Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ

፦ፕሌት 1mm-30mm any size ቆርጠን በስተን ጣጣዉን ጨርሰን እናስረክቦታለን

፦jbolt 12mm-32mm በፈለጉት ቁመት ጥርስ አዉጥተን አጥፈን እንሰጦታለን

፦ankerbolt

፦stafa(ስታፋ ባለ 6 እና ባለ 8)በየትኛዉም size የተዘጋጀ አለን

፦ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን

አድራሻችን
ቁ.1  መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር  ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ
0904040477
0911016833
0994941706 ወይም @heavenic1 ፃፉልን

ይደዉሉልን ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም ቢሆኑ ካሉበት እንልክልዎታለን።
👍2🙏2
👉የወንጪ ፕሮጀክት

🌟የገበታ ለሀገር አንዱ አካል የሆነው የወንጪ ፕሮጀክት መጋቢት 11 ቀን 2013 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

🚧ፕሮጀክቱ በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በወንጪ ወረዳ የሚገኝ ሲሆን÷ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

🚧ከአዲስ አበባ በ150 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ወንጪ 3 ሺህ 380 ሜትር ከፍታ ላይ ሲገኝ ሃይቅና ፍል ውሃን ጨምሮ እጅግ ማራኪ የሆኑ የተፈጥሮ ሃብቶችን ይዟል።

🚧በአካባቢው የሚገኘው ደንና በውስጡ ያሉት ብርቅዬ አዕዋፋት ዝማሬ የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስቡ ናቸው።

🚧ስራው በተለያዩ ምዕራፎች ተከፋፍሎ የሚካሄድ ነው።

⏺በዚህም በመጀመሪያው ምዕራፍ ወደ ወንጪ ሃይቅ የሚወስደው የአስፋልት መንገድ፣ ሁለቱን ሃይቆች የሚያገናኝ የአስፋልት መንገድ፣ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት፣ የጤና ማዕከል፣ ትምህርት ቤቶች፣ የቴሌኮም ማሻሻያ ፕሮጀክት እንዲሁም በባለሃብቶች የሚገነቡ ደረጃቸውን የጠበቁ ማዕከሎችን የሚያካትት እንደሆነ ገልጸዋል።
ከዚህ ባለፈም፣ የጤና ማዕከል፣ የቴሌኮም ማሻሻያ፣ በግል ባለሀብቶች የሚሰሩ መዝናኛ ስፍራዎች እንዲሁም የትምህርት ማዕከል እና አነስተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ይገነባል ማለታቸው ይታወሳል፡፡

🖱ቱሪስቶችን በስፋት የመሳብ አቅም እንዳለው የሚነገርለት የወንጪ ፕሮጀክት የአካባቢው ነዋሪዎችም በብዙ እንደሚጠቀሙ ታምኖበታል፡፡

Via FBC

@etconp
👍12
👉ግንባታ ከመጀመሩ በፊት Geo Technical site investigation ( የጂኦ-ቴክኒካል ምርመራ ) ለምን እናደርጋለን ጥቅሙስ ?

🌟የጂኦ-ቴክኒካል ምርመራ ዋና ዓላማ ግንባታ በሚካሄድበት ቦታ የአፈር ምርመራ ማድረግ ነው።

▶️በግንባታ መስክ ውስጥ ሊከተሏቸው ከሚገቡ ዋና ዋና ተግባራት መካከል የጂኦቴክኒካል ምርመራ አንዱ ነው።

▶️የጂኦቴክኒካል ምርመራዎች የሚከናወኑት በጂኦቴክኒካል መሐንዲሶች ወይም በምህንድስና ጂኦሎጂስቶች የመሬት ስራዎችን እና ለታቀዱ አወቃቀሮች ለመንደፍ እና ለመሬት ስራዎች እና አወቃቀሮች መሠረቶችን ለመንደፍ በአንድ ግንባታ ቦታ ዙሪያ ስላለው የአፈር እና የድንጋይ አካላዊ ባህሪያት መረጃን ለማግኘት ነው።

🚧ይህ ዓይነቱ ምርመራ የሳይት ምርመራ ተብሎ ይጠራል.

⏺በተጨማሪም፣ የጂኦቴክኒካል ምርመራዎች እንዲሁም ለመሬት ስር ማስተላለፊያ መስመሮች፣ ዘይት እና ጋዝ ቧንቧዎች፣ ሬዲዮአክቲቭ የቆሻሻ አወጋገድ እና የፀሐይ ሙቀት ማከማቻ ፋሲሊቲዎች የሚፈለጉትን የአፈር ወይም የድጋሚ ሙሌት ቁሶች የሙቀት መቋቋምን ለመለካት ጥቅም ላይ ይውላሉ።

🖱የጂኦቴክኒካል ምርመራ ለምን አስፈላጊ ነው?

✨ሊያጋጥሙ የሚችሉ የመሬት ሁኔታዎችን ጥሩ ግምገማ ያቀርባል።

✨ግንባታው ለታለመለት ልማት ወይም መልሶ ማልማት ዓላማ ተስማሚ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ይሰጣል።

✨በጥሩ ምህንድስና አሠራር መሰረት ዲዛይን እና ግንባታን ለመርዳት ተስማሚ መለኪያዎችን ያቀርባል።

✨በፕሮጀክቱ የሕይወት ዑደት ውስጥ በአካባቢ ላይ ያለውን አደጋ እና በሰዎች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ፈልጎ እና ክትትል ያደርጋል።

⚡️በሁሉም የፕሮጀክት በጀት አወጣጥ ላይ ይረዳል፣ ቀልጣፋ ዲዛይን ይፈቅዳል፣ እና ግንባታው በምሰራበት ቦታ ላይ ሊከሰቱ ስለሚችሉ አደጋዎች አስቀድሞ ያስጠነቅቃል።

🫵በቀላል አነጋገር

☄የጂኦቴክኒካል ምርመራ ፕሮጀክቱ አዋጭ እንደሆነ እና በተቀላጠፈ መልኩ ሊቀረጽ እና ሊገነባ እንደሚችል እንደ ጠቃሚ ማረጋገጫ ሆኖ ያገለግላል።

📎የጂኦቴክኒክ መሐንዲሶች በአንድ ቦታ ላይ በታቀዱ የግንባታ መዋቅሮች ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉትን አደጋዎች በመለየት የተካኑ ናቸው።

🔗ይህንን በተለያዩ የምርመራ ቴክኒኮች፣ በጉድጓዶች ቀጥተኛ ናሙና እና የሙከራ ጉድጓዶችን እና ቀጥተኛ ያልሆኑ የጂኦፊዚካል ቴክኒኮችን ጨምሮ ሊያደርጉ ይችላሉ።

📝የጂኦቴክኒካል ትንተና ልዩ ሶፍትዌርን በመጠቀም የገሃዱ አለም እንቅስቃሴን እና የድርጊት ሁኔታን ለመገመት በጂኦቴክኒካል መለኪያዎች መሰረት መዋቅራዊ ባህሪን መምሰል ይችላል።

@etconp
👍13❤4
ጀንቦሮ ሪል ስቴት ለዳያስፖራ ማኅበር አባላት በልዩ ቅናሽ ቤት ለመሸጥ ተስማማ

“በጊዜ ግቡ!” በማለት የሚታወቀው ጀንቦሮ ሪል ስቴት ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበር ጋር ዛሬ ጥር 2 ቀን 2016 ዓ.ም በተለያዩ ዓለማት ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት በልዩ ቅናሽ ቤት ለመሸጥ መፈራረሙን ገልፀዋል::

በስምምነቱም መሠረት ጀንቦሮ ሪል ስቴት ቦሌ ቡልቡላ 70 በመቶ ግንባታቸው የተጠናቀቁ አንድ መቶ ቤቶችን እንዲሁም ዲፕሎማቲክ ሰፈር በሆነው ሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አካባቢ በሦስት ዓመት ውስጥ ተገንብቶ በሚጠናቀቀው ቅንጡው የኪሩ አፓርትመንት፣ አራት መቶ ቤቶችን ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበር አባላት በልዩ ቅናሽ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበር በ2001 ዓ.ም የተቋቋመና በሥሩም ከ10,000 በላይ በተለያዩ አገራት የሚኖሩ አባላት ያቀፈ ነው።

ጀንቦሮ ከገነባቸውና እየገነባ ካላቸው ስድስት ፕሮጀክቶች ሦስቱን ያስረከበ ሲሆን፣ በሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አካባቢ እያስገነባ ያለው ኪሩ አፓርታማ ከመኖሪያ ቤት በዘለለ ጥሩ የሕይወት ዘይቤና ቅንጡ አኗኗርን ለሚመኙ ኢትዮጵውያን የመጀመሪያው አማራጭ እንደሆነ ነው የተገለፀው።

በ5,077 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ኪሩ ፕሮጀከት ሲጠናቀቅ፣ 30 ወለሎች የሚኖሩት ሲሆን፣ ሰባት ወለል የመኪና ማቆሚያ እንዲሁም አምስት ወለሎች ደግሞ ለዓለም አቀፍ ብራንድ ሱቆች በተጨማሪም 1,000 ካሬ ሜትር አረንጓዴ ስፍራ ይኖረዋል።

መነሻውን ቦሌ ቡልቡላ አድርጎ ከአራት ዓመታት በፊት በሪል ስቴት ዘርፍ ልማት ላይ የተሰማራው ጀንቦሮ ሪል ስቴት፣ በቦሌ ቡልቡላ አምስት ፕሮጀከቶችን እንዲሁም በቅርቡ ደግሞ በሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አጠገብ ለአካባቢው የተለየ ገፅታ የሚሰጠውን ኪሩ አፓርትመንት በመገንባት ላይ ይገኛል።

@etconp
👍8❤7👌2
👉የቴምብር ቀረጥ (Stamp Duty)

🚧በኮንስትራክሽን ሥራዎች ውስጥ ታሳቢ የሚደረግ የግልግል (award)፣ የማገቻ (bonds)፣ የውል ስምምነትና መግለጫ (5) contract and agreements and memoranda thereof) ፣ የማስጠበቂያ መያዣ (security deeds) ፣ የሥራ (ቅጥር) ውል (contract of employment) ፣ የመሳሪያ፣ ቢሮ ኪራይ ማስተላለፊያ ሰነዶች (lease, including sub-lease and transfer of similar Rights) ፣ የውክልና ሥልጣን ማረጋገጫ (power of attorney) ሰነዶችን ሕጋዊ በማድረግ ሂደት ውስጥ የሚኖሩ የቴምብር ቀረጥ (Stamp Duty) ይጣልባቸዋል።

🌟ይህ ሕግ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነጋሪት ጋዜጣ ላይ የወጣው አዋጅ ቁጥር 110/1990 ዓ.ም ገጽ 736 ላይ የተመለከተ ሲሆን በግልግል ላይ የሚተመን ዋጋ ያለው ከሆነ 1% ሲሆን የማይተመን ዋጋ ላለው ግልግል 35 ብር ነው።

⏺የቴምብር ቀረጥ (Stamp Duty)

▶️የማገቻ (bonds) እና የመያዣ (security deeds) በፐርሰንት 1% ሲሆን የቅጥር ውል ላይ ለመዘጋጅ ሰነድ የአንድ ወር ደመወዝን 1% ነው።

▶️የመሳሪያ፣ ቢሮ ኪራይ ማስተላለፊያ ሰነዶች ሲዘጋጁ 0.5% ሲሆን በማንኛውም ጨረታ ላይ የሚሳተፍን አንድ ሰው የውክልና ሥልጣን ማረጋገጫ (power of attorney) ለሚሰጥበት ሰነድ ብር 35.00 ያስከፍላል።

🖱በዚህ አግባብ የአቅም ማረጋገጫ (Performance bond/guarantee) ማገቻ በሚል ምድብ ሥር የሚያርፍ ስለሆነ ባንኩ በሚጽፈው የጋራንቲ ሰነድ ላይ ቴምብር ማስቀመጥ ስላለበት የቴምብር 1% (1/100 of Performance bond) መክፈል ግዴታ ነው።

📍ፌስቡክ👇
https://www.facebook.com/etconp/

📩ሊያናግሩን ካሰቡ በቴሌግራም t.me/ETCONpBOT ይጻፉልን።

@etconp
👍12❤1
👉በያዝነው የፈረንጆች አዲስ አመት ግንባታቸው የሚጀምርና በግንባታ ላይ የሚገኙ ስድስት ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች የሚከተሉት ናቸው

🖱ሦሰቱ ከግብጽ ሲሆኑ ኬንያ፣ አይቮሪኮስትና ኢትዪጵያ አንድ አንድ አስመዝግበዋል።

🌟ከእነዚህ ውስጥ  ቁመቱ 270 ሜትር የአቢሲኒያ ባንክ የሚያስገነባው ዋና መሥሪያ ቤት በሁለተኛነት ደረጃ ተቀምጧል።

🚧Tallest Buildings Under Construction in Africa  2024

✨1. Tour F

   - Height: 386 m (1,266 ft)
   - Location: Abidjan, Ivory Coast
   - Expected Completion: 2025

✨2. Bank of Abyssinia Headquarters

   - Height: 270 m (890 ft)
   - Location: Addis Ababa, Ethiopia
   - Expected Completion: 2025

✨3. Iconic Tower Alamein

   - Height: 250 m (820 ft)
   - Location: El Alamein, Egypt
   - Expected Completion: 2026

✨4. Capital Diamond Tower

   - Height: 239 m (784 ft)
   - Location: New Admin, Egypt
   - Expected Completion: 2026

✨5. Infinity Tower

   - Height: 200 m (660 ft)
   - Location: New Admin, Egypt
   - Expected Completion: 2024

✨6. 88 Nairobi Condominium Tower

   - Height: 176 m (577 ft)
   - Location: Nairobi, Kenya

@etconp
👍14
👉የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የእድሳትና የጥገና ስራ 65 በመቶ መጠናቀቁ ተገለፀ።

🚧የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል 65 በመቶ መድረሱ ሲገለፅ የጉብኝት ስነ ሥርዓት ተካሂዶ ዕድሳቱ ስለደረሰበት ደረጃ በተቋራጭ መሐንዲሱ ቨርኔሮ በኩል በቅፅር ጊቢው ገለጻ ተደርጓል።

🖱በገለፃው መሰረት ፦

✨የጉልላት ጥገና ስራ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን የጉልላት ውስጥ የስእል ጥገና እና እድሳት ስራ በመካሄድ ላይ ይገኛል ተብሏል።

✨የመዋቅር ማጠናከር ስራ 95 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ የቤተክርስተያኑ የውስጥ የፎቅ ወለል (ሜዛኒን) 100 % መጠናቀቁ ተጠቁሟል።

✨የአጠቃላይ የእድሳትና የጥገና ስራ 65 በመቶ መጠናቀቁ የተገለፀ ሲሆን የፅዳት ሥራ ፣ የውሀ መተላለፊያ መስመሮችን ማስተካከል እንዲሁም የጥገና ሥራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑን ተጠቁሟል።

⏺የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ እሴቱን በጠበቀ መንገድ የዕድሳትና የጥገና ስራው እንዲከወን በመስከረም 2015 ዓ/ም ርክክብ ተደርጎ እየተሰራ መሆኑ ሲገለፅ በቀጣይም ሌሎች ሥራዎች እንዳሉና በተያዘለት የጊዜ ገደብ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚታመን የካቴድራሉ ፀሐፊ ላዕከ ሰላም ሽታው አድማሱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

⏺አጠቃላይ የእድሳቱ የኮንትራት ጊዜ 545 ቀናት ሲሆን እድሳቱን ለማከናወን አሁናዊ የዋጋ ጭማሪና የእቃዎች ሀገር ውስጥ አለመገኘት የመሳሰሉ ችግሮች በማጋጠሙ ሕዝበ ክርስቲያኑ በአቢሲኒያ፣ አዋሽ፣ ዓባይ፣ ንግድ እና ቡና ባንክ በተከፈቱት አካውንቶች የተቻለውን እንዲያደርግ የደብሩ አስተዳዳዳሪ ሊቀ ሥልጣናት ቆሞስ አባ ሲራክ አድማሱ ጥሪ አቅርበዋል።

  @etconp
❤7👍4
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ

፦ፕሌት 1mm-30mm any size ቆርጠን በስተን ጣጣዉን ጨርሰን እናስረክቦታለን

፦jbolt 12mm-32mm በፈለጉት ቁመት ጥርስ አዉጥተን አጥፈን እንሰጦታለን

፦ankerbolt

፦stafa(ስታፋ ባለ 6 እና ባለ 8)በየትኛዉም size የተዘጋጀ አለን

፦ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን

አድራሻችን
ቁ.1  መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር  ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ
0904040477
0911016833
0994941706 ወይም @heavenic1 ፃፉልን

ይደዉሉልን ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም ቢሆኑ ካሉበት እንልክልዎታለን።
👍2🏆1
👉ነጻ የስልጠና እድል🌟

🖱አቡቀለምሲስ ግሩፕ የተመሰረተበትን 15ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በአቡቀለምሲስ ሪል እስቴት ማሰልጠኛ ተቋም ለ25 የሪል እስቴት ሙያ ስልጠና ፈላጊዎች ሙሉ ክፍያቸውን ሸፍኖ ልዩ ስልጠና እንዲወስዱ እድሉን አመቻችቷል።

✨የስልጠናው መስፈርቶች

1) ቢያንስ አንድ የመጀመሪያ በማንኛው ዘርፍ ዲግሪ ያላቸው
2) ስራ የሌላቸው
3) የተዘጋጀውን የመግቢያ ቃለ መጠይቅ የሚያልፉ
4) ምንም አይነት የሪል እስቴት ሽያጭ ስራ ያልሰሩ
5) ለአንድ ወር ከሰኞ እስከ አርብ በከሰዓት ክፍለ ጊዜ qqየሚሰጠውን የክፍል ውስጥ ስልጠና ተከታትለው ለመጨረስ ጊዜ ያላቸው
6) በልዩ ሁኔታ ለዚህ ዙር የተዘጋጀው የሶስት ሳምንት ተግባራዊ ስልጠና መታደም
7) ቢያንስ ለ ሶስት ወራት በወር 5000 ብር ክፍያና ከ2-4% commission ክፍያ ከእህት ሽያጭ ተቋማችን ጋር ለመስራት የሚፈቅዱ

📩በስልጠናው ለመሳተፍ የምትፈልጉ በስልክ ቁጥሮቻችን 0951040404 እና 0993232323 በመደወል ወይም ቴክስት በመላክ መመዝገብ ይችላሉ።

@etconp
👍19
👉የወንጪ - ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደር ዛሬ ይመረቃል

🌟በ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ገበታ ለሀገር" መርሃ ግብር ከተገነቡት መዳረሻዎች ሶስተኛው የወንጪ - ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደር ዛሬ እንደሚመረቅ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

@etconp
❤12👍4
👉የፎርምወርክ ማፍረሻ ቀነ ገደብ

🚧በቀድሞው የሀገራችን የሕንጻ እና መንገድ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ባለሥልጣን (Building and Transport Construction Design Aucthority – BaTCoDA Specification) ላይ በቁጥር 03244  ላይ እንደተመለከተው  ፎርምወርክ የሚነሳበት (የሚነቀልበት/የሚፈርስበት) ቀንን (Formwork Removal) በተመለተ እንደሚከተለው አስቀምጧል።

⏺አቀባዊ የአርማታ ግድግዳዎች ( shear wall)፣ አምዶች (columns) እና aግዳሚ ጋንዴላዎች ወይም ምሰሶዎች (beams) = ከ16 ሰዓታት በኋላ

⏺የወለል አርማታ ሙሌት የታችኛው አልጋ (slab soffit) = በ21 ቀናት ውስጥ

⏺የወለል አርማታ የጎንዮሽ ማፈኛ (props of slab) = በ14 ቀናት

⏺የአግዳሚ ጋንዴላ/ምሰሶ የታችኛው አልጋ (soffit of beam) = 21 ቀናት

⏺የአግዳሚ ጋንዴላ/ምሰሶ የጎንዮሽ ማፈኛ (Props of beam) = 14 ቀናት

🖱ማሳሰቢያ፦ ለተዘረዘሩት የአርማታ ስትራክቸር ክፍሎች (Concrete skeletons) የተጠቀሱት ቀናት "ቢያንስ ቢያንስ" ተብሎ የተቀመጠ ዝቅተኛው የጊዜ ገደብ ነው።

@etconp
👍15❤9
👉በ600 ሚሊየን ብር የተገነባው የሰንጋተራ ህንፃ ተመረቀ

🚧የሰንጋተራ ነጋዴዎች ህብረት አክሲዮን ያስገነባው ህንፃ በዛሬው እለት የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት አካላትና እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

🌟የሰንጋተራ ነጋዴዎች ህብረት አክሲዮን ማህበር በ1995 ዓ.ም በ71 አባላት የተመሰረተ ሲሆን ማህበሩም አዲስ አበባ ሰንጋተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ላይ በ600 ሚሊየን ብር ያስገነባውን ባለ 23 ወለል ትልቅ የገበያ ማዕከል ገንብቶ ስራ በማስጀመር በዛሬው እለትም የህንፃውን ምረቃ መርሃግብር አካሄዷል።

🖱አጠቃላይ ለህንፃው የተሰጠው ቦታ 3 ሺ 500 ካሬ ሜትር ሲሆን ህንፃው ያረፈበት 2 ሺ 800 ካሬ ላይ መሆኑ ተገልጿል

🖱ህንፃው 5 ባንኮችን ፣ የብሄራዊ ቲያትር ጽ/ቤት ፣ ፐርፐዝ ብላክ ከፍተኛ ቢሮዎች ፣ የህንፃ መሳሪያዎች ፣ የኤኬክትሪክ እቃዎች መሸጫ ፣ የጥርስ ህክምና ፣ የእርዳታ ድርጅቶች ፣ የግል ሰራተኞች ጽ/ቤት ፣ የምግብ አዳራሽ ካፌ አገልግሎትና የመሰብሰቢያ አዳራሾችን በውስጡ ይዟል።

⏺በቅርቡም የጂም አገልግሎት በቅርብ የሚከፈት ሲሆን ከ3000 በላይ ለሆኑ ሰራተኞች የስራ እድል መፍጠሩም ተገልጿል።

⏺እንዲሁም ህንፃው 2 ቤዝመንት የፓርኪንግ አገልግሎት እንደሚሰጥም ተነግሯል።

Via ድሬቲዩብ

@etconp
👍16❤2