👉ደቡብ ሱዳንና ኡጋንዳ በነጭ አባይ ላይ በ98 ሚሊየን ዶላር ግድብ ሊገነቡ መሆኑ ተሰምቷል።
🏷ጥቁር አባይና ነጭ አባይ ሱዳን ላይ ሲገኙ ጥቁር አባይ 100% መገኛው ኢትዮጵያ ነች::
@etconp

👍12😁10👏2
👉አስደሳች ዜና
🏷በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ተግባራዊ ምርምር እና ፈጠራን ለማበረታታት ይፈልጋል።
⭐️ለዚህም የ ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን (ECWC) ከሰራተኞች አዳዲስ የምርምር ሀሳቦችን በማስተዋወቅ ቀጣይነት ያለው ሙያዊ እድገት እና እውቀትን የማጎልበት ፖሊሲውን በማስቀጠል ግልፅ ውድድር እንደሚካሄድ አስታውቋል።
📜የዚህ ማስታወቂያ አላማ የ ECWC ሰራተኞችን የጋራ እውቀትን ማበረታታት ነው ወደተወሰኑ የምርምር ጭብጦች የሚያጠኑ የምርምር ሀሳቦችን እንድታቀርቡ ይጋብዛል።
💫ይህ ጥሪ የኮርፖሬሽኖቻችንን አሠራር ለማሻሻል አዲስ አስተሳሰብን የሚያነሳሳ እና ተግባራዊ መፍትሄዎችን ያበረታታል።
ሽልማቶች፡-
❇️1ኛ አሸናፊ፡ 200,000 ብር
❇️2ኛ አሸናፊ፡ 150,000 ብር
❇️3ኛ አሸናፊ፡ 100,000 ብር
📜የምርምር ገጽታዎች፡-
⏺የግንባታ ቁሳቁስ
⏺የግንባታ ቴክኖሎጂ
⏺የግንባታ ዘዴ
⏺የግንባታ አስተዳደር
🚧ውሎች እና ሁኔታዎች፡-
⏺ብቁነት፡ ይህ ጥሪ ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ሰራተኞች ክፍት ነው።
⏺የዳኝነት መስፈርት፡ ወረቀቶች የሚገመገሙት በዋናነት፣ ከጭብጡ አግባብነት፣ የጥናት ጥልቀት፣ የአቀራረብ ግልፅነት እና ተግባራዊ እንድምታዎች በባለሙያዎች ቡድን ነው።
⏺የማስረከቢያ መስፈርቶች፡ ወረቀቶች ኦሪጅናል ያልታተሙ መሆን አለባቸው፣ እና ከተጠቀሱት የምርምር ጭብጦች አንዱን የሚያብራራ ለማንኛውም ጆርናል ወይም አሳታሚ መሆን የለበትም፡ የግንባታ ቁሳቁስ፣ የግንባታ ቴክኖሎጂ፣ የግንባታ ዘዴ ወይም የግንባታ አስተዳደር።
⏺መብቶች እና ፈቃዶች፡- ወረቀት በማቅረብ ተሳታፊዎች ገንዘቡን ይሰጣሉ፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ደግሞ ይዘቱን አሳትሞ ለፓተንት ወይም ለስራ ማስኬጃነት የመጠቀም መብት አለው።
⭐️መስፈርቱን የሚያሟላው ፕሮፖዛል/ወረቀት/ጥናት ሙሉ ወረቀቱን ለማቅረብ ይነገራል።
⏺ብቁ አለመሆን፡ የማስረከቢያ መመሪያዎችን የማያሟሉ፣ ከቀነ-ገደቡ በኋላ የሚቀርቡ፣ ወይም የሀሰት ወሬዎችን የሚያሳዩ ወይም የትኛውንም አይነት ታማኝነት የጎደላቸው ወረቀቶች ውድቅ ይሆናሉ።
🏷የማስረከቢያ ቀን
• የማስረከቢያ የመጨረሻ ቀን፡ ኖቬምበር 5፣ 2024
• ፕሮፖዛሉን ሲያዘጋጁ፣ ከዚህ በታች የተያያዘውን ቅጽ ይጠቀሙ።
📩በኢሜል ያስገቡ፡- projm2021@gmail.com ወይም rkmt2017@gmail.com ይላኩ
• አስቻለው መርሻ፣ ስልክ ቁጥር +251 912 687699 ወይም
• አንሙት ሞላ፣ ስልክ ቁ. +251 964 063944

👍15🙏2
ታምራት ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ
👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ
🔰ምን ይፈልጋሉ?
📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን
✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል
🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ
📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን
☎️ይደዉሉልን ያማክሩን
📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን
አድራሻችን፦ 1. መርካቶ
ቁ.1 አየር ጤና
ቁ.3 ተክለሀይማኖት
0904040477
0911016833

👍4
👉40 በመቶ የአዲስአበባ ከተማ ክፍል ፈራሽ ነዉ ተባለ
🚧በፈረሳዉ የተነሳ 300 ሺህ ሰዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ይነካሉ
40 በመቶ የአዲስአበባ ክፍል ፈራሽ መሆኑን መሠረት ሚዲያ ምንጮች ነግረዉኛል ሲል ዘግቧል። የዜና ምንጩ ፈረሳዉ በሁለተኛዉ ምዕራፍ የአዲስአበባ የኮሪደር ልማት መስመሮች የተነሳ ነዉ ብሏል።
የኮሪደር ልማቱን ለመከወን ከ 110 ቢሊዮን ብር በላይ ይጠይቃል መባሉንም ዳጉ ጆርናል ከዘገባዉ ሰምቷል። በዚህም የተነሳ 300 ሺህ ሰዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ይነካሉ ብሏል። በዚህም መሰረት በፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎችም ተጎጂዎችም ሊኖሩ ይችላሉ ተብሏል። በመጀመሪያዉ ዙር የኮሪደር ልማት ቀደምት የአዲስአበባ ሰፈሮች መፍረሳቸዉ ይታወቃል።
በአጠቃላይ በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት 2817 ሄክታር የቦታ ስፋት ሲኖረው 132 ኪሎሜትር ርዝመትን እንደሚሸፍን መዘገባችን አይዘነጋም።

👍14💔4
👉በ መቐለ ከተማ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ተጀመረ
🚧በ መቐለ ከተማ በ2 ነጥብ 1ቢሊዮን ብር በጀት የአስፋልት መንገድ ግንባታ መጀመሩን በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመቐለ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
💫የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ የመሰረተ ልማት አማካሪ አቶ ሀፍቱ መብራህቱ እንደገለፁት፤ በከተማዋ በ2017 በጀት ዓመት 9 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ለመገንባት የተያዘውን እቅድ ተግባራዊ ማድረግ ተጀምሯል።
Via EBC

👍13🥰1
👉አንድን ጨረታ የሚያሸንፈው ዝቅተኛ ዋጋ አቅራቢ ተጫራች ወይስ ከመሐንዲሱ ግምት ተቀራራቢ የሆነ ዋጋ ያስገባ ተጫራች?
💫ጨረታ ለተቋራጮች በሁለት አይነት መንገድ ሊፈጸም ይችላል።
⭐️አንደኛ ግልጽ ጨረታ ሲሆን ማንኛውም ብቁ የሆነ፣ ህጋዊ ፍቃድ ያለው እና ፍላጎት ያለው ተቋራጭ መሳተፍ የሚችልበት በጋዜጣ ወይም በአካባቢው ባሉ የማታወቂያ መንገዶች ወይም በማህበራዊ መገናኛ ድረገጾች (website) ላይ በሚለቀቅ የተጫራችነት ግብዣ ጥሪ (Invitation to Tender) አማካኝነት ተጫራቾች ኩል ዕድል ተሰጥቷቸው እንዲሳተፉ የሚጋበዙበት ሂደት ሲሆን
⭐️ሁለተኛው ውስን ጨረታ የሚባል ነው። ውስን ጨረታ አንድ ተጋባዥ ወይም ውስን ቁጥር ያላቸው ልዩ መስፈርት የተሰጣቸው ተጫራቾች ጋር በሚደረግ ድርድር ወይም የመለያ ጨረታ አማካኝነት የሚከናወን የጨረታ አይነት ነው።
📜በግልጽ ጨረታ ሂደት ደግሞ አጫራቹ አካል ሁለት አይነት መንገድን ሊጠቀም ይችላል።
🏷[አንደኛው] ፖስት ኳሊፊኬሽን (Post Qualification) የሚባል ሲሆን ሥራው ቀለል ያለ እና ማንኛውም ተጫራች ሊያከናውነው የሚችል ከሆነ ቅድሚያ ኢኮኖሚያው (የገንዘብ) መጠናቸውን መመዘን ነው።
⏺በዚህ ሂደት ቅድሚያ ቅንሽ ዋጋ ያስገቡ ተጫራቾች ተለይተው እነዚያ ደግሞ በቴክኒካዊ ልኬት ተመዝነው አሸናፊ የሚለይበት መንገድ ነው።
🏷[ሁለተኛው] ፕረ ኳሊፊኬሽን (Pre-Qualification) የሚባለው ደግሞ ማንኛውም ተጫራች ቅድሚያ በቴክኒካዊ ልኬት ተመዝነው በኋላ በገንዘብ ዝቅተኛ ያስገባው አሸናፊ የሚሆንበት የጨረታ ምዘና መንገድ ነው።
⏺በመሆኑ ይህ ሂደት በፌደራል የግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የወጣው መመሪያ ክፍል አምስት (5) ንዑስ ክፍል (1), (2) እና (3) ላይ በዝርዝር የተብራራ ነው።
🚧በመሆኑም በጨረታ ሰነዶች ምዘና (Bid Response Document Evaluation) ሂደት ላይ ተጫራቾት እንደጨረታ ሰነዱ አወጣጥ ተመስርቶ በቅድሚያ ዝቅተኛ ዋጋ ያስገቡትን በመምረጥ (Post Qualification ሂደትን በመከተል) በቴክኒካል ሰነዳቸው አXእናፊውን የሚለይበትን መንገድ ሊከተል ይችላል።
▶️አልያም ደግሞ Pre-Qualification ሂደትን በመከተል ቅድሚያ የቴክኒካል ሰነዳቸው ታይቶ ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ብቻ ተለይተው ዝቅተኛ ገንዘብ ባስገባ (Lowest bidder) የሚለዩበት መንገድ ነው።
▶️ይህ ሁለቱም መንገድ በግል ፕሮጀክቶችም ይሁን በመንግሥት ፕሮጀችቶች ላይ ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉና ህጋዊ እውቅና ያላቸው መንገዶች ናቸው።
▶️የጨረታውን አከፋፈት በተመለከተ በ ክፍል 2 (2.2.1.5) ላይ እንደተብራራው ቃለጉባኤ ተይዞ፣ የጨረታውን አከፋፈት ሂደት ላይ ውይይት ከተካሄደባቸው ጉዳዮች በተጨማሪ ጨረታው ሲከፍተ የተገኙ ተጫራቾች ወይምህጋዊ ወኪሎቻቸው ስለጨረታው አከፋፈት ሂደት የሚያብራራ ቃለጉባኤ ላይ ስማቸውን እና ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይገባቸዋል። etconp
❇️አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የመሐንዲስን ግምት ያማከለ የጨረታ ሰነዶች ምዘና የሚካሄድበት አጋጣሚ አለ።
⏺ይህም Federation Internationale Des Ingenieurs Conseil – FIDIC አንቀጽ 14 ላይ እንደተገለጸው ተጫራቾች መሐንዲሱ ገምቶ ያስቀመጠውን የግንባታ ዋጋ (Engineering Estimation of Construction Cost) እንደመነሻ በመቁጠር ተጫራቾች ከግምቱ በታች ከ20% በታችን የቀነሰ ዋጋ እንዳያስገቡ ወይም ከግምቱ በላይ ከ20% በላይ እንዳይጨምሩ ገደብ በማስቀመጥ ከዚህ እሳቤ ውጪ የሆኑትን የተጫራቾች ሰነዶች በመጣል በዚህ ክፍተተ (interval) ውስጥ ያሉትን ብቻ የማወዳደር ሥራ የሚሰሩበት መንገድ ነው። etconp
⏹ቢሆንም ግን ይህ አካሄድ ግምቱን ባወጣው መሐንዲስ (ግለሰብ) ጥንቃቄ እና እውቀት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ብዙ ክፍተቶች የሚፈጠሩበት ቢሆንም የፌደራል መንግስት የግዢ መመሪያ ቀድሞ በነበረው በዚህ አሰራር ላይ ግልጽ ማብራሪያ ሳያስቀምጥ አልፎታል።
❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!
📜ለ ስራ እና ጨረታዎች ምንለቅበት ቻናል ለመቀላቀል👉 @ETCONpWORK
📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT
💫ቲክቶክ:👇
www.tiktok.com/@etconp7

👍33❤4🔥2👏2
👉ይህ ከላይ በ ምስል ያያዝነው ህንፃ ካክተስ ታወር (Kaktus towers) ይባላል ኮፐንሀገን ዴንማርክ የሚገኝ ሲሆን በ BIG ብያርክ ኢንገልስ ግሩፕ የተነደፈ የጋራ መኖርያ ህንጻ ነው።
💫ጠቅላላ የያዘው የ አባ ወራ ብዛት 495 ሲሆን የ ህንፃው ቁመት 80 ሜትር ነው።
🚧በረጅም ህንጻዎች ምክርቤት እና በኧርባን ሀቢታት ስብሰባ ላይ ምርጡ የአውሮፓ ከፍተኛ ፎቅ ሽልማትን ተቀብሏል።
🏷በየወለሉ መሽከርከሩ እንዲሁም እያንዳንዱ ወለል የተለየ አጠቃላይ ቅርጽ ማግኘቱ ለህንጻው ውበት ልህቀት አስተዋጽኦ አድርገዋል።
🔰ንድፉን ስንመለከት የ እውቁ ዴንማርካዊ ነዳፊ የ ብያርክ ኢንገልስ ስራ መሆኑን መገመት አያዳግትም።

👍19❤1
👉የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅን ለቋሚ ኮሚቴ ተመራ
ግንባታ ከማከናወናቸው አስቀድመው ቤት የሚሸጡ ሪል ስቴት አልሚዎች፤ ከደንበኞቻቸው የሚሰበስቡትን ገንዘብ በዝግ የባንክ አካውንት እንዲያስቀምጡ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።
አዲሱ ረቂቅ አዋጅ፤ ቤት ለመገንባት የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ያላገኙ የሪል ስቴት አልሚዎች ደንበኞችን እንዳይመዘግቡ እና ቅድመ ክፍያ እንዳይሰበስቡም ይከለክላል።
“የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ” የተሰኘው ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ዛሬ ሐሙስ መስከረም 30/2017 ዓ.ም. በተደረገው የፓርላማው አራተኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመጀመሪያ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።
በአሁኑ ጊዜ ባለው አሠራር መሠረት የንግድ ፈቃድ በማውጣት ብቻ ወደ ሪል ስቴት ገበያው ሲቀላቀሉ የነበሩት አልሚዎች፤ በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ “የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ” የማውጣት ግዴታ ተጥሎባቸዋል።
የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ ባለሀብት ሪል ስቴት አልሚዎች ይህንን ፈቃድ ለማግኘት ቢያንስ 50 ቤቶችን ገንብተው የሚያስከረክቡ መሆን እንዳለባቸው ረቂቅ ላይ ሰፍሯል።
ረቂቁ፤ “የሪል ስቴት አልሚው በቤት ቅድሚያ ሽያጭ ስልት ለመሥራት መፈለጉን አግባብ ላለው አካል አሳውቆ ፈቃድ ማግኘት [አለበት]” ሲል አዲሱን ሕግ ግዴታ አስቀምጧል።
የቅድመ ሽያጭ ዘዴን መጠቀም የሚፈልጉት ሪል ስቴት አልሚዎች፤ ከቤት ገዢዎች የሚሰበስቡት ገንዘብ የሚቀመጥበት የባንክ ሂሳብ እና የገንዘብ አወጣጥ ላይም አስገዳጅ አሠራር በረቂቅ አዋጁ ተጥሎባቸዋል።
አልሚዎቹ ከቤት ገዢዎች የሚሰበስቡትን ገንዘብ “የዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ ማደረግ ወይም ማስያዝ” እንዳለባቸው ረቂቅ ሕጉ ላይ ሰፍሯል።
ከዚህም ባሻገር በቅድሚያ የተሸጠው ቤት ተገንብቶ ለተጠቃሚዎች እስከሚተላለፍ ድረስ የቤት የመሥሪያ ቦታው የይዞታ ማስረጃ “በሚመለከተው አካል እንዳይሸጥ፣ እንዳይለወጥ” እንደሚታገድ ረቂቁ ይገልጻል።
ቤት ቀድመው በሚሸጡ ሪል ስቴት አልሚዎች ላይ እነዚህ አስገዳጅ አሠራሮች የተቀመጡት “ደንበኞች የሚደርስባቸውን እንግልት እና ኪሳራ ለመቀነስ በማሰብ” እንደሆነ የአዋጁ ማብራሪያ ያስረዳል።
በረቂቁ መሠረት፤ የሪል ስቴት አልሚዎች ግንባታው 80 በመቶ ላይ ያልደረሰን ቤት ለደንበኞች እንዳያስተላልፉ ተከልክለዋል።
ረቂቁ፤ “ያለደንበኛው ፍላጎት እና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ አይችልም” ይህንን ለማድረግ በቅድሚያ ደንበኛው መስማማት እንዳለበት ያመለክታል።
ሪል ስቴት አልሚዎች ቤት ገዢዎችን መመመዝገብ እና ቅድመ ክፍያ መሰብሰብ የሚችሉበት ጊዜም ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦበታል።
Via BBC Amharic

👍20❤1
👉የግንባታ ተቆጣጣሪ መሒንዲሶች (𝐒𝐮𝐩𝐞𝐫𝐯𝐢𝐬𝐨𝐫) ዋና ዋና ሥራዎች
🏷የግንባታ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ (𝔖𝔲𝔭𝔢𝔯𝔳𝔦𝔰𝔬𝔯) የአንድ ፕሮጀክት ግንባታ ሂደት በአስተማማኝ፣ በብቃት እና ሀገሪቷ በምትጠቀምባቸው የግንባታ መሪ ሰነዶች (𝔰𝔱𝔞𝔫𝔡𝔞𝔯𝔡𝔰) መሰረት መከናወኑን የመቆጣጠርና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው።
ተቆጣጣሪዎች ለግንባታ ባለቤት እና ተቁቅራጭ ዋና ዋና የግንባታ ውስንነቶችን ወይም 𝔠𝔬𝔫𝔰𝔱𝔯𝔞𝔦𝔫𝔱𝔰 ተብለው የሚታወቁትን (ወጪ ገንዘብ፣ ጥራት እና ጊዜ) በአግባቡ ለመጠቀም እና ከማንኛውም ግጭት ወይም ቅሬታ ነጻ ለማድረግ የሚሰየሙ አካላት ናቸው።
⭐️ጠቅላል ሲል የሚከተሉት የሥራ ድርሻዎች አሉባቸው።
[1] የጥራት ቁጥጥር - 𝑸𝒖𝒂𝒍𝒊𝒕𝒚 𝒄𝒐𝒏𝒕𝒓𝒐𝒍፦ የግንባታ ስራዎች የተቀመጡትን ደረጃዎች (𝚜𝚝𝚊𝚗𝚍𝚊𝚛𝚍𝚜) እንዲያሟሉ እና የፕሮጀክቱን የጥራት መስፈርቶች እንዲያከብሩ የስራውን ጥራት መከታተል
[2] የጊዜ አስተዳደር - 𝑻𝒊𝒎𝒆 𝒎𝒂𝒏𝒂𝒈𝒆𝒎𝒆𝒏𝒕፦ ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ (መርሐግብር) መሰረት እንዲጠናቀቅ የግንባታ ሂደቱን በየጊዜው መመዘንና መከታተል፣ መዘግየቶችን መለየት እና በፕሮጀክቱ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፉ የሚችሉ ችግሮችን ለማስወገድ የእርምት እርምጃዎችን መውሰድ
[3] የሀብት አስተዳደር - 𝑹𝒆𝒔𝒐𝒖𝒓𝒄𝒆 𝑴𝒂𝒏𝒂𝒈𝒆𝒎𝒆𝒏𝒕፡ ለተገቢ ተግባራት ተገቢውን ግብአት መመደብ፣ ትክክለኛ ሰውን ለትክክለኛው ስራ በትክክለኛው ጊዜ መመደብ፣ የቁሳቁስ እና የመሳሪያ ሃብቶችን በብቃት ማስተዳደር፣ ለተያያዥ ችግሮች አስቸኳይ መፍትሔ መስጠት
[4] ደህንነትን እና ጤናን ማረጋገጥ - 𝑰𝒏𝒔𝒖𝒓𝒊𝒏𝒈 𝒔𝒂𝒇𝒆𝒕𝒚 𝒂𝒏𝒅 𝒉𝒆𝒂𝒍𝒕𝒉፦ በግንባታው ቦታ ላይ የደህንነት እርምጃዎችን በመተግበር የደህንነት ፕሮቶኮሎችን በመከተል የመከላከያ መሳሪያዎችን በመጠቀም እና አደጋዎችን እና ጉዳቶችን ለመከላከል እርምጃዎች እንዲተገበሩ ማድረግ
[5] የክፍያ ልኬቶችን ማስተዳደር - 𝑪𝒉𝒆𝒄𝒌𝒊𝒏𝒈 & 𝑨𝒑𝒑𝒓𝒐𝒗𝒊𝒏𝒈 𝑾𝒐𝒓𝒌𝒔 𝒆𝒙𝒆𝒄𝒖𝒕𝒆𝒅፦ ተቆጣጣሪዎች በኮንትራክተሩ ለክፍያ ጥያቄ የተዘጋጁትን መጠኖች የማረጋገጥ እና ትክክለኛ መጠን ከሆኑ ማሳለፍ ወይም አስተያየት በመስጠት ማስተካከያ እንዲደረግባቸው ማስደረግ
[6] ተከታታይ ሥራዎች በጊዜው እንዲከናወኑ ማዘዝ/መፍቀድ - 𝑶𝒓𝒅𝒆𝒓𝒊𝒏𝒈 𝒇𝒐𝒓 𝒑𝒓𝒐𝒄𝒆𝒆𝒅𝒊𝒏𝒈 𝒕𝒂𝒔𝒌፦ በተቋራጩ አስቀድሞ የተፈጸሙ ሥራዎችን በአግባቡ የተከናወኑ መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ተከታይ (ቀጣይ) ተግባራት እንዲቀጥል ትዕዛዝ መስጠት።
[7] ባለድርሻ አካላትና መገናኘት እና የሥራ ቅንጅትን መፍጠር - 𝑪𝒐𝒎𝒎𝒖𝒏𝒊𝒄𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏 𝒂𝒏𝒅 𝒄𝒐𝒐𝒓𝒅𝒊𝒏𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏፡- ለፕሮጀክቱ ስኬታማ አፈፃፀም ያግዙ ዘንድ በተለያዩ የፕሮጀክት ባለድርሻ አካላት መካከል ለሚደረግ ንግግር ግልጽ እና ውጤታማ ግንኙነት ለመፍጠር እንደ መገናኛ/ድልድይ ማገልገል
[8] የተፈጸሙ ስራዎችን ማረጋገጥ - 𝑪𝒐𝒏𝒇𝒊𝒓𝒎𝒊𝒏𝒈 𝒆𝒙𝒆𝒄𝒖𝒕𝒆𝒅 𝒘𝒐𝒓𝒌𝒔፡- የተከናወኑ የሥራ ክፍሎችን ለእያንዳንዱ ሥራ ማረጋገጫ በሆኑ ተያያዥ የፍተሻ ዝርዝሮች (𝚝𝚊𝚜𝚔-𝚛𝚎𝚜𝚙𝚎𝚌𝚝𝚒𝚟𝚎 𝚌𝚑𝚎𝚌𝚔𝚕𝚒𝚜𝚝𝚜) መገምገም እና የተግባር ማረጋገጫ መስጠት /𝚌𝚘𝚗𝚏𝚒𝚛𝚖𝚊𝚝𝚒𝚘𝚗/ ወይም ውድቅ ማድረግ /𝚛𝚎𝚓𝚎𝚌𝚝𝚒𝚘𝚗/ ወይም የጥገና ማዘዣ መስጠት /𝚖𝚊𝚒𝚗𝚝𝚎𝚗𝚊𝚗𝚌𝚎 𝚘𝚛𝚍𝚎𝚛/ ወይም እንዲፈርሱና እና እንደገና እንዲሰሩ ማዘዝ /𝚍𝚎𝚖𝚘𝚕𝚒𝚜𝚑𝚒𝚗𝚐 𝚊𝚗𝚍 𝚛𝚎𝚠𝚘𝚛𝚔 𝚘𝚛𝚍𝚎𝚛/ ወይም አሳማኝ ማሻሻያ እንዲደረግላቸው ማድረግ /𝚖𝚘𝚍𝚒𝚏𝚒𝚌𝚊𝚝𝚒𝚘𝚗/ የመሳሰሉትን ውሳኔዎችን /𝚍𝚎𝚌𝚒𝚜𝚒𝚘𝚗𝚜/ ለኮንትራክተሩ መስጠት
[9] ችግር መፍታት - 𝑷𝒓𝒐𝒃𝒍𝒆𝒎 𝑺𝒐𝒍𝒗𝒊𝒏𝒈፦ ችግሮችን አስቀድሞ በመለየት ተግባራዊ መፍትሄዎችን በማፈላለግ ያልተጠበቁ ተግዳሮቶችን መከላከል
[10] መረጃን ሰንዶ ማስቀመጥ - 𝑫𝒐𝒄𝒖𝒎𝒆𝒏𝒕𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏፦ የእለት ሪፖርቶችን፣ የሂደት ማሻሻያዎችን፣ እና የፕሮጀክት ምእራፎችን ለመከታተል፣ አለመግባባቶችን ለመፍታት እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በመጀመሪያዎቹ እቅዶች ላይ የተደረጉ ማናቸውንም ለውጦችን ጨምሮ የግንባታ ስራዎችን ትክክለኛ ክስተት ወይም አጋጣሚዎች ወይም ሂደቶች በአግባቡ መዝግቦ መያዝ
[11] የአካባቢን ሁኔታ ታሳቢ ማድረግ - 𝑬𝒏𝒗𝒊𝒓𝒐𝒏𝒎𝒆𝒏𝒕𝒂𝒍 𝑪𝒐𝒏𝒔𝒊𝒅𝒆𝒓𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏𝒔፦ በግንባታ ተግባራት ላይ የሚኖረውን የአካባቢ ተፅእኖ ለመቀነስ እርምጃዎችን መተግበር፣ የአካባቢ ደንቦችን እና ምርጥ ልምዶችን ማክበር እና ማስከበር
🔰እነዚህ እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በዝርዝር እና በጥልቀት ይዘው ማስተዳደር ይጠበቅባቸዋል።

👍29🔥2❤1
Intercon Construction Chemicals
👉 Authorized agent of MC (Conmix), Weber and SIMENTEK
● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grout
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials
Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall

👍2🥰1
👉በግንባታ ቦታ ስለሚደርስ አደጋ (ጉዳት) የሕግ እይታ
—————————————
🚧በሀገራችን የግንባታ ቦታዎች ላይ ስለሚኖረው ደህንነትን የመጠበቅ ትኩረት እየተስተዋለ ያለው ቸልተኝነት አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል።
🏷በ'𝙵𝙸𝙳𝙸𝙲 𝙲𝚘𝚗𝚍𝚒𝚝𝚒𝚘𝚗𝚜 𝚘𝚏 𝙲𝚘𝚗𝚝𝚛𝚊𝚌𝚝 𝙷𝚊𝚛𝚖𝚘𝚗𝚒𝚣𝚎𝚍 𝙴𝚍𝚒𝚝𝚒𝚘𝚗, 𝟸𝟶𝟷𝟶 አንቀጽ 18 (18.3 – 18.4) ሥር “ማንኛውም ሥራ ተቋራጭ ኢንሹራንስ የገባ መሆን ያለበት ሲሆን በውል ሰነዱ ውስጥ በልዩ የውል ድንጋጌ (special condition of contract) ውስጥ ካልተገለጸ በቀር የአካል ጉዳት፣ ሞት ወይም የንብረት ጉዳት ቢደርስ ተገቢውን ካሳ የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል፣ ይህ ግዴታው የግንባታ ባለቤቱን ንብረቶችም የጎዳ ከሆነ ያንንም እስከመሸፈን ይደርሳል” ብሎ አስቀምጧል።
⏺ነገር ግን በውል ሰነዱ ውስጥ በልዩ ሁኔታ የተቀመጠ እና አሰሪው (የፕሮጀክት ባለቤቱ) ማሟላት የነበረበትን ሳያሟላ ቀርቶ አልያም በታወቀ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ በፕሮጀክት ባለቤቱ (client) ጥፋት የተከሰተ አደጋ ከሆነ በውሉ መሰረት ኃላፊነቱን (ካሳን ጨምሮ) ባለቤቱ ይወስዳል ማለት ነው።
(ለዝርዝር ሁኔታዎች አንቀጽ 17.2 እስከ 17.7 እና አንቀጽ 18.3 እስከ 18.4፣ እና አንቀጽ 19.1ን ይመልከቱ)
💫የኢትዮጵያ ፍትሐ ብሔር ህግ አንደኛ መጽሐፍ ልዩ ድንጋጌ ሥር፦ አንድ ሰው በሰራው (በሚሰራው) ሥራ በሌላ ሰው አካል ላይ ጉዳት ያደረሰ (ለምሳሌ በመዶሻ የመታ) እንደሆነ ኃላፊነት እንደሚወስድ በፍት.ሕ. ቁጥር 2067(1) መሰረት ኃላፊነት ይወስዳል።
⏺ነገር ግን ራስን በመከላከል ሂደት ከሆነ ወይም በህግ የተፈቀደ ቅጣት ከሆነ ወይም በተበዳዩ ጥፋት የተነሳ ከሆነ በሚቀርበው ማስረጃ መሰረት ቅጣቱ የእርሱ ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን በቁጥር 2079 (3) መሰረት “ጉዳት ይደርስብኛል” ብሎ የሚሰጋ ሰው ይህንን አሥጊ ጉዳይ ጉዳቱ ከመድረሱ በፊት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲደረግበት እና ጉዳት እንዲወገድለት ሊጠይቅ ይችላል።
❇️በዚሁ ድንጋጌ ላይ በቁጥር 2070 አሰሪው ወይም ተቋራጩ ትፋትን የሚያስከትሉ አሰራሮችን ካልተጠቀመ በቀር በጎረቤት ንብረቶች ላይ ለደረሱ መበላሸቶች ተጠያቂ አይሆንም።
📜በቁጥር 2076 መሰረት ደግሞ የአንድ ሰው ሕንጻ ያልታሰበ ድንገተኛ አደጋን በሌላ ወገን ላይ ቢያደርስ ባለይዞታው ኃላፊነትን ይወስዳል፣ በዚህ አግባብ ካሳ መክፈል ካልቻለ ሕንጻውን ለተበዳዩ እስከመልቀቅ ሊደርስ ይችላል።
🔰በቁጥር 2080 (4) ላይ እንደተመለከተው “በአንድ ሕንጻ ሥር የሚኖር ሰው ከሕንጻው ላይ እየወደቁ ጉዳት የሚያደርሱበት ተንቀሳቃሽ ነገሮች ካሉ የተንቀሳቃሾቹ (የወደቁት) ነገሮች ባለቤት ኃላፊነትን ይወስዳል።
⏺ይህ ህግ በግንባታ ሥራ ጊዜ የሚኖሩ የግንባታ ግብቶች እና በአግባቡ ያልተደገፈ የሚናድ የመሬት ክፍል በሠራተኞቹ ላይ ለሚያደርሱትን ድንገተኛ ጉዳት የግንባታ ሥራውን ዋና ኃላፊ (ተቋራጩን) ተጠያቂ እስከማድረግ ሊተረጎም ይችላል።
⏺በእርግጥ ከላይ ሆኖ ቀጥታ ግብአቶችን ጉዳት ወደደረሰበት ሠራተኛ የለቀቀው ሠራተኛም በልዩ ሁኔታ ተጠያቂ ነው።
🙏ክብር ለአርክቴክቶችና መሐንዲሶች!
🌟ሰላምና ጤና ለግንባታ ሠራተኞች!

👍10
👉የርዕደ-መሬት ክስተት እና የግንባታ ጥራት ትኩረት
🏷አምና በሰሜናዊ ምዕራብ አፍጋኒስታን 6 ነጥብ 5 ሬክተር ስኬል በተመዘገበ
ርዕደ መሬት ምክንያት ከ2400 በላይ የሆኑ ሰዎች ህይወት ተቀጥፏል፡፡
🚧12 መንደሮች እንዳልነበሩ ሆነዋል 1320 መኖሪያዎች ዶግ አመድ እንደሆኑ የሀገሪቱ መንግስት አስታውቆ ነበር፡፡
❇️በአጠቃላም የአደጋው ሰለባ የሆኑት ቤተሰቦች ተበትነዋል፣ ለስነልቦና ቀውስ ተዳርገዋል ፣ ጥሪት አልባ ሆነዋል፡፡
በአደጋው ክፉኛ ጉዳት የደረሰባቸው የርዕደ መሬት አደጋውን መቋቋም ያልቻሉ ህንጻዎች ውስጥ ሲሆን በፍርስራሹ ተቀብረዋል፡፡
❇️በተመሳሳይ ሞሮኮ ላይ 6 ነጥብ 8 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ ርዕደ መሬት አደጋ መከሰት ምክንት 2900 የሚሆኑ ሰዎች የአደጋው ሰለባ በመሆን ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ወደ ስድስት ሺህ የሚጠጉት ደግሞ ቁስለኛ ሆነዋል፡፡
❇️ አደጋው መጠለያ አልባ ያደረጋቸው ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ሰዎች ለማህበረ-ኢኮኖሚ ቀውስ እንዲሁም ለስደት ተዳርገዋል፡፡ በአገሪቱ ገጠራማና ተራራማ አካባቢ ያሉ ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጡ ቤቶች ተንኮታኩተው ትቢያ ሆነዋል፡፡
❇️አብዛኛዎቹ የተንኮታኮቱት ህንፃዎች ርዕደ-መሬትን መቋቋም በሚችል መልኩ አለመገንባታቸው ነው፡፡ በማራካሽ ከተማ አካባቢ አዲስ የተገነቡት ህንፃዎች ከቀድሞ ግንባታዎች ይልቅ አደጋውን መቋቋም እንዳስቻላቸው፣ ይህም አደጋን የመቋቋም ስታንዳርድን አሟልተው በመገንባታቸው መሆኑ በወቅቱ ተዘግቧል፡፡
❇️በሌላ በኩል ታይዋን ለርዕደ-መሬት ከፍተኛ ተጋላጭ ናት፡፡ በወርሃ መጋቢት 2016 ዓ.ም በታይዋን 7 ነጥብ 4 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ ርዕደ-መሬት ቢከሰትም ባላት ጠንካራ የቅድመ መከላከል ስርዓት የከፋ አደጋ እንዳልደረሰ ተዘግቧል፡፡
✅በጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ማኔጅመንት መምህር እንዲሁም የድንገተኛ አደጋ ሕክምና ባለሙያ የሆኑት ጆሴፍ ባርባራ እንደሚሉት ታይዋን አደጋን መቋቋም የሚያስችሉ ግንባታዎችን በማከናወን ረገድ ተምሳሌት ናት።
✅በሌሎች ሀገሮች በተመሳሳይ መጠን በደረሰ ርዕደመሬት ክስተት በርካታ ህንፃዎች ላይ ጉዳት የደረሰው በግንባታ መዋቅሮች ላይ በደረሰ ውድቀት ነው ይላሉ ጆሴፍ ባርባራ፡፡
✅ታይዋን ግን ምስጢሯ በግንባታዎች ላይ አደጋ እንዳይደርስ ለአስር አመታት ያሳየችው ቁርጠኝነት ውጤት ነው ሲሉም አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡ (የመረጃ ምንጮች ሬውተርስ፣ ቢቢሲ ፣ዋሽንግተን ፖስት አሶሺትድ ፕሬስ፣ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ፣ አል-ጀዚራ፣ ዩ ኤስ ቱደይ)
⭐️ከኢትዮጵያ አንፃር
🚧በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የርዕደ መሬት ሊከሰትባቸው የሚችሉ አካባቢዎች ስለመኖራቸው ሳይንሳዊ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
❇️ሰሞኑን በኢትዮጵያ አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ በዓይነቱ ቀላል የሚባልና በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበ ርዕደ-መሬት ስለመከሰቱ የሀገር እና አለማቀፍ የዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡
❇️በክስተቱ ሳቢያ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ አደጋ አለማስከተሉም ተመልክቷል፡፡
❇️በኢትዮጵያ በመሬት ውስጣዊ ኃይል ምክንያት በግንባታዎች ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ የተቀናጀ ሰፊ ስራዎች መከናወን አለባቸው፡፡
❇️በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በኢትዮጵያ የተከናወኑ እና በመከናወን ላይ የሚገኙ ግንባታዎች ለመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የተጋላጭነታቸው መጠን እና የምህንድስና ሙያተኞች የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ ላይ በግንቦት ወር 2015 ዓ.ም ማካሄዱ ይታወሳል፡፡
❇️በወቅቱ የርዕደ መሬት አፈጣጠር ሳይንሳዊ ዳራዉን፣ አለም አቀፍ ገፅታውን ፣ አደጋን የመፍጠር መጠኑን፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊከሰትባቸው የሚችሉ ዞኖችና ቀጠናዎች ላይ የተከናወኑ ሳይንሳዊ ጥናቶች ላይ የዘርፉ ሊቀ-መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር መሰለ ኃይሌ ሰፊ ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡ የመፍትሄ አማራጮችንም ከተጨባጭ እና ሳይንሳዊ ማስረጃዎች አንፃር አብራርተዋል፡፡
❇️ዕምቅ እንዲሁም ንቁ የመሬት ውስጥ ኃይል ክምችት ምክንያት ሊከሰት የሚችል የመሬት መንቀጥቀጥ ምልክቶችና ክስተቶች ያሉባቸውን ብሎም አለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ አካባቢዎችን የተመለከቱ ታሪካዊ መረጃዎችን አጋርተዋል፡፡
❇️የመሬት መንቀጥቀጥ ቢከሰት ምን የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች እንደሚደረጉ ፣ ከተፈፀመ በኋላም መከናወን የሚገባቸውን ተግባራት አቅዶ መንቀሳቀስ አስፈላጊነቱን ከሀገራት ተሞክሮዎች ጋር በማዛመድ ትንታኔ አቅርበዋል፡፡
❇️በግንባታ ሂደት ውስጥ በሚፈጠሩ የዲዛይን ፣ የኮድና ስታንዳርድ መፋለሶች ብሎም በዘርፉ የተንሰራፋ ሙስና ባሉባቸው ሀገሮች ላይ በርዕደ-መሬት ምክንያት የሚደርሱ የጉዳት መጠኖችንና ዓይነቶችን ከተጨባጭ ክስተቶች ጋር በማጣቀስ አስረድተዋል፡፡
❇️በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ጥፋቶችን ለመታደግ ከዘርፉ ባለሙያዎችና ከባለድርሻ አካላት የሚጠበቁ ኃላፊነቶች፣ ሚና እንዲሁም ተግባር ረገድ ሊቀ-መምህሩና ተመራማሪዉ ዶ/ር መሰለ ኃይሌ ሰፊ ግንዛቤ አስጨብጠዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የዘርፉ የፌዴራል ተቋማት ባለድርሻዎች፣ የክልሎች የኮንስትራክሽ ቢሮ የስራ ኃላፊዎች፣ ከ70 ከተሞች የተውጣጡ የህንፃ ሹሞች፣ የዘርፉ ሙያ ማህበራት ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
✳️ለማጠቃለል የግንባታዎችን ኮድና ስታንዳርድ ማስጠበቅ፣ እንዲሁም ጥራትና ደህንነትን ማረጋገጥ የግንባታው ዘርፍ ተዋናዮችና ባለድርሻ አካላት የዘወትር ቁጥር አንድ አጀንዳቸው ሊሆን ይገባል፡፡
በዋናነትም የግንዛቤ ማስጨበጫው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ እንዲሁም የምህንድስና ባለሙያዎች፣ የዘርፉ ተዋናዮች እና ባለድርሻ አካላት በመሰረተ ልማት ግንባታ ሂደቶች ላይ ጥራትን የማስጠበቅ ጉዳይ የልብ ትርታዎቻቸው እንዲሆኑ ማድረግ ይጠበቃል፡፡
በቀጣይም መሰል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች በዘርፉ ተዋናዮች እና ባለድርሻ አካላት ዘንድ ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው፡፡
Via ኢኮባ

👍17❤4🔥1
2017 1st QUARTER CONSTRUCTION WORKS ONLY DIRECT COST.pdf
22.3 MB
#የ2017_የአንደኛ_ሩብ_ዓመት_የኮንስትራክሽን_ስራዎች_ቀጥተኛ_ዋጋ_ጥናት
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥቅምት 01/2017

👍16❤1
የሪል_ስቴት_ልማት_እና_የማይንቀሳቀስ_ንብረት_ግብይትና_ግመታ_አዋጅ_2.pdf
1.7 MB
👉ያልተገነባ ቤት /ግንባታ ከማከናወናቸው በፊት ቤት የሚሸጡ ሪል ስቴት አልሚዎች የሚሰበስቡትን ገንዘብ በዝግ አካውንት እንዲያስቀምጡ ሊገደዱ ነው ፤ በተጨማሪ ግንባታው 80 በመቶ ላይ ያልደረሰን ቤት ለደንበኞች እንዳያስተላልፉ ሊከለከሉ ነው።
🏷ይህንም የሚመለከት ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ቀርቧል።
🚧አዲሱ ረቂቅ አዋጅ እንዴት አገኙት ?

🙏9👍5👏1
የሪል እስቴት ልማትና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጁን በተመለከተ ቢካተቱ የምላቸው ነጥቦች
1) የተፈጻሚነት ወሰኑ ትኩረት ከ50 ቤቶች በላይ ለሚገነቡ የሪል እስቴት አልሚ ተብለው የተጠቀሱት ላይ መሆኑ።
2) ከ50 ቤቶች በታች የሚገነቡና የተገነባ አንድ ቤት ብቻ ያለው ባለቤት ግብይት በሚፈጽምበት ጊዜ ሊመራበት የሚችል አቅጣጫ አለማስቀመጡ።
3) ከውጭ ለሚመጡ አልሚዎች አነስተኛ የኢንቨስትመንት ካፒታል መጠንና ሊገነቡት የሚገባ አነስተኛ የቤት ቁጥር አለመቀመጡ። በኢንቨስትመንት ጋይዱ መሰረት ከተወሰደ ከ200ሺ ዶላር ጀምሮ ስለሚያስተናግድ ፍትሃዊ አይሆንም።
4) የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች በጋራ ወደ ሪል እስቴት ቢዝነስ ሲገቡ በጋራ ሊሰሩት ስለሚገባው የፕሮጀክት መጥንና አነስተኛ ድርሻ የተጠቀሰ ንገር የለውም።
5) ተጀምረው በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ወደ ህጉ ማዕቀፍ ስለሚገቡበት አግባብ የተጠቀሰ አካሄድ የለም። በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ከሚጠናቀቁት ውጪ ወደ ህግ ማዕቀፉ የሚገቡበት መንገድ መቀየስ ይኖርበታል።
6)ግንባታ ላልጃመሩ አልሚዎች ሊከፈል ስለሚገባው ትልቁ የቅድመ ክፍያ መጠን ገደብ አላስቀመጠም። ብዙ ሃገራት ከ10% እንዳይበልጥ ያደርጋሉ።
7) የሪል እስቴት ግብይት ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን የሚዳኝ የተለየ አካል እንደሚኖር አይገልጽም። ዘርፉ የተወሳሰበና ልዩ እውቀትንና ዝግጅትን ስለሚፈልግ ሪል እስቴት ጉዳዮችን ብቻ የሚዳኝ የተለየ የህግ አካል ይፈልጋል።
8) ከውል መዋዋል እስከ ርክክብ ያለውን የግብይት ሂደት የሚያሳይ ግልጽ የስራ ሂደትን የሚያሳይ አካሄድን ማሳየት ይጠበቃል።
9) ግብይቱን ለመምራት ወጥ የሆነ መሪ ውል ተዘጋጅቶ አስገዳጅ መሆን አለበት።
10) የሽያጭ ባለሙያዎችንና እንደራሴዎችን በተመለከተ ፈቃድ ማውጣት እና ማሳደስ እንዳለባቸው እንጂ በዘርፉ ሰልጥነው ተፈትነው ፈቃድ እንደሚሰጣቸው የሚገልጽ ሃሳብ የለውም።
11) የቤት ብድር ለመስጠት የሚቋቋሙ ባንኮች ከተቋቋሙበት ዓላማ ማለትም ለቤት ገዢዎች ከማበደር ይልቅ ወደማልማት እንዳይገቡ አስገዳጅ ሁኔታ መቀመጥ አለበት።
12) አልሚዎች በራሳቸው አመቻችነት ለቤት ገዢዎች ብድር በሚያመቻቹበት ጊዜ መከተል ስለሚገባቸው አሰራርና ስለሚተገበር ክትትል የሚያሳይ ነገር የለውም።
13) አልሚዎች ለደንበኛቻቸው በረጅም ጊዜ በሚከፈል ብድር ቤት በሚሸጡበት ወቅት ሊያስከፍሉ የሚችሉት ትልቁ የወለድ ምጣኔ መካተት አለበት።
14) አልሚዎች በተቀመጠው የፕሮጀክት ማስረከቢያ ጊዜ ተቀባይነት የሌለው መዘግየት ከተከሰተ ሊከፍሉ ስለሚገባው ቅጣት በዝርዝር አልተቀመጠም። አንዳንድ ሃገራት ደንበኛው የገዛውን ቤት የሚመጥን ቤት የሚከራይበትን ወርሃዊ የቤት ኪራይ ሲያስከፍሉ በመዘግየቱ የተነሳ ውሉን ደንበኛው ለማቋረጥ ከፈለገ ክፍያው አልሚው ገንዘቡን በተጠቀመበት ጊዜ የሚለካ ከፍተኛው የሃገሪቱ የብድር ወለድ ምጣኔ ተሰልቶ እንዲመለስ ያደርጋሉ።
15) ለቅድመ ክፍያ እንደ ዋስትና የተጠቀሰው የአልሚውን ካርታ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ማገድ ነው። ይህ ለቤት ገዢ አስተማማኝ ዋስትና አይደለም። ግብይቱ በግለሰብ ደረጃ የሚደረግ በመሆኑ ለተከፈለው መጠን የሚመጥን ዋስትና ከዋስትና ሰጪ ተቋማት እንዲሰጥ ቢደረግ ለአልሚውም ለገዢውም ጥሩ ይሆናል።
16)ስለ ግንባታ ጥራት ቁጥጥር ምንም ያለው ነገር የለም።
17) ስለ ልኬት ምንም የተባለ ነገር የለውም። በሀገራችን የሪል እስቴት ግብይት ውስጥ አንዱ አወዛጋቢ የ Net Area, common arae እና Gross Area ቀመር ነው። ከ ዋና መጠቀሚያው አንጻር የጋራ መጠቀሚያ መጠን ገደብ ሊኖረው ይገባል። ይህ የጋራ መጠቀሚያ ከዋናው መጠቀሚያ ከ20-80% የሚደርስ ሆኖ ገበያ ውስጥ ይታያል። ገደብ እንዲኖረው ቢደረግ። አንዳንዶች ደረጃና የአሳንሰር መዘዋወሪያውን የውሃ ማማዎችን ሳይቀር አስልተው ይጨምራሉ ይህም ገደብ እንዲኖረው ሊደረግ ይገባል።
18)በውጭ ምንዛሪ ስሌት ስለሚደረግ የግብይት ውልስ ምን ታስቧል ? ይህም በግልጽ መልክ ሊይዝ ይገባል።
19) ከርክክብ በኋላ ስለሚሰጥ ዋስትናና የዋስትናው የጊዜ ገደብ ዋስትና የሚሰጥባቸው እንከኖችን በተመለከተ ምንም አልተባለም። ብዙ ሃገራት ከ አንድ እስከ ሁለት ዓመታት ለጥቃቅን ለማይታዩ እንከኖች (latent defects) ሲሰጡ ለ መዋቅራዊ እንከኖች (Structural defects) ከ 5 እስከ10 ዓመታት እንዲሰጥ ያስገድዳሉ። የእኛም ገደብ ይኑረው።
20) አልሚዎች ቀድመው ከፍለው ለሚገዙ ደንበኞቻቸው የፕሮጀክቱን ሂደት በየተወሰነ የጊዜ ገደብ የሚያሳውቁበት አስገዳጅ ሁኔታ መቀመጥ አለበት። ብዙሃገራት አልሚዎች ለደንበኞቻቸው ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ሂደት የሚያሳውቁበት ድረ ገጽ እንዲኖርና አንዳንዶች በየወሩ ብዙዎች በተ ሶስት ወሩ የደረሰበትን እንዲያሳውቁ (Update) ያስገድዳሉ።
21)በሽያጭ ሰራተኞችና አልሚዎች/ገዢዎች መካከል ስለሚደረግ የእንደራሴነት ስራ እንዲሁን በወኪሎችና በስራቸው የሚሰሩ የሽያጭ ሰራተኞች ስምምነትና የክፍያ ሁኔታ ፣ የክፍያ መጠንና የጊዜ ገደብ መተማመንን የሚፈጥር የውል ስምምነት እንዲኖር ቢደረግ መልካም ነው። ጥቂት የማይባሉ የሽያጭ ወኪሎችና የሽያጭ ሰራተኞች የስሩበትን ሲያጡ ይስተዋላል።
22) ታላላቅ ፕሮጀክቶች የሚገነቡ ኢንቨስተሮች የተጠቀሰውን የ40% ለአነስተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖች የሚሆን ቤት እንዲያቀርቡ መሬት ከማመቻቸት ባሻገር የተለያዩ ማበረታቻዎች ሊቀርብ እንደሚችል ቢገለጽና ቢተገበር። በተለይ ከቀረጥ ነጻ መብቶች።
23) የሪል እስቴት ግመታ ስራ ላይ የተቀመጡት መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆነው አንዳንድ አንቀጾች አለመተማመንን የሚፈጥሩና ለንብረት ገማቾች ነጻነትን የማይሰጡ ናቸው። ግምት ሁሉ ግምት ነውና ልዩነት የሚጠበቅ ነው። ታሳቢ ሊደረጉ የሚገባቸው ጉዳዮችን በሚገባ ዘርዝሮ በየጊዜው መረጃ በማሰባሰብና በማጋራት ለሁሉም የሚያግባባ ነገር መፍጠር ላይ ትኩረት እንዲደረግ ቢደረግ መልካም ነው።
24) በዝግ ሂሳብ የሚገባው ገንዘብ ፕሮጀክቱ እስኪጀመርና ውል እስኪፈረም መሆን ይኖርበታል። ፕሮጀክት ትግበራው ላይ የሚቋቋማው አካል የስራ ድርሻ በየጊዜው በሚደርሰው ሪፖርት መሰረት ገንዘቡ ቀጥታ ለታሰበው ፕሮጀክት መዋሉን ማረጋገጥ ነው የሚጠበቅበት። የሌሎች ሃገራት ልምድ ከገባው ገቢ ውስጥ ከ70% በላይ ቀጥታ ፕሮቃጀክቱ ላይ ማዋሉን ያረጋግጣሉ። የአንዱ ፕሮጀክት ገቢ ለሌላ ፕሮጀክት አለመዋሉን ይከታተላሉ። እያንዳዱ ፕሮጀክት የተለየ የባንክ አካውንት ይኖረዋል።
25) በተለያዩ ተጠያቂ በሚያደርጉ ጉዳዮች የሚጠየቀው አካል ተለይቶ መቀመጥ አለበት። አንዳንድ ሃገራት አልሚ ተቋማትን ብቻ ሲቀጡ አንዳንዶች የስራ መሪዋችን እስከ መቅጣት ይደርሳሉ።
እስኪ እናንተም ቢሆን የምትሉትን አክሉበትና ለቋሚ ኮሚቴው እንዲደርስ እናድርገው።
Via ደሳለኝ ከበደ ሲቪል መሀንዲስ እና ሪል ስቴት አማካሪ

👍14❤1
👉ስለ FIDIC
🏷FIDIC የአማካሪ መሐንዲሶች ማኅበራት ፌዴሬሽን በ1957 የመጀመሪያውን ስታንዳርድ ውል አሳትሞ ባወጣ ጊዜ ወይም በዚያው አካባቢ የኢትዮጵያ መንግሥት ሕግ አውጪዎች የፍትሐ ብሔር ሕግ ባረቀቁ ጊዜ የወጣ ነው።
📜FIDIC በየጊዜው ሰነዶቹን እያሻሻለ እ.ኤ.አ በ1987 ያወጣው 4ኛ እትም በዓለም ዙሪያ በሰፊው እየተሰራበት ይገኛል።
💫FIDIC ከዚያ በኋላ በ1999 እንደገና በአዲስ መልክ የተለያዩ ዓላማዎች ላሏቸው ውሎች የሚስማሙ የተለያዩ ቀለሞች ያሏቸውን ስታንዳርድ ውሎች (መጽሐፎች) አውጥቷል።

👍14