Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉አርኖ ሩሱቩዎሪ (Aarno Ruusuvuori 1925-1992 እኤአ)

✳️የልማት ባንክ ህንጻ ነዳፊ

❇️አርኖ ሩሱቩዎሪ ፊንላንዳዊ ህንጻ ነዳፊ፣ ፕሮፌሰር እና የፊንላንድ የኪነህንጻ ቤተመዘክር ስራአስኪያጅ ነበር።

❇️ሩሱቩዎሪ በፊንላንድ እኤአ  በ1960ዎቹ ስመጥር ህንጻ ነዳፊ የነበረ ሲሆን ዘወትር በጥሬ ኪነህንጻ ዘይቤ (brutalism) የተጋለጡ የአርማታ ንድፎችን በዘመናዊው ፍልስፍና በመንደፍ   የሚታወቅ ነዳፊ ነበር።

🔰አዲስ አበባ በተለምዶ ሱፐር ማርኬት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ1960ዎቹ አጋማሽ ልማት ባንክ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚገኙበትን በተጋለጠ አርማታ፣ በድግግሞሽ መርህ (modularization) እንዲሁም በሰፋፊ የአእማድ ርቀት የተገነባውን አስገራሚ ህንጻ ሩሱቩዎሪ ነበር የነደፈው።

@etconp
👍9
👉የአዲስ አበባ ካቢኔ 3ኛ ዓመት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ካፀደቃቸው ጉዳዮች አንዱ የመንገድ ሴት ባክ (Set Back) አጠቃቀምን በተመለከተ ከላይ ያለው ይመልከቱ

@etconp
👍8❤3😁2
👉ታሪካዊ ኪነ ህንጻ

☄ቤተጊዮርጊስ ላሊበላ

📌ቤተጊዮርጊስ እንደኪነህንጻው ሁሉ አገባቡና መዳረሻውም አጓጊ እንዲሆን ታስቦ ተነድፏል።

🔰በሰያፍ ተዳፋት ከተወረደ በኋላ ፐ ቅርጽ ያለው መገናኛ ይደረሳል ከዝያም ወደቀኝ ሲታይ ፈንጠር ብሎ የሚታየው የቤተክርስትያኑ ደጅ መዳረሻውን ያመለክታል።

@etconp
❤6👍3
👉ቻይና በዓለም ትልቁን የትስስር አውራ ጎዳና መገንባቷ ተገለጸ

ቻይና በዓለም ትልቁን የትስስር አውራ ጎዳና በከፍተኛ ወጪ መገንባቷ ተመላክቷል፡፡

የቻይና የማሳለጫ መንገዶች ርዝማኔ በፈረንጆቹ 2023 ከ6 ሚሊየን ኪሎ ሜትሮች በላይ ማደጉ ተገልጿል፡፡

ይህም በዓለም ትልቁ የፍጥነት ባቡር፣ የፈጣን መንገድ ኔትወርክ፣ የፖስታ ኤክስፕረስ ማከፋፈያ አውታር እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የወደብ መገልገያ ትስስር ያለው መሆኑን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አመልክቷል።

የሀገሪቱ የትራንስፖርት ዘርፍ ፈጣን እድገት በማስመዝገብ ለቻይና ኢኮኖሚ እድገት መሰረት የሆነውን ጠንካራ የትራንስፖርት አገልግሎት በማቀጣጠል ላይ እንደሚገኝም ነወ የተገለጸው።

በፈረንጆቹ 2023 ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ያሳየው ዘርፉ÷ 3 ነጥብ 91 ትሪሊየን ዩዋን ወይም 539 ቢሊየን ዶላር ቋሚ የንብረት ኢንቨስትመንት ዕድገት ማሳየቱ ተመላክቷል፡፡

በዚህም ዘርፉ ከዓመት ወደ ዓመት 1 ነጥብ 5 በመቶ እድገትን እያሳየ መሆኑን ጠቁሟል።

በፈረንጆቹ 2023 መገባደጃ ላይ ቻይና 159 ሺህ ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና ከዚህም ውስጥ 45 ሺህ ኪሎ ሜትሩ ለፈጣን ጉዞ የተወሰነ በዓለም ትልቁን የባቡር መስመር ዘርግታለች።

የሀገሪቱ የመንገድ አውታር መስፋፋትም 5 ነጥብ 44 ሚሊየን ኪሎ ሜትር የደረሰ ሲሆን÷ ከዚህም ውስጥ 183 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር የሚሆኑት ነፃ ጎዳናዎች መሆናቸውን የሲጂቲኤን ዘገባ አመላክቷል።

በተጨማሪም ቻይና በ2023 አምስት አዳዲስ የንግድ አውሮፕላን ማረፊያዎችን በማከል አጠቃላይ ድምሩን 259 ማድረሷ ተጠቁሟል።

@etconp
👍13👌3
Maximum size of coarse aggregates for the construction of highway embankment is restricted to (mm)
Anonymous Quiz
29%
50
25%
20
38%
75
7%
85
👍21😢2
👍10🙏1🕊1
Intercon Construction Materials 
    
👉 Specialized in construction chemicals, Authorized agent of MC (Conmix) and Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofing Chemicals and Materials
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● External finishes (Quartz paint, Contextra),
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy, Self-level              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍4
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ መቁረጫ መብሻና  ማጠፊያ ማሽኖች አሉን

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ እናበጃለን እንዲሁም እናጥፋለን

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
🙏3👍2
ካዳስተር ማለት ምን ማለት ነው?

ካዳስተር ማለት መሬት ይዞታን መሰረት ያደረገ የመሬት መረጃ ሥርዓት ሲሆን የሚደራጁት መረጃዎችም በዋናነት ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡

ይኸውም የካርታ መረጃ (spatial data) የይዞታውን መገኛ ቦታ፣ ወሰኑን፣ ስፋቱንና ቅርፁን፣ አጎራባች ይዞታዎችን እና አዋሳኝ መንገዶችን የሚያሳይ ሲሆን ሌላኛው ገላጭ መረጃ (non-spatial data) በመባል የሚታወቀው የባለይዞታውን ማንነት (ስም፣ አድራሻ፣ ጾታ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ ወዘተ.)፣ በይዞታው ላይ ያለው መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት፣ የቦታው አገልግሎትና ደረጃ፣ ወዘተ… እንደ ካዳስተር ዓይነቱ ተዘርዝረው የሚያዙ መረጃዎችን ያካትታል፡፡

እነዚህ ሁለት የመረጃ ዓይነቶችም በልዩ የይዞታ መለያ ኮድ እንዲገናኙ ይደረጋል፡፡

ካዳስተር በሦስት ዓይነት ይከፈላል፡- አንደኛው ህጋዊ ካዳስተር ሲሆን ለእያንዳንዱ ህጋዊ ወሰን ለተለየለት ይዞታ፣ የይዞታ መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት የሚያመለክት መረጃ ከይዞታው ካርታ ጋር አጣምሮ የያዘ ወቅታዊ የመሬት ይዞታ መረጃ ሥርዓት ሲሆን አስፈላጊነቱም ዬትኛው ይዞታ በማንና በምን አግባብ ተይዟል የሚለውን በማጣራት የባለይዞታውን የይዞታ ዋስትና ለማረጋገጥ ነው፡፡

ሁለተኛው ዓይነት ፊስካል ካዳስተር ሲሆን በይዞታው ላይ ስላረፈው ቋሚ ንብረት ዝርዝር መረጃ እና የመሬቱን ወቅታዊ ግምት ከይዞታው ካርታ ጋር የሚይዝ ሆኖ ለቦታና ለንብረት ግብር ክፍያ የሚያገለግል ሥርዓት ነው፡፡

ሦስተኛው ዓይነት ካዳስተር ሁለገብ/ሁሉን አቀፍ ካዳስተር/ የሚባለው በሁለቱ የካዳስተር ዓይነቶች የተገለፁትን መረጃዎች የሚይዝ ሆኖ በተጨማሪም የመሰረተ ልማት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ሌሎች መረጃዎችን እና ካርታን አካቶ የሚይዝ የመረጃ ሥርዓት ነው፡፡

የካዳስተር ሥርዓት በመገንባት ሂደት በርካታ ልምድ ያላቸውና ብዙ ርቀት የሄዱ አገሮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በዚህ የግንባታ ሂደት እያንዳንዱ አገር ከራሱ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር አጀማመሩና አካሄዱ የተለያየ ነው፡፡

አንዳንድ ሀገሮች ከፊስካል ካዳስተር ጀምረው ወደ ሁለገብ የሄዱ አሉ ለምሳሌ ፈረንሳይ፤ ሌሎች ደግሞ ከህጋዊ ካዳስተር ጀምረው ወደ ሁለገብ የካዳስተር ሥርዓት የተሸጋገሩበት ሁኔታም አለ ለምሳሌ ኔዘርላንድ፡፡

በእኛ አገር ደረጃም ከዚህ ቀደም በከተማ ደረጃ ሥርዓቱን ለመዘርጋት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ የተሞከሩትም ሁለገብ ካዳስተርን በመዘርጋት ነበር ሆኖም ግን የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣና የሥርዓቱን ዘለቄታዊነት የሚያረጋግጥ ሊሆን አልቻለም፡፡

በመሆኑም በቅድሚያ ባለይዞታውን ተጠቃሚ የሚያደርገው ከተማ አስተዳደሮችም መሬታቸውን ቆጥረው ሊያውቁ የሚችሉበትን የህጋዊ ካዳስተር በመዘርጋት በመቀጠልም የፊስካል ካዳስተር ብሎም ወደ ሁለገብ ካዳስተር የሚያድግ ሥርዓት መዘርጋቱ ሥርዓቱን ቀጣይ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ ተመርጧል፡፡

በዚህ ሂደት የካርታው መረጃ አንድ ጊዜ የሚዘጋጅ ሲሆን ለውጥን ተከትሎ ወቅታዊ ማድረግ የሚያስፈልግ ሆኖ ሁሉም የካዳስተር ዓይነት መሰረት የሚያደርገው በህጋዊ ካዳስተር የተዘጋጀውን የካዳስተር ካርታ ነው::

@etconp
👍14❤3
112. The highest CBR number is required for __________
Anonymous Quiz
25%
A. Base
20%
B. Sub base
19%
C. Pavement
36%
D. Sub grade
👍23😢2
Which type of bond can be made for 10 cm thick wall-
Anonymous Quiz
35%
English bond
19%
Flemish bond
17%
Heading bond
29%
Stretching bond
👍17🙏3
👉በሀዋሳ እንደ አዲስ አበባው አይነት የመንገድ ማስፋትና የማስዋብ ስራ / የኮሪደር ልማት / መታሰቡን ተከትሎ " የሚፈርሱ ይዞታዎቻችን ግምት ባልታወቀበት እና በቂ የሆነ የዝግጅት ጊዜ ባልተሰጠበት ይዞታችሁን አፍርሱ " ተብለናል ያሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ስራው ወደተግባር ከመግባቱ በፊት ካንዴም ሁለቴ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት ማድረጉን ገልጿል።

በቅርቡ በነበረ መድረክ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ መኩሪያ ማርሻዬ á¤ 10 መንገዶች መለየታቸውን እና እነዚህን ውብና ዘመናዊ አድርጎ በመስራት ለትዉልድ የሚተላለፍ አሻራ የመጣል እቅድ መያዙን ገልጸው ነበር።

በመድረኩ ተገኝተው የነበሩ ነዋሪዎች ልማቱን እንደሚደግፉ የካሳ እና የዝግጅት ጊዜ ግን እንዲሰጣቸዉ ጠይቀው ነበር።

ይህን ተከትሎ የንብረት ግምትን በተመለከተ ተመጣጣኝ ካሳ እንደሚኖርና የቦታ ሽግሽጎችም እንደሚደረጉ በመግለጽ ከንቲባዉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ይሁንና የከተማ መስተዳድሩ ከመረጣቸዉ 10 ቦታዎች መካከል 3ቱን ባጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ ማሰቡን ተከትሎ በተለይ ከስሙዳ በሳዉዝ ስታር ሆቴል ወደ ኢንዱስትሪ መንገድ የሚሄደው እና ከሻፌታ አደባባይ አስከሳዉዝ ስፕሪንግ ያለው መስመር ያሉ ነዋሪዎች ጥያቄ እንዳላቸው ገልጸዋል።

በዚህ በኩል በርካታ የመኖሪያ ቤቶች፣ ድርጅቶችና ትምህርት ቤቶች የሚነኩ መሆኑን ተከትሎ ነዋሪዎች ድንጋጤ ውስጥ መግባታቸዉን ተናግረዋል።

በከተማ መስተዳድሩ በእቅድ የተያዘዉ  የከተማ ልማት የምንደግፈዉ ቢሆንም የካሳና የቦታ ሽግሽግ ጉዳይ ባልተወሰነበትና ሰዉ ዝግጅት ባላጠናቀቀበት " በቅርቡ ፈረሳ ይጀምራል " መባሉ አሳስቦናል ብለዋል።

ነዋሪዎቹ በተሰጣቸው ደብዳቤ በ2 ቀን ውስጥ አፍርሰው ማስተካከያ እንዲያደርጉ መባላቸውን ጠቁመዋል።

በተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ የሚፈርሱ ድርጅቶች መኖሪያ ቤቶችና አጥሮች ምልክት በመደረጉና ስራውበፍጥነት ይጀመራል መባሉን ተከትሎ ፦
➡️ የካሳና የቦታ ለዉጥ ወይም ሽግሽግ ጉዳይ ምን ይመስላል ?
➡️ በትክክል ስራዉስ መች ይጀምራል ? በማለት ጥያቄ ይዘን የሚመለከተዉን አካል ለማናገር ያደረግነዉ ጥረት አልተሳካም።

Via Tikvah

@etconp
👍8😢2
👉ከግንባታ ፕሮጀክቶች ጋር ተያይዞ ስለሚሰጡ የዋስትና ዓይነቶች መጠነኛ ገለጻ [Construction Security]

🌟ክፍል አንድ

▶️በውል አፈጻጸም ወቅት የተለያዩ ዋስትናዎች ሲተገበሩ ይስተዋላል፡፡

⏺ለምሳሌ፡-
-የግምጃ ቤት ሰነድ (treasury bill)

-ማገቻ(bond)

-በቅድመ ሁኔታ የሚሰጡ ዋስትናዎች (conditional guarantees)

-ያለቅድመ ሁኔታ የሚሰጡ ዋስትናዎች (on demand/Unconditional guarantees)

- የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና (Bid security)

-የቅድመ ክፍያ ዋስትና((Advance security bond)

-የሰው ዋስትና (surety ship)

-የንብረት ዋስትና (pledge or mortgage)

-ራሳቸውን የቻሉ የብድር ሰነዶች ወይም ክሬዲት (Standby letters of credit) ወዘተ የመሳሰሉት ናቸው፡፡

አብዛኛውን ከላይ የተባሉት የዋስትና ሰነዶች በገንዘብ አበዳሪ ተቋማት እና ኢንሹራንስ ድርጅቶች ይዘጋጃሉ፡፡

ነገር ግን የሰው እና የንብረት ዋስትና ግን በግራ ቀኝ ተዋዋይ ወገኖች በራሳቸው አሊያም በሌላ ሦስተኛ ወገን አላፊነት ሊከናወኑ ይችላል፡፡

በውል አፈጻጸም ወቅት የዋስትና መኖር በተዋዋዮች ዘንድ ከፍተኛ መተማመን እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ሌላው የውሉን አፈጻጸም ተጠባቂ (predictable) እንዲሆን ያደርጋል፡፡

በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪም አንድ የፕሮጀክት ባለቤት ሥራው በተያዘለት ጊዜ እንዲያልቅ በማሰብ የፕሮጀክት አፈጻጸም ዋስትና አስፈላጊነት ትዝ ካለው፤ ለፕሮጅቱ የሚመቸውን የዋስትና ዓይነት ማለትም የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና፣ በገንዘብ አበዳሪ ተቋማት የሚዘጋጅ ዋስትና ወይም ክሬዲ አንዳንዴ ደግሞ የፕሮጀክቱን ክፍያ ገንዘብ በፐርሰንት መያዝ (retention) እንዲኖር ሊያስብ ይችላል፡፡

የሆነው ሆኖ እነዚህ የዋስትና መንገዶች ተመሳሳይ ዓላማ አላቸው፡፡ ይህም በተዋዋዮች መካከል መተማመን እና ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎች (risk) በመቀነስ ግብይትን ማፋጠን ነው፡፡ ዳሩ ግን እያንዳንዳቸው የራሳቸው ባህሪይ አላቸው ብሎም በአፈጻጸም እና አተገባበር የተለያዩ ናቸው፡፡ ስለሆነም አሰፈላጊነታቸው መታየት ያለበት እንደየ ፕሮጀክቱ አካሄድ፣ መጠን እና ጊዜ ሊሆን ይቻላል፡፡

በዓለምአቀፍ ደረጃ ባሉ ግብይቶችም የዋስትና ሰነዶች በጣም የተለመዱ ናቸው፡፡ በተለይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) የዋስትና ወረቀቶች እና ክሬዲ ሥምምነት (UN Convention on Independent Guarantees and Standby Letter of Cedit) በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ነው፡፡

ይህ ዓለምአቀፍ ሥምምነት እኤአ በ1995 በአሜሪካዋ የኒዮርክ ከተማ ለሥምምነት ክፍት የሆነ ሲሆን 8 (ስምንት) አገራት በመፈረምና በማጽደቅ ተቀብለውታል፡፡ ኢትዮጵያ ግን የዚህ ሕግ ፈራሚ አገር አይደለችም፡፡

ሆኖም ግን ይህ ሥምምነት በዓለምአቀፉ የንግድ ሕግ ኮሚሽን (United Nations Commission on International Trade Law/UNCTRAL) እንደመዘጋጀቱ መጠን ዋስትናን በተመለከተ በቀጣይ ሌሎች የዓለም ሀገራት ለሚያዘጋጇቸው ዝርዝር ህጎች በሞዴልነት እንደመነሻ ሊያገለግል ይችላል፡፡ በተለይ ስምምነቱን የፈረሙ አገራት በዓለምአቀፍ ደረጃ ለሚያከናውኗቸው የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ላይ ዋስትናን በተመለከተ ይህ ሕግ ተፈጻሚ ነው፡፡

ሌላው ዋስትና ሲነሳ ምንጊዜም ቢሆን አብሮ የሚነሳው የመድን ውል (insurance) ነው፡፡ ዋስትናም (security/guarantee) ሆነ መድን አንድ የሚያደርጋቸው ነገር አለ፡፡ ይህም ሁለቱም ባለመብቱን ሊደርስ ከሚችል የአደጋ ስጋት መጠበቃቸው ነው፡፡

ሆኖም ግን በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ሁለቱም የተለያየ የሕግ ውጤት ያላቸው ተግባራት ናቸው፡፡

ዋስትና:
በዋስትና ተግባር ዋስ የሚሆነው ግለሰብ የሚጠበቅበት ግዴታ ቢኖር ባለእዳው ለባለገንዘቡ በውል መሰረት ካልከፈለ ወይም መክፋል ካልፈለገ በሕግ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን ጠብቆ በባለእዳው እግር ተተክቶ ዕዳውን ሊወጣ የሚችልበት ሁኔታ ነው፡፡

መድን: 
መድን የገባ ሰው  መደበኛ የሆነ አረቦን (premium) መክፈል እንደተጠበቀ ሆኖ መድን በተገባለት ጉዳይ ሊደርሱ የሚችሉ  አደጋዎችን ይፋ ማድረግን ጨምሮ የመድን ጥቅም (insurable interest) ሊኖረው ግድ ይላል፡፡

በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪም ከላይ የጠቀስናቸው የዋስትና ዓይነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ አስፈላጊነታቸው እየታመነበት ስለመጣ በፕሮጀክት አፈጻጸም ወቅት ሲተገበሩ ይታያል፡፡

📌በ ክፍል ሁለት የዋስትና ምንነት ትርጉም እናያለን።

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

YouTube:- https://youtube.com/@Etconp432

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=

Twitter :- https://twitter.com/etconpc?s=21&t=_pdndPJF1qt6WZkNGOtqCg
👍19❤2🎉1🙏1🕊1
Intercon Construction Materials 
    
👉 Specialized in construction chemicals, Authorized agent of MC (Conmix) and Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofing Chemicals and Materials
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● External finishes (Quartz paint, Contextra),
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy, Self-level              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍5❤1
👉Building Spatial Design
Definition

🚧Accessible - a site, building, facility or portion thereof that can be approached, entered and used by physically disabled persons.

🚧Approved - approved by the building official having jurisdiction.

🚧Balcony - a horizontal projection, including a hard nail, or balustrade to serve as an outside space.

🚧Basement - that portion of a building that is partly or completely below grade.

🚧Building line - the line established by law, beyond which a building shall not extend, except as specifically provided by law.

🚧Building official - the officer or other designated authority charged with the administration and enforcement of this code, or duly authorized representative.

🚧Court - an open, uncovered space, unobstructed to the sky, bounded on three or more sides by exterior building walls or other enclosing devices.

🚧Combination sign - a sign incorporating any combination of the features of pole, projecting and roof signs.

🚧Dwelling - a building that contains one or two dwelling units used, intended or designed to be used, rental, leased, let or hired out to be occupied for living purposes.

🚧Exit - a passage or means of egress from any building, storeys or floors to street or other open space of safety.

🚧Fire door - a door and it's assembly so constructed and assembled in place as to give protection against the passage of fire.

@etconp
👍19