Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉ታላቁ አል-ነጃሺ ፕሮጀክት

🚧የፕሮጀክት ስም፡- አል-ነጃሺ መልሶ ግንባታ እና ልማት ተነሳሽነት፣ ታላቁ አል-ነጃሺ ፕሮጀክት

📍ቦታ፡ ነጋሽ ከተማ (ከመቀሌ በስተሰሜን 58.5 ኪሜ)

📐የቦታው ስፋት፡ 117,380m2

📌አማካሪ፡- ዮሐንስ አባይ አማካሪ አርክቴክቶችና መሐንዲሶች።

📏ጠቅላላ ሕንፃዎች የወለል ስፋት: 92,586.60m2

📝የፕሮጀክት ይዘቶች፡ ባለ 5 ኮኮብ ሆቴል፣ አዳራሽ፣ ሙዚየም፣ የገበያ አዳራሽ፣ አል-ነጃሺ ዩኒቨርሲቲ፣ የመቻቻል ምርምር ማዕከል፣ ሂሳ (መድረሳ)፣ የአይን እንክብካቤ ማዕከል፣ መስጊድ፣ መኖሪያ ቤት፣ ኢኮ ሎጅ፣ የቤት ውስጥ እና የውጪ መዝናኛ እና መዝናኛ፣ አምፊ ቲያትር፣አሹራ፣ ፓርክ ወዘተ ይገኙበታል።

@etconp
👍14❤4🙏3
👉ኦሮሚያ ባንክ በገላን ለሚያስገነባዉ የልዕቀት ማዕከል ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ በ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ዉል መፈራረሙን አስታወቀ

🚧ባንኩ በኦሮሚያ ክልል በገላን ክፍለ ከተማ በ20 ሔክታር መሬት ላይ እያስገነባ የሚገኘዉ ሁለገብ የልህቀትና ኮይቬንሽን ማዕከል የመጀመሪያው ምዕራፍ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ተከትሎ ለሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ ጥላሁን አበበ ከተባለው ተቋራጭ ጋር የ 1.1 ቢሊየን ብር የግንባታ ዉል ከሰሞኑ መፈራረማቸውን ካፒታል ከባንኩ ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል ።

✳️በገላን የሚገነባው ማዕከል የባንክ ባለሙያዎች ማሠልጠኛና የማደሪያ ሕንፃዎችን ጨምሮ የመሰብሰብያ አዳራሾች፣ የገበያ ማዕከሎች የነዳጅ ማደያ፣ የመዋኛ ገንዳዎች ለተለያዩ ቢዝነሶችና አገልግሎቶች የሚውሉ ግንባታዎችን አካቶ የሚይዝ ነው፡፡

🔰ከ1.1 ቢሊዮን በሚጠጋ ብር የሚገነባዉ ይህ ለተለያዩ አገልግሎት የሚዉል ግዙፍ ባለ 9 ወለል ህንፃ በ1200 ካሬ መሬት ላይ ያርፋል ተብሏል፡፡

❇️ፊርማዉን የተፈራረሙት የኦሮሚያ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተፈሪ መኰንን እና የጥላሁን አበበ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን አበበ መሆናቸው ተነግሯል።

@etconp
👍10👏6❤3
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ መቁረጫ መብሻና  ማጠፊያ ማሽኖች አሉን

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ እናበጃለን እንዲሁም እናጥፋለን

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍7❤1
Intercon Construction Materials 
    
👉 Specialized in construction chemicals, Authorized agent of MC (Conmix) and Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofing Chemicals and Materials (Cementitious, Acrylic,  Crystalline, Bituminious and Liquid membrane, Liquid Glass, Sealants)
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● External finishes (Quartz paint, Contextra),
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy, Self-level              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍6
👉ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን የሚያገናኘው የመንገድ ግንባታ በቅርቡ ይጀመራል ተባለ

🚧ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን የሚያገናኘው የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በቅርቡ እንደሚጀመር በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ እንደገለፁ ዘ ሲቲ ሪቪው የተሰኘው የሀገሪቱ የዜና ምንጭ ዘግቧል።

✳️አምባሳደሩ ይህንን የገለፁት በኢትዮ-ደቡብ ሱዳን የቢዝነስ ፎረም ላይ ሲሆን ሁለቱን ሀገራት የሚያገናኘው አገር አቋራጭ መንገድ የሚገነባው በጋምቤላ እና በፓሎች የላይኛው የናይል ግዛት በኩል ነው ተብሏል።

🔰አገር አቋራጭ መንገዱን ለማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንግግር እንዲያደርጉ ባላስልጣናቸውን ከወራት በፊት ማዘዛቸውን አምባሳደሩ ሲገልፁ ኢትዮጵያም የመንገዱን ግንባታ ለማስጀመር ቁርጠኛ አቋም እንዳላት ጠቁመዋል።

@etconp
👍9
👉Green Construction - Green City

✳️አረንጓዴ ግንባታ የተገነባውን አካባቢ መፍጠር እና መጠቀም በተቻለ መጠን ለተፈጥሮ አካባቢ ተስማሚ እንዲሆን የሚያደርገውን ፍልስፍና እና ሂደቶችን ያመለክታል::

🚧ከዲዛይን ደረጃ ጀምሮ እስከ ስብሰባ ድረስ መዋቅሩ ሲጠናቀቅ ተግባራዊነት፣ አረንጓዴ ግንባታ በፕላኔቷ ላይ አሉታዊ ተጽእኖዎችን በመቀነስ እና አንዳንድ አወንታዊ ጥቅሞችን በመጨመር ላይ ያተኩራል።

✳️ግንባታ የዘመናዊው ህይወት አስፈላጊ አካል ነው - ሰዎች የሚኖሩበት ቤት፣ የሚማሩበት ትምህርት ቤቶች፣ የሚሠሩበት ንግዶች እና የሚነዱበት መንገዶች ያስፈልጋቸዋል።

✳️ማንኛውም ግንባታ በአካባቢው ላይ አንዳንድ የማይቀር ተጽእኖ ይኖረዋል ዘላቂነት ላይ እያደገ ባለው ዓለም አቀፋዊ አጽንዖት ፣ አዲስ ሕንፃ በማሳደግ ረገድ የራሳቸውን አሻራ ለማሳነስ እና ህንጻውን ለብዙ ዓመታት በዘላቂነት እንዲሠራ ለማድረግ ሁለቱንም እርምጃዎችን መውሰድ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ኃላፊነት ነው።

✳️አረንጓዴ ግንባታ ለዚያ ጥሪ መልስ ሲሆን በፍጥነት እያደገ የመጣ የኢንዱስትሪው ገጽታ ነው።

✳️የአረንጓዴው የግንባታ እንቅስቃሴ አካል የሆኑ አንዳንድ አዳዲስ ሂደቶች እና ፈጠራዎች እነኚሁና።

✳️ኮንስትራክሽን በኢኮኖሚው ውስጥ ትልቅ ከሚባሉት ዘርፎች አንዱ ሲሆን የአዳዲስ እና የታደሱ ህንፃዎች እና መሰረተ ልማቶች ፍላጎት ኢንዱስትሪውን ለቀጣይ አመታት እንዲጠመድ ያደርገዋል።

✳️በህብረተሰቡ ውስጥ እንደዚህ ያለ ጠቃሚ ሚና ያለው ግንባታ ዘላቂ አሰራሮችን በመተግበር እና በአካባቢ ላይ ያለውን ተፅእኖ በመገደብ ረገድ መሪ የመሆን ሃላፊነት አለበት::

@etconp
👍8❤3
Ethio Construction Engineering
👉የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱን 5 ቢሊየን ዶላር ሚያወጣ ‘የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተማ’ ግንባታ በአራት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሠራ መሆኑን ገለጸ፡፡ 🌟አየር መንገዱ “ኤርፖርት ሲቲ” ብሎ የሚጠራውን ግንባታ ለመጀመር ከጫፍ የደረሰው እየጨመረ የመጣውን የደንበኞች ፍላጎት ለማርካት መሆኑን የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የንግድ ሥራ ዘርፍ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ለማ ያደቻ ተናግረዋል፡፡ 🚧የ ‘አየር…
👉አዲሱን የኤርፖርት ሲቲ ግንባታ ዲዛይን የሚያከናውን የአማካሪ ድርጅት መረጣ እስከ መጪው መስከረም ይጠናቀቃል።

🚧የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱን የኤርፖርት ሲቲ  ግንባታ ለማስጀመር ዝርዝር ዲዛይኑን የሚያከናውን አማካሪ ድርጅት መረጣ እስከ መጪው መስከረም እንደሚጠናቀቅ አስታወቀ።

✳️አየር መንገዱ በፍጥነት እያደገ የመጣውን የደንበኞቹን ቁጥር ታሳቢ በማድረግ ዘመናዊና ግዙፍ የኤርፖርት ከተማ ግንባታ እንደሚያከናውን ከ4 ዓመት በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

✳️በኦሮሚያ ክልል ከቢሾፍቱ ከተማ ወጣ ባለ ሥፍራ ላይ የሚገነባው ይህ ፕሮጀክት፥ የካርጎ ሎጂስቲክ ማዕከል፣ ዘመናዊ ሆቴሎችና ከቀረጥ ነጻ የተለያዩ የግብይት ስፍራዎች እንደሚኖረውም ተገልጿል።

🔰የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምክንያቶች በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ሳይጀመር ቆይቷል።

✳️የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት እስከ 25 ሚሊዮን ያህል ብቻ መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ያነሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ ሆኖም የደንበኞች ቁጥር በመጪዎቹ ጥቂት ዓመታት በእጥፍ እንደሚያድግ ይጠበቃል ብለዋል።

✳️በመሆኑም የአየር መንገዱን እድገት እና የመንገደኞችን ቁጥር መጨመር ታሳቢ ያደረገ ግዙፍ አውሮፕላን ማረፊያ (ኤርፖርት ሲቲ) መገንባት የግድ መሆኑን በማመን ወደ ስራ መገባቱን ጠቅሰዋል።

✳️ከቢሾፍቱ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ ስፍራ የሚገነባውን አዲሱን ፕሮጀክት ግንባታ ለመጀመርም የተለያዩ የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል።

✳️ለአብነትም የኤርፖርት ሲቲ ግንባታውን ዲዛይን የሚሰሩ ሁለት አማካሪ ድርጅቶችን ለመቅጠር ይፋዊ ጨረታ መውጣቱን ጠቅሰው፥ የአማካሪዎች መረጣ እስከ መጪው መስከረም  እንደሚጠናቀቅ አመላክተዋል።

✳️ፕሮጀክቱ ከዘገየባቸው ምክንያቶች አንዱ  ኤርፖርት ሲቲው በሚገነባበት ቦታ የሚኖሩ አርሶ አደሮችን ሁኔታ ለማስተካከል ረጀም ጊዜ በመውሰዱ ነው ብለዋል።

✳️በአሁኑ ወቅት አርሶ አደሮቹ ኑሯቸውን የሚመሩበትን ስራ ለመፍጠር የሚያስችል ጥናት መከናወኑን ገልጸዋል።

✳️የአርሶ አደሮቹን ፕሮጀክት ወደ ተግባር ለማስገባትም የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን የታወቀ ሲሆን፥ የፕሮጀክት ዲዛይን የሚሰራ አማካሪ እየመረጥን ነው ብለዋል።

✳️አዲስ የሚገነባው ኤርፖርት ሲቲ ለአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክና ለሞጆ ደረቅ ወደብ ቅርብ በመሆኑ ትልቅ የኢንዱስትሪያል ሎጂስቲክ ማዕከል እንደሚሆንም ተገልጿል።

❇️የኤርፖርት ሲቲ ግንባታ ሲጠናቀቅ በዓመት 100 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም እንዳለውም ነው የገለጹት፡፡

Via ENA

@etconp
👍16❤2
👉የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በአቃቂ ግዙፉን ዋና መስሪያ ቤት ግንባታ በ 1.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ሊገነባ ነዉ

🚧መንግስታዊዉ ነዳጅ አቅራቢ የሆነዉ ድርጅቱ 1.6 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚያደርግበትን ግዙፉን ህንፃ ለመገንባት የኮንትራት ዉል ስምምነት ማድረጉ ታዉቋል።

🚧በአቃቂ የሚገነባው 2B+G+14 ስማርት የችርቻሮ ጣቢያ ዋና መስሪያቤት በ 24 ወራት ዉስጥ ለማጠናቀቅ ዕቅድ መያዙን ካፒታል ሰምቷል።

🔰ኢኢአይጂ ከተባለው ተቋራጭ ጋር የዉል ስምምነት ያደረገው የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ አማካሪ ነዉ።

Via Capital

@etconp
👍13👏9
👉ኢትዮጵያና አዘርባጃን በቤት ልማት ዙሪያ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና የአዘርባጃን ቤት ልማት ኤጀንሲ በቤት ልማት ዙሪያ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ተስማምተዋል፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ እና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማልን ያካተተ ልዑክ ከአዘርባጃን የቤት ልማት ኤጀንሲ አመራሮች ጋር በቤት ልማት ዙሪያ ተወያይቷል፡፡

በውይይቱም የአዘርባጃን የቤት ልማት ኤጀንሲ እና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት በአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ ስምምነት ላይ መድርሳቸው ተገልጿል፡፡

የአዘርባጃን የቤት ልማት ኤጀንሲ በመንግስት መነሻ የኢንቨስትመንት ፋይናንስ ድጋፍ ተደርጎለት ቤቶችን እንደሚገነባ በውይይቱ ወቅት ተነስቷል፡፡

በዚህም ከ30 በመቶ እስከ 40 በመቶ ከገበያው የዋጋ ቅናሽ ያላቸውን ቤቶች ለሀገሪቱ ዜጎች በሽያጭ እያቀረበ ገበያ የማረጋጋት ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው፡፡

ኤጀንሲው ከመንግስት የሚያገኘውን መነሻ የኢንቨስትመንት ፋይናንስ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ ገበያ ለማረጋጋት ለሚገነባቸው ቤቶች ግንባታ እንደሚያውልም ተጠቁሟል፡፡

ያገኘውን የበጀት ድጋፍ ለመንግስት የመመለስ ግዴታ የሌለበት ተቋም መሆኑንም የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከቅረብ ጊዜ ወዲህ የሪል ስቴት ገበያውን ለማረጋጋት እያደረገ ላለው ጥረት የአዘርባጃን የቤት ልማት ኤጀንሲ ያለውን ሰፊ ልምድ እንደሚያጋራ ተገልጿል፡፡

በስምምነቱ መሰረት የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የአዘርባጃን የቤት ልማት ኤጀንሲን ልምድና ተሞክሮ በኢትዮጵያ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡

Via FBC

@etconp
👍10❤2😁2
👉ማርስ ላይ ዘመናዊ ከተማ

🚧በቀጣይ 10 አመታት ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንደሚጀመርና በ30 አመት ውስጥ ማርስ ላይ ዘመናዊ ከተማ እንደሚገነባ የስፔስ ኤክስ መስራች ኤለን መስክ ገልጿል።

✳️የማርስ ከተማ ግንባታን እውን ለማድረግ ስፔስ ኤክስ በርካታ የቅኝት ሳተላይቶችን በቅርቡ እንደሚልክ ማስታወቁን የዴይሊ ስታር ዘገባ ያመላክታል።

🚧"በጥቂት አመታት ውስጥ ሰዎችን በማርስ ላይ የማስፈር ዕቅዳችንን ዕውን እናደርጋለን" ብሏል የ52 ዓመቱ ቢሊየነር ኤለን መስክ።

🚧"ከ10 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንጀምራለን፤ ከበረታን እስከ 20 ዓመት፣ በእርግጠኝነት ግን በ30 ዓመት ውስጥ ዘመናዊ ከተማ በማርስ ላይ እንገነባለን" ብሏል ኤለን መስክ።

🔰እ.አ.አ 2002 የተመሰረተው ስፔስኤክስ ወደ አለማቀፉ የህዋ ጣቢያ ለመጀመሪያ ጊዜ መንኮራኩር እና ጠፈርተኞችን የላከ የግል ኩባንያ ነው።

@etconp
👍14❤1🕊1
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ መቁረጫ መብሻና  ማጠፊያ ማሽኖች አሉን

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ እናበጃለን እንዲሁም እናጥፋለን

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍5❤1👏1
👉የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ከውጭ ከሚመጡ ግብዓቶች ጥገኝነት እንዲላቀቅ ተጠየቀ

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ከውጭ ከሚመጡ ግብዓቶች ጥገኝነት እንዲላቀቅ የዘርፉ ባለሙያዎች ጠየቁ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ‹‹የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ተግዳሮት፣ መውጫ መንገዶችና የሕግ አውጭው ሚና›› በሚል ርዕስ የሚመለከታቸው የዘርፉና የመንግሥት አካላት በተገኙበት የፓናል ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱ የኮንስትራክሽን ባለሙያውና የኢትዮጵያ ሲቪል መሐንዲሶች ማኅበር የቦርድ ሊቀመንበር ውብሸት ዠቅአለ (ዶ/ር)፣ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን በተመለከተ ባቀረቡት የመነሻ ጹሑፍ፣ የኮንስትራክሽን ግብዓቶች በአመዛኙ በገቢ ንግድ ላይ ጥገኛ በመሆናቸው በአማካይ ከ30 በመቶ በላይ የውጭ ምንዛሪ እንደሚጠይቁ አስረድተዋል፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በገቢ ምርቶችና በውጭ ምንዛሪ ላይ ጥገኛ መሆኑና ዓለም አቀፍ ገበያውም በበቂ ደረጃ ተገማች ባለመሆኑ፣ የገበያ ዋጋ ሲንር፣ አለመግባባት ሲከሰት፣ የውጭ ምንዛሪና የፀጥታ ችግር ሲፈጠር በቀላሉ የሚጎዳ እየሆነ ነው ብለዋል፡፡

ተቋማዊ ያልሆነና በግለሰቦች ላይ የተንጠለጠለ የኮንስትራክሽን ኩባንያና አሠራር ችግር አለመቀረፉ፣ ፍላጎትና አቅርቦት አለመመጣጠኑ፣ በመንግሥት የገንዘብ ምንጭ ላይ ጥገኛ መሆኑ፣ እንዲሁም የኢንዱስትሪው ዋና ዋና ባለድርሻዎች አለመቀናጀትና የአቅም ውስንነት መኖሩ፣ ያልተገባ የአሠሪ ጣልቃ ገብነት የሚበዛበት መሆኑ በዘርፉ ላይ አደጋ ተደቅኖበታል በማለት ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ የመወያያ ጽሑፍ ያቀረቡት የኢትዮጵያ የአማካሪ መሐንዲሶችና አርክቴክቶች ማኅበር የቦርድ ፕሬዚዳንት ዳዊት ኡርጌቾ (ዶ/ር)፣ ‹‹የኢንዱስትሪው ቀጥተኛ ባለድርሻዎች ምልከታ›› በሚል ባቀረቡት የጥናት ጹሑፍ፣ ከውጭ በሚገቡ የግንባታ ግብዓቶች ላይ ጥገኛ መሆንና የምንዛሪ እጥረት፣ እንዲሁም የኢንዱስትሪው የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ከጊዜና ከዋጋ አንፃር ከታለመው በላይ መሆን የዘርፉ ትልቁ ማነቆ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት፣ ጥናቶችንና ምርምሮችን በተቀናጀ መንገድ በማካሄድ ምርጥ ተሞክሮዎችንና የአሠራር ሥርዓቶችን ለማስረፅ ውስንነት መኖሩ፣ ከዩኒቨርሲቲዎች የሚመረቅ የሰው ኃይል በብዛት ቢኖርም የሚታየውን የክህሎት ክፍተት ለመሙላት አለመቻልና የመሳሰሉትን ችግሮች ጠቅሰዋል፡፡

ዘርፉ እንዲሻሻል ለግንባታ ዕቃዎች፣ ግብዓቶችና ምርቶች ከዓለም አቀፍ ደንቦች ጋር የሚስማማ የኢንዱስትሪ አቀፍ ወጥ ብሔራዊ ደረጃ ማዘጋጀት፣ የአገር ውስጥ ምርቶችን በዓይነትም ሆነ በጥራት ለማስፋፋት የቴክኖሎጂ ሽግግርን፣ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ልዩ መብቶችንና የፋይናንስ አቅርቦትን በጥናት ላይ በመመረኮዝ ማመቻቸትና የአገር ውስጥ ምርቶችን/ግብዓቶችን ለማሻሻልና ለማስፋፋት ለምርምርና ለልማት ፈንድ መመደብ እንደሚስፈልግ ተናግረዋል፡፡

ውብሸት (ዶ/ር) በሰጡት አስተያየት ትላልቅ የኮንስትራክሽን ኩባንያዎችን በማቋቋም ከአገር አቀፍ እስከ ዓለም አቀፍ የዕድገት አቅጣጫዎችን መተለይም፣ ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ ተወዳዳሪነትንና ምርታማነትን ያማከሉ የዕድገት አቅጣጫዎች ማካተት፣ የመንግሥት ቀጥተኛ ተሳትፎ ማጠናከር፣ የመንግሥትና የግል ትብብርና ድርሻ እያደገ የሚመጣበት ከቁጥጥር ወደ ማስቻል ተኮር የሚሸጋገርና ከአገር ወደ ዓለም አቀፍ ውድድር የሚያድግ ሥርዓት እንዲፈጠር ጠይቀዋል፡፡

@etconp
👍15❤1
👉ዱባይ የዓለማችንን ግዙፍ አየር ማረፊያ እየገነባች ነው

ዱባይ የዓለማችንን ትልቁን አየር ማረፊያ ተርሚናል ኮምፕሌክስ መገንባት ጀምራለች ሲሉ የኢሚሬቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ መሀመድ ቢን ራሺድ አል ማክቱም ተናግረዋል።

"አል ማክቱም ኢንተርናሽናል" ተብሎ የሚጠራው የዱባዩ አዲሱ ኤርፖርት አምስት የተርሚናል ህንጻዎች ያሉትና 35 ቢሊየን ዶላር የሚፈጅ ሲሆን፣ ከዱባይ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአምስት እጥፍ ይበልጣል። 260 ሚሊዮን መንገደኞችን በአመት የመቀበል አቅምም ይኖረዋል።

በዓለም ላይ በጣም የተጨናነቀ አውሮፕላን ማረፊያ በአትላንታ ሃርትስፊልድ-ጃክሰን የሚገኘው የአሜሪካ ማዕከል ሲሆን፣ ይህም ወደ 105 ሚሊዮን የሚጠጉ መንገደኞች ያስተናግዳል።

ሁለተኛው በጣም የተጨናነቀው ዱባይ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ሲሆን አመታዊ መንገደኞች የመቀበል አቅሙ 87 ሚሊዮን ነው። ይሁን እንጂ ይህ ነባር ኤርፖርት በዙሪያው ባሉ ሰፋፊ ዕድገቶች የተገደበ በመሆኑ፣ በቀጣይ ሁሉም የኤርፖርት ሥራዎች በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ ወደ አል ማክቱም ይዘዋወራሉ።

የአል ማክቱም አውሮፕላን ማረፊያው የመጀመሪያ ምዕራፍ የተከፈተው በ2010 ዓ.ም ነበር። ኤርፖርቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በ70 ካሬ ኪሎ ሜትር ቦታ ላይ 400 በሮች እና አምስት ትይዩ የማኮብኮቢያ ሜዳዎች ይኖሩታል።

ከዚህም በላይ፣ የአንድ ሚሊዮን ሰዎች መኖሪያ ያላት ከተማ በኤርፖርቱ ዙሪያ ይገነባል። ይህ የሎጂስቲክስ ኩባንያዎችን ለመሳብ ያለመ ይሆናል።

ሼክ መሀመድ እንዳሉት "ለልጆቻችን ቀጣይነት ያለው እና የተረጋጋ ዕድገትን በማረጋገጥ ለመጪው ትውልድ ግዙፍ ፕሮጀክት እየገነባን ነው። ዱባይ የዓለም አውሮፕላን ማረፊያ፣ ወደብ፣ የከተማዋ ማዕከል እና አዲስ ዓለም አቀፍ ማዕከል ትሆናለች ሲሉ ገልጸዋል።

@etconp
👍10👏8❤3
👉ትልቁ ከተማ

🔰ቶክዮ፣ ጃፓን

🚧ቶክዮ በአለም ላይ ትልቋ ከተማ ስትሆን 37.4 ሚልዮን ህዝብ አሏት።

📌ስፋቷም 13,452 ካሬ ኪሎሜትር ነው።

@etconp
👍13❤1👌1
Intercon Construction Materials 
    
👉 Specialized in construction chemicals, Authorized agent of MC (Conmix) and Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofing Chemicals and Materials (Cementitious, Acrylic,  Crystalline, Bituminious and Liquid membrane, Liquid Glass, Sealants)
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● External finishes (Quartz paint, Contextra),
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy, Self-level              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
❤4👍2💔1
👉ስለ ንኡስ ተቋራጭነት (sub-contract) ጥቂት መረጃ እናጋራችሁ

🚧ንኡስ ተቋራጭነት(sub-contract) በፍትሀብሄር ህጉ አገላለጽ ከዋናው ተቋራጭ የተስማማ ሁለተኛ ተቋራጭ ይባላል፡፡

⏺ይሄውም ዋናው ተቋራጭ የግንባታ ውሉን ስራ በከፊል ለማስፈጸም ከአንድ ሶስተኛ ወገን ከሆነ ሰው ጋር የሚደረግ ነው፡፡(የፍ/ህ/ቁ 3201(2))

🔰ውሎችን ለሌላ መልቀቅ(Assignment) ደግሞ ዋናው ተቋራጭ የግንባታ ውሉን ስራ በሙሉ እንዲፈጽምለት ለአንድ ሶስተኛ ወገን ለሆነ ሲያስተላልፍ ነው፡፡(የፍ/ህ/ቁ 3201(1))

⏺ስለዚህ ንኡስ ተቋራጭነት የግንባታ ስራ ተቋራጮች ከአሰሪው ጋር ሊገነቡት ግዴታ የገቡበትን የግንባታ ስራ በከፊል ለሌላ ተቋራጭ በውል በሚያሰሩበት ጊዜ የሚነሳ ጉዳይ ነው፡፡

❇️ውሎችን ለሌላ መልቀቅ የሚባለውም ከንኡስ ተቋራጭነት ጋር ሁኔታው አንድ አይነት ሲሆን ልዩነቱ ዋናው ተቋራጭ ለሌላ ተቋራጭ የሚያሰራው ሙሉውን የግንባታ ስራ ነው፡፡

☄ንኡስ ተቋራጭነት ሁለት አይነት ነው፡፡

📌በአሰሪው የሚታወቅ (Nominated sub-contracting) እና በአሰሪው የማይታወቅ (Non nominated sub-contracting)::

⏺ከውጤት አንጻር ተመሳሳይ ቢሆኑም ንኡስ ተቋራጭነቱን አሰሪው የፈቀደውና ያወቀው የሆነ እንደሆነ ልዩነቱ ዋናው ተቋራጭ ከመዘግየት ቅጣት ነጻ ይሆናል፡፡(የፍ/ህ/ቁ 3206)

✅ንኡስ ተቋራጮች ለሰሩበት ክፍያ ከማን መጠየቅ ይችላሉ?

✋ንኡስ ተቋራጮች ለሰሩት ስራ በውላቸው መሰረት ከዋናው ተቋራጭ ክፍያ የመጠየቅ መብት ይኖራቸዋል፡፡(የፍ/ህ/ቁ 1755፣1756) ምክንያቱም ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል ህግ ነው፡፡(የፍ/ህ/ቁ1731)

⏺በተጨማሪም የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3040 በአንድ የህንጻ ስራ ተቋራጭነት ውስጥ የሚሰሩ ስራ ተቋራጮች ወይም ሰራተኞች የሰሩበትን ስራ ዋጋ ለመከፈል ክሳቸውን ባቀረቡበት ጊዜ አሰሪው ለስራ ተቋራጩ ሊከፍል በሚገባው ገንዘብ መጠን ባሰሪው ላይ በቀጥታ ገንዘባቸውን ለመጠየቅ መብት አላቸው በሚል ይደነግጋል፡፡

📌ስለዚህ ከዋናው አሰሪ ላይም በቀጥታ ክፍያ ለመጠየቅ መብት ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡

#ConstructionLaw

@etconp
👍21❤2