Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.28K photos
359 videos
1.99K files
3.36K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

🔰ምን ይፈልጋሉ?

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍2❤1
👉በሊዝ የተያዘ መሬት ላይ ግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ

🚧ሀ) ግንባታ ማስጀመሪያ

አንድ ግለሰብ/ድርጅጥ በከተማ ቦታ ላይ በሊዝ የተረከበው ቦታ ላይ የሊዝ ውል ከፈረመበት ቀን ጀምሮ ለቦታው በተቀመጠው ደረጃ መረሰት ግንባታ እንዳለበት የሚደነግግ የጊዜ ጣሪያ ተቀምጧል።

በሊዝ ቦታ ላይ የግንባታ መጀመሪያ የጊዜ ጣሪያ፦ ለአንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች = 6 ወር፣ ለመካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች = 9 ወር፣ እና ለከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች = 18 ወር ነው ሆኖም ግን እስንደአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች በተጠቀሱት የጊዜ ገደቦች ግንባታ ሳይጀመር ቢቀር ለአንድ ዙር ብቻ የሚፈቀድ ለአንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች  6 ወር፣ ለመካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች 9 ወር፣ ለከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች አንድ ዓመት ተጨማሪ የግንባታ ማስጀመሪያ ጊዜ በግንባታ ፍቃድ ሰጪው አካል ከማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ጋር ሊሰጣቸው ይችላል።

🌟ለ) ግንባታ ማጠናቀቂያ

በሊዝ ቦታ ላይ ግንባታ የማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ፦ ለአንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች 24 ወራት፣ ለመካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች 36 ወራት፣ እና ለከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች  48 ወራት ነው። ነገር ግን የአካባቢው የግንባታ ፍቃድ ሰጪ አካል ካመነበት የግንባታውን ውስብስብነት እያየ ሊያራዝምለት ይችላል። ሆኖም ግን ለግንባታ ማጠናቀቂያ የሚሰጠው ጊዜ በማንኛውም ምክንያት (ሁኔታ) ቢሆን ለአንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች  2 ዓመት 6 ወር፣ ለመካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች 4 ዓምት፣ እና ለከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች ከአምስት ዓመት መብለጥ የለበትም።

❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

📜ለ ስራ እና ጨረታዎች ምንለቅበት ቻናል ለመቀላቀል👉 @ETCONpWORK

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp
👍6❤1🙏1
👉ግዙፉ ለሚ ብሔራዊ ሲሚንቶ ፈብሪካ

🚧በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ ዳርቻ የተንጣለለው ግዙፉ የለሚ ብሔራዊ ሲሚንቶ ፈብሪካ ዛሬ ተመርቆ በይፋ ሥራ ይጀምራል‼️

💫ኢንዱስትሪው ለአካባቢውና ለዞኑ ትልቅ የኢንቨስትመንት አቅም ከመሆኑም ባሻገር  የሀገሪቱን የሲሚንቶ እጥረት ችግር ይፈታል ተብሎ ይታመናል።

🏷ይህ ግዙፍ ፋብሪካ በአማራ ክልል የመጀመሪያው የሲሚንቶ ፋብሪካ ነው።

⏺ይህ ፋብሪካ በ125 ቢሊየን  ብር  (2.2 ቢሊየን ዶላር)  ወጪ  በኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ  ከቻይና ባለሃብቶች ጋር ያስገነባው ሲሆን ፋብሪካው ተጠናቆ ዛሬ ሊመረቅ ነው። 

🌟ይህ በሰሜን ሸዋ ዞን አንሳሮ ወረዳ  እየተገነባ የሚገኘው ለሚ ሲሚኒቶ ፋብሪካ  በቀን ከ 10ሺ ቶን በላይ  ሲሚንቶ የሚያመርት ሲሆን የኢትጵያን የሲሚንቶ ፍላጎት እና እጥረት በትንሹ እንደሚያግዝ ይጠበቃል።

@etconp
❤7👍3
👉ሁለተኛው የኮሪደር ልማት አለም አቀፍ ደረጃን ጠብቆ እንዲከናወን አቅጣጫ ተቀመጠ

🚧የ2ኛው ዙር የኮሪደር ልማት የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ግንባታ አለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ እና በላቀ ጥራት ለመፈፀም በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ  ገልጹ።

🌟ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ፦ የዋና ሥራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት የሚያስተባብረውን የ2ኛው ዙር የኮሪደር ልማት የመሠረተ ልማት ዝርጋታን አስመልክቶ በተካሄደ የውይይት መድረክ፣ የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ለ2ኛው ዙር ልማት ምቹ ሁኔታንና መደላድልን የፈጠረ መሆኑን ጠቁመው፤ በመሠረተ ልማት ዝርጋታው የነበሩ ጥንካሬዎችን የበለጠ ጥራቱን አስጠብቆ ለማስቀጠል አመራሩ ከፍተኛ ኃላፊነት እንደተጣለበት አስገንዝበዋል።

🏷አያይዘውም የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ኮሚቴው ግንባታውን በሚያካሄዱ ተቋማት መካከል የቅንጅት ችግሮችን በመቅረፍ እና ድግግሞሽን በማስቀረት ወጪ ቆጣቢና ዘመን ተሻጋሪ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ መሠረተ ልማቶችን መዘርጋት ላይ ትኩረት ሊያደርግ እንደሚገባም አመልክተዋል።

⭐️ለ2ኛው ዙር የኮሪደር ልማት የመሠረተ ልማት ግንባታ ያለንን ውስን ሃብት፣ የሎጅስቲክስ አቅርቦትና ግብዓቶችን አስተሳስሮ በተናበበ መረጃ ላይ የተመሠረተ የጋራ አመራር መስጠት እንዲቻል አንዱ ተቋም ከሌላው ልምድ እየቀሰመ እንዲሄድ መልካም አጋጣሚ እና እድል የሚፈጠርበት እንደሆነም ኢንጅነር ወንድሙ ጠቁመዋል።

⏺የ2ኛው ዙር የኮሪደር ልማት በቂ ጥናት የተደረገበት ዝርዝር ዓላማና እቅድ የተዘጋጀለት እንደመሆኑ የመሠረተ ልማት ተቋማት እቅዱን መነሻ በማድረግ የሚከናወኑ ሥራዎችን በጠንካራ የትግበራ ስትራቴጂና የክትትልና ድጋፉም በዚያው አግባብ በዲስፕሊን የሚመራ እንደሆነም አስገንዝበዋል።

⏺ኮሚቴው በእቅዱ የተያዙ ስራዎች አለምአቀፍ ደረጃቸውን በጠበቀ ሁኔታ በላቀ ጥራት እንዲፈፀምም በቋሚ የግኑኝነት ጊዜ እየተገመገመ የሚመራ መሆኑን ጠቁመው ውጤታማ እና የተሳካ ሥራ እንዲሠራ ኮሚቴው በእኔነት ስሜት እና በጋራ ግንዛቤ እንዲንቀሳቀስ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

Via AACMO

@etconp
👍3❤2
👉የፋሲል ግንብ መጠነኛ ጥገና ብቻ እንደሚደረግለት ተገለጸ

🚧በጎንደር የሚገኘው የፋሲል ግንብ መጠነኛ ጥገና ብቻ እንደሚደረግለት የኢትዮጽያ ቅርስ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

"የፋሲል ግንብ ጥገና ተጀምሯል" መባሉን ተከትሎ፤ የሚደረግለት እድሳት ወይም ጥገና የቀድሞ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ እንዲሆን ምን ያህል ጥንቃቄ ወይም ጥናት ተደርጓል ሲል አሐዱ ጠይቋል፡፡

በዚህ ረገድ ምላሽ የሰጡት የኢትዮጽያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌ፤ ግንቡ በ2013 እና 2014 በታሪክ ሙህራን እና በአከባቢዉ የመሀንዲስ ባለሙያዎች ጥናት ተደርጎ ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ አነስተኛ እድሳት እንደሚደረግለት ተናግረዋል፡፡

ቅርሱ ከ1980 ጀምሮ ምንም እድሳት እና ጥገና እንዳልተደረገበትም አንስተዋል፡፡

አክለዉም እድሳቱ 3 አይነት ሥራዎችን ያካተተ መሆኑን ገልጸው፤ የመጀመሪው ሙሉ ጥገና፣ ሁለተኛው ግቢውን ማስዋብ እና ሦስተኛው የኤሌትሪክ ሀይል የመስመር ዝርጋታን ያካተተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በ16ኛው ክፍለ ዘመን በተቆረቆረችው በጎንደር ከተማ የሚገኘው የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት እድሳት መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

በ1628 ዓ.ም. የተሠራው የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት ፋሲል ግቢ፤ በውስጡ ቤተ መዛግብት፣ የአፄ ፋሲል መዋኛ፣ ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ራስ ግምብና ደረስጌ ማርያምን የያዘ ሲሆን፤ ቤተ መንግሥቱ በዓለም ቅርሶች መዝገብ በ1979 ዓ.ም. መስፈሩ ይታወቃል፡፡

Via Ahadu Radio

@etconp
👍10❤2
👉Tarbela Dam is located in a small town in Haripur, KPK, and is the world’s largest fill-type dam. It has a total surface area of 260 km² and a catchment area of 170,000 km².

🚧It is also the second-largest dam in the world in terms of reservoir capacity, which is 11.62 million acre-feet (14.3 billion cubic meters).

⏺The project initially started in 1968 and was fully completed in 1984 at a cost of $1.49 billion.

⏺The dam plays a significant role in electricity generation for Pakistan, producing a total of 4,888 MW of power.

▶️In addition to power generation, the water from Tarbela Dam is also highly valuable for irrigation, benefiting regions in KPK, Punjab.

⏺The primary purpose of the Tarbela Dam Project was to regulate the flows of the Indus River for irrigation use.

⏺Other objectives included the substantial generation of hydroelectric power and flood control by conserving snowmelt and monsoon flows of the Indus River.

Via Eagleng

@etconp
👍7❤4
👉ባሳለፍነው ሳምንት ከኖህ ሪል እስቴት ቤት ገዝተው የነበሩ ግለሰቦች ከውላችን ውጪ መሠረተ ልማት ያልተሟላለት ቤት ተረክበን ከፍተኛ ችግር ላይ ነን ማለታቸውን መዘገቡ ይታወሳል።

🚧በዚህ ዘገባ ላይ ከኖህ ግሪን ፓርክ ሳይት መኖርያ አፓርታማ ገዝተው ከተረከቡ ከሁለት አመት በላይ እንደሆናቸው የሚናገሩት ግለሰቦች አሁን ድረስ መብራት እና ዉሀ እንኳን ስላልተሟላ ለመኖር አልቻልንም ማለታቸው ይታወሳል።

በዚህ ዙርያ ኖህ ሪል እስቴት ለመሠረት ሚድያ ምላሽ የላከ ሲሆን የኖህ ግሪን ፓርክ የመኖሪያ መንደር ግንባታ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን መሰረተ ልማት ከመሟላቱ በፊት በቤት ገዢዎች ጥያቄ ወደ ነዋሪዎች የተዛወረ ነው ብሏል፡፡

"የህንጻው ግንባታ ቢጠናቀቅም በወቅቱ መሰረተ ልማት ለማሟት ግን አልቻልንም ነበር፡፡ ገዢዎች ቤቱን የማስጌጥ ሥራ ለመስራት በሚል (ይህም በደብዳቤ ተገልጾላቸው) ቤቱን ተረክበዋል፡፡ ቤቱን ከተረከቡ በኋላ ግን አስቀድመው የገቡትን ቃል በማጠፍ ከጎረቤት መብራት በህገ ወጥ መንገድ በመዘርጋት እና ራሳቸውን ጭምር ለአደጋ በማጋለጥ በመኖር ላይ ይገኛሉ" ብሎ ድርጅቱ ምላሹን ሰጥቶናል።

የመብራት አገልግሎትን በተመለከተ የሪል እስቴት ድርጅቱ በህንጻዎቹ ላይ ያለውን የውስጥ መስመር በወቅቱ የዘረጋሁ ሲሆን ነገር ግን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ትራንስፎርመር በወቅቱ ባለመገኘቱ ከፍተኛ ጊዜ መዘግየት ተፈጥሯል ብሎ በአሁኑ ወቅት ችግሮች ሁሉ ተቀርፈው የመብራት ሥራ በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ ነው ብሏል።

ውሀን በተመለከተ ደግሞ ለውሀ ዝርጋታው መዘግዬት ዋናው ምክንያት ለጀነሬተር እና ለታንከር የተዘጋጀው ቦታ በሶስተኛ ወገን እጅ በመውደቁ እና ቦታውን ለማስለቀቅ በመስተዳድሩ በኩል ንግግር እየተደረገ በመሆኑ ሲሆን አሁን ግን ቦታውን ሙሉ በሙሉ ወደሌላ አቅጣጫ በመቀየር ስራው እየተሰራ ይገኛል ብሏል።

በመጫረሻም የካርታ ጥያቄን በተመለከተ ለግሪን ፓርክ የሚያስፈልገውን 700 ካርታ ካወጣን በኋላ ህትመት በማቆሙ 54 ካርታ ሳይታተም ቀርቷል፣ ይህም መዘግየት ፈጥሯል ብሏል።

በተያያዘ ዜና፣ ኖህ ሪል እስቴት የኢስት ኮንቬንሽን አፓርትመንቶቹን እንዲያስረክብ መደረጉ ታውቋል።

እነዚህ የኖህ አፓርትመንቶች አሁን በመገንባት ላይ ካለው አዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን ማዕከል በአጎራባች ላይ የተገነባ 192 አፓርትመንቶችን የያዘ ህንጻ እንደነበር ታውቋል፡፡

ህንጻው ግን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከፍተኛ ድርሻ ለያዘበት ለአዲስ አፍሪካ ኤግዚቢሽን እና ኮንቬንሽን ሴንተር ማስፋፊያነት ለሆቴል አገልግሎት እንዲሰጥ መስተዳደሩ በመወሰኑ መስተዳደሩ ህንጻውን እንዲያስረክብ ኖህን ማዘዙ ታውቋል፡፡

ይህን ተከትሎም ኖህ በህንጻው ላይ የነበሩትን ደንበኞቹን በቅርብ ርቀት ወደ ሚገኙ የድርጅቱ ሌሎች ህንጻዎች ላይ በመመደብ እያዘዋወረ መሆኑ ታውቋል።

Via Meseret Media

@etconp
👍14❤1🎉1
👉Roof types in building

💫Roof In Building construction play a critical role in aesthetics, functionality, and durability. Here are some common types of roofs, along with descriptions of their characteristics and advantages:

### 1. Gable Roof
   - Description: Characterized by two sloping sides that meet at a ridge, forming a triangular shape.
   - Advantages:
     - Simple design and easy to construct.
     - Excellent for water drainage and ventilation.
     - Allows for additional attic space or vaulted ceilings.

### 2. Hip Roof
   - Description: A roof with slopes on all four sides that converge at a top, forming a ridge.
   - Advantages:
     - Stronger against high winds compared to gable roofs.
     - Offers better stability and longevity.
     - Provides more ventilation options.

### 3. Flat Roof
   - Description: A horizontally level roof with a slight pitch for drainage.
   - Advantages:
     - Easily accessible for maintenance and equipment installations.
     - Suitable for rooftop gardens and recreational areas.
     - Cost-effective construction.

### 4. Mansard Roof
   - Description: A four-sided roof with two slopes on each side, the lower slope being steeper than the upper slope.
   - Advantages:
     - Maximizes living space in the attic.
     - Aesthetic appeal with a distinctive profile.
     - Can create extra room for living space.

### 5. Gambrel Roof
   - Description: Similar to a mansard but typically used in barns, with two slopes on each side and a horizontal gable.
   - Advantages:
     - Provides maximum headroom in the attic.
     - Offers good drainage.
     - Classic appearance, particularly in rural settings.

### 6. Shed Roof
   - Description: A single, sloping roof surface, often used for modern or minimalist designs.
   - Advantages:
     - Simple design, easy to construct, and cost-effective.
     - Good for rainwater drainage.
     - Aesthetic versatility, allowing for creative use of space.

### 7. Butterfly Roof
   - Description: An inverted gable roof that forms a V shape, with two roof surfaces that slope inward.
   - Advantages:
     - Allows for rainwater collection in the middle.
     - Creates a modern aesthetic.
     - Maximizes natural light with large windows.

### 8. Skillion Roof
   - Description: A single-pitched roof that is typically tilted at a steep angle.
   - Advantages:
     - Excellent for drainage and snow runoff.
     - Provides a contemporary and unique look.
     - Allows for large windows and natural daylight.

### 9. Dome Roof
   - Description: A rounded roof structure that can be hemispherical or pointed.
   - Advantages:
     - Strong and durable, providing excellent wind resistance.
     - Allows for natural ventilation.
     - Unique architectural style.

### 10. Tapered Roof
   - Description: A roof that has a slope but may switch slopes; commonly seen in commercial buildings.
   - Advantages:
     - Provides adequate drainage for flat areas.
     - Can be designed for specific aesthetic or functional needs.
     - Often used with lightweight materials for ease of installation.

### 11. Green Roof
   - Description: A roof that is partially or completely covered with vegetation and a growing medium.
   - Advantages:
     - Enhances insulation and reduces heating/cooling costs.
     - Improves air quality and biodiversity.
     - Reduces stormwater runoff.

### 12. Thatched Roof
   - Description: A traditional style made from dry vegetation, such as straw, reeds, or palm branches.
   - Advantages:
     - Excellent insulator, keeping interiors cool in summer and warm in winter.
     - Environmentally friendly and sustainable.
     - Unique, aesthetically pleasing appearance.

Each type of roof has its own unique characteristics, advantages, and considerations for design, materials, and construction processes. The choice of roof type often depends on factors such as climate, architectural style, cost, and functional requirements.

@etconp
👍12❤8🎉1
🚧 𝗦𝘁𝗿𝘂𝗴𝗴𝗹𝗶𝗻𝗴 𝘄𝗶𝘁𝗵 𝗰𝗼𝘀𝘁 𝗼𝘃𝗲𝗿𝗿𝘂𝗻𝘀 𝗼𝗿 𝗺𝗶𝘀𝘀𝗲𝗱 𝗱𝗲𝗮𝗱𝗹𝗶𝗻𝗲𝘀? It might be time to sharpen your understanding of the key project management terms that top professionals use to keep their projects on track. Whether you're managing a small-scale build or a large, multi-phase project, mastering the right terminology can drastically improve your ability to control costs, forecast outcomes, and streamline decision-making. These five essential terms will help you better manage resources, mitigate risks, and ensure your projects deliver value—without breaking the bank. Ready to level up your project management skills? Keep reading to find out how these terms can transform the way you manage projects!

𝗛𝗲𝗿𝗲 𝗮𝗿𝗲 𝘁𝗵𝗲 𝟱 𝗸𝗲𝘆 𝘁𝗲𝗿𝗺𝘀 𝘆𝗼𝘂 𝗻𝗲𝗲𝗱 𝘁𝗼 𝗸𝗻𝗼𝘄:

✅𝗖𝗼𝘀𝘁 𝗘𝘀𝘁𝗶𝗺𝗮𝘁𝗶𝗼𝗻 – Predict the financial resources required for your projects. Tip: Always involve key stakeholders during the estimation process to ensure accurate and realistic projections.

✅𝗕𝘂𝗱𝗴𝗲𝘁 𝗕𝗮𝘀𝗲𝗹𝗶𝗻𝗲 – Set the approved version of your project's budget and measure progress.
Tip: Once the baseline is set, continuously monitor it against actual performance to catch variances early.

✅𝗘𝗮𝗿𝗻𝗲𝗱 𝗩𝗮𝗹𝘂𝗲 𝗠𝗮𝗻𝗮𝗴𝗲𝗺𝗲𝗻𝘁 (𝗘𝗩𝗠) – Track your project performance and costs efficiently.
Tip: Use EVM regularly throughout your project, not just during major milestones, to detect any deviations and course-correct quickly.

✅𝗖𝗼𝘀𝘁 𝗩𝗮𝗿𝗶𝗮𝗻𝗰𝗲 – Understand the difference between planned and actual spending.
Tip: Track cost variance at key intervals and adjust your budget or scope immediately if the variance exceeds a threshold.

✅𝗖𝗼𝘀𝘁 𝗕𝗲𝗻𝗲𝗳𝗶𝘁 𝗔𝗻𝗮𝗹𝘆𝘀𝗶𝘀 – Weigh the costs and benefits of different project options to make informed decisions.
Tip: Don’t just consider financial returns—evaluate intangible benefits such as improved team morale or long-term sustainability.


𝗪𝗵𝘆 𝗧𝗵𝗲𝘀𝗲 𝗧𝗲𝗿𝗺𝘀 𝗠𝗮𝘁𝘁𝗲𝗿 𝘁𝗼 𝗬𝗼𝘂:

Mastering these five key project management concepts can be the difference between a successful, on-time, and on-budget project, and one that spirals out of control. By integrating them into your daily practice, you’ll not only improve financial management but also boost team efficiency and project outcomes. Whether you’re managing construction projects or complex multi-disciplinary teams, these terms will empower you to make data-driven decisions and minimize risk.
@etconp
👍21
👉BIM -Digital transformation

🚧Building Information Modeling (BIM) is a process that involves the generation and management of digital representations of physical and functional characteristics of places.

BIM is used in construction and infrastructure projects and facilitates collaboration among architects, engineers, and other stakeholders by providing a shared digital environment.

BIM Level of Development (LOD) 300

LOD refers to the level of detail or development in the BIM model. LOD 300 indicates that a BIM model’s elements are sufficiently defined for coordination and design purposes. Specifically:

• At LOD 300, model elements are represented as accurate in terms of size, shape, location, and quantity.
• Elements can be used to generate traditional construction documents, and coordination between disciplines is possible.
• The model is often suitable for extracting dimensions, schedules, and other data needed for fabrication or installation.

3D, 4D, and Beyond in BIM

BIM is often described in terms of various “dimensions” that represent different types of information incorporated into the model:

1. 3D BIM: The basic 3D geometrical representation of a building or infrastructure project. This includes physical elements like walls, floors, windows, etc.
2. 4D BIM: Adds time-related information to the 3D model, enabling project scheduling and construction sequencing. This helps visualize the construction process over time.
3. 5D BIM: Incorporates cost-related information into the model, allowing for cost estimation and tracking in conjunction with the time and materials data.
4. 6D BIM: Involves lifecycle management data, including sustainability and energy performance analysis.
5. 7D BIM: Focuses on facilities management, enabling efficient operation and maintenance of the building after construction.

Each dimension adds more depth and detail to the BIM model, enhancing project management and decision-making.

Via Eagleng

@etconp
👍13👏2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉በፋይበር የተጠናከረ ኮንክሪት/Fiber Reinforced Concrete (FRC)
 
🏷ጥቃቅን፣የተለያዩ ፋይበርዎችን ወደ ኮንክሪት ድብልቅ ውስጥ በማካተት ጥንካሬውን ማጎልበት የሚቻልበት ዘዴ ነው።

⏺እንደ ብረት፣ መስታወት ወይም ፖሊመሮች ካሉ ቁሶች የተሰሩ እነዚህ ፋይበርዎች በሲሚንቶው ውስጥ በሙሉ ተበታትነው ጥንካሬን ይሰጣሉ።

▶️በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች በFRC ፍላጎት ላይ 5.7% ጭማሪ እንደሚኖር ይተነብያሉ።

⏺የዚህ ዘዴ ቁልፍ ሚናው የተለመደውን ኮንክሪት በማጠናከር፣ ስንጥቅ/crack የመቋቋም ችሎታውን እና የቆይታ ዘመኑን/lifespan በመጨመር ላይ ነው።

⏺FRC በሽሪንኬጅ ፣ በሙቀት መለዋወጥ/T⁰ fluctuation ወይም በውጫዊ ግፊቶች የሚነሱ ስንጥቆችን/Cracks በሚገባ ይቀንሳል።

🚧Fiber Reinforced Concrete (FRC):- incorporates small, discrete fibers into the mix, enhancing its strength and durability.

▶️These fibers, crafted from materials like steel, glass, or polymers, disperse throughout the concrete, bolstering its performance.

⏺Recent research forecasts a 5.7% surge in FRC demand.

⏺Its key role lies in fortifying conventional concrete, augmenting its crack resistance and lifespan.

📜FRC effectively mitigates cracks arising from shrinkage, temperature fluctuations, or external pressures.

@etconp
❤3👍1
👉ሰላም በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ አዲስ ተመራቂዎች አስደሳች ሊያገኟቸው የሚችሉ አንዳንድ የስራ ፈጠራ ፅንሰ-ሀሳቦች እንሆ

⭐️1. ዘላቂ የግንባታ መፍትሄዎች

ይህ ጽንሰ-ሐሳብ የግንባታ ፕሮጀክቶችን የአካባቢ ተፅእኖ የሚቀንሱ የስነ-ምህዳር ቁሳቁሶችን, ንድፎችን እና ቴክኒኮችን ማዘጋጀት እና መተግበርን ያካትታል.  አዲስ ተመራቂዎች በአረንጓዴ ግንባታ፣ ኃይል ቆጣቢ ስርዓቶች እና ዘላቂ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ እድሎችን ማሰስ ይችላሉ።

⭐️2. የግንባታ ቴክኖሎጂ

የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ጅምሮች የግንባታ ሂደቶችን ለማሻሻል አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማዳበር ላይ ያተኩራሉ፣ ለምሳሌ፡-

* የግንባታ መረጃ ሞዴሊንግ (BIM)
* ምናባዊ እና የተሻሻለ እውነታ
* የነገሮች በይነመረብ (አይኦቲ) እና ዳሳሽ ቴክኖሎጂዎች
* የሞባይል መተግበሪያዎች ለግንባታ አስተዳደር እና ትብብር

⭐️3. ሞጁል እና ተገጣጣሚ ግንባታ

ይህ ጽንሰ-ሐሳብ በቀላሉ በቦታው ላይ ሊገጣጠሙ የሚችሉ ሞጁል ክፍሎችን ወይም ተገጣጣሚ ክፍሎችን መንደፍ እና መገንባትን ያካትታል።

አዲስ ተመራቂዎች በሞጁል ግንባታ፣ ተገጣጣሚ ቤቶች እና አዳዲስ የማምረቻ ቴክኒኮችን እድሎችን ማሰስ ይችላሉ።

⭐️4. የግንባታ ፕሮጀክት አስተዳደር አገልግሎቶች

ይህ ጽንሰ-ሀሳብ የሚከተሉትን ጨምሮአል ለግንባታ ኩባንያዎች ልዩ የፕሮጀክት አስተዳደር አገልግሎቶችን መስጠትን ያካትታል፡-

* የፕሮጀክት እቅድ ማውጣት እና ማቀድ
* ወጪ ግምት እና ቁጥጥር
* የጥራት ማረጋገጫ እና ቁጥጥር
* የአደጋ አስተዳደር እና ቅነሳ

⭐️5. የሕንፃ መረጃ ሞዴል (BIM) አገልግሎቶች

BIM አገልግሎቶች ዲዛይን፣ ግንባታ እና አሠራር ለማሻሻል የሕንፃዎችን እና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ዝርዝር ዲጂታል ሞዴሎችን መፍጠርን ያካትታል።

አዲስ ተመራቂዎች በBIM ማማከር፣ ሞዴሊንግ እና ትንተና እድሎችን ማሰስ ይችላሉ።

⭐️6. የግንባታ ቆሻሻ አያያዝ እና እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል

ይህ ጽንሰ-ሐሳብ የግንባታ ቆሻሻን ለመቀነስ፣ እንደገና ጥቅም ላይ ለማዋል እና አዳዲስ መፍትሄዎችን ማዘጋጀት ያካትታል።

አዲስ ተመራቂዎች በቆሻሻ አያያዝ፣ በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውሉ ቴክኖሎጂዎች እና ዘላቂ ቁሶች ላይ እድሎችን ማሰስ ይችላሉ።

⭐️7. ዘመናዊ የግንባታ እና የመሠረተ ልማት መፍትሄዎች

ይህ ጽንሰ-ሐሳብ ቴክኖሎጂን, የኃይል ቆጣቢነትን እና ዘላቂነትን የሚያዋህዱ ብልህ የግንባታ ስርዓቶችን እና መሠረተ ልማትን ያካትታል።

አዲስ ተመራቂዎች በዘመናዊ የግንባታ ዲዛይን፣ በ IT ውህደት እና በመረጃ ትንተና ላይ እድሎችን ማሰስ ይችላሉ።

⭐️8. የግንባታ ትምህርት እና ስልጠና

ይህ ጽንሰ-ሀሳብ ለግንባታ ባለሙያዎች ስልጠና እና የክህሎት እድገቶችን ለማቅረብ በ ኦንላይን ላይ ወይም ከ በ አካል የትምህርት መድረኮችን መፍጠርን ያካትታል።

አዲስ ተመራቂዎች በኢ-ትምህርት፣ በስልጠና ፕሮግራሞች እና በዎርክሾፖች እድሎችን ማሰስ ይችላሉ።

⭐️9. የግንባታ እቃዎች ኪራይ እና መጋራት

ይህ ጽንሰ-ሐሳብ የግንባታ መሳሪያዎችን ለመከራየት ወይም ለመጋራት፣ ወጪዎችን ለመቀነስ እና ለግንባታ ኩባንያዎች ቅልጥፍናን ለመጨመር መድረኮችን ማዘጋጀት ያካትታል።

አዲስ ተመራቂዎች በመሳሪያ ኪራይ፣ በጋራ ኢኮኖሚ እና በሎጂስቲክስ አስተዳደር እድሎችን ማሰስ ይችላሉ።

⭐️10. የአደጋ መቋቋም እና የማገገሚያ አገልግሎቶች

ይህ ጽንሰ-ሀሳብ ማህበረሰቦችን ከተፈጥሮ አደጋዎች እንዲያገግሙ ለመርዳት አዳዲስ መፍትሄዎችን ማዘጋጀትን ያካትታል፡-

* የአደጋ ጊዜ ምላሽ እቅድ ማውጣት
* የጉዳት ግምገማ እና ጥገና
* የመልሶ ግንባታ እና የመልሶ ግንባታ አገልግሎቶች

💫እነዚህ የኢንተርፕረነርሺፕ ፅንሰ-ሀሳቦች አዲስ ተመራቂዎች በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ላይ ፈጠራ እንዲፈጥሩ እና አወንታዊ ተፅእኖ እንዲኖራቸው የተለያዩ እድሎችን ይሰጣሉ።

Via FILA

@etconp
👍17🙏3
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

🔰ምን ይፈልጋሉ?

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ 1. መርካቶ
                   ቁ.1 አየር ጤና
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍2❤1🥰1💯1
👉The Great Wall of China is not a single continuous wall, but rather a series of walls, fortifications, and natural barriers that stretch over 13,000 miles. Built over several dynasties to protect China from invasions, the wall crosses various landscapes, including mountains, deserts, and plains.

⭐️It stands as one of the most impressive architectural feats in history and a symbol of China's strength and perseverance.

@etconp
❤5👍1
👉የግንባታ ቦታ ነጥቦችን መለየት (Site Setting Out) ልየታ ላይ ተቆጣጣሪ መሐንዲሱ ማረጋገጥ ያለበት ነጥቦች

🚧በግንባታ ሥራ ከቦታ መጥረግ ቀጥሎ የሚሰራው ሥራ የግንባታ መስመሮችን (Axis) እና የስትራክቸር መሰረታዊ ማዕከላዊ ነጥቦችን (Center of structures/column) መለየት ነው።

🏷ይህ ሥራ የግንባታ ቦታ ነጥቦችን መለየት የሚባል ሲሆን መሐንዲሱ ማረጋገጥ ያለበት ነጥቦች፦

1) የተዘጋጀ ቦታ መሆኑን ፦ የግንባታ ቦታ ነጥቦችን መለየት (Site Setting Out) ከመከናወኑ በፊት ሲባጎ የሚወጠሩባቸው ችካሎች ወይም የጂፒኤስ (GPS) መሳሪያ የሚያመለክትባቸው ነጥቦች ከፍታ (Elevation of setting out strings) በውል እንዲታወቅ እና ተፈጥሯዊ የላይኛው የመሬት ክፍል ያለበት ክፍታ (Top Surface /Elevation/ of Original Ground Level) የተለየ መሆን ስላለበት የግንባታ ቦታ ጠረጋ በሚገባ የተከናወነ መሆኑን እና ተፈጥሯዊ የመሬት የላይኛው ክፍል የተደረሰበት መሆኑ ማረጋገጥ አለበት።

2) መሪ ንድፍ  (site plan) መኖሩን እና በዚያ መሰረት እየተከናወነ መሆኑን፦ መሐንዲሱ አንድ ሕንጻ የሚያርፍባቸውን መሰረታዊ ነጥቦት (Axis & Center) ልየታ በሚከናወንበት ሰዓት ሕጋዊ የሆነ መሪ የቦታ ንድፍ (site plan) ያለው እና በግንባታ ቦታው ላይ የሚገኝ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።

3) ዋና ዋና ፍርግርግ መስመሮች (main grid/Axis/ lines)፦ የግንባታው ሁለትዮች አቅጣጫዎች (X-axis and Y-axis) የሚገናኙበትን የሚያመለክቱ ፍርግርግ መስመሮች መኖራቸውን፣ ከፍታ ልዩነት አለመኖሩን (water level) ማረገግጥ አለበት። በዚህም መሰረት እርስ በእርሳቸው የሚገናኙበት አንግል እና አንዱ ከሌላው ያለው ማዕከላዊ ርቀት (centerline dimensions) በስትራክቸራል የመሰረት አቀማመጥ ዲዛይኑ (Structural foundation layout) ላይ በተመለከተው ልኬት መሰረት ምንም አይነት የልኬት ክፍተት የሌለባቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ አለበት።

4) የስትራክቸር ክፍሎች መገኛ (Location of Structural Elements):- በዋናነት እያንዳንዱ የስትራክቸሩ ምሰሶዎች/ቋሚ አምዶች ማዕከላዊ ነጥብ(Columns centerline)፣ እና የስትራክቸሩ ምሰሶዎች የሚያርፉባቸውን አካላይ ነጥቦት (Coordinate points)፣ የምሰሶ ጫማ ስፋት (Footings coverage area) የሚያመለክት መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።

5) የአጥር ሥራ (fencing or barbed)፦ በሚቆፈረው የመሬት ክፍል ውስጥ ማየት የተሳናቸው፣ ሕጻናት፣ በጨለማ የሚጓዙ መንገደኞች፣ እንስሳት እንዳይወድቁና አካላዊ ጉዳት እንዳይደርስ፤ በተጨማሪም በግንባታው ክልል ውስጥ የሚገኙ እንደ ሚስማር፣ ብረት፣ እንጨት አይነት ግብአቶች እንቅፋት በመሆን ጉዳት እንዳያስከትሉ፣ ወይም በግንባታ ቦታው ውስጥ ያሉ የግንባታ ግብአቶች፣ ማሽኖች፣ እቃዎች፣ እና ሌሎች ንብረቶች እንዳይዘረፉ ለመከላከል የግንባታ ቦታው የታጠረ ወይም የተከለለ መሆኑ ማረጋገጥም የክትትል መሐንዲሱ ሥራ ነው።

❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

📜ለ ስራ እና ጨረታዎች ምንለቅበት ቻናል ለመቀላቀል👉 @ETCONpWORK

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp
👍22🙏5
👉ከቅንጡ የግንባታ መመሪያዎች በፊት መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ባለሙያዎች ተናገሩ

🚧የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በቅርቡ ባስተላለፈው የመንገዶች እና የግንባታ መመሪያ መሰረት፤ 15 ሜትር ስፋት ያላቸው መንገዶች በሚያዋስኗቸው ይዞታዎች ዝቅተኛው የቦታ ስፋት ቢያንስ 500 ሜትር ካሬ መሆን እንደሚገባው ደንግጓል።

⏺ውሳኔውን ተከትሎ አሐዱ ያነጋገራቸው ባለሙያዎች "መሰረታዊ ጥያቄዎች አስቀድሞ ምላሽ ሊያገኙ ይገባል" ይላሉ።

የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶ/ር አጥላው ዓለሙ፤ አሁን ባለንበት ሁኔታ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ገልጸዋል።

የሥራ እድል የፈጠሩ ቦታዎችን ማፍረስ፣ በባንክ ብድር እና በዜጎች አቅም የሚገነቡ ግንባታዎችን ማቋረጥ ጉዳቱ የጥቂት ግለሰቦች ብቻ አይሆንም ሲሉም ተናግረዋል።

አክለውም "አሁን እኛ ማድረግ ያለብን ሰዎች ሥራ ፈጥረው እራሳቸውን እንዲለውጡ፣ ባለው አቅም ተጠቅመው ሌላ ተጨማሪ አቅም እንዲፈጥሩ ማድረግ እንጂ እንዲህ አይነት ቅንጡ ነገሮች ማድረግ አለብን ብዬ አላምንም" ብለዋል፡፡

ይህ ህግ የወጣበት ምክንያት በግልጸ አልተነገረም የሚሉት ዶ/ር አጥላው፤ "ቢገለጽም ከጀርባው ያለው ምክንያት እና ፊት ለፊት ያለው ምክንያት ላይጣጣም ይችላል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

"ትናንሽ ሥራዎች ቢፈጠሩ ለብዙ ሰዎች መኖሪያ ናቸው፡፡ እነዚህን ሥራዎች ስንከለክል በብዙ ሰዎች ላይ ፈርደን ነው፡፡ ይህ ለምን እንደማይታይ አይገባኝም" ሲሉም ተገልጸዋል፡፡

የመሬት ባለቤትነት ከመንግሥት እጅ እንዲወጣ ማድረግ ከመመሪያው መቅደም የሚገባው ጉዳይ እንደሆነ የሚያብራሩት ደግሞ የምጣኔ ሐብት ባለሙያው አቶ መቆያ ከበደ ናቸው።

ግለሰቦች የመሬት ባለቤት መሆን እስካልቻሉና መሬት በመንግሥት እጅ እንስካለ ድረስ፤ የሚፈለገውን ያህል ውጤት ይመጣል ተብሎ እንደማይጠበቅ ባለሙያው ለአሐዱ ተናግረዋል።

"የግንባታው መመሪያ እና የኮሪደር ልማቱ በርካታ ቦታዎችን እያፈረሰ ነው" ያሉት ባለሙያው፤ የንግድ እንቅስቃሴዎች የሚኖሩት መንገድ በሚገነቡ ሕንጻዎች መሆኑን አንስተዋል።

"ይህ ደግሞ መንግሥት የግብር ተጠቃሚ ያደርገዋል" ያሉ ሲሆን፤ እነዚህ የገቢ ምንጮች ላይ ያደረጉ ስራዎችን መከልከል እራሱ መንግሥትን የሚጎዳ ነው ብለዋል።

በዚህ መመሪያ መሠረት በርካታ ግንባታዎች እየተቋረጡ ሲሆን፤ ይሄም ከጊዜና ከገንዘብ አንፃር ለኪሳራ እንደሚዳርግ አሐዱ ያነጋገራቸው ባለሙያዎች ተናግረዋል።

❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

📜ለ ስራ እና ጨረታዎች ምንለቅበት ቻናል ለመቀላቀል👉 @ETCONpWORK

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp

@etconp
👍28❤1
👉ዛሬ የወጡ አዳዲስ የ ስራ ቅጥሮች ለመመልከት ሌላኛው ቻናላችን ይቀላቀሉ

🏷NEW VACANCY

የስራው መጠሪያ: Architect / Interior designer

የስራው አይነት: በተመደቡበት የሚሰራ - ቋሚ

የስራው ዘርፍ: #አርክቴክቸር_እና_የከተማ_ፕላን

የስራው ቦታ: አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ

የትምህርት ደረጃ: የመጀመሪያ ዲግሪ

የልምድ ደረጃ: መካከለኛ

የተፈላጊ ሰው ብዛት: 2

የአመልካቾች ጾታ: ወንድ

ደሞዝ/ክፍያ: ወርሃዊ

የማመልከቻ ማብቂያ ቀን: October 12th, 2024

የስራው ዝርዝር:

The Interior Designer will be responsible for conceptualizing, designing, and overseeing the implementation of projects. This role requires a combination of creativity, technical skills, and a strong understanding of design principles.

Responsibilities

●  Develop design concepts based on client preferences, project requirements, and industry trends

● Prepare working and Presentation drawings, and material specifications

● Design or Select furniture, fixtures, and finishes that align with the overall design aesthetic

● Coordinate with contractors, suppliers, and other professionals involved in the project

● Oversee the implementation of the design, ensuring that it meets budget and timeline constraints

● Stay up-to-date with the latest interior design trends and technologies

Qualifications

● Bachelor's degree in Architecture
● 2+ years of experience in interior and furniture design
● Strong portfolio of design projects
● Proficiency in design software (e.g., AutoCAD, Revit, SketchUp)
● Excellent communication and interpersonal skills
● Ability to work independently and as part of a team
● Strong attention to detail

Note: Applicants must attach your Resume and Portfolio on subi.finishing@gmail.com

_
_

Subi Finishing

@ETCONpWORK
👍8❤3🙏2