Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.26K photos
359 videos
1.99K files
3.29K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
👉የ'አዲስ ቱሞሮ' ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ እየተካሄደ ነው

🚧በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት የ'አዲስ ቱሞሮ' ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን ገለጸ፡፡

"አዲስ ቱሞሮ" ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የልማት ፕሮጀክት የመዲናዋን ዓለም አቀፍ ሚና የሚያጎለብት መሆኑ የሚጠቀስ ነው።

በመዲናዋ በጎተራ አካባቢ የሚገነባው ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በውስጡ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ፣ የንግድ፣ የትምህርት፣ የባህል፣ የፋይናንስና የቢዝነስ ዞን ያካትታል ተብሏል።

በተጨማሪም ዘመናዊ የመኖሪያ ቤትና መዝናኛ ዞኖች እንደሚኖሩት ተመላክቷል።

የከተማ አስተዳደሩ ለዚህ ፕሮጀክት የሚሆን 35 ሄክታር መሬት በወቅታዊ የሊዝ ዋጋ አስልቶ እንደሚያቀርብ ተገልጿል።

የቻይናው የግንባታ ኩባንያ 'ቻይና ፈርስት ሃይዌይ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ' ወቅቱ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ፣ ፋይናንስና ሌሎች ግብዓት በማቅረብ ግንባታውን ማካሄድ ጀምሯል።

ልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ በሁለት ምዕራፎች ተከፋፍሎ የሚገነባ ሲሆን፣ የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ አካል የሆነው እጅግ ዘመናዊ ባለ 22 ወለል የመኖሪያ አፓርትመንት፣ ባለ 11 ወለል የቢሮ ግንባታ እንዲሁም ባለ 5 ወለል የ lobby እና podium ግንባታ ሥራ መጀመሩ ታውቋል።

ግንባታው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የቻይና ኩባንያ በሆነው FHEC Overseas Investment Company መካከል በተገባው የሽርክና (Joint Venture) ውል መሰረት እየተገነባ ያለ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክት ነው፡፡

አጠቃላይ ፕሮጀክቱ በ35 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በውስጡ ትላልቅ ሞሎች፣ የመኖሪያ አፓርትመንቶች፣ ቢሮዎች፣ ሰፋፊ የመዝናኛና የውኃ አካላትን እንዲሁም የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላትን ያካተተ ነው።

@etconp
👍8❤3
👉የጥራት ቁጥጥር ለኢትዮጵያ ሬዲሚክስ ኮንክሪት ኢንዱስትሪ‼️

💫ኢትዮጵያ ውስጥ እያደገ በመጣው የሬዲሚክስ ኮንክሪት ኢንዱስትሪ ውስጥ የጥራት ቁጥጥርን ማስፈን የዘርፉን የወደፊት እጣ ፈንታ ብሩህ ሊያደርገው ይችላል።

አሁን አሁን በኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥራት ያለው የኮንክሪት ፍላጎት እያደገ በመምጣቱ፣ የጥራት ቁጥጥርን አስፈላጊነት ማሳደግ ወሳኝ ነው።

የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች መስፋፋት በኢንዱስትሪው ውስጥ ያለውን የጥራት ቁጥጥር ለማሻሻል አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

ይህም አስተማማኝ፣ ረጅም ጊዜ የሚቆይ እና የበለጠ ወጪ ቆጣቢ ግንባታዎችን ዕውን እንዲሆኑ ያደርጋል፣ ይህም ለኮንስትራክሽን ኢንደስትሪውም ሆነ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ይጠቅማል።

በኢትዮጵያ በሬዲሚክስ ኮንክሪት ኢንዱስትሪ ላይ መካሄድ የሚገባው የጥራት ቁጥጥር ለኮንስትራክሽን ኢንደስትሪውንም ሆነ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ በርካታ አዎንታዊ ተጽእኖዎች አሉት። እነዚህ ተጽእኖዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

⏺የግንባታ ደህንነትን አስተማማኝነት ይጨምራል፦

የጥራት ቁጥጥር የኮንክሪት ግንባታዎችን ደህንነት ለማሻሻል ይረዳል። ይህ የሆነበት ምክንያት ከፍተኛ ጥራት ያለው ኮንክሪት የመሰባበር ወይም የመሰብሰብ እድሉ አነስተኛ ስለሆነ ነው።

⏺የቆይታ ጊዜ መጨመር፦

የጥራት ቁጥጥር የኮንክሪት አወቃቀሮችን ዘላቂነት ለመጨመር ይረዳል። ይህ የሆነበት ምክንያት ከፍተኛ ጥራት ያለው ኮንክሪት በተለያዩ ባዕድ ንጥረ ነገሮች የመጎዳት እድሉ አነስተኛ ነው።

⏺ወጪዎችን ለመቀነስ ያስችላል፦

የጥራት ቁጥጥር የግንባታ ፕሮጀክቶችን ወጪ ለመቀነስ ይረዳል። ምክንያቱም ከፍተኛ ጥራት ያለው ኮንክሪት አነስተኛ ጥገና ወይም ጨርሶ ጥገና ስለሚያስፈልገው ጭምር ነው።

⏺የደንበኛ እርካታን ይጨምራል፦

የጥራት ቁጥጥር የደንበኞችን እርካታ በኮንክሪት መዋቅሮች ለማሻሻል ይረዳል። ይህ የሆነበት ምክንያት ደንበኞች ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ረጅም አመት በሚቆዩ ግንባታዎችን ላይ የመርካት እድላቸው ሰፊ ነው።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው የሬዲሚክስ ኮንክሪት ኢንዱስትሪ የጥራት ቁጥጥር አስፈላጊ ነው። የኮንክሪት መዋቅሮችን ደህንነትን፣ ጥንካሬን እና ወጪ ቆጣቢነትን ለማሻሻል ይረዳል። በተጨማሪም የደንበኞችን እርካታ ለማሳደግ ይረዳል።

@etconp
❤8👍7
While drawing Mohr's envelope, the relationship can be considered to be a straight line, if the angle of internal friction is assumed to be....
Anonymous Quiz
25%
Right Angle
23%
Constant
34%
Zero
16%
Acute Angle
3%
None of the above
👍6❤5
👍7🔥2❤1😭1
Minimum %of tensile reinforcement in an RCC beam for Fe500 steel is
Anonymous Quiz
27%
A) 0.12
22%
B) 0.17
27%
C) 0.22
24%
D) 0.80
👍7
❤4👍4
St. 1- Cement is always taken by weight whatever type of batching.
St. 2- Water is always taken by volume whatever be type of batching.
St. 3- Mixing time of concrete depends upon the type of mixture and capacity of mixture.
Anonymous Quiz
16%
Only 1&2 are correct
23%
Only 2&3 are correct
20%
Only 1&3 are correct
8%
All 1,2,3, are wornog
33%
All 1,2,3, are correct
❤6👍3👏2
Density of medium density concrete varries b/w............... in kg/m^3
Anonymous Quiz
23%
1200-1800
49%
1800-2500
19%
2500-3000
6%
3200-4000
3%
None of the above
🥰5👏3
The maximum spacing of shear reinforcement along the axis of the member shall not exceed ___ times the effective depth of the section for vertical stirrups
Anonymous Quiz
44%
0.50
34%
0.75
13%
0.65
9%
1.20
👏9
In rigid pavement, Soil subgrade reaction (K) is determine by plate load test corresponding to the_____deflection
Anonymous Quiz
24%
0.15cm
31%
0.125cm
22%
0.20cm
20%
0.25cm
3%
None of the above
🔥7👍3
The design shear stress in reinforced cement concrete depends on???

A. Charectrestic strength of steel. B. Charectrestic strength of concrete. C. Percentage of longitudional tensile reinforcement.
Anonymous Quiz
8%
Only A
28%
A & B both
10%
Only B
13%
B & C both
40%
All
👍7❤3
👉ባለፉት ዘጠኝ ወራት 413 ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ ተደርገዋል።

💫በበጀት ዓመቱ 9 ወራት በማዕከል እና በክፍለከተማ ደረጃ 325 ግንባታዎችን ለማጠናቀቅ ዕቅድ ይዞ የነበረው የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በጊዜ ማዕቀፉ 413 ግንባታዎችን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉ በዛሬው ዕለት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን ከሰራተኛ ጋር በገመገመበት መድረክ ተገልጿል፡፡

ከዚህ አሀዝ ውስጥም 253 በማዕከል እንዲሁም 160 ፕሮጀክቶች በክፍለከተማ ደረጃ የተከናወኑ እንደሆነ በሪፖርቱ ተያይዞ ተጠቅሷል።

የቢሮው ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም በመድረኩ ባደረጉት ንግግር በተጠቀሰው የጊዜ ማዕቀፍ ቢሮው ከመደበኛ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም በተጨማሪ በኮሪደር ልማት እና በወንዝና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች ላይ ያከናወናቸው ተግባራት ትልቅ ውጤት የተመዘገቡባቸው መሆናቸውን አንስተው ለዚህ ውጤት መመዝገብ ፕሮጀክቶቹ የተመሩባቸው መርሆዎችና ዲሲፕሊን ፤ ወጥነት ያለው ድጋፍና ክትትል እንዲሁም በቢሮው መሬት የያዘው የ7/24 የስራ ባህል ትልቅ ድርሻ እንደነበራቸው ጠቅሰዋል።

ኃላፊዋ አክለውም በ9 ወሩ ቢሮው አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሄደውን ርቀት በተለይ በዲጂታላይዜሽን ትግበራ ላይ የታየውን እምርታ ለአብነት የጠቀሱ ሲሆን በቀሪ ወራትም ቢሮው የተለማቸውን ግቦች ዕውን ለማድረግና የከተማውን ሕብረተሰብ ጥያቄ ለመመለስ ዓቅም የሚፈጥሩ ያሏቸውን የስራ መመሪያና አቅጣጫዎች አውርደዋል።

በዚሁ መድረክ በ9 ወሩ ከዓቅም ግንባታ አንፃር የ1,685 ስራ ተቋራጮች ፣ አማካሪዎችና የመዋቅሩ ባለሞያዎችን ዓቅም ለመገንባት ታቅዶ በ28 ርዕሶች ላይ ለ2,274 ተዋንያን ተደራሽ የተደረጉ ስልጠናዎች እንደተሰጡ ተጠቁሟል።

የግንባታ ጥራትን ከማረጋገጥ አንፃር 5,258 የግንባታ ናሙናዎችን በመፈተሽ ጥራታቸወረን ለማረጋገጥ ዓቅዶ የነበረው ቢሮው 6,604 ናሙናዎች ላይ በራሱ ቤተ-ሙከራ ፍተሻ ማከናወን መቻሉ በመድረኩ ተመላክቷል።

ከስራ ዕድል ፈጠራ አንፃር በዘርፉ ለ41,250 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ-ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ  ለ38,094 ዜጎች የስራ-ዕድል መፍጠር እንደተቻለና በዚህም 5,520,056,811.60 ብር የገበያ ትስስር ዕውን እንደተደረገ በመድረኩ ተገልጿል።

ከዲዛይን ዝግጅት አንፃር በ9 ወሩ በማዕከልና በክፍለከተማ ደረጃ 292 ዲዛይኖች ለማዘጋጀት ታቅዶ 352 ዲዛይኖችን ማዘጋጀት እንደተቻለ የተመላከተ ሲሆን 172 የፕሮጀክቶች አዋጪነት ጥናት ለማድረግ ተወጥኖ 214 ማሳካት እንደተቻለ ተወስቷል።

ከምሕንድስና ግዢ አንፃርም የ495 ስራ ተቋራጮችና አማካሪዎች ግዢ ለመፈፀም ታቅዶ እንደነበርና 693 ግዢ መፈፀሙን በመድረኩ የቀረበው ሪፖርት ያሳያል።

የ አዲስ አበባ የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ

@etconp
❤10👍7
👉የ ዛሬ የ Quiz ብፌ እንዴት ነበር?

ሁሌ እሁድ ሙሉ ቀን የ Quiz Day እንዲሆን ከፈለጉ በ ❤ Reaction ኣሳውቁን🙏

@etconp
❤112👍28🔥1
👉 INTERCON Construction Chemicals 

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Wall Putty, Prime Coat
● Concrete Repair Mortar
● Floor hardener, Epoxy
● Grout, Self-level mortar
● Quartz paint, Contextra
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Geotextiles and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555
Address: Signal, around signal mall
👍3❤1
👉በጋራ የኮንስትራክሽን ሥራ ንግድ ፍቃድ ስታወጡ ስለስያሜው {ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (PLC) እና የአክሲዮን ማህበር (SC) ተመሳሳይነትና ልዩነት}

🚧በኮንስትራክሽን ሥራ ውስጥ አክሲዮን ማኅበር፣ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ሽርክና የሚባሉ ከአንድ በላይ የሆኑ አባላት በጋራ ሆነ ንግድ ፍቃድ የሚያወጡባቸው ዘርፎች አሉ እነዚህ ስያሜዎች በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ዉስጥ ካሉት የንግድ ማህበራት መካከል የሚጠቀሱ ሲሆን በዚህ ክፍል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር—ኃ.የተ.የግ.ማ (Private Limitted Company - PLC) እና የአክሲዮን ማህበር - አ.ማ (Social Company - SC) ያላቸውን አንድነትና ልዩነት እንመለከታለን።

💫ሁለቱም ማህበራት አክሲዮን ያላቸዉ ወይም ካምፓኒዎች ሲሆኑ ተመሳሳይነትና ልዩነት አላቸዉ።

📜ተመሳሳይነታቸዉ:-

• ህጋዊ ሰዉነት ያላቸዉ መሆኑ ፣
• የራሳቸዉ ንብረት ያላቸዉ መሆኑ፣
• የራሳቸዉን ትርፍና ኪሳራ ተጠያቂነት ያለባቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም ትንሹ የአባላት ብዛትና የመነሻ ካፒታል ያላቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም በቦርድና በማናጀር መመራት የሚችሉ መሆኑ ነገር ግን ለ PLC አሰገዳጅ አለመሆኑ፣
• የሁለቱም ተጠያቂ በተዋጣዉ የገንዘብ መጠን (አክሲዮን ) መሆኑ ፣
• ሁለቱም የሙያ መዋጮን የማይቀበሉ መሆኑ
• በሁለቱም ካፒታል ማሳደግና መቀነስ የሚቻል መሆኑ ፣
• በሁለቱም አክሲዮኖች በመያዣ /በዋስትና / መያዝ ሚችሉ መሆኑ ፣

📜ልዩነታቸዉ:-

⏺አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር / PLC/ private Limited Company/ ለማቋቋም የአባላት ብዛት ከሁለት ማነስ የማይችሉ መሆኑ እንዲሁም ከሀምሳ መብለጥ እንደማይችሉ በንግድ ህጉ ተገልጿል።
⏺የአክሲዮን ማህበርን (share company) በተመለከተ ለማቋቋም ከ5 አባላት ማነስ የማይችል ሲሆን ብዛት ግን ገደብ የሌለዉ መሆኑን በንግድ ህጉ ላይ ይገኛል።

🔰ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መነሻ ካፒታል 15000 ሺህ ብርና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋም በኢትዮጵያ ብር አንድ በመቶ ማነስ አይችልም።

🔰አክሲዮን ማህበር መነሻ ካፒታል 50000 ሺህ እና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋ ከአንድ መቶ ብር በታች መሆን አይችልም

🔰ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ካፒታሉ ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የተከፈለ ሲሆን የአክሲዮን ማህበር ግን ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የሚከፈል አይደለም ነገር ግን ከተፈረሙ አክሲዮኖች ቢያንስ 1/4 (25%) መከፈል አለበት የቀረዉ በሂደት የሚከፈል ይሆናል።

🔰ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የአክሲዮኖች ሽያጭ ለህዝብ ክፍት የሚደርግ አይደለም  ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ለህዝብ ክፍት የሚደረግ ነዉ

🔰ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC) ላይ አክሲዮን ማህበር ዉስጥ ያለ ሰዉ አክሲዮኑን ለሶስተኛ ሰዉ ማስተላለፍ አይችልም ምክንያቱም መተዳደሪያ ደንቡ ላይ አባላት ይህን እስካልፈቀዱ ድረስ በህጉ መሰረት sale freely transfrable አይደለም።

⏺ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ላይ አክሲዮን ማስተላለፍን በተመለከተ አክሲዮን የገዛ ሰዉ አክሲየኑን ለሌላ አባል ላልሆነ ሰዉ በቀላሉ ማስተላለፍ ይችላል። ⏺ስለዚህ አክሲዮን ማስተላለፍ ከተፈለገ በቀላሉ የአክሲዮን ማህበርን መምረጥ ያስፈልጋል ማለት ነዉ።

🔰አስተዳደራዊ አካል (ቦርድ) ን በተመለከተ አክሲዮን ማህበራት ሁሉ ከ 3-12 ሰዉ የሚይዝ ቦርድ ኦፍ ዳይሬክተር ሲቋቋም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (plc) ዉስጥ የቦርድ መዋቅር ግዴታ አይደለም።

@etconp
👍18❤2
👉READYMIX CONCRETE (የተዘጋጀ ቅይጥ አርማታ ጥራትን እንዴት ማረጋገጥ እንደሚቻል)

💫ቅይጥ አርማታ (ሬዲሚክስ ኮንክሪት) በኢትዮጵያ ውስጥ ለግንባታ ፕሮጀክቶች ተወዳጅና ተመራጭ ሆኗል፤ ምቹ እና አስተማማኝ ነው፤ ቅይጥ አርማታ በተፈለገው ጊዜ የተፈለገው የሥራ ቦታ ላይ ሊደርስ ይችላል።

⏺ይሁን እንጂ የኮንክሪቱ ጥራት ሁሌም ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።

⏺ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከጥራት ጋር በተያያዘ በቅይጥ አርማታ ምርት ላይ ቅሬታዎች ሲቀርቡ ይስተዋላል።

⏺በኢትዮጵያ ውስጥ የቅይጥ አርማታ ጥራትን ለማረጋገጥ የሚከተሉትን አማራጮች መፈተሽ ተገቢ ነው፤

🚧ታዋቂ የሆነ አቅራቢ ይምረጡ

⏺የቅይጥ አርማታ ምርት ከፈለጉ በቅድሚያ በምርቱ አቅራቢዎች ዙሪያ ጥልቅ ምርምራ ያድርጉ፤ ጥራት ያለው እና መልካም ስም የገነባን የቅይጥ አርማታ አቅራቢን ይምረጡ። ከሥራ አጋሮቹ፣ ቤተሰብ ወይም የሥራ ባልደረቦች ምክሮችን ይጠይቁ። እንዲሁም በግንባታ ኢንደስትሪ ውስጥ ያሉ ግምገማዎችን ለማረጋገጥ ይጣሩ።

🚧ስለ አቅራቢው የጥራት ቁጥጥር ሂደቶች ይጠይቁ

⏺ኮንክሪት ከፍተኛ ጥራት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ አቅራቢው ሥርዓት ያለው የጥራት ሂደት አሠራር የሚከተል መሆኑን ያረጋግጡ። በሲሚንቶ፣ በጠጠር፣ በኬሚካል እና በውሃ ስለሚያደርጉት የምጣኔ አሠራር ሂደቶችን፣ የኮንክሪትን ጥራት ለመጠበቅ ምን አይነት የአሠራር ስልት እና ቴክኖሎጂን እንደሚጠቀሙ እና የተገኙ ችግሮችን እንዴት እንደሚፈቱ ይጠይቁ።

🚧የኮንክሪት ናሙና ጠይቅ

⏺ይህ ኮንክሪቱን ለመፈተሽ እና የእርስዎን መስፈርቶች የሚያሟላ መሆኑን ለማረጋገጥ እድል ይሰጥዎታል። በቀለም እና በወጥነት አንድ ወጥ የሆነ ኮንክሪት ይፈልጉ። ኮንክሪቱ  ከማንኛውም ጉድለቶች የጸዳ መሆኑን አረጋግጡ።

🚧የቀረበልዎትን ኮንክሪት ይፈትሹ

⏺ኮንክሪት ትክክለኛው ቀለም፣ ወጥነት እና ጥንካሬ ያለው መሆኑን ያረጋግጡ። ኮንክሪት በትክክለኛ የሙቀት መጠን ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት። በጣም ቀዝቃዛ ወይም በጣም ሞቃት የሆነ ኮንክሪት ጠንካራ አይሆንም። ስለ ኮንክሪት ጥራት የሚያሳስብዎት ነገር ካለ፣ አቅራቢውን ለማነጋገር አያመንቱ። ጥሩ ስም ያለው አቅራቢ ማንኛውንም ችግር ለመፍታት ደስተኛ ነው።

@etconp
👍6❤5🔥1
👉የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መንደር ፕሮጀክት

💫በአዲስ አበባ ግንባር ቀደም የሆነ የትምህርት፣ የምርምር፣ የፈጠራ እና የባህል የዩኒቨርሲቲ መንደር ልማት ትግበራ በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ፕላን እና ልማት ቢሮ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ትግበራው የአካባቢ ልማትና የከተማ ዲዛይን ተዘጋጅቶ ደረጃ በደረጃ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል አቅፎ የሚለማ መሆኑን የገለጹት የፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ ናቸው፡፡

ቢሮዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለዉ አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር እንዲሆን ያፀደቀዉን የውሳኔ ሀሳብ መነሻ በማድረግ በአተገባበሩ ዙሪያ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ በጋዜጣዊ መግለጫቸዉ እንደገለፁት የ ዩኒቨርሲቲ መንደሩ የ10 ዓመት ዕቅድ የያዘ ዝርዝር የአካባቢ ልማትና የከተማ ዲዛይን ተዘጋጅቶለት ደረጃ በደረጃ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል አቅፎ የሚለማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አቶ አደም አያይዘውም የ4 ኪሎ፣ 5 ኪሎና 6 ኪሎ አካባቢ የዩኒቨርሲቲ እና ሌሎች የትምህርት አገልግሎት መስጫ ተቋማት የሚገኙበት ቢሆንም በአብዛኛው የታጠሩና ለማህበረሰቡ ክፍት ሆነው የሚጠበቀውን የጋራ ጥቅም ማስገኘት ያልቻሉ ናቸው፡፡

በመሆኑም በከተማዋ መዋቅራዊ ፕላን የመሬት አጠቃቀም ምድብ አንጻር የቦታ አጠቃቀም ክፍተቶች መኖራቸዉ እንደምክንያት ጭምር በመውሰድ የዩኒቨርሲቲ መንደሩም 500 ሄክታር የሸፈነ ጥናት መደረጉን ገልፀዉ ፤ የዩኒቨርስቲ መንደር ኮሪደሮችን ከማስተሳሰር በተጨማሪ በአፍሪካየዲፕሎማሲያዊ ዋና ከተማ በሆነችው አዲስ አበባ በ2027 ዓ.ም ግንባር ቀደም የሆነ የትምህርት፣ የምርምር፣ የፈጠራ እና የባህል መንደር ለማልማት እንዲያስችል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ማፅደቁን ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል በዩኒቨርሲቲ መንደሩ መገንባት ዘላቂና ህይወት ያለው ደህንነቱ የተረጋገጠ የከተማ ማዕከል እንዲኖር፤የተሻለ ማህበራዊ ግንኙነት ለመፍጠር፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ለሆኑ ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ማዕከልነት ብቁ ሆኖ እንዲገኝ፣ተወዳዳሪ የፈጠራ ማዕከል ለማበርከት እና በምርምር፣በቴክኖሎጂ እንዲሁም በንግድ ኢንኩቤሽን አማካኝነት ተጨማሪ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታሳቢ ያደረገ መሆኑን በማብራሪያቸዉ ገልፀዋል፡፡

በተያያዘም በመግለጫው በተባባሪነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተሳተፉት ኢሳያስ ገብረዮሐንስ (ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲዎችና የትምህርት ተቋማት አጥራቸውን ከፍተው ለነዋሪዎች አገልግሎት የሚሰጡበት፣ የአፍሪካ ሃገራት የፈጠራ ስራዎች የሚከናወኑበት፣ ቤተዕምነቶች የሚጠበቁበት፣ ጭስ አልባ ኢንዱስትሪዎች የሚለሙበት ጥናት መሆኑን በመግለጫው ተናግረዋል፡፡

ቢሮዉ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የምርምር ማዕከላት ወደዚህ መንደር እንዲገቡ ማድረግ፤ ከእንጦጦ እስከ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ድረስ ቀጣይነት ያለው የከተማ ልማትና አረንጓዴ መሰረተ ልማት መፍጠር ከዩኒቨርሲቲ መንደሩ የሚጠበቁ ተጨማሪ ውጤቶች መሆናቸውን ተናግረዋል፡:

በኮሪደርና በሌሎች የልማት መስኮች ያሳየነውን የይቻላል አቅም ጥናቱን ወደ ተግባር በመለወጥ ረገድ ላይም ሁላችንም ተቀናጅተን በመስራት የራዕዩን ፍሬ ለትውልድ ለማኖር ህብረተሰቡ የበኩሉን በጎ አስተዋፅዖ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አስተላልፏል፡፡

Via Addis Ababa City Plan & Development Bureau

@etconp
👍11❤5