Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉የጨረታ ማስጠበቂያ (Bid Security Bond)

🚧ለተቋራጮች የወጣ ጨረታ (በተለይ ክፍት ጨረታ /open tender/)

🌟የጨረታ ማስጠበቂያ መያዣ በማረጋገጫ ሰነድ (Bid Security Bond) ንዲካተት ይጠይቃል ይህ የጨረታ ማስጠበቂያ (Bid Security Bond) በ PPA (section 1) “instruction to bidder (ITB) አንቀጽ አሥራ ስድስት (article 16) ላይ እንደተመለከተው

⏺አንድ ተጫራች የወጣውን ጨረታ ሞልቶ ካስገባ በኋላ ጨረታውን ቢያሸንፍ እና አሸናፊነቱን የሚገልጽ የቅቡልነት ደብዳቤ ከተጻፈለት በኋላ ሀሳብ ቀይሮ “የተወዳደርኩበትን ጨረታ ትቼዋለሁ፣ የግንባታ ውል መፈራረም ይሁን ግንባታውን ማከናወን አልፈልግም” ቢል ጨረታውን ለማከናወን የወጣውን ወጪ ለመሸፈን እና በደረጃ ቅደም ተከተል መሰረት ለሌሎቹ አሸናፊዎች ጥሪ ለማድረግ አልያም እንደገና ውድድሩን የሚያስችል ገንዘብ ተደርጎ ጨረታውን ላወጣው አካል የሚሰጥ የባንክ ማረጋደረሰንጫ (Certified Payment Order - CPO) ሲሆን የገንዘቡ መጠን በጨረታ ሰነዱ Bid Data Sheet ITB 16 ላይ የተገለጸው መሆን አለበት።

▶️ነገር ግን አሸናፊው ተጫራች የአሸናፊነቱን ደብዳቤ ተቀብሎ ሥራውን መጀመር የሚችል ከሆነ በጨረታ ሰነዱ Bid Data Sheet ITB 15 (15.1 & 15.2) መሰረት ሙሉ ለሙሉ ተመላሽ ይሆናል።

🖱የጨረታ ማስጠበቂያ (ማስከበሪያ) ገንዘብ ለተጫራቹ የሚመለሰት ጊዜ በITB, article 16 (16.2) መሰረት ለ28 ቀናት በባንh ከቆየ በኋላ መሆን አለበት።

🫵የ ፌስቡክ ገፃችን መወዳጀት ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ በመግባት LIKE አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://www.facebook.com/etconp/
👍24👌3❤2
👉ነጻ የትምህርት እድል

🌟አጭር የማስተርስ ኮርስ

🚧በኪነ ህንጻ መሰረተ ልማትና ስነ ቤት ላይ ለሚያተኩረው ትምህርት እንዴት ማመልከት እንደሚቻል ዝርዝሩን በማስፈንጠርያው ተጠቅሞ ማየት ይቻላል።

https://www.ubi.pt/en/course/1319

@etconp
🙏12👍4❤2🕊2
የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ የግንባታ ስራ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽ ለማድረግ፣ ቀደም ሲል ምንም ዓይነት የመንገድ መሰረት ልማት ባልነበራቸው ፋኑኤል፣ በረከት እና ወታደር ሰፈር በመባል በሚታወቁት የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ጀመረ፡፡

በሁለት ሎት ተከፍሎ የሚገነባው የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገድ በተለያዩ ሀገር በቀል የስራ ተቋራጮች በኮብልና በአስፋልት ደረጃ የሚከናወን ነው፡፡

ሎት 2 በመባል የሚጠራውን የውስጥ ለውስጥ መንገድ ድሪባ ደፈርሻ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ በአስፋልት ደረጃ የሚገነባው ሲሆን፣ ሃይ ዌይ ኢንጂነሪንግ አማካሪ ድርጅት ደግሞ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን እየተከታተለው ይገኛል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 4.1 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን እና ለፕሮጄክቱ ማስፈፀሚያም ከ824 ሚሊዮን ብር በላይ የግንባታ ዋጋ ተይዞለታል፡፡

በሎት 2 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አሁን ላይ የአፈር ቆረጣ፣ የመንገድ ዳር የዝናብ ውሃ መፋሰሻ ቱቦ ቀበራና ሌሎች ተያያዥ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው፡፡

በሌላም በኩል ሎት 3 በመባል የሚጠራው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮጄክት 5.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን እና በኮብል የሚገነባ መንገድ ሲሆን፣ የግንባታ ሥራው ጥላሁን አበበ በተባለ ሀገር በቀል ጠቅላላ የስራ ተቋራጭ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ለሎት 3 ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከ252 ሚሊዮን ብር በላይ የግንባታ ዋጋ ተይዟል

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

@etconp
👍9❤5
👉የፌሮ ብረት ሥራ ላይ መሐንዲሱ መቆጣጠር ያለበት

🌟በግንባታ ሥራ ላይ የስትራhቸራል ክፍሎች ላይ የሚታሰር የፌሮ ብረት (Deformed Reinforcement bar) የኮንከሬት መዋቅርን ጥንካሬ የሚወስን ነው።

⏺ዋናውና ልዩ ትኩረት የሚሰጥበት ሥራ ስለሆነ መሐንዲሱ የሚከተሉትን ነጥቦች ማረጋገጥ አለበት።

▶️1. የፌሮ ብረት አይነትና ልኬት

🖱ለግንባታ ሥራው ጥቅም ላይ ለመዋል የቀረበው የፌሮ ብረት በውል ሰነዱ (contract document) ሥር ስፔስፊኬሽን ላይ የተመለከተውን የፌሮ ብረት ሳይንሳዊ መስፈርት ( Technical requirements) ያሟላ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት ይህ ማለት የሀገር
ውስጥ ብረት ፣ የቱርክ፣ የጣሊያን… Dia 8, Dia 10, Dia 14....» በሚል መለያ ትክክለኛ ብረት መቅረቡን እና በተገቢው ቦታ ጥቅም ላይ መዋሉን ማረጋገጥ አለበት።

▶️2.ብዛት ቅርጽ፦

🖱በኮንክሪት ስትራከቸር መዋቅር ከፍሎች ላይ Pad,Column,beams, slabs, concrete wall and stairs) የተዘረጋው የፌሮ ብረት በ ስትራክቸራል ዲዛይኑ ላይ በተመለከተው መሰረት ብዛቱ ተመሳሳይ መሆኑን፣ ብረቶቹ እርስ በእርሳቸው እና የብረቶቹ እጥፋት ቅርጽ በአግባቡ የተዘጋጁና የተሳሰሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለበት።

▶️3. የስታፋ እና ጥቁር ብረት አስተሳሰርን በተለይ የምሰሶ (column) እና ግንዴላ (beam) ፌሮ ብረቶች በስትራክቸራል ዲዛይኑ ላይ በተመለከተው የስታፋ ርቀት መሰረት (as per c/c of stirrups on ST drawing) መቀመጣቸውን፣ የስታፋ (stirrups) ብረቶች ዲያሜትር ትከከል
መሆኑን እና እያንዳንዱ ከስታፋ ጋር የተነካካ ዘላቂ በጥቁር ሽቦ የታሰሩ መሆናቸውን በሚገባ መርመር አለበት።

▶️4. ክፍተት መጠበቁን (spacing) አቀማመጥ፦

🖱በተለይ በጋንዴላ (beam) እና ወለል (slab) ሥራ ላይ ኮንክሬት ከመሞላቱ በፊት ብረት የተሰረው ከፎርምወርh ንጣፉ ቢያንስ 2.5 cm ርቀት ላይ መሆኑም ማረጋገጥ አለበት።

⏺በነገራችን ላይ እንደ ስትራክቸሩ ቢወሰንም spacing እስከ 7cm
ድረስ ሊሆን ይችላል የተነጠፈው
በቂ ክፍተት ያለው መሆን አለበት።

▶️5. የፌሮ ብረቶች እርስ በእርስ ርቀት፦
ያላቸውም ክፍተት መታየት

🖱ብረት ክፍተት ማስጠበቂያ (spacer) ለማሰር የሚያስችል የተዘረጉ ብረቶች ከ ፎርምወርክ ቦታ ብቻ ሳይሆን እርስ በእርስ
መታየት አለበት።

⏺የኮንክሬት ጠጠር ማለፍ በሚችልበት መልኩ በስትራክቸራል ዲዛይኑ ላይ የተመለከቱት ብረቶብ በአግባቡ መታሰራቸውን (ግማሹ የተጠጋጋ
ሌላው የተራራቀ አለመሆኑን) ማረጋገጥ አለበት በስትራከቸራል ዲዛይኑ
ያላቸውን ትስስር

▶️6.በቂ መደራረቢያ ርዝመት (lap length)፦

🖱አንድ ስትራክቸር ከሌላ የጎንዮሽ ወይን ወደ ላይ ከሚቀጥል ከፍል ጋር ለተሳሰር የሚያስችል በቂ የመደረቢያ ርዝመት ታሳቢ ተደርጎ የተቆረጠ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።

⚡️የዲዛይን ሶፍትዌር የራሱን መስጠት የሚችል ቢሆንም ብዙ ጊዜ 4 Cm*Diameter ነው።

📍ለምሳሌ:- ባለ dia 20 ፌሮ lap length= 40*20=800mm ይሆናል ማለት
ነው። Lap length ከሚያጥር ይልቅ ቢረዝም ይመረጣል፣ ካጠረ ግን ፌሮ ብረቱ መቀየር የሚኖርቡት ይሆናል።

▶️7. ጤናማ ፌሮ መሆኑን

🖱ጥቅም ላይ የዋለው ብረት ያልዛገ ወይም ያልተቀጠቀጠ ወይም አለግባብ ያልታጠፈ ወይም ምንም አይነት የመቆረጥ ምልክት የሌለበት መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።

@etconp
👍32👌9👏6😢1
👉ኣዲሱ ቻናላችን ተቀላቅለዋል?

⚡️ዛሬ የወጡ ጨረታዎች ጨምሮ

🌟አዳዲስ የ ኮንስትራክሽን ስራ እና ጨረታ ሲወጡ በቀላሉ ለመመልከት ከታች ባለው ሊንካችን ይቀላቀሉን።

📌እንዲሁም ለወዳጆቻቹ SHARE በማረግ አዳርሱ።

https://t.me/ETCONpWORK
🏆4👍1
#ADVERTISEMENTS

👉ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ

0904040477
0911016833 ደውለው ያግኙን

📩ወይም @heavenic1 ፃፉልን

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ ኮርቻ ተራ
                ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
                 ቁ.3 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት
                 ቁ.4 ቄራ ላይ በቅርቡ ይጠብቁን

🌟ከቃላችን ይልቅ ስራችን ይናገራል

🚧ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
👍2
👉የልኬት ውል (Admeasurement Contract)

🌟ይህ የውል አይነት ብዙ ጊዜ “unit rate Contract” ተብሎ ከሚታወቀው የውል አይነት ጋር እጅግ የተመሳሰለ ነው።

🫵ተቋራጩ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያስገባው የአንድ ልኬት ዋጋ እንዳለ ሆኖ የሥራው መጠን ግን አማናዊ ሥራው (Executed works) ላይ በተከናወነው ልኬት መሰረት የሚከፈልበት የውል ስጦታ አይነት ነው።

🖱ለምሳሌ፦ አንድ ተቋራጭ በጨረታው ላይ ለተመለከተው 4.5 ኪዩቢክ ሜትር አርማታ ቢሆን እና በአንድ ኪዩቢክ ሜትር 8ooo ብር አስገባ እንበል።

⏺ነገር ግን ወደ ሥራ ከገባ በኋላ የተሰራው አርማታ 5.0 ኪዩቢክ ሜትር
ቢሆን በልኬት ውል (Admeasurement Contract) ከተፈራረሙ ዋጋ ለመክፈውል የሚቆረጠው የሥራ መጠን ጨረታው ላይ
የነበረው 4.5 ኪዩቢክ ሳይሆን በሥራ ላይ
የተመዘገበው ልኬት ወይም 5.0 ኪዩቢክ ሜትር ነው።

▶️ነገር ግን አስቀድሞ ያስገባው የአንድ ኪዩቢክ ሜትር ማባዣ ዋጋ ወይም 8000 ብር ግን አይቀየርም።

📍ስለዚህ ለተቋራጩ የሚከፈለው 5.0*8000 = 40,000.00 ብር ይሆናል ማለት ነው።

▶️በዚህ ውል አይነት የሥራው መጠን በጨረታው ላይ ከተሞላው መጠን ሊለይ ቢችልም የአንድ ልኬት ዋጋ ግን መቀየር አይቻልም ማለት ነው።

@etconp
❤16👍6
👉ኣሰቸኳይ ጀማሪ አርክቴክት ፈልገናል

⏺ ጃክሮስ ኣከባቢ ቢሆን ይመረጣል

📩 @Maya923 ፃፉልን


@ETCONpWORK
👍3❤2🙏1
👉MOST USED SOFTWARE IN CONSTRUCTION ENGINEERING

🚧MS EXCEL

➡️Lets you store any complex data and simplIfy complicated calculations

🚧MS PROJECT & PRIMAVARA

➡️Lets you manage & scheduling huge projects (money,time,resources)

🚧SAP 2000

➡️The most popular structural analysis and design software used by Construction engineers all over the world.

🚧AutoCAD

➡️One of the most popular Construction engineering software by autodesk.

➡️This is used for 2D and 3D design, drafting, modeling, architectural drawing etc

🚧ARCHI CAD

➡️It is more of architectural design of different structures.

🚧ETABS

➡️The integrated software package for the structural analysis and design of buildings, ETABS offers unmatched 3D object based modeling and visualization tools, blazingly fast linear and nonlinear analytical power, sophisticated and comprehensive design capabilities for a wide range of materials, and insightful graphic displays, reports, and schematic drawings that allow users to quickly and easily decipher and understand analysis and design results.

🚧BIM

➡️BIM software is specifically built for Building Information Modelling (BIM), including features for architectural design, MEP and structural engineering and construction.

🚧AUTODESC CIVIL

➡️Builds on Autodesk Land Desktop with tools that automate Construction engineering tasks and enhance collaboration on projects from transportation engineering to hydraulics, site development to hydrology.

🚧SITE 3D

➡️Site 3D is a fully featured software product for the engineering design of road systems and housing developments. Quickly and accurately design whole sites including roads, junctions, roundabouts, footways, surface interfacing, contours, volumes, drainage, housing and more.

🚧REVIT

➡️for architectural design and for structural design and there is construction template in there and it’s very essential to calculate the wind load and seismic load.

🚧SAFE

➡️it’s for structural design and the difference between safe and ETABS is that it gives your the shape of the bar

🏷These are some the software Uses In Construction Industry.

@etconp
👍32❤12👏1🙏1🏆1
👉TYPES OF PIPES COMMONLY USED IN WATER SUPPLY SYSTEM

➡️TYPES OF PIPES

▶️The types of pipes commonly used in water distribution system are described below.

1⃣CAST IRON PIPES:

🚧Cast iron pipes or CI pipes are broadly utilized for distribution of water because they are less
expensive, corrosion resistant, and long lasting.
CI pipes are mainly produced by following four techniques.

⏺1. Horizontally cast ( MC ware pipes)
⏺2. Vertically cast ( Pit cast in sand molds)
⏺3. Centrifugally cast in sand lines molds spun
type.
⏺4. Centrifugally cast in water cooled molds.

▶️Uses of horizontally cast CI pipes are presently pretty much outdated, that’s why they are infrequently produced these days.

▶️Centrifugally cast pipes are most widely used because they have more grained dense structure and uniform thickness. Generally, CI pipes are 3-6 m long, so much heavy, and require extra care to avoid from damaging while transporting and creating connections.

2⃣STEEL PIPES:

🚧Steel pipes are utilized in water mains circumstances where the pipes are going through very high pressure ( More than 7 kg/cm2) and required large diameter pipes.

🚧These pipes have greater strength and less weight than CI pipes. Satisfactory treatments should be given to maintain antagonistic climatic conditions.

3⃣ GALVANIZED IRON PIPES:

🚧Galvanized pipes are also known as GI pipes are fashioned steel pipes with zinc coating.

🚧GI pipes are mostly utilized for water supply and service connections.

4⃣COPPER PIPES:

🚧Copper pipes are most commonly utilized in hot water supply establishment.

🚧Some features of
this pipes are as following:

⏺1. They possess high tensile strength.
⏺2. They can be bent easily.
⏺3. Copper pipes can be used in thin wall.

➡️Copper pipes are sometimes chromium plated to enhance their appearance and to match with the chromium plated water supply fittings.

5⃣POLYTHENE PIPES:

🚧Polythene and PVC pipes are being utilized progressively nowadays for cold water supply inside and outside works.

🚧These pipes are lightweight, cheaper, corrosion resistant, and require no threading for making any connections.

🚧Besides these, there are other pipes commonly used for water distribution such as : asbestos cement (AC) pipes, Reinforced concrete (RCC) pipes, prestressed reinforced concrete (PSC) pipes etc.

🚧The selection of the types of pipe for utilizing any purposes is adopted according to the design criteria, material availability, cost, and other comparative variables.

@etconp
👍21🙏3❤1💯1
👉ለ ባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ ማጠናቀቂያ ተጨማሪ 900 ሚሊዮን ብር ተመደበ

🚧የአማራ ክልል መንግስት ለባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ሁለተኛ ዙር ግንባታ ማጠናቀቂያ ተጨማሪ 900 ሚሊዮን ብር መመደቡን የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ገልጿል።

⏺ቢሮው የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅደ ትውውቅ እና የአንደኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ይገኛል፡፡

⏺በመድረኩ የባህርዳር ዓለም-አቀፍ ስታዲየም ግንባታን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ስለመሆኑ ተገልጿል፡፡

▶️ለዚህም የክልሉ መንግስት ተጨማሪ 900 ሚሊዮን ብር መመደቡ ነው የተገለፀው።

⏺እስካሁን ባለው አፈፃፀምም ከ676 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ ተፈፅሞ ስራው እየተካሄደ መሆኑም መገለፁን ከክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

⏺ባለፈው በጀት አመት የክልሉ መንግስት 700 ሚሊዮን ብር በመመደብ ሁለተኛውን ዙር የባህርዳር ስታዲየም ግንባታ ማስጀመሩ ይታወሳል።

Via EBC

@etconp
👍14😁2❤1
👉ለሚመለከታቹ በ ሙሉ

@etconp
👍10😁3🕊1
#ADVERTISEMENTS

👉ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ

0904040477
0911016833 ደውለው ያግኙን

📩ወይም @heavenic1 ፃፉልን

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ ኮርቻ ተራ
                ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
                 ቁ.3 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት
                 ቁ.4 ቄራ ላይ በቅርቡ ይጠብቁን

🌟ከቃላችን ይልቅ ስራችን ይናገራል

🚧ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
❤1
👉የአርማታ ሙሌታ (Concrete Compaction) ቁጥጥር

🌟1. የግብአት ጥራትን (Materials Quality)፦ በአርማታ ሙሌት ሥራ ሂደት ውስጥ የሚጠቀማቸውን የማምረቻ ግብአቶች ጥራት በተገለጸው መስፈርት መሰረት የሚያሟሉ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት። ይህ ማለት የቀረበው ሲሚንቶ (Cement) አይነትና የምርጥ ጥራት፣ የአሸዋ (sand or Fine aggregate) እና ጠጠር (Coarse Aggregate) ሳይንሳዊ ምዘናን ማሟላቱን፣ የማቅጠኛ ውሀ (Water) የኮንክሬት ስትራክቸሩን ሊጎዳ የሚችል ኬሚካልና ቆሻሻ የሌለው የጠራ ውሃ መሆኑን እና ሌሎች ተጨማሪ ኬሚካል (Admixture) መለያ አይነት የተሟላ መሆኑን ሳይንሳዊ ማስረጃ ላይ ተደግፎ የማረጋገጥ ሂደትን መተግበር ማለት ነው። በዚህ ረገድ የግብአት መሐንዲሱ (Materials Engineer) ለሳይቱ በቀረበው የቤተሙከራ ክፍል ውስጥ በመስራት የማረጋገጥ አልያም በቅርቡ በሚገኝ የቤተሙከራ አገልግሎት ሰጪ ተቋማ በማሰራት የግብአቶችን ጸባይ የመለየትና ማረጋገጫ የመስጠት ግዴታ ይኖርበታል።

🌟2. የግብአቶችን ልኬት (Batching of materials):- በተለይ በሀገራችን የግንባታ ልምድ ኮንክሬት በሚመረትበት ሰዓት ያለው የአሸዋ፣ የጠጠር እና የውሃ ልኬት ለችግር የተጋለጠ ነው። አንድ 1፡2፡3 ምጥጥንን መሰረት አድርጎ ዲዛይን የተሰራ አርማታ አንድ እጅ ሲሚንቶ፣ ሁለት እጅ አሸዋ፣ ሦስት እጅ ጠጠር መጠቀም አለበት ማለት ቢሆንም የመቀላቀያ ማሽኑ ተቆጣጣሪ (Mixer Operator) ይህንን ምጥጥን ጠብቆ አምራታ የማምረት ልምድ ቸልተኝነት የተሞላበት እንደሆነ ይስተዋላል። ተቆጣጣሪ መሐንዲስ በምጥጥን (Proportion) መሰረት እየተመረት መሆኑን መቆጣጠር የግድ ነው።

🌟3. የማሽን እና መሳሪያ ደህንነት (Equipments Security):- የኮንክሬት ድብልቅ ማምረቻ ማሽኖች (mixers) ደህንነታቸው የተረጋገጠ ወይም በአግባቡ የሚሰሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣ የኮንክሬት ግብአቶችን መለኪያ ሳጥኖችን (box) ርዝመት ወርድ እና ቀመት (L, W, H) አግባብነት ያለው መሆኑን (ለምሳሌ፦ 18*40*50)፣ የሰው ህይወት እንዳይጠፋ ብሎም የካሳ ሙግትና የሥራ ማቆም መሰናክል እንዳይፈጠር የሰራተኞች ደህንነት መጠበቂያ አልባሳት የተሟሉ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።

🌟4. በአግባቡ መጠቅጠቁን፦ የሚሞላው አርማታ በተለይ ምሰሶ (column) እና የምሰሶ ጫማ (Footing Pad) በክፍልፋይ ላየሮች  ከፋፍሎ እያንዳንዱ የላየር ክፍል ጫፍ ላይ ሲደርስ በኤሌክትሪክ መንዘሪያ (Vibrator) በደንብ መጠቅጠቅ መቻል አለበት። የአርማታ መጠቅጠቅ እያንዳንዱ የግንባታ ግብአት በአግባቡ የተሰራጨ እንዲሆን እና የቀጠነው አርማታ ወደታች ወርዶ ጠጠራማው ወደላይ እንዳይቀር በማድረግ የትኛውም የስትራክቸር ክፍል ተመሳሳይ አይነት ጥንካሬ እንዲኖረው ያደርጋል።

🌟5. የአርማታ ድርቀት እንዳይኖር መቆጣጠር፦ የአርማታ ሙሌት ሂደት ላይ አዲስ የተመረተ አርማታ አላስፈላጊ ደቂቃዎችን ሳይሞላ መቆየት የለበትም። አርማታ ሳይሞላ ከሚክሰር እንደተገለበጠ የሚቆይ ከሆነ በፎርምወርክ ውስጥ ሆኖ መያዝ ያለበትን የመጀመሪያ ጥንካሬ (Initial Setting) መያዝ ስለሚጀምር ከዚያ በኋላ ሙሌትን ለማከናወን አዳጋች ከመሆኑም በላይ የሚፈለገውን የኮንክሬት ስትራክቸር ጥንካሬ ለማግኘት አዳጋች ይሆናል።

🌟6. የድኅረ ሙሌት ቁጥጥር፦ አርማታ ከተሞላ በኋላ በሳይንስ የተቀመጡ የፎርምወርቅ ማስወገጃ ቀናቶችን (Formwork Removal time) ጠብቆ እንዲፈርስ ማድረግ (በተለይ በቀዝቃዛማ እና ዝናባማ አካባቢዎች)፣ የተሞላው አርማታ በአግባቡ ውሃ እየጠጣ (curing) መሆኑን መከታተል እና የሚቀጥሉ የኮንክሬት ስትራክቸሮች ካሉ የተሞላው አርማታ በቂ ጥንካሬ ካገኘ በኋላ ሥራቸው የሚጀምር መሆኑን መከታተል አለበት።

🫵የ ኮንስትራክሽን ስራ እና ጨረታ በ ትኩሱ እንዲደርስዎ ከታች ባለው የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇

t.me/ETCONpWORK

📩ሊያወሩን ካሰቡ በቴሌግራም @ETCONpBot ይጻፉልን።

@etconp
❤9👍8🙏1
👉አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) የዓባይ ግድብ ዋና ተደራዳሪ ሰለህዳሴ ግድብ ትላንት ከተናገሩት መካከል

🚧ሰኔ ላይ የኮንክሪት ስራዉ ሙሉ ለሙሉ ያልቃል፤

🚧በያዝነው አመት አምስት ተርባይኖች ወደ ስራ ይገባሉ፤

🚧ከ94 በመቶ በላይ ደርሷል፤

🚧ቀሪ ሥራዎች በፍጥነት እየሄዱ ነው፤ በ2016 ውስጥ ይጠናቀቃሉ >>ብለዋል።

@etconp
❤14👍1😢1