Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.31K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
ርዕደ መሬት በኢትዮዽያ

ሰርዶ ርዕደ መሬት

በመጋቢት 1962 ዓም 6.2 Mw እና 6.1Mw የሚለካ ሶስት ግዜ ለአንድ ሳምንት ያህል ርዕደ መሬት በአፋር ውስጥ በምትገኘው ሰርዶ ከተማ ደርሶ ነበር። ሶስቱም ርዕደቶች ከአደገኛ እስከ ከፍተኛ በሚለኩ ጉልበት ነበር የደረሱት። 24 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 165 ሰዎች ቆስለው ነበር። አደጋው የደረሰው በጭቃ በተሰሩ ቤቶች ደካማ አሰራር እንደነበር ታውቋል። 100 የጭቃ ቤቶች በሙሉ ፈርሰው ከአደጋው የተረፉት 300 ሰዎች በስተምዕራብ በ50 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደምትገኘው ወደ ሎጊያ ተሰደው ነበር። ርዕደ መሬቱ በ30 ኪሎሜትር ራዲየስ የተሰማ ነበር።

ምን ያህል ርዕደ መሬትን ለመከላከል የተዘጋጀ ዘመናዊና ባህላዊ የግንባታ ዘይቤ አለን?

የትኞቹ የኪነህንጻ የዲግሪ መርሀግብሮች "ርዕደ መሬት ከል" የንድፍ መርሆችን በስርዓተ ትምህርታቸው ውስጥ አካተዋል?

Via ethiopian architecture and urbanism

@etconp
👍15❤8
Earthquake resistant design 2017.pdf
2.5 MB
👉ርዕደ መሬት ተከላካይ ህንጻ ንድፍ

🏷በአገራችን የኪነህንጻና ስነከተማ ትምህርት ውስጥ የርዕደ መሬት መከላከያ የንድፍ መንገዶች አትኩሮት ከማይሰጥባቸው ዘርፎች አንዱ ነው።

⭐️የተያያዙትት የምስል ሰሌዳዎች በዶክተር አዲል በአዲስ አበባ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተዘጋጁ ሲሆኑ ጠቃሚ የርዕደ መሬት ተከላካይ የመዋቅር እና የኪነህንጻ ንድፍ ውሳኔዎች ን ያመላክቱናል።

💫በዶ/ር አዲል ዘ. AAiT

📜Useful Architectural and  Structural Considerations for  Earthquake Resistant
Design

By Dr Adil Z. AAiT

@etconp
🙏12👍8
👉በአማራ ክልል ፕሮጀክቶች ያለ ጨረታ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች ብቻ እየተሰጡ ነው ተባለ

በአማራ ክልል ያሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ያለ ጨረታ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች እየተሰጡ፤ የግሉ ዘርፍ ከሥራ እንዲወጣ እየተደረገ ነው ሲል የክልሉ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ገልጿል።

የአማራ ክልል ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ፕሬዝደንት አቶ ሙሉቀን ቢተው "በክልሉ የሚተገበሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶች 'ጨረታ አልወጣም' እንዳይባል ብቻ አምስት ያክል የመንግሥት ባለድርሻዎችን አሳትፈው፤ መልሰው የሚወስዱት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ናቸው" ሲሉ ለአሐዱ የገለጹ ሲሆን፤ ይህም ተግባር የግሉን ዘርፍ ይበልጥ እያዳከመው እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዚህም የተነሳ ከ6 ሺሕ በላይ ኮንትራክተሮች ችግር ውስጥ መሆናቸው በማንሳት፤ በክልሉ የሚንቀሳቀሱና በኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ የተሰማሩ አካላት ሥራቸውን መስራት እስካለመቻል የደረሱ ችግሮችን እያስተናገዱ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

"ችግሩ ከፍተኛ በመሆኑ በተለይም ያለው የሥራ ሁኔታ በቀዘቀዘበት እንዲሁም ፕሮጀክቶች ያለምንም ጨረታ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች በሚሰጥበት ሁኔታ ውስጥ ኮንትራክተሮች ከፍተኛ ችግር ላይ እየወደቁ ነው" ያሉት የማህበሩ ፕሬዝዳንት፤ በዚህም የተነሳ በርካቶች ቤታቸውን፣ ማሽኖቻቸውን፣ መኪኖቻቸውንና ሌሎች ንብረቶቻቸውን ለመሸጥ እየተገደዱ መሆኑን አስረድተዋል።

በክልሉ በአጠቃላይ ከ6 ሺሕ በላይ የዘርፉ ባለሙያዎች ቢኖሩም በማህበሩ ሥር የታቀፉት 755 አካባቢ ብቻ መሆናቸውን የገለጹም ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ ወርሃዊ መዋጮ መክፈል የማይችሉበት ደረጃ ላይ የደረሱ አባላት ስለመኖራቸውም ተናግረዋል፡፡

የለመዱንት ሼል ትቶ ወደ ሌሎች ዘርፎች መሰማራት ፈታኝ መሆኑን ያነሱት አቶ ሙሉቀን፤ "ይህን ዘርፍ ትተው ሌላ ሼል ላይ ቢሰማሩ ውጤታማ ላይሆኑ የሚችሉ ባለሙያዎችም አሉ፤ ስለዚህም ጉዳዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል፡፡   

አሐዱም "የአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አካባቢዎች ያሉ እንዲህ አይነት ችግሮችን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በምን መልኩ ነው የሚቆጣረው? እንዲሁም የፌደራል መንግሥቱ ሳያውቅ የአካባቢው እና የክልል ኃላፊዎች እንዲህ አይነቱን ተግባር እንዳይፈፅሙ ምን ድርሻ አላቸው?" ሲል የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ የትምጌታ አስራትን ጠይቋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በሰጡት ምላሽ፤ "አስቸኳይ እና በልዩነት የመንግሥት የልማት ድርጅቶት እንዲገቡባቸው የሚያስፈልጉ ቦታዎች ካልሆኑ በስተቀር፤ በሌሎቹ ፕሮጀክቶች ላይ ሁሉም በጨረታ እንዲሳተፉ ይደረጋል" ሲሉ ተናግረዋል።

እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ፤ የአማራ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር፤ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ችግሩን መግለጹን፣ ነገር ግን እስካሁን የመፍትሄ አለማግኘቱን አስታውቋል።

Via Ahadu Radio

@etconp
👍20
👉ሕንፃና መሬት ለቴሌኮም መሠረተ ልማት ግንባታ እንዲውሉ የሚያስገድድ ረቂቅ ሕግ ተዘጋጀ

የቴሌኮም መሠረተ ልማት ግባታዎች ለማከናወን የሚፈቅድና የሚያስገድድ የሕግ ረቂቁ ተዘጋጅቶ ውይይት እየተደረገበት መሆኑን የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ፡
ባለሥልጣኑ የመሬት አቅርቦት በሕግና በፖሊሲ እንዲፈታ ምክር ቤቱን ዕገዛ የጠየቁት የኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ባልቻ ሬባ (ኢንጂነር) ናቸው፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ የመሠረተ ልማት ከተገነባ በኋላ መጠበቅ ያለበት ቢሆንም፣ በመላ አገሪቱ ሰው ማስቀመጥ ስለማይቻል ሁሉም ሰው ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል፡፡
የመሬት አቅርቦት ችግር በፖሊሲ እንዲደገፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅሰው፣ ለዚህም የሚረዳ የሕግ ረቂቅ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለኢትዮ ቴሌኮም የቀረቡ የሕዝብ ጥያቄዎችን በተመለከተ ታኅሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም. ውይይት አካሂዷል፡፡
በመድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን በየምርጫ ጣቢያዎቻቸውና በወከላችው ማኅበረሰብ አካባቢ፣ የመሬት አቅርቦት እንዲኖራቸው ድጋፍ አድርጉ ዋና ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ችግሩን እንደ አገር ለማስተካከል ሕንፃና መሬትን ለቴሌኮም መሠረተ ልማት ግንባታ ስለመጠቀም የሚፈቅድ መመርያ ተዘጋጅቶ የመጨረሻ ረቂቅ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ ነገር ግን በመመርያው ሕግ ሁሉም ክልሎች እንዲሳተፉበት ለማድረግ ምክር ቤቱ ድጋፍ ያድርግልን ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የመሠረተ ልማት ደኅንነት ካልተጠበቀ አገልግሎት ማቅረብ አስቸጋሪ መሆኑን የገለጹት ባልቻ (ኢንጂነር)፣ የጋራ ንብረት የሆነውን ሀብት ሁሉም አካል እንዲጠብቀው ጥሪ መደረግ እንዳለበት አስረድተዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ በበኩላቸው፣ ለቴሌኮም መሠረተ ልማት የሚሆን የመሬት አቅርቦት በተለይም አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ ‹‹አዲስ ሳይት በመትከል ብቻ ሳይሆን የተተከሉና የተዘረጉ መስመሮች ጭምር ኢትዮ ቴሌኮም ሊዝ እንዲፈጽም እየተጠየቀ በመሆኑ አገልግሎት ማስፋፋቱ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳረፈብን ነው፤›› ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የፋይናንስ እጥረት፣ የመንገድ ዕጦት፣ የፀጥታ ችግር፣ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ስርቆት፣ የመሬት አቅርቦትና የካሳ ጥያቄ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ኢትዮ ቴሌኮም አጠቃላይ ሥራውን አዳጋች ስለማድረጉ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ በተያዘው ዓመት ለያዘው 1,296 የሚሆን የማስፋፊያ ፕሮጀክት ከ140 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልገው የገለጹት ሥራ አስፈጻሚዋ፣ የአገልግሎት ማስፋፊያው በገጠራማው አካባቢ በብዛት እንደሚያተኩር ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር 80.8 ሚሊዮን መድረሱን የገለጹት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ በመላ አገሪቱ 1,033 የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችና 8,530 ሞባይል ሳይቶቸ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ተቋሙ ቴሌ ብር በተሰኘው አፕሊኬሽኑ ከ3.38 ትሪሊዮን ብር በላይ ማንቀሳቅቀሱን፣ 8.7 ሚሊዮን ብር ከዓለም አቀፍ ሪሚታንስ ማግኘቱን፣ 16.9 ቢሊዮን ብር ብድርና 17.5 ሚሊዮን ቁጠባ መመዝገቡን ወ/ሪት ፍሬሕይወት አስረድተዋል፡፡

በመድረኩ ከምክር ቤቱ አባላት በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን፣ በተደጋጋሚ ተጠይቀው ያልተመለሱ የቴሌኮም አገልግሎት በተለይም በቤንሻንጉል፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ እንዲሁም በሌሎች ክልሎች ያሉ የቴሌኮም አግልግሎት ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡

በሌላ በኩል ከአባላቱ መካከል በግጭትና ጦርነት አካባቢዎች ተከታታይ የኢንተርኔት መቆራረጥና መዘጋት መኖሩን በተመለከት፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካዩ ደሳኝ ጫኔ (ዶ/ር) ባቀረቡት ጥያቄ፣ በግጭትና ጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች ተከታታይ የሆ የኢንተርኔት መቆራረጥ በተለይም የሞባይል ስልክና ኢንትርኔት መዘጋት ስለመኖሩ ተናግረዋል፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታት በትግራይ ክልል ለሁለት ዓመታት፣ በአማራ ክልል ጦርነት ከተጀመረ ጀምሮ ለአንድ ዓመት፣ ጦርነት ባለባቸው የከፊል ኦሮሚያ እንዲሁ የኢንተርኔትና የስልክ መቆራርጥ መኖሩን ተናግረዋል፡፡

ኢንተርኔት ከውኃና መብራት ተለይቶ አይታይም ያሉት አባሉ፣ ግጭትና ጦርነት ባሉባቸው አካባቢዎች ሰዎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቀስው ክፍያ መፈጸም በማይችሉባቸው ሁኔታ ኢንተርኔት ሲዘጋ ለግጭት ተጋላጭ እየተደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አክለውም ጉዳዩ መሰረታዊ የዜጎችን መብት የሚጋፋ ነው ብለዋል፡፡ ‹‹እስካሁን ሲቋረጥ የነበረው ለምንድነው? ኢትዮ ቴሌኮም ወደፊትስ እነዚህ ነገሮች ላለመቀጠላቸው ምን ዋስትና ይሰጣል?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የግለሰቦች ሲምካርድና ቀፎ እንዳይሠራ እንደሚደረግ የተናገሩት ደሳለኝ (ዶ/ር) ‹‹ይህ እኔን የገጠመኝ የግል ጉዳይ ነው፣ ባለፈው ዓመት በአማራ ክልል ጦርነት ሲከስት ስልኬም ሲም ካርዱም እንዳይሠራ ተደረገ፣ በዚህ ምክንያት ኢትዮቴሌኮም ይህን በማድረጉ እኔን አደጋ ላይ ጥሎኛል፣ ከወዳጅ ዘመድ ጋር የመግናኘት መብቴን ነፍጎኛል፤›› ብለዋል፡፡

አንድ ሰው በወንጅል የሚጠርጠርበት ጉዳይ ካለ እሱን ተከታትሎ የሚያስፈጽም አካል ስላለ ኢትዮ ቴሌኮም ይህን ሥራ መሥራት የለበትም ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሰጡት ምላሽ ‹‹ጥራት ያለው አገልግሎት እንድትጠቀሙ ነው የምንፈልገው በምንም መልኩ የእርስዎም ሆነ የሌሎች ደንበኞች ደንበኝነት እንዲቆረጥ ከፈለጉ ወይም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ባለዎት ስምምነት ለምሳሌ ደረሰኝ ባይከፈል ይሄንንም አሳውቀን ካልሆነ ዝም ብለን አንዘጋም ብለዋል››፡፡

ከፀጥታ ጋር ተያይዞ በአንዳንድ ቦታዎች ግጭቶች ሲኖሩ ለሚቋረጠው የኢንተርኔት ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ በመሆኑ ይህን እንደማያደርግ ተናግረዋል፡፡
‹‹ከኢንተርኔት ጋር ተያይዞ ለሚፈጠር መቆራረጥ የሚመለከተው ሌላ ተቋም ነው፣ የሚመለከተው ተቋም ጋር ጥያቄዎትን ቢያቀርቡ ወይም ውይይት ቢያደርጉ የተሻለ ነው እላለሁ፤›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

Via Reporter

@etconp
👍19
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ መቁረጫ መብሻና  ማጠፊያ ማሽኖች አሉን

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ እናበጃለን እንዲሁም እናጥፋለን

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
👍3
Intercon Construction Chemicals 
    
👉 Authorized agent of MC, SIMENTEK, Sika, Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grouting   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Floor hardener, Epoxy              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍5
👉𝗘𝗮𝗿𝘁𝗵𝗾𝘂𝗮𝗸𝗲 𝗘𝗻𝗴𝗶𝗻𝗲𝗲𝗿𝗶𝗻𝗴: 𝗦𝗲𝗶𝘀𝗺𝗶𝗰 𝗗𝗲𝘃𝗶𝗰𝗲𝘀?

Seismic devices are critical engineering tools designed to enhance the safety and resilience of structures in earthquake-prone areas.

By mitigating the impact of seismic forces, these devices play a key role in protecting buildings, bridges, and other infrastructure. 

Here are the main types: 

1️⃣ 𝗦𝗲𝗶𝘀𝗺𝗶𝗰 𝗜𝘀𝗼𝗹𝗮𝘁𝗼𝗿𝘀 

These devices decouple a structure from ground motion, allowing it to move independently during an earthquake. By reducing the forces transmitted to the structure, they help prevent damage. 

2️⃣ 𝗘𝗻𝗲𝗿𝗴𝘆 𝗗𝗶𝘀𝘀𝗶𝗽𝗮𝘁𝗼𝗿𝘀 (𝗼𝗿 𝗗𝗮𝗺𝗽𝗲𝗿𝘀) 

By absorbing and dissipating seismic energy, dampers reduce structural vibrations and enhance stability during an earthquake. 

3️⃣ 𝗦𝗵𝗼𝗰𝗸 𝗧𝗿𝗮𝗻𝘀𝗺𝗶𝘀𝘀𝗶𝗼𝗻 𝗨𝗻𝗶𝘁𝘀 (𝗦𝗧𝗨𝘀) 

Commonly used in bridges and other critical structures, STUs accommodate slow movements like thermal expansion but lock under sudden seismic forces to provide stability. 

As urban development continues to expand into seismically active regions, incorporating these devices into structural design is increasingly essential.

Their implementation can mean the difference between minor disruption and catastrophic failure. 

Via yonatan Tadesse PMP

@etconp
👍16👏3❤2
👉Pile Foundation

➡️A pile foundation is a type of deep foundation that transfers structural loads from a building or other structure to a deeper soil or rock stratum with greater load-bearing capacity.

Piles are essentially long, slender members made of materials like concrete, steel, or timber, driven or drilled into the ground to provide support.

👷Types of Pile Foundations

🚧Pile foundations can be classified based on various criteria, such as their function, material, and installation method.

💫Here are some common types:

👷1. Based on Function:

🚧 End-bearing Piles: These piles transmit the load to a strong, load-bearing stratum located at a considerable depth below the ground surface.

🚧Friction Piles: These piles develop their load-carrying capacity primarily through skin friction between the pile surface and the surrounding soil.

👷2. Based on Material:

🚧 Timber Piles: Made of wood, often treated to resist decay and insect attack. They are relatively inexpensive but have limited load-bearing capacity and durability.

🚧 Concrete Piles: Made of concrete, either precast or cast-in-place. They are strong, durable, and versatile, suitable for a wide range of soil conditions and loads.

🚧 Steel Piles: Made of steel, offering high strength and slenderness. They are commonly used in situations where high loads or space constraints are a concern.

🚧 Composite Piles: Combine two or more materials, such as concrete and steel, to optimize their properties.

👷3. Based on Installation Method:

🚧 Driven Piles: Installed by driving them into the ground using a hammer or other impact device.

🚧 Bored Piles: Formed by excavating a hole in the ground and then filling it with concrete.

🚧 Screw Piles: Installed by rotating a helical blade into the ground.

🚧 Sheet Piles: Interlocking elements driven into the ground to form a continuous wall, often used for excavation support or water barriers.

⭐️Choosing the Right Pile Foundation

🚧The selection of the appropriate pile foundation depends on various factors, including:
🚧 Soil conditions
🚧 Load requirements
🚧 Environmental considerations
🚧 Cost
🚧 Construction constraints

🔰A geotechnical engineer can assess the site conditions and design the most suitable pile foundation for a specific project.

@etconp
👍12❤1
@etconp 2017 2nd Quarter Direct Cost.pdf
20 MB
🏷በ2017 ዓ.ም ሁለተኛ ሩብ ዓመት ተግባራዊ የሚደረግ የግንባታ ሥራዎች ይፋዊ ቀጥተኛ ዋጋ ተመን (2nd Quarter Construction Works of Direct Cost)

🔑በተለይ የዋጋ ተመን (BOQ - Priced bill of Quantities) ለምታወጡ የዲዛይን አማካሪዎች እና የፕሮጀክት መሐንዲሶች ይጠማችኋል።

💫በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የምትገኙ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችም እንደመነሻ ሀሳብ ይጠቅማችኋል።


@etconp
🙏20👍9🔥1
#Advertising #ማስታወቂያ #MusaFide
Our Services Include:

💻 Civil 3D Full Tutorials (4K Video)

Tutorials with project files used throughout the video for hands-on learning.
📊 All Supporting Materials

Access materials, including PKT Files, Superelevation Excels, & ERA Manual XML, to streamline your design work.
🏗 Girder Bridge Working Drawing Preparation

Complete working drawings for Girder Bridges, including all materials used in the tutorial, & the 3D model created in SketchUp.
🚗 Highway Design Expertise

Professional highway design services
🛠 Template Production & PKT Development Template creation & PKT development as per your project standards.

📏 Earthwork & Pavement Quantity Preparation

Earthwork & pavement quantity preparation to ensure precise cost estimation.
🏗 Structural Working Drawing Preparation

Detailed structural working drawings Preparation
Connect with Us:
YouTube: http://www.youtube.com/@musfide
Telegram: https://t.me/musafide
WhatsApp: https://bit.ly/musfide
Call Us: +251 905 666 664
👍9👏1
👉የሲሚንቶ ቤተሙከራዎች »
  { Cement Tests }

A) የመኮማተር ጥንካሬ (Compressive Strength)፡- ይህ ምዘን ሲሚንቶ ከደረቀ በኋላ ያለምንም መኮማተር  ወይም መፈረካከስ የሚተገበርበትን ክብደት የመሸከም አቅሙን የምንለይበት ነው።

በመሆኑም ሲሚንቶው ምን ያህል ክብደትን ወይን ጭነትን (loads) የመቋቋም አቅም እንዳለው የምንለይበት ነው።

B) የመለጠጥ ጥንካሬ (Tensile strength)፡ ይህ ሙከራ የሲሚንቶን የመለጠጥ ጥንካሬን የምንመዝንበት ሲሆን ለጭንቀት ሊጋለጥ ለሚችልበትን የጭነት ትግበራ ለማወቅ ጠቃሚ ነው።

C) ጤናማነት ፍተሻ (Soundness):  ይህ የምዘና ሼል ሲሚንቶ ከውሃ ጋር ሲዋሃድ የሚኖረውን የመጠን ለውጥ እና መሰነጣጠቅን ለመቋቋም ያለውን ክህሎት (ጥንካሬ) የምናይበት ነው።

D) የመጠንከሪያ ሰዓት (Setting Time)፡ ይህ ሙከራ ሲሚንቶ የሚጠበቅበትን ጥንካሬ  የሚይዝበትን ወይን የሚደርቅበትን የሰዓት መጠን (ለማጠንከር የሚፈጀውን ጊዜ) ለማወቅ የሚደረግ ምዘና ነው።

ይህ ሂደት የቀረበው የሲሚንቶ አይነት ልንጠቀምበት ላቀድነው የሥራ ክፍል (application to intended works) ተስማሚ የሆነ የመጠንከሪያ ጊዜ መሆኑን ለመለየት ይጠቅማል።

E) ጥቃቅንነት ወይም ልመት (Fineness):  ይህ የሲሚንቶ ቤተሙከራዊ ምዘና የሲሚንቶውን ቅንጣት መጠን (particle size) ለመወሰን የምንሰራው ሲሆን ከውሃ ጋር የመዋሐድ (hydration) ምጣኔን እና በውኅደት ሂደት የሚኖረውን ጥንካሬ እድገት የምንለካበት ነው።

F) ከውሃ ጋር የሚዋሃድበትን የሙቀት መጠን (Heat of Hydration)፡ ይህ የምዘና ሂደት ሲሚንቶ ከእርጥበት ወይም ከውሃ ጋር ለሚያደርገው አጸግብሮት የሚያስፈልገውን የሙቀት መጠን ለማወቅ ይጠቅማል። ይህ ፍተሻ በእርጥበት ሂደት ውስጥ የሚፈጠረው ሙቀት በሲሚንቶው ላይ ስንጥቅ ወይም ሌላ ጉዳት እንዳይደርስበት መጠኑን ለመወሰን ወይም ለማረጋገጥ ጠቃሚ ነው።

G) የኬሚካል ይዘት (Chemical Analysis)፡ ይህ ሙከራ ሲሚንቶው የተመረተበትን የኬሚካል ስብጥር ለማወቅ የሚጠቅም ሲሆን በውስጡ ያሉ ኬሚካሎችና መጠናቸው ለሚፈለገው ሥራ ተስማሚ መሆኑንና አለመሆኑን ወይም የኬሚካል መመዘኛዎች የሚያሟላ መሆኑን እና ምንም ዓይነት ጎጂ ንጥረ ነገሮችን እንደሌለው ለማረጋገጥ ጠቃሚ ነው።

@etconp
👍20❤1
👉ከመንግሥት ጋር ከተያያዙ ተግዳሮቶች ባሻገር ተቋራጮች በራሳቸው ደካማ የሆነ የውል አስተዳደር (Contract Administration) ትግበራ እንዳላቸውም ተጠቅሷል።

ሳሙኤል (ኢንጂነር)፣ ‹‹ለምሳሌ የዋጋ ማስተካከያ ይፈቀድልን በሚል ገንዘብ ሚኒስቴር ሲጠየቅ፣ ‹ማን ከለከላችሁ?› የሚል ጥያቄ ሲያነሳ፣ የከለከለን አማካሪው በልዩ ሁኔታ (Special Condition) በማስፈረም መሆኑን ሲገልጹ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር እንደዚህ ያለ ውል ማን ፈርሙ አላችሁ? ብሎናል። የእኛንም ችግር ራሳችን መውሰድ መቻል አለብን። ግን ፍፁም የተከለከለ አይደለም። በፊት የ12 ወር ተባለ አሁን የ18 ወር ሆነ፣ ከዚያ ውጪ ግን ሙሉ ለሙሉ ይህ ፕሮጀክት ይህንን አያካትትም ብሎ መከልከልን ያመጣው በደካማ ውል አስተዳደር ትግበራችን ችግር ነው፤›› ብለዋል። 

ከዚህ ባሻገር የአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች የግንባታ ጥሬ ዕቃ ከውጭ አገሮች ለማስመጣት፣ ከፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ ከ40 እስከ 60 በመቶ የሚሆነውን ያህል ገንዘብ የሚያወጡ ቢሆንም፣ ግዥ ለመፈጸም የሚዋዋሉት አገር ውስጥ ካለ አስመጪ ድርጅት ጋር በመሆኑ፣ ዕቃዎቹ ወደ አገር ውስጥ የሚገባበት ጊዜ ፍጥነት አስተማማኝ አለመሆኑን ጥናቶቹን ያቀረቡት ባለሙያዎች አስረድተዋል።

Via ሪፖርተር

@etconp
👍13🥰2❤1🔥1
👉ኦቪድ ሪል እስቴት በ 21 ቢሊዬን ብር ወጪ የሚገነባዉ የጫካ ፕሮጀክት ግንባታዉን በይፋ አስጀመረ፡፡

ኦቪድ ሪል እስቴት ለሚያስገነባው የጫካ ፕሮጀክት የኮንኩሪት ሙሌት ማስጀመሪያ እና የሽያጭ ቢሮ ማስመረቂያ ፕሮግራም አካሂዷል፡፡

ግንባታዉ በ 9 ነጥብ 4 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን ባለ 18 ወለል 26 ህንፃዎች የሚኖሩት ይሆናል ተብሎል ፡፡

የኦቪድ ሪል እስቴት ዋና ስራ አሰፈፃሚ ኢንጂነር ሙሉቀን ምትኩ በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ላይ እንዳስታወቁት ግንባታዉ 2 ሺህ 1 መቶ 32 አባዎራዎችን መያዝ የሚችል ሲሆን የስፖርት ማዘውተሪያ ፤ሱፐር ማርኬትእንዲሁም አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችን ያካተተ ነው ሲሉ ገልፀዋል

ግንባታዉ በሁለት ምእራፍ የሚካሄድ ሲሆን ከ ከሁለት እስከ አምስት አመታት የሚዘልቅ ቆይታ ይኖረዋል ተብሏል

የጨካ ፕሮጀክቱን ኦቪድ ሪል እስቴት ከጠቅላይ ሚኒስተር ቢሮ ጋር በጋራ የሚለማው ይሆናል ፡፡

ኦቪድ እሪል እስቴት መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች ታሳቢ ያደረጉ ቤቶች በመገንባት የሚታወቅ ሲሆን ቅንጡ እና ዉድ ቤቶችን በአማራጭነት የተካተቱበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

Via Ethio FM

@etconp
👍16❤2
👉በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው የቦሌ አራብሳ ዘመናዊ  የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ:-

በቀን 30 ሚሊዮን ሊትር ፍሳሽ የማጣራት አቅም ያለው የቦሌ አራብሳ ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ

ይህ ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ  የከተማችንን የፍሳሽ ማጣራት አቅም ከአምስት ዓመት በፊት ከነበረበት በቀን 48 ሺሕ ሜትር ኪዮብ ወደ በቀን233 ሺሕ ሜትር ኪዮብ ከፍ ማድረግ አስችሎናል::

የቦሌ አራብሳ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ  ከ240 ሺህ በላይ የሚሆኑ የአካባቢውን ነዋሪዎች የዘመናዊ ፍሳሽ ማጣሪያ ፣ስርዓት ተጠቃሚ የሚያደርግ ነዉ። 

Via AAWSA

@etconp
👍12❤1
Intercon Construction Chemicals 
    
👉 Authorized agent of MC, SIMENTEK, Sika, Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grouting   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Floor hardener, Epoxy              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👍4
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ከ አባይ ግድብ እስከ ኮሪደር ልማት

ከግለሰብ ቤቶች እስከ ተቋማት እና

መጋዘኖች በሁሉም የኢትዮጽያ ክፍል

አሻራችንን አሳርፈናል

🔰ምን ይፈልጋሉ?

✂️ላሜራ መቁረጫ ÷ ማጠፊያ እና መብሻ ማሽኖች አሉን

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦
                    ቁ.1 መርካቶ
                    ቁ.2 ተክለሀይማኖት
                     ቁ.3 አየር ጤና

0904040477
0911016833
👍5