Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
✨Looking for premium materials for your next project? EKT Ceramics offers top-quality SPC flooring for durability and style, UV boards with a sleek, easy-to-maintain finish, and PVC ceilings that are lightweight, moisture-resistant, and easy to install. Complete your space with our SPC skirting, perfectly designed to match your flooring.

✨Trust EKT Ceramics for competitive prices, excellent customer service, and a comprehensive selection of products. Visit us today and start building your dream space!

📍Head Office
Location: Derar Mall 9th floor opposite to Sahlite Mihret Church

📱+251 929 93 0206
📱+251 929 53 1707  

www.ektceramics.com

#EKTceramics #ethiopia #theklinker #ektceramics #construction #admixture #ceramic #paint #sika #jotun #aquapa #primacera #hanbon #tesaassaabloy #spc #tiles #pprpipe #doorlock #sanitarywares #buildingmaterials
👍2🕊2❤1
🔰የመንገድ ደህንነት

👉ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ የሚፈስበት የመንገድ ሃብት የሚጠበቅበትን አገልግሎት እንዲሰጥ ተገቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ ያስፈልገዋል፡፡

ይህን ተግባር መፈጸም  የሁላችንም ኃላፊነት እንደሆነ የሚዘነጋ ጉዳይ አይደለም።

መንገዶችን ለብልሽት ከሚዳርጉ ምክንያቶች አንዱና ዋነኛው ከተፈቀደው ክብደት በላይ በመጫን መጓዝ (Axels load) ነው ።

በዚህም ረገድ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ከባድ ጭነትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ  ሚዛን ጣቢያዎችን በማቋቋም እንደሚሰራ ይታወቃል።

የተሽከርካሪዎችን ክብደት የመቆጣጠር ዋና አላማ በመንገዶች ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ከተፈቀደላቸዉ የአክስል ክብደት መጠን በላይ ጭነዉ በከፍተኛ ወጪ የተገነቡ የመንገድ አዉታሮች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ የመከላከል እንዲሁም መንገዶች እና ድልድዮች ሳይበላሹ በዲዛይኑ መሰረት አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ማድረግ ነዉ፡፡

በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የሚዛን ጣቢያዎች እና መገኛ ቦታቸው፡-
14 ሚዛን ጣቢያዎች በተለያዩ ቦታዎቸ ተቋቁመው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን ፣ መገኛ አካባቢያቸውም፡- ሞጆ ፣ ሆሎታ ፣ ሱሉልታ ፣ ሠንዳፋ ፣ ዲማ (ሰበታ) ፣ ጂማ ፣ ሻሸመኔ ፣ አዋሽ ፣ ሠመራ ፣ደንገጎ ፣ ኮምቦልቻ ፣ ጢቅ (ደጀን) ፣ወረታ ፣ ኩይሓ (መቀሌ) ናቸው።
በተለይም የአዋሽ 7 እና የሠመራ የሚዛን ጣቢያዎች ከፍተኛ የሆነ የወጪ እና ገቢ ንግድን ያስተናግዳሉ ይህ መስመር ከባባድ መኪኖች ከጅቡቲ ወደ መሃል ሀገር የሚመላለሱበት እና በቀን ውስጥ በርካታ ተሽከርካሪዎችን የሚያስተናግድ ዋና አውራ ጎዳና ነው። 

በመስመሩ ከተፈቀደው መጠን በላይ በመጫን የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች የሚስተዋሉ በመሆኑ መንገዱ ለከፍተኛ ጉዳት እየተዳረገ ይገኛል፡፡

ይህንን ክፍተት ለመዝጋት ትርፍ የጫነ ተሽከርካሪ ጉዞውን መቀጠል የሚችለው ለጫነው ትርፍ ጭነት ተገቢውን የቅጣት ክፍያ ከከፈለ በኋላ ትርፉን እንዲያራግፍ አሊያም በሌላ ተሽከርካሪ ጭኖ እንዲወስድ ህጉ ይደነግጋል፡፡ 

🏷ለእያንዳንዱ አክስል የሚፈቀድ የክብደት መጠን

I. የነጠላ አክስል (Axle) ሁለት ወይም ሶስት ጎማዎች የተገጠሙለት ተሽከርካሪ የፊት እና የኋላ የአክስል (Axle) ክፍሎች ጠቅላላ የክብደት መጠን የሚከተለዉ ነዉ፡-

ሀ) የፊት አክስል (የመሪ አክስል) Steering Axle የማይፈቀድ የክብደት መጠን ከ7.7 ቶን (77 ኩንታል) የበለጠ እንደሆነ ፤  

ለ) ከመሪዉ አክስል (Steering Axle) ዉጪ ሆኖ ነጠላ ጎማ የተገጠመለት ተሸከርካሪ ከሆነ ጠቅላላ ክብደቱ ከ8 ቶን (80 ኩንታል) የበለጠ እንደሆነ ነዉ፡፡  

ሐ) የኃላዉ የአክስል ክፍል አራት ጎማዎች የተገጠሙለት ከሆነ የአክስል ክብደቱ ከ10 ቶን (100 ኩንታል) የበለጠ እንደሆነ ነዉ፡፡  

II. የተሸከርካሪዉ የአክስል ክፍል ባለ ሁለት (Tandem Axle Unit) ወይም ባለሶስት (Tri-dem axle) ሲሆን ፣ ለተሽከርካሪዉ የማይፈቀድ የአክስል (Axle) የክብደት መጠን እንደሚከተለዉ ነዉ፡-  

ሀ) የጥንድ አክስል (Steering Tandem Axle) ክብደት ሳይጨምር ጠቅላላ የኋላ የአክስል ክብደቱ በአንድ ላይ ተደምሮ ከ18 ቶን (180 ኩንታል) የበለጠ እንደሆነ ነዉ፡፡

⭐️በመሆኑም ሁሉም የተሽከርካሪ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች እንዲሁም የመንገድ ተጠቃሚዎች ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጋር በመተባበር ከፍተኛ የሃገር ሃብት የፈሰሰበትን የመንገድ መሰረተ ልማት ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ ለማሳሰብ እንወዳለን።

Via ERA

@etconp
👍11❤1
የኅብረት_ሥራ_ማህበራት_አደረጃጀት_መመሪያ.pdf
1 MB
የኅብረት_ሥራ_ማህበራት_አደረጃጀት_መመሪያ

https://t.me/ETCONp
የኮንስትራክሽን_ሥራዎች_ውል_አዘገጃጀት፣_ለሕግ_ባለሞያዎችና_ለምሕንድስና_ባለሞያዎች_በአማርኛ_የቀረበ፤.pdf
271.8 KB
የኮንስትራክሽን_ሥራዎች_ውል_አዘገጃጀት፣_ለሕግ_ባለሞያዎችና_ለምሕንድስና_ባለሞያዎች_በአማርኛ_የቀረበ

https://t.me/ETCONp
የግንባታ_ፍቃድ_መጠየቂያ_ማመልከቻ_ፎርም_form_all_construction_permitWord.pdf
1.6 MB
የግንባታ ፍቃድ መጠየቂያ ማመልከቻ ፎርም

form all construction permit

https://t.me/ETCONp
የጋራ_መኖሪያ_ቤቶች_ኮንዶሚኒየም_አሰጣጥ_መመሪያ_ቁ_28_2013.pdf
1.6 MB
የጋራ_መኖሪያ_ቤቶች_ኮንዶሚኒየም_አሰጣጥ_መመሪያ_ቁ_28_2013

https://t.me/ETCONp
አግባብ_ባለው_አካል_ሳይፈቀድ_የተያዙ_ቦታዎችን_ለማስተካከል_እና_ለመከላከል_የወጣ_የአፈፃፀም_መመሪያ.pdf
11.3 MB
አግባብ_ባለው_አካል_ሳይፈቀድ_የተያዙ_ቦታዎችን_ለማስተካከል_እና_ለመከላከል_የወጣ_የአፈፃፀም_መመሪያ

https://t.me/ETCONp
የአዲስ_አበባ_ከተማ_አስተዳደር_የኮንስትራክሽን_ቢሮ_የመሰረተ_ልማት_ቅንጅት_ግንባታ_ፍቃድ_ቁጥጥር_የህንፃ.pdf
5.2 MB
የአዲስ_አበባ_ከተማ_አስተዳደር_የኮንስትራክሽን_ቢሮ_የመሰረተ_ልማት_ቅንጅት_ግንባታ_ፍቃድ_ቁጥጥር_የህንፃ

https://t.me/ETCONp
አዲሱ_የቤት_ሽያጭ_ዋጋ_ተመን_አሰራር_እና_ታክስ_አገልግሎት_ክፍያ_ማንዋል_ቁ_01_2016_watermark.pdf
1.2 MB
አዲሱ_የቤት_ሽያጭ_ዋጋ_ተመን_አሰራር_እና_ታክስ_አገልግሎት_ክፍያ_ማንዋል_ቁ_01_2016

https://t.me/ETCONp
👍24❤4🙏4👏1
👉በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የሰቆጣ -ፅፅቃ -መሸሃ መንገድን የሚያስተሳስረው የተከዜ ወንዝ የብረት ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክት ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ።

🚧ከዚህ በፊት የነበረው የብረት ድልድይ በ2011 ዓ.ም በተከስተ የጎርፍ አደጋ ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ ቆይቶ ነበር።

⭐️አዲሱ ድልድይ 4.2 ሜትር ስፋት
146 ሜትር ርዝመት ያለው ተገጣጣሚ ብረት ሲሆን፣ በድልድዩ ርዝመት ምክንያት በአንድ አቅጣጫ ብቻ አንድ ተሽከርካሪ በተራ ማሳለፍ የሚችል ነው።

🏷የድልድዩ ተሸካሚ ግንቦች የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት እንዲሁም የድልድዩ ተገጣጣሚ ብረት ደግሞ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በኩል የተከናወነ መሆኑ ታውቋል።
►
ተጨማሪ መረጃዎችን ከ ሌላኛው የቴሌግራም ቻናላቻን ማግኘት ይችላሉ👇
►
t.me/ETCONpWORK
👍5❤3
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

🔰ምን ይፈልጋሉ?

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍5❤2
Ethio Construction Engineering
👇
👉ከፍርስራሾች እንዴት እንጠበቅ?

🚧የሕንፃ ግንባታዎችን ዲዛይን መለወጥ እና እድሳት ማካሄድ ቀላል ሥራ ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም፡፡

የንግድ ሱቆችን እንዲሁም መኖሪያዎችን ለማደስ እና የዲዛይን ለውጥ ለማድረግ የሚካሄዱ ግንባታዎች እጅግም በጣም አድካሚ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡

በተለይ በሥራው ሂደት የሚፈጠሩ ፍርስራሾችን ቀደም ብሎ ለማስወገድ የሚያስችሉ ዝግጅቶች ካልተደረጉ ድካሙን የጎላ ከማድረጉም በላይ ብክነትንም ይጨምራል፣ ብክለትም እንዲፈጠር ያደርጋል፣ ለጤናም አደገኛ ነው፡፡

የግንባታ ባለሙያዎች እና ባለቤቶች በነባር ግንባታዎች ላይ እድሳት ወይም የዲዛይን ለውጥ ሲያደርጉ ከሚዘነጓቸው ጉዳዮች ዋነኛው በሥራው ወቅት የሚፈጠረውን የአቧራ እና ፍርስራሽ ክምርን ነው፡፡

ይህ ደግሞ ለጤና ጠንቅ በሆኑ አቧራዎች፣ የሊድ እና የአስፔስቶስ ብናኞች እንዲጠቁ ያደርጋቸዋል፡፡

ከዚህ የከፋ ውጣ ውረድ ለመዳን ከሚያስችሉ ዘዴዎች "Managing dust and debris during house remodeling or renovations time" በሚል ርዕስ ከሰፈሩ የባለሙያ ምክሮች ውስጥ የሚከተሉት አምስቱ በቀዳሚነት ይቀመጣሉ፡፡

1. የአቧራ እና የፍርስራሽ ጎጂነትን መረዳት

▶️የአቧራ እና የፍርስራሽ ጎጂነትን በቀላሉ መረዳት ዋናው አንገብጋቢ ጉዳይ ከመሆን ባለፈ፣ የማፅጃ መሳሪያዎችን ማዘጋጀት እና ቆሻሻን ቀብሮ ማስወገድን ማንም አይዘነጋውም፡፡

ችግሩ በቤት ቁሳቁሶች፣ ወለል እና ግድግዳዎች ላይ የሚያርፉ ቆሻሻዎች ሙሉ በሙሉ ማፅዳት አለመቻሉ እና በሂደት ወይም ውሎ አድሮ የጤና ጠንቅ መሆናቸው ነው፡፡

ለእንዲህ ዓይነት ችግር መፍትሄው በአየር ውስጥ የሚገኙ እና የሚተኑ እንደ ሊድ ብናኝ ዋናው ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪም የአሸዋ፣ የድንጋይ እና የማዕድን ብናኝ በመተንፈሻ አካላችን ገብተው እንደ ሲልኮሲስ ያሉ የጤና ጉዳቶችን እንዳያስከትሉብን፣ በሥራው ሂደት የመተንፈሻ አካላችንን ከጥቃት የሚከላከሉ እንደ ኦክሲጅን ማስክ የመሳሰሉ የፊት ጭምብሎችን ማጥለቅ እንዲሁም አፍ፣ አፍንጫችንን እና አይናችንን ከብናኞቹ የሚከላከሉ መሣሪያዎች መጠቀም ተገቢ ርምጃ ነው፡፡

2. አስፈላጊ የብክለት መከላከያ በጀት መመደብ

እድሳት ወይም የዲዛይን ለውጥ ሲደረግ እንደ ግንባታው ወጪ ከላይ የተጠቀሱ ብክለቶችን ለማስወገድ የሚያስችሉ የቁሳቁስ መሸፈኛ የማፅጃ እና የሰውነት ብክለት መከላከያ መሣሪያዎችን ለመግዛት የሚያስፈልግ በጀት መድቦ ቀደም ብሎ ማዘጋጀት ይገባል፡፡ ለዚህ ደግሞ የግንባታ ወጪ ሲታሰብ በተጨማሪ ቢያንስ 1ዐ በመቶ ተጨማሪ በጀት መመደብ ይገባል፡፡

3. ቁሳቁሶኝ ከቤት ማውጣት

ፍርስራሽ ብናኞች እንዳይፈጠሩ መከላከል ባይቻልም፣ ከቤት ውስጥ የሚገኙ መገልገያ መሣሪያዎችን እና ቀደም ብሎ ቁሳቁሶቹን ከቤት ውስጥ አውጥቶ ንጽሕናውን በተጠበቀ መጋዘን ወይም ክፍል ውስጥ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡ ምን አልባት አንዳንድ ቁሳቁስን ከቤት ለማውጣት አስቸጋሪ ወይም ከፍተኛ የማጓጓዣ ወጪን ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ለዚሁ አማራጭ መፍትሔ ተብሎ የተቀመጠው ቁሶቹ ላይ ብናኝ እንዳያርፍ የሚያስችሉ መሸፈኛዎችን በመጠቀም በሚያስተማምን መንገድ መሸፈን ነው፡፡

4. ወለሉን እና ቋሚ ቁሶችን መከላከል

ወለሎችን እና የማይንቀሳቀሱ ቁሶችን በአቧራ እና ብናኝ እንዳይበከሉ፣ እንዳይጫጫሩ እንዲሁም እንዳይጐዱ ለመከላከል በሚያስችሉ እንደ ታርባዩሊን ባሉ አስተማማኝ መከላከያዎች መሸፈን ይገባል፡፡

5.ሥራዎች በተቻለ መጠን ወጪ መሥራት

በመጨረሻም፣ በእድሳት ወቅት የሚበየዱ ብረቶችን፣ የሚቆረጡ እንጨቶችን የሚቦካ ኮንክሪት እና ሲሚንቶን ከግንባታው ራቅ ባለ ገላጣ ሜዳ ላይ የማይዘጋጅበት ምንም በቂ ምክንያት አይኖርም፡፡

እንደተጠቀሱት ያሉ ሥራዎችን ከግንባታ ራቅ ባለ ሜዳ ላይ ማከናወን ከዘላቂ ብክለት ከመጠበቅ ባለፈ፣ በቀጣይ በቀላሉ ንጹህ የመኖሪያ ወይም የመስሪያ  ከባቢን ለመፍጠር ያስለችናል፡፡

@etconp
👍16
Intercon Construction Chemicals 
    
👉 Authorized agent of MC (Conmix), Weber and SIMENTEK

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍4
👉ነጻ የስልጠና እድል

🚧ማንዴላ ዋሺንግተን ፌሎውሺፕ ፣ አሜሪካ

💫ማንዴላ ዋሺንግተን ፌሎውሺፕ በ 2025 ክረምት ወራት ለ6 ሳምንት የሚቆይ ስልጠና ለ700 አፍሪካውያን ወጣት መሪዎች አዘጋጅቷል።

🏷ዝርዝሩን ከተያያዘው ማስፈንጠርያ ይመልከቱ።

⭐️The Mandela Washington Fellowship will bring up to 700 young leaders to the United States in the summer of 2025 for a comprehensive executive-style program that is designed to build skills and empower Fellows to lead in their respective sectors and communities.

⏺The Fellowship is an unparalleled opportunity to…

• Participate in a six-week Leadership Institute at a U.S. college or university to share your experiences with and learn from U.S. citizens and other Fellows.

• Explore industries beyond your daily work and expand your expertise.

• Participate in a Summit with young African leaders.

• Meet with U.S. Government, civic, and business leaders.

• Strengthen your work through new connections, skills, and ideas.

• Join a continental and global Alumni Network to help you seek innovative solutions to common challenges.

❇️Application and Selection Timeline

• August 13, 2024 | Application opens

• September 10, 2024  |  Application deadline

• November 2024 – January 2025  |  Semi-finalists interviewed by local U.S. embassies and consulates

• March 2025 |  Applicants notified of their status

• May 2025  |  Visa processing and Pre-Departure Orientations for Finalists

• June 2025  |  Fellowship begins in the United States

https://tinyurl.com/2uxkjetz

@etconp
👍8❤2
የኮንስትራክሽን ዋስትና አይነቶች


1.ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond)

ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማለት ጨረታ ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች ለምሳሌ ሥራ ተቋራጩ በአሸነፈው መሰረት ውሉ ቢሰጠው ግዴታውን ስለመፈጸሙ የሚያቀርበው ዋስትና ነው፡፡ በሌላ አባባል ይህ ዋስትና ሥራ ተቋራጩ ለአሰሪው ጨረታውን በማሸነፉ ወደ ውሉ እገባለሁ ሲል የሚገባው የዋስትና ግዴታ ነው፡፡

ይህም ጉዳይ በመንግስት ግዥ አዋጅ ላይ በአንቀጽ 40 በስፋት ተመልክቷል፡፡ የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያሰሩት ግንባታ በሚያዘጋጁት የጨረታ ሰነድ ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም መያዣ ተጫራቹ ጨረታው አየር ላይ እያለ ከውድድሩ ከወጣ ወይም ከአሸነፈ በኋላ ውሉን ለመፈጸም ፈቃደኛ ካልሆነ የጨረታ መያዣ ገንዘቡ ሊወረስ ይችላል፡፡

በሌላ አባባል የጨረታ ማስከበሪያ በሚል የሚያዝ ገንዘብ ጨረታውን ባዘጋጀው አካል ሊወሰድ የሚችለው ተወዳዳሪው ጨረታውን ባሸነፈው መጠን ሆኖ በጨረታው መሠረት መፈጸም ካልቻለ ወይም አስቀድሞ ከወጣ ነው፡፡

የጨረታ ዋስትናው መጠኑን በተመለከተም እኤአ በ2010ዓ.ም በወጣው የገ/ኢ/ል/ሚ የግዥ መመሪያ አንቀጽ 16.16.2 ላይ እንደተገለጸው የጨረታ ዋስትና የውሉን አጠቃላይ ግምት ወስጥ 0.5 (ግማሽ) እሰከ 2(ሁለት) ፐርሰንት ሊደርስ ይችላል፡፡ ነገር ግን የተባለው የመንግስት መ/ቤት የጨረታ ዋስትናውን መጠን በሚወስንበት ጊዜ ከ500,000.00 (አምስት መቶ ሺ) ብር መብለጥ የለበትም፡፡

የጨረታው አካሄድ ሚዛናዊ እንዲሆን መመሪያው እንደሚለው የመንግስት የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ለማከናወን የሚወጣ ጨረታ ቢያንስ የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ በግዥ የሚሰራው ሥራ የዋጋ አስተማማኝነት ግምት ውስጥ መግባት ይኖርበታል፡፡

ሁለተኛ በጨረታው በቂ ቁጥር ያላቸው ተጫራቾች እንዲኖሩ ግድ ይላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘቡ ተጫራቾችን እንዳይሳተፋ አስቀድሞ የሚከለክል መሆን የለበትም፡፡ ሌላው #የጨረታ_ማስከበሪያ ገንዘቡ አጫራቹ የመንግስት መ/ቤት በጨረታው አሸናፊ የሆነው ተጫራች ጨረታውን ባለመፈጸሙ ምክንያት ሊደርስበት የሚችልን ጉዳት መሸፈን ይኖርበታል፡፡

2.የውል ማስከበሪያ ዋስትና (Contract security/ Performance  
                       ይቀጥላል.. .)
3.የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና (Advance Payment Guarantee)
                        ይቀጥላል.. .)
4.የጥገና ወይም የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)
                          ይቀጥላል.. .)

@etconp
👍22❤12🙏1🕊1
Ethio Construction Engineering
የኮንስትራክሽን ዋስትና አይነቶች 1.ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማለት ጨረታ ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች ለምሳሌ ሥራ ተቋራጩ በአሸነፈው መሰረት ውሉ ቢሰጠው ግዴታውን ስለመፈጸሙ የሚያቀርበው ዋስትና ነው፡፡ በሌላ አባባል ይህ ዋስትና ሥራ ተቋራጩ ለአሰሪው ጨረታውን በማሸነፉ ወደ ውሉ እገባለሁ ሲል የሚገባው የዋስትና ግዴታ ነው፡፡ ይህም ጉዳይ በመንግስት ግዥ አዋጅ…
የኮንስትራክሽን ዋስትና አይነቶች:-

            የቀጠለ.. .)

2.የውል ማስከበሪያ ዋስትና (Contract security/ Performance 


የውል ማስከበሪያ ዋስትና (contract security) ወይም የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና (performance bond) የሚባለው አንድም ግራ ቀኙ ለገቡት ውል መልካም አፈጻጸም ሲባል በአንድ ሦስተኛ ወገን የሚሰጥ ዋስትና ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜም ሥራ ተቋራጮች ለፕሮጀክት ባለቤቶች ወይም ንዑስ ተቋራጮች ለዋናው ሥራ ተቋራጭ ውል ለመፈጸም ብለው ከአንድ የፍይናንስ ተቋም ወይም ሌላ ሦስተኛ ወገን አማካኝነት የሚቀርብ ዋስትና ነው፡፡
ሁኖም ግን ቀደም ሲል እንደተገለጸው የውል ማስከበሪያ ዋስትና ተፈጻሚ የሚሆነው ዋናው ባለዕዳ(ለምሳሌ፡-ሥራ ተቋራጭ) ግዴታውን ባይወጣ ነው፡፡ 
"ከመንግስት አስተዳደር መ/ቤት ጋር የሥራ ውል ያደረገ ወገን እንደውሉ መፈጸም ባልቻለ ጊዜ የአስተዳደር መ/ቤቱ ተዋዋዩ የውል ማስከበሪያ (contract security) በሚል ካስያዘው ገንዘብ ላይ ውል ባለመፈጸሙ የደረሰበትን የጉዳት ኪሣራ መቀነስ ይችላል፡፡ ”
በፌደራል የመንግስት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁ.649/2001 አንቀጽ 47 ላይ በግልጽ እንደተመለከው በተለይም የመንግስት ግንባታ ውሎች ላይ አቅራቢ (ውል ተቀባይ) ሆኖ የሚቀርብ ወገን ግዴታውን ባለመፈጸሙ ምክንያት በውል ሰጪው መንግስት መ/ቤት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ማካካሻ የሚሆን የውል ማስከበሪያ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
መጠኑን በተመለከተም የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡ እኤአ በ ሰኔ ወር 2010 የወጣው የገ/ኢ/ል/ሚ መመሪያ አንቀጽ 16.25 ላይ እንደተመለከው አሸናፊው ሥራ ተቋራጭ ጨረታውን አሸንፎ ውል በተዋዋለ በ 15 ቀናት ውስጥ ቢያንስ የውሉን 10ፐርሰንት እንደ ውል ማስከበሪያ(Performance security) ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የዋስትናው መክፈያ መንገድም በመመሪያው አንቀጽ 16.16.4 በተመለከተው መሰረት በተጫራቹ ምርጫ በጥሬ ገንዘብ፣ በቼክ፣ የባንክ ዋስትና ሰነድ፣ ክሬዲት ወይም በቅድመ ሁኔታ በሚዘገጅ የመድን ቦንድ ሊሆን ይችላል፡፡
በተጨማሪም መመሪያው በአንቀጽ 16.25.3 ላይ ውል ሰጪው የመንግስት መ/ቤት አቅራቢው (ሥራ ተቋራጩ) በውሉ በተቀመጠው መሰረት ግዴታውን መወጣት ካልቻለ የያዘውን ውል ማስከበሪያ ገንዘብ እንደነገሩ ሁኔታ መጠቀም ወይም መውረስ ይችላል፡፡ እንዲሁም ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር ሥራ ተቋራጩ ውሉን በተወጣ ጊዜ ያስያዘው ገንዘብ ይመለስለታል፡፡ /የመመሪያው አንቀጽ 16.25.7 ይመለከተዋል፡፡ 
ሌላው ጉዳይ #የመልካም_ሥራ_አፈጻጸም ዋስትና (Performance bond) በመድን ድርጅቶች መውጣታቸው የዋሱን እና ባለገንዘቡን ግዴታ የሚገዛውን የሕግ ማዕቀፍ ይቀይራል ወይስ አይቀይርም? የሚለው ነጥብ ነው፡፡
ሲጠቃለልም የውል ማስከበሪያ ዋስትና ስለፕሮጀክቱ መልካም አፈጻጸም ውል ተቀባዩ ከአንድ ከሌላ ሦስተኛ ወገን ጋር በሚደርገው ግንኙነት ሊቋቋም ይችላል::

@etconp
👍13🙏8❤2
👉የግንባታ ላይ አረንጓዴ ስፍራ ህግ

🚧በ 100 ሜትር ካሬ ይዞታ ላይ 2 በ2 ሜትር ስፋት ያለው ከግንባታ ነጻ መሬት እንዲኖር የሚደነግገው ህግ ጽሁፍ ተያይዟል።

https://t.me/ETCONp
🙏2❤1👍1