Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
በአለም ሁለተኛው ረዥሙ ህንጻ
ቡርጅ አዚዚ፣ ዱባይ

በጥር ወር በዱባይ የዓለማችን ሁለተኛው ረጅሙ ህንጻ አዲስ ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ለመገንባት መታቀዱ ታውቋል።

አሁን፣ በአዚዚ ዴቨሎፕመንትስ እየተገነባ ያለው 725 ሜትር (2,378 ጫማ) ቡርጅ አዚዚ በግንባታ እየገሰገሰ መሆኑ ተረጋግጧል።

ይህ ባለ 131 ፎቅ ህንጻ  ውበት ያለው፣ የሚያብረቀርቅ ውጫዊ ክፍል እና በሰባት የባህል ጭብጦች ተመስርቶ  የቅንጦት "ሰባት ኮከብ" ሆቴል ይኖረዋል። 

እንዲሁም ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው መኖሪያ ቤቶችን፣ ፔንት ሃውስን፣ አፓርታማዎችን እና የዕረፍት ጊዜ ቤቶችን ጨምሮ ይይዛል።

በውስጡ፣ ቡርጅ አዚዚ የዓለምን ከፍተኛውን የምሽት ክበብ፣ ሬስቶራንት እና የመመልከቻ መድረክንም ይይዛል ሌሎች መገልገያዎች ደግሞ የጤንነት ማእከላትን፣ የመዋኛ ገንዳዎችን፣ ሲኒማ ቤቶችን እና ጂሞችን ያካትታሉ።

አዚዚ ህንጻውን በ2028 ለመጨረስ በማለም ከ6 ቢሊዮን ድርሃም (1.6 ቢሊዮን ዶላር) በላይ ኢንቨስት አድርጓል።

ህንጻው  ለከፍተኛው የሆቴል አዳራሽ ( 1ኛ ፎቅ )፣ የምሽት ክበብ (126ኛ ፎቅ )፣ የመመልከቻ ወለል (130ኛ ፎቅ ) እና ሬስቶራንት (122ኛ ፎቅ ) ላይ በመገንባት አለምአቀፍ  ሪከርዶችን ይሰብራል።

በሼክ ዛይድ መንገድ፣ በዱባይ የዓለም ንግድ ማእከል አውራጃ፣ ቡርጅ አዚዚ አሁንም ከሁለት ማይል ባነሰ ርቀት ላይ ካለው 2,717 ጫማ ቁመት ቡርጅ ካሊፋ በ 340 ጫማ ያጥራል ነገር ግን ከአሁኑ የዱባይ ሁለተኛው ረጅሙ ህንጻ  ማሪና 101 (1,394 ጫማ) በልጦ ለከተማው ሁለተኛ ረጅሙ ህንጻነት ውድድርን ያሸንፋል።

አንዴ ግንባታው ከተጠናቀቀ  አሁን ካለው የአለም ሁለተኛ-ረጅሙ ህንጻ፣ የማሌዢያ 2,227 ጫማ ቁመት ያለው መርዴካ 118 በቁመት ይበልጣል።

@etconp
👍14❤3
🩸⏺The property of soil by virtue of which it takes any desired pattern shapes under pressure and retains it after the pressure is removed is known as:
Anonymous Quiz
68%
Plasticity
8%
Flow ability
14%
Porosity
10%
Collapsibility
👍9❤4
Q. After which of following water treatment units, turbidity is maximum?
Anonymous Quiz
17%
A. Chlorination
27%
B. Primary sedimentation
39%
C. Flocculation basin
17%
D. Secondary sedimentation
👌6👍4
👍10🏆10❤3
Intercon Construction Chemicals 
    
👉 Authorized agent of MC (Conmix), Weber and SIMENTEK

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍4
. 人 ★* 。 • ˚* ˚ 🌙
. ( _ _) * ኢድ * ★
. ┃口┃ * ሙባረክ *
. ┃口┃★ * ***. . *˛•
. ┃口┃★ * •★ 。•˛˚˛*
. ┃口┃ •˛˚˛* 人 •˛˚ *
. ┃口┃ .-:'''"''''"''.-.
. ┃口┃ (_(_(_()_)_)_)
. ┃口┃_┃∩∩∩∩∩∩┃
. ┃口┃_┃∩∩∩∩∩∩┃
. ||三||_||三三三三三||
👉የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ለሆናችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች እንዲሁም ለመላው ሙስሊም ኢትዮጵያውያን እንኳን ለተከበረው ለ መውሊድ በዐል በሰላም አደረሳችሁ።
. ‌‌‌‌ ╔═════ ❁✿❁ ═════╗
. ★ ★ ★ ☆ ☆ ☆
@etconp
❤8👍4🙏4💔1
👉የዓለማችን ድንቅ እስላማዊ የ ኮንስትራክሽን ስትራክቸሮች እንሆ

🚧1. መስጂድ አል-ሀራም፡-

መካ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኝ መስጂድ አል-ሀራም የአለማችን ትልቁ መስጂድ ሲሆን በእስልምና እጅግ የተቀደሰ ቦታ የሆነውን ካባንን ይከብባል። 

መስጂዱ በሀጅ ወቅት እስከ 4 ሚሊዮን ሰጋጆችን ማስተናገድ ይችላል።

🚧2. መስጂድ አል-ነበዊ፡-

በመዲና፣ ሳውዲ አረቢያ፣ መስጂድ አል-ነበዊ በእስልምና ሁለተኛው ቅዱስ መስጂድ ነው። etconp

የነብዩ መሐመድ መቃብር የሚገኝበት ሲሆን በግሩም አረንጓዴ ጉልላት እና በዓይነቱ ልዩ የሆነ የስነ-ህንፃ ጥበብ ይታወቃል።

🚧3. ቡርጅ ካሊፋ፡ 828 ሜትር ላይ የቆመው ቡርጅ ካሊፋ በዱባይ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ በአለማችን ረጅሙ ህንፃ ነው።

ኢስላማዊ እና ዘመናዊ ኪነ-ህንፃዎች ቅልቅል ያለው እና ተወዳጅ የቱሪስት መስህብ ነው። etconp

4. ሱልጣን አህመድ መስጂድ፡-

በተለምዶ ሰማያዊ መስጂድ በመባል የሚታወቀው በቱርክ ኢስታንቡል የሚገኘው ሱልጣን አህመድ መስጂድ የውስጥ ግድግዳውን እና ስድስቱን ሚናራዎችን በሚያጌጡ ሰማያዊ ሰቆች ይታወቃል። etconp

የኦቶማን አርክቴክቸር ድንቅ ስራ ነው።

🚧5. ሀሰን II መስጂድ፡

በሞሮኮ ካዛብላንካ ውስጥ የሚገኝ፣ ሀሰን 2 መስጂድ በአለም ላይ ካሉት ትልቁ መስጊዶች አንዱ ነው እና አስደናቂ የእብነበረድ ውስጠኛ ክፍል፣ ውስብስብ የጣር ስራ እና አስደናቂ የባህር ዳርቻ አቀማመጥ አለው። etconp

🚧6. አልሀምብራ፡

በግራናዳ፣ ስፔን ውስጥ የምትገኝ፣ አልሀምብራ መጎብኘት ያለበት የእስልምና አርክቴክቸር ድንቅ ነው። etconp

ይህ ቤተ መንግስት እና ምሽግ ውስብስብ የስቱኮ ማስዋቢያዎች፣ የፈረስ ጫማ ቅስቶች እና የተረጋጋ የአትክልት ስፍራዎችን ያሳያል።

🚧7. የሼክ ዛይድ ታላቁ መስጊድ፡

በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አቡ ዳቢ የሚገኘው የሼክ ዛይድ ታላቁ መስጂድ የዘመናዊ ኢስላማዊ ኪነ-ህንፃ ድንቅ ስራ ነው። etconp

ነጭ የእብነበረድ ጉልላቶች፣ ውስብስብ ቅርጻ ቅርጾች እና አስደናቂ የአበባ ንድፎችን ይዟል።

🚧8. ታላቁ የኮርዶባ መስጊድ፡

በ8ኛው ክፍለ ዘመን በኮርዶባ፣ ስፔን ውስጥ የተገነባው ታላቁ የኮርዶባ መስጊድ የሞሪሽ፣ የጎቲክ እና የህዳሴ ስነ-ህንፃ ቅጦች ድብልቅልቅ የሚያሳይ የባህል ሀብት ነው። 

ውስጣዊ ክፍሎቹ ከ 850 በላይ አምዶች እና ውስብስብ ቢሞች ኣሉት።

❤️መልካም ዒድ😇

@etconp
❤13👍12🙏1
Ethio Construction Engineering
👉የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት) አቦሴራ በሚባል ሥፍራ  የሚያስገነባውን የግዙፉን ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ዛሬ ይፋ ያደርጋል። 🚧አየር መንገዱ ፕሮጀክቱን በይፋ ለማስጀመር፣ በስካይ ላይት ሆቴል ከቀትር በኋላ ከአንድ ዓለማቀፍ ኩባንያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት እንደሚፈራረም ታውቋል። ⭐️አየር መንገዱ የፕሮጀክቱን የመግባቢያ ስምምነት ከየትኛው ዓለማቀፍ…
👉ከ 6 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው አዲሱ ኤርፖርት ምን ምን ይይዛል?

በዓመት 100 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ያለው አውሮፕላን ጣቢያ በቢሾፍቱ ከተማ እንደሚገነባ ገልጿል።

ይህ አውሮፕላን ማረፊያ ወይም ኤርፖርት የሚገነባው በዓመት 25 ሚሊዮን መንገደኞችን ብቻ የማስተናገድ ያለው ቦሌ ዓከም አቀፍ ኤርፖርትን ለመተካት እንደሆነ የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።

በቢሾፍቱ ልዩ ስሙ አቡ ሴራ በተባለው ስፍራ የሚገነባው ይህ ኤርፖርት ግንባታ ዲዛይን መቀመጫውን አረብ ኢምሬትስ ያደረገው ዳር የተሰኘው ኩባንያ መመረጡንም አቶ መስፍን ገልጸዋል።

አቶ መስፍን አክለውም አዲሱ ኤርፖርት ግንባታ በአምስት ዓመታት ውስጥ በሁለት ዙር ይገነባል ያሉ ሲሆን ለመጀመሪያው ዙር ግንባታ ስድስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደርግበታልም ብለዋል።

ኤርፖርቱ ባንድ ጊዜ አራት አውሮፕላኖችን የማሳረፍ እና መንደርደሪያ መም ይኖረዋል ተብሏል።

270 አውሮፕላኖችን የማሳረፍ አቅም ያለው አዲሱ ኤርፖርት ከቦሌ ኤርፖርት ጋር የሚያስተሳስር ፈጣን ባቡር እና መንገድ እንደሚገነባ ተገልጿል።

ለአዲሱ ኤርፖርት ግንባታ የሚያስፈልገው ስድስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ በብድር እንደሚሸፈን የተገለጸ ሲሆን ብድር ለመስጠት የሚፈልጉ ተቋማት መገኘታቸውንም አቶ መስፍን ተናግረዋል።

ይሁንና የአዲሱን ኤርፖርት ግንባታ ዲዛይን የሚሰራው ዳር ኩባንያ ወጪ ምን ያህል እንደሆነ አቶ መስፍን ከማገር ተቆጥበዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2016 በጀት ዓመት 7ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንዳገኘ በመግለጽ፤ በዓመቱ 17 ሚሊዮን መንገደኞችንም እንዳስተናገደ ማስታወቁ ይታወሳል።

@etconp
👍14❤5
@etconp_CAUSES_OF_FAILURES_OF_FOUNDATIONS_AND_REMEDIAL_MEASURES.pdf
541.9 KB
Causes of failure of foundation and remedial measures

1. Unequal settlement of subsoil

2. Unequal settlement of masonry

3. Subsoil moisture movement

4. Lateral movement of sub soil

5. Lateral movement of sub soil

6. Weathering of subsoil due to tress and shrubs

7. Atmospheric action


Video ይዘንላችሁ እንመጣለን

@etconp
🙏14👍5❤3😢1
👉በቻይና የሪል ስቴት ቤት ዋጋ ቀነሰ

🚧ዋጋው በዘጠኝ ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት መውደቁ እየተገለጸ ነው።

በዚህ የተነሳ የቻይና ገንቢዎች ከመጠን በላይ በሆነ አቅርቦት እና ፍላጎት እየቀነሰ ስለመጣ ከከባድ ዕዳ ጋር እየታገሉ ነው ተብሏል።

ይፋዊ መረጃ እንደሚያሳየው በቻይና ውስጥ ያሉ የሪል ስቴት የቤት ዋጋዎች ባለፈው ወር የተመዘገበው ብቻ ካለፉት በዘጠኝ አመታት ወዲህ በጣም ፈጣን ቅናሽ ማሳየቱን ሮይተርስ ዘግቧል።

ባለፈው ግንቦት ወር ብቻ የአዳዲስ ሪል ስቴት የቤት ዋጋ ካለፈው ሚያዝያ ወር ከነበረበት ዋጋ  0.7 ፐርሰንት ቀንሷል።

ሮይተርስ በቻይና ብሄራዊ ስታቲስቲክስ ቢሮ ከተለቀቀው መረጃን ጠቅሶ እንደዘገበው፦  የሪል ስቴት የቤት ዋጋዎች ከወር እስከ ወር የሚመዘገው ዴታ አሁንም በቀጥታ ለ11ኛ ጊዜ የቀነሰ ሲሆን፣ ከጥቅምት 2014 ወዲህ ቅናሹ ቀስ በቀስ እየጨመረ መጥቷ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ ዋጋው እያሽቆለቆለ ሊመጣ ችሏል። በግንቦት ወር የተመዘገው የሪል ስቴ ዋጋ አሃዝ ከአንድ አመት በፊት ከነበረው በ3.9% መቀነሱን ሮይተርስ ጠቅሷል።

የቻይና የፕሮፐርቲ ሴክተር የኢኮኖሚ እድገቷ ዋና ሞተር ቢሆንም በ2021 ግን የመንግስት ቁጥጥሮች እና እገዳዎች በሪል ስቴት ዘርፍ ያለውን ዘላቂ ያልሆኑ የብድር እዳዎችን ሲያጋልጡ በቤቶች ዋጋ ዙሪያ ቀውሱ መከሰት መጀመሩ ይነገራል።

በቻይና ውስጥ ከሚገኙ የሪልስ ስቴት አልሚዎች መካከል Country Garden፣ Evergrande እና Vanke የመሳሰሉ ከፍተኛ የዕዳ ጫና ያለባቸው ገንቢዎች  እንደሆኑ ተገልፆል።

የሪል ሴቴት ኩባንያዎቹ  አስቀድመው የተሸጡ የቤት ግንባታዎችን አፓርታማዎች መጨረስ አልቻሉም፣ ይህም ቅር በተሰኙ እና በዘርፉ ላይ እምነት ባጡ ተጠቃሚዎች መካከል ያለው የግብይት መስመር እንዲቋረጥ በር ከፍቷል።

@etconp
👍17❤2
👉መያዥያ ገንዘብ (Retention money)

🚧ስራ ተቋራጩ የተሰጠውን ስራውን ጨርሶ የስህተት ማስተካከያ ግዜ ድረስ (defect liability period) ሀላፊነት ለመወጣቱ ማረጋገጫ እንዲሆን ከእያንዳንዱ የክፍያ ቅፅ የሚያዝ ገንዘብ ነው።

💫ከክፍያ ቅፅ ምን ያህል ሊቆረጥበት እንደሚገባ ለፕሮጀክቱ በልዪ ሁኔታ የተዘጋጀው ውል/special condition of contract/በግልፅ ሊያስቀምጥ ይገባል።

🏷ሆኖም ከ አስር ፐርሰንት (10%) የበለጠ መሆን አይችልም።

🌟በሀገራችን አብዛኛውን ግዜ አምስት ፐርሰንት(5%) ብቻ የተለመደ ነው ስራው እንደተጠናቀቀ ግማሹ ከመጨረሻ ክፍያ ጋር ቀሪው ደግሞ ከርክክብ በኋላ ስራው ላይ ስህተት ቢፈጠር በውሉ ላይ የማስተካከያ ቀነ ገደብ ሲጠናቀቅ ከመጨረሻ ርክክብ ጋር በ አርባ አምስት (45) ቀናት ውስጥ ይለቀቅለታል።

❇️ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን!

@etconp
👍19❤7
ሥራ ተቋራጩ የኮንስትራክሽን አገልግሎቱን በሚያከናወንበት ጊዜ ብዙ ፈተናዎች እየገጠሙት እነደሆነ ይታወቃል፡፡እስቲ ከስር ከተዘረዘሩት ምርጫዎች ሦስት አንገብጋቢ የሥራ ተቋራጮችን ፈተናዎች ይምረጡልን፡፡
(በሥራ ተቋራጭነት አገልግሎት ቀን ዙሪያና ሥራ ተቋራጩ እየገጠመው ሥላለው ፈተናዎች በ Comment ላይ አጋሩን፡፡)
Anonymous Poll
25%
ወጥነት ያለው ህግ አለመኖር የህጎች መቀያየር
54%
የግንባታ ግብዓት የአቅርቦት ችግሮች
56%
የገንዘብ የመግዛት አቅም መቀነስ
47%
ፍትሃዊ ያለሆነ የገበያ ውድድር መኖር
17%
ችሎታ ያለው የግንባታ ሰራተኛ አለማግኘት
52%
የጸጥታ ችግር
56%
ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ ለማድረግ የባለቤቶች በጀት እጥረት መኖር እና የባንኮች የፋይናንስ አማራጭ እንደልብ አለመኖር
🕊14👍4❤3
👉ሌላኛው ቻናላችን ተቀላቅለዋል?

⚡️ዛሬ የወጡ  የስራ ቅጥሮች ጨምሮ

🌟አዳዲስ የኮንስትራክሽን ጨረታዎች ሲወጡ በቀላሉና በ ትኩሱ ለመመልከት ከታች ባለው ሊንካችን ይቀላቀሉን።

📌እንዲሁም ለወዳጆቻቹ SHARE በማረግ አዳርሱ።

https://t.me/ETCONpWORK
🙏5👍2
Intercon Construction Chemicals 
    
👉 Authorized agent of MC (Conmix), Weber and SIMENTEK

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍7