Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉በ25 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የተባለ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ታይዋንን መምታቱ ተሰማ

⚡️በዛሬው እለት በታይዋን ምሥራቃዊ የባህር ዳርቻ ላይ በሬክተር ስኬል 7.4 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የተከሰተ ሲሆን በ25 ዓመታት ውስጥ በደሴቲቱ ላይ ከደረሰው አደጋ ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ መሆኑ ተሰምቷል።

🚧የመሬት መንቀጥቀጡ የነፍስ አድን ጥረቶችን አዳጋች ያደረገው ሲሆን በርካታ ሕንፃዎች እንዲናጉ አድርጓል።

🌟የመሬት መንቀጥቀጡ በከፍተኛ የመሬት መንሸራተት የታይዋን ተራራማ ውስጠኛ ክፍል ድረስም ተሰምቷል።

🖱ቢያንስ ሁለት ህንጻዎች በሁአሊየን ከተማ በከፊል ፈርሰዋል።

🖱ህንፃዎች በአደገኛ ሁኔታ ማዕዘኖች ተደግፈው የሚታዩ ሲሆን የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ከሁአሊየን በስተደቡብ 18 ኪሜ ርቀት ላይ ነው።

🚧በደቡባዊ ኦኪናዋ ላሉ የጃፓን ደሴቶች የሱናሚ ማስጠንቀቂያ ታውጇል፣ በተመሳሳይ በታይዋን አቅራቢያ የምትገኘው ፊሊፒንስ በሰሜናዊ የባህር ዳርቻዋ ላይ የሱናሚ ማስጠንቀቂያ አውጇለች።

🌟የታይዋን ማዕከላዊ የዜና ወኪል በዘገባው እንዳስታወሰው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1999 7.6 በሬክተር ስኬል የተለካ  የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ አጋጥሞ 2,400 ሰዎችን ሲገድል ፣ 50,000 ህንጻዎችን ካወደመው አደጋ በኋላ በደሴቲቱ ላይ የተከሰተ ትልቁ አደጋ የዛሬው ነው ብሏል።

@etconp
👍8😢3
ETCONp የግንባታ ፈቃድ ማመልከቻዎች.pdf
2 MB
👉የግንባታ ፈቃድ ለማውጣት የሚጠቅሙ ማመልከቻዎች የያዘ PDF ፋይል

📽ለ YOUTUBE ቻናላችን አዲስ ከሆኑ SUBSCRIBE በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ እንዲሁም ለወዳጅዎ ያጋሩ👇

https://www.youtube.com/@ETHIOCONp

@etconp
🙏8❤2👍2
_ETCONp_የኮንስትራክሽን_ሥራዎች_ውል_አዘገጃጀት.pdf
271.8 KB
👉የኮንስትራክሽን ሥራዎች ውል አዘገጃጀት፣ ለሕግ ባለሞያዎችና ለምሕንድስና ባለሞያዎች በአማርኛ የቀረበ

📽ለ YOUTUBE ቻናላችን አዲስ ከሆኑ SUBSCRIBE በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ እንዲሁም ለወዳጅዎ ያጋሩ👇

https://www.youtube.com/@ETHIOCONp

@etconp
👍11❤1
_ETCONp_የኮንስትራክሽን_አማካሪዎች_የአሰራር_መመሪያ.pdf
10.1 MB
👉የኮንስትራክሽን አማካሪዎች የአሰራር መመሪያ

📽ለ YOUTUBE ቻናላችን አዲስ ከሆኑ SUBSCRIBE በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ እንዲሁም ለወዳጅዎ ያጋሩ👇

https://www.youtube.com/@ETHIOCONp

@etconp
👍15❤1
#NewsAlert

👉በአዲስ አበባ ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባቸው ውሳኔ ተላለፈ።

🌟የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 3ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ በ3 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

🚧ከውሳኔዎቹ አንዱ ግንባታዎችን የሚመለከት ነው።

⏺በዚህም የከተማዋን ስታንዳርድ እና መዋቅራዊ ፕላን ለማስጠበቅ እንዲሁም መልሶ ማፍረስ እንዳይገጥም ፤ ግንባታዎች ከመንገድ ያላቸው ርቀት ከዚህ በኋላ ወጥነት ያለው የከተማ አሰራር አንዲኖር በማሰብ ከመንገድ መራቅ ያለባቸውን 3 ደረጃዎች ወጥተዋል።

🖱ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ፦

➡ ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባው ፤
➡ ከንዑስ ዋና መንገድ 5 ሜትር ርቀት፤
➡ ሰብሳቢ መንገድ ደግሞ 3 ሜትር ርቀት
➡ በተጨማሪ የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2 ሜትር ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸው ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

@etconp
👍22❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
35- story building, standing at a height of 160 meters, designed with a dual load-bearing system comprising reinforced concrete shear walls and special moment-resisting frames.

@etconp

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://www.youtube.com/@ETHIOCONp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

X formerly (Twitter):- https://x.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
👍10❤3👏1
ታምራት ፕሌት & jbolt አቅራቢ

፦ፕሌት 1mm-30mm any size ቆርጠን በስተን ጣጣዉን ጨርሰን እናስረክቦታለን

፦jbolt 12mm-32mm በፈለጉት ቁመት ጥርስ አዉጥተን አጥፈን እንሰጦታለን

፦ankerbolt

፦stafa(ስታፋ ባለ 6 እና ባለ 8)በየትኛዉም size የተዘጋጀ አለን

፦ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

፦ማንኛዉንም አይነት ብረታ ብረት እንገዛለን

አድራሻችን
ቁ.1  አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
ቁ.2 ተክለሐይማኖት
ቁ.3 መርካቶ
ቁ.4 በቅርቡ ቄራ ላይ

0904040477
0911016833
0994941706

ይደዉሉልን ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም ቢሆኑ ካሉበት እንልክልዎታለን።
👍2👏1
👉በዓለም በቁመቱ ትልቁ እስር ቤት ሊገነባ ነው ተባለ።

🚧ከዓለም በቁመቱ አንደኛ የሆነው ይህ እስርቤት የሚገነባው በአሜሪካ ኒው ዮርክ ግዛት ውስጥ ነው።

🚧በኒው ዮርክ ከተማ የምትገኘው ቻይናታውን በርካታ የዳቦ አይነት ባላቸው ሱቆች፣ በጠባብ መንገዶቿ እና በጠንካራ ማህበራዊ መስተጋብሯ ነበር በልዩ ሁኔታ የምትታወቀው።

🚧ነገር ግን በሶሆ እና ትሪቤካ መካከል ያለችው ይህች የማንሀተን መሀል ከተማ መንደር በሌላ ነገር ታዋቂ ሆናለች ተሰርቶ ሲጠናቀቅ በዓለም በቁመት ትልቁ እስር ቤት መገኛ ትሆናለች።

🚧በአካባቢው ነዋሪዎች "ጄልስክራፐር" ወይም የእስረኞች ማማ ብለው የሚጠሩት ይህ 300 ጫማ ቁመት እና 1040 ክፍል ያለው ባለ40 ፎቅ ህንጻ የኢምፓየር ስቴት ህንጻን 1/3ኛ ይሆናል ተብሏል።

🚧ይህ እስር ቤት አምስት ብሎኮች ላይ ጥላ የሚያጠላ እና በክረምት ወቅት አካባቢውን ወደ ጨለማ ሊቀይር የሚችል ነው።

🚧በኃይት ስትሪት የሚኖሩት ሰዎች በጓሯቸው ባለው የማንሀተን ነባር እስርቤት ወይም ቶምብ ጉዳይ ለረጅም ጊዜ ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

🚧ነገር ግን ሰማይ ጠቀሱን እስር ቤት ለመስራት ቶምቡ ሲፈርስ አካባቢው በአቧራ መሞላቱ ነዋሪዎችን ቅር አሰኝቷል።

🚧የአዲሱ ህንጻው ግንባታው ገና ያልተጀመረ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች በሂደት ለሚያጋጥማቸው ችግር ዝግጁ መሆናቸውን ለኒው ዮርክ ታይምስ ተናግረዋል።

🚧በ2019 የካውንስል ባለስልጣናት በማንሀተን ፣ በኩይንስ፣ በብሩክሊን እና ብሮክስ አዳዲስ እስርቤቶችን ለመገንባት 8.3 ቢሊዮን ዶላር መመደባቸውን አስታውቀው ነበር።

🚧ቶምቡ በ2025 እንደሚፈርስ እና ሰማይ ጠቀስ በሆነ እስርቤት እንደሚተካ የፕሮጀክቱ ኮንትራክተሮች ተናግረዋል።

🚧በርካቶች ፕሮጀክቱ ለአመታት ሲቃወሙ ከቆዩ በኋላ በ2020 ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ከሰው ግንባታው በጊዜያዊነት እንዲቆም ማድረግ ችለው ነበር።

🚧በቻይናታውን ከ57ሺ በላይ ነዋሪዎች ያሉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 34,295 የሚሆኑት የእስያ ዝርያ ያላቸው መሆናቸውን በ2022 የወጣው ሪፖርት ያመለክታል።

🚧ፕሮጀክቱን የሚቃወመው 'ዌልካም ቱ ቻይናታውን' የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርድት የቶምቡ ወይም የብሎኩ መፍረስ እና አዲስ ሰማይ ጠቀስ ህንጻ የማቆም ተግባር በአካባቢው ላይ ከፍተኛ አደጋ ያስከትላል ብሏል።

🚧ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ለማስቆም 12ሺ ሰዎች አቤቱታ አቅርበዋል።

Via Alain

@etconp
👍20❤2
EARTHBAG TECHNOLOGY

The use of this eco-friendly building method is on the rise in many parts of the world especially Africa as it is a sustainable and low cost alternative. Not only is it cheap but Earthbags are proven to be more resistant to earthquakes and faster to set up.


@etconp

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://www.youtube.com/@ETHIOCONp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

X formerly (Twitter):- https://x.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
👍11❤2
What’s this rebar used for ???

Comment down below ⬇️

@etconp

Telegram:- https://t.me/ETCONpWORK

YouTube:- https://www.youtube.com/@ETHIOCONp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

X formerly (Twitter):- https://x.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
👍9❤1
👉ስለ ተጫራቾች እና ሀገራት ብቁነት (Eligible Bidders & Countries)

🚧ሀ) ስለተጫራቾች ብቁነት (Eligible Bidders)

⏺ጨረታ የሚወዳደሩ አካላት የሚባሉት ጨረታ የወጣበትን ሥራ ማከናወን የሚችሉ ግለሰቦች ወይም ሕጋዊ ሰውነት የተሰጣቸው የግል ወይም የመንግሥት ተቋማትን ሲሆን የመንግሥት ተቋማት ከሆኑ ከንግድ ሕግ ጋር የማይጣረሱ እና ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው ከሆኑ ብቻ ነው። በመሆኑም ሁሉም ተጫራቾች

✅የታደሰ የቢዝነስ (ንግድ ፍቃድ) ያላቸው መሆን
✅የመንግሥት ክፍያዎችን መክፈል የሚያችል መዝገብ ያላቸው (e.g., VAT)
✅የየዓመት የግብር ክፍያ ማረጋገጫ ያስመሰከሩ
✅ተገቢውን የባለሙያ ቁጥርና ሙያዊ ደረጃ ፍላጎት ማሟላት የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

🚧ለ) ስለተጫራች ሀገራት ብቁነት (Eligible Countries)

⏺በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ሀገራት ማለት "እያንዳንዱ ተጫራች ግለሰብ ወይም ድርጅት የተነሳበት እናት ሀገር" ማለት ነው።

🔰ለምሳሌ፦ የቻይና ሀገር ተቋራጮች፣ የጀርመን ሀገር ተቋራጮች፣ ወይም የንግድ ፍቃዳቸው እና የሥራ ጅማሬያቸው ከሌላ ሀገር የተነሱ ዓለምአቀፍ ተቋራጮች ማለት ነው::

✳️በመሆኑም፦ ለጨረታው ብቁ የሆኑ ሀገራት ሲባል ጨረታው ከወጣበት ሀገር ጋር ወይም ከዓለም ሀገራት ጋር ጤናማ ግንኙነት ያላቸው ሀገራትን የሚያጠቃልል ሲሆን በእኛ ሀገር ሕግ መሰረት በሀገሪቷ ጨረታ ላይ የማይሳተፉ ሀገራት

❇️በኢትዮጵያ ፓርላማ በጠላትነት ያልተፈረጀች ሀገር ወይም በኢትዮጵያ ህግ መሰረት በሀገሪቱ የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ላይ ግንኙነት እንዳይኖራት ከተከለከለች ሀገር የተነሱ/የመጡ ተቋራጮች

❇️በተባበሩት ሀገራት የጸጥታው ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ጋር ምንም አይነት የንግድ ግንኙነት እንዳይኖራት የታገደች ሀገር ዜጋ የሆኑ ግለሰቦች ወይም የንግድ መነሻቸው ከዚያ የሆኑ ድርጅቶች መሳተፍ አይችሉም።

@etconp
❤7👍6🙏1
✋ሰላም ውድ የ ሀገራችን ኮንትራክተሮች እና ኮንሰልታንት ባለቤቶች

🚧በኮንስትራክሽን ዘርፉ ኣዳዲስ የወጡ እና የሚወጡ ጨረታዎች እና የ ስራ ቅጥሮች ካላቹ በ @ETCONpBOT በኩል ላኩልን በነፃ እናጋራለን!

https://t.me/ETCONpWORK
🙏7❤2
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
👍3❤1🙏1
👉ኮንስትራክሽን "Construction” ስለሚለው ቃል የኢትዮጵያ ሕጎች ይስማማሉ ወይ?

🌟የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል “ለመኖሪያም ሆነ ለሌላ አገልግሎት እንዲሆን ከድንጋይ ከሸክላ ከብረትና ከመሳሰሉት ነገሮች የሚሰራ ፎቅ ያለው ወይም የሌለው ቤት” ሕንጣ ይባላል እንጂ ኮንስትራክሽን የሚል ስያሜ አልሰጠውም (የኢ.ቋ.ጥናትና ምርምር, 1993)።

⏺በተጓዳኝ ደግሞ BATCODA Specification በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 327/1979 አንቀጽ 2(1) ኮንስትራክሽን የሚለውን ቃል ለሁለት ክፍል ሰጥቶ የሕንጻ ኮንስትራክሽን እና የመንገድ ኮንስትራክሽን በማለት ይከፍለዋል።

▶️የሕንጻ ኮንስትራክሽን የሚለውን ሀረግ “ማንኛውም በከፊል ወይም በሙሉ የወለል የግድግዳና የጣሪያ ሥራ ያለው ለመኖሪያ ወይም ለሌላ አገልግሎት የሚውል ሕንጻና ተዛማጅ ሥራዎችን የመስራት ወይም የማሻሻል ሥራ ው” የሚል ብያኔ የሰጠ ሲሆን በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 327/1979 አንቀጽ 2(2) ሥር የትራንስፖርት ኮንስትራክሽን በሚል ዘርፍ “የሐረግ መንገዶች፣ ድልድዮች፣ የባቡር ሀዲዶች፣ የአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ የወደቦችና የየብስ ማመላለሻ ተርሚናሎች የመሥራት ወይም የማሻሻል ሥራ” እንደሆነ ተርጉሟል።

⏺የኢ.ፌ.ድ.ሪ መንግሥት የግንባታ ግዢና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 430/1997 አንቀጽ 2(ሐ) እና አዋጁን በሻረው አዋጅ ቁጥር 649/2001 አንቀጽ 2(3) “የግንባታ ዘርፍ” ለሚለው ትርጉም “የግንባታ ዘርፍ ሥራ ማለት ከሕንጻ፣ ከመንገድ ወይ ከመሰረተ ልማት ሥራ ጋር በተያያዘ የሚከናወን አዲስ ግንባታ፣ የመልሶ ግንባታ፣ ደረጃ የማሳደግ፣ የማፍረስ፣ የጥገና፣ የማደስ ሥራ እንዲሁም ተጓዳኝ የሆነና ከዋናው ሥራ ያልበለጠ ዋጋ ያለው አገልግሎት ሲሆን፣ የመገንባት፣ በባለቤትነት የመያዝ፣ ሥራውን የማንቀሳቀስ፣ የማስተላለፍ ወይም የመገንባት፣ የማንቀሳቀስ የማስተላለፍ ወይም የመገንባት፣ በባለቤትነት የመያዝ የማንቀሳቀስ ውል” በማለት ኮንስትራክሽን የሚለውን ቃል ምን ያክል ሰፊ እንደሆነ በሚያስገነዝብ መልኩ አስቀምጦታል።

▶️በ2006 ዓ.ም በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ ደግሞ  “ኮንስትራክሽን ማለት የመሬት ውስጥ ወይም ከመሬት በላይ ያለ ንብረትና አገልግሎትን የሚፈልግ የማሳደግ፣የማስፋፋት፣ የመዘርጋት፣ የመልሶ ግንባታ፣ የጥገና፣ የዕድሳት፣ የማበልጸግ፣ የመቀየር፣ የቁፋሮ፣ የመንቀል ወይም የማፍረስ የሕንጻ ወይም የማንኛውም ምህንድስና ሥራ ነው - Construction” means a provisions of combination of goods and services carried out under or  over ground for the development, extension, installation, repair, maintenance, renewal, renovation,  alteration, excavation, dismantling or demolition of a fixed asset including building and  engineering infrastructure.” ይላል።

🚧በ2001 ዓ.ም የወጣው የሕንጻ አዋጅ ቁጥር 324/2001 አንቀጽ 2(9) ደግሞ ግንባታ ማለት አዲስ ሕንጻ መገንባት ወይም ነባር ሕንጻ ማሻሻል ወይም አገልግሎቱን መለወጥ ነው - Construction" means the construction of a new building or the modification of an existing building or alteration of its use” በማለት አስቀምጧል።

#ConstructionLaw

https://t.me/ETCONpWORK
👍18