Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

🔰ምን ይፈልጋሉ?

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍2❤1
INTERCON Construction Materials
    
👉 Authorized agent of MC (Conmix) and Weber 

● Concrete Admixtures
● Concrete Repair Mortar
● Bonding Agent     
● Self-level, Floor hardener, Epoxy
● Grout       
● Quartz Paint
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Waterproofing chemicals and Materials (Cementitious, Crystalline, Acrylic, Sealants, Membrane)
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
❤1👍1
👉ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እድሳትና ታሪክ

የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን እድሳት በገንዘብ እጥረት ሳቢያ እየተጓተተ ሲሆን ለማጠናቀቅ 85 ሚልየን ብር ያስፈልጋል ተብሏል።

በኢትዮጵያ የፓትሪያርክ ሹመት የሚፈጸምበቱ ብቸኛ ስፍራ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ነው።

የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደር ሰበካ ጉባዔ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የህንፃ እድሳቱ እስካሁን 75 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን 90 ሚሊዮን ብር ገደማ እንደፈጀ ተጠቁሟል።

የቤተ ክርስቲያኗ የእድሳት ሂደት ለ16 ወራት ያህል ጥናት ሲደረግበት ቆይቶ "በቅርስ እድሳት ልምድ ካለው" ቫርኔሮ ከተባለ ድርጅት ጋር በ172 ሚሊዮን ብር የሥራ ውል መጀመሩን አዲስ ማለዳ ከመግለጫው ተረድታለች።

በዚህ የእድሳት ሂደት ከውጪ ለሚገቡ እቃዎች የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዲሁም ቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ ገቢ ታገኛለች በሚል ግምት ህብረተሰቡ ለመርዳት ፍቃደኝነት አለማሳየታቸው እንደ ተግዳሮት ተጠቅሰዋል።

ድጋፍ የሚሰበሰብባቸው መንገዶችም እንደቀጠሉ ነው።

እድሳቱ ከተጀመረ አንድ ዓመት ከግማሽ ገደማ ያስቆጠረ ሲሆን መጋቢት 30 ቀን 2016 እንደሚጠናቀቅ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በገንዘብ እጥረት ሳቢያ ለሦስት ወራት እንዲራዘም መደረጉን አዲስ ማለዳ ከታደመችበት መግለጫ ሰምታለች።

የቤተ ክስርስቲያኗ አስተዳዳሪ ሊቀ ስልጣን ቆሞስ አባ ሲራክ አድማሱ እንደገለጹት እድሳቱ ከኢትዮጵያ ቅርስና ጥበቃ ህጋዊ ፈቃድ አግኝቶ የሚታደስ መሆኑን ጠቁመው በግንባታ ሂደት ያጋጠመ ችግር የለም ብለዋል።

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን በ1924 ከተመሰረተ ጀምሮ ከ90 ዓመታት በላይ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ጥናቱን ያጠናው የታዋቂው የኪነህንጻ ታሪክ አዋቂው እና የታሪካዊ ህንጻዎች እድሳት ጠበብቱ፥ ህንጻ ነዳፊ ፋሲል ጊዮርጊስ አማካሪ ጽ/ቤት ሲሆን ገንቢው ደግሞ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የግንባታ ታሪክ ከ65 አመታት በላይ የግንባታ ልምድ ያለው ጂዮም ሉዊጂ ቫርኔሮ ኢምፕሬሳ ኮስትሩዚዮኒ ፒኤልሲ ነው።

📌የቅድስት ስላሴ ካቴድራል ህንጻ ታሪክ

የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሕንፃ የመሠረት ድንጋይ ታኅሣሥ 15 ቀን 1924 ዓ/ም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሲያስቀምጡ የእስክንድርያ ኮፕት ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ዮሐንስ እና የሀገር ጳጳሳትም በተገኙበት ልዩ ጸሎት እና ቡራኬ ተሠጥቶ ተመረቀ።

በ1924 አካባቢ የተጀመረው ህንጻ ወደመጨረሻው ደርሶ ሳይጠናቀቅ ጣልያን በ1928 ኢትዮዽያን ወሮ ነበር።

የግንባታ ስራው ጣልያን ኢትዮዽያን በወረረበት ከ1928 እስከ 1933 ባሉት አምስት አመታት ተቋርጦ ነበር።

በጣልያን ወረራ ወቅት እና ከዚያ በፊት ከተነሱ ምስሎች የተነሳ ህንጻው አስቀድሞ የኒዮ ክላሲካል ዘይቤ የነበረው መሆኑን እንረዳለን።

ግንባታው ከነጻነት በኋላ የቀጠለ ሲሆን በጥር 6 ቀን 1935 ተስፋፍቶና ተሻሽሎ የንድፍ ዘይቤውም ወደ ኒዮ ባሮክነት ተለውጦ ለምርቃት ሊበቃ ችሏል።

ከዝያም እንደገና በ1960 በዩጎዝላቭያ ህንጻ ነዳፊዎች አማካኝነት ለሶስተኛ ግዜ ተስፋፍቶ ተገንብቷል። ለሶስተኛ ግዜ አስፋፍተው የነደፉት ህንጻ ነዳፊዎቹም ስላቪሳ ፔትሮቪች እና ዜድ ድራይጎሎቪች ይባላሉ።

የመጨረሻውን እድሳቱን ስራ ዩጎዝላቪያው ተቋራጭ ዩኒየን ኢንጂነሪንግ የሰራው ሲሆን በግዜው ታዋቂ የነበረው ጂዎርዳኖ ኮንቼቶ ስራ ተቋራጭ የእጅ ስራ ድንጋይ እና ስቱኮ ስራውን ሰርቷል።

Via አዲስ ማለዳ፣ ውኪፔዲያ፣ ማህበራዊ መገናኛ፣ አርቺቪዮ ሉቼ፣ እና ዋልተር ሚተልሆልዘር

@etconp
👍4👏3
_@etconp_የኮንስትራክሽን_ብቃት_ማረጋገጫና_ምዝገባ_መመሪያ.pdf
50.8 MB
👉የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ መመሪያ

✳️በነገራችን ላይ ለ YOUTUBE ቻናላችን አዲስ ከሆኑ ከታች ባለው ሊንክ ገብተው SUBSCRIBE በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ እንዲሁም ለወዳጅዎ ያጋሩ

https://www.youtube.com/@ETHIOCONp

@etconp
👍10🙏3
👉የቻይና ከተሞች እየሰመጡ ነው ተባለ

❇️ከቻይና ዋና ዋና ከተሞች ግማሽ ያህሉ ላይ የመስመጥ አደጋ መጋረጡ ተሰምቷል።

🔰በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በተለይ የባህር ከፍታ ሲጨምር ለጎርፍ አደጋ እየተጋለጡ ነው ሲል በአገር አቀፍ ደረጃ የወጣው የሳተላይት መረጃ አመልክቷል።

❇️በሳይንስ ጆርናል የታተመው ይኸው ጥናት 45 በመቶው የቻይና የከተማ መሬት በአመት ከ3 ሚሊ ሜትር በላይ በፍጥነት እየሰመጠ ነው ያለ ሲሆን 16 በመቶው ደግሞ በዓመት ከ10 ሚሊ ሜትር በላይ መስመጡን ገልጿል።

✳️በከተሞቹ የሚገኙ በርካታ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ምክንያት መሆናቸውን ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል።

@etconp
👍7😢6❤5
👉ኣዲሱ ቻናላችን ተቀላቅለዋል?

⚡️ዛሬ የወጡ የ ስራ ቅጥሮቾ ጨምሮ

🌟አዳዲስ ጨረታዎች እና የኮንስትራክሽን ስራ ቅጥሮች ሲወጡ በቀላሉ ለመመልከት ከታች ባለው ሊንካችን ይቀላቀሉን።

📌እንዲሁም ለወዳጆቻቹ SHARE በማረግ አዳርሱ።

https://t.me/ETCONpWORK
👍6❤1👏1
Bolts are most suitable to carry ?
Anonymous Quiz
29%
Shear
8%
Bending
26%
Shear and bending
37%
Axial tension
👍19❤2👌2🕊1
The last staff reading in any set up of the instrument and Indicates shifting the instrument is
Anonymous Quiz
34%
Back sight
36%
Fore sight
17%
Change point
13%
Intermediate point
👍11❤3
A map having a scale of 1 cm = 3 km, is represented as a representative fraction as:
Anonymous Quiz
14%
1 : 30000
42%
1 : 300000
20%
1 : 3000000
25%
1 : 3000
👍15🕊5❤3🙏1
Intercon Construction Materials 
    
👉 Specialized in construction chemicals, Authorized agent of MC (Conmix) and Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofing Chemicals and Materials (Cementitious, Acrylic,  Crystalline, Bituminious and Liquid membrane, Liquid Glass, Sealants)
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● External finishes (Quartz paint, Contextra),
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy, Self-level              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍3❤1🙏1
👉አዲስ አበባ ውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 209.86 ኪ.ሜ የፍሳሽ መስመር ጥናት እና ዲዛይን ስራ አከናወንኩ ኣለ

ባለስልጣኑየከተማዋን የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ለማዘመን የሚያስችል 166.43ኪ.ሜ የፍሳሽ መስመር ጥናት እና ዲዛይን ስራ ለማከናወን አቅዶ 209.86 ኪ.ሜ ማከናወን ተችሏል ይህም የዕቅዱ 126% ነው፡፡

ለዕቅድ አፈፃፀሙ መጨመር በዋነኛነት በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ወቅት የጥናት እና ዲዛይን ዝግጅት ስራ ለዝርጋታ ስራ ቅልጥፍና እንዲረዳ በቅርንጫፎች እና በዋናው መ/ቤት በሚመለከተው ክፍል በስፋት በመከናወኑ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ከኮሪደር የመንገድ ዳር ልማት ጋር በተያያዘ የጥናት እና ዲዛይን ስራው በልዩ ሁኔታ ቀን እና ከሌት በመከናወኑ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ከጥናት እና ዲዛይን ስራ በተጓዳኝ በራ ሀይል እና ሶስተኛ ወገን በማሳተፍ የ78.61ኪሎ ሜትር መስመር ዝርጋታ አከናውኗል፡፡

Via AAWSA

@etconp
👍5🏆2
👉ጀጎል የምስራቅ አፍሪካው አውራ ግንብ

✳️ሀገራችን ድንቅና ውብ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ መስህቦች እንዲሁም ታሪካዊ ቅርሶችና ባህላዊ እሴቶች ባለቤት ናት። እነዚህ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች የውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን ቀልብ በመግዛት ይታወቃሉ።

🚧ምርጥ የቱሪዝም መዳረሻ ከመሆን ባሻገርም የዓለም ቅርስ ሆነው የተመዘገቡ ብዙ ናቸው፡፡

🔰ከእነዚህ የሀገራችን ውብ ቅርሶች በምሥራቁ የሀገራችን ክፍል የሚገኘው የጀጎል ግንብ አንዱ ሲሆን የግንባታው መሀንዲሶች በወቅቱ የነበሩ አባቶች ናቸው።

☄የጀጎል ግንብ የሀረሪ ህዝብ የኪነ ህንፃ ችሎታውን የሚያስመሰክር የታሪክ እና የጥበብ ውጤትም ነው፡፡

☄የሀረር ከተማ መለያና የዓለም ቅርስ የሆነው የጀጎል ግንብ የተገነባው በ16ኛው ክፍለ ዘመን በአሚር ኑር ቢን ሙጃሂድ መሆኑን ታሪክ ያስረዳል።

☄ጀጎል በሀገር በቀል ዕውቅ የፈጠራ ባለቤቶች የተገነባ የሀገረሰብ ጥበብ ውጤት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዘመኑ አባቶች ያለምንም ቴክኖሎጂ እገዛ ነበር ግንቡን ያበጃጁት::

🔰ከፋብሪካ ውጤቶች ነፃ የሆነና በአካባቢያቸው የሚገኘውን ጥሬ ዕቃ በመጠቀም የገነቡት የዚህ ግንብ ቆይታው ደግሞ የአባቶችን የጥበብ ከፍታን ያሳየ ነው።

☄በዘመኑ በምስራቅ አፍሪካ በግንብ የታጠረች የመጀመሪያዋ ድንቅ ከተማ ሀረር እንደሆነች መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

📌የግንባታው ዓላማም ከተማዋን ከጠላት ለመከላከል እንደሆነ ይነገራል፡፡


Via Addis Walta

@etconp
👍8
Rate this building out of 10

Telegram:- https://t.me/
ETCONpWORK

YouTube:- https://www.youtube.com/@ETHIOCONp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

X formerly (Twitter):- https://x.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
❤8👍7
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

🔰ምን ይፈልጋሉ?

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍3❤1
በአዲስ_አበባ_2ኛው_ዙር_የመሬት_ሊዝ_ጨረታ.pdf
5.3 MB
በአዲስ አበባ ከተማ የ2ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ ከተማ (ፒያሳ) በዓድዋ ድል መታሰቢያ አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ ፦
- በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣
- በኮልፌ ቀራንዮ፣
- በአራዳ፣
- በአቃቂ ቃሊቲ፣
- በየካ፣
- በቦሌ፣
- በአዲስ ከተማ፣
- በቂርቆስ፣
- በጉለሌ
- በልደታ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ እንደሚፈልግ አሳውቋል።

(ዝርዝር የጨረታው መረጃ በPDF ተያይዟል - ይመልከቱ)

Via አዲስ ልሳን

@etconp
👍8❤1
👉የመኖሪያ ቤት እጥረትን የሚያስወግዱ የፕሪካስት ሕንፃዎች

ሀገራችንን ኢትዮጵያን ጨምሮ ፈጣን የሆነ የህዝብ ቁጥር ዕድገት በሚታይባቸው ሀገራት ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት ወይም አፓርትመንት እጥረት እየተከሰተ ነው፡፡

የሰው ልጅ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ ነገሮች አንዱ የሆነውን መኖሪያ ቤት ለኑሮ አመቺ በሆነ ቦታ እና ተገቢ በሆነ ወጪ ማግኘት ቀዳሚ ጉዳይ ነው፡፡

ይህንን እጥረት እና ፍላጎት ለማሟላት ከሚያስችሉ የግንባታ ዘዴዎች ውስጥ ቀደም ብለው በተለያዩ ሳይቶች የሚዘጋጁ ተገጣጣሚ የኮንክሪት የወለል ምንጣፎች፣ ግርግዳዎች እና ቋሚ ማዕዘኖች "ፕሪካስት ኮንክሪቶች" ትኩረት ከሚሹ የግንባታ ዘዴዎች መካል በቀዳሚነት የሚቀመጡ ናቸው፡፡

በፕሪካስት ቴክኖሎጂ በፋብሪካ ውስጥ እየተመረቱ በሰለጠነ መንገድ የሚገጣጠሙ የሕንፃ ቁሳቁሶች፣ የመኖሪያ ቤትን ዕጥረትን በፍጥነት ለመቅረፍ ከሚያስገኙት ተጨማሪ ጠቀሜታዎች እና የአመራረት ዘዴዎች መካከል የሚከተሉት በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡

🔰የጥራት ደረጃን መጨመር እና መጪን መቀነስ

ለሕንፃ ግንባታ የሚያስፈልጉ ተገጣጣሚ ኮንክሪቶች የሚዘጋጁት ለቁጥጥር አመቺ በሆኑ ገላጣ ቦታዎችና መጠኑ ባልተዛባ እንደ ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ውኃ በመሳሰሉ የግንባታ ቁሳቁሶች በመሆኑ አላስፈላጊ ብክነት ወይም ዕጥረትን በማስወገድ ወጪን ይቀንሳሉ፡፡

ኮንክሪቶቹ የሚዘጋጁት ከሰው ፍላጎት እና ተጽዕኖ በጸዳ፣ በፕሮግራም በሚታዘዝ (አውቶማቲክ) የማምረት ዘዴ በመሆኑ የተፈለገውን ምርት በተፈለገው ፍጥነት በማምረት የጊዜ ብክነትን ያስወግዳሉ፡፡

በተለመደው የሕንፃ ግንባታ ዘዴ በግንባታ ሳይት ላይ የተለያየ ቅርፅ ያላቸው ዲዛይኖችን ለመስራት የሚያስፈልጉ ውስብስብ የእንጨት እና የብረት ድጋፎችን በማስወገድ ለሚፈለገው ቅርፅ ሞልድ (ቅርፅ) ማውጫ በማዘጋጀት የተፈለገውን ዲዛይን በፍጥነት ለማምረት የባለሙያን ወጪን ይቀንሳል፡፡

🔰አስተማማኝ የስራ ዕድል ይፈጥራል

አንድ የፕሪካስት ማምረቻ ድርጅት ወደ ማምረት ሂደት የሚገባው አንድ አስገንቢ ድርጅት ለሚሠራው ሕንፃ የሚያስፈልገውን የተገጣጠመ ኮንክሪት መጠን እና ዲዛይን መነሻ በማድረግ ቀደም ያለ የውል ስምምነት በመፈረም ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ አምራች ድርጅቱ ግንባታው እስኪጠናቀቅ ድረስ የማያቋርጥ አስተማማኝ የሥራ ዕድል እንዲፈጠርለት ያደርጋል፡፡

🔰የኮንክሪት እና የኃይል ወጪን ይቀንሳል

በፕሪካስት የሚገነቡ ሕንፃዎች ትርፍ የሆነ ሙቀትን በማመቅ በዝግታ ወደ ከባቢ አየር መልቀቅ እንዲወገድ በማድረግ፣ በሕንፃ ላይ የሚፈጠረውን አላስፈላጊ ክብደት ወይም ጭነት በማስወገድ፣ በተለመደው መንገድ ሳይት ላይ ከሚገነቡ ሕንፃዎች ከ50 በመቶ የበለጠ የኮንክሪት እና የኃይል ወጪን ይቀንሳሉ፡፡

ይህን ብቃት እንዲላበሱ ከሚያደርጋቸው ውስጥ ለምሳሌ፣ የተለያዩ ፎቅ ባላቸው ሕንፃዎች ለወለል የሚዘጋጁ ውስጣቸው ክፍት በሆነ ብሎኬት እና ኮንክሪት የሚዘጋጁ ተገጣጣሚ የኮንክሪት ምንጣፎች ከተለመደው ግንባታ ከ50 እስከ 60 በመቶ ክብደታቸው የቀነሰ ከመሆኑም በላይ ጥራታቸው በተጠበቀ እንደ ሲሚንቶ፣ ብረት እና የመሳሰሉት የግንባታ ቁሶች የሚዘጋጁ ናቸው፡፡

ከዚሁ በተጨማሪ፣ እንደየአስፈላነቱ ግንባታው በሚካሄድበት ቦታ ያለውን የከባቢ አየር ድምጽ መስተጋባት፣ የመሬት ርደት ወዘተን መነሻ አድርገው ስለሚመረቱ አላስፈላጊ የሆነ የኮንክሪት እና የኃይል ወጪን በመቀነስ  የበለጠ ዕድሜ እና ጥንካሬን እንዲኖራቸው የሚያደርግ ብቃት የተላበሱ ያደርጋቸዋል፡፡

🔰ለዕድሳት፣ ለግንባታ እና ለማጓጓዝ የሚያስፈልገውን ጊዜ እና ወጪን ይቀ ንሳል

በፕሪካስት ኮንክሪት የሚገነቡ ሕንፃዎች ከሚያስፈልጋቸው ቁሳቁሶች ውስጥ በብረት እና በኮንክሪት የሚዘጋጁ ተገጣጣሚ ወለሎች፣ በአራት መዐዘን እና በተፈለገው ቅርጽ የሚዘጋጁ ጠፍጣፋ የኮንክሪት ወለሎች ተገጣጣሚ ግድግዳዎች፣ የቋሚ እና የአግድም መዐዘን የኮንክሪት ፍሬሞች ይገኙባቸዋል፡፡ እነዚህ ተገጣጣሚ የግንባታ ቁሳቁሶች የሚዘጋጁት በተወሰነ ሳይት ላይ ሆኖ፣ በቀላሉ ሊገጣጠሙ በሚችሉ እና ለማጓጓዝ አመቺ በሆነ መጠን እና ዲዛይን ነው፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ ሳይት ላይ ጥሬ ቁሶችን በማቅረብ እና በተለመደው መንገድ ለመገንባት የሚያስፈልጉ የቁሳቁስ ማጓጓዣ፣ በኮንክሪት ሙሌት የሚወጣ የጉልበት እና የመሳሪያ አቅርቦት ወጪን ይቀንሳሉ፡፡ ክፍት የሆኑት የኮንክሪት ምንጣፎች እስከ 20 ሜትር የሚረዝም ቁመና የተላበሱ በመሆናቸው በተለመደው መንገድ ከ6 እስከ 10 ሜትር ብቻ በሚረዝም ፓሌት (የብረት ማዕዘን) እየተገጣጠመ የሚሞላ የኮንክሪት መዐዘን ለማዘጋጀት የሚያስፈልግ የጉልበትና የግንባታን ወጪን በመቀነስ ግንባታው በፍጥነት እንዲከናወን በማድረግ ያላቸውን ጠቀሜታ የጎላ ነው፡፡ 

@etconp
👍11❤4👏1
Office building in Kyiv made of steel structures.
7 floors. The weight of steel structures is 260 tons.

📍 Ukraine 🇺🇦

@etconp

Telegram:- https://t.me/
ETCONpWORK

YouTube:- https://www.youtube.com/@ETHIOCONp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

X formerly (Twitter):- https://x.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
👍7
Intercon Construction Materials 
    
👉 Specialized in construction chemicals, Authorized agent of MC (Conmix) and Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofing Chemicals and Materials (Cementitious, Acrylic,  Crystalline, Bituminious and Liquid membrane, Liquid Glass, Sealants)
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● External finishes (Quartz paint, Contextra),
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy, Self-level              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍7
👉በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት ተደርምሶ በደረሰ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ

✳️በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ጠሮ መስጊድ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የመኖሪያ ቤት ተደርምሶ በደረሰ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

🚧የክፍለ ከተማው ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አይዳ አወል እንዳሉት÷አደጋው የግለሰብ መኖሪያ ቤት ተደርምሶ በጀርባ በሚገኝ ሌላ መኖሪያ ቤት ላይ በማረፉ ነው የተከሰተው፡፡

🔰ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በደረሰው አደጋም እስካሁን የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ነው ሥራ አስፈጻሚዋ የተናገሩት ሲል ፋና ነው የዘገበው።

@etconp
😢10❤2👍2