበሰቡ ቅርሶች ስላሉትም ትንሿ ኢትዮጵያ እየተባለ ይጠራል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሙዚየም አጀማመር

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሙዚየም በ1936 ዓ.ም የብሔራዊ ቤተ መፃህፍት አካል ሆኖ ተከፍቷል በዚህም ከነገስታቱ ቤተሰቦችና ባለሟሎቻቸው በስጦታ መልክ የተበረከቱ ጥቂት የክብርና የማዕረግ መግለጫ ቅርሶች ለመጀመሪያ ጊዜ በአውደ ርዕይ መልክ ቀርበዋል ከዚህ ጋር ተያይዞ በአርኪዎሎጂ ኢንስቲትዩት በ1946 ዓ.ም áˆ˜áˆ˜áˆľáˆ¨á‰ľ ለሙዚየሙ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡
ይህም በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የፈረንሳይ አርኪዎሎጂስቶች ተልዕኮ ውጤታማ ስራዎችን በማከናወን ጠቃሚ ታሪካዊና የአርኪኦሎጂ ግኝት ለማግኘት አስችሏል በቀጣይነትም ሙዚየሙ የተዛወረው በአሁኑ ሰዓት የብሔራዊ ባንክ ሰራተኞች ክበብ ሆኖ ወደሚያገለግለው ህንፃ  ሲሆን ቀስ በቀስም በ1958 ዓ.ም ወደ አሁኑ ይዞታው መጥቷል፡፡

በ1947 ዓ.ም የተቋቋመው የአርኪዎሎጂ  ሙዚየም ስራውን የጀመረው ከሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተገኙ የአርኪዎሎጂ ውጤቶችን ለእይታ በማቅረብ ነበር ሆኖም በ1958 ዓ.ም ብሔራዊ ሙዚየም የማቋቋም ሀሳብና የኢትዮጵያ የጥንታዊና ታሪካዊ ቅርስ አስተዳደር መመስረት መንግስት ለጉዳዩ ትኩረትና ድጋፍ እንዲሰጥ አድርጎታል፡፡

በመቀጠልም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም በአዋጅ ስራውን የጀመረ ሲሆን ይህም ለጥንታዊ ቅርሶች ጥበቃና እንክብክቤ ህጋዊ ከለላ በማግኘት የአገሪቱን አርኪዎሎጂካዊና ፓሊዩንቶሎጂካዊ  መገኛዎች እንዲሁም የጥንታዊ ህንፃዎችና ሀውልቶች የመጠበቅና የማቆየት ስልጣን አግኝቷል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በሙዚየሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘው አሮጌው ህንፃ የተገነባው በ1928 ዓ.ም ፋሽስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ሲሆን የተገነባውም በወቅቱ ከፋሽስት ኢጣሊያ የጦር መሪዎች አንዱ ለሆነው እና አዲስ አበባን ሲያስተዳደር ለነበረው መኖሪያ ቤት እንዲሆን ነበር፡፡

የፋሽስት ኢጣሊያ የወረራ ዘመን ካበቃ በኋላ ህንፃው ለቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ልጅ ለልዑል መኮንን በመኖሪያነት ሲያገለግል ቆይቶ በመቀጠልም ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተሰጠ በመጨረሻም በ1957 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሁን ወደሚገኝበት ቦታ ሲዛወር ህንፃው ለሙዚየም አገልግሎት እንዲውል ተደረገ፡፡

አዲሱ ቋሚ የትርኢት አዳራሽ ወይም የሙዚየም ህንፃ የተገነባው በዩ.ኤስ.ኤይድ ድጋፍና በግንባታ ሚኒስቴር ተቆጣጣሪነት እ.ኤ.አ ከ1978 እስከ 1981 ዓ.ም ዓ.ም ነው በህንፃው ግንባታ ወቅት የዬኒስኮ አማካሪዎች በኢግዚቢሽን አደረጃጀትና በትርኢት አቀራረብ ከፍተኛ የማማከር ሾል ሰርተዋል ይህ ህንፃ በአሁኑ ወቅት ቋሚ  የትርዒት አዳራሽ በመሆን እያገለገለ ይገኛል፡፡በውስጡም በርካታ ቅርሶች ሲኖሩ ከእነዚህ መካከል በአብዛኛው የአርኪዎሎጂካዊ ግኝቶች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ፡፡

በአለምአቀፍ ደረጃ በጥሬ ኪነህንጻ ሾል መዝገብ (Brutalist architecture) ሰፍሮ የሚገኘዉ ይህ አዲሱ ቋሚ የትርኢት አዳራሽ በነፍሰሔር ህንጻ ነዳፊ በጋሻውበዛ ተስፋሚካኤል የተነደፈ ሲሆን ስራዉ ደግሞ ይህ ህንጻ በአገራችን ከሚገኙት  አይነተኛ ጥሬ ህንጻዎች መካከል  ግንባር ቀደሙ ምሳሌ ነዉ። ገጽታዉ ባልተቀባ አርማታ መጨረሱ፣ መዋቅራዊ አካሎቹ በግላጭ በገጽታዉ መንጸባረቃቸዉ እንዲሁም የመስኮት ክፍተቶች ሳይበዙ ድፍን ያለ ግድግዳ መብዛቱና ጠንካራ ማንነት ያለዉ የዉጭ ደረጃ መጠቀሙ ለስራዉ አለማቀፍ ታዋቂነትን አስገኝቶለታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ስር ካሉት ስራ አስፈፃሚዎች በብሔራዊ ሙዚየም ስራ አስፈፃሚ ስር የሚገኝ ሲሆን የሚገኘውም በአዲስ አበባ ከተማ 5ኪሎ አካባቢ ከቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አጠገብ ነው፡፡

በ1992 ዓ.ም የሙዚየሙ ቋሚ ትርዒት ከአሮጊው ህንፃ ወደ አዲሱ ህንፃ  ተዛውሮ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ዋቢ ኢትዮዽያ ቅርስ ባለስልጣን

#ConstructionHistory

@etconp
👍7👌3👏2
👉በጋራ የኮንስትራክሽን ሥራ ንግድ ፍቃድ ስታወጡ ስለስያሜው
{ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (PLC) እና የአክሲዮን ማህበር (SC) ተመሳሳይነትና ልዩነት}


🚧በኮንስትራክሽን ሥራ ውስጥ አክሲዮን ማኅበር፣ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ሽርክና የሚባሉ ከአንድ በላይ የሆኑ አባላት በጋራ ሆነ ንግድ ፍቃድ የሚያወጡባቸው ዘርፎች አሉ እነዚህ ስያሜዎች በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ዉስጥ ካሉት የንግድ ማህበራት መካከል የሚጠቀሱ ሲሆን በዚህ ክፍል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር—ኃ.የተ.የግ.ማ (Private Limitted Company - PLC) እና የአክሲዮን ማህበር - አ.ማ (Social Company - SC) ያላቸውን አንድነትና ልዩነት እንመለከታለን። ሁለቱም ማህበራት አክሲዮን ያላቸዉ ወይም ካምፓኒዎች ሲሆኑ ተመሳሳይነትና ልዩነት አላቸዉ።

🌟ተመሳሳይነታቸዉ

• ህጋዊ ሰዉነት ያላቸዉ መሆኑ ፣
• የራሳቸዉ ንብረት ያላቸዉ መሆኑ፣
• የራሳቸዉን ትርፍና ኪሳራ ተጠያቂነት ያለባቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም ትንሹ የአባላት ብዛትና የመነሻ ካፒታል ያላቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም በቦርድና በማናጀር መመራት የሚችሉ መሆኑ ነገር ግን ለ PLC አሰገዳጅ አለመሆኑ፣
• የሁለቱም ተጠያቂ በተዋጣዉ የገንዘብ መጠን (አክሲዮን ) መሆኑ ፣
• ሁለቱም የሙያ መዋጮን የማይቀበሉ መሆኑ
• በሁለቱም ካፒታል ማሳደግና መቀነስ የሚቻል መሆኑ ፣
• በሁለቱም አክሲዮኖች በመያዣ /በዋስትና / መያዝ ሚችሉ መሆኑ ፣

🌟ልዩነታቸዉ

⏺አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር / PLC/ private Limited Company/ ለማቋቋም የአባላት ብዛት ከሁለት ማነስ የማይችሉ መሆኑ እንዲሁም ከሀምሳ መብለጥ እንደማይችሉ በንግድ ህጉ ተገልጿል። የአክሲዮን ማህበርን (share company) በተመለከተ ለማቋቋም ከ5 አባላት ማነስ የማይችል ሲሆን ብዛት ግን ገደብ የሌለዉ መሆኑን በንግድ ህጉ ላይ ይገኛል።

〰️ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መነሻ ካፒታል 15000 ሺህ ብርና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋም በኢትዮጵያ ብር አንድ በመቶ ማነስ አይችልም።
〰️ አክሲዮን ማህበር መነሻ ካፒታል 50000 ሺህ እና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋ ከአንድ መቶ ብር በታች መሆን አይችልም
〰️ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ካፒታሉ ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የተከፈለ ሲሆን የአክሲዮን ማህበር ግን ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የሚከፈል አይደለም ነገር ግን ከተፈረሙ አክሲዮኖች ቢያንስ 1/4 (25%) መከፈል አለበት የቀረዉ በሂደት የሚከፈል ይሆናል
〰️ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የአክሲዮኖች ሽያጭ ለህዝብ ክፍት የሚደርግ አይደለም  ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ለህዝብ ክፍት የሚደረግ ነዉ
〰️ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC) ላይ አክሲዮን ማህበር ዉስጥ ያለ ሰዉ አክሲዮኑን ለሶስተኛ ሰዉ ማስተላለፍ አይችልም ምክንያቱም መተዳደሪያ ደንቡ ላይ አባላት ይህን እስካልፈቀዱ ድረስ በህጉ መሰረት sale freely transfrable አይደለም። ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ላይ አክሲዮን ማስተላለፍን በተመለከተ አክሲዮን የገዛ ሰዉ አክሲየኑን ለሌላ አባል ላልሆነ ሰዉ በቀላሉ ማስተላለፍ ይችላል ። ስለዚህ አክሲዮን ማስተላለፍ ከተፈለገ በቀላሉ የአክሲዮን ማህበርን መምረጥ ያስፈልጋል ማለት ነዉ።
〰️ አስተዳደራዊ አካል (ቦርድ) ን በተመለከተ አክሲዮን ማህበራት ሁሉ ከ3-12 ሰዉ የሚይዝ ቦርድ ኦፍ ዳይሬክተር ሲቋቋም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (plc) ዉስጥ የቦርድ መዋቅር ግዴታ አይደለም።

🖱ምንጭ፦ ሳሙኤል ግርማ  — የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ

🌟የኮንስትራክሽን ስራ እና ጨረታ በ ትኩሱ እንዲደርሶ ከታች ባለው ሊንክ ይወዳጁን

https://t.me/ETCONpWORK
👍35
👉የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱን 5 ቢሊየን ዶላር ሚያወጣ ‘የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተማ’ ግንባታ በአራት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሠራ መሆኑን ገለጸ፡፡

🌟አየር መንገዱ “ኤርፖርት ሲቲ” ብሎ የሚጠራውን ግንባታ ለመጀመር ከጫፍ የደረሰው እየጨመረ የመጣውን የደንበኞች ፍላጎት ለማርካት መሆኑን የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የንግድ ሥራ ዘርፍ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ለማ ያደቻ ተናግረዋል፡፡

🚧የ ‘አየር መንገድ ከተማው’ ካልተገነባ ዓየር መንገዱ በዘርፉ እያስመዘገበ ካለው ፈጣን ዕድገት አንጻር እንደሚፈተን ከግምት ውስጥ በማስገባት ፕሮጀክቱ መታቀዱን አብራርተዋል፡፡

🚧ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 5 ቢሊየን ዶላር በጀት የተያዘለት ሲሆን፥ በዓመት 100 ሚሊየን መንገደኞችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።

🚧አሁን ላይ አየር መንገዱ በኦሮሚያ ክልል ከቢሾፍቱ ከተማ ጥቂት ወጣ ብሎ በሚገኝ ሥፍራ የመጀመሪያውን የ ‘አየር መንገድ ከተማ’ ግንባታ ለማስጀመር በዝግጅት ላይ ነው፡፡

🚧ፕሮጀክቱ ዘመናዊ ሆቴሎች ፣አፓርትመንቶች፣ ከቀረጥ ነፃ የግብይት ሥፍራና የካርጎ ሎጂስቲክስ ማዕከል እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡

✨የአዋጭነት ጥናቱን በማጠናቀቅም ለዓለም አቀፍ ጨረታ ለማውጣት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል፡፡

@etconp
👍9😢7❤4
👉የመንግሥት መሥሪያ ቤት በሚያስገነባቸው ግንባታዎች ላይ ትዕዛዝ መሥጠት

🚧“አንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት በሚያስገነባቸው ግንባታዎች ላይ በግንባታ ሒደት ውስጥ ለተቋራጩ የስራ ትዕዛዞችን እየሰጠ፣ የስራዎቹን አካሄድ የመወሰንና ስራው በሚፈቅደው አይነት እንዲፈፀም የስራ ተቋራጩን የማዘዝ ሥልጣን ያለው ሲሆን፣ ተቋራጩ በበኩሉ በአሠሪው የመንግሥት መሥሪያ ቤት በተሰጡት ፕላኖች አይነቶችና የዋጋና የስራ ማስታወቂያ መሰረት ጠንቅቆ የግንባታ ሥራውን የመስራት ግዴታ እንዳለበት በፍ/ብሔር ህግ ቁጥር 3252 ንዑስ አንቀጽ 1 እና ንዑስ አንቀጽ 2 በግልፅ ተደንግጓል።

🌟ነገር ግን የጨረታ ሰነዱ በሚወጣበት ጊዜ በግንባታ ዲዛይኑ ላይ ከተመለከተው ልኬት በታች ሆኖ በኋላ በዲዛይኑ መሰረት ለሚሰራ ግንባታ የሥራው ባለቤት በግንባታው ሥራ ውል ሰነዱ ላይ ከተመለከተው ክፍያ ውጪ በተጨማሪነት በባለቤቱ ፈቃድና ትዕዛዞች መሠረት ለተሠሩ ሥራዎች ክፍያ ለመክፈል የሚገደድ ሲሆን በህጉ አግባብ በባለቤቱ የተሰጡ ተጨማሪ የሥራ ትዕዛዞች የሥራ ውሉ አካል ተደረገው የሚወሰዱ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ.3244, 3225,(1)(2), 3152(1), 3266(1), 3263, 3265(3) በዝርዝር ተዳስሰዋል።

⏺በተለይ አሠሪው መሥሪያ ቤት በሚመለከተው ክፍል ማህተም ያለበት ደብዳቤ ተጠቅሞ አልያም በተመደበው ተቆጣጣሪ ፊርማ ሥራዎችን እያጸደቀና እያዘዘ እንዲሰሩ የተደረጉ ሥራዎች በፍ/ብሔር ሕግ ቁጥር 3152 ንዑስ አንቀጽ 1 እና በፍ/ብሔር ህግ ቁጥር 3266(1) ድንጋጌዎች መሰረት የሰጣቸው ተጨማሪ የስራ ትዕዛዞች የግንባታ ሥራ ውሉ አካል ተደርገው የሚያዙ ናቸው።

🚧የ መወያያ ግሩፓቹ ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ ቤተሰብ ይሁኑ

https://t.me/COTMp
👍9🏆2
👉"የቤት ዋጋ በኢትዮጵያ በመቀነስ ላይ ነዉ" - ኪ ሃዉሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን

🌟
ኪ ሃዉሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን የቤት ችግር ችግርን ለመቅረፍ አዲስ በጀመረዉ አሰራር ተጠቃሚ የሆኑ ደምበኞቹን የቤት ባለቤት ለማድረግ በዛሬዉ እለት ከሪስልስቴት አልሚ ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሷል።

🚧ተቋሙ በመጪው ታህሳስ 27 ባለእድለኛ ለሆኑ ደምበኞቹ በቁጥር ያልተጠቀሱ ቤቶችን እንደሚያስተላልፍ አስታዉቋል።

🚧ከተቋሙ ጋር በጋራ የሚሰራዉ የብሉ ዞን ማርኬቲንግ ስራ አስኪያጅ አቶ ቸርነት መንግስቴ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ፤ በኢትዮጵያ በመተዋወቅ ላይ ባሉ አዳዲስ የግንባታ ጥበቦች እና ቴክኖሎጂን መጠቀም መጀመር ምክኒያት በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ላይ ቅናሽ እያሳየ መሆኑን ገልጸዋል።

🌟ለአብነትም ፕራይም ኮት የተሰኘ የሲሚንቶ ልስንን የሚያስቀር አሰራር እስከ 12 በመቶ አጠቃላይ የግንባታ ወጪን እንደሚቀንስ ተናግረዋል። በተጨማሪም አልሙኒየም ፎርዎርክ በዘርፉ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እያሳደረና ወጪ እየቀነሰ መምጣቱን ገልጸዋል። በአሁኑ ሰዓት ከአስፈላጊ የግንባታ እቃዎች ዉስጥ ከ 60 በመቶ በላይ ያህሉ በሀገርቤት ይመረታል ያሉት አቶ ቸርነት ፤ ይህም ለቤት ዋጋ ቅናሽ ማሳየቱ የራሱን ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚወጣ አስረድተዉናል።

🚧ኪ ሃዉሲንግ ፋይናንሻል ሶሉሽን ወደ ስራ ከገባ በኋላ ከ 10 ሺህ በላይ ደምበኞችን የመዘገበ ሲሆን በ 30 አመት ዉስጥ ተከፍሎ በሚያልቅ ወርሃዊ የ 2ሺህ ብር ቁጠባ የቤት ባለቤት የሚሆኑበትን አሰራር አስተዋዉቋል። ብስራት ለአቶ ቸርነት በርካታ ጥያቄዎችን ያቀረበ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ የዋጋ ንረት ቢከሰት የወርሃዉ ክፍያዉ ላይ ጭማሪ ሊደረግ ይችላል ወይ? የሚለዉ ላይ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

🚧በየጊዜው የሚፈጠሩ ኢኮኖሚያዊ ክስተቶችን ታሳቢ ያደረገ ወርሃዊ ክፍያን ወስነናል ያሉት አቶ ቸርነት ጭማሪ የሚደረግባቸዉ ሁኔታዎች ቢፈጠሩ እንኳ የጎላ ልዩነት የማይታይባቸዉ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም ደምበኞች ክፍያዉ ከአቅማቸዉ በላይ ቢሆንባቸዉ አቋርጠዉ የሚወጡበት እንዲሁም ድርሻቸዉን መሸጥ መለወጥ የሚችሉበትን አማራጭ መያዛቸዉን ተናግረዋል።

⏺ታህሳስ 27 እጣቸዉ ይወጣል የተባለላቸዉ ቤቶች ተቋሙ ከሰበሰባቸዉ 2 ሺህ ቤቶች ዉስጥ የተወሰኑት ሲሆኑ በጋርመንት ፣ አያት ፣ እሪ በከንቱ እና ሰሚት አካባቢዎች የሚገኙ መሆናቸዉን አቶ ቸርነት መንግስቴ ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

@etconp
👍18❤1
👉የቁፋሮ ሥራ (Excavation works) ላይ መረጋገጥ ያለባቸው የቁጥጥር ነጥቦት

🌟የቁፋሮ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ቁፋሮዎች፣ አጎራባች ቦታዎች እና የመሬት መንሸራተት መከላከያ ዘዴዎች በባለሙያ ጥናት ሊደረግባቸው ይገባል።

⏺ይመረመራሉ በመሆኑም በቁፋሮ ሥራ የግንባታ ቁጥጥር ባለሙያው የሚከተሉትን ነጥቦች ትኩረት አድርጎ ማረጋገጥ አለበት።

🚧1. የአጎራባች ወሰንን ከመፍረስ መታደግ፦ በግንባታ ሥራ የመጀመሪያው ተግባር ቁፋሮ ሲሆን ማንኛውም ቦታ አጎራባች የሆነ የሕንጻ ቦታ ወይም መንገድ የሚኖረው ሲሆን ቁፋሮው ወደአጎራባች ወሰን ተጠግቶ የሚከናወን ከሆነ በቁፋሮው መጠጋት አልያም በንቅናቄ (Vibration) የተነሳ የአጎራባች መሬት በመውደቅ ወይም በመንከባለል ለሁለቱም ቦታዎች አደጋ እንዳይፈጥር የሚያስችል ቅድመ ጥንቃቄ መደረጉን ማረጋገጥ አለበት። ይህ ሳይሆን ቀርቶ የጎረቤት ወሰን/አጥር/ ቢፈርስ ወይም ሕንጻ ቢወድቅ በመሐንዲሱ የክትትል ድክመት የተነሳ ካሳ እንዲከፍሉ ሊገደዱ ይችላሉ።

🚧2. በሕግ የሚፈቀደውን የውጪ መስመር አለማለፉን ማረጋገጥ፦ ሕንጻው የሚሰራበት የካርታ ቦታ በአካባቢ ልማት (Local development plan) መሰረት ከፍተኛ የኢሌክትሪክ ኃይል (High Electric tension) የሚያልፍበት አልያም የመንገድ ማስፋፊያ ስፋት (Road Widening Area) የሚገባበት ሊሆን ስለሚችል በግንባታ ወቅት የተዘጋጀ አዲስ የፕላን ስምመትን በማመሳከር እንደዲዛይኑ በተፈቀደ ክልል ውስጥ ማረፉን እና በባለቤት ግፊት የተነሳ ያልተፈቀደ ቦታ ላይ አለማረፉን ማረጋገጥ አለበት።

🚧3. በቁፋሮ ክልል ደህንነትን ማረጋገጥ፦ ከቁፋሮው በኋላ ከመሬት ውስጥ ያለው ሥራ (Sub Structure Works) ተጠናቆ የተቆፈረው ክፍል እስኪሞላ ድረስ የሰከረ፣ ወይም የአእምሮ እክል ያለበት፣ ወይም ሕጻናት፣ ወይም ሽማግሌዎች ወደጉድጓድ ገብተው አካላዊ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ከተፈቀደላቸው የግንባታ ሰራተኞች ውጪ ወደ ክልሉ እንዳይገቡ የታጠረ (Fenced) እና የውስጥ መሸጋገሪያ (Bridge Ladders) የተሰራላቸው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።

🚧4. የመሬት ውስጥ ዝርጋታዎች (Underground installations)፦ በሰፋፊ ግቢዎች ውስጥ ለግቢው አግልግሎት የሚሰጡ አስቀድሞ የተዘረጉ የውኃ፣ የኢንተርኔት፣ የመረጃ እና የመብራት ዝርጋታዎች የሚኖሩ ከሆነ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር በጥንቃቄ እንዲነሱ አልያም ግንባታው ጉዳት ሳያደርስባቸው እንዲከናወን ማድረግ ይኖርበታል።

🚧5. የቁፋሮውን ልኬት ማረጋገጥ፦ በተለይ በአርክቴክቸራል፣ ስትራክቸራል እና ሳኒታሪ ንድፎች ላይ የተመለከተው ተጓዳኝ የቁፋሮ ሥራ የሚጠይቁትን ልኬቶች ማሟላቱን (ወርዱን፣ ስፋቱን፣ ርዝመቱን፣ ዲያሜትሩን፣ ጥልቀቱን) ጠብቆ ቁፋሮ መንዲከናወን የመቆጠጠርና መከናወኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት።

🚧6. ውኃ እንዳይቋጥር ማስደረግ፦ በዝናባማ እና የመሬት ውኃ በሚፈልቅባቸው አካባቢዎች ቁፋሮ እንደተከናወነ ዝናብ ቢዘንብ ቢያንስ የጎርፍ ውሃ እንዳይገባ የመከላከያ ሥራዎች፣ እንዲሁም የመሬት ውስጥ ምንጭ ውሃን የመከላከያ (like: Permeable hardcore layer, geotextile material, channelization...) መንገዶች ተግባራዊ የሚደረጉበት መሆኑን ማረጋገጥና መከታተል አለበት።

🚧7. የቁፋሮ ግብአቶችና ማሽኖችን ደህንነት ማረጋገጥ፦ በቁፋሮ ሥራ መወጣጫ የሚሆኑ የብረት፣ የእንጨት እና የፕላስቲክ ግብአቶችን ብልሽት የሌለባቸው መሆኑ እና ለቁፋሮ ሥራ የቀረቡ የእጅ መሳሪያዎች እና ማሽኖች የደህንነት ችግር የሌለባቸው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።

🚧8. በቂ አየርና ብርሃን የሚገኝበት መሆኑን፦ በጣም ልዩ ሁኔታ የሚባልና በብዙዎቹ ግንባታዎች ላይ የማይገጥም ቢሆንም በውኃ ውስጥ፣ በመሬት ውስጥ ለሚከናወኑ ቁፋሮዎች የሚሳተፉ ሰራተኞች በቂ የሆነ የኦክስጅን አየር ማግኘት ስላለባቸው መሐንዲሱ የአየር ሁኔታውን የሚቆጠጠሩ ማሽኖች፣ አልባሳት እና ብርሃን መቅረባቸውን ማረጋገጥ ማድረግ አለበት።

@etconp
👍13❤12😢2
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ

፦ፕሌት 1mm-30mm any size ቆርጠን በስተን ጣጣዉን ጨርሰን እናስረክቦታለን

፦jbolt 12mm-32mm በፈለጉት ቁመት ጥርስ አዉጥተን አጥፈን እንሰጦታለን

፦ankerbolt

፦stafa(ስታፋ ባለ 6 እና ባለ 8)በየትኛዉም size የተዘጋጀ አለን

፦ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን

አድራሻችን
ቁ.1  መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር  ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ
0904040477
0911016833
0994941706

ወይም @heavenic1 ፃፉልን

ይደዉሉልን ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም ቢሆኑ ካሉበት እንልክልዎታለን።
👍1
👉Contract Review Process

•What is a Contract Review?

Contract review is a contractual process used to identify & analyse the key provisions within an agreement.

A legal professional will read each contract thoroughly to understand the terms & conditions & highlight risks or relevant information.
‍
When presented with a new contract or agreement, parties are allowed & most of the time expected to check & potentially rework the T&Cs, ensuring the contract works for both parties.

Reviewing a contract before signing clarifies each party's obligations, protects their interests and ensures that all parties are treated fairly.
‍
Both sides may want to suggest contractual changes, leading to further negotiations & compromise before signing a final contract.
‍
•The Contract Review Process

Starts with preparation in the pre-review stage & includes:
-Clarifying contract-related facts -Measuring the feasibility of the contract & forecasting contractual risks.
-Reviewing payment terms & triggers -Commercial terms & duration periods.

The team need to be sure that the deal is on record, deep-dive interrogation into the contract's finer points to ensure that no terms are missing.

If the contract review occurs pre-signature, then there will also be a negation period.

Any changes will need to be marked up & the new version shared with the other party.

This will likely lead to some back & forth to finalise an agreement that works for everyone at the end of the contract review process.

•How to Review a Contract (Contract Review Checklist)

The contract review checklist is a detailed list that contains every part of a contract that needs to be checked during the review & negotiation process.

Contracts can vary significantly depending on the type of agreement.

But there are some common elements that every contract should include.

Key points to include in your contract review checklist:

-Does the contract accurately describe the negotiated agreement?
-Are the parties involved properly identified?
-Is the duration of the contract clear, including any expiration dates & break clauses?
-What are the payment terms & triggers? -What are the payment dates & are they accurate?
-Are there any terms that could be open to interpretation?
-Are both parties' obligations accurately described?
-Are there terms in place for the termination & renewal of the contract?
-Is there an agreed mechanism in place for the resolution of any disputes?

•Why Are Contract Reviews Important?

It reduces any agreement's legal & financial risk, provides both parties with a chance to fully understand T&Cs they are agreeing to before signature.

Post-signature, a contract review allows the business to check clauses & provisions to ensure they still cover the company needs & relevant regulations.

A contract review ensures that all terms are fair, enforceable & properly documented; it clarifies what happens if either party breaks the conditions laid out in the contract.

#ConstructionLaw

@etconp
👍8❤7
በሶስት ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

በኦሮሚያ ክልል ሶስት የሲሚንቶ አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ የጥራት ችግር በመኖሩ ምክንያት እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ወስጥ በጥራት ችግር ምክንያት ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ሶስት ፋብሪካዎች ላይ አስተተዳደራዊ እርምጃ  ወስደናል ሲሉ የኦሮሚያ ንግድ ቢሮ የኢንዱስትሪ ገበያ ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ ታጁ መሀመድ አስታውቀዋል፡፡

የምርት ሰርተፍኬት በመሰረዝ የማምረት ስራ እንዲያቆሙ ተደርጓል ያሉት ሀላፊው ሁለቱ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች እስከ ሶስት ወር ድረስ በመቆየት የጥራት ማስተካከያ አድርገው ወደ ማምረት ስራው ሊመለሱ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የተቀረው አንደኛው ፋብሪካ ግን ወደ ስራ እናዳልገባ እና ማምረት እንዳልጀመረ ነው የገለፁት፡፡

አሁን ላይም የሲሚንቶ ዋጋ በገበያ ላይ ቅናሽ ማሳየተኑን እና የአቅርቦት ፍላጎት መጨመር እያሳየ ነው ሲሉ የገለፁትን መዘገባችን የሚታወስ ነው ፡፡

Via አሐሬ

@etconp
👍15❤2🕊1
👉የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር፣የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን እንዲሁም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዮት አብሮ በጋራ ለመስራት የሶስትዮሽ የመግባቢያ የስምምነት ፊርማ ትላንት ታህሳስ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በሽራተን አዲስ ተፈራርመዋል።

🌟የውል ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር የቦርድ ሊቀመንበር ኢ/ር ግርማ ሀብተ ማርያም ፡ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ኢ/ር መስፍን ነጋዎ እንዲሁም በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማናጅመንት ኢንስቲትዮት በኩል ደግሞ ዋና ዳይሬክተሩ ኢ/ር ታምራት ሙሉ ናቸው።

@etconp
👍14❤1
👉የአቅም ማረጋገጫ (Performance bond/guarantee)

🌟የአቅም ማረጋገጫ አንድ ተቋራጭ ለክፍት ጨረታ ተወዳድሮ ሲያሸንፍ ቅድመ ክፍያ ወይም ፐርፎርማንስ ጋራንቲ እንዲያስገባ ይጠየቃል።

📂ይህ ሰነድ ጨረታውን ያሸነፈው ተቋራጭ ፕሮጀክቱን በብቃትና በጥራት ማጠናቀቅ ለመቻሉ እንደማስያዣ ሆኖ በባንክ የሚቀመጥ ቅድመ ክፍያ ነው።

📍በሀገራችን የኮንስትራክሽን ውል ሰነድ (Public Procurement Agency – PPA) መሰረት አንድ የጨረታ ተወዳዳሪ የቅቡልነት (የጨረታ አሸናፊነት) ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የብቃት ማረጋገጫ (Performance bond) ጨረታ ላወጣው አካል ማቅረብ እንዳለበት በክፍል አንድ (section 1)  “instruction to bidder (ITB) article 33 (33.1) ላይ ተቀምጧል።

🔗ይህ የብቃት ማረጋገጫ ገንዘብ መጠንና የገንዘብ አይነት (Amount and Currencies) በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት መሆን የሚገባው ሲሆን  በብዛት ጨረታውን ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ያህል የባንክ ማረጋገጫ ማቅረብ የተለመደ ነው። 

📇የብቃት ማረጋገጫ ሰነድ የቴምብር ቀረጥ (Stamp Duty) ክፍያ የሚከፈልበት ጭምር ሲሆን ስለ ቴምብር ቀረጥ (Stamp Duty) ምንነት በሚቀጥለው ክፍል እንመለከታለን።

በ ኢ/ር ዳንኤል ታጠቅ

🫵የ ኮንስትራክሽን አዳዲስ ጨረታዎች እና የ ስራ ቅጥሮች በ ትኩሱ እንዲደርሶ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ በመግባት እና ጆይን በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://t.me/ETCONpWORK
👍21👌2❤1
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ

፦ፕሌት 1mm-30mm any size ቆርጠን በስተን ጣጣዉን ጨርሰን እናስረክቦታለን

፦jbolt 12mm-32mm በፈለጉት ቁመት ጥርስ አዉጥተን አጥፈን እንሰጦታለን

፦ankerbolt

፦stafa(ስታፋ ባለ 6 እና ባለ 8)በየትኛዉም size የተዘጋጀ አለን

፦ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን

አድራሻችን
ቁ.1  መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር  ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ
0904040477
0911016833
0994941706

ወይም @heavenic1 ፃፉልን

ይደዉሉልን ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም ቢሆኑ ካሉበት እንልክልዎታለን።
👍8
👉Proper reinforcement fabrication in the concrete
construction is very important..

🌟There are some errors which may occur in the reinforcement
placement on the site.

1. Errors in the placement of
Reinforcement

2. Improper spacing of the reinforcement (Main, Distribution)

3. Inadequate lap length. At the continuous edge of the slab, the discontinuity of reinforcement may occur.

4. Improper anchorage of the main reinforcement,With respect to the member

5. depth ineffective reinforcement was provided.

6. Improper spacing of rings (Stirrups, Ties)

7. Bar with less diameter was used.

8. Concrete cover may not properly provided.

9. The use of the rusted reinforcement in the construction.

10. Non uniform concrete cover of the reinforcement.

@etconp
👍16❤2
👉የጨረታ ማስጠበቂያ (Bid Security Bond)

🚧ለተቋራጮች የወጣ ጨረታ (በተለይ ክፍት ጨረታ /open tender/)

🌟የጨረታ ማስጠበቂያ መያዣ በማረጋገጫ ሰነድ (Bid Security Bond) ንዲካተት ይጠይቃል ይህ የጨረታ ማስጠበቂያ (Bid Security Bond) በ PPA (section 1) “instruction to bidder (ITB) አንቀጽ አሥራ ስድስት (article 16) ላይ እንደተመለከተው

⏺አንድ ተጫራች የወጣውን ጨረታ ሞልቶ ካስገባ በኋላ ጨረታውን ቢያሸንፍ እና አሸናፊነቱን የሚገልጽ የቅቡልነት ደብዳቤ ከተጻፈለት በኋላ ሀሳብ ቀይሮ “የተወዳደርኩበትን ጨረታ ትቼዋለሁ፣ የግንባታ ውል መፈራረም ይሁን ግንባታውን ማከናወን አልፈልግም” ቢል ጨረታውን ለማከናወን የወጣውን ወጪ ለመሸፈን እና በደረጃ ቅደም ተከተል መሰረት ለሌሎቹ አሸናፊዎች ጥሪ ለማድረግ አልያም እንደገና ውድድሩን የሚያስችል ገንዘብ ተደርጎ ጨረታውን ላወጣው አካል የሚሰጥ የባንክ ማረጋደረሰንጫ (Certified Payment Order - CPO) ሲሆን የገንዘቡ መጠን በጨረታ ሰነዱ Bid Data Sheet ITB 16 ላይ የተገለጸው መሆን አለበት።

▶️ነገር ግን አሸናፊው ተጫራች የአሸናፊነቱን ደብዳቤ ተቀብሎ ሥራውን መጀመር የሚችል ከሆነ በጨረታ ሰነዱ Bid Data Sheet ITB 15 (15.1 & 15.2) መሰረት ሙሉ ለሙሉ ተመላሽ ይሆናል።

🖱የጨረታ ማስጠበቂያ (ማስከበሪያ) ገንዘብ ለተጫራቹ የሚመለሰት ጊዜ በITB, article 16 (16.2) መሰረት ለ28 ቀናት በባንh ከቆየ በኋላ መሆን አለበት።

🫵የ ፌስቡክ ገፃችን መወዳጀት ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ በመግባት LIKE አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://www.facebook.com/etconp/
👍24👌3❤2
👉ነጻ የትምህርት እድል

🌟አጭር የማስተርስ ኮርስ

🚧በኪነ ህንጻ መሰረተ ልማትና ስነ ቤት ላይ ለሚያተኩረው ትምህርት እንዴት ማመልከት እንደሚቻል ዝርዝሩን በማስፈንጠርያው ተጠቅሞ ማየት ይቻላል።

https://www.ubi.pt/en/course/1319

@etconp
🙏12👍4❤2🕊2
የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ የግንባታ ስራ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽ ለማድረግ፣ ቀደም ሲል ምንም ዓይነት የመንገድ መሰረት ልማት ባልነበራቸው ፋኑኤል፣ በረከት እና ወታደር ሰፈር በመባል በሚታወቁት የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ጀመረ፡፡

በሁለት ሎት ተከፍሎ የሚገነባው የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገድ በተለያዩ ሀገር በቀል የስራ ተቋራጮች በኮብልና በአስፋልት ደረጃ የሚከናወን ነው፡፡

ሎት 2 በመባል የሚጠራውን የውስጥ ለውስጥ መንገድ ድሪባ ደፈርሻ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ በአስፋልት ደረጃ የሚገነባው ሲሆን፣ ሃይ ዌይ ኢንጂነሪንግ አማካሪ ድርጅት ደግሞ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን እየተከታተለው ይገኛል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 4.1 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን እና ለፕሮጄክቱ ማስፈፀሚያም ከ824 ሚሊዮን ብር በላይ የግንባታ ዋጋ ተይዞለታል፡፡

በሎት 2 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አሁን ላይ የአፈር ቆረጣ፣ የመንገድ ዳር የዝናብ ውሃ መፋሰሻ ቱቦ ቀበራና ሌሎች ተያያዥ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው፡፡

በሌላም በኩል ሎት 3 በመባል የሚጠራው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮጄክት 5.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን እና በኮብል የሚገነባ መንገድ ሲሆን፣ የግንባታ ሥራው ጥላሁን አበበ በተባለ ሀገር በቀል ጠቅላላ የስራ ተቋራጭ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ለሎት 3 ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከ252 ሚሊዮን ብር በላይ የግንባታ ዋጋ ተይዟል

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

@etconp
👍9❤5