Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
አንድ ግለሰብ ለረጅም ጊዜ መንግሥት ወይም ሌላ አካል የገነባውን ቤት ለረጅም ጊዜ መያዙ ባለቤት ሊያደርገው ይችላልን?


🚧አንድ ግለሰብ አንድን የመንግሥት የኪራይ ቤት ወይም በሌላ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተገንብቶ ለረጅም ዓመት እንዲኖርበት የተፈቀደለትን ቤት ለረጅም ግዜ ስለኖረበት ብቻውን የባለቤትነት መብት እንደማያሰጠው የሰበር ሰሚ መዝገብ ቁጥር 228002 (ሠ/መ/ቁጥር 228002) በውሳኔ አጽንቷል።

▶️ይህ መዝገብ "አንድን ቤት ለረጅም ግዜ መያዝ ብቻውን የባለቤትነት መብት የማያጎናጽፍ ነው" ብሏል።

⏺አያይዞም "ቤቱ የቀበሌ /የመንግስት/ ቤት መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ 003 እና ቅጽ 004 በሌሉበት ሁኔታ በተቋሙ የመረጃ ስርአት ቅጽ 008 በቀበሌ ቤትነት መመዝገቡ ብቻ ቤቱ በመንግስት የተወረሰ የቀበሌ /የመንግስት ቤት ነው ሊያስብለው አይችልም" ብሎም አረጋግጧል።

💫በተጨማሪም "በአዋጅ ቁጥር 47/67 ተወርሶ ለረጅም ግዜ በመንግስት እጅ የነበረ ቤትን በሚመለከት በስህተት አላግባብ ያለህጋዊ ምክንያት የተሰጠ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የመከነና በመንግሰት ባለቤትነት የሚታወቅ መሆኑ በተገለጸበት በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት መንግስት የወረሰው መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ 003 እና ቅጽ 004 በሌለበት ቤቱን የመንግስት ንብረት አያሰኘውም" ብሏል።

▶️በዚህ አግባብ ለረጅም ጊዜ የኖረበት አካል ረጅም ዓመት ስለኖረ ብቻ  የባለቤትነት መብት እንደማያገኘው ሁሉ መንግሥት ወይም የቤቱ ባለቤት የባለይዞታ ማረጋገጫ ለማግኘትም እንዲሁ ማሟላት ያለበት መስፈርት ተቀምጧል።

❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

🌟ሌላኛው የ ስራ ቅጥር እና ጨረታች ሚወጡበት ቴግራም ቻናላችን ለመቀላቀል t.me/ETCONpWORK

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp
👍13🙏3
"በሕንጻ ግንባታ ሥራ selective material ከመጠቅጠቁ (ከመረምረሙ) በፊት ውኃ የሚጠጣው ለምንድነው? የጎንዮሽ ተጽእኖስ አለው ይላሉ?"


🏷የአፈር መጠቅጠቅ ሂደት ቅንጣቶች በመካከላቸው ያለውን ክፍተት ለመቀነስ የሚደረግ የመጫን ጉልበት (compaction) ትግበራ ነው።

💫በጣም የታመቀ፣ የተጠቀጠቀ አፈር የቅንጣቶችን ክፍተት በመቀነስ አፈሩ በጣም ጥቂት ቦታን (ስፋትን) እንዲይዝ ያግዘዋል።

⭐️ነገር ግን ይህንን የመጠቅጠቅ (ጥግግት) ደረጃ  የምናገኘው ጥሩ የእርጥበት መጠን ካለው  ነው። አፈሩ በጣም ጥሩ እርጥበት የሌለው ከሆነ የአፈር ቅንጣት ጥግግት በሚፈለገው ልክ ሊከናወን ስለማይችል ውስጥ ውስጥ  ያሉትን ክፍተቶች በሙሉ ለመሙላት አስቸጋሪ ይሆናል።  የተደፋው አፈር (Back filled or selective material) ሁሉም አካሉ በቂ እርጥበት እንዲኖረው ቢያንስ ከአንድ ሌሊት በፊት ቀደም ብሎ  ውኃ መጠጣት አለበት።

🌟የተወሰነ ጊዜ ቀድሞ ማጠጣት (አንደኛ) በሰዓቱ መርዘም የተነሳ የውኃውን የስርገት ሂደት በመጨመር እና ሁሉንም አካል የማግኘት (የማዳረስ) ዕድሉን በማስፋት ሁሉም የአፈር ቅንጣት በቂ እርጥበት እንዲያገኝ ያደርገዋል።

🌟(ሁለተኛ) የአፈሩ የመጠቅጠቅ ሂደት አስቀድሞ በውኃው ስርገት የተነሳ እየተከናወነ እንዲቆይ ያድርጋል። ያ ማለት የመጠቅጠቂያ ጉልበትን ይቀንሳል።

❇️ሆኖም ግን የተመረጠው አፈር በቂ የሆነ የኮረት፣ የጓል እና የደቃቅ አፈር መዋጮ የሌለበት ከሆነ ውኃ ሲጠጣ የባሰ የላመ አፈር (silty) የመሆን እድሉን ስለሚጨምር ከሚፈለገው አገልግሎት አንጻር ጉዳት እንዳይደርስበት የውኃውን መጠን እና የሚጠጣበትን የጊዜ ርዝማኔ እንደአፈሩ አይነት እና እንደአካባቢው አየር የመመጠን ሥራ ከአንድ መሐንዲስ የሚጠበቅ የውሳኔ አካል ነው።

❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

🌟ሌላኛው የ ስራ ቅጥር እና ጨረታች ሚወጡበት ቴግራም ቻናላችን ለመቀላቀል t.me/ETCONpWORK

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp
👍24🙏5
👉ለገጠር መንገዶች ግንባታ 407 ሚሊየን ዶላር ተዘጋጀ

🏷የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የገጠር መንገዶችን ከቀበሌ እስከ ዋና መንገዶች የሚያስተሳስር የ407 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

⏺የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና የተሰኘ ፕሮግራም ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

▶️ፕሮጀክቱ ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ እና በክልሎች መንገድ ፈንድ የሚተገበር መሆኑን የከተማና መሠተ ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ሄለን ደበበ ተናግረዋል።

⏺ፕሮጀክቱ በገጠር የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ በማድረግ ኑሯቸውን እንደሚያሻሽል አንስተዋል።

⏺አርሶ አደሮች ምርታቸውን በተገቢው ሰዓት ለገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያሳድግም ጠቅሰው፤ በሁሉም ክልሎች እንደሚተገበርና ከ11 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

🚧የመንገድ ግንባታው በቀጣይ 5 ዓመታት የሚከናወን ሲሆን፥ ለ200 ሺህ ዜጎች በቀጥታና ለ360 ሺህ ዜጎች ደግሞ በተዘዋዋሪ የሥራ እድል እንደሚፈጥር ተመላክቷል።

@etconp
👍20❤5
Intercon Construction Chemicals 
    
👉 Authorized agent of MC (Conmix), Weber and SIMENTEK

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
❤3👍3
ኮንስትራክሽን ክሌም

         
💫የኮንስትራክሽን ክሌም ለመስራት የውሉ የክፍያ መንገድ ላምፕ ሰም ወይስ አድሜዠርመንት የሚለውን መለየት ግድ ነው።

🚧የውሉ አይነትም ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(DBB) ወይም ዲዛይን ቢዩልድ(DB) ስለመሆኑ  መለየት ይገባል።

⭐️DBB እና DB የተለያየ ጀኔራል ኮንዲሽን ይጠቀማሉ።

❇️ለምሳሌ FIDIC 2017 Red Book ለ DBB እና Yellow Book ለ DB መጠቀም ይቻላል።

▶️የክፍያ መንገዱ ላምፕ ሰም ወይም አድሜዠርመንት መሆኑ ግን የጀኔራል ኮንዲሽን እንድትቀይር አያስገድድም።

🏷ለምሳሌ ፒፒኤ 2011 ቨርሽን ለሁለቱም የክፍያ መንገዶች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

▶️ስፔሻል ኮንዲሽን ላይ የተለወጠ የጀኔራል ኮንዲሽን ክሎስ ያለ እንደሆነ ማረጋገጥም ቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት።

⏺ከዚህ በኋላ ለክሌሙ አግባብነት ያለውን የውል ድንጋጌ፣የህግ ድንጋጌ እና የጀኔራልና ስፔሻል ኮንዲሽን ድንጋጌ መለየትና መስፈርቱን የሚያሟላ ክሌም ማዘጋጀት ይቻላል።

▶️ከዚያም ክሌሙ ለአማካሪ፣ለዲስፒውት ሪቪው ቦርድ፣ለአርቢትሬሽን ወይስ ለፍርድ ቤት መቅረብ እንደሚገባው ለመለየት ጀኔራል ኮንዲሽኑን እና በዋናነት ስፔሻል ኮንዲሽኑን ማየት ይገባል።

Via ጉባዔ አሰፋ

@etconp
👍15❤9
👉ጥያቄ፦ በግንባታ ሥራ ሂደት የሚመጡ የሥራ መለዋወጦች ወይም በውል ከተያዘው ሥራ የሚጨምሩ ወይም የሚቀንሱ ልዩነቶች (Variation) ሲኖሩ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ በራሱ ውሳኔ ማጽደቅ የሚችለው በውል ከተያዘው የግንባታ ዋጋ ላይ ከስንት ፐርሰንት በላይ ካልጨመረ ወይም ካልቀነሰ ነው?
...

🚧ስለሥራ መለዋወጥ (ጭማሪ ወይም ቅናሽ - Variation) ትንሽ እናብራራላቹ

▶️በግንባታ ሂደት የሥራ መለዋወጥ (Variation) የሚከሰት አጋጣሚ ሲሆን ይህ መለዋወጥ የሥራ መቀነስ ወይም የሥራ መጨመር ሊሆን ይችላል። ይህ የሥራ መለዋወጥ በተቆጣጣሪ መሐንዲሱ (Engineer) ትዕዛዝ የሚከናወን ነው።

▶️ነገር ግን በ1988 እና በ1992 ሁለተኛ እና ሦስተኛ እትም በወጣበት FIDIC 1987 አንቀጽ (clause) 52.3 መሰረት የሥራ መለዋወጡን ተቆጣጣሪ መሐንዲሱ ለአሠሪው አካል ሳያሳውቅ የማጽደቅ መብታ ያለው  የውሉን ጠቅላላ ዋጋ ከ15% በላይ የማይጨምር ወይም የማይቀንስ እስከሆነ  ድረስ ብቻ ነው።

🔰የሥራ መለዋወጡ ከ15% በላይ የሚጨምር ወይም የሚቀንስ ከሆነ ግን ከአሠሪው ባለቤት (Employer) ጋር ተወያይቶ በጋራ ቃለጉባኤ ወስነው መሆን ይገባዋል።

⭐️ስለዚህ ከላይ ለተነሳው ጥያቄ መልሱ፦ 15% ነው።

❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

🌟ሌላኛው የ ስራ ቅጥር እና ጨረታች ሚወጡበት ቻናል ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp
👍16🙏4❤2🏆1
This media is not supported in the widget
VIEW IN TELEGRAM
👍9🙏4😢2
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

🔰ምን ይፈልጋሉ?

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ 1. መርካቶ
                   á‰.1 አየር ጤና
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍4❤1🔥1
👉ስለ Athematic Error

በጨረታ ግምገማ ሂደት አንድ ተቋራጭ ባስገባው ጨረታ ሰነድ ላይ የሞላው እያንዳንዱ የሥራ ልኬት (quantities) በተቀመጠላቸውነጠላ ዋጋ (Unit price/rate) እየተባዙ በገምጋሚ ኮሚቴው የሚረጋገጡበት ሂደት Athematic checking ይባላል።

የዚህ ሂደት ዋናው ዓላማ አሸናፊው ተቋራጭ ያስገባቸው ነጠላ ዋጋዎች እና ብዜቶች ትክክል መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሲሆን ስህተቶች (Errors) ሊገኝበት ይችላል።

እንደ መነሻ ኬዝ ከላይ የተጠየቀውን ምሳሌ እናንሳ፦ አንድ ተቋራጭ የጨረታ ሰነዱ ሲከፈት ጠቅላላ ድምር 50,000,000 ብር ያስገባ ሲሆን ሁለተኛ የወጣው ተጫራች 50,050,000 ብር አስገብቷል።

ሃምሳ ሚሊዮን (50,000,000 ብር ) ያስገባው ተጫራች ዝቅተኛ ዋጋ (List Price) መሰረት አድርጎ Athematic checking
ላይ ችግር ካልተገኘበት አሸናፊ እንደሆነ ይገለጻል።

ተቋራጩ በ'Athematic checking ሂደት ውስጥ ለ112 ኪዩቢክ ሜትር አርማታ በአንድ ኪዩቢክ ሜትር ልኬትነጠላ ዋጋ በ8,000 ብር ሂሳብ ጠቅላላ የአርማታ ዋጋ 896,000 ብር  አስገብቷል።

ነገር ግን ወረቀቱ ላይ የመዘገበው ነጠላ ዋጋ 8000 (ስምንት ሺህ) ሳይሆን አንድ ዜሮ ጨምሮ 80000 (ሰማንያ ሺህ) ነው። 'Athematic checking የ112 ኪዩቢክ ሜትር አርማታ ዋጋ ከ896,000 ብር ወደ 8,960,000 ብር ከፍ ያለ ሲሆን ከስምንት ሚልዮን ብር በላይ ልዩነት አመጣ።

ነገር ግን ይህ ተጫራች ሁለተኛ የወጣውን ተጫራች በሃምሳ ሺህ (50,000) ብር ልዩነት አሸንፎ ነበር። በዚህ ሂደት ሊታዩ የሚገባቸው የሕግ አግባቦች፦

የኢትዮጵያ የመንግስት ግዢ ባለሥልጣን የነበረው (Public Procurement Agency - PPA) ለተለያዩ የግዢ ሁኔታዎች መመሪያ ያጸደቀ ሲሆን ለኮንስትራክሽን ሥራዎች በሚያገለግለው መመሪያ Instructions to Bidders (ITB) አንቀጽ 33.1. (a) ላይ "በአንድ ልኬት ላይ የተቀመጠ ነጠላ ዋጋ እና በሥራ መጠንና ነጠላ ዋጋ ብዜት በሚገኘው አጠቃላይ ዋጋ መካከል ልዩነት ከተፈጠረ የነጠላ ዋጋ (unite price) እንደገዢ ተቆጥሮ በብዜት የተገኘው አጠቃላይ ዋጋ (sub total) ይስተካከላል ወይም ይታረማል።

ነገር ግን የሕዝብ አካሉ (አሠሪው ወይም ሕጋዊ ተቀካይ ባለሙያዎቹ) የነጠላ ዋጋ ሲጻፍ የአስርዮሽ ነጥብ የተሳሳተ አቀማመጥ (misplacement of the decimal point) እንዳለ ካሰበ ወይም ካመነበት፣ በዚህ ሁኔታ የተጠቀሰው የብዜቱ አጠቃላይ ዋጋ (total price) ገዢ ሆኖ ለአንድ ሥራ ልኬት የተቀመጠው ነጠላ ዋጋ (unit price) ይስተካከላል ወይም ይታረማል" የሚል ግልጽ ሀሳብ አስቀምጧል።

በመሆኑም ተቋራጩ ያስገባው ዋጋ የአስርዮሽ ነጥብ የተሳሳተ አቀማመጥ (misplacement of the decimal point) ኖሮበት ብዜቱ ግን በአግባቡ ከተቀመጠ እና የጨረታ ኮሚቴው ስህተት መሆኑን ካለው ነበራዊ የግንባታ ሥራዎች ነጠላ ዋጋ አንጻር ተቀራራቢ የሚሆነው የአሥርዮሽ ማስተካከያ ሲሆን እንደሆነ ካረጋገጠ ነጠላ ዋጋውን ትቶ ብዜቱን እንዲይዝና ነጠላ ዋጋው እንዲስተካከል ማድረግ አለበት።

ከላይ በተጠቀሰው አንቀጽ መሰረት፦

[1ኛ]፦  በሀገራችን የትኛውም ቦታ የአንድ ኪዩቢክ ሜትር አርማታ ሙሌት ዋጋ ከ6,000 እስከ 15,000 ብር ስለሆነ 8,000 ብር ተቀባይነት ይኖረዋል እንጂ "ተቋራጩ ለአንድ ኪዩቢክ ሜትር ዋጋ ሰማንያ ሺህ (80,000 ብር) አስገብቷል ብሎ መጣል ሙያዊ እምነት ያልታከለበት ወይም አውቆ እንደመካድ የሚቆጠር ነው።

[2ኛ]፦ ተጫራቹ ለ112 ኪዩቢክ ሜትር ያስገባው ብዜት ዋጋ 896,000 ብር መሆኑ የአንድ ኪዩቢክ ሜትር አርማታ ሙሌት ስምንት ሺህ (8000) ብር መሆኑ ስለሚጠቁም ለሙያው ቅርብ የሆነ ወይም ምክንያታዊ የሆነ ውሳኔ እንዲወሰን መደረግ ይኖርበታል ማለት ነው።

በዚሁ አንቀጽ ሥር ንዑስ አንቀጽ (b) ላይ "በእያንዳንዱ የሥራ ክፍሎች ሥር ያለው ንዑስ ድምሮች እና ጠቅላላ ድምር መካከል የመጨመር ወይም የመቀነስ ልዩነት ከተስተዋለ በእያንዳንዱ ሥራዎች ሥር ያለው ንዑስ ድምር ገዢ ይሆንና ጠቅላላ ድምሩ ይስተካከላል።

በንዑስ አንቀጽ (c) ደግሞ በፊደል የተጻፈው እና በአሐዝ የተቀመጠው ልዩነት ካለው በፊደል የተቀመጠው ዋጋ ገዢ ይሆናል።

ነገር ግን ይህ በፊደል የተቀመጠው ዋጋ ከ'Athematic Error ጋር የሚገናኝ ከሆነ በአሐዝ የተቀመጠው ዋጋ ገዢ ይሆናል በማለት አስቀምጧል።

@etconp
👍18🙏3
ጥያቄ፦ አንድ ተቋራጭ ግንባታውን አጠንቅቆ ባስረከበው ሕንጻ ላይ በሥራ ጉድለት (ግድፈት) ወይም በመሬቱ የአፈር አለመርጋት የተነሳ በሕንጻው ላይ ለሚደርስ ጥፋት ተቋራጩ ተጠያቂ የሚሆነው እስከስንት ዓመት ድረስ ባለው ጊዜ ችግሩ ከተፈጠረ ነው? @etconp
Anonymous Quiz
50%
ሀ) እስከ አንድ ዓመት
13%
ለ) እስከ አምስት ዓመት
33%
ሐ) እስከ አሥር ዓመት
4%
መ) እስከ ሃያ ዓመት
🙏20👍8❤3
Ethio Construction Engineering
💫ጥያቄውን በመመለስ ለተሳተፋቹ በ ሙሉ እናመሰግናለን!

መልስ፦ ሐ) እስከ አሥር ዓመት


⭐️ማብራሪያ፦ አንድ ተቋራጭ በገነባው ሕንጻ ላይ በጥገና እና በትንሽ ገንዘብ ሊስተካከል የሚችል ቀለል ያለ ግድፈት ከታየበት በአንድ ዓመት ውስጥ እንዲጠግን ይደረጋል።

⏺የጥገና ማስያዣ ቦንድ (ብዙ ጊዜ 5%) ክፍያ እየተቀነሰ የሚቆየውም ከዚህ አንጻር ነው፣

▶️ነገር ግን ሕንጻው ከባድ ጥፋት ወይም የስትራክቸራል ችግር ወይም መሰረቱ በተሰራበት የመሬት ክፍል አለመርጋት የተነሳ ከጥገና አልፍ ያለ ጥፋት (ምናልባትም መፍረስ) ከታየበት የኢትዮጵያ ሕንጻ አዋጅ በቁጥር 624/2001 በሚያዝያ 29/2002 ዓ.ም ሥራ ላይ የዋለው አዋጅ የሕንጻ ሥራ ለመገንባት ውል የገቡ የሥራ ተቋራጮች እና አማካሪ ባለሙያዎች በጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ ለሚያደርሱት ጉዳት ዋስትና ማቅረብ የሚገባቸው ስለመሆኑ እና በዚህም ስለሚከተለው የወንጀልና የፍትሐብሔር ተጠያቂነት ያለባቸው ስለመሆኑ ደንግጓል።

❇️አንድ ተቋራጭ የጥገና ዋስትና (retention bond) ቢኖርም ከጥገና እሳቤ ወጣ ያለ ጥፋት ከሆነ በፍ/ህ/ቁ 3039 ላይ “ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ካስረከበበት ጊዜ ጀምሮ ስለመልካም አሰራር፣ ስለ ሥራው እና ስለጠንካራነቱ ለአስር (10) አመት መድን (guarantee/ warranty) ነው።

💫በዚህም ጊዜ ውስጥ በሥራው ጉድለት ወይም በተሰራበት መሬት ዓይነት ምክንያት በተሰራው ሥራ ላይ ለሚደርሰው መጥፋት ወይም መበላሸት አላፊ (ኃላፊ) ነው” ተብሎ እንደተደነገገው ተጨማሪ የመድን ወይም ኢንሹራንስ ባለቤት መሆን ይጠበቅበታል።

🔰የተቋራጮች መድን አስፈላጊነቱም ለዚህ ጭምር ነው።

#ConstructionLaw

🎲ሌላኛው የ ስራ ቅጥር እና ጨረታች ሚወጡበት ቻናል ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp
👍8🙏6❤1
🌼🌼 እንኳን አደረሳችሁ🌼🌼

➡️ውድ ቤተሰቦቻችን አዲሱ አመት የሰላም፤ የፍቅር፤ የአንድነት፤ የብልፅግናና የደስታ ይሆንላቹ ዘንድ ልባዊ ምኞታችን ነው!

🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት 🌼🌼

@etconp
❤9👍3🙏3
👉ኢትዮጵያ አየር መንገድ በ50 ሚሊዮን ዶላር የሚያስተዳድራቸውን ሪዞርቶች ሊያዘመን ነው

🚧የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አካል በሆነው ስካይላይት ሆቴል አስተዳደር ክፍል እንዲከናወን የተላለፉትን አራት ሪዞርቶች ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ የ50 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት እንደሚጠይቅ ታወቀ።

የስካይላይት ሆቴል አስተዳደር በሁለት ክፍሎች ተከፍሎ፣ የአየር መንገዱን ባለአምስት ኮከብ ሆቴል የሚያስተዳድረው ክፍል፣ እንዲሁም የተረከባቸውን ሪዞርቶች ለማስተዳደር የተመደበውን ክፍል በሌላ በኩል የሚመሩ የየራሳቸው ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጆች ተሹመውላቸዋል።

እነዚህ ሁለት የሥራ ክፍሎች ሪፖርት የሚያቀርቡላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ያደቻ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የወንጪ፣ የጎርጎራ፣ የሀላላ ኬላ እንዲሁም የጨበራ ጩርጩራ ሪዞርቶችን አጠናቆ ወደ ሥራ ለማስገባት በአጠቃላይ 50 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀን ገደብ ባልተቀመጠለት የማስተዳደርና የዕለት ተዕለት ሥራዎችንም የማስፈጸም ኃላፊነቱ፣ ሪዞርቶቹ የሚያስፈልጓቸውን ያላለቁ ግንባታዎች ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገውን ወጪ በአየር መንገዱ እንደሚሸፈን ኃላፊው ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በበላይነት በሚመሩት በ‹ገበታ ለአገር› እና በ‹ገበታ ለትውልድ› ፕሮጀክቶች ተሠርተው፣ የአስተዳደር ሥራቸው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተላለፉት መካከል የወንጪ ሪዞርት የማስታዋወቅ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ (Soft Opening) መከናወኑን፣ ሀላላ ኬላም በተመሳሳይ ባለፈው በነሐሴ ወር ሥራ መጀመሩን አሳውቀው፣ በጨበራ ጩርጩራ ግን የቀሩ የሚሠሩ ሥራዎች መኖራቸውንና ጎርጎራም በተመሳሳይ ሒደት ውስጥ እንደሚገኝ አሳውቀዋል።

አቶ ለማ ‹‹ሆቴሎች ሥራ ሲጀምሩ ምንጊዜም እስከ ሦስት ወር ያለው የመጀመርያ ጊዜ ያለው የሥራ ጫና የሚታይበት፣ የሥራ ሒደት ፍሰቱ ልከኝነት የሚገመገምበትና በሙሉ አቅሙ እስኪሠራ ድረስ በዚህ ሁኔታ እየሠራን ነው፤›› ብለዋል።

በአራቱም ሪዞርቶች ያልተጠናቀቁ ሥራዎች ለመጨረስና ሙሉ ለሙሉ በይፋ ወደ ሥራ ለማስገባት የሚፈጀው የገንዘብ መጠን ምን ያህል እንደሆነ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ አቶ ለማ ‹‹ይህንን በምንገመግምበት ጊዜ ሪዞርቶቹ የሦስት ኮከብ ደረጃ ነው ያላቸው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስካይላይት ሆቴል ደግሞ ባለ አምስት ኮከብ ደረጃ ነው ያለው፡፡

ስለዚህ እኛ እነዚህን እንድናስተዳድር ከመንግሥት የሚጠበቅብን በባለአምስት ኮከብ ደረጃ ነው ይህም እያንዳንዱ ሆቴል የተለያዮ የኢንቨስትመንት ደረጃዎችን እንዲፈልጉ ያደርጋቸዋል በዚህ ደረጃ ወደ 50 ሚሊዮን ዶላር የሚፈጁ ይሆናል፤›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ገንዘቡ በአንድ ጊዜ ወጪ የሚደረግ እንደማይሆን የገለጹት የንግድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ወጪው ምንም ያህል ቢሆን አየር መንገዱ ሪዞርቶቹን ወደ አምስት ኮከብ ደረጃ ለማምጣት የሚያስፈልገውን ኢንቨስትመንት እንደሚያደርግ አሳውቀዋል።

የስካይላይት ሆቴል አስተዳደር አሁን ከመንግሥት ከተረከባቸው በተጨማሪም፣ መንግሥት አፈጻጸማቸውን ገምግሞ፣ አሁን በግንባታ ላይ ያሉትን በገረዓልታ፣ ሐይቅና ጅግጅጋ ላይ የሚሠሩትን ሪዞርቶችም እንዲያስተዳድሩ ዕጩ እንዲያደርጋቸው ፍላጎት እንዳላቸውም ጠቅሰዋል።

አሁን የተረከባቸውን በሚያስተዳድራቸው ሪዞርቶች ሰዎች በመኪና ከመሄድ ይልቅ በአየር ትራንስፖርት ሐሳብ ካላቸው በሚል፣ አንዳንዶቹ ሪዞርቶች በውኃ የተከበቡ መሆናቸውንም ታሳቢ በማድረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስካይላይት ሆቴልስ የተለዩ በውኃና በየብስ ላይ ማረፍ የሚችሉ ትንንሽ አውሮፕላኖች (Amphibious Aircraft) አስገብቶ ለማሰማራት የዋጋ ጥናቶችን አከናውኖ የግዥ ሒደቱ ላይ ውሳኔ ለመስጠት የመጨረሻ ክፍል ግምገማ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

አቶ ለማ ሦስት ዓይነት የአውሮፕላን ዓይነቶች ተለይተው ለግምገማ መቅረባቸውንና ግዥውም እንደሚፈጸም ገልጸዋል።

ምን ያህል ገንዘብ ይፈጃል? የሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚወሰነው በሚመረጠው የአውሮፕላን ዓይነት መሆኑን ገልጸው፣ ‹‹ትንሽ ገንዘብ አይደለም የሚሆነው፣ ግን ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ዕድገት የምናበረክተው አስተዋጽኦ ስለሆነ፣ እኛ አሁን ስለገንዘቡ ብዙም ችግር የለብንም፤›› ብለዋል።

አየር መንገዱ እ.ኤ.አ. በ2035 በዓመት 100 ሚሊዮን ደንበኞች ማስተናገድ የሚያስችለውን በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ የሚያስገነባው የኤርፖርት ከተማ ከሚፈጥራቸው ዕድሎች አንዱም፣ አየር መንገዱ 15 ሚሊዮን መንገደኞችን ያስቀመጠውን ዕቅድ እንዲያሳካ ማስቻሉ ነው ብለዋል።

በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑ መንገደኞች ከ65 እስከ 70 በመቶ የሚሆኑት ተላላፊ (Transit) መንገደኞች መሆናቸውንና ወደ አገሪቱ ገብተው ኢንቨስት እንደማያደርጉ ሪፖርተር ከአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ባለሙያዎች ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

@etconp
👍14❤4💔2
Intercon Construction Chemicals 
    
👉 Authorized agent of MC (Conmix), Weber and SIMENTEK

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍4
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

🔰ምን ይፈልጋሉ?

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ 1. መርካቶ
                   á‰.1 አየር ጤና
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👉ተቋራጩ የሚጠበቅበት ሥለሥራ ሪፖርት ማድረግ ግዴታ

በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 3025 (1) እና (2) መሰረት ተቋራጩ የተከናወኑ ሥራዎች የደረሱበትን ሁኔታና እንዲሁም የሥራውን ዋጋ፣ ለሥራ የተጠቀማቸውን ነገሮች (ግብአቶችን የሰው ኃይል እና ማሽኖች/እቃዎች) ታሳቢ ያደረገውን ወጪ ላሠሪው አካል የማሳወቅ ግዴታ አለበት።

በውሉ ላይ የተገለጸ ተቃራኒ ቃል የሌለ እንደሆነ ተቋራጩ በየወሩ መጨረሻ ለአሠሪው ማስታወቅ (ሪፖርት ማቅረብ) እንዲኖርበት ይገደዳል።

[ስንቶቻችሁ ሥራ ቦታ ላይ ተግባራዊ እየተደረገ ነው?]


የቴሌግራም ቻናላችንን ስለሚከታተሉ እጅግ እናመሰግናለን። መሐንዲሶችን እና አርክቴክቶችን ይጋብዙልን! ቤተሰብ እንሁን።

ክብር ለአርክቴክቶች እና መሐንዲሶች!

🎲ሌላኛው የ ስራ ቅጥር እና ጨረታች ሚወጡበት ቻናል ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp
❤7👍6
👉የጨረታ ማስጠበቂያ (Bid Security Bond)

🚧የጨረታ ማስጠበቂያ ለተቋራጮች የወጣ ጨረታ (በተለይ ክፍት ጨረታ /open tender/) የጨረታ ማስጠበቂያ መያዣ በማረጋገጫ ሰነድ ላይ በቴክኒካል ሰነድ (Technical Documents) እንዲካተት ይጠበቃል።

ይህ የጨረታ ማስጠበቂያ (Bid Security Bond) በ’ PPA (section 1)  “instruction to bidder (ITB) አንቀጽ አሥራ ስድስት (article 16) ላይ እንደተመለከተው አንድ ተጫራች የወጣውን ጨረታ ሞልቶ ካስገባ በኋላ ጨረታውን ቢያሸንፍ እና አሸናፊነቱን የሚገልጽ የቅቡልነት ደብዳቤ (Acceptance Letter) ከተጻፈለት በኋላ ሀሳብ ቀይሮ “የተወዳደርኩበትን ጨረታ ትቼዋለሁ፣ የግንባታ ውል መፈራረምም ይሁን ግንባታውን ማከናወን አልፈልግም” ቢል ጨረታውን ለማከናወን የወጣውን ወጪ ለመሸፈን እና በደረጃ ቅደም ተከተል መሰረት ለሌሎቹ አሸናፊዎች ጥሪ ለማድረግ አልያም እንደገና ውድድሩን ለማከናወን የሚያስችል ገንዘብ ተደርጎ ይታሰብና ጨረታውን ላወጣው አካል የሚሰጥ የባንክ ማረጋገጫ ደረሰኝ (Certified Payment Order - CPO) ነው።

የጨረታ ማስከበሪያ(Bid Security Bond) በ'PPA ITB 16.2 መሰረት በካሽ ወይም በተፈረመበት ቼክ ወይም በክፍያ ማዘዣ ወይም በተቀናሽ ሂሳብ ደብዳቤ ወይም በየትኛውም የባንክ ዋስትና ማረጋገጫ ሊገለጽ የሚችል ሆኖ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን መጠን ያህን የሆነ ገንዘብ ወይም ግምቱ ከዚያ የማያንስ ንብረት/ዋስትና ሊሆን ይችላል።

በውጪ ባንኮች የተሰጠ ዋስትና ከሆነ በሀገር ውስጥ ባንኮች በኩል ዋስትናውን የማረጋገጫ ሰነድ መቅረብ አለበት እንጂ የውጪ ባንኮች ዋስትና በቀጥታ ተግባራዊ ሊደረግ አይችልም።

ማንኛውም አስተማማኝ የጨረታ ማስከበሪያ የሌለው የጨረታ መልስ ሰነድ (Bid response) ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ውድቅ መደረግ ይኖርበታል።

ከአንድ በላይ የሆኑ ማኅበራት ላቀረቡት የጨረታ ሙሌት ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ በጋራ ሲያስገቡ የሁሉም ድርጅቶች ስም በጨረታ ማስከበሪያው ላይ መዘርዘር ይኖርበታል።

የገንዘቡ መጠን በጨረታ ሰነዱ Bid Data Sheet ITB Article16ን ተመርኩዞ በወጣው የጨረታ ሰነድ Bid Data Sheet section ሥር ባለው Preparation of Bids በሚለው ሰንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሰው መጠን የተገለጸው መሆን አለበት።

መጠኑ እንደፕሮጀክቱ ስፋት፣ እንደፕሮጀክቱ ወሳኝነት እና እንደተገመተው የጨረታ ማፍረስ ስጋት ታይቶ በጨረታ አውጪው አካል ሊወሰን ይችላል ነገር ግን አሸናፊው ተጫራች የአሸናፊነቱን ደብዳቤ ተቀብሎ ሥራውን መጀመር የሚችል ከሆነ በጨረታ ሰነዱ Bid Data Sheet & ITB 16.5 መሰረት ሙሉ ለሙሉ ተመላሽ ይሆናል።

የጨረታ ማስጠበቂያ (ማስከበሪያ) ገንዘብ ለተጫራቹ የሚመለስበት ጊዜ በ’ITB, article 16 (16.2) መሰረት ለ28 ቀናት በባንክ ከቆየ በኋላ መሆን አለበት።

በህግ ረገድ ስለዋስተና አይነቶች የሚያብራራው የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 646/2001 ዝርዝር አንስቷል።

የጨረታ ማስከበሪያ ለተጫራቹ የማይመለስባቸው ምክንያቶች፦

[1ኛ] ተጫራቱ ጨረታውን ቢያሸንፍም ሥራውን ተዋውሎ ለመሥራት ፍቃደኛ ካልሆነ ወይም ሀሳብ ከቀየረ፣

[2ኛ] ተጫራቹ የዋጋ ማስተካከያ በPPA ITB clause 27 (በታወቁ ስህተቶች መሰረት የተሞላ አግባብነት የሌለውን ዋጋ ስለማውጣት የተደነገገ አንቀጽ) መሰረት የተደረገ የዋጋ ማስተካከያ ርምጃዎችን አልቀበልም ካለ::

[3ኛ] አሸናፊው ተጫራች ሥውል ፈጽሞ ራውን ለመሥራት ፈቃደኛ ቢሆንም በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ውል መፈረም ካልቻለ ወይም ሌሎች የውል ማስከበሪያዎችን ማቅረብ ካልቻለ ነው።

🔰የቴሌግራም ቻናላችንን ስለሚከታተሉ እጅግ እናመሰግናለን።

🌟መሐንዲሶችን እና አርክቴክቶችን ይጋብዙልን! ቤተሰብ እንሁን።

Link: t.me/ETCONp

ማንኛውንም ሀሳብዎን ሊጽፉልን ካሰቡ t.me/ETCONpBOT ላይ ይጻፉልን።

@ETCONpWORK
👍17❤1
👉የከተማ መሬት መረጃ አያያዝ ስርአት / ካዳስተር/ ምንነትና የሚያስገኘው ጠቀሜታ

🚧ካዳስተር ማለት የመሬት ይዞታን መሰረት ያደረገ የመሬት መረጃ ሥርዓት ሲሆን የሚደራጁት መረጃዎችም በዋናነት ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡

ይኸውም የካርታ መረጃ (spatial data) አንዱ ሲሆን የይዞታውን መገኛ ቦታ፣ ወሰኑን፣ ስፋቱንና ቅርፁን፣ አጎራባች ይዞታዎችን እንዲሁም አዋሳኝ መንገዶችን የሚያሳይ ይሆናል፡፡

ሁለተኛው ገላጭ መረጃ (non-spatial data) በመባል ይታወቃል ይህም የባለይዞታውን ማንነት (ስም፣ አድራሻ፣ ጾታ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ ወዘተ.)፣ በይዞታው ላይ ያለው መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት፣ የቦታው አገልግሎትና ደረጃ፣ ወዘተ. እንደ ካዳስተር ዓይነቱ ተዘርዝረው የሚያዙ መረጃዎችን የሚያካትት ሲሆን እነዚህ ሁለት የመረጃ ዓይነቶችም በልዩ የይዞታ መለያ ኮድ እንዲገናኙ ይደረጋል፡፡

ካዳስተር ህጋዊ ካዳስተር ፤ፊስካል ካዳስተር እና ሁለገብ ወይም ሁሉን አቀፍ ካዳስተር ተብሎ በሦስት ይከፈላል፡፡  

ህጋዊ ካዳስተር ተብሎ የሚጠራው ለእያንዳንዱ ህጋዊ ወሰን ለተለየለት ይዞታ፣ የይዞታ መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት የሚያመለክት መረጃ ከይዞታው ካርታ ጋር አጣምሮ የያዘ ወቅታዊ የመሬት ይዞታ መረጃ ሥርዓት ሲሆን አስፈላጊነቱም የትኛው ይዞታ በማንና በምን አግባብ ተይዟል የሚለውን በማጣራት የባለይዞታው የይዞታ ዋስትና የሚረጋገጥበት ይሆናል፡፡

ሁለተኛው ፊስካል ካዳስተር ሲሆን በይዞታው ላይ ስላረፈው ቋሚ ንብረት ዝርዝር መረጃ እና የመሬቱን ወቅታዊ ግምት ከይዞታው ካርታ ጋር የሚይዝ ሆኖ ለቦታና ለንብረት ግብር ክፍያ የሚያገለግል ሥርዓት ነው፡፡

ሦስተኛው የካዳስተር ዓይነት ሁለገብ ወይም ሁሉን አቀፍ ካዳስተር የሚባለው ሲሆን በሁለቱ የካዳስተር ዓይነቶች የተገለፁትን መረጃዎች የሚይዝ ሆኖ በተጨማሪም የመሰረተ-ልማት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ሌሎች መረጃዎችን እና ካርታን አካቶ የሚይዝ የመረጃ ሥርዓት ነው፡፡

የካዳስተር ሥርዓት በመገንባት ሂደት በርካታ ልምድ ያላቸውና ብዙ ርቀት የሄዱ አገሮች እንዳሉ ይታወቃል በዚህ የግንባታ ሂደት እያንዳንዱ አገር ከራሱ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር አጀማመሩና አካሄዱ የተለያየ ነው፡፡

በእኛ አገር ደረጃም ከዚህ ቀደም በከተማ ደረጃ ሥርዓቱን ለመዘርጋት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፤ የተሞከረውም ሁለ-ገብ ካዳስተርን በመዘርጋት ነበር፤ ሆኖም ግን የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣና የሥርዓቱን ዘለቄታዊነት የሚያረጋግጥ ሊሆን አልቻለም፡፡

በመሆኑም በቅድሚያ ባለይዞታውን ተጠቃሚ የሚያደርገው ከተማ አስተዳደሮችም መሬታቸውን ቆጥረው ሊያውቁ የሚችሉበትን የህጋዊ ካዳስተር በመዘርጋት በመቀጠልም የፊስካል ካዳስተር ብሎም ወደ ሁለ-ገብ ካዳስተር የሚያድግ ሥርዓት መዘርጋቱ ሥርዓቱን ቀጣይ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን በመገንዘብ በአገራችን በሚገኙ ከተሞች ተግባራዊ ማድረግ እጅግ በጣም አስፈላጊ ሁኖ ተገኝቷል፡፡

መሬት በቁጠባ ሊተዳደር የሚገባው አላቂ ሃብት በመሆኑ በአጠቃቀም እንዳይባክን ብክነት የሚወገድበትን አሰራር መፍጠር ያስፈልጋል፡፡

የመሬት መረጃ አያያዝ እንደ ወቅቱ የቴክኖሎጂ ደረጃ መንግስታት መሬትን ለማስተዳደር እንደሚከተሉት የመሬት አስተዳደር እንዲሁም መረጃን ዘመናዊ ለማድረግ ካላቸው ቁርጠኝነት ጋር ተያይዞ የሚወሰን ሲሆን ይህም በፖሊሲዎች እና በህግ ማዕቀፎች ላይ የሚንጸባረቅ ይሆናል፡፡

በዋናነት ካዳስተር መረጃ ላይ በመመርኮዝ በከተሞች የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ የቋሚ ንብረት ሃብት ወደ ገበያ እንዲገባ ከማስቻል ባለፈ ዜጎች የኢኮኖሚው እድገት እንቅስቃሴ አካልና ተጠቃሚ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፤ ይህ ደግሞ መልካም አስተዳደርን እውን ከማድረግና ልማታዊነትን ከማረጋገጥ አንፃር ትርጉም የሚሰጠው ሆኖ እንዲተገበር ተከታታይነት ያለው ሥራ በእቅድ ይዞ መስራት ያስፈልጋል፡፡

ዘመናዊ እና የተደራጀ የከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባ ስርዓት ዝርጋታ እውን መሆን፤ ውስን የሆነውን የከተማ መሬት በተገቢው መንገድ ለተገቢው አገልግሎት ለማዋል ብሎም በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ መስጠት እንዲቻል ከማድረጉም በላይ የህብረተሰቡን የመሬት ይዞታ ባለቤትነት ዋስትናን በማረጋገጥ የከተሞች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ያስችላል፡፡

የከተማ መሬት መረጃ ሥርዓትን በከተሞች ተግባራዊ ማድረግ በዘርፉ የሚስተዋሉትን የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮች ለማድረቅ፤ ለልማት የተመቻቸ ፖለቲካል ኢኮኖሚ ለመፍጠር፤ ህገ-ወጥነትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል፤ የከተሞችን የገቢ አቅም ለማሳደግ፤ በይዞታ የመጠቀም መብትንና የንብረት ባለቤትነት ዋስትናን ለማረጋገጥ፤ ቀልጣፋ፤ ግልፅና ተጠያቂነት ያለበት የመሬት አስተዳደርን ለማረጋገጥ እንዲሁም የከተማ መሰረተ-ልማትን ለማስፋፋትና በአግባቡ ለማስተዳደር ትልቅ አቅም ይሆናል፡፡

በአጠቃላይ በአገራችን የህጋዊ ካዳስተር ዝርጋታ በአተገባበር ሂደት እየጋጠሙ የሚገኙ ዋና ዋና ችግሮችን ለመቅረፍና አፈጻጸሙን ከፍ ለማድረግ  የመሬት ይዞታ መዝጋቢ ተቋማት፣ የመሬት ልማት ማኔጅመንትና የከተማ ፕላን ወጥና ተናባቢ የመሬት ዕቅድ በማውጣት ለዕቅዱ መሳካት በጋራ ሊረባረቡ ይገባል፡፡

እነዚህን ሥራዎች ለማከናወን የሚያስችል የፋይናንስ አቅም መፍጠር፣ ይሄን ስራ ለማቀላጠፍና ዘመናዊ ለማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ማድረግና ፈፃሚውና አስፈፃሚው፣ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ነዋሪው በአሰራሩ ላይ ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ እና በስራው ላይ ሙሉ ተሳታፊ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

@etconp
👍14🙏4
👉ሞሮኮ የዓለማችን ግዙፍ ስታዲየም ግንባታ ዲዛይን ይፋ አደረገች

ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ የ2030ን ፊፋ ዓለም ዋንጫ ከስፔን እና ፖርቹጋል ጋር በቅንጅት የማዘጋጀት እቅድ አላት።

48 ብሔራዊ ቡድኖች እንደሚሳተፉበት የሚጠበቀው ይህ የዓለም ዋንጫ በ20 ስታዲየሞች እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ስፔን ለዚህ ውድድር 11 ስታዲየሞችን እንደምታዘጋጅ ስትገልጽ ቾርቹጋል ሶስት እንዲሁም ሞሮኮ ደግሞ ስድስት ስታዲየሞችን እንደሚያዘጋጁ አስታውቀዋል።

ሞሮኮ ለዚህ ውድድር ከምታዘጋጃቸው ስድስት ስታዲየሞች መካከል አንዱ "ሀሰን ሁለተኛ" የተሰኘ ስታዲየም የግንባታ ዲዛይን ይፋ አድርጋለች።

ይህ ስታዲየም ሲጠናቀቅ 115 ሺህ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ይኖረዋል የተባለ ሲሆን በግዝፈቱ ከዓለም ትልቁ እንደሚሆን ተገልጿል።

የሞሮኮ ብዙሀን መገናኛዎች እንደዘገቡት ከሆነ አዲሱ ስታዲየም ከሀገሪቱ ዋና ከተማ ካዛብላንካ 38 ኪሎ ሜትር ላይ ይገነባል።

በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ግንባታው ይጀምራል የተባለው ይህ ስታዲየም በ2028 ይጠናቀቃል ተብሏል።

ዓለም አቀፉ የስፖርት ፌዴሬሽን ወይም ፊፋ የ2030 ዓለም ዋንጫ አስተናጋጅ ሀገራትን እስካሁን በይፋ አላሳወቀም።

ውድድሩን ለማዘጋጀት እየተፎካከሩ ካሉ ሀገራት መካከል ሞሮኮ፣ ስፔን እና ፖርቹጋል እንደሚያሸንፉ ይጠበቃል።
ይሁንና ሶስቱ ሀገራት የፍጻሜውን ውድድር ማን ያስተናግድ የሚለውን እስካሁን አልተስማሙም።

@etconp
👍16
👉የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት የላቀ ብቃት ያካበቱ ባለሙያዎችን ለማፍራት ማስቻሉ ተገለጸ

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት በሲቪልም ሆነ በሃይድሮ ሜካኒካል ሥራዎች የላቀ ብቃት ያካበቱ ባለሙያዎችን ማፍራት መቻሉ ተገለጸ።

የግድቡ ግንባታ ፕሮጀክት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ኤፍሬም ወልደኪዳን (ኢ/ር)፤ ለፕሮጀክቱ ስኬት ከዲዛይን ጀምሮ እስከ ግንባታው የኢትዮጵያውያን ሚና የላቀ መሆኑን አስታውሰዋል።

የፕሮጀክቱ ግንባታ ሲጀመር በአንድ ጊዜ እስከ 15 ሺህ ዜጎች በግንባታው ሂደት ላይ በተለያዩ ሙያዎች ይሳተፉ የነበሩ ባለሙያዎች ሌት ከቀን በመትጋት ለግድቡ እውን መሆን ዘላለማዊ አሻራቸውን በማሳረፍ የሚያኮራ ተግባር ፈፅመዋል ብለዋል።

በግንባታው የረጅም ዓመት ልምድ በቀን ሰራተኝነት የጀመሩ በርካታ ወጣቶች አሁን ላይ ከፎርማን እስከ ሱፐርቫይዘርነት መድረሳቸውን አብራርተዋል።

በዚህም በሲቪልም ሆነ በሃይድሮ ሜካኒካል ሥራዎች የላቀ ብቃት ያካበቱ በርካታ ባለሙያዎችን ማፍራት ስለመቻሉ መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ግድቡ 13 ተርባይኖች እንዳሉት ገልጸው፤ የጀነሬተር አካል እስከ 12 ሜትር ዲያሜትርና ከ460 ቶን በላይ ክብደት ስላለው በትራንስፖርት አጓጉዞ ለማድረስ ፈታኝ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ነገር ግን በፕሮጀክቱ ግንባታ ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን በየጊዜው አቅማቸውን በማጎልበት ዛሬ ላይ ግብዓቶችን በስፍራው እንዲገጣጠሙ ማድረግ የሚችሉበት አቅም ተፈጥሯል ብለዋል፡፡
በመሆኑም በቀጣይ ኢትዮጵያ

ለምትገነባቸው የሀይድሮ ፓወር ፕሮጀክቶች የሙያ ብቃትና ዝግጁነት እንዲኖር አስችሏል ሲሉ ተናግረዋል።

የግድቡ ግንባታ ሲጀመር ተቀጥረው ይሰሩ እንደነበር ያስታወሱት የኬ.ቲ ኢንዱስትሪያል ሶሉሽን ሥራ አስኪያጅ ሞላ አስማረ፤ በሂደት የራሳቸውን ድርጅት ከፍተው ለተርባይን ማቀዝቀዣ ክፍል አካል የሆነውን ራዲያተር በራሳቸው መስራት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡

አብዛኛውን የፕሮጀክቱን ግብዓት በራሳቸው መሥራት እንደሚችሉ ገልጸው፤ ከአቅም ግንባታ ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ያስችላልም ብለዋል፡፡

በግድቡ ላይ በተለያዩ ሙያዎች ላይ የተሳተፉ በርካታ ወጣቶች በየዘርፉ የተሻለ የሙያ ደረጃ ላይ የደረሱ እንዳሉም ተናግረዋል።

Via FBC

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍12❤5🏆1