Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👆👆👆👆

👉ለ ኮንስትራክሽን ስራ ማለትም ለ ማኔጅመንት ማማከር፣ለ ህንጻ ማማከር፣ለ ምህንድስና ማማከር፣ለ ከተማ ፕላን ማማከር፣ለ ህንፃ ንብረት ግመታ ስራ እና ጠቅላላ ተቋራጭ ድርጅት ለመክፈት ፈልጋቹ ሟሟላት ያለባቹ መስፈርቶች እና ምን እንደሚያስፈልጋቹ ለጠየቃቹን ከላይ ያሉትን ፋይሎች ልናጋራቹ ወደድን ተመልከቱት🙏

🏷Share በማድረግ ሌሎች ጋ እንዲደርስ እናርግ❤

🚧Minimum requirement for All Construction and Consulting Works

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍6🙏3❤2👌1
👉አለም አቀፍ ስብሰባ (ፎረም)

⭐️“Sustainable Urbanization for Africa’s Transformation: Agenda 2063” በሚል ርዕስ በአድዋ ቤተመዘክር ስብሰባ አዳራሽ በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት ከ ረቡዕ, ነሐሴ 29 2016 እስከ አርብ ጳጉሜ 1 2016 (Sept 4-6 2024) የሚካሄደውን አለምአቀፍ የሶስት ቀን ስብሰባ በተያያዘው ማስፈንጠርያ ተመዝግቦ መታደም ይቻላል።

💫ህንጻ ነዳፊዎች፣ ከተማ አቃጆችና ነዳፊዎች እንዲሁም መሀንዲሶች እና የከተማ ፖሊሲ አውጪዎች እንዲሳተፉ ይመከራል።

🏷መመዝገብያውን ጨምሮ ለአጠቃላይ መረጃ ከታች ያለው መስፈንጠሪያ ይጫኑ

https://tinyurl.com/2push63d

Via Africa Union

@etconp
🙏7👍4❤1
👉ልዩ የምሕንድስና ጥበብ የታየበት የቻይናው ሺዚጉዋን ተንሳፋፊ ድልድይ ከፍተኛ የቱሪስት መስህብ እየሆነ ነው።

🚧በሁቤይ ግዛት በቻይና ቺንግጂያንግ ወንዝ ላይ የተሠራው የሺዚጉዋን ተንሳፋፊ ድልድይ እስከ 2.8 ቶን ክብደት ያላቸው መኪናዎችን ማስተናገድ የሚችል ነው።

🏷ከ 8 ዓመት በፊት ግንባታው የተጠናቀቀው የሺዚጉዋን ተንሳፋፊ ድልድይ ለተሽከርካሪም ሆነ ለእግረኛ ክፍት በመሆን አገልግሎት መስጠት መጀመሩንም ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።

💫የሺዚጉዋን ተንሳፋፊ ድልድይ "ረጅሙ የሕልም ድልድይ" በመባልም ይታወቃል።

⭐️በኪንግጂያንግ ወንዝ ላይ በእግር ወይም በተሸከርካሪ ለመጓዝ ለሚፈልጉ ዜጎች እና ቱሪስቶች ድልድዩ ጥሩ ዕድል ጥሯል።

▶️እ.አ.አ በ2016 የተከፈተው ይህ ድልድይ 500 ሜትር እርዝመት እና 4.5 ሜትር ስፋት አለው።

▶️የድልድዩ ስፋቱ አንድ መኪና እና ከግራና ቀኝ እግረኞችን እንዲያሳልፍ ተደርጎ የተገነባ ሲሆን በውኃ ላይ መንዳትን ለሚወዱ ቱሪስቶች መስህብ እየሆነ መምጣቱም ይነገራል።

▶️ከድልድዩ ጎን ለጎንም በሐይቁ ላይ ባሉ ጀልባዎች የትራንስፖርት አገልግሎት መሰጠቱ ለተሳፋሪው አማራጭ ከመስጠቱ ባለፈ የተለየ ውበት አጎናፅፎታልም።

▶️ድልድዩ አሽከርካሪዎችም ሆነ እግረኞች ምንም ዓይነት ስጋት እንዳይኖርባቸው የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን የተጠቀመ ሲሆን አሽከርካሪዎች በድልድዩ ላይ የተጣለውን የፍጥነት ገደብ እንዲያከብሩ ይጠበቃል።

Via AMN

@etconp
👍11❤4
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

🔰ምን ይፈልጋሉ?

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍4❤1
👉ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል ከእስካሁኑ በእጥፍ በለጠ

🚧ኢትዮጵያ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ የምታመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ከእጥፍ በላይ ማሳደግዋን አስታወቀች።

🏷የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የታላቁ የሕዳሴ ግድብ መስሪያ ቤትን ጠቅሶ እንደዘገበው በቅርቡ ሁለት ተጨማሪ መዘዉሮች (ተርባይኖች) አገልግሎት በመጀመራቸዉ ከግድቡ የሚመረተዉ የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ወደ 1 ሺሕ 550 ሜጋዋት ከፍ ብሏል።

▶️ከዚሕ ቀደም ሥራ የጀመሩት ሁለት መዘዉሮች እያንዳዳቸዉ 375 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫሉ። ሰሞኑን የተመረቁት ሁለት ተጨማሪ መዘዉሮች ደግሞ እያንዳዳቸዉ 400 ሜጋዋት ኃይል ያመነጫሉ።

▶️ኢትዮጵያ ከግብፅና ሱዳን ጋር የሚያወዛግባትን ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ በአባይ ወንዝ ላይ መገንባት የጀመረችዉ በመጋቢት 2003 አጋማሽ ነዉ።

▶️ግድቡ የመጀመሪያዉን ኃይል ማመንጨት የጀመረዉ ግን ሐቻምና ነዉ።

⏺ብዙ ቢሊዮን ዶላር የፈሰሰበት ግድብ ከአፍሪቃ ትልቁ የኃይል ማመነጫ ነዉ።

▶️ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ከ5ሺሕ ሜጋዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሏል።

▶️የግድቡ ስራ ከግንባታ ደረጃ ወደ ኃይል ማመንጫ መሸጋገሩን የገለጸው መሥሪያ ቤቱ የግድቡ ግንባታ አሁን ተጠናቋል ብሏል።

▶️ኢትዮጵያ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ለመጀመሪያ ጊዜ ኃይል ማመንጨት የጀመረችው በየካቲት 2014 ዓ.ም. ነበር።

▶️ግድቡ በስተመጨረሻ ከ5ሺህ ሜጋ ዋት በላይ ያመነጫል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም ከአሁን ከደረሰበት ከእጥፍ በላይ ነው የሚሆነው።

Via DW

@etconp
👍15❤1