2017 1st QUARTER CONSTRUCTION WORKS ONLY DIRECT COST.pdf
22.3 MB
#የ2017_የአንደኛ_ሩብ_ዓመት_የኮንስትራክሽን_ስራዎች_ቀጥተኛ_ዋጋ_ጥናት
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥቅምት 01/2017
@etconp

👍16❤1
የሪል_ስቴት_ልማት_እና_የማይንቀሳቀስ_ንብረት_ግብይትና_ግመታ_አዋጅ_2.pdf
1.7 MB
👉ያልተገነባ ቤት /ግንባታ ከማከናወናቸው በፊት ቤት የሚሸጡ ሪል ስቴት አልሚዎች የሚሰበስቡትን ገንዘብ በዝግ አካውንት እንዲያስቀምጡ ሊገደዱ ነው ፤ በተጨማሪ ግንባታው 80 በመቶ ላይ ያልደረሰን ቤት ለደንበኞች እንዳያስተላልፉ ሊከለከሉ ነው።
🏷ይህንም የሚመለከት ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ቀርቧል።
🚧አዲሱ ረቂቅ አዋጅ እንዴት አገኙት ?

🙏9👍5👏1
የሪል እስቴት ልማትና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጁን በተመለከተ ቢካተቱ የምላቸው ነጥቦች
1) የተፈጻሚነት ወሰኑ ትኩረት ከ50 ቤቶች በላይ ለሚገነቡ የሪል እስቴት አልሚ ተብለው የተጠቀሱት ላይ መሆኑ።
2) ከ50 ቤቶች በታች የሚገነቡና የተገነባ አንድ ቤት ብቻ ያለው ባለቤት ግብይት በሚፈጽምበት ጊዜ ሊመራበት የሚችል አቅጣጫ አለማስቀመጡ።
3) ከውጭ ለሚመጡ አልሚዎች አነስተኛ የኢንቨስትመንት ካፒታል መጠንና ሊገነቡት የሚገባ አነስተኛ የቤት ቁጥር አለመቀመጡ። በኢንቨስትመንት ጋይዱ መሰረት ከተወሰደ ከ200ሺ ዶላር ጀምሮ ስለሚያስተናግድ ፍትሃዊ አይሆንም።
4) የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች በጋራ ወደ ሪል እስቴት ቢዝነስ ሲገቡ በጋራ ሊሰሩት ስለሚገባው የፕሮጀክት መጥንና አነስተኛ ድርሻ የተጠቀሰ ንገር የለውም።
5) ተጀምረው በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ወደ ህጉ ማዕቀፍ ስለሚገቡበት አግባብ የተጠቀሰ አካሄድ የለም። በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ከሚጠናቀቁት ውጪ ወደ ህግ ማዕቀፉ የሚገቡበት መንገድ መቀየስ ይኖርበታል።
6)ግንባታ ላልጃመሩ አልሚዎች ሊከፈል ስለሚገባው ትልቁ የቅድመ ክፍያ መጠን ገደብ አላስቀመጠም። ብዙ ሃገራት ከ10% እንዳይበልጥ ያደርጋሉ።
7) የሪል እስቴት ግብይት ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን የሚዳኝ የተለየ አካል እንደሚኖር አይገልጽም። ዘርፉ የተወሳሰበና ልዩ እውቀትንና ዝግጅትን ስለሚፈልግ ሪል እስቴት ጉዳዮችን ብቻ የሚዳኝ የተለየ የህግ አካል ይፈልጋል።
8) ከውል መዋዋል እስከ ርክክብ ያለውን የግብይት ሂደት የሚያሳይ ግልጽ የስራ ሂደትን የሚያሳይ አካሄድን ማሳየት ይጠበቃል።
9) ግብይቱን ለመምራት ወጥ የሆነ መሪ ውል ተዘጋጅቶ አስገዳጅ መሆን አለበት።
10) የሽያጭ ባለሙያዎችንና እንደራሴዎችን በተመለከተ ፈቃድ ማውጣት እና ማሳደስ እንዳለባቸው እንጂ በዘርፉ ሰልጥነው ተፈትነው ፈቃድ እንደሚሰጣቸው የሚገልጽ ሃሳብ የለውም።
11) የቤት ብድር ለመስጠት የሚቋቋሙ ባንኮች ከተቋቋሙበት ዓላማ ማለትም ለቤት ገዢዎች ከማበደር ይልቅ ወደማልማት እንዳይገቡ አስገዳጅ ሁኔታ መቀመጥ አለበት።
12) አልሚዎች በራሳቸው አመቻችነት ለቤት ገዢዎች ብድር በሚያመቻቹበት ጊዜ መከተል ስለሚገባቸው አሰራርና ስለሚተገበር ክትትል የሚያሳይ ነገር የለውም።
13) አልሚዎች ለደንበኛቻቸው በረጅም ጊዜ በሚከፈል ብድር ቤት በሚሸጡበት ወቅት ሊያስከፍሉ የሚችሉት ትልቁ የወለድ ምጣኔ መካተት አለበት።
14) አልሚዎች በተቀመጠው የፕሮጀክት ማስረከቢያ ጊዜ ተቀባይነት የሌለው መዘግየት ከተከሰተ ሊከፍሉ ስለሚገባው ቅጣት በዝርዝር አልተቀመጠም። አንዳንድ ሃገራት ደንበኛው የገዛውን ቤት የሚመጥን ቤት የሚከራይበትን ወርሃዊ የቤት ኪራይ ሲያስከፍሉ በመዘግየቱ የተነሳ ውሉን ደንበኛው ለማቋረጥ ከፈለገ ክፍያው አልሚው ገንዘቡን በተጠቀመበት ጊዜ የሚለካ ከፍተኛው የሃገሪቱ የብድር ወለድ ምጣኔ ተሰልቶ እንዲመለስ ያደርጋሉ።
15) ለቅድመ ክፍያ እንደ ዋስትና የተጠቀሰው የአልሚውን ካርታ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ማገድ ነው። ይህ ለቤት ገዢ አስተማማኝ ዋስትና አይደለም። ግብይቱ በግለሰብ ደረጃ የሚደረግ በመሆኑ ለተከፈለው መጠን የሚመጥን ዋስትና ከዋስትና ሰጪ ተቋማት እንዲሰጥ ቢደረግ ለአልሚውም ለገዢውም ጥሩ ይሆናል።
16)ስለ ግንባታ ጥራት ቁጥጥር ምንም ያለው ነገር የለም።
17) ስለ ልኬት ምንም የተባለ ነገር የለውም። በሀገራችን የሪል እስቴት ግብይት ውስጥ አንዱ አወዛጋቢ የ Net Area, common arae እና Gross Area ቀመር ነው። ከ ዋና መጠቀሚያው አንጻር የጋራ መጠቀሚያ መጠን ገደብ ሊኖረው ይገባል። ይህ የጋራ መጠቀሚያ ከዋናው መጠቀሚያ ከ20-80% የሚደርስ ሆኖ ገበያ ውስጥ ይታያል። ገደብ እንዲኖረው ቢደረግ። አንዳንዶች ደረጃና የአሳንሰር መዘዋወሪያውን የውሃ ማማዎችን ሳይቀር አስልተው ይጨምራሉ ይህም ገደብ እንዲኖረው ሊደረግ ይገባል።
18)በውጭ ምንዛሪ ስሌት ስለሚደረግ የግብይት ውልስ ምን ታስቧል ? ይህም በግልጽ መልክ ሊይዝ ይገባል።
19) ከርክክብ በኋላ ስለሚሰጥ ዋስትናና የዋስትናው የጊዜ ገደብ ዋስትና የሚሰጥባቸው እንከኖችን በተመለከተ ምንም አልተባለም። ብዙ ሃገራት ከ አንድ እስከ ሁለት ዓመታት ለጥቃቅን ለማይታዩ እንከኖች (latent defects) ሲሰጡ ለ መዋቅራዊ እንከኖች (Structural defects) ከ 5 እስከ10 ዓመታት እንዲሰጥ ያስገድዳሉ። የእኛም ገደብ ይኑረው።
20) አልሚዎች ቀድመው ከፍለው ለሚገዙ ደንበኞቻቸው የፕሮጀክቱን ሂደት በየተወሰነ የጊዜ ገደብ የሚያሳውቁበት አስገዳጅ ሁኔታ መቀመጥ አለበት። ብዙሃገራት አልሚዎች ለደንበኞቻቸው ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ሂደት የሚያሳውቁበት ድረ ገጽ እንዲኖርና አንዳንዶች በየወሩ ብዙዎች በተ ሶስት ወሩ የደረሰበትን እንዲያሳውቁ (Update) ያስገድዳሉ።
21)በሽያጭ ሰራተኞችና አልሚዎች/ገዢዎች መካከል ስለሚደረግ የእንደራሴነት ስራ እንዲሁን በወኪሎችና በስራቸው የሚሰሩ የሽያጭ ሰራተኞች ስምምነትና የክፍያ ሁኔታ ፣ የክፍያ መጠንና የጊዜ ገደብ መተማመንን የሚፈጥር የውል ስምምነት እንዲኖር ቢደረግ መልካም ነው። ጥቂት የማይባሉ የሽያጭ ወኪሎችና የሽያጭ ሰራተኞች የስሩበትን ሲያጡ ይስተዋላል።
22) ታላላቅ ፕሮጀክቶች የሚገነቡ ኢንቨስተሮች የተጠቀሰውን የ40% ለአነስተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖች የሚሆን ቤት እንዲያቀርቡ መሬት ከማመቻቸት ባሻገር የተለያዩ ማበረታቻዎች ሊቀርብ እንደሚችል ቢገለጽና ቢተገበር። በተለይ ከቀረጥ ነጻ መብቶች።
23) የሪል እስቴት ግመታ ስራ ላይ የተቀመጡት መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆነው አንዳንድ አንቀጾች አለመተማመንን የሚፈጥሩና ለንብረት ገማቾች ነጻነትን የማይሰጡ ናቸው። ግምት ሁሉ ግምት ነውና ልዩነት የሚጠበቅ ነው። ታሳቢ ሊደረጉ የሚገባቸው ጉዳዮችን በሚገባ ዘርዝሮ በየጊዜው መረጃ በማሰባሰብና በማጋራት ለሁሉም የሚያግባባ ነገር መፍጠር ላይ ትኩረት እንዲደረግ ቢደረግ መልካም ነው።
24) በዝግ ሂሳብ የሚገባው ገንዘብ ፕሮጀክቱ እስኪጀመርና ውል እስኪፈረም መሆን ይኖርበታል። ፕሮጀክት ትግበራው ላይ የሚቋቋማው አካል የስራ ድርሻ በየጊዜው በሚደርሰው ሪፖርት መሰረት ገንዘቡ ቀጥታ ለታሰበው ፕሮጀክት መዋሉን ማረጋገጥ ነው የሚጠበቅበት። የሌሎች ሃገራት ልምድ ከገባው ገቢ ውስጥ ከ70% በላይ ቀጥታ ፕሮቃጀክቱ ላይ ማዋሉን ያረጋግጣሉ። የአንዱ ፕሮጀክት ገቢ ለሌላ ፕሮጀክት አለመዋሉን ይከታተላሉ። እያንዳዱ ፕሮጀክት የተለየ የባንክ አካውንት ይኖረዋል።
25) በተለያዩ ተጠያቂ በሚያደርጉ ጉዳዮች የሚጠየቀው አካል ተለይቶ መቀመጥ አለበት። አንዳንድ ሃገራት አልሚ ተቋማትን ብቻ ሲቀጡ አንዳንዶች የስራ መሪዋችን እስከ መቅጣት ይደርሳሉ።
እስኪ እናንተም ቢሆን የምትሉትን አክሉበትና ለቋሚ ኮሚቴው እንዲደርስ እናድርገው።
Via ደሳለኝ ከበደ ሲቪል መሀንዲስ እና ሪል ስቴት አማካሪ

👍14❤1
👉ስለ FIDIC
🏷FIDIC የአማካሪ መሐንዲሶች ማኅበራት ፌዴሬሽን በ1957 የመጀመሪያውን ስታንዳርድ ውል አሳትሞ ባወጣ ጊዜ ወይም በዚያው አካባቢ የኢትዮጵያ መንግሥት ሕግ አውጪዎች የፍትሐ ብሔር ሕግ ባረቀቁ ጊዜ የወጣ ነው።
📜FIDIC በየጊዜው ሰነዶቹን እያሻሻለ እ.ኤ.አ በ1987 ያወጣው 4ኛ እትም በዓለም ዙሪያ በሰፊው እየተሰራበት ይገኛል።
💫FIDIC ከዚያ በኋላ በ1999 እንደገና በአዲስ መልክ የተለያዩ ዓላማዎች ላሏቸው ውሎች የሚስማሙ የተለያዩ ቀለሞች ያሏቸውን ስታንዳርድ ውሎች (መጽሐፎች) አውጥቷል።
❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!
📜ለ ስራ እና ጨረታዎች ምንለቅበት ቻናል ለመቀላቀል👉 @ETCONpWORK
📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT
💫ቲክቶክ:👇
www.tiktok.com/@etconp7

👍14
Ethio Construction Engineering
👉ስለ FIDIC 🏷FIDIC የአማካሪ መሐንዲሶች ማኅበራት ፌዴሬሽን በ1957 የመጀመሪያውን ስታንዳርድ ውል አሳትሞ ባወጣ ጊዜ ወይም በዚያው አካባቢ የኢትዮጵያ መንግሥት ሕግ አውጪዎች የፍትሐ ብሔር ሕግ ባረቀቁ ጊዜ የወጣ ነው። 📜FIDIC በየጊዜው ሰነዶቹን እያሻሻለ እ.ኤ.አ በ1987 ያወጣው 4ኛ እትም በዓለም ዙሪያ በሰፊው እየተሰራበት ይገኛል። 💫FIDIC ከዚያ በኋላ በ1999 እንደገና በአዲስ…
👉ዓለም ዐቀፍ የውል ሰነዶች (መደበኛ ውሎች)
🚧ከ 'FIDIC' በተጨማሪ በእኛ ሀገር ብዙም አይታወቁም እንጂ ሌሎች ተቋሞች ያዘጋጇቸው ስታንዳርድ ውሎችም አሉ።
💫ለምሳሌ፦ Joint Contract Tribunal (JCT) የሚባል ዘርፉ የሚመለከታቸው ቡድኖች ተሰባስበው ያዘጋጁት ከ1909 ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለ ሰነድ አለ።
📜ሰነዱ በ2005 ተሻሽሎ የወጣ ሲሆን JCT Standard Building Contract የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።
💫የአሜሪካ አርክቴክቶች ማኅበር (AIA) ያዘጋጀውም General Conditions አለ።
💫Institute of Civil Engineers (ICE) ደግሞ በ2005 ያወጣው The New Engineering Contract (NEC 3) በጣም ተወዳጅ እየሆነ መምጣቱንና በእንግሊዝ ሀገር በባሕር ሥር የሚያልፈውን የባቡር ሐዲድ ውል የተፈራረሙበት መሆኑን Murdoch and Huges የተባሉ ጸሐፊዎች የኮንስትራክሽን ውሎች በሚል ርእስ በጻፉት መጽሐፍ ጠቅሰዋል።
ይህ ተቋም ቀደም ብሎ በ1945 ለመጀመሪያ ጊዜ ስታንዳርድ ውል አዘጋጅቶ ነበር።
⭐️በየጊዜው እየተሻሻለ መጥቶ ሰባተኛው እትም በ1999 ICE 7 Condition of Contract – measurement Version በሚል ርእስ ታትሟል።
💫FIDIC ያዘጋጀው ስታንዳርድ ውል ከዚህ ICE ካዘጋጀው ስታንዳርድ ውል ከ4ኛ እትም የተወሰደ ወይም የተቀዳ እንደሆእነ መርዶክ የተባለ ጸሕፊ እና ዘውዱ ተፈራም ጠቅሰውታል።
🏷ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅቶች (ለምሳሌ የዓለም ባንክ) Standard Biding Docuement for Procurement በሚል በ1995 ባዘጋጀው ሰነድ ውስጥም ጠቅላላ አናቅጽ ሰፍረው እናገኛለን።
❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!
📜ለ ስራ እና ጨረታዎች ምንለቅበት ቻናል ለመቀላቀል👉 @ETCONpWORK
📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT
💫ቲክቶክ:👇
www.tiktok.com/@etconp7
@etconp
🚧ከ 'FIDIC' በተጨማሪ በእኛ ሀገር ብዙም አይታወቁም እንጂ ሌሎች ተቋሞች ያዘጋጇቸው ስታንዳርድ ውሎችም አሉ።
💫ለምሳሌ፦ Joint Contract Tribunal (JCT) የሚባል ዘርፉ የሚመለከታቸው ቡድኖች ተሰባስበው ያዘጋጁት ከ1909 ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለ ሰነድ አለ።
📜ሰነዱ በ2005 ተሻሽሎ የወጣ ሲሆን JCT Standard Building Contract የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።
💫የአሜሪካ አርክቴክቶች ማኅበር (AIA) ያዘጋጀውም General Conditions አለ።
💫Institute of Civil Engineers (ICE) ደግሞ በ2005 ያወጣው The New Engineering Contract (NEC 3) በጣም ተወዳጅ እየሆነ መምጣቱንና በእንግሊዝ ሀገር በባሕር ሥር የሚያልፈውን የባቡር ሐዲድ ውል የተፈራረሙበት መሆኑን Murdoch and Huges የተባሉ ጸሐፊዎች የኮንስትራክሽን ውሎች በሚል ርእስ በጻፉት መጽሐፍ ጠቅሰዋል።
ይህ ተቋም ቀደም ብሎ በ1945 ለመጀመሪያ ጊዜ ስታንዳርድ ውል አዘጋጅቶ ነበር።
⭐️በየጊዜው እየተሻሻለ መጥቶ ሰባተኛው እትም በ1999 ICE 7 Condition of Contract – measurement Version በሚል ርእስ ታትሟል።
💫FIDIC ያዘጋጀው ስታንዳርድ ውል ከዚህ ICE ካዘጋጀው ስታንዳርድ ውል ከ4ኛ እትም የተወሰደ ወይም የተቀዳ እንደሆእነ መርዶክ የተባለ ጸሕፊ እና ዘውዱ ተፈራም ጠቅሰውታል።
🏷ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅቶች (ለምሳሌ የዓለም ባንክ) Standard Biding Docuement for Procurement በሚል በ1995 ባዘጋጀው ሰነድ ውስጥም ጠቅላላ አናቅጽ ሰፍረው እናገኛለን።
❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!
📜ለ ስራ እና ጨረታዎች ምንለቅበት ቻናል ለመቀላቀል👉 @ETCONpWORK
📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT
💫ቲክቶክ:👇
www.tiktok.com/@etconp7
@etconp
🙏7👍3❤2
Intercon Construction Chemicals
👉 Authorized agent of MC (Conmix), Weber and SIMENTEK
● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grout
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials
Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall

👍3
👉የጨረታ ማስጠበቂያ (Bid Security Bond)
🏷የጨረታ ማስጠበቂያ ለተቋራጮች የወጣ ጨረታ (በተለይ ክፍት ጨረታ /open tender/) የጨረታ ማስጠበቂያ መያዣ በማረጋገጫ ሰነድ ላይ በቴክኒካል ሰነድ (Technical Documents) እንዲካተት ይጠበቃል።
▶️ይህ የጨረታ ማስጠበቂያ (Bid Security Bond) በ’ PPA (section 1) “instruction to bidder (ITB) አንቀጽ አሥራ ስድስት (article 16) ላይ እንደተመለከተው አንድ ተጫራች የወጣውን ጨረታ ሞልቶ ካስገባ በኋላ ጨረታውን ቢያሸንፍ እና አሸናፊነቱን የሚገልጽ የቅቡልነት ደብዳቤ (Acceptance Letter) ከተጻፈለት በኋላ ሀሳብ ቀይሮ “የተወዳደርኩበትን ጨረታ ትቼዋለሁ፣ የግንባታ ውል መፈራረምም ይሁን ግንባታውን ማከናወን አልፈልግም” ቢል ጨረታውን ለማከናወን የወጣውን ወጪ ለመሸፈን እና በደረጃ ቅደም ተከተል መሰረት ለሌሎቹ አሸናፊዎች ጥሪ ለማድረግ አልያም እንደገና ውድድሩን ለማከናወን የሚያስችል ገንዘብ ተደርጎ ይታሰብና ጨረታውን ላወጣው አካል የሚሰጥ የባንክ ማረጋገጫ ደረሰኝ (Certified Payment Order - CPO) ነው።
🏷የጨረታ ማስከበሪያ(Bid Security Bond) በ'PPA ITB 16.2 መሰረት በካሽ ወይም በተፈረመበት ቼክ ወይም በክፍያ ማዘዣ ወይም በተቀናሽ ሂሳብ ደብዳቤ ወይም በየትኛውም የባንክ ዋስትና ማረጋገጫ ሊገለጽ የሚችል ሆኖ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን መጠን ያህን የሆነ ገንዘብ ወይም ግምቱ ከዚያ የማያንስ ንብረት/ዋስትና ሊሆን ይችላል።
🌟በውጪ ባንኮች የተሰጠ ዋስትና ከሆነ በሀገር ውስጥ ባንኮች በኩል ዋስትናውን የማረጋገጫ ሰነድ መቅረብ አለበት እንጂ የውጪ ባንኮች ዋስትና በቀጥታ ተግባራዊ ሊደረግ አይችልም።
🌟ማንኛውም አስተማማኝ የጨረታ ማስከበሪያ የሌለው የጨረታ መልስ ሰነድ (Bid response) ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ውድቅ መደረግ ይኖርበታል።
⏺ከአንድ በላይ የሆኑ ማኅበራት ላቀረቡት የጨረታ ሙሌት ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ በጋራ ሲያስገቡ የሁሉም ድርጅቶች ስም በጨረታ ማስከበሪያው ላይ መዘርዘር ይኖርበታል።
❇️የገንዘቡ መጠን በጨረታ ሰነዱ Bid Data Sheet ITB Article16ን ተመርኩዞ በወጣው የጨረታ ሰነድ Bid Data Sheet section ሥር ባለው Preparation of Bids በሚለው ሰንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሰው መጠን የተገለጸው መሆን አለበት።
❇️መጠኑ እንደፕሮጀክቱ ስፋት፣ እንደፕሮጀክቱ ወሳኝነት እና እንደተገመተው የጨረታ ማፍረስ ስጋት ታይቶ በጨረታ አውጪው አካል ሊወሰን ይችላለ ነገር ግን አሸናፊው ተጫራች የአሸናፊነቱን ደብዳቤ ተቀብሎ ሥራውን መጀመር የሚችል ከሆነ በጨረታ ሰነዱ Bid Data Sheet & ITB 16.5 መሰረት ሙሉ ለሙሉ ተመላሽ ይሆናል።
⏺የጨረታ ማስጠበቂያ (ማስከበሪያ) ገንዘብ ለተጫራቹ የሚመለስበት ጊዜ በ’ITB, article 16 (16.2) መሰረት ለ28 ቀናት በባንክ ከቆየ በኋላ መሆን አለበት።
📜በህግ ረገድ ስለዋስተና አይነቶች የሚያብራራው የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 646/2001 ዝርዝር አንስቷል።
💫የጨረታ ማስከበሪያ ለተጫራቹ የማይመለስባቸው ምክንያቶች፦
⏺[1ኛ] ተጫራቱ ጨረታውን ቢያሸንፍም ሥራውን ተዋውሎ ለመሥራት ፍቃደኛ ካልሆነ ወይም ሀሳብ ከቀየረ።
⏺[2ኛ] ተጫራቹ የዋጋ ማስተካከያ በPPA ITB clause 27 (በታወቁ ስህተቶች መሰረት የተሞላ አግባብነት የሌለውን ዋጋ ስለማውጣት የተደነገገ አንቀጽ) መሰረት የተደረገ የዋጋ ማስተካከያ ርምጃዎችን አልቀበልም ካለ እና [3ኛ] አሸናፊው ተጫራች ሥውል ፈጽሞ ራውን ለመሥራት ፈቃደኛ ቢሆንም በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ውል መፈረም ካልቻለ ወይም ሌሎች የውል ማስከበሪያዎችን ማቅረብ ካልቻለ ነው።

👍19❤1
👉ሼቤሌይ ሪዞርት ሶማሌ ክልል
⭐️የ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነውና ከጅግጅጋ ከተማ ወጣ ብሎ እየተገነባ ያለው የሸቤለይ ሪዞርት ስምንት ዘመናዊ መንደሮች፣ ሦስት ሰው ሰራሽ ግድቦች፣ 13 ኪሜ ኮንክሪት አስፋልት ግንባታ፣ የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት፣ የመብራትና የቴሌኮም መሰረተ ልማት ያካተተ ነው።
💫በምስሉ ላይ በሚታየው መልኩ የሶማሊ ማህበረሰብን ቤት አሰራርን ለመግለጽ ተነድፏል፡፡

❤7👍7
👉Here are the main types of column failure, along with explanations of what causes them:
1. Buckling:
• Cause: This occurs when a column is subjected to a compressive load that exceeds its buckling capacity. Buckling is essentially a sudden lateral (sideways) deformation of the column, often resulting in a sudden collapse.
• Factors:
* Slenderness Ratio: The ratio of the column's length to its least radius of gyration. Slender columns are more prone to buckling.
* Load: High compressive loads increase the risk of buckling.
* Material Properties: The stiffness and strength of the column material play a role.
2. Crushing:
• Cause: Crushing occurs when the compressive load applied to a column exceeds its compressive strength. The column literally crushes under the weight.
• Factors:
* Load: High compressive loads increase the risk of crushing.
* Material Strength: The material's resistance to compression.
* Cross-Sectional Area: A smaller cross-sectional area makes the column more vulnerable to crushing.
3. Shear Failure:
• Cause: Shear failure happens when the shear stress in the column exceeds its shear strength. This often occurs in columns subjected to lateral loads or eccentric loads.
• Factors:
* Lateral Loads: Forces applied perpendicular to the column's axis.
* Eccentric Loads: Loads applied off-center of the column, causing bending.
* Material Strength: The column's resistance to shear stress.
4. Combined Failure:
• Cause: Columns can fail due to a combination of factors. For example, buckling can lead to increased shear stresses, which then contribute to shear failure.
• Factors:
* Slenderness Ratio: A slender column is more susceptible to both buckling and shear failure.
* Load Type: A combination of compressive, lateral, and eccentric loads can lead to a complex failure mode.
5. Fatigue Failure:
• Cause: Fatigue failure occurs due to repeated or cyclic loading. Over time, these repeated stresses can lead to cracks and eventually failure.
• Factors:
* Load Cycles: The number of times the load is applied and removed.
* Stress Range: The difference between the maximum and minimum stress levels in each cycle.
* Material Properties: The fatigue resistance of the column material.
6. Corrosion-Induced Failure:
• Cause: Corrosion can weaken the column material, reducing its strength and load-carrying capacity.
• Factors:
* Exposure: Exposure to moisture, chemicals, and salt can accelerate corrosion.
* Material Type: Some materials are more susceptible to corrosion than others.
Prevention and Mitigation:
• Proper Design: Ensure the column is adequately designed to resist the expected loads.
• Material Selection: Choose materials with appropriate strength and durability.
• Corrosion Protection: Use protective coatings or treatments to prevent corrosion.
• Regular Inspection: Monitor the column for signs of damage or deterioration.
In summary, column failures are a serious concern in structural engineering. Understanding the different modes of failure is essential for ensuring the safety and stability of structures.

Telegram
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World
Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK
📩 @Philemona7

👍17❤2
𝑷𝒓𝒊𝒄𝒊𝒏𝒈 𝑪𝒐𝒏𝒕𝒓𝒂𝒄𝒕𝒐𝒓 𝑫𝒆𝒍𝒂𝒚 𝑪𝒐𝒔𝒕𝒔
Almost all projects encounter compensable delay at some point during the performance of the work.
Few contracts set forth any specific method for calculating the cost of a day of delay in the contract documents.
Assuming agreement on an extension of time can be reached and a method for calculating the cost of the extended field office overhead resulting from the compensable delay, delay damages are still subject to two additional markups. The first markup is profit. “… [A] contractor would be entitled to profit as an element of its quantum recovery if delays are compensable.”
The second markup applies if the owner has required Performance and Payment Bonds on the project. If so, the sum of the delay damages plus profit is subject to bond cost markup as this is now an added cost to the project and the bond cost is based on total actual project costs.
What are Delay costs?
-Labor Costs
-Equipment Costs
-Material Costs
-Subcontractor Costs
-Jobsite Overhead Costs
-Home Office Overhead Costs
How is extended field office overhead calculated?
•Actual cost method
•Total cost method
•Jury verdict (or “fair and reasonable approximation” of the damages.
•Stipulated contract method
It is recommended that the owner, their design professionals and their legal counsel consider this issue during the design period select a method and carefully craft and include the method in the contract documents prior to bid.
Thank you

👍20
👉ደረጃቸውን ያልጠበቁ ግንባታዎችን የሚያከናውኑ ላይ ከእስራት እስከ ፈቃድ ዕገዳ ቅጣት የሚጥል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ
🚧ደረጃቸውን ያልጠበቁ ግንባታዎች በሚያከናወኑና ሌሎች የወንጀል ድንጋጌዎችን የሚጥሱ ባለሙያዎች፣ የሥራ ተቋራጮችና አማካሪዎች ላይ ከእስራት እስከ ፈቃድ ማገድ ቅጣት የሚጥል በሕንፃ ረቂቅ አዋጅ ተካቶ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡
⏺ረቂቁ የቀረበው ሐሙስ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በተካሄው ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አራተኛ ዓመት የሥራ ዘመን አንደኛ ስብሰባ ነው፡፡ በረቂቅ አዋጁ ክፍል ዘጠኝ የተቀመጠው አስተዳደራዊ የወንጀል ቅጣቶችን በተመለከተ፣ አዋጁን ለማስፈጸም የሚወጡ ድንጋጌዎችን በሚተላለፉ ሰዎች ላይ አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንደሚወስድ ይደነግጋል፡፡
በአሠሪ ስለሚፈጸሙ ወንጀሎች፣ የአማካሪነት የሙያ ኃላፊነት መጣስና በረቂቅ አዋጁ የተቀመጡ ዝርዝር ድንጋጌዎችን ተላልፈው የተገኙ ግለሰቦች፣ የሥራ ተቋራጮችና የሚመለከታቸው አካላት በፍርድ ቤት ጥፋተኛ በተባሉበትና አንቀጽ እስከ ተመለከተው ከፍተኛ እስራት ዘመን ቅጣት በተጨማሪ፣ የሙያ ወይም የሥራ ፈቃዳቸው እንደሚታገድ ተደንግጓል፡፡
በሕንፃ በረቂቅ አዋጅ ዘጠኝ የተቀመጠው አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶችን በተመለከተ፣ አዋጁን ለማስፈጸም የሚወጡ ድንጋጌዎችን በሚተላለፉ ሰዎች ላይ አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንደሚወስድ በረቂቁ ተመላክቷል፡፡
ያላግባብ በተሰጠ የግንባታ ፈቃድ፣ እንዲሁም የመቆጣጠር ግዴታን ባለመወጣት ሕገወጥ ግንባታ እንዲከናወን የረዳ ግለሰብ ከአምስት ዓመታት እስከ አሥር ዓመታት የሚደርስ ፅኑ እስራት፣ ከአሥር ሺሕ ብር ጀምሮ እስከ አምስት ሺሕ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚቀጣ ተደንግጓል፡፡
ደረጃው የማይፈቅድለት ወይም ተገቢው ፈቃድ ሳይኖረው ግንባታ ያከናወነ ግለሰብ (ሥራ ተቋራጭ) እስከ አሥር ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራትና እስከ አሥር ሺሕ የሚደርስ የገንዘብ መቀጫ እንደሚቀጣ በረቂቁ ተዘርዝሯል፡፡
ማንኛውም የተመዘገበ የሥራ ተቋራጭ ደረጃውን ያልጠበቀ ግንባታ ሲያከናውንና ግንባታው አደጋ ያስከተለ ከሆነ፣ ከአምስት ዓመታት እስከ አሥር ዓመታት ፅኑ እስራትና ከ50,000 እስከ 100,000 ብር እንደሚቀጣ በረቂቁ ተቀምጧል፡፡
የሕንፃ ረቂቅ አዋጅ የሕዝብ ጤንነትና ደኅንነት መጠበቅ፣ የሕንፃ ተደራሽነት ለአካል ጉዳተኞችና ለሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች ለማረጋገጥ የሚያስችል፣ በአገሪቱ በአጠቃላይ ተፈጻሚ የሚሆን ዝቀተኛውን ደረጃ ለመወሰን አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ነባሩ ሕግ በአፈጻጸም ወቅት የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ስላሉበት፣ የአካል ጉዳተኞችን ተደራሽነት የሚያረጋግጥ፣ የግንባታ ጥራትና የሀብት ብክነት ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ግልጽና ለአተገባር ምቹ የሆኑ አሠራር መዘርጋት ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቁ አዋጅ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡
ረቂቁ በአሥር ክፍሎችና በ54 አንቀጾች የተዋቀረ መሆኑን፣ የተፈጻሚነት ወሰኑ ስለሕንፃ ግንባታ ፈቃድ አሰጣጥ፣ ክትትልና ቁጥጥር፣ አስፈጻሚ አካላት ተግባርና ኃላፊነት፣ አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶችን የተመለከቱን ጨምሮ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ተካተውበታል፡፡
የሕንፃ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 2/2017 ሆኖ ለፓርላማው የከተማ መሠረተ ልማትና ትርንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡
Via Reporter

👍23👏3🤝1
👉Why is the pH of Concrete Important?
🚧The pH of concrete plays a crucial role in its durability and long-term performance. Here’s why it matters:
⭐️1. Corrosion Protection for Steel Reinforcement: Concrete has a naturally high pH (around 12-13), which creates a protective alkaline environment around steel reinforcements, preventing corrosion.
⭐️2. Indicator of Chemical Reactions: A drop in pH can signal carbonation or other chemical reactions that might weaken the concrete, leading to structural failures.
⭐️3. Maintaining Structural Integrity: High pH ensures that harmful elements like chlorides and sulfates don’t penetrate the concrete and compromise its strength over time.
⭐️4. Longevity of the Structure: Ensuring that concrete maintains its ideal pH is key to extending the life of the structure and reducing maintenance costs.
🏷Have you ever encountered issues due to a low pH in concrete? Share your thoughts and experiences!
Via Yonatan

👍12❤1
2017_E_C_1st_QUARTER_CONSTRUCTION_WORKS_ONLY_DIRECT_COST_01_02_171.pdf
26.8 MB
ቢሮው ጥቅምት 01/2017 ዓ/ም ባወጣው የ2017 አንደኛ ሩብ ዓመት የኮንስትራክሽን ስራዎች ቀጥተኛ ዋጋ (Direct Cost) ጥናት ሰነድ ላይ sanitary እና Road work ጥናቶችን የያዙ ገፆች በመዘለላቸው ይቅርታ እየጠየቅን የተሟላው ሰነድ እንሆ፡፡
ጥቅምት 04/2017 ዓ/ም የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ

🙏12👍3👏2