👉የ SAP እና ETABS ንፅፅሮች
🚧SAP (Structural Analysis Program) and ETABS (Extended Three-dimensional Analysis of Building Systems)
🌟SAP:- (የመዋቅር ትንተና ፕሮግራም) እና ETABS:- (የተራዘመ የሶስት
አቅጣጫዊ የሕንፃ ሲስተሞች ትንተና) ሁለቱም በመዋቅር ምህንድስና
ለህንፃዎች ትንተና እና ዲዛይን የሚያገለግሉ ኃይለኛ የሶፍትዌር
ፕሮግራሞች ናቸው።
🖱ሆኖም በሁለቱ ፕሮግራሞች መካከል አንዳንድ ቁልፍ ልዩነቶች አሉ፡
✨1. የትንታኔ ወሰን፡ SAP አጠቃላይ ዓላማ ያለው መዋቅራዊ ትንተና ፕሮግራም ሲሆን ይህም ህንፃዎችን፣ ድልድዮችን እና ግድቦችን ጨምሮ ለተለያዩ መዋቅሮች ሊያገለግል ይችላል።
⏺በሌላ በኩል ኢቲቢኤስ በተለይ የግንባታ መዋቅሮችን ለመተንተን እና ዲዛይን ለማድረግ የተነደፈ ነው::
✨2. የሞዴሊንግ አቅም፡- ETABS ከ SAP ጋር ሲወዳደር የላቀ የሞዴሊንግ ችሎታዎች አሉት፣በተለይም ውስብስብ የሕንፃ ጂኦሜትሪዎችን ሞዴል ለማድረግ፣እንደ መደበኛ ያልሆኑ ቅርጾች እና ኦርቶጎን ያልሆኑ የፍሬም ስርዓቶች።
▶️ETABS እንደ ዛጎሎች፣ ሽፋኖች እና
ኬብሎች ያሉ የተለያዩ አይነት መዋቅራዊ አካላትን ለመቅረጽ የላቀ አማራጮችን ይሰጣል።
✨3. የትንታኔ ዘዴዎች፡- ሁለቱም SAP እና ETABS ተመሳሳይ የትንታኔ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ መዋቅራዊ ትንተና,እንደ ውስን ንጥረ ነገር ዘዴ (FEM) እና የማትሪክስ ግትርነት ዘዴ ሆኖም፣ ETABS የበለጠ የላቀ የትንታኔ አማራጮችን ያካትታል፣ ለምሳሌ ለሴይስሚክ ዲዛይን የግፊት አዙር ትንተና እና ተለዋዋጭ ጭነቶች አወቃቀሮችን ምላሽ ለመገምገም።
✨4. ከሌሎች ሶፍትዌሮች ጋር ውህደት፡- ሁለቱም SAP እና ETABS ከሌሎች የሶፍትዌር ፕሮግራሞች እንደ Revit እና AutoCAD ጋር ሊዋሃዱ ይችላሉ ያልተቆራረጠ የስራ ፍሰት እና በተለያዩ የሶፍትዌር መድረኮች መካከል የመረጃ ልውውጥ።
⏺ሆኖም፣ ETABS ከ SAP ጋር ሲወዳደር በተሻለ የመዋሃድ አቅሙ
ይታወቃል፣በተለይ ከግንባታ መረጃ ሞዴሊንግ (BIM) ሶፍትዌር ጋር አብሮ
መስራትን በይበልጥ ይመከራል።
✨5. የተጠቃሚ በይነገጽ፡ SAP በቀላሉ ለማሰስ እና ለመጠቀም ምቹ የሆነ በይነገጽ ስላለው ለጀማሪዎች እና ልምድ ላላቸው ተጠቃሚዎች ምቹ ያደርገዋል።
▶️ETABS ለተጠቃሚ ምቹ የሆነ በይነገጽ አለው፣ ነገር ግን በላቁ የሞዴሊንግ ብቃቶች እና የትንታኔ አማራጮች ምክንያት ለአዳዲስ ተጠቃሚዎች ሾጣጣ የመማሪያ መንገድ ሊኖረው ይችላል።
☄በማጠቃለያው SAP አጠቃላይ ዓላማ ያለው መዋቅራዊ ትንተና ፕሮግራም ሲሆን ለተለያዩ መዋቅሮች ተስማሚ ነው፣ ETABS ደግሞ በተለይ የላቀ የሞዴሊንግ አቅም እና የመተንተን አማራጮችን ለግንባታ አወቃቀሮች ለመተንተን እና ለመንደፍ የተነደፈ ነው።
📍በ SAP እና ETABS መካከል ያለው ምርጫ የሚወሰነው በተወሰኑ የፕሮጀክት መስፈርቶች እና በተጠቃሚው የመዋቅር ትንተና ሶፍትዌር የልምድ ደረጃ ላይ ነው።
Via FILA
@etconp

👍17❤3🙏1
🌟ውድ ቤተሰቦቻችን የ Ms Project ቲቶርያል ለ ጀማሪዎች የሚሆን እየሰራን ቆይተናል ዛሬ የመጨረሻዎቹ ክፍል 8 እና 9 በ YouTube ገፃችን ለቀነዋል
🖱ለ ቀጣይ ተለቅ ያለ ፕሮጀክት ለ Advanced የሚሆን በ ኣዲሱ ሶፍትዌር እንደምንሰራ ቃል እንገባለን❤️
👉Amharic Ms Project Tuetorial last Part 8 & 9 is Uploaded
🫵ለ YOUTUBE ቻናላችን አዲስ ከሆኑ SUBSCRIBE በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ እንዲሁም ለወዳጅዎ ያጋሩ🙏👇
https://www.youtube.com/@ETHIOCONp
https://youtu.be/7HDnLiP00kA?si=1pCNTQ6VYyu0wX5L

👍10🙏4
👉ተቋማቱ የግንባታ ግብአቶችን ጥራት ማስጠበቅ የሚያስችል የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ
🚧የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የግንባታ ጥራትና ደህንነትን ለማስጠበቅ የሚስያስችል የጋራ ስምምነት የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ተፈራርመዋል።
🌟የጋራ መግባቢያ ስምምነቱ በዋናነት የግንባታ ፕሮጀክቶች ከዲዛይን እስከ ግንባታ ማጠናቀቅ ባሉት ሂደቶች የሚካሄደው የቁጥጥር ስራ ውጤታማ እንዲሆን የሚያችል የጥራት ፍተሻና ማረጋገጫ ስራዎችን በተቀናጀ መልኩ ማከናወን የሚያስችል መሆኑ ተመልክቷል፡፡
🖱የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ ተቋሙ የግንባታ ፕሮጀክቶች በጥራት፣ በተመጣጣኝ ዋጋ፣ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲሁም የአካባቢና ሰብአዊ ደህንነትና ጤንነትን በጠበቀ መልኩ መገንባታቸውን እንደሚቆጣጠር አውስተዋል።
🖱በዚህ ሂደት ውስጥ የግንባታ ግብዓቶችን ጥራትና ደረጃ ከማረጋገጥ አንፃር ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ጋር በጋራ ተቀናጅቶ መስራት ውጤታማ እንደሚያደርግም ገልፀዋል፡፡
⏺ውጤታማነቱ አስተማማኝ እንዲሆንም ሁለቱም ተቋማት ዓመታዊ ዕቅዳቸው እና በትግበራ ሂደታቸው ላይ በተናበበ መልኩ የግብረ መልስ እንዲሁም የመረጃ ልውውጥ ስርዓትን መዘርጋት ይገባቸዋል ብለዋል ይህም ውጤታማ ለሆነ የውሳኔ አሰጣጥ መሰረት ነው ሲሉም ገልፀዋል፡፡
⏺የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛ አበራ በበኩላቸው እንደ ሀገር የምርቶችን ጥራት የማስጠበቅ ጉዳይ የዘመነ፣ የተናበበ እና ግልፅ አሰራር ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡
▶️ህብረተሰቡን ከጉዳት ለመጠበቅ፣ የምርት ብክነትንና የአካባቢ ብክለትን ለመታደግ ጥራትን እና ደህንነትን ማስጠበቅ አማራጭ ጉዳይ አይደለም ሲሉም አስምረውበታል።
▶️ከግንባታ አንፃርም የግብአቶች የጥራት ደረጃ መፈተሹና መረጋገጡ ለትውልድ የሚተላለፉ ግንባታዎችን እውን ማድረግ እንደሚያስችል የገለፁት ወ/ሮ መኣዛ አበራ ለዚህም የጋራ ስምምነቱ የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋት ረገድ አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልፀዋል፡፡
🖱በመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ስነስርአቱ ላይ የሁለቱም ተቋማት ም/ዋና ዳይሬክተሮች እና የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
🚧የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የምርቶችን ጥራትና ደረጃ በላቦራቶሪ ፍተሻ የማረጋገጥ፣ እንዲሁም የኢንስፔክሽንና የሰርቲፊኬሽን አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ፣ ለዚህም በኢትዮጵያ 8 ቅርንጫፎች እንዲሁም በጅቡቲ ወደብ አንድ ቅርንጫፍ እንዳለው ታውቋል፡፡
Via ኢኮባ

👍8
👉የ 2024 ፕሪትዝከር ሽልማት አሸናፊ
🌟ሪከን ያማሞቶ፣ ዮኮሀማ ጃፓን
🚧ባለ 78 ዓመቱ ጀፓናዊ ህንጻ ነዳፊ ሪከን ያማሞቶ (Riken Yamamoto) በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነውን አለምዓቀፋዊ የኪነህንጻ የ2024 Pritzker አርክቴክቸር ሽልማት ተሸላሚ ሆኖ ተመርጧል።
⏺"በሕዝብ እና በግል ቦታዎች መካከል ያለውን ዝምድና" በመመሥረት እና "ኪነ ሕንፃን ለዕለት ተዕለት ሕይወት እንደ ጀርባና ፊት ለፊት" በመፍጠር የሚታወቀው ያማሞቶ ይህንን እውቅና ለማግኘት ይህንን የፕሪትዝከር አርክቴክቸር ሽልማት 53ኛ ተሸላሚ ነው። ከጃፓን ደግሞ 9ኛው ይህንን ሽልማት ያገኘ ነዳፊ ነው።
🖱በሆታኩቦ መኖሪያ ቤት (1991) እና በዮኮሱካ የስነጥበብ ሙዚየም (2006) ( Hotakubo Housing and Yokosuka Museum of Art) የሚታወቀው ያማሞቶ "እራሱን አስረጂ ነገር ግን ልከኛ እና አውዳዊነት ያለው ኪነህንጻ ፣ መዋቅራዊ ታማኝነት እና ትክክለኛ ልኬት፣ ለአካባቢው ገጸ ምድር ንድፍ በጥንቃቄ ትኩረት በመስጠት" ተመርጧል።
⏺የፕሪትዝከር ዳኞች የ2016 የፕሪትዝከር ሽልማት ተሸላሚ አሌሃንድሮ አራቬና እና አለምአቀፍ ህንጻ ነዳፊ ፣ አስተማሪ እና የዬል የኪነ-ህንፃ ትምህርት ቤት ዲን ዲቦራ በርክን ያካተተ ነበር።
Via ArchDaily

👍4👌2
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ
፦የአገልግሎታችንን አድማስ በማስፋት የክቡራን ደንበኞቻችንን ፍላጎት ለማርካት በታማኝነት እንተጋለን
፦ፕሌት 1mm-30mm any size
፦jbolt 12mm-32mm
፦ankerbolt
፦stafa
፦any modefic wor
፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን
telegram:https://t.me/heavenic1
ቁ.1 መርካቶ ኮርቻ ተራ
ቁ.2 ተክለሐይማኖት ወረድ ብሎ
ቁ.3 አየር ጤና ኪዳነምህረት
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ
0904040477
0911016833
0994941706

👍5🏆1
In the levelling, value of B.S., F.S. & I.S. readings continuously decreasing with respect to one line of sight and then these readings starts increasing with respect to other line of sight of telescope which shows contour lines representing a _____
Anonymous Quiz
30%
Hill
29%
Pond/valley
21%
Uniform Flat or slope terrain
20%
Maybe Hill or valley
👍4
For through mixing up coagulant with the water violent agitation is done in
Anonymous Quiz
29%
a) sedimentation tank
40%
b) flocculator
26%
c) flash mixer
5%
d) pressure filter
❤2👍1
Web crippling is due to
Anonymous Quiz
29%
Bearings stress
34%
Diagonal compression
30%
Bending compression
7%
None of above
🙏7👍2
ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች 5 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሊገነባ ነው ተባለ
በ450 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ለሚገነባው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሰራተኞች ሁለተኛ ምዕራፍ የ5 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ዛሬ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።
የግንባታ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ የመሰረት ድንጋዩን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስቀምጠዋል።
በግንባታ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ የሰንሻይን ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አስፈጻሚ ሳሙኤል ታፈሰ፣ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታረቀኝ ገመቹና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
በ17 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የቤቶቹ ግንባታ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሲኤምሲ ልዩ ሥሙ ሃያት-49 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ እንደሚከናወን ተገልጿል።
ግንባታው በሰንሻይን ኮንስትራክሽንና በቻይናው ኮንስትራክሽን ኮሙኒኬሽን ኩባንያ (ሲሲሲሲ) የሚከናወን ሲሆን በአራት ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።
በፕሮጀክቱ ከ5 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎችን የሚይዝ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራ፣ የልጆች መጫወቻ፣ አረንጓዴ ሥፍራ፣ ትምህርት ቤት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራና የገበያ ማዕከላት እንደሚይዝ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም ቤቶቹ የራሱ ጥልቅ ጉድጓድ ውኃና የፀሐይ ኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንደሚኖረውም ተመላክቷል።

👍13❤3🙏2
👉በሳዑዲ ዓረቢያ የዓለማችን የመጀመሪያው ባለ ሦስት አውታር (3ዲ) ቴክኖሎጂ የተሠራ መስጂድ ተመርቋል።
🚧5 ሺህ 600 ካሬ ሜትር ስፋት ያለውን መስጂድ ግንባታ በግንባር ቀደምትነት የመሩት የፉርሳን ሪል እስቴት ባለቤት የሆኑት አብዱልዋህድ ሲሆኑ፣ ባለ ሦስት አውታር (3ዲ) ቴክኖሎጂ ታዋቂ ከሆነው ጓንሊ ከተባለ የቻይና ኩባንያ ጋር በመሆን እንደተሠራም ተገልጿል፡፡
⏺አብዱልዋህድ ከዓረብ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የመዝጂዱን የውስጥና የውጪ ውበት በጣም ልዩ መሆኑን ተናግረዋል።
⏺"የመስጂዱ ዲዛይን ጽንሰ ሀሳብ በዕምነቱ ተከታዮች ዘንድ የመረጋጋት፣ የመሰብሰብ እና የመልካምነት ስሜት እንዲፈጥር ለማድረግ ታስቦ የተሠራ ነው" ብለዋል።
⏺"የመስጂዱ ዲዛይን በቀላሉ ወደ ‘ቂብላ’ ሊያመራ የሚችል ክበብ በመፍጠር ላይ ያተኮረ ነው፤ የህንጻው ክብደት እና ከተፈጥሮ ብርሃን ጋር ያለው ግንኙነት፣ የመግቢያ በሮቹ ዲዛይን እንዲሁም የህንፃውን ምንነት ለማንጸባረቅ ውጫዊ ገጽታዎቹ ላይም ትኩረት ተደርጎ ተሠርቷል" ብለዋል።
▶️እነዚህ ሁሉ ዝርዝር ጉዳዮች በአብዱልአዚዝ አብዱል ሻርባትሊ መስጂድ ውስጥ መካተታቸው መስጂዱ ልዩ ምስል ያለው መዋቅር እንዲኖረው እና በዓለም ላይ የመጀመሪያው እንዲሆን እንዳደረገው ተገልጿል።
🖱አል ጃዋራ በተባለው የጅዳ ከተማ ዳርቻ የተሠራው መስጂድ በሟቹ አብዱልአዚዝ አብዱላህ ሻርባትሊ ስም ተሰይሟል፡፡
☄ስያሜው የተሰጠው የአብዱልአዚዝ አብዱላህ ሻርባትሊ ባለቤት በሆኑት የሰዑዲ ታዋቂ ነጋዴ ዋጅናት አብዱልዋህድ በተሰጠ ገንዘብ የተሠራ በመሆኑ ነው።
✨ይህ በአዲስ ቴክኖሎጂ የተሠራው መስጊድ የተመረቀው ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የንግድ ድርጅቶች መሪዎች በተገኙበት መሆኑን የዘገበው ዓረብ ኒውስ ነው።

👍6
🫵የ @ETCONp Crew ኢንጅነር ጆርዳኖ ባለፈው እሁድ በ ኤቫ ሸው FM 97.1 ቀርቦ ነበር
🚧ከተዳሰሱ መልእክቶች መካከል
🌟በውጭ ሀገር ኮንትራክተሮች በርካታ ስራዎች በመያዛቸው የሀገራችን ኮንትራክተሮች ስራ አጥ ሆነዋል፣ ከሀገር እየሸሹ መሆኑ እየተሰማ ነው
☄ለዚህ መፍትሔ ምን ይደረግ በሚለው ጉዳይ ኢኒጂነር Danat እና ጆርዳኖ የተወያዩበትን ፕሮግራም ከዩቲዩብ ቻነሉ ያድምጡ።
https://youtu.be/40hFJ30Tk20?si=GTs4PVsQS9J6VXio

🙏4❤1👍1