👉አለም አቀፍ ስብሰባ (ፎረም)
⭐️“Sustainable Urbanization for Africa’s Transformation: Agenda 2063” በሚል ርዕስ በአድዋ ቤተመዘክር ስብሰባ አዳራሽ በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት ከ ረቡዕ, ነሐሴ 29 2016 እስከ አርብ ጳጉሜ 1 2016 (Sept 4-6 2024) የሚካሄደውን አለምአቀፍ የሶስት ቀን ስብሰባ በተያያዘው ማስፈንጠርያ ተመዝግቦ መታደም ይቻላል።
💫ህንጻ ነዳፊዎች፣ ከተማ አቃጆችና ነዳፊዎች እንዲሁም መሀንዲሶች እና የከተማ ፖሊሲ አውጪዎች እንዲሳተፉ ይመከራል።
🏷መመዝገብያውን ጨምሮ ለአጠቃላይ መረጃ ከታች ያለው መስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://tinyurl.com/2push63d
Via Africa Union
@etconp

🙏7👍4❤1
👉ልዩ የምሕንድስና ጥበብ የታየበት የቻይናው ሺዚጉዋን ተንሳፋፊ ድልድይ ከፍተኛ የቱሪስት መስህብ እየሆነ ነው።
🚧በሁቤይ ግዛት በቻይና ቺንግጂያንግ ወንዝ ላይ የተሠራው የሺዚጉዋን ተንሳፋፊ ድልድይ እስከ 2.8 ቶን ክብደት ያላቸው መኪናዎችን ማስተናገድ የሚችል ነው።
🏷ከ 8 ዓመት በፊት ግንባታው የተጠናቀቀው የሺዚጉዋን ተንሳፋፊ ድልድይ ለተሽከርካሪም ሆነ ለእግረኛ ክፍት በመሆን አገልግሎት መስጠት መጀመሩንም ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።
💫የሺዚጉዋን ተንሳፋፊ ድልድይ "ረጅሙ የሕልም ድልድይ" በመባልም ይታወቃል።
⭐️በኪንግጂያንግ ወንዝ ላይ በእግር ወይም በተሸከርካሪ ለመጓዝ ለሚፈልጉ ዜጎች እና ቱሪስቶች ድልድዩ ጥሩ ዕድል ጥሯል።
▶️እ.አ.አ በ2016 የተከፈተው ይህ ድልድይ 500 ሜትር እርዝመት እና 4.5 ሜትር ስፋት አለው።
▶️የድልድዩ ስፋቱ አንድ መኪና እና ከግራና ቀኝ እግረኞችን እንዲያሳልፍ ተደርጎ የተገነባ ሲሆን በውኃ ላይ መንዳትን ለሚወዱ ቱሪስቶች መስህብ እየሆነ መምጣቱም ይነገራል።
▶️ከድልድዩ ጎን ለጎንም በሐይቁ ላይ ባሉ ጀልባዎች የትራንስፖርት አገልግሎት መሰጠቱ ለተሳፋሪው አማራጭ ከመስጠቱ ባለፈ የተለየ ውበት አጎናፅፎታልም።
▶️ድልድዩ አሽከርካሪዎችም ሆነ እግረኞች ምንም ዓይነት ስጋት እንዳይኖርባቸው የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን የተጠቀመ ሲሆን አሽከርካሪዎች በድልድዩ ላይ የተጣለውን የፍጥነት ገደብ እንዲያከብሩ ይጠበቃል።
Via AMN

👍11❤4
ታምራት ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ
👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ
🔰ምን ይፈልጋሉ?
📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን
✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል
🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ
📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን
☎️ይደዉሉልን ያማክሩን
📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን
አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
ቁ.2 መርካቶ
ቁ.3 ተክለሀይማኖት
0904040477
0911016833

👍4❤1
👉ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል ከእስካሁኑ በእጥፍ በለጠ
🚧ኢትዮጵያ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ የምታመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ከእጥፍ በላይ ማሳደግዋን አስታወቀች።
🏷የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የታላቁ የሕዳሴ ግድብ መስሪያ ቤትን ጠቅሶ እንደዘገበው በቅርቡ ሁለት ተጨማሪ መዘዉሮች (ተርባይኖች) አገልግሎት በመጀመራቸዉ ከግድቡ የሚመረተዉ የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ወደ 1 ሺሕ 550 ሜጋዋት ከፍ ብሏል።
▶️ከዚሕ ቀደም ሥራ የጀመሩት ሁለት መዘዉሮች እያንዳዳቸዉ 375 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫሉ። ሰሞኑን የተመረቁት ሁለት ተጨማሪ መዘዉሮች ደግሞ እያንዳዳቸዉ 400 ሜጋዋት ኃይል ያመነጫሉ።
▶️ኢትዮጵያ ከግብፅና ሱዳን ጋር የሚያወዛግባትን ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ በአባይ ወንዝ ላይ መገንባት የጀመረችዉ በመጋቢት 2003 አጋማሽ ነዉ።
▶️ግድቡ የመጀመሪያዉን ኃይል ማመንጨት የጀመረዉ ግን ሐቻምና ነዉ።
⏺ብዙ ቢሊዮን ዶላር የፈሰሰበት ግድብ ከአፍሪቃ ትልቁ የኃይል ማመነጫ ነዉ።
▶️ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ከ5ሺሕ ሜጋዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሏል።
▶️የግድቡ ስራ ከግንባታ ደረጃ ወደ ኃይል ማመንጫ መሸጋገሩን የገለጸው መሥሪያ ቤቱ የግድቡ ግንባታ አሁን ተጠናቋል ብሏል።
▶️ኢትዮጵያ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ለመጀመሪያ ጊዜ ኃይል ማመንጨት የጀመረችው በየካቲት 2014 ዓ.ም. ነበር።
▶️ግድቡ በስተመጨረሻ ከ5ሺህ ሜጋ ዋት በላይ ያመነጫል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም ከአሁን ከደረሰበት ከእጥፍ በላይ ነው የሚሆነው።
Via DW

👍15❤1
👉የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።
🚧የመንግስት የልማት ድርጅት የሆነው ኮርፖሬሽኑ በፕሮጀክቶች አፈጻጸም ዙሪያ የውይይት መድረክ እያካሄደ ይገኛል።
🚧በመድረኩ በ2016 በጀት ዓመት በበርካታ ችግሮች ውስጥ ያለፈ ቢሆንም በፈተና ውስጥ ሆኖ ስኬት ማስመዝገቡን ተገልጿል።
💫ይህንን ስኬት ማስመዝገቡ በአፍሪካ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ የልማት ድርጅቶች ውስጥ አንዱ እንዲሆን እንዳደረገው የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ተናግረዋል።
🏷ኮርፖሬሽኑ ከተለያዩ የግንባታ ስራዎችና ከኮንስትራክሽን ግብዓት አምራች ኢንዱስትሪዎች ከ11 ነጥብ 8 ቢቢሊን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ ተገልጿል።
⏺በውሃ፣ በትራንስፖርት፣ በህንፃና በቤቶች ኮንስትራክሽን ዘርፍ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን እየገነባ ይገኛል።
Via FBC

👍9❤2
🚧የሮቤ-ጋሰራ-ጊኒር የመንገድ ክፍል ከትራፊክ እንቅስቃሴ ለጥቂት ቀናት ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ፡፡
💫አስተዳደሩ በባሌ ዞን በሮቤ-ጊኒር መስመር ከጋሰራ መገንጠያ ኪሎ ሜትር 30 ላይ የሚገኘው የደንበል ወንዝ የብረት ድልድይ ከባድ ጭነት በጫነ ተሸከርካሪ ምክንያት ጉዳት እንደደረሰበት አስታውቋል፡፡
🚧በመሆኑም የጥገና ሥራው ተጠናቆ ድልድዩ ለትራፊክ ክፍት እስኪደረግ ድረስ አሽከርካሪዎች የሮቤ-ጎሮ-ጊኒር እና ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ አሳስቧል፡፡

👍7❤3
Intercon Construction Chemicals
👉 Authorized agent of MC (Conmix), Weber and SIMENTEK
● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grout
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials
Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall

👍5
የግንባታ ቦታን ማስረከብ
🏷የግንባታ ባለቤት (Client) ለግንባታ ሥራ መሰናክል ከሆኑ ነገሮች (ለምሳሌ፦ የካሳ ጥያቄ ከሚያነሱ ሰዎች ቁጥጥር፣ ከመብራት፣ ከውሃ፣ ከቴሌ ግንባታዎችና መሣሪያዎች) በማጽዳት ወይም ነጻ በማድረግ ዝግጁ የሆነ የግንባታ ቦታን ለሥራ ተቋራጩ (Contractor) የማስረከብ ሕጋዊ ኃላፊነት አለበት።
💫ባለቤቱ የግንባታ ቦታውን ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ ለሥራ ተቋራጩ ካላስረከበ የግንባታ ማስረከቢያ ጊዜ መራዘም/መዘግየት/ ላይ ለሚያስከትለው ኪሳራ ወይም ወጪ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ የሕንጻ ግንባታ ደንቦች (Standard Building Contract with quantities) በአንቀጽ 2.4 እና 2.24 ስር የሰፈረ ድንጋጌ ነው።
#ConstructionLaw
@etconp
👍13
አንድ ሰው ግንባታ እያከናወነ የጎረቤት ቤት ቢፈርስበት የጎረቤቱን ቤት እንዲያሰራ ይገደዳል ወይስ ሌላ የህግ እይታ አለ?
🏷አንድ ሰው ግንባታውን ሲያከናውን የጎረቤቱን ቤት ቢናድበት ወይም በግንባታ ሥራው የተነሳ የጎረቤቱን ቤት ቢያፈርስ ተጠያቂ ነው።
💫የመፍረስ አደጋ ባይገጥምም እንኳን በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2077 (1) እና (2) መሰረት አንድ ሕንጻ በሌላው ይዞታ ላይ ያልታሰበ ድንገተኛ ሌላ አደጋ ቢያደርስ የሕንጻው ባለቤት ተጠያቂ (ካሳ ከፋይ) ይሆናል።
▶️ይህም ማለት እንዲፈርስ ያደረገውን ቤት በእራሱ ወጪ እንዲጠግን/እንዲሰራ ይገደዳል።
⏺ቢሆንም ግን በቁጥር 2079 መሰረት በግንባታ ወቅት (በተለይ ከቁፋሮ ጀምሮ ባሉት የመሰረት ሥራዎች ጊዜ) በሌላ የጎረቤት ሕንጻ ላይ የመፍረስ አደጋ ከመድረሱ በፊት አስቀድሞ ሥጋት ላይ ያለው ክፍል አስፈላጊውን ድጋፍ ወይም ጥንቃቄ እንዲደረግለት ማድረግ ይችላል።
▶️“ጎረቤት” የተባለው አካልም ይህ ስጋት ከተሰማው አስቀድሞ ጥንቃቄ እንዲደረግለት የመጠየቅ ሕጋዊ መብት አለው።
🚧ጠቅለል ሲደረግ፦ አንድ የሕንጻ ባለይዞታ በግንባታ ወቅት በጎረቤት ይዞታ ላይ የተገነባን ሕንጻ የመፍረስ ወይም የመሰንጠቅ ጉዳት ቢያደርስ እንዲሁም ሕንጻው በሚገነባበት ወቅትም ይሁን ከተጠናቀቀ በኋላ ከዚያ ሕንጻ ላይ እየወደቁ በሌላው ሕንጻ ወይም ይዞታ ላይ ለሚያደርሱት ጉዳት ተጠያቂ ነው (ፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2080)።
❇️የጎረቤት ሕንጻ ቢፈርስ ተጠያቂ የማይሆንበት አግባብ
▶️በጎረቤት ይዞታ ወይም ሕንጻ ላይ ጉዳት ቢደርስ የማይጠየቀው በሁለት ምክንያት ነው።
📜[አንደኛው] በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2078 (1) መሰረት ጎረቤት የተባለው ባለይዞታ ይዞታውን ግንባታ ለሚያከናውነው ሰው የለቀቀለት እንደሆነ ወይም ግንባታ የሚያከናውነት አካል የራሱን ሕንጻ ለፈረሰበት ጎረቤቱ የሚለቅለት ከሆነ ነው።
📜[ሁለተኛው] “ጎረቤት” የተባለው አካል ሕንጻው የመፍረስ አደጋ እንዳይገጥመው ጥንቃቄ እንዲደረግለት የመጠየቅ መብት የሚኖረው ግን አስቀድሞ የገነባው ሕንጻ በመሬት ውስጥ፣ በመሬት ላይም ይሁን በአየር ላይ አዲስ የሚገነባውን ባለይዞታ የካርታ መስመር ያላለፈ ከሆነ ብቻ ነው።
🗂ለምሳሌ፦ አስቀድሞ የገነባው ጎረቤት የመሰረት ግንባታው ወይም ተንጠልጣይ የባልኮኒ ወለል ወደሰው ይዞታ አንድ ሳንቲሜትርም ቢሆን ካለፈ እንዲያስተካክል ወይም እንዲያፈርስ ይገደዳል።
⏹አዲስ ግንባታ የሚገነባውም ሰው ጎረቤቱ ወደይዞታው ገብቶ የሰራውን የሕንጻ አካል እንዲያፈርስና እንዲያስተካክል ሳያስጠነቅቅ ማፍረስ የለበትም፣ በፍርድ ቤት በተቆረጠ ቀነ ገደብ እንዲያስተካክል ማሳሰብ ሲኖርበት በዚያ ቀነገደብ ካላስተካከለ ግን ትእዛዝ አስወጥቶ ማስፈረስ/ማፍረስ/ ይችላል።

👍14❤3
የግንባታ ውል ሰነድ በግልጽ ማስቀመጥ ያለበት ነጥቦች]
🚧የፕሮጀክቱን ዲዛይን እና ዝርዝሮች
▶️የፕሮጀክት ባለድርሻ አካላትን ድርሻ፣ መብትና ግዴታ
▶️የሚጠበቀውን የግንባታ ጥራት የሚገልጹ ትንታኔዎች
▶️የፕሮጀክቱን ተጠባቂ የጊዜ ሰሌዳዎች
▶️የፕሮጀክቱን ዋጋ እና አከፋፈል ሁኔታዎች
▶️የደህንነት እና የጤና አጠባበቅ መመሪያዎች
▶️ፕሮጀክቱን የሚመለከቱ የሕግ ማእቀፎች
▶️የፕሮጀክቱ ባለድርሻ አካላትን ፊርማ እና ማኅተም
▶️ፕሮጀክቱ የሚፈልገውን የሰው ኃይል ብቃትና ብዛት
▶️ፕሮጀክቱ የሚፈልገው ማሺነሪ አይነትና ብዛት
▶️የእያንዳንዱን የሥራ አይነት ዝርዝርና የግንባታ ስነዘዴ
▶️የፕሮጀክቱን ባለድርሻ አካላት ዝርዝር መረጃ
🏷አንድ የግንባታ ውል ሰነድ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ዋና ዋና ጭብጥ ጉዳዮች በግልጽ እና በዝርዝር ማስቀመጥ ይኖርበታል።
💫የተወሳሰበ፣ ያልተብራራ እና እርስ በእርሱ የሚጋጭ ሀሳብ ቢኖርበት ግን በሚኖረው የፍርድ ቤት ክርክር ባለድርሻ አካላትን በተናጠል አልያም በጋራ ኪሳራ ላይ ሊጥል ይችላል።
⭐️ይህ ሁኔታ ደግሞ ፕሮጀክቱን በጤናማ ግንኝነት ለመፈጸም እክል ሊፈጥር ስለሚችል ለጥራት ችግር እና ለጊዜ ብክነት እንዲጋለጥ ያደርገዋል።

👍12❤3🙏3
BIM TALKS: Leveraging EIR and 4D BIM to Elevate Construction Projects
Unlock the future of Building Information Modeling (BIM) with our exclusive "BIM Talks" series tailored for professionals in the Ethiopian AEC industry. Dive deep into the preparation of EIR for BIM projects and discover how 4D BIM is set to revolutionize construction management.
🗓 Date: Saturday, September 07, 2024
🕒 Time: 1:30 - 5:00 PM
📍 Location: EiABC
💼 Registration: Mandatory – https://forms.gle/4YvehajPuGRj5Q7U8
🎟 Free Event
This is your chance to gain cutting-edge insights and network with industry leaders. Don’t miss out—join us for an afternoon that could redefine your approach to construction management!

👍5❤2
👉የአለማችን ረጅሙ የእንጨት ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ በአሜሪካ ሊገነባ ነው
⭐️በአሜሪካ ዊስኮንሲን ግዛት ውስጥ የሚገነባው 55 ፎቅ ያለው አዲሱ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ የዓለማችን ረጅሙ የእንጨት ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ይሆናል ተብሏል።
🚧የሕንፃው ነዳፊ የሆነው ሚሼል ግሪን አርክቴክቸር (ኤምጂኤ) መስራች በአሜሪካ የዘመናዊ የእንጨት ግንባታ ፈር ቀዳጅ ሲሆን፣ በሰሜን አሜሪካ ታዋቂ በሆኑ ትላልቅ የእንጨት ግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ መሥራቱም ታውቋል።
🏷አዲሱ ሰማይ ጠቀስ የእንጨት ሕንፃ ሰፊ አረንጓዴ እና በርካታ ቴራሶች የያዘ ሲሆን፣ አጠቃላይ ወጪው ከ700 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ይሆናል።
💫ሕንፃው እስከ 750 የሚደርሱ መኖሪያ ቤቶች፣ 17,600 ካሬ ሜትር የቢሮ ቦታ፣ 3,700 ካሬ ሜትር ቦታ የንግድ ሱቆች፣ 300 የሆቴል ክፍሎች፣ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች እና ክፍት የህዝብ መናፈሻ ቦታዎች እና የእግረኛ መንገዶችን ያካተተ እንደሚሆን ታውቋል።
⏺ሰማይ ጠቀስ ሕንፃው በግንባታ ሂደት ውስጥ የትኛውንም ኮንክሪት እንደሚጨምር እርግጠኛ አይደለንም የሚሉት ነዳፊዎቹ፣ ነገር ግን ቁመቱን ግምት ውስጥ በማስገባት የተወሰነ ኮንክሪት እንደሚካተት እናምናለን ይላሉ።
⏺ሰዎች ከእንጨት የተሠራ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ በቀላሉ በእሳት ሊያያዝ ይችላል የሚል ስጋት ሊኖራቸው ይችላል፣ ነገር ግን ከባህላዊው እንጨት በተለየ፣ በዘመናዊው ሁኔታ ለግንባታ የተዘጋጀው ጠንካራ የእንጨት ምሰሶ ከብረት ይልቅ እሳትን በተሻለ ሁኔታ መቋቋም የሚችል ነው ተብሏል።
🌟በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ 25 ፎቆች ብቻ የሚረዝመው የዓለማችን ረጅሙ በእንጨት የተገነባ ሕንፃ የሚገኘው በተመሳሳይ ዊስኮንሲን ግዛት ውስጥ ነው።
Via infra con media

👍15🏆2❤1👏1