Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.32K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉የግንባታ ወጪን ለመቀነሰ የሚረዱ አማራጭ ዘዴዎች

🚧ለህንፃ ግንባታ የሚያስፈልጉ እንደ ብረት፣ ሲሚንቶ፣ ብሎኬት፣ ጠጠር ያሉ ጥሬ ዕቃዎች ዋጋ እየጨመረ የመሄዱ ጉዳይ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡

💫ለዚህ መንስኤ በዋነኝነት የሚጠቀሱት የማምረቻ፣ የሠራተኛ ጉልበት፣ የትራንፖርት ዋጋ መጨመር እና ተያያዥነት ያለው የዋጋ ግሽበት ናቸው፡፡

⏺የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ልዩ ባህሪ ደግሞ ጥሬ ዕቃዎችን በመግዛት እና በመደባለቅ፣ ጠንካራ ረጅም ዕድሜ የሚኖረው እና ውብ የሆኑ ህንፃዎችን መገንባት ነው፡፡

▶️ከዚህ በመነሳት የኮንስትራክሽን ኤክስፐርቶች የጥሬ ዋጋ ንረትን በመቋቋም ወጪን ለመቀነስ ያስችላሉ ብለው በቀዳሚነት ያስቀመጧቸውን አሠራሮች መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

🔰ጠንካራ የዕቅድ ፕላን መዘርጋት

⏺እንደ ማንኛውም የንግድ ዘርፍ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ የመጨረሻ ልብ ማትረፍ ነው፡፡ ይህንን ትርፍ ለማግኘት ለግንባታው የሚያስፈልገውን በጀት እና ዝርዝር የግንባታ ሂደቶች የተመለከተ ጠንካር ያለ የዕቅድ ፕላን መቀየር ነው፡፡

▶️ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከሚያስችሉ ጠንካር ያሉ የዕቅድ ፕላኖች ውስጥ ጥሬ ዕቃዎችን ካለው  ነባራዊ ሁኔታ በመመርመር ቀደም ብሎ ማከማቸት በእያንዳንዱ የግንባታ ሂደት የሚያስፈልጉ ግብዕቶችን ቀደም ብሎ ማዘጋጀት ናቸው፡፡


🔰መደበኛ የሆነ እና የሚደጋገም ዲዛይን

⏺አንድ ህንፃ ከመሬት ተነስቶ እያደገ በሄደ ቁጥር፣ የሚይዛቸው የክፍል ገፅታዎች መደበኛ የሆነ ስፋት እና ገፅታ የተለበሱ እንደሆኑ ማድረግ ዋጋን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

▶️ህንፃው ባደገ ቁጥር የውስጥ ገፅታ ዲዛይን የሚለዋወጥ ከሆነ፣ የጥሬ ቁስ ብክነት ያስከትላል፡፡ ለተለዋጭ ዲዛይን የሚሆን ሌላ ጥሩ ቁስ መግዛትን ይጠይቃል፡፡

▶️እስከ ዘለቄታው ለግንባታ የሚያገለግሉ ቁሶችን ቀደም ብሎ ማከማቸት እንዳይቻል ያደርጋል፡፡ ለግንባታ የሚያስፈልጉ መሣሪያዎች በየጊዜው እንዲለዋወጡ ያደርጋል፡፡

⏹የሥራ ፍጥነት እና ሂደትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ጋሬጣ ይፈጥራል፡፡


🔰አማራጭ ቁሶችን መጠቀም

⏺በህንፃ ግንባታ ህንፃው ለወደፊት የሚሰጠውን አገልግሎት ከግምት በማስገባት ረሳይክልድ የሆኑ ብረቶችን ከጂፕሰም እና ከጣውላ የሚዘጋጀ የውስጥ ማከፋፈያ ግርግዳዎችን መጠቀም፣ ተገጣማሚ ብሎኬቶች እና ግርግዳዎችን መጠቀም የህንፃው የግንባታ ዋጋ እንዲቀነስ ያደርጋሉ::

🔰የግንባታ ባለሙያዎች ወጪን መቀነስ

⏺የግንባታ ሂደትን በጊዜ ሰሌዳ ሸንሽኖ አስፈላጊውን ቁስ ቀደም ብሎ በማሟላት፣ ለግንባታው የሚያስፈልገውን ባለሙያ በጊዜው በመቅጠር ግንባታ የሚያስፈልግ የጉልበት (የሙያ) ክፍያ ወጪን በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ ይረዳል::

🔰ጊዜ እና ገንዘብን መቆጠብ

⏺ለግንባታ የሚያስፈልጉ እና ሥራን የሚያቀላጥፉ እንደ ሎደር፣ ኤክስካቫተር፣ ፓሌት (የብረት ምንጣፍ) የኮንክሪት ምንጣፍ ተሻካሚ፣ ተገጣጣሚ ብረቶችን፣ ግንባታው ሳይቋረጥ በሚፈለግበት ጊዜ ወዲያው የሚቀርቡበትን ቀደም ያለ ዝግጅት ማድረግ ለግንባታ የሚያስፈልግ ጊዜ በመቆጠብ፣ በፍጥነት ወደሚፈለገው ትርፋማ ጉዞ ለማምራት በተዛማጅነትም ወጪን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

▶️ብርሃን የሚያስገቡ መስታወቶችን እና የፀሀይ ብርሃንን ወደ ኤሌክትሪክ የሚለውጡ ግርግዳዎችን ማካተት፣ ህንፃው ከተጠናቀቀ በኃላ ዘላቂ የኃይል ፍጆታ (ገንዘብ) እንዲቆጠብ ያደርጋል

🎲ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

📜ለ ስራ እና ጨረታዎች ምንለቅበት ቻናል ለመቀላቀል👉 @ETCONpWORK

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp
👍15👏2❤1😁1
👉Did you know that the distribution of soil pressure varies with time and also depends on the type of soil as well as the stiffness of the base and the structure.

💫However, it is quite important to note that adequate depth of footing helps to regulate the movement of foundation as a result of seasonal changes.

@etconp
🙏7
👉'ሴት ባክ' የተባለው አነጋጋሪ የግንባታ መመርያ ከኮሪደር ልማት ውጪ ባሉ ዋና ዋና መንገዶች እና በንዑስ ዋና መንገዶች ላይ ጭምር ተግባራዊ ይደረጋል ተባለ

🏷ከሶስት ሳምንት በፊት በወጣው መመርያ መሰረት ህንፃዎች ከመንገድ መራቅ ያለባቸው ርቀት (ወይም set back)፣ የመሬት ስፋት እና ዝቅተኛው ገደብ እና የህንፃ የጎን ስፋት (ወይም frontage) መወሰኑን ዘግበን ነበር።

▶️በወቅቱ በሰራነው ዘገባችን በሴት ባክ ህጉ መሰረት ከ15 ሜትር እና በላይ ስፋት ያላቸው መንገዶች የሚያዋስኗቸው ይዞታዎች ዝቅተኛው የቦታ ስፋት ሴት ባክ ከተቀነሰ በኋላ ቢያንስ 500 ሜትር ካሬ መሆን እንዳለበት መደንገጉን ገልፀን ነበር።

⏺በተጨማሪም በነዚህ መንገዶች ላይ ዝቅተኛው የህንፃ የጎን ስፋት ከ20 ሜትር ያላነሰ መሆን እንዳለት ህጉ እንደሚጠቅስ መረጃ አቅርበን በዚህም ምክንያት በርካታ የህንፃ ኮንስትራክሽን ስራዎች ከተማው ውስጥ እንደቆሙ ጠቁመን ነበር።

ይህ መስከረም 3 ቀን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለሳጣን የወጣ የአተገባበር መመርያ ለአስራ አንዱም ክ/ከተሞች ተልኮ የነበረ ቢሆንም አሁን ደግሞ አዲስ ማሻሻያ እንደተደረገበት ሰምተናል።

⏺በዚህም መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላን እና ልማት ቢሮ አዲስ በፃፈው ደብዳቤ የኮሪደር ልማቱ ለ5 አመት የተያዘ እቅድ መሆኑን በመግለፅ ከ15 ሜትር እና በላይ ስፋት ያላቸው መንገዶች የሚያዋስኗቸው ይዞታዎች ዝቅተኛው የቦታ ስፋት ሴት ባክ ከተቀነሰ በኋላ ቢያንስ 500 ሜትር ካሬ መሆን እንዳለበት የሚደነግገው መመርያ ከኮሪደር ልማት ውጪ ባሉ ዋና ዋና መንገዶች እና በንዑስ ዋና መንገዶች ላይ ለሚገኙ ይዞታዎች ጭምር የሚመለከታቸው መሆኑን ገልጿል።

⭐️በተጨማሪም ከኮሪደር ውጪ ከሰብሳቢ መንገድ እና ከውስጥ ለውስጥ መንገዶች ጋር የሚዋሰኑ ይዞታዎች ግንባታቸውን በተመለከተ የተሻሻለውን የሴት ባክ ህግ መጠበቅ እንዳለባቸው ጠቅሶ 500 ካሬ ሜትር አነስተኛ የይዞታ ስፋት ውሳኔ እና 20 ሜትር የመንገድ ፊት ለፊት ገፅታ አስገዳጅ የማይሆን መሆኑን አብራርቷል።

Via meseret

@etconp
👍16❤1🔥1
👉አስቸኳይ ማስታወቂያ ለ ኮንስትራክሽን ማህበራት

🏷የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በተለያዩ ጊዜያት ባከናወናቸው በርካታ የግንባታ ስራዎች ላይ በመሳተፍ የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገባችሁና ስማችሁ የተያያዘ ማሕበራት በቀጣይ በተለያዩ ሳይቶች በሚከናወኑ አስቸኳይ የቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ዕድሳት ስራዎች ላይ ለማሳተፍ በነገው ዕለት ማለትም ዓርብ ጥቅምት 15/2017 ዓ/ም የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት ይካሄዳል።

⭐️ስለሆነም ስማችሁ የተዘረዘረ ማሕበራት ተወካዮች ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ በ1:00 ሰዓት መገናኛ በሚገኘው የካ ክፍለከተማ አስተዳደር ትልቁ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ ጥብቅ ጥሪ ተላልፏል።

⚡️ማሳሰቢያ-በተጠቀሰው ቀን፣ቦታ እና ሰዓት በማይገኝ ማሕበር ላይ ቢሮው ኃላፊነቱን አይወስድም!!!!

💥መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ ሼር ያድርጉ

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ

@etconp
👏8❤5👍3
👉የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች የጊዜና የዋጋ መገመቻ ማንዋልና ሶፍትዌር ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሂዷል

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን  የግንባታ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ እንዲሁም  በተገቢ ዋጋ ተፈጻሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ሀገር አቀፍ አሰራርን ለመዘርጋት አልሞ እየሰራ ይገኛል።

በዚሁ መሰረትም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሲያስጠናው የነበረው የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች የጊዜና የዋጋ መገመቻ ማንዋልና ሶፍትዌር ተቋሙ ሲያስጠና ቆይቷል ፡፡ 

በጥናቱ ረቂቅ ሰነድ ላይ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት ጥቅምት 14/2017ዓ.ም ምክክር ተካሂዶበታል።

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የሆኑት ተስፋሁን ንጋቱ እና በጋሻው ወርቁ በቀረበው የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች የዋጋና የጊዜ መገመቻ ረቂቅ ሰነድ ላይ መካተት ስላሉባቸው ሳይንሳዊ፣ ቴክኖሎጂያዊ እና ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ግብረ መልሶች ቀርበዋል፡፡

አሁን ላይ ያለውን የግንባታ ፕሮጀክቶች የዋጋና የጊዜ ግመታ አሰራር ክፍቶችን በአግባቡ የመለየት፣ የማንዋሉና የሶፍትዌሩ ዝርዝር እና ጥቅል ይዘቶችን ግልፅ የማድረግ እና በአተገባበር ሂደት ላይ የተሳታፊ አካላትን ሃላፊነትና ሚና የማሳየት ጉዳዮች መካተት እንዳለባቸው ተሳታፊዎች ሙያዊ ግብረ መልስ ሰጥተዋል፡፡

እንዲሁም ማንዋሉና ሶፍትዌሩ ከግንባታ መረጃ ማናጅመንት/ BIM / ጋር የሚናበብ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ትኩረት እንዲሰጥ፣ በቀጣይም ወደ ትግበራ ከመገባቱ አስቀድሞ በተመረጡ ፕሮጀክቶች ላይ የማሳያ ትግበራ እንዲካሄድም ግብረ መልስ ተሰጥቷል፡፡

የጥናት ሰነድ አቅራቢዉ ተስፋሁን ንጋቱ በተሰጡ ግብረ መልሶች ላይ ምሁራዊና ሳይንሳዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በቀጣይም የጥናት ረቂቅ ሰነዶቹ በፍጥነት ዳብረው ለትግበራ እንደሚዘጋጁም ገልፀዋል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ ረቂቅ ሰነዶቹ ማለፍ የሚገቧቸውን ሂደቶችና ደረጃዎች እንዲያልፉ ጥረት እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡

በዋናነትም ለጥናቱ ግብአት የሚዉሉ የመረጃ አሰባሰብ ላይ ትኩረት እንዲደረግ አስገንዝበዋል፡፡

የጥናት ሰነዶቹ ሲገባደዱ ከትግበራ አስቀድሞ የሙከራ ትግበራ እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ደረጃዎችን ያልፋል ያሉት ኢ/ር መስፍን ነገዎ የወደፊት አሰራሩ በቀጣይ ትግበራ እያደረገ እንደሚሄድ ገልፀዋል፡፡ 

Via ኢኮባ

@etconp
👍14👏6
👉Foundation Waterproofing

🏷Protecting Your Building from Moisture Damage

💫Foundation waterproofing is a critical aspect of construction that protects buildings from water infiltration and moisture damage.

⏺It involves the application of materials and systems designed to keep water from penetrating the foundation, which is vital for preserving the structural integrity of any building.

▶️Why Foundation Waterproofing Matters

🔰Water is one of the most destructive forces that can affect a building.

⏺When water seeps into a foundation, it can cause serious issues such as:

🏷Cracks in walls and floors
Mold growth Structural weakening Damage to interiors and finishes These problems are not only costly to repair but can also pose health risks to occupants due to mold and mildew.

⏺Proper waterproofing prevents these issues, ensuring the building remains durable and safe over the long term.

🌟Types of Waterproofing Systems

⏺Several methods are used to waterproof foundations, including:

🎲Membrane Waterproofing

⏺This involves applying a waterproof membrane (such as liquid-applied or sheet membranes) to the exterior or interior of the foundation to create a barrier against moisture.

🎲Cementitious Waterproofing

⏺Often used for internal foundation walls, this method involves coating the surface with a cement-based material that prevents water penetration.

🎲Bentonite Clay

⏺A natural waterproofing method using bentonite clay sheets or powder, which swells when in contact with water, sealing off any gaps or cracks.

🎲Drainage Systems

⏺These include the installation of French drains or sump pumps that help divert water away from the foundation, reducing hydrostatic pressure and minimizing moisture buildup.

💫Best Practices for Effective Foundation Waterproofing
To ensure a building's foundation remains waterproofed, it is important to follow certain best practices:

⚡️Prepare the surface: Clean and smooth out foundation walls before applying any waterproofing materials.

⚡️Proper drainage: Install an efficient drainage system to redirect water away from the foundation.

⚡️Regular maintenance: Inspect the foundation periodically to check for any cracks or signs of moisture and address them immediately.

📜Conclusion

⏺Foundation waterproofing is essential for protecting your building from moisture damage. By using the right materials and systems, you can prevent costly repairs, maintain the building’s structural integrity, and create a healthy living environment. Proper waterproofing from the start is a wise investment for long-term durability.

@etconp
👍10❤2🔥1
👉Cause Of cracking

💫Many construction professionals think that cracking is only caused by incorrect mix design, but we have explored the causes of cracking below👇

⭐️[1] - If we use low quality materials

If we use low-quality materials, cracking will occur, so we must check the quality of the materials we use for concrete (cement, sand, concrete). If the concrete has a steel structure, we must evaluate the quality of the steel.

⭐️[2] - Shrinkage

If we do not take proper care when mixing and watering the concrete, shrinkage will cause cracking.

Shrinkage is very important for high concrete strength. If we do not use the required water-cement ratio, shrinkage cracking can occur.

⭐️[3] - If we do not use quality Aggregate

Aggregate determines the overall strength of concrete. If we use aggregate that is not good quality, our construction may crack because it does not create the desired bond with cement.

⭐️[4] - When our structure handles excessive weight

Cracking occurs if the structure is subjected to a large load before it has attained adequate strength. In addition, if the stirrups and the arch (formwork) are raised prematurely, it will expose our construction to cracks.

⭐️[5] - Improper curing

This is one of the main causes of cracking in our country - improper watering.
As soon as the concrete is set, it should be watered at the appropriate time and rate.

⭐️[6] - Inequality of stress distribution

When we fill a very large steel structure with a small mix ratio of concrete, the stress distribution between the steel and the concrete becomes non-linear, which causes cracking.

⭐️[7] - If proper care is not taken when casting on site and if a suitable professional (including day laborer) is not assigned to the job, cracking is likely to occur in the concrete.

@etconp
👍9👏5🙏2
Intercon Construction Chemicals 
    
👉 Authorized agent of MC (Conmix), Weber and SIMENTEK

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍2
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ መቁረጫ መብሻና  ማጠፊያ ማሽኖች አሉን

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ እናበጃለን እንዲሁም እናጥፋለን

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍2
👉Mix design can be divided into following two categories

💫1. Design mix concrete

💫2. Nominal mix concrete.

🏷1. DESIGN MIX CONCRETE:

⭐️When the proportions of concrete ingredients are decided by adopting certain established relationships (based on assumptions from a lot of experiments) to produce the concrete it is known as design mix concrete.

⏺In design mix concrete, it is assumed that compressive strength of concrete is totally
dependent on the water- cement ratio.

🏷2. NOMINAL MIX CONCRETE:

⭐️When the concrete is produced by taking standard arbitrary proportions of concrete ingredients, it is known as nominal mix concrete.

▶️This method is generally used when the quality control requirement for design mixes are difficult to execute.

⏺As we have explained for normal work, nominal mix concrete can be designed by taking cement, fine aggregate and coarse aggregate in
the ratio of 1 : n : 2n

🎲ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

📜ለ ስራ እና ጨረታዎች ምንለቅበት ቻናል ለመቀላቀል👉 @ETCONpWORK

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp
👍11🕊1
👉የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የባለድርሻ አካላት ውይይት በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።

በአማራ ክልል የከተሞች እና መሠረተ ልማት ቢሮ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የባለድርሻ አካላት ውይይት በባሕር ዳር ተጀምሯል።

በውይይቱ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተሞች እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አህመዲን መሐመድን (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና የዘርፉ አጋር አካላት ተገኝተዋል።

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ቁጥጥር እና ትግበራ፤ አጠቃላይ የፕሮጀክት አፈጻጸም ግምገማ እና በፕሮጀክት አተገባበር ሂደት ላይ የሚስተዋሉ የአፈጻጸም ጉድለቶች የውይይቱ ዋና ዋና አጀንዳዎች ናቸው ተብሏል።

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ያሉባቸውን ችግሮች በመፍታት አፈጻጸማቸውን በሚያሻሽሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል።

Via አሚኮ

@etconp
👍6
👉ኖህ ሪል ስቴት ከ750 በላይ የመኖሪያ አፓርታማዎችን እና የንግድ ቤቶችን ዛሬ አስረከበ።

ኖህ ሪል ስቴት ከ750 በላይ የመኖሪያ አፓርታማዎችን እና የንግድ ቤቶችን ዛሬ ጥቅምት 16/2015 ዓ.ም አስረከበ።

ሰሚት አከባቢ የተገነባው "ኖህ ኤርፖርት ድራይቭ ሳይት" የተሰኘ ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ለቤት ባለቤቶች የተላለፉት መኖሪያ ቤቶች ከ75 ካሬ አስከ 128 ካሬ ስፋት ያላቸው መሆናቸው በቤት ማስረከቢያ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

ቤቶቹ ከባለ 2 እስከ ባለ 3 መኝታ ክፍሎች ያሏቸው 750 በላይ አፓርታማ የመኖሪያ ቤቶች፣ 32 በላይ ቪላ ቤቶች እና 45 የንግድ ሱቆች ናቸው።

ኖህ ሪልስቴት ዛሬ ያስረከባቸው መኖሪያ ቤቶች መዋኛ ገንዳ፣ የከርሰ ምድር ውሃ እንዲሁም የስፖርት ማዘወተሪያ ያካተቱ መሆናቸው ተጠቅሷል።

የኖህ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ አዋሽ ኖህ ሪል ስቴት ስፋት የመኖሪያ አፓርታማዎችን በጊዜ እና በጥራት በመገንባትና በማጠናቀቅ ኩባንያው የደንበኞቹን እምነት ያተረፈ ኩባንያ ነው ብለዋል።

ኩባንያው በቅርቡ በእንቁላል ፋብሪካ "ኖህ አስኳልን" 750 በላይ መኖሪያ ቤቶችን በአዋሬ ሴቶች አደባባይ "ኖህ ቪክትሪ ሳይት" 152 ቤቶችን ለቤት ባለቤቶች እንደሚያስረክብ ጠቅሷል።

የድርጅቱ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ዘሪሁን በበኩላቸው "አዲስ አበባን ውበት በሚመጥን መልኩ እስከ 2020 ዓ.ም አብዛኛውን የከተማችን ነዋሪዎች ተደራሽ የሚያደርጉና ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው ቤቶች ገንብቶ ለማስረከብ እየሰራን እንገኛለን" ብለዋል።

በቀጣይ ወር በቦሌ ሆምስ በሚባለው አካባቢ ከ5,000 በላይ የሚሆኑ ቤቶችን ግንባታ እንደሚያስጀምሩ ተናግሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ባደረጉት ንግግር በከተማችን ከፍተኛ የሆነ የቤት ፍላጎት አለ ይህ በመንግስት ብቻ ሊሸፈን አይችልም የግል ቤት አልሚዎችን በመደገፍ ለነዋሪው ቤት ፍላጎት መሸፈን አስፈላጊ ነው፣ ዛሬ የተመረቀው የኖህ ሳይት ለከተማችን ቤት ብቻ ሳይሆን ውበትም የሚጨምሩ ናቸው ብለዋል።

ኖህ ሪል ስቴት ባለፉት አስርት ዓመታት በ33 ሳይቶች ከ9,800 በላይ የመኖሪያ ቤቶችን፣ የንግድ ማዕከላትን ከ25,000 በላይ ለሚሆኑ ቤት ፈለጊዎች ገንብቶ አስረክቧል።

@etconp
👍17🕊1