Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉አፍሪካ እና አውሮፓ በባቡር ትራንስፖርት ሊገናኙ ነው!

🚧ለ2030ው የዓለም ዋንጫ አፍሪካ እና አውሮፓ በባቡር ትራንስፖርት ሊገናኙ መሆኑ ተገለጸ።

✳️በስፔን ፖርቹጋል እና ሞሮኮ አስተናጋጅነት እንደሚካሄድ በሚጠበቀው የ2030ው ዓለም ዋንጫ አፍሪካ እና አውሮፓ በባቡር ትራንስፖርት ለማገናኘት ታቅዷል ተብሏል።

🔰ሞሮኮ እና ስፔን በጋራ የባቡር ትራንስፖርት መስመሩን ለመገንባት ጥረት መጀመራቸው ተገልጿል።

❇️የግንባታው ወጪ በሁለቱ ሀገራት ይሸፈናል የተባለ ሲሆን ግንባታው በቅርቡ እንደሚጀመር የይሮ ኒውስ ዘገባ ያመለክታል፡፡

☄ስፔን ፖርቹጋል እና ሞሮኮ የ2030 የዓለም ዋንጫን በጋራ ለማዘጋጀት ለፊፋ ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

@etconp
👍16😁1
Intercon Construction Materials 
    
👉 Specialized in construction chemicals, Authorized agent of MC (Conmix) and Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofing Chemicals and Materials (Cementitious, Acrylic,  Crystalline, Bituminious and Liquid membrane, Liquid Glass, Sealants)
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● External finishes (Quartz paint, Contextra),
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy, Self-level              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍2
👉እንኳን ለ እየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ❤️

🙏መልካም በዓል😇

@etconp
❤10👍2
በቻይና በተከሰተው የድልድይ መደርመስ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 48 ደረሰ፡፡

በጉዋንዶንግ ግዛት በጣለው ከባድ ዝናብ የፈጣን መንገድ ድልድይ ተደርምሶ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን TRT World ዘግቧል፡፡

በአደጋው 48 ሰዎች መሞታቸውን ያረጋገጡት የአካባቢው ባለስልጣናት ሌሎች በርካቶች ቆስለዋል ብለዋል፡፡

18 ሜትር በሚረዝመው ፈጣን መንገድ አደጋው በተከሰተበት ወቅት 23 ተሸከርካሪዎች በአካባቢው እንደተገኙ ተገልጿል፡፡

@etconp
👍14😢4
🔰ከ በረከቱ እንሳተፍ

👉በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

በትግራይ ምስራቅ ዓዲግራት ዞን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ደብረ ፀሐይ ቅድስት ሥላሴ ሀገረ ስብከት ይህ (አዲግራት ዩኒቨርስቲ የተማርችሁት ታውቁታላችሁ። ከአዲግራት ዩኑቨርስቲ መግቢያ ፊት ለፊት የሚታየው ቤተ/ክ አዲስ ዲዛይን ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ እየተገነባ ነው።

እዚህ ሰዓት ያደረስን አጋዝእተ ዓለም ስላሤ ምስጋና ይግባቸው እና ህንጻ ስላሤ ተበልን ምንጠራውን እኛ ሰዎችን ያነጹ ስላሤ ቤታቸውን እኛ ደሞ በተራችን ልናንጽ ይገባልና ሁላችንም ከበረከት እንሳትፍ ።

ሰማያዊ ቤቱን በምድር ላይ ለመሥራት የማይጓጓ እና የማይጨነቅ ማነው? " ይህ የእግዚአብሔር ቤት እንጂ ሌላ አይደለም፥ ይህም የሰማይ ደጅ ነው።

ስለሆነም ሁላችሁም የምትችሉትን የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታበረክቱ እና እንድትሳተፉ በደብሩ ልማት ኮሚቴ እና በአዲግራት (በዓቲ) ሰበካ ጉባኤ ስም በትህትና እንጠይቃለን።

- 1000305183915 (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
- 3071197401646(አንበሳ ባንክ)
- 0782718830201(ወጋገን ባንክ)
- 01352777585 (አዋሽ ባንክ)

"የሰማይ አምላክ ይመራናል እኛም ባሪያዎች ተነስተን እንሰራለን" ነህ 2÷2

@etconp
👍19🙏2💔2❤1
እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን🙏

መልካም በዓል❤️

@etconp
❤6👍5
ጌታ በእውነት ተነስቷል።
ሉቃ 24 ፡ 34


ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በአብይ ኃይል ወስልጣን
አሰርዎ ለሰይጣን
አግዓዝዎ ለአዳም
ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም።


እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የመተሳሰብ ይሁልን።

ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላምን ያድርግልን
🙏

@etconp
🙏16👍7❤4🏆1
👉እየሩሳሌም በሺህ የሚቆጠሩ አመታትን ያስቆጠረ ረጅም እና የበለጸገ የግንባታ ታሪክ አላት

የከተማዋ አርክቴክቸር የተለያዩ ባህላዊ እና ሀይማኖታዊ ተጽእኖዎችን የሚያንፀባርቅ ሲሆን ከጥንታዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስፍራዎች ጀምሮ እስከ ዘመናዊ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ድረስ ያሉ መዋቅሮች አሉት።

በኢየሩሳሌም ታሪክ ውስጥ በጣም ዝነኛ ከሆኑት የግንባታ ፕሮጀክቶች አንዱ በንጉሥ ሰሎሞን በ10ኛው ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት የገነባው የመጀመሪያው ቤተመቅደስ ነው።

ይህ ቤተ መቅደስ በ586 ልክበ ዠ በባቢሎናውያን ፈርሶ ነበር፣ ነገር ግን በአይሁድ ሕዝብ በ6ኛው ክፍለ ዘመን እንደገና ተገነባ።

ሁለተኛው ቤተመቅደስ በኋላ በሮማውያን በ70 ዓ.ም ተደምስሷል፣ እና ምዕራባዊው ግንብ፣ የቤተ መቅደሱ ግቢ ቅሪት፣ ዛሬም እንደ አይሁዶች የፅናት እና የእምነት ምልክት ነው።

ባለፉት መቶ ዘመናት ኢየሩሳሌም በተለያዩ የሃይማኖት ቡድኖች አብያተ ክርስቲያናትን፣ መስጊዶችን እና ምኩራቦችን ግንባታን ጨምሮ የበርካታ የግንባታ ፕሮጀክቶች ማዕከል ሆና ቆይታለች።

በሮማውያን ዘመን የጀመረችው አሮጌው ከተማ፣ የሮክ ጉልላት እና የቅዱስ መቃብር ቤተክርስቲያንን ጨምሮ ብዙ ታሪካዊ ሕንፃዎች እና ሀውልቶች ይገኛሉ።

በዘመናችን እየሩሳሌም በከተማዋ ውስጥ አዳዲስ የመኖሪያ እና የንግድ ሕንፃዎች በመስፋፋት ከፍተኛ መጠን ያለው የከተማ እድገት አሳይታለች።

ቢንያነይ ሃኡማ በመባል የሚታወቀው የኢየሩሳሌም አለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል ግንባታ እና የኢየሩሳሌም ማእከላዊ አውቶብስ መናኸሪያ ለከተማዋ ዘመናዊ የኪነ-ህንፃ ጥበብ ማሳያዎች ናቸው።

የከተማዋ አርክቴክቸር የተለያዩ ያለፈውን እና ቀጣይ ዝግመተ ለውጥን እንደ ደማቅ እና ተለዋዋጭ የከተማ ማእከል ያንፀባርቃል።

በ ድጋሜ መልካም የ ትንሳዔ በዓል❤️

Via Fila

@etconp
👍11❤6
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

🔰ምን ይፈልጋሉ?

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍2
👉አሁናዊ ኪነህንጻ

🚧ደብረ እንቁ ልደታ ለማርያም ቤተክርስትያን።

📌ቀበና አካባቢ ከፍ ባለ ቦታ ላይ የተገነባ፣ አዲስ አበባ።

☄የግሪካውያን ወይም የሮማውያን ፔዲመንቶች፣ አእማዶችና ንድፍ ውሰቶች የሌሉበት ሊጎበኝ የሚገባው ነው።

📷 BCAA በኩል

@etconp
❤17👍9🥰1
Intercon Construction Materials 
    
👉 Specialized in construction chemicals, Authorized agent of MC (Conmix) and Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofing Chemicals and Materials (Cementitious, Acrylic,  Crystalline, Bituminious and Liquid membrane, Liquid Glass, Sealants)
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● External finishes (Quartz paint, Contextra),
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy, Self-level              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍5❤1
👉የሁለት ቢሊዮን ዶላር ኤርፖርት ግንባታ

✳️የኬንያ ትልቁ ኤርፖርት የሰሞኑን ዝናብ መቋቋም አቅቶት ክፉኛ ሲያንጠባጥብ ተስተውሏል።

🚧የኬንያ መንግስት ይህንን ተግዳሮት ለማለፍ በሁለት ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ አዲስ አውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት ዕቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ ነው።

✳️አዲስ የሚገነባው ኤርፖርት "New Nairobi" የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፣ ግንባታው በታሰበው መሠረት ከተጠናቀቀ ባረጀ የመሠረተ ልማት ደረጃ የሚገኘውን እና 66 አመት ያስቆጠረውን የጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ ኤርፖርት የመተካት ሚና ይኖረዋል።

🔰የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ በሚቀጥለው ወር በዩናይትድ ስቴትስ ዋሽንግተን ዲሲ ሊያደርጉ በተዘጋጁት ጉብኝታቸው ለአዲሱ ኤርፖርት ግንባታ ከዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ጥያቄ ያቀርባሉ ተብሏል።

❇️ይህ አዲሱ የናይሮቢ አውሮፕላን ማረፊያ የመገንባት ግዙፍ እቅድ ኬንያ በአካባቢው ወሳኝ የአቪዬሽን ማዕከል ለመሆን የያዘችው ውጥን አካል ነው።

❇️የአዲስ ናይሮቢ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ወጪን በመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት (PPP) ለመገንባት ታሳቢ ተደርጓል።

🚧በጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ያለው ደካማ መሠረተ ልማት ኤርፖርቱ ቀስ በቀስ አገልግሎት መስጠት ወደ ማቆም ሊያመራል የሚል ስጋትም ተፈጥሯል።

❇️አሁን ያለው የጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ ልማት የመንገደኛ ተርሚናሎች ጣሪያ ዝናብ የሚያንጠባጥብ ሁኔታን በሚመለከት የኬንያ የወደብ ባለስልጣን በኤርፖርቱ የሚያንጠባጥቡ ጣሪያዎች የማደስ ሥራው የተጀመረው ከባድ ዝናብ ከመጀመሩ በፊት በመጋቢት ወር ነው ብሏል።

❇️ይህ የሚያመለክተው የኤርፖርቱ እድሳት የመሠረተ ልማት ችግሩ እንደ ስጋት መነሳት ከጀመረ ከአምስት ወራት በኋላ ነው።

❇️ይህ የመሠረተ ልማት ሁኔታ ባለፉት አስር አመታት ውስጥ በጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በቂ የሆነ የመገልገያ እና የመሠረተ ልማት ጥገና እና ማሻሻያ ያለመኖሩን ያሳያል ተብሏል።

🔰በኤርፖርቱ ላይ ያሉ አንዳንድ ጣሪያዎችም እያፈሰሱ ይገኛሉ፣ በዚህም የኳታር አየር መንገድን፣ ሉፍታንዛን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን፣ የቱርክ አየር መንገድን እና የሩዋንዳ አለም አቀፍ አየር መንገዶችን የሚያገለግሉ ተርሚናሎች ሥራዎቸውን ማቋማቸው ተነግሯል።

@etconp
👍15❤3
👉በኢትዮጵያ በ600 ሚሊዮን ብር 11 የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ነው

🔰የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር 11 የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን ለማስገንባት ከስድስት ሥራ ተቋራጮች ጋር የ600 ሚሊየን ብር የውል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

✳️የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ፦ በኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት በአምስት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ለመጠጥ ውሃ፣ ለመስኖ ልማት እና የከርሰ-ምድር ውሃ ሀብት አስተዳደር ሥራዎችን ለመደገፍ የተቀረጸ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።

❇️ለሶስት ሀገራት ከአለም ባንክ ከተገኘው የ385 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ኢትዮጵያ 210 ሚሊየን ዶላር ድጋፉን አግኝታለች።

❇️በዚህም በ55 ወረዳዎችና በ110 የገጠር ቀበሌዎች ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በመገንባት 1.4 ሚሊየን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ነው፡፡

🚧ፕሮጀክቶቹ በኦሮሚያ ቦረና ዞን፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጉራጌ ዞን፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ ዞን፣ በሲዳማ ዳራ ዞን እና በሶማሌ ክልል በዳሌ ዞን ይገነባሉ፡፡

📌ግንባታውን በአንድ ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ ለማጠናቀቅ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

🚧ተቋራጮቹ በገቡት ውል መሠረት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ሠርተው እንዲያጠናቅቁ ጥብቅ ቁጥጥሬ እንደሚካሄድ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

@etconp
👍17😢1👌1🏆1
"Hello everyone,
I am conducting a research study on "The Role of BIM in Enhancing Construction Cost and Time Performance." And I would greatly appreciate your help by filling out a Google form that I have created. Your participation is important for the success of this study.

👉Anyone who is in a construction field and have an experience starting from one can fill it.

https://forms.gle/t3d9mtYKeagq24i1A

thank you in advance.🙏
👍6
ቻይና አዲስ ድልድይ ይዛ መጥታለች

✳️ይህ በሎንግሊ ወንዝ ላይ የተሠራው ድልድይ የሚገኘው፦ በጉዋንዡ ክፍለ ግዛት ውስጥ ሲሆን፣ የድልድዮን መጠናቀቅ ተከትሎ ባገኘው የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ባለፈው ቅዳሜ አፕሪል 27 ቀን 2024 ቀን ጀምሮ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል።

@etconp
👍21
👉በደቡብ አፍሪካ ህንፃ ተደርምሶ የአምሥት ሰዎች ህይወት አለፈ

✳️በደቡብ አፍሪካ በተከሰተ የህንፃ መደርመስ አደጋ የአምሥት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።

🚧በሀገሪቱ ዌስተርን ኬፕ ግዛት ጆርጅ ከተማ በመገንባት ላይ ያለ ባለ 5 ወለል ህንጻ ተደርምሶ በስራ ላይ ከነበሩ አጠቃላይ 75 ሰዎች አምሥቱ ህይወታቸው ሲያልፍ 24 ሰዎችን ከፍርስራሹ ማውጣት ተችሏል ተብሏል።

🔰ከፍርስራሹ ስር ይገኛሉ የተባሉ 50 ያክል ሰዎችን ለመታደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።

🚧የአደጋው ምክንያት እየተጣራ መሆኑንም ዘገባው አመላክቷል።

📌በነፍስ አድን ስራው ከመቶ በላይ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከአነፍናፊ ውሾች ጋር እንደተሰማሩ ዘገባው ጠቁሟል።

#FirstSafety

@etconp
👍11😢4
Intercon Construction Materials 
    
👉 Specialized in construction chemicals, Authorized agent of MC (Conmix) and Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofing Chemicals and Materials (Cementitious, Acrylic,  Crystalline, Bituminious and Liquid membrane, Liquid Glass, Sealants)
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● External finishes (Quartz paint, Contextra),
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy, Self-level              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍5
👉ሲሲሲሲ የግዙፉን “ኤግል ሂልስ” ግንባታ ፕሮጀክት ሥራ እያካሄደ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሽርክና ከሚያሠራቸው ፕሮጀክቶች መካከል ተጠቃሽ የሆነው ግዙፉ የ"ኤግል ሂልስ" ግንባታ ፕሮጀክት የምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ግንባታ ሥራ ከመሬቱ አለታማነት አንፃር የተወሰነ ጊዜ ቢወስድም የፕሮጀክት ግንባታ ሥራ በጥሩ አፈፀፃም ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የፕሮጀክት ግንባታ ሥራውን የቻይናው ኮሚዩኒኬሽንስ ኮንስትራክሽን ኩባንያ (CCCC) እያከናወነ ሲሆን፣ በአሁን ወቅት የግንባታ ሥራው 24 ሰዓት ሙሉ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልፆል፡፡

የ"ኤግል ሂልስ" ግንባታ ፕሮጀክት ኮርዲኔተር አቶ ሰለሞን ከፈለኝ እንደገለጹት፣ በመሃል አዲስ አበባ በለገሃር ግንባታው እየተካሄደ የሚገኘው "ኤግል ሂልስ" ግንባታ ፕሮጀክት የምዕራፍ አንድ የመኖሪያ አፓርትመንት መዋቅር ሥራ ተጠናቆ የማጠቃለያ ሥራዎች እየተፋጠነ ይገኛል፡፡

የዚሁ ምዕራፍ ግንባታ አካል የሆነው ሌላኛው የሦስት በጣም ትልልቅና ዘመናዊ የሆነ ሞል፣ አፓርትመንትና ሆቴል ግንባታ ሥራ የሚሆነው መሬት አለታማ በመሆኑ ለማስተካከል ጊዜ የወሰደ እና አሁን ላይ ለግንባታ ምቹ የማድረግ ሥራ የተጠናቀቀ በመሆኑ የኮንክሪት ሥራውን ለመሥራት በሚያስችል ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

የፕሮጀክት ግንባታው አሁን ባለው አቅም ለ200 ሰዎች በቋሚና ጊዜያዊነት የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን ፣ የመዋቅር (structure) ግንባታ ስራው ሲጀመር ደግሞ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የፕሮጀክት ግንባታ ሥራው በርካታ ተግባራትን በአንድ ጊዜ እና ተመሳሳይ ሰዓት ማከናወን የሚያስችል አቅም ፈጥሮ የሚንቀሳቀስ እንደመሆኑ ጥሩ ልምድና ትምህርት የሚወሰድበት የመዲናችን ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

@etconp
👍15❤3