Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉የግንባታ ላይ አደጋ

🚧እየተገነባ ባለ ህንጻ አርማታና ብረት ተደርምሶ ሁለት ሰራተኞች ህይወታቸው አለፈ


🌟በአዲስ አበባ ከተማ ጥር 19 ቀን 2016 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኦርማ ጋራዥ ጀርባ እየተገነባ ባለ ህንጻ ላይ እየተሞላ ያለ አርማታና ብረት ተደርምሶ በስራ ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አስታውቋል።

🖱የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደተናገሩት የሟቾቹ ዕድሜ 32 እና 35 መሆኑን ገልፀዋል።

🖱የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የሟቾቹን አስከሬን ከተጫናቸዉ ፍርስራሽ ስር አንስተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።

⚡️የኮንትራክሽን ስራዎች በሚሰሩበት ጊዜ አስሪዎችም ሆነ ሙያተኞች አስፈላጊዉን የደህንነት መርሆዎች ባለመከተል መሰል አደጋዎችን የሚያስከትል በመሆኑ የጥንቃቄዉ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ያሻዋል ሲሉ አቶ ንጋቱ ተናግረዋል።

Via Ethio FM107.8

@etconp
👍4😢3❤1
Ethio Construction Engineering
👉የኮንስትራክሽን ባለሙያ ብቃት ማረጋገጫ (ክፍል አንድ) 🌟በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የወጣ "የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ ቁጥር 648/2013" የሚል ስያሜ የተሰጠው መመሪያ  አንቀጽ 15 (1 እና 2) ላይ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችን እና ሙያተኖችን  ሙያተኞች በሦስት ዋና ዋና ምድቦች ከፍሏቸዋል። 🚧ምድብ ሀ፦ አነ ስተኛ ሙያተኛ…
👉የኮንስትራክሽን ባለሙያ ብቃት ማረጋገጫ

🖱ክፍል ሁለት

🌟በደረጃ ሦስት ሥር የሚመደቡት ከፍተኛ ባለሙያ እርከን ሥር ያሉት ባለሙያዎች፦ ምሩቅ መሐንዲስ ወይም አርክቴክት (Graduate Engineer/Architect)፣ ፕሮፌሽናል መሐንዲስ ወይም አርክቴክት (Professional Engineer/Architect) እና ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል መሐንዲስ ወይም አርክቴክት (Practicing Professional Engineer/Architect) በሚል ሦስት ዋና ዋና እርከኖች ሥር ይካተታሉ።

⏺ሀ) ምሩቅ መሐንዲስ ወይም አርክቴክት (Graduate Engineer/Architect)

📏ምሩቅ ባለሙያ የሚባለው በምህንድስና ወይም ከምህንዴስና ጋር ተዛማጅነ ት ባላቸው የትምህርት መስክ ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ ወይም ተመሳሳይ የትምህርት ተቋም በመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ እና ከዜሮ እስከ ሶስት ዓመት የስራ ልምድ ያለው ምሩቅ የምህንድስና (ተያያዥ) ባለሙያ  የሚጠራበት፣ ሲቪል ምህንድስና፣ ቅየሳ ምህንድስና፣ ኮንስትራክሽን  ቴክኖሎጂ እና ማኔጅመንት፣ አርክቴክቸር፣ ከተማ ፕላን፣ ኤሌክትሪካል፣ ሳኒታሪ፣  ኤሌክትሮመካኒካል ኢንጂነሪንግ ባለሙያዎች  እናሌሎች በዘርፉ ያሉ መሐንዲሶች የሚሰየሙበት ምድብ ነው።

⏺ለ) ፕሮፌሽናል መሐንዲስ ወይም አርክቴክት (Professional Engineer/Architect)

📏በዚህ ዘርፍ የብቃት ማረጋገጫ የ ሚወስዱ ባለሙያዎች ከምህንድስና ጋር ተዛማጅነት ባላቸው የትምህርት መስክ ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ ወይም ተመሳሳይ የትምህርት ተቋም የመጀመሪያ ዱግሪ የትምህርት ማስረጃ እና ቢያንስ ከሶስት ዓመት በላይ የሆነ  የስራ ልምድ ሊኖራቸው የሚገባ ናቸው።

🗞ፕሮፌሽናል የምህንድስና (ተያያዥ) ባለሙያዎች የሚያካትተው በስትራክቸራል፣  ጂኦቴክኒካል፣  መንገድ እና ድልድይ፣ ኤሌክትሪካል፣  ሳኒታሪ፣  ኤሌክትሮ መካኒካል፣  ማቴሪያል ኢንጂነሪንግ ባለሙያዎችን  እና ሌሎች ወደፊት የሚፈጠሩ የኢንጂነሪንግ ዘርፎች   የተመረቁ ናቸው።

▶️በዚህ ምድብ የሚከተሉት ስያሜዎች ሊሰጡ ይችላሉ።

~ ፕሮፌሽናል አርክቴክት
~ ፕሮፌሽናል የከተማ ልማት ባለሙያ
~ ፕሮፌሽናል የመሬት ገጽታ ማስዋብ ባለሙያ
~ ፕሮፌሽናል የማቴሪያል ምህንድስና ባለሙያ
~ ፕሮፌሽናል የከርሰ ምድር ባለሙያ
~ ፕሮፌሽናል ጂኦቴክኒካል ባለሙያ
~ ፕሮፌሽናል የመንገድ ምህንድስና ባለሙያ
~ ፕሮፌሽናል ሎኬሽን መሐንዲስ
~ ፕሮፌሽናል የድልድይ ባለሙያ
~ ፕሮፌሽናል የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ባለሙያ
~ ፕሮፌሽናል ሳኒተሪ መሐንዲስ
~ ፕሮፌሽናል ስትራክቸራል መሐንዲስ
~ ፕሮፌሽናል ኤሌክትሪካል መሐንዲስ

⏺ሐ) ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል መሐንዲስ ወይም አርክቴክት

📌(Practicing Professional Engineer/Architect)
፦ አመልካቹ ከታወቀ በኮንስትራክሽን ዘርፍ በዲግሪና ከዚያ በላይ በሆነ  ደረጃ የተመረቀ መሆን ያለበት ሲሆን፤  የዲግሪ  ሰባት ዓመት፣  የማስተርስ አምስት ዓመት እንዲሁም የድክትሬት ሶስት ዓመት ላመለከተበት ዘርፍ አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ ሊኖረው የሚገባ ሲሆን ከተገለጸው የስራ ልምድ ዉስጥ ቢያንስ 2 ዓመቱ እንደአግባቡ በዲዛይን ወይም በዲዛይን  ክለሳ ወይም በኮንስትራክሽን  ግንባታ ወይም ማኔጅመንት ወይም ከሙያቸው ጋር ተያያዥነት ያላቸው ስራዎች ላይ የተሳተፈ መሆን  ይኖርበታል።

📐ባለሙያው ከላይ የተዘረዘሩትን  ስራዎች በቁጥር ሁለት (2) በራሱ እና እንደየአግባቡ በተቆጣጣሪነት የ ተሰሩ ለፕሮፌሽናል ብቃት ማረጋገጫ ካቀረቡት ተጨማሪ አንድ (1) ስራ ማቅረብ ይኖርበታል።

✨በዚህ ዘርፍ ስያሜ የሚሰጥባቸው ሰርቲፊኬቶች፦

~ ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል (PP) አርክቴክት
~ ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል (PP) የከተማ ልማት ባለሙያ
~ ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል (PP) የመሬት ገጽታ ማስዋብ ባለሙያ
~ ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል (PP) የማቴሪያል መሐንዲስ
~ ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል (PP) ጂኦቴክኒካል መሐንዲስ
~ ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል (PP) የመንገድ መሐንዲስ
~ ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል (PP) ሎኬሽን መሐንዲስ
~ ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል (PP) የድልድይ ባለሙያ
~ ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል (PP) የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት
~ ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል (PP) ሳኒተሪ መሐንዲስ
~ ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል (PP) ስትራክቸራል መሐንዲስ
~ ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል (PP) ኤሌክትሪካል መሐንዲስ
~ ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል (PP) መካኒካል መሐንዲስ
~ ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል (PP) ሰርቬየር
~ ፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል (PP) ፔቭመንት መሐንዲስ

☄የተሰራ ስራ ማስረጃ ማቅረብ የማይችል የፔራክቲሲንግ ፔሮፋሽናል የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ለማግኘት ያመለከተ ባለሙያ  እራሱ የሰራቸውን  ሌሎች ሁለት (2) የስራ ልምዶችን በተጨማሪነ ት ማቅረብ አለበት።

@etconp
👍25❤3🎉1
👉የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ያስገነባውን ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ነገ ያስመርቃል

🌟የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ያስገነባውን ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ በነገው እለት ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ያስመርቃል።

🚧የሚዲያ ኮምፕሌክሱ ዘመኑ የደረሰበትን የሚዲያ ቴክኖሎጂ ያሟላ ሲሆን ሦስት የቴሌቪዥንና አራት የሬዲዮ ዘመናዊ ስቱዲዮዎችም አሉት።

🖱በተጨማሪም ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ በርካታ ክፍሎች፣ የመሰብሰቢያ አዳራሾች ቤተ-መጽሀፍት፣ የመዝናኛ ማዕከልና ዘመናዊ ጂምናዝየም ያካተተ ነው።

@etconp
❤6👍6😁2😢1
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
👉የንድፍ ውድድር ለወጣት ህንጻ ነዳፊዎች

🗞ሙሉ ዝርዝሩን ከታች ከተያያዘው ማስፈንጠርያ ይመልከቱ።

🌟Kaira Looro 2024

🖱Architecture Competition

🖱Maternity Centre

⏺Kaira Looro Architecture Competition is a design contest open to students and young architects with aims to discover new talents and to adopt sustainable architecture models for humanitarian purpose to improve life conditions in developing countries.

▶️Cash prizes, Internship and construction are provided for winners, selected by an international jury made up of pregistous architectural firms.

⏺The challenge of 2024's edition is to design a ‘Maternity Centre’ in Southern of Senegal. We are looking for a ‘Maternity Centre’ facility where women can feel safe, receive essential medical care, and enjoy optimal sanitary conditions as well as the presence of qualified medical staff👇

https://www.kairalooro.com/competition_maternitycenter/en_index.html

@etconp
👍4🙏2❤1
📍አዲስ አበባ

🌟ከሸራተን በውጭ ጉዳይ ጀርባ ፍልውሃ የሚወስደው አዲሱ መንገድ

🚧ይህ መንገድ 450 ሜትር ርዝመት እና 40 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡

@etconp
👍13🕊1
👉የሕንጻ ምድብ አወሳሰን

🚧በ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሰረተ ልማት ቅንጅት እና ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የአሰራር መመሪያ 1/2011 ክፍል 1፣ አንቀጽ ሁለት ሥር ባስቀመጠው መሰረት ሕንጻዎች በሦስት ምድብ ማለትም "ምድብ ሀ" ፣ "ምድብ ለ" እና "ምድብ ሐ" ተብለው ሊወሰኑ ይችላሉ።

🚧ምድብ "ሀ" ሕንፃ

▶️በሁለት የኮንክሪት ወይም የብረት ወይም ሌሎች ስትራክቸራል ውቅሮች መካከል ያለው ርቀት ከ7 ሜትር ወይም ከዚያ በታች የሆነ ባለ አንድ ፎቅ ሕንፃ ወይም ማናቸውም ከሁለት ፎቅ በታች የሆነ የግል መኖሪያ ቤት ነው።  

🚧ምድብ "ለ" ሕንፃ

▶️የኮንክሪት ወይም የብረት ወይም ሌሎች ስትራክቸራል ውቅሮች መካከል ያለው ከ7ሜትር  በላይ የሆነ ወይም ባለሁለት ፎቅና ከሁለት ፎቅ በላይ የሆነና በምድብ "ሐ" የማይሸፈን ሕንፃ ወይም "ምድብ "ሀ" የተመደበ እንደሪል እስቴት ያሉ የቤቶች ልማት ነው።

🚧ምድብ "ሐ" ሕንፃ

▶️የሕዝብ መገልገያ ወይም ተቋም ነክ ሕንፃ ፣የፋብሪካ ወይም የወርክ ሾፕ ሕንፃ ወይም ከመሬት እስከ መጨረሻው ወለል ከፍታ ከ12 ሜትር በላይ የሆነ ማናቸውም ሕንፃ ሲሆን፣ በዚህ መመሪያ የተካተቱትን ማስተካከያዎች ያካትታል።

🖱ይህ የሕንጻዎች ምድብ አንድ የመሬት ባለቤት በቦታው ላይ ያለውን የግንባታ ሁኔታ (የሕንጻ አይነት፣ ከመንገድ ወደቦታው ሊገባ የሚችል የመንግሥት መሰረተ ልማትን እና የመሳሰሉትን ለማየት ስለሚጠቅም ዲዛይን የሚሰሩ አማካሪዎች ይህንን መረጃ የሚያሳይ ከተጻፈበት ቀን ጀምሮ ከሦስት ወይም ስድስት ወር በላይ ጊዜ ያላለፈው የፕላን ስምምነት ወረቀት ሊኖራቸው ይገባል።

@etconp
👍9
👉PICTURE OF THE DAY

🌟አድዋ ዜሮ ዜሮ በምሽት

🫵ውብ ምሽት ተመኘን❤️

@etconp
❤10👍3
Why is the opening in the bridge deck ? @etconp

Adwa 00 project at the verge of completion

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=OGQ5ZDc2ODk2ZA==

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp?mibextid=LQQJ4d

Telegram:- https://t.me/ETCONp
❤5👍3🏆1
👉በአዲስ አበባ የመሬት አገልግሎቶች ታገዱ

🚧የመሬት አገልግሎቶች መታገዳቸውን የተናገረው የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ እግዱ እንከ መቼ እንደሚቆይ በግልጽ አልተናገረም፡፡

🚧በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት ተከናውኖ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ጸድቆ ወደ ተግባር እንዲገባ የተወሰነውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ የሠራተኞች የባህሪ እና የቴክኒክ ፈተና ተሰጥቶ ውጤቱ ይፋ መደረጉን ቢሮው አስታውሷል።

▶️በዚህም አዲስ በተጠናው መዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት መሰረት የሰራተኞች ድልድል ተሰርቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከዛሬ ጥር 21፣2016 ዓ.ም ጀምሮ የመሬት አገልግሎቶች በጊዜያዊነት ታግዷል ተብሏል።

▶️ቢሮው ይህን እንዲያውቁትም ለሁሉም ክፍለ ከተሞች ደብዳቤ ጽፏል፡፡

⏺ሸገር ከዚህ በፊት በሰራው ዘገባ ፈታና የተቀመጡ የከተማዋ የመንግሰት ሰራተኞች ደልድላቸውን ባለማወቃቸው እንደ መሬት ነክ ባሉ አገልግሎቶች ሰራተኞች በስራ ገበታቸው ላይ እንዳልነበሩ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

@etconp
👍4❤1
👉ወደ ጅቡቲ የሚያስገባ ተጨማሪ መንገድ ተከፈተ

🚧የአሳይታ- አፋምቦ- ጅቡቲ ድንበር መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት መጠናቀቁ ተገለጸ

🌟ወደ ጅቡቲ ለመጓዝ አገልግሎት በመስጠት ላይ ከሚገኘው የጋላፊ መስመር በተጨማሪ ሌላ አማራጭ ሆኖ የሚያገለግለው የአሳይታ-አፋምቦ-ጅቡቲ ድንበር መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለትራንስፖርት አገልግሎት ክፍት መሆኑ ተገለጸ።

⏺መንገዱ በዋናነት ኢትዮጵያን በአሳይታ በኩል ከጅቡቲ ጋር በቅርበት ከማስተሳሰር ባለፈ የሀገራችንን የገቢ እና ወጪ ንግድ በማቀላጠፍ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንደሚኖረው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በማኅበራዊ ትስስር ፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ ጠቁሟል።

🖱የመንገዱን ግንባታ ለማከናወን የተመደበው 1,600,901,379 (አንድ ቢሊዮን ስድስት መቶ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር) ሙሉ ለሙሉ የተሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው።

🚧ግንባታውን ሲያካሂድ የቆየው  ሀገር በቀሉ የስራ ተቋራጭ አሰር ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲሆን ፣ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ይዲዲያ ኢንጅነሪንግ ኮንሰልታንትስ ሲያከናውን ቆይቷል።

▶️በተጨማሪም ይህ መስመር አሁን ላይ ያለውን ሚሌ - ዲቼ ኦቶ-ጋላፊ-ጅቡቲ ወደብ ያለውን መንገድ በ 30 ኪሎ ሜትር ያሳጥረዋል ያለው የአስተዳደሩ መረጃ ወደፊት በአካባቢው ሊመረቱ የሚችሉ የፋብሪካ ውጤቶችን (ስኳር ፣ የስንዴ ዱቄት) ወደ ውጪ ገበያ ለማቅረብ ፋይዳው የጎላ እንደሚሆን አመላክቷል።

🚧የመንገዱን ግንባታ ለማከናወን የተመደበው ከ1 ነጥብ ስድስት ቢለየን ብር በላይ የሆነው ወጪ ሙሉ ለሙሉ የተሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት መሆኑን የጠቆመው የመንገዶች አስተዳደር የመንገዱ ርዝማኔ 50.34 ኪሎ ሜትር መሆኑን አስታውቋል።

@etconp
👍8❤5
👉በከተሞች እየጨመረ የመጣውን ህዝብ ሊሸከም የሚችል የቤት አቅርቦት እንዲኖር በትኩረት እንዲሰራ ተጠየቀ

🌟በከተሞች እየጨመረ የመጣውን የህዝብ ብዛት ሊሸከም የሚችል የቤት አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ ማሳሰቢያ ተሰጠ።

⏺6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ሲያካሂድ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴርን የግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡
በስብሰባው የከተማ እና መሰረተ ልማት ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ÷ በከተሞች የአገልግሎት አሰጣጥ አለመዘመን፣ የአሰራር ግልጸኝነትና ተጠያቂነት አለመኖር በመደለያና ባልተገባ የጥቅም ትስስር አገልግሎት መስጠት፣ ህገወጥነትና ብልሹ አሰራር መስፋፋት በመኖሩ ተገልጋዩ ቅሬታ እያቀረበ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

▶️በመሆኑም የከተሞችን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን፣ ብልሹ አሰራርን ለማጥፋት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ሚኒስቴሩ ምን እየሰራ እንደሆነ በቋሚ ኮሚቴው ተጠይቋል።

👷‍♀የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት÷ በከተሞች አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን በመፍታት የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ የከተሞች ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎትን ውጤታማ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

🖱500 ሚሊየን ዶላር ለሁለተኛ ዙር የከተሞች ተቋማዊ እና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም፣ ለአዲሱ የተቀናጀ መሬት ማኔጅመንት ፕሮግራም 100 ሚሊየን ዶላር፣ ለገጠር ትስስር ተደራሽነት ፕሮግራም 300 ሚሊየን ዶላር በጥቅሉ ከ900 ሚሊየን ዶላር በላይ ለማግኘት ከዓለም ባንክ ጋር ስምምነት መፈጸሙን ጠቅሰዋል፡፡

🚧የኮንስትራክሽን ምህንድስና አቅም ግንባታን እውን ለማረግ የልማት ጥረቶችን በማቀናጀት ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል የኮንስትራክሽን ምህንድስናና ማኔጅመንት የልህቀት ማእከል ተቋም ለማቋቋም የዲዛይን፣ የአፈር ምርመራና የቅየሳ ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ ግንባታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

▶️የሕግ ማዕቀፎች አለመጽደቅ፣ የሲሚኒቶ አቅርቦት ውስንነት፣ ፕሮጀክቶች በጸጥታ ችግር ምክንያት ሙሉ በሙሉና በከፊል መቆማቸው እንዲሁም የስራ ተቋራጮችና አማካሪ ድርጅቶች የመፈጸም አቅም ማነስና የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Via FBC

@etconp
👍9❤1
👉PICTURE OF THE DAY

🌟ፒያሳ

🚧በእድሳት ላይ የሚገፕው አራዳ ህንጻ

🙏ውብ ምሽት ተመኘን❤️

@etconp
❤8👍4
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
❤2👍1
👉Reinforced concrete sections can be constructed with different percentages of steel reinforcements.

🚧The code specifications list three types of RCC sections as balanced, under-reinforced and over-reinforced based on the amount of reinforcement used.

🚧In balanced reinforced concrete sections, the tensile steel reaches the yield strain while the concrete reaches the failure strain in bending.

🚧In under-reinforced concrete sections, the steel reinforcement reaches the yield strain at stresses lower than the stress at which the concrete fails.

🚧An over-reinforced section in RCC structures is those in which the concrete reaches its collapse strain earlier than the steel reaches its yield strain.

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Telegram:- https://t.me/ETCONp

📩Contact us @ETCONpBot

♡ ㅤ   ❍ㅤ    ⎙ㅤ    ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ

╔═════
    🌐   join 👇
   @ETCONpWORK
   @COTMp
╚══ ☆☆☆☆☆══════
👍11❤4
❤10👍7😢1🕊1