Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
🏷የ ዕለቱ ጥቆማችን

👉የውጭ ምንዛሪ ተመን ተከትሎ ተጀምረው የቆሙ ፕሮጀክቶች ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ስላለው መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል!

https://t.me/ETCONpWORK
👍3❤2🙏1
👉አለምአቀፍ የንድፍ ውድድር

🚧Architecture Competition for Undergraduate Students.

💫The Drawing Board 2024 ህንድ አገር


⭐️ለመጀመርያ ዲግሪ ኪነህንጻ ተማሪዎችና አሁን ለተመረቁ ምሩቃን።

🏷ሙሉ ዝርዝሩን ከተያያዘው ማስፈንጠርያ ተመልክቶ መመዝገብ እና መወዳደር ይቻላል።

🔖የመጨረሻው የንድፍ ማስረከብያ ቀን 16 September 2024 ነው።

🎲በግልም በቡድንም መወዳደር ይቻላል። የሚረከበው የገጽ መጠንና ብዛት እጅግ አነስተኛ ስለሆነ መወዳደር ይጠቅማል።

📜በመመዝገብያ ወቅት የምናስገባው username እና password የራሳችንን የግል የኢሜል አካውንት ሳይሆን ለዚህ ውድድር የምንፈጥረው ስም እና አዲስ ይለፍ ቃል መሆን አለበት

https://tinyurl.com/29svdbh9

Via Architecture and Urban

@etconp
👍9🙏1
እዚህ መንደር ስንት አባወራ ይኖራል?

ስንት ቤቶች አሉ? ስንት ሰው? ምናልባት በአንድ ቤት ውስጥ አማካይ ሰባት ሰዎች ቢኖሩ?
50 ቤቶች ቢኖሩ ነው። 50 ሲባዛ በ7 = 350 ዜጎች።

G+22 ህንፃ በ500 ካሬ ሜትር ላይ በአንድ ወለል 5 አባወራ፣ እያንዳንዱ ባለ ሶስት ምኝታ ቤት ይደርሳቸዋል። 5 ሲባዛ በ20 መቶ ቤቶች ማለት ነው። 50 ቤቶች ለነዋሪው 50ዎቹ ደግሞ ለሽያጭ ይቀርባሉ። ሁለቱ/ሶስት ወለሎች ለመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) ናቸው።

እያንዳንዱ ነዋሪ ቀሪውን ይዞታ ሰፊ ቦታ ለአነስተኛ ፓርክ፣ በኢንቨስትመንት መልክ በማስያዝ ከሚያገኘው ገቢ ሌሎች ህንፃዎችን ይገነባሉ።

የውጭ ባንኮች ሲመጡ ይህንን ሃሳብ ይገዙታል። የኛ ሀገር ባንኮች "ቆጥቡ" ከማለት ውጪ ሌላ ተግባር አላሳዩንም።

ነዋሪዎቹ ከቀያቸው ከጉርብትናቸው #በፖሊሲ አይፈናቀሉም ማለት ነው።

ጊዜ፣ ንብረት እና እውቀት የዘመኑ ሃብቶች ናቸው።

Via Tesfu Belaymeh

@etconp
❤26👍17
👉የዘላቂ ማረፊያ ምንድን ነው?

🏷ዘላቂ ማረፊያ ማለት የሰውን አስክሬን በመሬት ውስጥ የሚያርፍበትን ቦታ
የሚያመለክት ሲሆን ለዚሁ አላማ በተዘጋጀ ቦታ እንደየእምነቱ ሁኔታ የሰው አስክሬን/ ቅሪት የሚቀመጥበት ቦታ ነው፡፡

▶️በሀገራችንምየመቃብር ቦታ ተብሎ ይጠራል፡፡

▶️ስለ ዘላቂ ማረፊያ ሲታሰብ ከሰው ልጅ ውልደት ጋር አብሮተሳስሮ የኖረ እንደመሆኑ ሞት ወይም የቀብርአገልግሎትን ከሰዎች መፈጠር እና ጥንታዊታሪክ ጋር ተሳስሮ የሚገኝ ነው፡፡

▶️በሃገራችን በርካታ ዘላቂ ማረፊያዎች
ሲኖሩ አብዛኞቹ በእምነት ተቋማት ስር የሚገኙናቸው፡፡

⏺በተለምዶ የቀብር ቦታ የምንላቸው
ዘላቂ ማረፊያዎችን የማልማትና የማስተዳደር ሃላፊነቱን ወስዶ በመስራት ላይ የሚገኘው ኤጀንሲ ዘላቂ ማረፊያዎቹን በአዲስ መልክ ማልማት ከጀመረ ወዲህ በርካታ ማሻሻያዎችንበማድረግ በአዳዲስ ዲዛይን እንዲለሙ የማድረግስራ እየሰራ ይገኛል፡፡

⭐️በተለይ ለረጅም ዓመታት በከተማችን ውስጥ የሚገኙ ዘላቂ ማረፊያዎች መገለጫ የሆነው አስፈሪ ገፅታና በሰዎች ዘንድ ያለውን ወደ ዘላቂ ማረፊያዎች ከቀብር ሰዓት ውጪ ለመሄድያለመድፈር ስሜት ለመቀየር በማሰብ ዘላቂማረፊያዎቹ ከቀብር አገልግሎት ውጪ ሰዎችፀጥታ ሲፈልጉ የሚያርፉበት ሰላማዊ ስፍራ እንዲሆኑ የማድረግ ሰፊ ስራ እየሰራ ነው፡፡

@etconp
👍6👏3👌1💔1
Intercon Construction Chemicals 
    
👉 Authorized agent of MC (Conmix), Weber and SIMENTEK

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
❤4👍3
👉የፕሮጀክት ማናጀሮች ስኬታማ እንዴት ሊሆኑ ይችላሉ?
➟➟➟
በኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች በማናጀርነት በመስራት የሚፈልገውን ውጤት ለማግኘት እና ተገቢውን ሚና ለመጫወት የሚፈልግ  በዘርፉ የሰለጠነ ባለሙያ፣ በመጀመሪያ ደረጃ እንደ ማንኛውም የሥራ መሪ ለሥራው ዓይነት የሚያስፈልገውን ሥልጠና  እና ትምህርት መውሰድ እንደሚገባ ለመገመት አያዳግትም፡፡

ከዚህ ውስጥ አንድ ፕሮጀክት ማናጀር የተለመዱ አምስት ሂደቶችን ማለትም ለስራው መነሳሳት ወይም ጅማሮ (initiation)፣ እቅድ፣ ውሳኔ፣ ትግበራ፤ ክትትል እና አጨራረስ ከመደበኛ የማኔጅመንት ኃላፊነት በኃላ የሚጋራቸው የሥራ ሂደቶች በቀዳሚነት የሚቀመጡ ናቸው፡፡

ከነዚህ መደበኛ የሥራ ሂደቶች በተናጠለ መንገድ የአንድ የኮንስትራክሽን ማናጀር የሥራ ሂደት በጣም ጥልቅ ዕውቀት የሚጠይቅ እና ውስብስብ የሆነ የሥራ ሂደትን በመጋፈጥ ምላሽ መስጠትን የሚጠይቅ የሥራ ዘርፍ ነው፡፡ በአሜሪካ የኮንስትክሽን ማኔጅመንት ማህበር ያስቀመጠው መሥፈርት፣ አንድ የኮንስትራክሽን ማናጀር  በአማካይ ወደ 120 የሚጠጉ ኃላፊነቶች እንዳሉበት የሚያመለክት ነው፡፡

እነዚህ ኃላፊነቶችን ለመወጣት ከሕንፃ ዲዛይን ባለሞያ፣ ከኮንትራክተር፣ ከእቃ አቅራቢዎች፣ ከሂሳብ እና በጀት ባለሞያዎች ጋር በመገኘት አስፈላጊውን ዕውቀት መቅሰም፣ ሥራን በቀላሉ እና በፍጥነት ለመሥራት የሚያስችሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና መሳሪያዎችን በተመለከተ የጠለቀ የቴክኒካል ዕውቀት ማዳበር  ይጠበቅበታል፡፡ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ከግምት በማስገባት አንድ የኮንስትራክሽን ማናጀርን ስኬታማ ያደርጋሉ ተብለው የተቀመጡ አምስት እቅዶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

▪️በየዘርፉ የማያቋርጥ የግንኙነት መረብ መዘርጋት

ለአንድ ኮንስትራክሽን ማናጀር ወሳኝ ከሆኑ መሳሪያዎች አንዱ በእያንዳንዱ  የሥራ ሂደት የሚያገኘው ትክክለኛ መረጃ ነው፡፡ በሥራ ሂደት ዕቅዶችን ለመንደፍ እና ለመተግበር ከሁሉም በላይ መሬት ወርዶ ከባለድርሻ አካላት፣ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢዎች፣ ከኮንትራክተሮች ከሂሳብ (በጀት) ኃላፊዎች፣ ከሥራ  የቡድን መሪዎች፣ ከተራ ሰራተኞች ጋር በመገናኘት የሚያገኘው መጥፎም ሆነ ጥሩ መረጃ ፈጣን፣ ውሳኔ እና ማስተካከያ ለመስጠት የሚያስችል ከፍተኛ ግብዕት ይለግሱታል፡፡

በሥራው ቦታ እና ከሚመለከታቸው አባላት ጋር የሚገኙ መረጃዎች፣ በኢሜል ወይም በስልክ ከሚገኙ መረጃዎች የበለጠ ችግሮችን በፍጥነት ለመቅረፍ  የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን ለመንደፍ  ያላቸው ጠቀሜታም የጎላ ነው፡፡
የማያቋረጥ ዕቅድ ማውጣትን ልምድ ማድረግ
በማኔጅመንት የሥራ ዘርፍ ዕቅድ (Planning) ከአምስቱ የሥራ ሂደቶች በሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጥ ነው፡፡

በኮንስትራክሽን የፕሮጀክት ማናጀር የሥራ ዘርፍ ደግሞ ዕቅድ የሚወጣው ሥራው ከመጀመሩ እጅግ በጣም ቀደም ብሎ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ያለማቋረጥ እየተከለሰ እና እያዳበረ መሄድ ይኖርበታል፡፡

በኮንስትራክሽን የሥራ ሂደት ዲዛይኖች፣ ቅድመ ግንባታዎች፣ ድህረ ግንባታዎች በየዘርፉ ሂደቱን እየተከተሉ መለወጥ እና መታደስ የሚያስፈልጋቸው በርካታ ያልተጠበቁ ገጠመኞችን፣ የዲዛይን ለውጦችን የግብዓት እና የበጀት እጥረቶችን ማስተናገዳቸውን እንደማይቀር ቀድሞ በመረዳት፣ በተለይ ከፍተኛ ልምድ ካላቸው የዘርፉ ኢንጂነሮች እና ባለሞያዎች ጋር በመገናኘት የማያቋርጥ ዕቅድ የማውጣት ልምድን በማዳበር በአቋራጭ ወደተፈለገው ግብ ለመድረስ ያስችላል፡፡

▪️በአካል እየተገኙ መጎብኘትና መጠየቅ

በየትኛውም የኢንደስትሪ ዘርፍ የተሰማራ ማናጀር ከሚመራው የሥራ ዘርፍ የሥራ ሂደት እና ከበታች አካል ተነጥሎ ቢሮ ውስጥ ተቀምጦ የሚያስተላልፈው ውሳኔ፣ መሬት ወርዶ የሚያስገኘው ውጤት ባይኖርም፣ የማናጀሩ ኃላፊነት በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ ከዚህ የበለጠ ትኩረትን የሚሻ ነው፡፡

ምክንያቱም  የኮንስትራክሽን ሼል ያለመቋረጥ ክትትል ካልተደረገበት እና ሥራውን በሚያጓትቱ ብዙ ውስብስብ ሴራዎች እና ጋሬጣዎች የተከበበ በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት አንድ የፕሮጀክት ማናጀር፣ ሥራው የሚካሄድበት ሳይትን እየጎበኘ፣ ከበታች ያሉትን ኃላፊዎች ወይም የሳይት መሪዎች በቦታው ተገኝቶ  እያነጋገረ ተጨባጭ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ በየዓመቱ እየተለወጡ እና እያዳበሩ ሼል ላይ የሚውሉ መሣሪያዎች እና የአሰራር ዘዴዎች መረዳት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በስኬት እንዲወጣ ያደርጉታል፡፡

▪️በጀት እና ወጪን መቆጣጠር

አንድ የፕሮጀክት ማናጀር እቅድ ነደፎ ወደ ተግባር ሲገባ ቀድም ብሎም ሆነ በየሂደቱ ከሚያስባቸው ነገሮች አንዱ፣ ለሥራው የሚያስፈልገው በጀት እና ወጪን በተቀመጠለት ጊዜ ሳይስተጓጎል ማግኘት ወይም ማወራረድ ነው፡፡

ወደ ተግባር ሲመጣ ደግሞ የኮንስትራክሽን ሥራ ቀደም ብሎ ለመገመት የሚያስቸግሩ ቀጥተኛ ያልሆኑ ወጪዎችን ይዞ ከተፍ የሚል የሥራ ዘርፍ ነው፡፡ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚሰማራ የሒሳብ ባለሞያ ደግሞ ሂደቱ ህጋዊነት እየተከተለ እንዲወራረድ ከማድረግ ወጪ፣ ወደፊት የዋጋ ንረት ሲፈጠር፤ ለሠራተኞች የሚከፈል ደመወዝ ሲጓተት ሥራውን እንዲያጓትት የሚያደርግ ተፅእኖ በመፍጠሩ ለዚሁ እልባት የሚያስገኝ ከእቅድ ውጪ የሆነ የገንዘብ ጥያቄ ቢቀርብ ኃላፊነቱን ፕሮጀክት ማናጀሩ ላይ ከመወዘፍ ውጪ የመወሰን ኃላፊነትም የሌለው እና ተጠያቂነት በመፍራት በጥንቃቄ መጓዝን ምርጫው ያደርጋል፡፡

ከዚሁ በመነሳት፣ አንድ የፕሮጀክት ማናጀር የሚቀርብለትን የግዥ ጥያቄ እና የወጪ ሰነድ መፈረም ብቻ ሳይሆን፣ ከመደበኛ ወጪው ከፕሮጀክቱ የሥራ ሂደት እና ዕድገትን እየገመገመ መቆጣጠር እንደ አስፈላጊነቱም መገደብ  ይኖርበታል፡፡ ይህን በሚያደርግበት ጊዜ  ተጨማሪ  የሥራ ጫና እንዳይፈጠርበት የሚያደርጉ እንደ "ዶኩ ሳይን" የመሳሰሉ የወጪ እና የበጀት መቆጣጠሪያ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም በቀላሉ ለመቆጣጠር ይችላል፡፡

▪️የተቀናጀ የሪፖርት ዘዴን መከተል

አንድ የፕሮጀክት ማናጀር በየቀኑ ለሚቀርቡለት የኢሜይል ጥያቄዎች፣ የስልክ ጥሪዎች፣ የበጀት ጥያቄዎች፣ የሥራ ሂደት ሪፖርቶች በሙሉ ምላሽ   የሚሰጥበት ጊዜ አይኖረውም፡፡ ለነዚህ ጥያቄዎች የተቻለውን ያህል ምላሽ ለመስጠት ቢሞክር እንኳ፣ ዋና የሥራ ክትትሎችን በማጓተት የሚያስከትልበት ጉዳት እና ጫና እየጨመረ መሄዱ አይቀሬ ነው፡፡

ለዚህ ችግር መፍትሄው ደግሞ አውቶሞቴድ ሪፖርቲንግ ሲስተም የተባለ የሪፖርት ዘዴን በመከታተል ለእያንዳንዱ ጥያቄ የሚፈልገው አካል ምላሽ እንዲሰጥ የሚያደርጉ፣ ሳምንታዊ የሥራ ሂደቶችን፣ ሪፖርቶችን፣ የገንዘብ ጥያቄዎችን በየዘርፉ እየተቀበሉ በተቀላጠፈ ብሎም በአጭር ጊዜ እና አቀራረብ ሪፖርት የሚያደርጉ ሶፍትዌሮችን ወይም የኮምፒዩተር ዘዴዎችን መጠቀም ይኖርበታል፡፡

@etconp
50👍33❤7🏆1
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ መቁረጫ መብሻና  ማጠፊያ ማሽኖች አሉን

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ እናበጃለን እንዲሁም እናጥፋለን

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍3
Ethio Construction Engineering
የኮንስትራክሽን ዋስትና አይነቶች:-             የቀጠለ.. .) 2.የውል ማስከበሪያ ዋስትና (Contract security/ Performance  የውል ማስከበሪያ ዋስትና (contract security) ወይም የመልካም ሼል አፈጻጸም ዋስትና (performance bond) የሚባለው አንድም ግራ ቀኙ ለገቡት ውል መልካም አፈጻጸም ሲባል በአንድ ሦስተኛ ወገን የሚሰጥ ዋስትና ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜም…
የኮንስትራክሽን ዋስትና አይነቶች:-

                    
                               የቀጠለ.. .)

3.የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና (Advance Payment Guarantee)

የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ሲባል ሥራ ተቋራጩ ጨረታውን አሸንፎ ውል ተፈርሞ ወደ ሥራው ሊገባ ሲል የፕሮጀክቱ ባለቤት ለሥራ ተቋራጩ የተወሰነ የቅድሚያ ገንዘብ በመስጠቱ ምክንያት ሥራ ተቋራጩ በአንጻሩ ለወሰደው ገንዝብ የሚያቀርበው ዋስትና ነው፡፡

በመሰረቱ በኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ጅማሮ የቅድሚያ ክፍያ መኖር በአንድ በኩል ሥራ ተቋራጩ ያለምንም የገንዘብ ችግር ለሥራው የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች መግዣ ይሆነዋል፡፡ ወይም ደግሞ ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ከፍሎ ለንዑስ ተቋራጮች በሚሰጥበት ጊዜ እንደ ሥራ ማስጀመሪያ (mobilization commission) ይሆናቸዋል፡፡

ስለ ቅድሚያ ክፍያ አስፈላጊነት ታዋቂው የኮንስትራክሽን ክሌም ጸሀፊ ጆን ስካይስ እ.ኤ.አ 1999 በወጣው መጽሀፋቸው እንዳብራሩት ቅድሚያ ክፍያ መኖር ለሥራ ተቋራጮች ከመጥቀሙ ባሻገር የጨረታ ወጥ መለኪያ (tender standardization) ተድርጎ ስለሚወሰድ ጭምር ነው፡፡
የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና መኖረን አስመልክቶ የመንግስት ግዥ አዋጅ ቁ.649/2001 በአንቀጽ 48 እንደተመለከተው የቅድመ ክፍያ ሊፈጸም የሚችለው ሥራ ተቋራጩ በቅድሚያ ክፍያ መልክ ከሚወስደው ገንዘብ መጠን ጋር እኩል የሆነ ዋስትና ሲያቀርብ እንደሆነ ይናገራል፡፡

የመንግስት የኮንስትራክሽን ውሎችን የቅድሚያ ክፍያ መጠንን በተመለከተ እኤአ በ2010 የወጣው የገ/ኢ/ል/ሚ የግዥ መመሪያ አንቀጽ 16.26 ላይ የቅድመ ክፍያ መጠን የውሉን 30(ሰላሣ) ፐርሰንት መብለጥ የለበትም፡፡ ሆኖም ግን በአገር በቀል የሥራ ተቋራጮች የሚሰራ የመንገድ ግንባታ ሲሆን ግን የቅድሚያ ክፍያ ገንዘቡ እስከ 50(ሃምሳ) ፐርሰንት ይደርሳል፡፡
ዝርዝር ሁኔታው በእያንዳንዱ ጨረታ ይገለጻል፡፡

በሥራ ተቋራጩ የሚቀርበው የቅድሚያ ክፍያ ዋስትናው መጠን የተከፈለውን የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ጋር እኩል መሆን አለበት፡፡ የዋትናው አቀራረብም በቼክ፣ ያል ቅደመ ሁኔታ የሚቀርብ የባንክ ዋስትና ወይም በቅድመ ሁኔታ የሚዘጋጅ የመድን ዋስትና ሊሆን ይችላል፡፡

ሌላው የቅድሚያ ክፍያ ገንዘቡ ለምን ዓላማ መዋል እንደለበትና በምን አግባብ ሊሰጥ እንደሚችል መመሪያው በአንቀጽ 16.26.7 ተመልክቶታል፡፡ በተለይም የመንገድ እና ህንጻ ግንባታ የሚሰሩ ሥራ ተቋራጮች በቅድሚያ ክፍያው ገንዘብ ስለሚገዙት የማሽነሪ ዝርዝር በመመሪያው መሰረት ብቻ ይሆናል፡፡


4.የጥገና ወይም የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)
                          ይቀጥላል.. .)

@etconp
🙏19👍14❤1
Ethio Construction Engineering
የኮንስትራክሽን ዋስትና አይነቶች:-                                                     የቀጠለ.. .) 3.የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና (Advance Payment Guarantee) የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ሲባል ሼል ተቋራጩ ጨረታውን አሸንፎ ውል ተፈርሞ ወደ ሥራው ሊገባ ሲል የፕሮጀክቱ ባለቤት ለሼል ተቋራጩ የተወሰነ የቅድሚያ ገንዘብ በመስጠቱ ምክንያት ሼል ተቋራጩ በአንጻሩ…
የኮንስትራክሽን ዋስትና አይነቶች:-

                    
                               የቀጠለ.. .)

4.የጥገና ወይም የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)

የጥገና ዋስትና የተበላሹ የግንባታ ግብዓቶችንና የሥራ አሰራር ግድፈቶችን ለመከላከል በሚል ሥራ ተቋራጩ ለፕሮጀክት ባለቤቱ የሚገባው ዋስትና ነው፡፡ በተለይም ከላይ ስለዋና ገንዘብ መያዣ (retention) ቆይታ እንደተመለከተው ለአንድ ዓመት ጊዜ የሚያዝበት ምክንያት ከጥራት ጉድለት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመጠገን ነው፡፡ በሚለቀቅበትም ጊዜ ያለቅድመ ሁኔታ ዋስትና ሥራ ተቋራጩ እንዲያቀርብ የሚደረግበት ምክንያት በህንጻው ግንባታ ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ለመጠገን በሚል ነው፡፡

የጥገና እና ብልሽጽ አላፊነት መያዣ በዋናነት የዋና ገንዘብ መያዣ ቆይታ እንዳበቃ የሚጀምር ነው፡፡ በርግጥ ሥራ ተቋራጩ ለባለቤቱ ለተወሰኑ ዓመታት ዋቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ፡-በሲቪል የግንባታ ሥራዎች በተለይም በፍ/ህ/ቁ 3039 እንዲህ የሚል ዐ.ነገር ይነበባል፡-

"ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ካስረከበበት ጊዜ ጀምሮ ስለመልካም አሰራር፣ ስለሥራው እና ስለጠንካራነቱ ለ10 (አስር) አመት መድን (guarantee/ warranty) ነው፡፡ በዚህም ጊዜ ውስጥ በሥራው ጉድለት ወይም በተሰራበት መሬት ዓይነት ምክንያት በተሰራው ሥራ ላይ ለሚደርሰው መጥፋት ወይም መበላሸት አላፊ ነው፡፡ ”


በተመሳሳይ መልኩ የመንግስት የግንባታ ውሎችንም በተመለከተ የፍትሐብሔር ሕጉ ከአንቀጽ3277-3282 ላይ የ10 (አስር) አመት የብልሽት መድን ጊዜ ያስቀምጣል፡፡
ሆኖም~ አንድ ሥራ ተቋራጭ በሠራው ህንጻ ላይ የተከሠተ እርግጠኛ የአሰራር ጉድለት በሌለበት ሁኔታ ወደፊት የሚታይና የሚከሰት የአሰራር ጉድለት ሊኖር ይችላል በሚል ምክንያት ሥራ ተቋራጮች ለሰሩት ሥራ የመጨረሻ ክፍያ የማግኘት መብት መከልከል አግባብነት የለውም::

@etconp
👍14👌1
Statement 1: A slump cone measures 100 mm (top diameter), 200 mm (bottom diameter) and 350 mm height.
Statement 2: Slump test helps in qualitatively understanding the setting time of concrete
Anonymous Quiz
20%
Both statements are false
41%
Statement 1 is true and statement 2 is false
22%
Both statements are true
17%
Statement 1 is false and statement 2 is true
👍7❤3👏1
The self-compaction concrete has ______ slump value
Anonymous Quiz
44%
250 mm
16%
500 mm
27%
100mm
13%
650 mm
😢9🙏3❤2🏆1
Quantity of cement required (in terms of 50 kg. bags) to cast a 5 m × 4 m slabs (RCC 1 ∶ 2 ∶ 4) of thickness 10 cm is approximately:
Anonymous Quiz
39%
8 bags
18%
11 bags
24%
13 bags
19%
14 bags
👍16❤10🙏2
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

🔰ምን ይፈልጋሉ?

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍6❤1
በ እግረመንገዳችን የታዘብነውን እናካፍላችሁ!

ቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት ወደ 22 ተብሎ በሚጠራው መንገድ ላይ ነው፡፡

ይህን የምትመለከትቱት ... በዚህ መንገድ ይታይ የነበረው ትንንሽ የመንገድ መበላሸቶችና ጉድጓዶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ሰፋ መለስተኛ ባህር በመለወጥ ላይ ናቸው፡፡

በተለይ አደይ አባባ ስታዲየም እስክትጨርሱ ያለው የጎርፍና የመንገድ ብልሽት መኪና የሚያበላሽና ለ እግረኞች እዳ ሆንዋል፡፡

በጅምር ላይ ያለው አደይ አበባ ስታዲየም አጥሩን እያጠበበ ሲሆን ለመንገዱ የውስጥ ቱቦዎች እየገቡ መሆኑ ይታያል፡፡

ይህ መንገድ እንደሌሎቹ መንገዶች በፍጥነት ሊሰራ ከሚገባው ውስጥ ይመስለናል፡፡

መንገዱ መቼ ይሆን ቀን የሚወጣለት ያስብላል?

@etconp
❤8👍5