Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.3K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉መንግሥት በራሱና በውጭ ተቋራጮች ግንባታዎችን በመቆጣጠሩ የግል ሥራ ተቋራጮች ከሥራ ውጪ መሆናቸውን አስታወቁ!

መንግሥት የመንገድና የሕንፃ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የራሱን የግንባታና የዲዛይን ድርጅቶች በማቋቋም፣ ፕሮጀክቶችን መያዙና የተቀረውን ለውጭ አገር የሥራ ተቋራጮች እየተሰጠ መሆኑ፣ የአገር ውስጥ የግል የሥራ ተቋራጮች ከሥራ ውጪ መሆናቸውን አስታወቁ።

ይህ የተገለጸው የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከግሉ የግንባታ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ባለፈው ሳምንት ባደረገው የምክክር ጉባዔ ላይ ነው።

ሚኒስቴሩ የአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች በአሥር ዓመታት ውስጥ በአገር ውስጥ ያላቸውን የገበያ ድርሻ ወደ 75 በመቶ፣ በቀጣናው ደግሞ የ25 በመቶ ድርሻ እንዲያሳድጉ ዕቅድ ቢይዝም፣ የሥራ ተቋራጮች በበኩላቸው መንግሥት በውጭ ተቋራጮች ላይ ያለውን ከፍተኛ ጥገኝነት፣ የክፍያዎች መዘግየት፣ በቅርብ የተካሄደው የኢኮኖሚክ ሪፎርም በኢንዱስትሪው ላይ ያሳደረውን ጫናና ሌሎችም ማነቆዎችን በማንሳት፣ መንግሥት በእርግጥ ኢንዱስትሪውን ያውቀዋል ወይ? የሚል ጥያቄ አንስተዋል።

አቶ ሀብታሙ ጌታቸው የተባሉ ተሳታፊ፣ መንግሥት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢንዱስትሪውን በብቸኝነት ወደ መቆጣጠር እያመራ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

‹‹ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያው ከመሰላቸትምም ተነስቶ ሊሆን ይችላል፣ ግን በመንግሥት በኩል ኢንዱስትሪውን በብቸኝነት የመያዝ ሒደት ነው እያየን ያለነው። መንግሥት የራሱን የዲዛይን፣ የኮንስትራክሽን ተቋማት እያደራጀና እያዘጋጀ ነው። ስለዚህ ፕሮጀክት ሲመጣ ራሱ ዲዛይን ያደርጋል፣ ራሱ ግንባታ ይፈጽማል፣ በጣም ከእሱ አቅም በላይ የሆነውን ለውጭ ኩባንያዎች ይሰጣል። ስለዚህ ለግሉ ዘርፍ ቦታው ባዶ ነው ብዬ ነው የምገምተው፤›› ብለዋል።

በሌላ በኩል በምክክር መድረኩ የቀረቡ ሁለት ጥናቶች፣ በአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች የሚገነቡ መንገዶች በ143 በመቶ፣ ሕንፃዎች ደግሞ በ110 በመቶ ከተያዘላቸው ጊዜ አሳልፈው እንደሚጠናቀቁ፣ ከተያዘላቸው በጀትም እንዲሁ የመንገድ ፕሮጀክቶች በ18 በመቶ፣ ሕንፃዎች ደግሞ በ35 በመቶ እንደሚያሳልፉ አመላክተዋል።

ከሚኒስቴሩ በኩል ጥናት ያቀረቡት ባለሙያ፣ ‹‹ከዚህ ጥናት በኋላ በፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በተደረጉ የፕሮጀክቶች ክትትል በብዙ ፕሮጀክቶች እያንዳንዱ እየተነጠለ ሲታይ የጭማሪዎቹ መጠን ከዚህም በላይ እንደሆነ ማየት ተችሏል፤›› ብለዋል።

ሳሙኤል ሳህለ ማርያም (ኢንጂነር) የተባሉ ጥናት አቅራቢ በበኩላቸው፣ የውጭ ኮንትራክተሮች የሚይዙት ግንባታ መጠን አነስተኛ ሆኖ፣ ነገር ግን የሚይዙት የገበያ ድርሻ እስከ 62 በመቶ እንደሚደርስ አሳውቀዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ያሉ ሥጋቶች ላይ ማብራሪያ ሲሰጡ፣ ‹‹የግንባታ ዘርፉ አሁንም ትልልቅ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ትልቁን ድርሻ የያዙት የውጭ ሥራ ተቋራጮች ናቸው። ይህንን ልንቀይርበት የምንችልበት አካሄድ እስካልተፈጠረ ድረስ አሁን በቅርብ ይህ ንግድ ለዓለም የንግድ ድርጅት ክፍት ነው የሚሆ ነው።

ስለዚህ እኛ ምን ይዘን ነው የምንቀላቀለው? ምን ይዘን ነው ለውድድር ልንቀርብ የምንችለው? በዚህ ሁኔታ ከሆነ የምንቆየው ሁላችንም ተበልተን ነው የምናልቀው፤›› ብለዋል።

በሚኒስቴሩ በኩል የቀረቡት ባለሙያ የውጭ ተቋራጮች ጉዳይ እስከ ሉዓላዊነት የደረሰ ችግር ሊያስከትል ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ ያሉት የአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮችና አማካሪ ኩባንያዎች 35 ሺሕ መድረሳቸውን፣ የባለሙያዎች ብዛትም 151 ሺሕ መሆኑን ጠቅሰዋል።

‹‹በቁጥር ይግዘፍ እንጂ በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ የመንግሥት ሜጋ ፕሮጀክቶች በብዛት የተያዙት በሚያሳዝን ሁኔታ በውጭ ኮንትራክተሮች ነው። መጀመሪያ የአገራችንን 75 በመቶ ይዘን የቀጣናውን 25 በመቶ ገበያ ለመያዝ ነው ዕቅዳችን። እነዚህ ቁጥሮች ሳይሆኑ እኛን የሚታደጉን ሄዶ ሄዶ ጉዳዩ የሉዓላዊነት ጉዳይ ጋር ይመጣል፤›› ብለዋል።
ሳሙኤል (ኢንጂነር) የውጭ አገር የሥራ ተቋራጮች ከዚህም ባሻገር ከበጀት ጋር የተያያዙ ጫናዎች እየፈጠሩ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

‹‹አንድ በውጭ ተቋራጭ የሚሠራ በጀቱ 800 ሚሊዮን ብር የነበረ ፕሮጀክት፣ ግንባታውን በመሀል አቁመው 3.2 ቢሊዮን ብር ካልከፈላችሁን አንሠራም ማለታቸውን እናውቃለን። ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚሠራው ስታዲየምን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጀመር በጀቱ ከሁለት ቢለዮን ብር ጥቂት ነበር ከፍ የሚለው። ግን በኋላ ላይ እስከ 12 ቢሊዮን ብር አይበቃም ማለታቸውን ሰምተናል፤›› ብለዋል።

ባለሙያው ይህ ዓይነቱ አሠራር ለአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች እንደማይሠራ ገልጸው፣ ኩባንያዎች፣ ከባንኮች ከግንባታ ዕቃ አቅራቢዎች ጋር ተያይዞ ሊሠራበት የሚችልበት ሁኔታ እንደሌለ ገልጸዋል።

የውጭና የአገር ውስጥ ተቋራጮች አፈጻጸምን በተመለከተ ለአብነት የቻይና ተቋራጮችን አፈጻጸም ያነሲ ሲሆን፣ ፕሮጀክቶችን በሚያገኙበት ወቅት ዕቃ አቅራቢ ፋብሪካ አዘጋጅተው፣ አማካሪ ኩባንያው የራሳቸው አገሮች ኩባንያ መሆኑንና ንዑስ ተቋራጮችም በራሳቸው እንደሚያዘጋጁ ጠቅሰው፣ የቻይና ኤግዚም ባንክ እዚህ ለሚሠሩ ሥራ ተቋራጮች የገንዘብ ፍሰት (Cash Flow) ችግር እንዳያጋጥማቸው እንደሚያቀርብላቸውና በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ የሚያልፍ የውጭ ተቋራጭ በተገቢው ሁኔታ ሥራውን አከናወነ እንደሚባል ተናግረዋል።

‹‹የእኛ ሥራ ተቋራጭ እኮ በክፍያ ምክንያት የሚያጋጥመው ጫና ምናልባት መንግሥትና ዘርፉ የእውነት ይተዋወቃሉ?› የሚል ጥያቄ እንዳነሳ ነው የሚያደርገኝ። የእውነት ይተዋወቃሉ ወይ? ዘርፉ እኮ እየሞተ ነው ያለው። ክፍያ በአግባቡ ካልተከፈለው የፕሮጀክት ቆይታ በከፍተኛ ሁኔታ ነው እየጨመረ የሚመጣው። ስለዚህ ይህንን ክፍተት መሙላት የሚያስችል የፋይናንስ ሲስተም ያስፈልጋል፤›› ብለዋል።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ የትምጌታ አሥራት በበኩላቸው፣ መንግሥት ፕሮጀክቶችን ለአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች ለማስተላለፍ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በውይይት መድረኩ ከተነሱ ዋነኛ ጉዳዩች የውጭ ምንዛሪ ላይ የተደረገው ሪፎርም በኢንዱስትሪው ላይ ሌላ ጫና ይገኝበታል።

‹‹የኢንዱስትሪው ገበያ የሚንቀሳቀሰው በጥቁር ገበያው ነበር፡፡ እዚህ ላይ ምንም ልንወሻሽ የሚገባ ነገር የለም። ለምን አንድ አቅራቢ ዕቃ ከውጭ አምጥቶ ለመሸጥ ለሒደት ማስፈጸሚያ (Procedure Issue) ብቻ የባንክን ምጣኔ ይጠቀማል። ለምሳሌ 60 ብር በነበረበት ሰዓት ለፕሮሲጀር የባንክን ይጠቀማል፡፡ ሌላውን ግን በጥቁር ገበያ ሴኪውር ያደርጋል። ከዚያ በኋላ ግን ዋጋ ሲያወጣ በጥቁር ገበያው ምጣኔ ነው የሚያወጣው፡፡ በዚህ ምክንያት የፕሮጀክት ዋጋ ከፍ ይላል፤›› ብለዋል።


በተጨማሪም፣ ‹‹ምንዛሪ በገበያው መወሰን ሲጀምር በፊት ግብር የሚከፍል የነበረው ባንክ በሰጠው ምጣኔ ነበር። ለምሳሌ ምንዛሪው ሰባት ብር ከነበረ፣ አሁን ግን 125 ሲሆን ግብሩም በዚያው መጠን ከፍ ይላል ምክንያቱም በደረሰኝ ገንዘቡን ዝቅ አያደርግም። እንደነዚህ ዓይነት ዕርምጃዎችን እንዳይሄድና ኃላፊነት እንዲወስድ ብሔራዊ ባንክ አስገዳጅ መመርያ አውጥቶበታል። ያንን ስናይ ደግሞ ከኢንሹራንስና ከትራንስፖርት ጋርና ከሌሎች ሎጂስቲክስ ጉዳዮች ጋር የተገናኙ የወጪ ክፍያዎች አሉበት። ስለዚህ በኢኮኖሚክ ሪፎርሙ የኮንስትራክሽን ዘርፉ አሁንም እንደገና ደግሞ ሌላ ተጋላጭነት አጋጥሞታል፤›› ሲሉ አብራርተዋል።

@etconp
👍12💔2
👉ጥቂት ስለ መሬት መንቀጥቀጥ እና የሕንጻ መዋቅር ዲዛይን

የመሬት መንቀጥቀጥ ከመሬት የውስጠኛው ክፍል በድንገት በሚለቀቅ 'ኢነርጂ' ምክንያት የላይኛው የመሬት ክፍል ላይ በሞገዶች (seismic waves) አማካኝነት የሚተላለፍ ንዝረት ወይም መንቀጥቀጥ ነው።

ለመሬት መንቀጥቀጥ በተጋለጡ አካባቢዎች ያሉ ሕንፃዎች የመሬት መንቀጥቀጥ በሚከሰትበት ጊዜ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እና ነዋሪዎችን ለመጠበቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ኃይሎችን እንዲቋቋሙ ሆነው የተነደፉ መሆን አለባቸው። ይህ የመሬት መንቀጥቀጥን የሚቋቋም ንድፍ earthquake-resistant design (ERD) በመባል የሚታወቅ ሲሆን ይህንንም ለመስራት ልዩ የምህንድስና ትምህርት እና ልምዶችን ይፈልጋል።

በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት መሬቱ በምን ያህል ፍጥነት እንደሚንቀጠቀጥ የሚለካበት በ PGA(Peak Ground Acceleration) መንገድ ነው።

ይህ ለዲዛይን ዋናው መሰረት ነው ፤ እርሱም ከፍተኛውን የመንቀጥቀጥ ፍጥነት ከመሬት የስበት ኃይል (9.81 m/s²) ጋር አዛምዶ ያሳየናል።

ከፍ ያለ PGA ማለት ጠንካራ መንቀጥቀጥ እና የበለጠ ጉዳት ሊያስከስት የሚችል  ማለት ነው።

PGA ከ0.1%g ያነሰ ከሆነ ላናስተውለው እንችላለን ፤ ከ 0.1-1% g ከሆነ ምንም ጉዳት ሳያስከትል በትንሽ እናስተውለዋለን ፤ ከ1-3% g ቀላልና አነስተኛ ፤ ከ3-10% መካከለኛና ትንሽ ጉዳት ፤ ከ10-30% በጣም ጠንካራ የመዋቅራዊ ስንጥቆች (Very strong, structural cracks )፤ከ30-50% ከባድና ከፍተኛ ጉዳት፤ ከ50-100% ኃይለኛና የሕንፃዎች መፈራረስ ፤ ከ100% g በላይ ከሆነ ደግሞ እጅግ በጣም ከባድና  አጠቃላይ ጥፋትን ያስከትላል።

የኢትዮጵያ የሕንፃ ኮድ ኢትዮጵያ ለመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭ የሆነ አካባቢ እንዳላት በግልጽ ያስቀምጣል።

ለመሬት መንቀጥቀጡ እንዳላቸው ተጋላጭነት ቦታዎቹን አዲሱ የ2015ቱ ኮድ( EBCS EN: 2015) Zone 0, Zone 1, Zone 2, Zone 3, Zone 4 እና Zone 5 በማለት በ6 ምድቦች አስቀምጧቸዋል።

በነገራችን ላይ ይህ ኮድ በጣም የተሻለ ቢሆንም እንኳን በባለሙያዎች ዘንድ በቂ ግንዛቤና ይሁንታን ሳያገኝ እና በበቂ ሁኔታ ተግባራዊ ሳይሆን አዲሱ ኮድ እንደተባለ ይኸው አስር አመት ሞላው ፤ በኮዱ አጠቃቀም ዙርያ በሥራ ላይ ያጋጠሙ ችግሮችንና ያሁኑን ክስተት ከግምት ወስጥ በማስገባት በፍጥነት መከለስ (ክለሳው መጠናቀቅ) ይኖርበታል።

በአዲስ አበባ ያሉ ሕንጻዎች አሁን ባለው የሕንጻ ኮድ (EBCS EN-1998-1:2015)መስፈርት መሰረት ለ 0.1g (ማለትም 10% g) PGA የተሠሩ እና ሊሠሩ የሚገባቸው ናቸው።

የቀድሞው ኮድ እንኳን (EBCS 8 1995) በአዲስ አበባ ለሚሰሩ ሕንጻዎች ከ 5% g እስከ 7% g PGA ታሳቢ ተደርገው እንዲሰሩ ያዛል።

በዚህም መሰረት እስካሁን ባለው ሁኔታ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀት ጥንካሬ (ማለትም 1% g) በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉት በበቂ ባለሙያ እና ኮዱን ተከትለው የተሠሩ ሕንጻዎች ላይ ጉዳት ለማድረስ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀት በጣም ትንሽ ነው።

ነገር ግን፣ ከመሬት መንቀጥቀጡ በተወሰኑ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለው አካባቢ፣ 10% g የመሬት መንቀጥቀጥ በሚገመትበት ቦታ ላይ ጉዳት ሊደርስ ይችላል።

ይህ ማለት ግን ስጋቱ የለም ማለት አይደለም ፤ የመሬት መንቀጥቀጡ እየጨመረበት ያለበት ሁኔታ እና ከዚህ ቀደም በ1961 ካራቆሬ ላይ በሬክተር ስኬል 6.5 ተከስቶ የሰዎች ሕይወት እንዳለፈ ሲታሰብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያሰፈልግ እንረዳለን ።

⭐️ሊደረጉ የሚገባ ጥንቃቄዎች

▶️ተደጋጋሚ እና ጥልቅ የባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው አካላት የቀጥታ ውይይትና ገለጻ ችግሩ እስኪቀረፍ ድረስ በቋሚነት በሁሉም የመንግስት እና የግል መገናኛ ተቋማት ያስፈልጋል። ጉዳዩ በመግለጫ ብቻ የሚታለፍ አይደለም ።

▶️አደጋ ቢከሰት ስለሚደረጉ ጥንቃቄዎች ቀድሞ  ማስተማር እና ማዘጋጀት

▶️ያረጁ ሕንፃዎች - በዲዛይን ጊዜ የሚታሰበው የሕንጻዎቹ የአገልግሎት ዘመን  ያበቃ (ከ50 ዓመት በላይ የሆናቸው)ያረጁ ሕንፃዎች በብዙ ምክንያት ለዚህ አደጋ የተጋለጡ ናቸው።

▶️በዘመን ብዛት በ Creep effect እና fatigue ምክንያት የኮንክሪት ስትራክቸር ጥንካሬ ይቀንሳል።

🔰በንጉሡ ጊዜ ተሠርተው አሁንም አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ሕዝብ መገልገያ ሕንጻዎች ማለትም ትምህርት ቤት ፤ የህክምን ተቋማትና ሌሎችም።

📜እነዚህ የማጠናከርያ ሥራ (Retrofitting) ይፈልጋሉ ።

⏺በድንጋይ ግንብ (Masonry) ብቻ እና መሰል የአርማታ ብረት የሌላቸው ግንባታዎች።

⏺ተገቢውን የአፈር ጥናት፣ ዲዛይን እና ክትትል ሳይደረግላቸው የተገነቡ ግንባታዎች ለአደጋ ተጋላጭ ናቸው።

⏺በሚገባው ባለሙያ ዲዛይን ያልተደረጉ እና ያልተገነቡ ግንባታዎች ለዚህ ተጋላጭ ናቸው።

⏺ከተገነቡ በኋላ በተለይ ግርግዳቸውና ሌሎች የሕንጻ አካላት ፍርሰው ባዶ ሲሆኑ በወለሎቹ መካከል የጥንካሬ ልዩነት  ሲከሰት (Soft stories) በሰላም ለዘመናት የኖሩትን ሕንጻ ለአደጋ እንዳርጋቸዋለን።

⏺የሕንጻ ኮድ ክለሳውን ማፋጠን

🏷መልካሙን ነገር ያሰማን🙏

Via አቶ ኤልያስ ደፋልኝ መሀንዲስ እና  አትሮንስ ኮንሰልት አማካሪ መሐንዲሶችና አርክቴክቶች ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ

@etconp
👍19❤2🔥1
👉ውድ ቤተሰቦቻችን ባለፈው እንዲሰራላቹ ምትፈልጉት ቲቶርያል ጠቁሙን ባልነው መሰረት ከ 65 በላይ መልእክቶች SAP የሚል ስለበዛ ይህ ቲቶርያል ቪድዮ እየሰራንላቹ ነው የመጀመርያ ክፍል ነገ ይለቀቃል።

🌟እስከዛ ለ YOUTUBE ቻናላችን ኣዲስ ከሆናቹ ከታች ባለው ሊንክ ገብተው SUBSCRIBE ያድርጉ እንዲሁም ለወዳጅዎ ይደርስ ዘንድ SHARE በማድረግ ያበርቱን🙏

https://youtube.com/@ethiopianconstruction?si=i3B2u9LyWBNjqAAO

@etconp
👍8
“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”
— ሉቃስ 2፥11

💫ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሰላም በጤና አደረሳቹ አደረሰን ❤️🎄🎄

@etconp
❤27👍3💔2🙏1
👉የቤተልሔም የግንባታ ታሪክ

ቤተልሔም በታሪክ ውስጥ የተዘፈቀች ከተማ፣ በኖረችበት ዘመን ሁሉ የተለያዩ የሕንፃ ስልቶችን ተመልክታለች።

የከተማዋ የግንባታ ታሪክ በእድገቷ ላይ ተፅእኖ ያላቸውን የተለያዩ ሥልጣኔዎች እና ኢምፓየሮች ያሳያል።

ቀደምት ጊዜያት፡-

* የከነዓናውያን ዘመን፡ ትክክለኛው አመጣጥ ግልጽ ባይሆንም፣ የቤተልሔም መገኘት የከነዓናውያን ዘመን ጀምሮ ነው። ቀደምት ሕንፃዎች ቀላል የጭቃ ጡብ መኖሪያ እና የእርሻ ሕንፃዎች ሊሆኑ ይችላሉ::

* የእስራኤል ዘመን፡- በእስራኤል ዘመን ቤተ ልሔም የንጉሥ ዳዊት የትውልድ ቦታ እንደሆነች ትታወቅ ነበር።

የግንባታ ቴክኒኮች እንደ ድንጋይ ያሉ ይበልጥ ዘላቂ የሆኑ ቁሳቁሶችን በመጠቀም የዳበረ ነበር።

* የሮማውያን ዘመን፡- አካባቢውን የተቆጣጠሩት ሮማውያን የሕንፃ ስልታቸውን አስተዋውቀዋል እንደ ቤተመቅደሶች እና የአስተዳደር መዋቅሮች ያሉ ህዝባዊ ሕንፃዎች የተገነቡት የሮማውያን የሥነ ሕንፃ ክፍሎችን በመጠቀም ነው።

▶️የባይዛንታይን እና የመስቀል ጦርነት ጊዜያት፡-

* የባይዛንታይን ዘመን፡ የባይዛንታይን ዘመን የልደተ ልደትን ባዚሊካን ጨምሮ አስደናቂ የሆኑ አብያተ ክርስቲያናት ሲገነቡ ተመልክቷል።

ይህ ወቅት በሥነ ሕንፃ ቴክኒኮች እና ቁሳቁሶች ውስጥ ትልቅ እድገት አሳይቷል።
* የመስቀል ጦርነት ጊዜ፡- እየሩሳሌምን እና ቤተልሔምን የያዙት የመስቀል ጦረኞች፣ ምሽጎችንና አብያተ ክርስቲያናትን በሮማንሳዊ ዘይቤ ገነቡ።
የኦቶማን ጊዜ።
* የኦቶማን አገዛዝ፡ የኦቶማን ኢምፓየር ወደ ቤተልሔም የተለየ የሕንፃ ጥበብ አመጣ።

የኦቶማን ዘመን ህንጻዎች የሚታወቁት በአካባቢው ድንጋይ፣ በሮች የተሸፈኑ እና ውስብስብ ጌጣጌጦችን በመጠቀም ነው።

🚧ዘመናዊ ጊዜ

* የብሪቲሽ ስልጣን፡ በብሪቲሽ ስልጣን ጊዜ፣ ቤተልሔም የዕድገት እና የዘመናዊነት ጊዜን አሳልፋለች።

Art Deco እና Bauhausን ጨምሮ አዳዲስ ሕንፃዎች በተለያዩ ቅይጦች ተገንብተዋል።

* ዘመናዊ ዘመን፡ ዘመናዊቷ ቤተልሔም በዝግመተ ለውጥ መምጣቷን ቀጥላለች፣ አዳዲስ ሕንፃዎች ዘመናዊ የሥነ ሕንፃ አዝማሚያዎችን የሚያንፀባርቁ ናቸው።

ነገር ግን፣ የከተማዋ ታሪካዊ እምብርት ባህላዊ ባህሪውን ይይዛል፣ ብዙ የኦቶማን ዘመን ሕንፃዎች አሁንም ቆመዋል።

⭐️የቤተልሔም ከተማ ታሪክ

የቤተልሔም ታሪክ ዓለም አቀፋዊ ጠቀሜታ ካላቸው ሃይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ ክስተቶች ጋር የተጣመረ ነው።

* መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጠቀሜታ፡- ቤተ ልሔም በጣም ዝነኛ የሆነችው ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ጋር ያላት ግንኙነት ነው።

*ከተማዋ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የንጉሥ ዳዊት የትውልድ ቦታ እንደሆነች ተጠቅሷል።

* የሮማውያን አገዛዝ፡- ሮማውያን ኢየሱስ በተወለደበት ጊዜ አካባቢውን ይቆጣጠሩ ነበር።

* የባይዛንታይን እና የመስቀል ጦርነት ጊዜዎች፡- የባይዛንታይን እና የመስቀል ጦርነት ጊዜያት ቤተልሔም የክርስቲያኖች የጉዞ ቦታ ሆና አብባ ነበር።

* የኦቶማን አገዛዝ፡- የኦቶማን ኢምፓየር ቤተልሔምን ለዘመናት በመግዛት የባህልና የሕንፃ መልከዓ ምድሩን ቀርጿል።

* የብሪቲሽ ስልጣን፡ የብሪቲሽ ማንዴት ጊዜ የቱሪዝም እድገትን ጨምሮ ከፍተኛ ለውጦችን አምጥቷል።

* የዘመናችን ዘመን: ዘመናዊቷ ቤተልሔም ከእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች ከፊቷ ተደቅነዋል፣ነገር ግን ጉልህ የሆነ የሃይማኖት እና የባህል ማዕከል ሆና ቆይታለች።

💫 ቁልፍ ታሪካዊ ቦታዎች፡-

* የልደቱ ቤተ ክርስቲያን፡ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት ያስመዘገበው ይህ ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ የትውልድ ቦታ ላይ እንደሚሠራ ይታመናል።

* ማንገር አደባባይ፡- በቤተልሔም ማእከላዊ አደባባይ፣ በልደተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ይገኛል።

* ሚልክ ግሮቶ፡- በወግ መሠረት ድንግል ማርያም ሕፃኑን ኢየሱስን የምታጠባበት በአቅራቢያው ያለ ዋሻ ነው።

የቤተልሔም ታሪክ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ጠቀሜታ ያለው ቦታ ለመሆኗ ዘላቂ ጠቀሜታዋን የሚያሳይ ነው የበለፀገው ያለፈው ታሪክ የአሁኑን እና የወደፊቱን መቀረፅ ይቀጥላል።

መልካም በዓል

Via Fila

@etconp
❤13👍12
#Advertising #ማስታወቂያ #MusaFide
Our Services Include:

💻 Civil 3D Full Tutorials (4K Video)

Tutorials with project files used throughout the video for hands-on learning.
📊 All Supporting Materials

Access materials, including PKT Files, Superelevation Excels, & ERA Manual XML, to streamline your design work.
🏗 Girder Bridge Working Drawing Preparation

Complete working drawings for Girder Bridges, including all materials used in the tutorial, & the 3D model created in SketchUp.
🚗 Highway Design Expertise

Professional highway design services
🛠 Template Production & PKT Development Template creation & PKT development as per your project standards.

📏 Earthwork & Pavement Quantity Preparation

Earthwork & pavement quantity preparation to ensure precise cost estimation.
🏗 Structural Working Drawing Preparation

Detailed structural working drawings Preparation
Connect with Us:
YouTube: http://www.youtube.com/@musfide
Telegram: https://t.me/musafide
WhatsApp: https://bit.ly/musfide
Call Us: +251 905 666 664
👍9❤2👏2
👉Cost Control Process Flow Chart

🚧Below step-by-step flowchart structure for effective cost control in project management

1️⃣ Project Budget Development

Define the total project budget, including direct and indirect costs.

2️⃣ Cost Baseline Establishment 📊

Set a baseline to track and compare actual costs.

3️⃣ Resource Allocation 🔧

Assign resources based on the budget and schedule.

4️⃣ Cost Monitoring and Tracking 🔍

Collect actual cost data regularly.

Compare actual costs with the baseline.

5️⃣ Variance Analysis 📈

Identify cost variances (overruns or savings).

Analyze the reasons for discrepancies.

6️⃣ Cost Forecasting 🔮

Predict future costs based on current trends.

Adjust estimates to reflect project changes.

7️⃣ Corrective Actions 🛠

Implement measures to control overruns ( reduce scope, optimize resources)

8️⃣ Cost Reporting 📑

Share cost performance reports with stakeholders.

Highlight key findings and financial health.

9️⃣ Continuous Improvement ♻️

Document lessons learned for better cost management in future projects.

This flow ensures project costs are managed effectively, helping to complete projects within budget while maintaining quality.

@etconp
👍21
ርዕደ መሬት በኢትዮዽያ

ሰርዶ ርዕደ መሬት

በመጋቢት 1962 ዓም 6.2 Mw እና 6.1Mw የሚለካ ሶስት ግዜ ለአንድ ሳምንት ያህል ርዕደ መሬት በአፋር ውስጥ በምትገኘው ሰርዶ ከተማ ደርሶ ነበር። ሶስቱም ርዕደቶች ከአደገኛ እስከ ከፍተኛ በሚለኩ ጉልበት ነበር የደረሱት። 24 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 165 ሰዎች ቆስለው ነበር። አደጋው የደረሰው በጭቃ በተሰሩ ቤቶች ደካማ አሰራር እንደነበር ታውቋል። 100 የጭቃ ቤቶች በሙሉ ፈርሰው ከአደጋው የተረፉት 300 ሰዎች በስተምዕራብ በ50 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደምትገኘው ወደ ሎጊያ ተሰደው ነበር። ርዕደ መሬቱ በ30 ኪሎሜትር ራዲየስ የተሰማ ነበር።

ምን ያህል ርዕደ መሬትን ለመከላከል የተዘጋጀ ዘመናዊና ባህላዊ የግንባታ ዘይቤ አለን?

የትኞቹ የኪነህንጻ የዲግሪ መርሀግብሮች "ርዕደ መሬት ከል" የንድፍ መርሆችን በስርዓተ ትምህርታቸው ውስጥ አካተዋል?

Via ethiopian architecture and urbanism

@etconp
👍15❤8
Earthquake resistant design 2017.pdf
2.5 MB
👉ርዕደ መሬት ተከላካይ ህንጻ ንድፍ

🏷በአገራችን የኪነህንጻና ስነከተማ ትምህርት ውስጥ የርዕደ መሬት መከላከያ የንድፍ መንገዶች አትኩሮት ከማይሰጥባቸው ዘርፎች አንዱ ነው።

⭐️የተያያዙትት የምስል ሰሌዳዎች በዶክተር አዲል በአዲስ አበባ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተዘጋጁ ሲሆኑ ጠቃሚ የርዕደ መሬት ተከላካይ የመዋቅር እና የኪነህንጻ ንድፍ ውሳኔዎች ን ያመላክቱናል።

💫በዶ/ር አዲል ዘ. AAiT

📜Useful Architectural and  Structural Considerations for  Earthquake Resistant
Design

By Dr Adil Z. AAiT

@etconp
🙏12👍8
👉በአማራ ክልል ፕሮጀክቶች ያለ ጨረታ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች ብቻ እየተሰጡ ነው ተባለ

በአማራ ክልል ያሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ያለ ጨረታ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች እየተሰጡ፤ የግሉ ዘርፍ ከሥራ እንዲወጣ እየተደረገ ነው ሲል የክልሉ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ገልጿል።

የአማራ ክልል ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ፕሬዝደንት አቶ ሙሉቀን ቢተው "በክልሉ የሚተገበሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶች 'ጨረታ አልወጣም' እንዳይባል ብቻ አምስት ያክል የመንግሥት ባለድርሻዎችን አሳትፈው፤ መልሰው የሚወስዱት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ናቸው" ሲሉ ለአሐዱ የገለጹ ሲሆን፤ ይህም ተግባር የግሉን ዘርፍ ይበልጥ እያዳከመው እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዚህም የተነሳ ከ6 ሺሕ በላይ ኮንትራክተሮች ችግር ውስጥ መሆናቸው በማንሳት፤ በክልሉ የሚንቀሳቀሱና በኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ የተሰማሩ አካላት ሥራቸውን መስራት እስካለመቻል የደረሱ ችግሮችን እያስተናገዱ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

"ችግሩ ከፍተኛ በመሆኑ በተለይም ያለው የሥራ ሁኔታ በቀዘቀዘበት እንዲሁም ፕሮጀክቶች ያለምንም ጨረታ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች በሚሰጥበት ሁኔታ ውስጥ ኮንትራክተሮች ከፍተኛ ችግር ላይ እየወደቁ ነው" ያሉት የማህበሩ ፕሬዝዳንት፤ በዚህም የተነሳ በርካቶች ቤታቸውን፣ ማሽኖቻቸውን፣ መኪኖቻቸውንና ሌሎች ንብረቶቻቸውን ለመሸጥ እየተገደዱ መሆኑን አስረድተዋል።

በክልሉ በአጠቃላይ ከ6 ሺሕ በላይ የዘርፉ ባለሙያዎች ቢኖሩም በማህበሩ ሥር የታቀፉት 755 አካባቢ ብቻ መሆናቸውን የገለጹም ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ ወርሃዊ መዋጮ መክፈል የማይችሉበት ደረጃ ላይ የደረሱ አባላት ስለመኖራቸውም ተናግረዋል፡፡

የለመዱንት ሥራ ትቶ ወደ ሌሎች ዘርፎች መሰማራት ፈታኝ መሆኑን ያነሱት አቶ ሙሉቀን፤ "ይህን ዘርፍ ትተው ሌላ ሥራ ላይ ቢሰማሩ ውጤታማ ላይሆኑ የሚችሉ ባለሙያዎችም አሉ፤ ስለዚህም ጉዳዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል፡፡   

አሐዱም "የአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አካባቢዎች ያሉ እንዲህ አይነት ችግሮችን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በምን መልኩ ነው የሚቆጣረው? እንዲሁም የፌደራል መንግሥቱ ሳያውቅ የአካባቢው እና የክልል ኃላፊዎች እንዲህ አይነቱን ተግባር እንዳይፈፅሙ ምን ድርሻ አላቸው?" ሲል የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ የትምጌታ አስራትን ጠይቋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በሰጡት ምላሽ፤ "አስቸኳይ እና በልዩነት የመንግሥት የልማት ድርጅቶት እንዲገቡባቸው የሚያስፈልጉ ቦታዎች ካልሆኑ በስተቀር፤ በሌሎቹ ፕሮጀክቶች ላይ ሁሉም በጨረታ እንዲሳተፉ ይደረጋል" ሲሉ ተናግረዋል።

እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ፤ የአማራ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር፤ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ችግሩን መግለጹን፣ ነገር ግን እስካሁን የመፍትሄ አለማግኘቱን አስታውቋል።

Via Ahadu Radio

@etconp
👍20
👉ሕንፃና መሬት ለቴሌኮም መሠረተ ልማት ግንባታ እንዲውሉ የሚያስገድድ ረቂቅ ሕግ ተዘጋጀ

የቴሌኮም መሠረተ ልማት ግባታዎች ለማከናወን የሚፈቅድና የሚያስገድድ የሕግ ረቂቁ ተዘጋጅቶ ውይይት እየተደረገበት መሆኑን የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ፡
ባለሥልጣኑ የመሬት አቅርቦት በሕግና በፖሊሲ እንዲፈታ ምክር ቤቱን ዕገዛ የጠየቁት የኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ባልቻ ሬባ (ኢንጂነር) ናቸው፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ የመሠረተ ልማት ከተገነባ በኋላ መጠበቅ ያለበት ቢሆንም፣ በመላ አገሪቱ ሰው ማስቀመጥ ስለማይቻል ሁሉም ሰው ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል፡፡
የመሬት አቅርቦት ችግር በፖሊሲ እንዲደገፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅሰው፣ ለዚህም የሚረዳ የሕግ ረቂቅ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለኢትዮ ቴሌኮም የቀረቡ የሕዝብ ጥያቄዎችን በተመለከተ ታኅሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም. ውይይት አካሂዷል፡፡
በመድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን በየምርጫ ጣቢያዎቻቸውና በወከላችው ማኅበረሰብ አካባቢ፣ የመሬት አቅርቦት እንዲኖራቸው ድጋፍ አድርጉ ዋና ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ችግሩን እንደ አገር ለማስተካከል ሕንፃና መሬትን ለቴሌኮም መሠረተ ልማት ግንባታ ስለመጠቀም የሚፈቅድ መመርያ ተዘጋጅቶ የመጨረሻ ረቂቅ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ ነገር ግን በመመርያው ሕግ ሁሉም ክልሎች እንዲሳተፉበት ለማድረግ ምክር ቤቱ ድጋፍ ያድርግልን ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የመሠረተ ልማት ደኅንነት ካልተጠበቀ አገልግሎት ማቅረብ አስቸጋሪ መሆኑን የገለጹት ባልቻ (ኢንጂነር)፣ የጋራ ንብረት የሆነውን ሀብት ሁሉም አካል እንዲጠብቀው ጥሪ መደረግ እንዳለበት አስረድተዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ በበኩላቸው፣ ለቴሌኮም መሠረተ ልማት የሚሆን የመሬት አቅርቦት በተለይም አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ ‹‹አዲስ ሳይት በመትከል ብቻ ሳይሆን የተተከሉና የተዘረጉ መስመሮች ጭምር ኢትዮ ቴሌኮም ሊዝ እንዲፈጽም እየተጠየቀ በመሆኑ አገልግሎት ማስፋፋቱ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳረፈብን ነው፤›› ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የፋይናንስ እጥረት፣ የመንገድ ዕጦት፣ የፀጥታ ችግር፣ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ስርቆት፣ የመሬት አቅርቦትና የካሳ ጥያቄ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ኢትዮ ቴሌኮም አጠቃላይ ሥራውን አዳጋች ስለማድረጉ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ በተያዘው ዓመት ለያዘው 1,296 የሚሆን የማስፋፊያ ፕሮጀክት ከ140 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልገው የገለጹት ሥራ አስፈጻሚዋ፣ የአገልግሎት ማስፋፊያው በገጠራማው አካባቢ በብዛት እንደሚያተኩር ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር 80.8 ሚሊዮን መድረሱን የገለጹት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ በመላ አገሪቱ 1,033 የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችና 8,530 ሞባይል ሳይቶቸ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ተቋሙ ቴሌ ብር በተሰኘው አፕሊኬሽኑ ከ3.38 ትሪሊዮን ብር በላይ ማንቀሳቅቀሱን፣ 8.7 ሚሊዮን ብር ከዓለም አቀፍ ሪሚታንስ ማግኘቱን፣ 16.9 ቢሊዮን ብር ብድርና 17.5 ሚሊዮን ቁጠባ መመዝገቡን ወ/ሪት ፍሬሕይወት አስረድተዋል፡፡

በመድረኩ ከምክር ቤቱ አባላት በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን፣ በተደጋጋሚ ተጠይቀው ያልተመለሱ የቴሌኮም አገልግሎት በተለይም በቤንሻንጉል፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ እንዲሁም በሌሎች ክልሎች ያሉ የቴሌኮም አግልግሎት ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡

በሌላ በኩል ከአባላቱ መካከል በግጭትና ጦርነት አካባቢዎች ተከታታይ የኢንተርኔት መቆራረጥና መዘጋት መኖሩን በተመለከት፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካዩ ደሳኝ ጫኔ (ዶ/ር) ባቀረቡት ጥያቄ፣ በግጭትና ጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች ተከታታይ የሆ የኢንተርኔት መቆራረጥ በተለይም የሞባይል ስልክና ኢንትርኔት መዘጋት ስለመኖሩ ተናግረዋል፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታት በትግራይ ክልል ለሁለት ዓመታት፣ በአማራ ክልል ጦርነት ከተጀመረ ጀምሮ ለአንድ ዓመት፣ ጦርነት ባለባቸው የከፊል ኦሮሚያ እንዲሁ የኢንተርኔትና የስልክ መቆራርጥ መኖሩን ተናግረዋል፡፡

ኢንተርኔት ከውኃና መብራት ተለይቶ አይታይም ያሉት አባሉ፣ ግጭትና ጦርነት ባሉባቸው አካባቢዎች ሰዎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቀስው ክፍያ መፈጸም በማይችሉባቸው ሁኔታ ኢንተርኔት ሲዘጋ ለግጭት ተጋላጭ እየተደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አክለውም ጉዳዩ መሰረታዊ የዜጎችን መብት የሚጋፋ ነው ብለዋል፡፡ ‹‹እስካሁን ሲቋረጥ የነበረው ለምንድነው? ኢትዮ ቴሌኮም ወደፊትስ እነዚህ ነገሮች ላለመቀጠላቸው ምን ዋስትና ይሰጣል?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የግለሰቦች ሲምካርድና ቀፎ እንዳይሠራ እንደሚደረግ የተናገሩት ደሳለኝ (ዶ/ር) ‹‹ይህ እኔን የገጠመኝ የግል ጉዳይ ነው፣ ባለፈው ዓመት በአማራ ክልል ጦርነት ሲከስት ስልኬም ሲም ካርዱም እንዳይሠራ ተደረገ፣ በዚህ ምክንያት ኢትዮቴሌኮም ይህን በማድረጉ እኔን አደጋ ላይ ጥሎኛል፣ ከወዳጅ ዘመድ ጋር የመግናኘት መብቴን ነፍጎኛል፤›› ብለዋል፡፡

አንድ ሰው በወንጅል የሚጠርጠርበት ጉዳይ ካለ እሱን ተከታትሎ የሚያስፈጽም አካል ስላለ ኢትዮ ቴሌኮም ይህን ሥራ መሥራት የለበትም ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሰጡት ምላሽ ‹‹ጥራት ያለው አገልግሎት እንድትጠቀሙ ነው የምንፈልገው በምንም መልኩ የእርስዎም ሆነ የሌሎች ደንበኞች ደንበኝነት እንዲቆረጥ ከፈለጉ ወይም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ባለዎት ስምምነት ለምሳሌ ደረሰኝ ባይከፈል ይሄንንም አሳውቀን ካልሆነ ዝም ብለን አንዘጋም ብለዋል››፡፡

ከፀጥታ ጋር ተያይዞ በአንዳንድ ቦታዎች ግጭቶች ሲኖሩ ለሚቋረጠው የኢንተርኔት ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ በመሆኑ ይህን እንደማያደርግ ተናግረዋል፡፡
‹‹ከኢንተርኔት ጋር ተያይዞ ለሚፈጠር መቆራረጥ የሚመለከተው ሌላ ተቋም ነው፣ የሚመለከተው ተቋም ጋር ጥያቄዎትን ቢያቀርቡ ወይም ውይይት ቢያደርጉ የተሻለ ነው እላለሁ፤›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

Via Reporter

@etconp
👍19
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ መቁረጫ መብሻና  ማጠፊያ ማሽኖች አሉን

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ እናበጃለን እንዲሁም እናጥፋለን

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍3
Intercon Construction Chemicals 
    
👉 Authorized agent of MC, SIMENTEK, Sika, Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grouting   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Floor hardener, Epoxy              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍5
👉𝗘𝗮𝗿𝘁𝗵𝗾𝘂𝗮𝗸𝗲 𝗘𝗻𝗴𝗶𝗻𝗲𝗲𝗿𝗶𝗻𝗴: 𝗦𝗲𝗶𝘀𝗺𝗶𝗰 𝗗𝗲𝘃𝗶𝗰𝗲𝘀?

Seismic devices are critical engineering tools designed to enhance the safety and resilience of structures in earthquake-prone areas.

By mitigating the impact of seismic forces, these devices play a key role in protecting buildings, bridges, and other infrastructure. 

Here are the main types: 

1️⃣ 𝗦𝗲𝗶𝘀𝗺𝗶𝗰 𝗜𝘀𝗼𝗹𝗮𝘁𝗼𝗿𝘀 

These devices decouple a structure from ground motion, allowing it to move independently during an earthquake. By reducing the forces transmitted to the structure, they help prevent damage. 

2️⃣ 𝗘𝗻𝗲𝗿𝗴𝘆 𝗗𝗶𝘀𝘀𝗶𝗽𝗮𝘁𝗼𝗿𝘀 (𝗼𝗿 𝗗𝗮𝗺𝗽𝗲𝗿𝘀) 

By absorbing and dissipating seismic energy, dampers reduce structural vibrations and enhance stability during an earthquake. 

3️⃣ 𝗦𝗵𝗼𝗰𝗸 𝗧𝗿𝗮𝗻𝘀𝗺𝗶𝘀𝘀𝗶𝗼𝗻 𝗨𝗻𝗶𝘁𝘀 (𝗦𝗧𝗨𝘀) 

Commonly used in bridges and other critical structures, STUs accommodate slow movements like thermal expansion but lock under sudden seismic forces to provide stability. 

As urban development continues to expand into seismically active regions, incorporating these devices into structural design is increasingly essential.

Their implementation can mean the difference between minor disruption and catastrophic failure. 

Via yonatan Tadesse PMP

@etconp
👍16👏3❤2
👉Pile Foundation

➡️A pile foundation is a type of deep foundation that transfers structural loads from a building or other structure to a deeper soil or rock stratum with greater load-bearing capacity.

Piles are essentially long, slender members made of materials like concrete, steel, or timber, driven or drilled into the ground to provide support.

👷Types of Pile Foundations

🚧Pile foundations can be classified based on various criteria, such as their function, material, and installation method.

💫Here are some common types:

👷1. Based on Function:

🚧 End-bearing Piles: These piles transmit the load to a strong, load-bearing stratum located at a considerable depth below the ground surface.

🚧Friction Piles: These piles develop their load-carrying capacity primarily through skin friction between the pile surface and the surrounding soil.

👷2. Based on Material:

🚧 Timber Piles: Made of wood, often treated to resist decay and insect attack. They are relatively inexpensive but have limited load-bearing capacity and durability.

🚧 Concrete Piles: Made of concrete, either precast or cast-in-place. They are strong, durable, and versatile, suitable for a wide range of soil conditions and loads.

🚧 Steel Piles: Made of steel, offering high strength and slenderness. They are commonly used in situations where high loads or space constraints are a concern.

🚧 Composite Piles: Combine two or more materials, such as concrete and steel, to optimize their properties.

👷3. Based on Installation Method:

🚧 Driven Piles: Installed by driving them into the ground using a hammer or other impact device.

🚧 Bored Piles: Formed by excavating a hole in the ground and then filling it with concrete.

🚧 Screw Piles: Installed by rotating a helical blade into the ground.

🚧 Sheet Piles: Interlocking elements driven into the ground to form a continuous wall, often used for excavation support or water barriers.

⭐️Choosing the Right Pile Foundation

🚧The selection of the appropriate pile foundation depends on various factors, including:
🚧 Soil conditions
🚧 Load requirements
🚧 Environmental considerations
🚧 Cost
🚧 Construction constraints

🔰A geotechnical engineer can assess the site conditions and design the most suitable pile foundation for a specific project.

@etconp
👍12❤1
@etconp 2017 2nd Quarter Direct Cost.pdf
20 MB
🏷በ2017 ዓ.ም ሁለተኛ ሩብ ዓመት ተግባራዊ የሚደረግ የግንባታ ሥራዎች ይፋዊ ቀጥተኛ ዋጋ ተመን (2nd Quarter Construction Works of Direct Cost)

🔑በተለይ የዋጋ ተመን (BOQ - Priced bill of Quantities) ለምታወጡ የዲዛይን አማካሪዎች እና የፕሮጀክት መሐንዲሶች ይጠማችኋል።

💫በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የምትገኙ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችም እንደመነሻ ሀሳብ ይጠቅማችኋል።


@etconp
🙏20👍9🔥1
#Advertising #ማስታወቂያ #MusaFide
Our Services Include:

💻 Civil 3D Full Tutorials (4K Video)

Tutorials with project files used throughout the video for hands-on learning.
📊 All Supporting Materials

Access materials, including PKT Files, Superelevation Excels, & ERA Manual XML, to streamline your design work.
🏗 Girder Bridge Working Drawing Preparation

Complete working drawings for Girder Bridges, including all materials used in the tutorial, & the 3D model created in SketchUp.
🚗 Highway Design Expertise

Professional highway design services
🛠 Template Production & PKT Development Template creation & PKT development as per your project standards.

📏 Earthwork & Pavement Quantity Preparation

Earthwork & pavement quantity preparation to ensure precise cost estimation.
🏗 Structural Working Drawing Preparation

Detailed structural working drawings Preparation
Connect with Us:
YouTube: http://www.youtube.com/@musfide
Telegram: https://t.me/musafide
WhatsApp: https://bit.ly/musfide
Call Us: +251 905 666 664
👍9👏1